የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን🙏
الذهاب إلى القناة على Telegram
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና የጠበቁ የነፍስ ስንቅ የምናገኝበት፦ ✍️"ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም" ፩ኛ ቆሮ. ፰፥፪ #ለተጨማሪ፦👇✞👇 https://www.youtube.com/EOTC2921 https://www.facebook.com/eotc2921 https://www.tiktok.com/@eotc2921 https://www.instagram.com/eotc2921
إظهار المزيد4 374
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
4 374
•••✞ #በህይወቴ_በዘመኔ ✞•••
ሕይወቴ ሲመራ ጌታ በቃልህ
ብርታት አገኛለሁ ሲያድሰኝ ፍቅርህ
ያንተ ጸጋ ጌታ ስለበዛልኝ
ጨለማው ተገፎ ብርሃንህ መራኝ
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
በሕይወቴ በዘመኔ ደስ የሚለኝ ለእኔ በወንጌል ማመኔ
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ወዴት እሄዳለሁ የእጅህ ጥበብ ሆኜ
ፍቅርህ እያደሰኝ ሞተህልኝ ድኜ
ምን አይነት መውደድ ነው አንተ ለኔ ያለህ
ምን ይከፈልሀል ለፍፁሙ ፍቅርህ
#አዝ•••••••
ምን አይነት መውደድ ነው አንተ ለኔ ያለህ
ምን ይከፈልሀል ለፍፁሙ ፍቅርህ
ደጅህ ላይ ተጥዬ ደጅህ ላይ ልሙት
ቃልህን ልጠብቅ በፍፁም ፍርሃት
#አዝ•••••••
☞ @EOTC2921 Channel
☞ @Ethio_Orthodox1 Group
4 374
✞በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሃዱ አምላክ አሜን✞
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ምስጢረ_ስላሴ_በጥቂቱ
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
እኛ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች የእግዚአብሔር አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው፤ ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በአንድነትና በሦስትነት የሚመሰገን አንድ ሕያው አምላክ በሆነው በእግዚአብሔር እናምናለን፡፡ #አንድ_ሲሆን_ሦስት_ሦስት_ሲሆን_አንድ_በአካል_ሦስት_ሲሆን_በመለኮት_በአንድ_አምላክ_በሆነው_በልዑል_እግዚአብሔር ብቻ ነው የምናምን፡፡ ይህ ምስጢር ስጋን በለበሰ ህሊናችን ተመራምሮ ማወቅ አይቻልም በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ካልሆነ በስተቀር፡፡ ለዛም ነው ቤተ ክርስቲያናችን አምስቱ አዕማደ ምስጢራትን ስታስተምር በመጀመሪያ ምስጢረ ስላሴን መማር እንዳለብን ያስቀመጠችልን፡፡ ምስጢር ማለት፦ እጅግ ጥልቅ፣ የተሰወረ፣ የረቀቀ፤ ከመሆኑ የተነሳ #ምስጢር ይባላል፡፡ #ስላሴ ማለት ደግሞ "ሰለሠ" ወይም ሦስት አደረገ ማለት ሲሆን ትርጉሙም፦ ሦስትነት ማለት ነው፡፡
✞✞✞
#የስላሴ_አንድነትና_ሦስትነት፦
✞✞✞
☞✞ #የስላሴ_አንድነት ፦ በአገዛዝ፣ በስልጣን፣ ይህን አለም በመፍጠርና በማሳለፍ፣ በህልውና፣ በመለኮት፣ በልብ፣ በቃል፣ በእስትንፋስ፤ በእነዚህ ሁሉ የመለኮት ባህርይ #አንድ ነው፡፡
#የእግዚአብሔር_ሦስትነት_ስንል፦እግዚአብሔር የማይለያይና የማይቀላቀል ፍጹም የሆነ ሦስትነት አለው ማለታችን ነው። የእግዚአብሔር ሦስትነትም፦ በስም፣ በግብር፣ በአካል ነው።
☞✞ እግዚአብሔር #በስም ሦስት ነው ስንል ሦስት የተለያዩ ስሞች አሉት ማለታችን ነው። እነዚህም፦ #አብ #ወልድ #መንፈስ_ቅዱስ የሚባሉት ሲሆኑ እርስ በርሳቸው አይወራረሱም፤ አንዱ በሌላው ስም አይጠራም። "ዘፍ፡1፥2 ፣ ምሳ፡30፥4" ።
☞✞ እግዚአብሔር #በግብር ሦስት ነው ስንል፤ ሦስት የተለያዩ የአካል ሥራዎች አሉት ማለት ነው። እነሱም፦
መውለድና ማስረጽ =የአብ፤
መወለድ=የወልድ፤ መስረጽ =የመንፈስ ቅዱስ፤ የሚሉት ሲሆኑ የአካል ግብር ይባላሉ። "መዝ፡2፥7"
☞✞ እግዚአብሔር በአካል ሦስት ነው ማለት ደግሞ
#ለአብ፦ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው።
#ለወልድ ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ።
#ለመንፈስ_ቅዱስ ፤ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ማለታችን ነው።
☞✞ የሦስቱ የእግዚአብሔር ስሞች ትርጉም፦
#አብ፦ ማለት አባት ማለት ሲሆን የሚወልድ፤የሚያሰርጽ ወይም የሚያስገኝ ያለ እናት ወልድን የወለደ፤ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸ ነው።
#ወልድ፦ ልጅ ማለት ሲሆን የሚወለድ ወይም ያለ እናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድህረ ዓለም የተወለደ ነው። "መዝ፡2፥7" #መንፈስ_ቅዱስ፦ ረቂቅ፣ ልዩ፣ ንፁህ ከፍጡራን መናፍስት ሁሉ የተለየ ማለት ነው። "እዮ፡26፥13"
✞በመጽሐፍ_ቅዱስም ከበቂ በላይ ሁኖ ተገልፆልናል፡፡
ዘፍ፡1፥26 ፣ ዘፍ፡11፥7 ፣ ኢሳ፡6፥1-3 ፣ ኢሳ፡48፥16 ፣ ማቴ፡3፥16 ፣ ማቴ፡28፥19 ሉቃ፡1፥35 ፣ ዮሐ፡14፥25 ፣ ማቴ፡21፥18 ፣ 1ኛ ቆሮ፡12፥3 ፣ 2ኛ ቆሮ፡13፥14 ፣ ዘፍ፡3፥22 ፣ ማር፡10፥6 ፣ ማር፡10፥18 ፣ ዘፍ፡1፥3 ፣ ዘፅ፡5፥1 ፣ ዘፅ፡7፥17 ፣ ኢያ፡3፥17 ፣ ሐዋ፡1፥23 ወዘተ.... ከዚህም በላይ ስለአንድነትና ሦስትነታቸው እናገኛለን፡፡ የእግዚአብሔር አብ በረከት፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት፣ የእመቤታችን የድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✞
4 374
የአብይ ፆም 7ኛ ሳምንት "ኒቆዲሞስ"
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
☞✞ ኒቆዲሞስ ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የነበረው ሰው ነው፡፡ የአይሁድ አለቆች አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ‹‹ምልክት አሳየን›› እያሉ ይፈታተኑት ነበር፡፡ ጌታችን ስለ ሞቱና ትንሣኤው በምሳሌ እያስረዳ ቢያስተምራቸውም እነርሱ ግን አልገባቸውም ነበር፡፡ ከዚህም አልፎ ጌታችን በተአምራቱ የታመሙትን ሲፈውስ ‹‹ሕጋችን ተሻረ›› ይሉ ነበር፡፡ በዚህ ዅሉ ተአምራትና ትምህርት የአይሁድ አለቆች ክርስቶስን ለመክሰስ በሚፈልጉበት ወቅት ከአይሁድ አለቆች አንዱ ኒቆዲሞስ በቀን እንዳያደርገው አይሁድን ቢፈራ፣ አንድም ጊዜ ባያደርሰው እንደ ባልንጀሮቹ ክርስቶስን ሳይቃወም በሌሊት ወደ ጌታችን ዘንድ እየሔደ ወንጌልን ይማር ነበር፡፡
#የዮሐንስ_ወንጌል_ምዕራፍ፡3፤
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
1፤ከፈሪሳውያንም፡ወገን፡የአይሁድ፡አለቃ፡የኾነ፡ኒቆዲሞስ፡የሚባል፡አንድ፡ሰው ነበረ፤ርሱም፡በሌሊት፡ወደ፡ኢየሱስ፡መጥቶ፦
2፤መምህር፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡ከርሱ፡ጋራ፡ከኾነ፡በቀር፡አንተ፡የምታደርጋቸውን፡እነዚህን፡ምልክቶች፡ሊያደርግ፡የሚችል፡የለምና፡መምህር፡ኾነኽ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡እንደ፡መጣኽ፡እናውቃለን፡አለው።
3፤ኢየሱስም፡መልሶ፦እውነት፡እውነት፡እልኻለኹ፥ሰው፡ዳግመኛ፡ካልተወለደ፡በቀር፡የእግዚአብሔርን፡መንግሥት፡ሊያይ፡አይችልም፡አለው።
4፤ኒቆዲሞስም፦ሰው፡ከሸመገለ፡በዃላ፡እንዴት፡ሊወለድ፡ይችላል፧ኹለተኛ፡ወደ፡እናቱ፡ማሕፀን፡ገብቶ፡ይወለድ፡ዘንድ፡ይችላልን፧አለው።
5፤ኢየሱስም፡መለሰ፥እንዲህ ሲል፦ እውነት፡እውነት፡እልኻለኹ፥ሰው፡ከውሃና፡ከመንፈስ፡ካልተወለደ፡በቀር፡ወደ እግዚአብሔር፡መንግሥት፡ሊገባ፡አይችልም።
6፤ከሥጋ፡የተወለደ፡ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም፡የተወለደ፡መንፈስ፡ነው።
7፤ዳግመኛ፡ልትወለዱ፡ያስፈልጋችዃል፡ስላልኹኽ፡አታድንቅ።
8፤ነፋስ፡ወደሚወደ፟ው ይነፍሳል፥ ድምፁንም፡ትሰማለኽ፥ነገር፡ግን፥ከወዴት፡እንደ፡መጣ፡ወዴትም፡እንዲኼድ፡አታውቅም፤ከመንፈስ፡የተወለደ፡ዅሉ፡እንዲሁ፡ነው።
9፤ኒቆዲሞስ፡መልሶ፦ይህ፡እንዴት፡ሊኾን፡ይችላል፧አለው።
10፤ኢየሱስም፡መልሶ፡እንዲህ፡አለው፦ አንተ፡የእስራኤል፡መምህር፡ስትኾን፡ይህን፡አታውቅምን፧
11፤እውነት፡እውነት እልኻለኹ፥ የምናውቀውን፡እንናገራለን፡ያየነውንም፡እንመሰክራለን፥ምስክራችንንም አትቀበሉትም።
12፤ስለ፡ምድራዊ፡ነገር፡በነገርዃችኹ፡ጊዜ፡ካላመናችኹ፥ስለ፡ሰማያዊ፡ነገር፡ብነግራችኹ፡እንዴት፡ታምናላችኹ፧
13፤ከሰማይም፡ከወረደ፡በቀር፡ወደ፡ሰማይ፡የወጣ፡ማንም፡የለም፥ርሱም፡በሰማይ፡የሚኖረው፡የሰው፡ልጅ፡ነው።
14-15፤ሙሴም፡በምድረ፡በዳ፡እባብን፡እንደ፡ሰቀለ፡እንዲሁ፡በርሱ፡የሚያምን፡ዅሉ፡የዘለዓለም፡ሕይወት፡እንዲኖረው፡እንጂ፡እንዳይጠፋ፡የሰው፡ልጅ፡ይሰቀል፡ይገ፟ባ፟ዋል።
16፤በርሱ፡የሚያምን፡ዅሉ፡የዘለዓለም፡ሕይወት፡እንዲኖረው፡እንጂ፡እንዳይጠፋ፡እግዚአብሔር፡አንድያ፡ልጁን፡እስኪሰጥ፡ድረስ፡ዓለሙን፡እንዲሁ፡ወዷ፟ልና።
17፤ዓለም፡በልጁ፡እንዲድን፡ነው፡እንጂ፥በዓለም፡እንዲፈርድ፡እግዚአብሔር፡ወደ፡ዓለም፡አልላከውምና።
18፤በርሱ፡በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን፡ግን፡በአንዱ፡በእግዚአብሔር፡ልጅ፡ስም፡ስላላመነ፡አኹን፡ተፈርዶበታል።
19፤ብርሃንም፡ወደ፡ዓለም፡ስለ፡መጣ፡ሰዎችም፡ሥራቸው፡ክፉ፡ነበርና፥ከብርሃን፡ይልቅ፡ጨለማን፡ስለ፡ወደዱ፡ፍርዱ፡ይህ፡ነው።
20፤ክፉ፡የሚያደርግ፡ዅሉ፡ብርሃንን፡ይጠላልና፥ሥራውም፡እንዳይገለጥ፡ወደ፡ብርሃን፡አይመጣም፤
21፤እውነትን፡የሚያደርግ፡ግን፡ሥራው፡በእግዚአብሔር፡ተደርጎ፡እንደ፡ኾነ፡ይገለጥ፡ዘንድ፡ወደ፡ብርሃን፡ይመጣል።
22፤ከዚህ፡በዃላ፡ኢየሱስ፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ጋራ፡ወደይሁዳ፡አገር፡መጣ፥በዚያም፡ከነርሱ፡ጋራ፡
ተቀምጦ፡ያጠምቅ፡ነበር።
23፤ዮሐንስም፡ደግሞ፡በሳሌም፡አቅራቢያ፡በሄኖን፡በዚያ፡ብዙ፡ውሃ፡ነበርና፥ያጠምቅ፡ነበር፥
24፤እየመጡም፡ይጠመቁ፡ነበር፡ዮሐንስ፡ገና፡ወደ፡ወህኒ፡አልተጨመረም፡ነበርና።
25፤ስለዚህም፡በዮሐንስ፡ደቀ መዛሙርትና ፡በአይሁድ፡መካከል፡ስለ፡ማንጻት፡ክርክር፡ኾነ።
26፤ወደ፡ዮሐንስም፡መጥተው፦መምህር፡ሆይ፥በዮርዳኖስ፡ማዶ፡ከአንተ፡ጋራ፡የነበረው፡አንተም የመሰከርኽለት፥ እንሆ፥ ርሱ፡ያጠምቃል፡ዅሉም፡ወደ፡ርሱ፡ይመጣሉ፡አሉት።
27፤ዮሐንስ፡መለሰ፥እንዲህ፡ሲል፦ ከሰማይ፡ካልተሰጠው፡ሰው፡አንዳች፡ሊቀበል፡አይችልም።
28፤እናንተ፦እኔ፡ክርስቶስ፡አይደለኹም፥ ነገር፡ግን፦ከርሱ፡በፊት፡ተልኬያለኹ፡እንዳልኹ፡ራሳችኹ፡ትመሰክሩልኛላችኹ።
29፤ሙሽራዪቱ፡ያለችው፡ርሱ፡ሙሽራ፡ነው፤ቆሞ፡የሚሰማው፡ሚዜው፡ግን፡በሙሽራው፡ድምፅ፡እጅግ፡ደስ፡ይለዋል።እንግዲህ፡ይህ፡ደስታዬ፡ተፈጸመ።
30፤ርሱ፡ሊልቅ፡እኔ፡ግን፡ላንስ፡ያስፈልጋል።
31፤ከላይ፡የሚመጣው፡ከዅሉ፡በላይ፡ነው፤ከምድር፡የሚኾነው፡የምድር፡ነው፥የምድሩንም፡ይናገራል።ከሰማይ፡የሚመጣው፡ከዅሉ፡በላይ፡ነው።
32፤ያየውንና፡የሰማውንም፡ይህን፡ይመሰክራል፥ምስክሩንም፡የሚቀበለው፡የለም።
33፤ምስክሩን፡የተቀበለ፡እግዚአብሔር፡እውነተኛ፡እንደ፡ኾነ፡አተመ።
34፤እግዚአብሔር፡የላከው፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ይናገራልና፤ እግዚአብሔር፡መንፈሱን፡ሰፍሮ፡አይሰጥምና።
35፤አባት፡ልጁን፡ይወዳል፡ዅሉንም፡በእጁ፡ሰጥቶታል።
36፤በልጁ፡የሚያምን፡የዘለዓለም፡ሕይወት፡አለው፤በልጁ፡የማያምን፡ግን፡የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡በርሱ፡
ላይ፡ይኖራል፡እንጂ፡ሕይወትን፡አያይም።
በዕለቱም፦
#መዝሙር
ሖረ ኅቤሁ ዘስሙ ኒቆዲሞስ ወይቤሉ ለኢየሱስ ረቢ ሊቅንሕነ ነአምነ ብከ•••
#ምንባባት
ሮሜ 7:1-14
1ኛ.ዮሐ፡4፥18-ፍፃሜው
ሐዋ፡5፥34-ፍፃሜው
#ምስባክ
መዝ.16÷ 3 "ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፡፡ አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመፃ በላዕሌየ፡፡ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመ ሕያው፡፡"
#ትርጉም፦ በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ልቤንም ፈተንኸው÷ ፈተንኸኝ÷ ዐመፅም አልተገኘብኝም፡፡ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር÷ ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ፡፡
#ወንጌል
ዮሐ. 3÷1-12
#ቅዳሴ
ቅዳሴ ዘእግዝትነ•••
በሌሊት ከአምላኩ ተምሮ ምሥጢሩ የተገለጸለት ኒቆዲሞስ ቀድሞ በአደባባይ ሔዶ መማርን ይፈራ እንዳልነበረ ምሥጢሩ ሲገለጽለት ግን አይሁድ ጌታችንን በሰቀሉት ዕለት ፍርኃት ርቆለት ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር ቅዱስ ሥጋውን ገንዞ ለመቅበር በቃ፡፡ ‹‹ወአልቦ ፍርኃት ውስተ ተፋቅሮትነ፤ ፍጹም ፍቅር ፍርኃትን አውጥቶ ይጥላል›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (ማቴ. ፳፯፥፶፰፤ ፩ኛዮሐ. ፬፥፲፰)፡፡ ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ያመነ፣ የተጠመቀ ይድናል፡፡ ያላመነ፣ ያልተጠመቀ ግን ይፈረድበታል›› (ማር. ፲፮፥፮) በማለት በሰጠን ቃል ኪዳን መሠረት በአምላክነቱ አምነን የመንግሥቱ ወራሾች እንኾን ዘንድ ለኒቆዲሞስ ምሥጢሩን እንደ ገለጸ ለእኛም ይግለጽልን፡፡
🙏እንደ ኒቆዲሞስ ራሳችንን ዝቅ አድርገን በምሥጢራት በመሳተፍ ለታላቅ ክብር እንበቃ ዘንድ የአምላካችን የልዑል እግዚአብሔር መልካም ፈቃዱ ይኹንልን፡፡🙏
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
4 374
ሸከመችው በእሳቱ መንበር ላይ የሚቀመጠውን እሳተ መለኰት ነው።
✍ቅዱስ ዳዊት «እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ አለ» በማለት እመቤታችን ለማኅደረ መለኮትነት እንደተመረጠች አስቀድሞ በትንቢት ተናግሮላታል።
📖መዝ 132፥13
✍ከዚህም ሌላ «የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል» በማለት እርሷን ዙፋን አድርጐ እንደሚገለጥም ተናግሯል።
📖መዝ 86፥7
↪️በሰማይ ያለ የእግዚአብሔር ዙፋን በውስጥ በአፍአ እሳት እንደሆነ፤ እመቤታችንም በውስጥ በአፍአ (በነፍስም በሥጋም) እሳት ምሳሌው በሆነ በመንፈስ ቅዱስ የተከበበች የታጠረች ናት።
✍«እንደ እሳት የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎችም ታዩአቸው፤ በሁሉም ላይ ተቀመጡባቸው፤ ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ተሞሉ» ይላል።
📖የሐዋ 2፥3
↪️የአሥራ አምስት ዓመት ብላቴና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ማኅደረ መለኮት ሆና መገኘቷ ቃላት የማይገልጡት ከመነገር በላይ ነው።
↪️ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ድርሰቱ
✍«የአብ ቃል እናቱ ንጽሕት ድንግል ሆይ ስለአንቺ የሚነገረውን ነገር መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው፤ ኪሩቤል ለሚሸከሙት ንጉሥ ዙፋኑ (ማደሪያው) ሆንሽ» ያለው ለዚህ ነው።
↪️አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም ድርሰቱ
✍«ድንግል ሆይ እሳተ መለኮት በሆድሽ ባደረ ጊዜ ፊ ቱ እሳት ልብሱ እሳት ቀሚሱ እሳት ነው እንደምን አላቃጠለሽም፤ ሰባት የእሳት ነበልባል መጋረጃ በሆድሽ ውስጥ ወዴት ተጋረደ ወዴትስ ተዘረጋ ከጐንሽ በቀኝ ነውን ከጐንሽ በግራ ነውን ትንሽ አካል ስትሆኝ፤ የሚያንጸባርቅ ነደ እሳት የሚከበው ኪሩቤል የተሸከሙት ዙፋን በሆድሽ ውስጥ ወዴት ተዘጋጀ ወዴትስ ተተከለ ታናሽ ሙሽራ ስትሆኝ» እያለ ከሰማያዊው ማደሪያ ጋር እያነጻጸረ አድንቋል።
↪️ምክንያቱም እርሷ የእሳቱንም ዙፋን የእሳቱንም መጋረጃዎች ሆና ተገኝታለችና።
✞👑✞👑✞👑✞👑✞👑✞👑✞👑✞
•••✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞•••
✞👑✞👑✞👑✞👑✞👑✞👑✞👑✞
4 374
አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ:
✝👑✝ 👑✝ 👑✝ 👑 ✝ 👑 ✝ 👑
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
✞✞✞ #ነገረ_ማርያም ✞✞✞
#ጽርሐ_አርያም
↪️ጽርሐ አርያም የእግዚአብሔር ማደሪያ ናት።
↪️ትርጉሙም በሰማይ ያለ አዳራሽ፣ ታላቅ ቤት ማለት ነው።
↪️ጌታ በተወለደ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት «ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ሰላምም በምድር ለሰው ልጅም በጎ ፈቃድ ሆነ» እያሉ ዘምረዋል።
📖ሉቃ 2፥14
↪️ይህም በሰማይ ባለ ማደሪያህ የምትመሰገን መለኮት ነህ ሲሉት ነው።
↪️ጌታችንም በምትጸልዩበት ጊዜ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ በሉ» ብሎናል።
📖ማቴ 6፥8
✍በኦሪት ደግሞ «ከቅዱስ ማደሪያህ ከሰማይ ጐብኝ ሕዝብህንም እስራኤልን ለአባቶቻችን እንደማልህላቸው የሰጠኸንንም ወተትና ማር የምታፈሰውን አገር ባርክ» የሚል ተጽፏል።
📖ዘዳ 26፥15
↪️ከዚህም ለላ በመጽሐፈ ነህምያ ላይ «የሰማዮች ሰማይ» የተባለችው ጽርሐ አርያም ናት። 📖ነህ 9፥6
↪️ንጉሡ ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱን ሠርቶ ከጨረሰ ታቦቱንም ካስገባ በኋላ ወደ እግዚአብሔር የጸለየው።
✍«በማደሪያህ በሰማይ ስማ ሰምተህም ይቅር በል» እያለ ነው።
✍እግዚአብሔርም «በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ» ብሎታል።
📖2ኛ ዜና 6፥12-42፣
📖2ኛ ዜና 6፥11-18
↪️ጽርሐ አርያም ከሰባቱ ሰማያት አንዷ ናት።
✍ቅዱስ ዳዊት «ወበቃለ እግዚአብሔር ጸንአ ሰማያት በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ» እንዳለ ባለማለፍ ጸንተው ለዘለዓለም የሚኖሩ ሰማያት ሰባት ናቸው።
📖መዝ 32፥6
↪️እነዚህም
👑መንበረ መንግሥት፣
👑ጽርሐ አርያም፣
👑ሰማይ ውዱድ፣
👑ኢየሩሳሌም
👑ሰማያዊት፣
👑ኢዮር፣
👑ራማና
👑ኤረር ናቸው።
↪️በሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ጽርሐ አርያምን በተመለከተ
✍«መንበሩ በእሳት ክሉል ወማኅደሩ በማይ ጥፉር ወዲበ ተድባበ ቤቱ ኅንባበ ማይ ዘኢይትከዐው።
☞✞ ዙፋኑ በእሳት የተከበበ ነው ማደሪያውም በውኃ የተታታ ነው በቤቱም ዙሪያ ላይ የማይፈስ የውኃ መርገፍ አለ» የሚል ተጽፏል።
↪️በማደሪያው ውስጥ ስላለው ነገር ሲያብራራም
✍«ከዙፋኑም ብልጭልጭታ ይወጣል ውስጡ እንደ ጋለ እሳት ነው፤ በውስጡ እንደ ክረምት ቀስተ ደመና ያለ ደገኛ ብርሃን አለ ዙሪያውም መብረቅ ነው።
↪️ከዚያም መንበር አጠገብ አራቱ እንስሳ (ገጸ ሰብእ፣ ገጸ ላህም፣ ገጸ ንስር፣ ገጸ አንበሳ) ኅብሩ እንደ በረድ ነጭ የሆነ ሰፊ መንበር በራሳቸው እንደ ተሸከሙ ሆነው አሉ።
↪️በዚህ መንበር ዙሪያ ሃያ አራት ካህናተ ሰማይ (ሱራፌል) አሉ በፊታቸውም የበጉን ሥዕል ደም የተረጨች ልብስ የታተመ መጽሐፍም ያያሉ።
↪️ይህንንም መንበር በዞሩ ቁጥር ለዚያ ለበጉ ሥዕልና በደም ለታለለች ለዚያች ልብስ ለታተመው መጽሐፍም ሦስት ጊዜ ይሰግዳሉ፤ በአዳራሹም ድንኳን የምሥጋና ጢስ ይመላል ከዚያም መንበር በታች ጐዳናው ሁለት የሆነ የብርሃን እና የነፋስ ባሕር ይፈልቃል፤ የአማልክት አምላክ በዚያ አለ የአጋዕዝትም (የጌቶች) ጌታ በዚያ አለ፤ በውጭ ይኖራል በውስጥም ይገኛል፤ ያገኙት ዘንድ አይሄዱም በፈለጉት ጊዜም አይታጣም በያዙት ጊዜ አይዳሰስም ከሕሊና ልዩ ነውና» የሚል ተጽፏል።
📚በሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ቁጥር 53-58
↪️#ቅዱስ_አትናቴዎስም በቅዳሴው
✍«እንዳንተ ዙፋኑን በእሳት የጋረደ ማነው
❓በልብሱ የውኃ ሥዕል ያደረገ ማነው
❓ተራራዎችንስ እንዳንተ በሚዛን የመዘናቸው የባሕርንስ ውኃ በእፍኙ የሚሰፍር ማነው
❓እንዳንተ አዳራሹን (ማደሪያውን) በውኃ የሚታታ
❓ዙሪያውንስ በእሳት የሠራ ማነው፤ በላይ ያለው የውኃ ጠፈር በጥበብህ ወደ እሳት ግድግዳ አይወርድም፤ በታች ያለው የውኃ ግድግዳም በአኗኗርህ በላይ ወዳለው ወደ ውኃው ጠፈር አይወጣም» ብሏል።
📚ቅዱስ አትናቴዎስም በቅዳሴው ቁጥር 118
↪️#ቅዱስ_ኤጲፋንዮስ
✍«ሁሉ ከእርሱ ነው ሁሉም ስለ እርሱ ነው ሁሉም የርሱ ነው ሰማይ በርሱ ነው ከሰማያት በላይ ያለ ሰማይም የርሱ ነው የአርያም ሰፋት የክብሩ ዙፋን ነው የምድርም ስፋት የእግሩ መመላለሻ ናት፤ ፀሐይ የርሱ ነው ጨረቃም ከርሱ ነው ከዋክብትም የእጁ ሥራ ናቸው፤ ደመናትም መልእክተኞቹ ነፋሳትም ሠረገላዎቹ ናቸው፤ እሳትም የቤቱ ግድግዳ ነው፤ የቤቱ ጠፈር ውኃ ነው የዙሪያውም ጸፍጸፍ የበረድ ሰሌዳ ነው ድንኳኖቹ ብርሃናት ናቸው፤ የመሠወሪያ መጋረጃውም የብርሃን መብረቅ ነው መመላለሻውም በአየር ነው» ብሏል።
📚ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ቁጥር 36-43
❓ጠፈር ማለት
↪️በቁሙ ሰማይ ማለት ነው የቤትም ክዳን ወይም ጣራ ጠፈር ይባላል።
✍ይህንን በተመለከተ «እግዚአብሔርም በውኃው መካከል ጠፈር ይሁን፤ በውኃና በውኃ መካከል ማለትም በሐኖስና በውቅያኖስ መካከል ይለይ አለ፤ እንዲህም ሆነ፤ እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ፤ ከጠፈር በላይና ከጠፈር በታች ያሉትንም ውኆች ለየ፤ እግዚአብሔር ያን ጠፈር ሰማይ ብሎ ጠራው» የሚል ተጽፏል።
📖ዘፍ 1፥1-8
☑️የቤትን ጣራ በተመለከተ ደግሞ
✍«ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ አኮ ዘይደልወኒ ትባእ ታሕተ ጠፈረ ቤትየ ርኲስት፤
☞✞አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ርኲስት ከሆነች ከቤቴ ጣራ በታች ትገባ ዘንድ የሚገባኝ አይደለም» የሚል አለ።
📖ሉቃ 7፥6
↪️መታታት ማለትም መሥራት መጐንጐን፣ ማክረር፣ መግመድ ናመሸረብ ማለት ነው።
✍#ነቢዩ_ሕዝቅኤል_ሰባቱ_ሰማያት_ተከፍተውለት (ምሥጢር ተገልጦለት) የእግዚአብሔርን ራእይ አይቷል፤ በማየቱም መንበሩን ስለሚሸከሙ ኪሩቤል መልካቸውን ጭምር ተናግሯል።
✍«የፊታቸው አምሳያ
✞እንደ ሰው ፊት . . .
✞እንደ አንበሳ ፊት . . .
✞እንደ ላም ፊት . . . .
✞እንደ ንስር ፊት . . . . ነበራቸው» ብሏል፤ እሳታውያንና በፊትም በጀርባም ባለ ከበርሽና ከፍ ከፍ ያልሽ ነሽ የብርሃን መውጫ የሕይወት መሰላል ነሽ፤ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ ከተለዩ የተለየሽ የመለኮት ማደሪያ ነሽ» እያለ ካመሰገናት በኋላ
✍«ከፍጥረት ሁሉ ይልቅ የተከበርሽ ሆይ አብ የወደደሽ ወልድ ያደረብሽ መንፈስ ቅዱስ ያረፈብሽ ተባልሽ፤ በምድር ላይ ከፍተኛ አርያምን የሆንሽ ከሰማያት በላይ ያለ የአርያም የልዑል ሥፍራ ምትክ አንቺ ነሽ» ብሏታል።
↪️በሰማይ ባለ በእግዚአብሔር ማደሪያ ሰባት የእሳት መጋረጃዎች ያሉት የእሳት ዙፋን አለ፤ እግዚአብሔር ወልድ አካላዊ ቃል ከሰማይ ወርዶ የእመቤታችንን ማኅፀን እንደ እሳት ዙፋን አድርጎ ተቀምጦባታል።
↪️ሰባቱን የሥጋና የነፍስ ባሕርያቷንም እንደ #ሰባቱ_የእሳት_መጋረጃ አድርጓቸዋል።
↪️አራቱ የሥጋ ባሕርያት
1⃣መሬት
2⃣እሳት
3⃣ነፋስና
4⃣ውኃ ሲሆኑ
↪️ሦስቱ የነፍስ ባሕርያት ደግሞ
1⃣ለባዊነት (ማሰብ) 2⃣ነባቢነት(መናገር)
3⃣ሕያውነት (ዘለዓለማዊነት) ናቸው።
↪️የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነችው ሰማይ በተቀሩት ስድስት ሰማያት ታጥራ ተከብራ እንደምትኖር እመቤታችንም
1⃣ በንጽሐ ሥጋ፤
2⃣ በንጽሐ ነፍስ
3⃣ በንጽሐ ልቡና
4⃣ በድንጋሌ ሥጋ
5⃣ በድንጋሌ ነፍስ
6⃣ በድንጋሌ ልቡና ታጥራ፣ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች።
↪️ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ድርሰቱ
✍እመቤታችንን «ከቅዱሳን ክብር የማርያም ክብር ይበልጣል፤ የአብን ቃል ለመቀበል በተገባ ተገኝታለችና፤ መላእክት የሚፈሩትን ትጉሆች በሰማያት የሚያመሰግኑትን ድንግል ማርያም በማኅፀንዋ ተሸከመችው፤ ይህች ከኪሩቤል ከሱራፌልም ትበልጣለች ከሦስቱ አካል ለአንዱ ማደሪያ ሆናለችና» ብሏል።
↪️ምክንያቱም ኪሩቤል ቢሸከሙ መንበሩን ነው ሱራፌልም ቢያጥኑ መንበሩን ነው፤ እርሷ ግን በማኅፀኗ የተ
4 374
#የዓቢይ_ጾም_ስድስተኛ_ሳምንት_ገብርኄር
☞✞ስለ ገብርኄር /ስለ ታማኝ/ አገልጋይ ያስተማረውን የሚያዘክር ምስጋና ይቀርብበታል፡፡
#ምስባክ መዝ. ፴፱÷፰
"ከመ እንግር ፈቃደከ መከርኩ አምላኪየ፡፡ ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ፡፡ ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ፡፡"
#ትርጉም፦ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ መከርሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው። በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህን አወራሁ።
#ወንጌል ማቴ. ፳፭÷፲፬-፴ “መንገድ እንደሚሄድ÷ አገልጋዮቹንም ጠርቶ ሊያተርፉበት ገንዘቡን እንደ ሰጣቸው ሰው እንዲሁ ይሆናልና፤ ለእያንዳንዱ እንደ ችሎታው ለአንዱ አምስት÷ ለአንዱ ሁለት÷ ለአንዱም አንድ ሰጠና ወዲያውኑ ሄደ፡፡ ያ አምስት መክሊት የተቀበለውም ሄደ፤ ነግዶም ሌላ አምስት መክሊት አተረፈ፡፡ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ፡፡ አንድ መክሊት የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና የጌታዉን ወርቅ ቀበረ፡፡ ከብዙ ጊዜም በኋላ የእነዚያ አገልጋዮች ጌታ ተመልሶ ተቈጣጠራቸው፡፡ #አምስት_መክሊት የተቀበለውም ቀረበና፡ አቤቱ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ሌላ አምስት አተረፍሁ ብሎ አምስት መክሊት አስረከበ፡፡ ጌታውም፡- መልካም÷ አንተ የታመንህ በጎ አገልጋይ በጥቂት የታመንህ ስለ ሆንህ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡ #ሁለት_መክሊት የተቀበለውም መጥቶ፡- አቤቱ÷ ሁለት መክሊትን ሰጥተኸኝ አልነበረምን? እነሆ ሌላ ሁለት መክሊትን አተረፈሁ አለ፡፡ ጌታውም፡- መልካም÷ አንተ የታመንህ በጎ አገልጋይ በጥቂቱ የታመንህ ስለ ሆንህ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡#አንድ_መክሊት የተቀበለውም መጣና እንዲህ አለ፡- አቤቱ÷ አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ÷ ካልበተንህበትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንህ አውቃለሁ፤ ስለ ፈራሁም ሄድሁና መክሊትህን በምድር ውስጥ ቀበርሁ፤ እንግዲህ እነሆ÷ መክሊትህ፡፡ ጌታውም መልሶ አለው፡- አንተ ክፉና ሰነፍ አገልጋይ÷ እኔ ካልዘራሁበት የማጭድ÷ ካልበተንሁበትም የምሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ ታውቃለህን? ገንዘቤን ለለዋጮች መስጠት በተገባህ ነበር፤ እኔም ራሴ መጥቼ ገንዘቤን ከትርፉ ጋር በወሰድሁ ነበር፡፡ ከዚያ የቆሙትንም እንዲህ አላቸው፤ ይህን መክሊት ከእርሱ ተቀብላችሁ ዐሥር መክሊት ላለው ስጡት፡፡ ላለው ሁሉ ይሰጡታልና፤ ይጨምሩለታልም፤ ለሌለው ግን ያንኑ ያለውን ይወስዱበታል፡፡ ክፉውን አገልጋይ ግን÷ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወደ አለ ጨለማ አውጡት፡፡"
☞✞አባቶቻችን በትምህርታቸውም እንዲህ ያመሰጥሩታል፦
አምስት መክሊት የተቀበለው የአምስቱ አዕማደ ምስጢር ምሳሌ፤ ሁለት መክሊት የተቀበለው የጴጥሮስ ምሳሌ በሰማይና በምድር ስልጣን እንደተሰጠው፤ አንድ መክሊት የተቀበለው የይሁዳ ምሳሌ እንደሆነም በሰፊው ያስተምሩናል።
#ምንባብ ፪ኛ ጢሞ.፪÷፩-፲፭ "ልጄ ሆይ÷ አንተም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ በርታ፡፡ በብዙ ምስክሮች ፊት ከእኔ የሰማኸውን ትምህርት ለሌሎች ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች እርሱን አስተምራቸው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደሚያገለግል በጎ አርበኛ ሆነህ መከራ ተቀበል፡፡ ወደ ሰልፍ የሚሄድ÷ አለቃውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ነው እንጂ የዚህን ዓለም ኑሮ አያስብምና፡፡ የሚታገልም ቢሆን እንደ ሕጉ ካልታገለ አክሊልን አያገኝም፡፡ የሚደክም አራሽም አስቀድሞ ፍሬውን ሊያገኝ ግድ ነው፡፡ ያልሁህን አስተውል፤ እግዚአብሔርም በሁሉ ነገር ጥበብን ይስጥህ፡፡
በወንጌል እንደምሰብከው÷ ከሙታን ተለይቶ የተነሣውን ከዳዊት ዘር የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስበው፡፡ ስለ እርሱም እንደ ወንጀለኛ አስክታሰር ድረስ መከራ እቀበላለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም፡፡ ስለዚህ እነርሱ ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን ሕይወትና የዘለዓለም ክብር በሰማያት ያገኙ ዘንድ÷ ስለ ተመረጡት ሰዎች በሁሉ ነገር እታገሣለሁ፡፡ ነገሩ እውነት ነው፤ ከእርሱ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንኖራለን፡፡ ብንታገሥም ከእርሱ ጋር ደግሞ እንነግሣለን፤ ብንክደው ግን እርሱም ይክደናል፡፡ ባናምነውም እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን መካድ አይቻለውምና፡፡ እንግዲህ ይህን አሳስባቸው፤ በቃልም እንዳይጣሉ ÷ በእግዚአብሔር ፊት ምከራቸው፤ ይህ ምንም የማይጠቅም÷ የሚሰሙትንም የሚያፈርስ ነውና፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል በእውነት አቃንቶ ሲያስተምር እንደማያፍር ሰራተኛ ሆነህ ፣ራስህን የተመረጠ አድርገህ ለእግዚአብሔር ታቀርብ ዘንድ ትጋ።" ፩ኛ ጴጥ.፭÷፩-፲፩ "እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ÷ የክርስቶስም መከራ ምስክር÷ ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግለዎችን እማልዳቸዋለሁ፡፡ በእናንተ ዘንድ ያሉትን የእግዚአብሔርን መንጋዎች ጠብቁ፤ ስትጠብቁአቸውም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ አይሁን፤ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘትም አይሁን፡፡ ለመንጋዉ ምሳሌ ሁኑ እንጂ ሕዝቡን በኀይል አትግዙ፡፡ የእረኞችም አለቃ በተገለጠ ጊዜ የማይጠፋውን የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ፡፡ እንዲሁ እናንተ ጐልማሶች ሆይ÷ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን ልበሷት፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ያዋርዳልና፤ ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉትን ግን ያከብራቸዋል፡፡ እንግዲህ በጐበኛችሁ ጊዜ ከፍ ከፍ ያደርጋችሁ ዘንድ ከጸናችው ከእግዚአብሔር ክንድ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፡፡ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት፡፡ እንግዲህ ዐዋቂዎች ሁኑ፤ ትጉም፤ ጠላታችሁ ጋኔን የሚውጠውን ፈልጎ÷ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና፡፡ እርሱንም በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት፤ እንዲህም ያለ መከራ በዓለም በአሉ ወንድሞቻችሁ ሁሉ እንደሚፈጸም ዕወቁ፤ ፍቅርንም አጽንታችሁ ያዙአት፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዘለዓለም
ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ፍጹማን ያደርጋችኋል፤ ያጸናችኋል፤ ልባሞችም ያደርጋችኋል፡፡ለእርሱ ክብርና ኅይል እስከ ዘለአለም ይሁን፤አሜን።" የሐዋ.፩÷፮-፰ "እነርሱም ተሰብስበው ሳሉ÷ "ጌታ ሆይ÷ በዚህ ወራት ለእስራኤል ልጆች መንግሥትን ትመልሳለህን?” ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው÷ “አብ በገዛ ሥልጣኑ የወሰነውን ቀኑንና ዘመኑን ልታውቁ አልተፈቀደላችሁም፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኅይልን ትቀበላላችሁ፤በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፣በሰማሪያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ምስክሮቸ ትሆኑኛላችሁ።"
ቅዳሴ ዘባስልዮስ
•••✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞•••
4 374
ጋዊ ጠላት አድኖ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን መድኀኒት
መባሉ ሥጋውን ቈርሶ ደሙን አፍስሶ፤ ጠላት ዲያብሎስን ሰራዊቱ አጋንንትን ድል
ነሥቶ ምእመናን በኀጢአታቸው ከመጣባቸው ፍዳ አድኖ ነውና የስሙን ነገር
ካነሣ ብሎ ለማነጻጸር ያመጣዋል፡፡
❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም የኢያሱን ለኢየሱስ ምሳሌነት እንዲኽ
አመሰጥሮታል፡- “በከመ ኢያሱ ዜናዌ ተሰምየ ኢየሱስሀ እምቅድመ ኢየሱስ
ናዝራዊ ኢየሱስ ብሂል መድኅን ብሂል …” (የነዌ ልጅ ኢያሱ ከናዝሬቱ ኢየሱስ
በፊት መድኅን እንደተባለ፤ ኢየሱስ ማለት መድኀኒት ነውና፤ ኢያሱ ወገኖቹን
ከጠላት ጦር እንዳዳናቸው ጌታ ኢየሱስም ወገኖችን ከኀጢአታቸው አዳናቸው
(ዘዳ ፴፬፥፱)፤ ኢያሱ ከሙሴ በረከትን እንደተቀበለ ጌታ ኢየሱስም ከአባቱ ዘንድ
ክብሩ ተገለጠ (ማቴ ፫፥፲፯)፤ ኢያሱ ከወገኖቹ ጋር የብስ የኾነ የዮርዳኖስን ወንዝ
እንደተሻገረ (ኢያ ፫፥፲፯) ጌታ ኢየሱስም የዮርዳኖስን ውሃ በጥምቀቱ ቀደሳት
(ማር ፩፥፱-፲፩)፤ ኢያሱ የእስራኤልን የሰውነታቸውን ሸለፈት በስለታም ምላጭ
እንደገዘረ (ኢያ ፭፥፯) ጌታ ኢየሱስም በወንጌል ምላጭ የአሕዛብን የበደላቸውን
ሸለፈት ገዘረ፤ ኢያሱ በገባዖን ፀሓይን እንዳቆመ ኹለተኛውንም ቀን አንድ ቀን
እንዳደረገ (ኢያ ፲፥፲፪-፲፫) ጌታ ኢየሱስም ፀሓይን በቀራንዮ አጨለመ አንዲቱንም
ቀን ኹለት ዕለት አደረጋት (ማቴ ፳፯፥፵፭)፤ ኢያሱ ምድረ ርስትን ለወገኖቹ
በየነገዳቸው እንዳደላቸው ጌታ ኢየሱስም የገነትን ምድር ለነቢያቱ በየወገናቸው
አደላቸው (ኢያ ፲፩፥፳፫፤ ኤፌ ፩፥፲፩)) እንዲል፡፡
ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (መልክአ ኢየሱስ ንባቡና ትርጓሜው የተወሰደ)
4 374
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን✞✞✞
#የመልክአ_ኢየሱስ_ለዝክረ_ስምከ_ለጌታ_ስም_የቀረበ_ትርጓሜ
•••✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
“ሰላም ለዝክረ ስምከ ስመ መሐላ ዘኢይሔሱ ዘአንበረ ቅድመ እግዚአብሔር በአትሮንሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዳዊት ባሕርየ ከርሡ አክሊለ ስምከ እንዘ ይትቄጸል በርእሱ አህጉረ ጸር ወረሰ ኢያሱ”
(የማይከዳ የቃል ኪዳን ስም ለኾነ የስም አጠራርኽ ሰላምታ ይገባል፤
እግዚአብሔር አስቀድሞ በዙፋኑ ያስቀመጠኽ የዳዊት የኾዱ ባሕርይ ኢየሱስ
ክርስቶስ ሆይ ኢያሱ መድኀኒትነት ያለው የስምኽን አክሊል ተቀዳጅቶ የጠላቶችን
ሀገሮች ወረሰ (ገንዘብ አደረገ))
❖ (ትርጓሜ)፡- ሊቁ በዚኽ የመልክአ ኢየሱስ ድንቅ ድርሰቱ ላይ “ነገርን
ከሥሩ ውሃን ከጥሩ” እንዲሉ “ኢየሱስ ክርስቶስ” ከሚለው ከስም አጠራሩ
በመነሣት ምስጋናውን ይዠምራል፤ “የማይከዳ የቃል ኪዳን ስም” ስለምን
አለው? ቢሉ አዳምና ሔዋን ከገነት ከተባረሩ በኋላ እንኳ አዳም የቤተ ፈት
ልማድ አላገኘውም፤ ቤተ ፈት በዚኽ ጊዜ እበላ እጠጣ፤ በዚኽ ጊዜ ተድላ ደስታ
አድርግ ነበር ብሎ ያዝናል፤ አዳም ግን ፈጣሪዬ አትብላ ያለኝን ዕፀ በለስን በልቼ
በደልኍ ብሎ በኀጢአቱ ፲፬ ሱባዔ ፺፰ ዓመት መሪር ልቅሶን አለቀሰ፡- “ወአልቦቱ
ካልዕ ኅሊና ላዕለ ኀጢአቱ ዘእንበለ ብካይ ወላህ” (ኀጢአቱን እያሰበ ከማልቀስ
ውጪ ሌላ ዐሳብ አልነበረውም) እንዳሉ አሞንዮስና አውሳብዮስ በመቅድመ
ወንጌል
❖ ያን ጊዜ የምሕረት ባለቤት አዳምንና ሔዋንን እንደሚቤዣቸው
እንደሚያድናቸው የማይታበል ጽኑ ቃል ኪዳንን ገብቶላቸዋል፡-
☞ “ወእምድኅረ ኀሙስ መዋዕል ወመንፈቀ መዓልት እምሕረከ ወእሣሃለከ
በብዝኀ ሣህልየ ወምሕረትየ፤ ወእወርድ ውስተ ቤትከ ወአኀድር ውስተ ከርሥከ
ወበእንቲኣከ ኦ አዳም እትወለድ ከመ ሕፃን ወበአንቲኣከ ኦ አዳም አሐውር ውስተ
ምሥያጥ፤ ወበእንቲኣከ እጸውም ፵ መዓልተ ወ፵ ሌሊተ፤ ወበእንቲኣከ እትዌከፍ
ወእትዔገሥ ሕማማተ ወበእንቲኣከ እሰቀል ዲበ ዕፀ መስቀል” (በፍጹም
ይቅርታዬ ከዐምስት ቀን ተኩል በኋላ በፍጹም ምሕረቴ ይቅር እልኻለኍ፤ ወደ
ቤትኽም ወርጄ በባሕርይኽ ዐድራለኍ፤ አዳም ሆይ ስለ አንተ እንደ ሕፃን
እወለዳለኍ፤ ስለ አንተ ወደ ገበያ እኼዳለኍ፤ ስለ አንተም አርባ ቀን አርባ ሌሊት
እጾማለኍ፤ ስለ አንተ መከራ መስቀልን በትዕግሥት አቀበላለኍ፤ ስለ አንተም
በዕንጨት መስቀል ላይ እሰቀላለኍ) እንዲል (መጽሐፈ ቀሌምንጦስ፣ ፫ኛ መቃ
፬፥፳፫-፳፬፤ ዕዝ ሱቱ ፬፥፩፤ ሲራ ፳፬፥፮፤ ገላ ፬፥፬)፡፡
❖ በመኾኑም “እትቤዘወከ” ብሎ እንደሚቤዠው እንደሚያድነው ለአዳም
የነገረው ሊደርስ ሊፈጸም ዘመኑ ሲፈጸም ቅዱስ ገብርኤል ወደ እመቤታችን ተልኮ
“ወናሁ ትፀንሲ ወትወልዲ ወልደ ወትሰምዪዮ ስሞ ኢየሱስ” (እነሆም ትፀንሻለሽ
ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ) በማለት የስሙን
መድኀኒትነት ነግሯታልና ደራሲው “የማይከዳ የቃል ኪዳን ስም ለኾነ የስም
አጠራርኽ ሰላምታ ይገባል” ይለዋል (ሉቃ ፩፥፴፩)፡፡
❖ መጋቤ ሐዲስ ቅዱስ ገብርኤል ለአረጋዊዉ ለዮሴፍም ኢየሱስ የሚለውን
ንባቡንም ትርጓሜውን ሲገልጽለት፡- “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ ከርሷ የተፀነሰው
በግብረ መንፈስ ቅዱስ ነውና ዕጮኛኽን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ ልጅም
ትወልዳለች፤ ርሱ ሕዝቡን ከኀጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ
ትለዋለኽ” በማለት ወገኖቹን በኀጢአታቸው ከመጣባቸው ፍዳ የሚያድናቸውን
መድኅነ ዓለም ኢየሱስን ቅድስት ድንግል ማርያም በግብረ መንፈስ ቅዱስ
እንደፀነሰችው ነግሮታልና (ማቴ ፩፥፲፰-፳፫)፡፡
❖ ከሊቃውንት አንዱ ሶርያዊዉ ቅዱስ ኤፍሬምም ስለዚኽ ነገር በጥልቀት
በትርጓሜ ወንጌሉ ላይ ሲገልጸው፡- “The words in the ‘sixth month’ are
reckoned in Elizabeth’s pregnancy…” (መልአኩ “በስድስተኛው ወር”
የሚለው ኤልሳቤጥ ከፀነሰችበት ወራት ዠምሮ በመቊጠር ነው፤ መልአኩ ወደ
አንዲት ድንግል ተላከ ወደ ርሷ ገብቶም “እነሆ ድንግልናሽ ሳይነዋወጥ
ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ” አላት፤
ይኸውም በሥጋ ተገልጦ ሊመጣ ስላለው ስለ አካላዊ ቃል ሲናገር ነው፤
ሲነግራትም “ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ” አላት እንጂ “ኢየሱስ የተባለው”
አላላትም፤ ይኸውም ወልደ እግዚአብሔር በተዋሐደው ሥጋ የሰው ልጆች
የሚድኑበት ስም መኾኑን የሚያመለክት ነው፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ማለት
በዕብራይስጥ “መድኅን” ማለት ነውና፤ መልአኩ “ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ”
ሲላት መድኅን ትዪዋለሽ ማለቱ ነው፤ ለምን? ቢሉ ሕዝቡን ኹሉ ከኀጢአታቸው
ያድናቸዋልና) በማለት ተርጒሞታል፡፡
❖ ክርስቶስ “Χριστός” የጽርዕ ቃል ነው፤ በዕብራይስጥ “መሲሕ” ሲባል፤
በግእዝ ቋንቋ “ቅቡዕ” ማለት ነው፤ ይኸውም ብቻ የትስብእት፤ ብቻ የመለኮት
ስም አይደለም፤ ከኹለት አካል አንድ አካል፤ ከኹለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ቢኾን
የወጣለት የተዋሕዶ ስም ነው፤ “ቅቡዕ” መባሉም ሥጋ ከአካላዊ ቃል ጋር
ቢዋሐድ የባሕርይ አምላክ መኾኑን ያመለክታል፤ ይኸውም የአካል የባሕርይ
ተዋሕዶ ነውና ትስብእት ከባሕርይ ልጅ ከባሕርይ አምላክ የባሕርይ ተዋሕዶ
ቢዋሐድ ሥጋ የባሕርይ አምላክነትን የባሕርይ ልጅነትን አገኘ፤ በባሕርይ
አምላክነት፣ በባሕርይ ልጅነት ከበረ፤ ውሱን ሲኾን ምሉዕ፤ ግዙፍ ሲኾን ረቂቅ፤
መዋቲ ሲኾን ሕያው ኾነ፤ ኀየሰ፣ ወረሰ፣ ነግሠ፣ ዐብየ፣ ከብረ፣ ተለዐለ ተባለ፡፡
ኹሉ የሚቻለው ከሌላ አካል ክብር ከማይሻ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ዕሩይ
ከሚኾን ከቃል ጋራ የባሕርይ ተዋሕዶን ቢዋሐድ ሥጋ በተዋሕዶተ ቃል ከአብ
ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለ የባሕርይ አምላክ ኾኗልና፡፡
❖ አንድም “ስመ መሐላ” ብሎ የያዘውስ ለዳዊት የገባለትን ቃል ኪዳን ነው
ብሎ፤ ለዳዊት አስቀድሞ ከባሕርዩ የተከፈለ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስን በዙፋኑ
እንደሚያስቀምጥለት፡- “መሐለ እግዚአብሔር ለዳዊት በጽድቅ ወኢይኔስሕ
እስመ እምፍሬ ከርሥከ አነብር ዲበ መንበርከ” (እግዚአብሔር ለዳዊት እንዲኽ
ሲል በእውነት ማለ አይጸጸትምም፤ ከኾድኽ ፍሬ በዙፋንኽ ላይ አስቀምጣለኹና)
ብሎታልና፤ ደራሲውም ከዚኽ አያይዞ “እግዚአብሔር አስቀድሞ በዙፋኑ
ያስቀመጠኽ የዳዊት የኾዱ ባሕርይ ኢየሱስ ክርስቶስ” በማለት ተናገረ (መዝ
፻፴፩፥፲፩)፡፡
❖ ይኽማ የተነገረው ለሰሎሞን አይደለም ቢሉ? ለጊዜው ለሰሎሞን ቢኾን
ፍጻሜው ለጌታ ነውና፤ ለጊዜው ለሰሎሞን ፍጻሜው ለጌታ መኾኑ እንደምን
ነው? ቢሉ ሰሎሞን በጸጋ የገዛቸውን ኹሉ ጌታ በባሕርይ ገዝቷቸዋልና፡፡
አንድም ሰሎሞን በሥጋ የገዛቸውን ኹሉ ጌታ በነፍስ ገዝቷዋልና፡፡
አንድም ሰሎሞን በግድ የገዛቸውን ጌታ በፈቃድ ገዝቷቸዋልና፡፡
አንድም የጌታ መንግሥት መታወቁ ነቢዩ “መንበርከ እግዚኦ ለዓለመ ዓለም”
ብሎ በተናገረለት ነውና (መዝ ፵፬፥፮)፡፡
አንድም “ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምኢ እዝነኪ” ብሎ የትንቢት ዙፋን አድርጎ
በተናገረላት በምእመን ላይ ነውና (መዝ ፵፬፥፲)፡፡
አንድም “ዲበ መንበረ ዳዊት ትጸንዕ መንግሥቱ ለክርስቶስ” እንዲል ከዳዊት
የነሣው ሥጋ እንደ አብ እንደ መንፈስ ቅዱስ የሚያድን የሚገድል ኾኗልና ፡፡
❖ ደራሲው በመጨረሻ፡- “ኢያሱ መድኀኒትነት ያለው የስምኽን አክሊል
ተቀዳጅቶ የጠላቶችን ሀገሮች ወረሰ (ገንዘብ አደረገ)” በማለት ኢያሱን አነሣ
ስለምን ቢሉ? ኢያሱ ማለት የስሙ ፍቺ መድኀኒት ማለት ነውና ይኸውም ኢያሱ
መድኀኒት መባሉ በዐጭር ቃጥቆ ዘገር ነጥቆ ጦር ነቅንቆ አማሌቃውያንን
አጥፍቶ እስራኤልን ከሥ
4 374
በ#data ለምትጠቀሙ ምዕመናን በሙሉ፦ #telegram ብር እየጨረሰ ካስቸገራችሁ፦ ይህን አስተካክሉ፦
step~1 #settings ግቡ
step~2 #data_and_storage
step~3 #when_using_mobile_data
step~4 #ሁሉንም_አጥፏቸው
#ጥቅሙም፦
➊data ስንከፍት በራሱ ጊዜ download አያደርግም
➋እናንተ የምትፈልጉትን ፈቅዳችሁ ስትነኩት ብቻ download ያደርጋል ማለት ነው ?
አደራ_ሁላችሁም_ተጠቀሙት
4 374
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን✞✞✞
#እንኳን_ለጌታችን_ለአምላካችንና_ለፈጣሪያችን_መድኃኔዓለም_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ዓመታዊ_የስቅለት_በዓል_በሰላምና_በጤና_አደረሰን_አደረሳችሁ ✞•••
መጋቢት ፳፯
✞✞✞ #መድኃኔ_ዓለም ✞✞✞
☞✞ ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ በዚሕ ዕለት ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት። ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና፡ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት፡ አስረው ሲደበድቡት አድረዋል።
☞✞ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት። ምራቃቸውን ተፉበት፤ ዘበቱበት። ራሱንም በዘንግ መቱት። እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ።
☞✞ በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት። በሠለስት (ሦስት ሰዓት ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ጊዜ በአለንጋ/በጅራፍ ገረፉት። ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት።
☞✞ ስድስት ሰዓት ላይ በረዣዥም ብረቶች አምስት ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት። የአምስቱ ቅንዋተ መስቀል ስማቸውም፦
➊ሳዶር፣ ➋አላዶር፣ ➌ዳናት፣ ➍አዴራና ➎ሮዳስ ነበር፡፡
☞✞ ሰባት ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ። ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ ሰባት ቃላትን ተናገረ። እነርሱም፦
➊አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው
➋ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ?አምላኬ አምላኬ ስለምን ተውኸኝ
➌አባት ሆይ ነፍሴን በእጅ አደራ እሰጣለሁ
➍እውነት እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከኔ ጋር በገነት ትኖራለህ
➎ተጠማሁ
➏እንሆ ልጅሽ እነኋት እናትህ እና
➐ተፈፀመ የሚሉት ሲሆኑ
☞✞የአሥራ ሦስቱ ኅማማተ መስቀል ስሞችም፦
➊የኋሊት መታሰር
➋ራሱን በዘንግ መመታት
➌መስቀሉን መሸከም
➍መስቀሉን ተሸክሞ በምድር መውደቅ
➎በእግር መረገጥ
➏በምድር መጎተት
➐ጀርባውን 6666 ጊዜ መገረፍ
➑ፌቱን በጥፌ መመታት
➒መጋፌያው እስኪ ላጥ ድረስ በሀብል ታስሮ መገረፍ
➓በመስቀል ላይ መሰቀል
➊➊በራሱ ላይ የሾህ አክሊል መቀዳጀት(መልበስ)
➊➋መራራ ሀሞት መጠጣት
➊➌በ5ቱ ቅንዋተ መስቀላት መቸንከር እነርሱም ሳዶር ፣አላዶር፡ዳናት ፡አዴራ እና ሮዳስ ናቸው።
•••✞✞✞••• ደግሞም ጌታችን በተሰቀለበት ጊዜ በሰማይ እና በምድር ላይ የተፈፀሙ ተአምራት፦
#በሰማይ ፀሀይ ከ6 ሰዓት እስከ 9 ሰዓት ብርሃኗን ከለከለች፣ ጨረቃ ደም መሰለች፣ ከዋክብት ረገፉ።
#በምድር ምድርም ተናወጠች፣ አለቶች ተሰነጣጠቁ፣ መቃብሮችም ተከፈቱ፣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፡፡ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በባሕርይ ሥልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ። በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ። አሥራ አንድ ሰዓት ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት።
☞✞"የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና። እርሱም ኃጢአት አላደረገም። ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም። ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም። መከራንም ሲቀበል አልዛተም... እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ።"
፩ኛ ጴጥ. ፪፥፳፩-፳፭
☞✞በዚያች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ። ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ። ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ። {ማቴ.፳፯፥፩, ማር.፲፭፥፩, ሉቃ.፳፫፥፩, ዮሐ.፲፱፥፩}
🙏✞ጌታችን አምላካችን ፈጣሪያችን መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ቅዱስ መስቀሉ: ስለ ድንግል እናቱ ለቅሶና ስለ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስ ብሎ ይማረን ይቅር ይበለን አሜን ✞🙏
•✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ✞✞✞•
4 374
•✞ #አልፋና_ኦሜጋ ✞•
•••✞•••✞•••✞•••
አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ (2)
በከሃዲዎች እጅ ተይዘክ ቀረብክ (2)
•••✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ
እየደበደቡ ክርስቶስ ሆይ አሉህ
ጽድቅን ስለሰራህ በወንጀል ከሰሱህ
ለአዳም ቤዛ ብለህ ብዙ ተንገላታህ
#አዝ•••
ቅዱሳን እጆችህ የፍጥኝ ታስርው
እንደ በግ ተጎትተህ ልትመራቸው
የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ
ፊትህን ሸፈኑት ለመመጻደቅ
#አዝ•••
በአውደ ምኩና ከጲላጦስ ዘንድ
አሳልፈው ሰጡ አጋልጠው ለፍርድ
ከሃና ቀያፋ ከመሳፍንቱ ደጅ
ከነሄሮድስ ዘንድ አቀረቡ በአዋጅ
#አዝ•••
ግርፋት ሕማሙ አልበቃ ብሎህ
በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ
ሳዶርና አላዶር ዳናትና አዴራ
ተፈልገው መጡ ለችንካር በተራ
#አዝ•••
የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ
ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ
ግፈኞች አይሁዶች ባንተ ላይ ቀለዱ
ምራቅን ተፉብህ እራስህን ሊጎዱ
#አዝ•••
4 374
✞✞✞ #ጌታ_ሆይ ✞✞✞
ጌታ ሆይ አይሁድ አማፅያን ሰቀሉህ ወይ
የዓለም መድኃኒት የዓለም ሲሳይ ሰቀሉህ ወይ/2/
የአዳም በደል አደረሰህ አንተን ለመሰቀል
የሄዋን ስህተት አበቃህ ለሞት ቸሩ አባት/2/
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ንጹህ ክርስቶስ ሆንክ በደለኛ ብለህ ስለኛ
መስቀል አሸክመው አሥረው ገረፉህ እያዳፉህ/2/
ግብዞች እንደራሳቸው መስሏቸው
ምራቅ እየተፉ በፊትህ ቀለዱ አንተን ሊጎዱ/2/
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
እጅና እግርህ በችንካር ተመታ የዓለሙ ጌታ
የእሾህ አክሊል ደፍተህ ጎንህን ተወጋህ አልፋ ኦሜጋ/2/
በመስቀል ላይ ተጠማሁ ስትል ታላቅ በደል
ሃሞትና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው ጠጣ ብለው/2/
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ይቅር ባይ ግልጽ በደላችን ሁሉን ሳታይ
አንተ ይቅር በለን በእኛ ሳትከፋ እንዳንጠፋ/2/
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
