cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ስለሀገራችን እንፀልይ

በዚህ ቻናል ዉስጥ ✔ሀይማኖታዊ ትምህርቶች ✔መንፈሳዊ መዝሙር ✔መፅሐፍ በPdf ✔የተለያዩ መረጃዎች እና ሌሎችንም ታገኙበታላችሁ ። #SHARE_THIS_CHANEL 👇 @bisratnews @bisratnews @bisratnews https://telegram.me/bisratnews

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
195
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

@Keraniyomedhanialem @Keraniyomedhanialemgroup @Keraniyomedhanialem @Keraniyomedhanialemgroup @Keraniyomedhanialem @Keraniyomedhanialemgroup @Keraniyomedhanialem @Keraniyomedhanialemgroup @Keraniyomedhanialem @Keraniyomedhanialemgroup ይህን ቻናል ለወዳጆ #ሼር በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎች ን እንዲያገኙ ተባበሯቸው። ስለ ትብብሮ ከልብ እናመሠግናለን ።🙏🙏🙏
إظهار الكل...
(የማቴዎስ ወንጌል 1 ) ------------ 1፤ የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ። 2፤ አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤ 3፤ ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፤ 4፤ ኤስሮምም አራምን ወለደ፤ አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤ 5፤ ሰልሞንም ከራኬብ ቦኤዝን ወለደ፤ ቦኤዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤ 6፤ እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ፤ 7፤ ሰሎሞንም ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓምም አቢያን ወለደ፤ አቢያም አሣፍን ወለደ፤ 8፤ አሣፍም ኢዮሣፍጥን ወለደ፤ ኢዮሣፍጥም ኢዮራምን ወለደ፤ ኢዮራምም ዖዝያንን ወለደ፤ 9፤ ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ፤ ኢዮአታምም አካዝን ወለደ፤ 10፤ አካዝም ሕዝቅያስን ወለደ፤ ሕዝቅያስም ምናሴን ወለደ፤ ምናሴም አሞፅን ወለደ፤ 11፤ አሞፅም ኢዮስያስን ወለደ፤ ኢዮስያስም በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ። 12፤ ከባቢሎንም ምርኮ በኋላ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ፤ 13፤ ዘሩባቤልም አብዩድን ወለደ፤ አብዩድም ኤልያቄምን ወለደ፤ ኤልያቄምም አዛርን ወለደ፤ 14፤ አዛርም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪምን ወለደ፤ አኪምም ኤልዩድን ወለደ፤ 15፤ ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም ማታንን ወለደ፤ ማታንም ያዕቆብን ወለደ፤ 16፤ ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ። 17፤ እንግዲህ ትውልድ ሁሉ ከአብርሃም እስከ ዳዊት አሥራ አራት ትውልድ፥ ከዳዊትም እስከ ባቢሎን ምርኮ አሥራ አራት ትውልድ፥ ከባቢሎንም ምርኮ እስከ ክርስቶስ አሥራ አራት ትውልድ ነው። 18፤ የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። 19፤ እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ። 20፤ እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ። 21፤ ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ። 22፤ በነቢይ ከጌታ ዘንድ፦ 23፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው። 24፤ ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መልአክ እንዳዘዘው አደረገ፤ እጮኛውንም ወሰደ፤ 25፤ የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው። @Keraniyomedhanialem @Keraniyomedhanialem @Keraniyomedhanialem
إظهار الكل...
إظهار الكل...
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን እንወቅ!

ተዋህዶ የጸናች እምነት ናት! ሰውን ታድሳለች እንጂ ሰው የማያድሳት ናት፡፡ " አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቅት፡፡ ኤፌ ፬፡፭" ሼር በማድረግ ኦርቶዶክሳዊ ግዴታዎን ይወጡ!

ሰንበት ተማሪ ነኝ! ***** ትዕዛዙን ልከተል ፣ ያቅሜን የምታትር ዘወትር በምስጋና ፣ ስሙን የምዘክር ከማህሌቱ ቆሜ ፣ ኪዳኑን አድርሼ ሰዓተ ሩፋዱን ፣ ፆሜ አስቀድሼ እርሱ እንደወደደኝ ፣ ልወደው የምሻ ቀዳሚ የምገኝ ፣ ከፀበሉ ቅምሻ በትጋት በፍቅር ምስጢር ምመረምር አጋንንት የሚጥል ፣ ንፁህ እምነት ያለኝ የብርሃን ኮከብ ፣ ሰንበት ተማሪ ነኝ °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ስለ ማህተቤ አንገቴን የምሰጥ ለሚያልፍ ማዕበል ፣ የማልንቀጠቀጥ ወንጌልን ገልጬ ፣ የምማር አንድምታ የረቀቀ ምስጢር ፣ ቅኔ የምፈታ የትግስቴን አጥር ፣ ክፋት የማይንደው ጠፊ እንግዳ ስብከት ፣ ልቤን የማይወስደው እምነቴን አስይዤ ፣ ለንዋይ የማልወድቅ ዝሙትን የምሸሽ ፣ የማልዋሽ ፣ የማልሰርቅ ሰባት ጊዜ ብወድቅ ፣ ሳባቴ ምነሳ በጥበብ በብልጠት ፣ የማጠፋ አበሳ መመላለስ ሳይሆን ፣ መመለስ የምመኝ የፃድቅ አወዳሽ ፣ ሰንበት ተማሪ ነኝ °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° መልካም ምግባር ይዤ ፣ ከደጁ ማልጠፋ ተግሳፅ  የምቀበል ፣ ክብር የማልገፋ በሽብሻቦ እልልታ ፣ በያሬድ ዝማሬ በውዳሴ ማርያም ፣ በ'የሱስ ፍካሬ ቀኔን የማሳምር በፈተና ዓለም ፣ ምሬት የማልሰፍር ለውበት ሰግጄ ፣ ተስፋዬን የማልሸጥ እንደ ወይራ በትር ፣ የማልለማመጥ ሰንበት ተማሪ ነኝ ... በቅዱሳን ስፍራ ፣ ፀሎት አደርሳለሁ የወላዲተ አምላክ ፣ ምልጃዋን አምናለሁ @Keraniyomedhanialem @Keraniyomedhanialemgroup
إظهار الكل...
#ክፍልአንድ #ምዕራፍአንድማንነበርኩ? #ናህድማሕሙድሙትዋሊ እባላለሁ። ሴቶችን ብቻ የሚያስተምረው የሄልሜት ኤል ዘይቱን ትምህርት ቤት ዲን ነበርኩ። በካይሮ የታወቀ እና ትልቁ ትምህርት ቤት ነው። 4000 ልጃገረዶችን ያስተምራል። ከተማሪዎቹ ብዛት የተነሣ ት/ቤቱ የሚያስተምረው በጥዋት እና በከሰዓት ፈረቃ ነበር። የት/ቤቱ ዲን እንደመሆኔ መጠን ሁለቱንም ፈረቃዎች መከታተል ነበረብኝ። ምንም እንኳን ከሁሉም ዲኖች በዕድሜ ታናሿ እና በቅርብ ከኮሌጅ የተመረቅኩ ብሆንም ይህንን ወንበር እንዳገኝ ግን ሁለት ነገሮች ረድተውኛል። እግዚአብሔር ብስለትን፣ በራስ መተማመንን፣ እንዲሁም ኃላፊ ነቴን በሚገባ የመወጣት ችሎታን አድሎኝ ነበር። የማንም ርዳታ ሳያስፈልገኝ የሚሰጠኝን ሥራ ሁሉ በአፋጣኝ የማከናወን ልምድ አለኝ። ሰወች አንድን ነገር ሲሠሩ መመልከት ብቻ ለእኔ በቂዬ ነበር። ያንኑ ነገር ወዲያውኑ ልምድ እንዳለው ሰው አድርጌ ማከናወን እችላለሁ። በዚህ ችሎታዬ የተነሣ ይህንን ቦታ ያገኘሁት ቦታውን ላገኘው ከሚገባኝ ዐሥር ዓመታት ቀድም ነበር ከዚህ ችሎታዬ ጋር ተጨምሮ በት/ቤቱ የነበሩትን የሁለቱን ረዳት ዳይሬክተሮች ተግባር የማወቅ ዕድልም ገጥሞኛል። የተማሪዎችን ሰሞች በምሥጢራዊ ኮድ ካገኘኋቸው ዋና ዋና ልምዶች መካከል የሚጠቀሱት ናቸው። እንዚህ ሁለቱ ተግባራት ደግሞ በት/ቤታችን ውስጥ ዋነኞቹ ሥራዎች ናቸው። ምክንያቱም ሁለቱም ፍጹም የሆነ ምሥጢር ጠባቂነትን የሚጠይቁ ናቸውና። አንደኛው ረዳት ዳይሬክተር በ60 ዓመቱ ጡረታ ወጣ፣ ሌላው ደግሞ ወደ ሌላ የዓረብ ሀገር ለሥራ ሄደ። ይህንን አጋጣሚ በመጠቀምም እነዚህን ሁለቱን ኃላፊነቶች ጠቀለልኳቸው። ይህም የት/ቤቱን ቁሌፍ ቁልፍ አስተዳደራዊ ኃላፈነቶች እንድቆጣጠር ዕድል ከፈተልኝ። እነዚህን ኃላፊነቶች ከጠቀለልኩ በኃላ ልክ የት/ቤቱ ንግሥት የሆንኩ ያህል ይሰማኝ ነበር። በእነዚህ ነገሮች ሙሉ ሥልጣን እና ፍጹም የሆነ ኃላፈነት ነበርኝ። ሌላው ቀርቶ የእኔ የበላይ የሆነችው የት/ቤቱ ዳይሬክተር እንኳን በጣም ትቅርበኝ፣ የምትሠራውንም ነገር ሁሉ ታማክረኝ ነበር። የሚፈራ፣ ኃይለኛ፣ አድራጊ ፈጣሪ ሆንኩ። ለመኞቴ ወሰን አልነበረውም። ለዝቅተኛ ተማሪዎች የሚሰጠውን የትምህርት እገዛ እኔ ራሴ እንድከታለው ኃላፈነቱ እንዲሰጠኝ አስተዳደሩን ጠይቄ ተፈቀደልኝ። በዚህ የተነሣም በየወሩ ከእነዚህ ክፍሎች ለሚሰበሰበው ከ12ሺ-15ሺ ለሚጠጋው ገንዘብ ኃላፊ ሆንኩ። ለዚህ ኃላፊነቴ እንዲሁም ፈተና ለማዘጋጀት እና ለማባዛት ተግባሬ የሚከፈለኝ ገንዘብ ወራኃዊ ገቢዬን በሦስት እጥፍ አሳደገው። ወደዚህ የሥልጣን እርከን ያሸጋገረኝ ሌላው ነገር ደግሞ የቤተ ሰቦቼ ታዋቂነት እና በመንግሥታዊ ቦታዎች ያላቸው ሥልጣን ነቀር። ወንድሜ በማዕከላዊው የአስተዳደር እና የአመራር ሥርዓት ቢሮ ውስጥ ሥራ እስኪያጅ ነበር። አንደኛው ዋርሳዬ ደግሞ የማዘጋጃ ቤቱ ጸሐፊ እና የት/ቤቱ የወላጆች እና መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት ነው። የእርሱ ሁለቱ ሴቶች ልጆቹም የት/ቤቱ ተማሪዎች ነበሩ። ሌላው ዋርሳዬ ደግሞ የቤተ መንግሥቱ ፓይለት ነው። እኅቴ የሄልዮፓሊስ አካባቢ የት/ቤቶች አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስኪያጅ ናት። ባልዋም በማዕከላዊው የመረጃ አገልግሎት ሹም ነበር። እንዚህ ሁሉ ከእኔ ሰብእና እና በት/ቤቱ ከተፈጠረው ክፍተት ጋር ተደማምረው ከሥልጣን ወደ ሥልጣን አሸጋገሩኝ። ይህ ሁሉ በሀብት እና በሥልጣን ይጠቀመኝ እንጂ ወስጤን ግን ትዕቢተኛ ፣ ዕብሪተኛ እና ግብዝ አድርጎኛል። በሌላ በኩል ልቡናዬን ለሚያይ ደግሞ የተለየሁ ፍጥረት ነበርኩ። አምላኬን እወደዋለሁ የምል ቆዳ ስሱ ሰው ነኝ። አዎን ጌታዬ ሆይ ምንም እንኳን ከአንተ ርቄ ብኖርም በፍጹም ልቤ እወድድህ እና እፈራህ ነበርኮ። እግዚአብሔርን ስፈልገው ኖሬያለሁ፣ እነዚያ የሕይወቴ የተበላሹ ገጽታዎች ግን እርሱን እንዳላገኝው የመከለያ ግንብውቅም ነበር። አብዝቼ እጸልያለሁ፣ ቁርዐንንም አዘውትሬ አነባለሁ ፣ ይሁን እንጂ በውስጤ አንዳች የጎደለ ነገር መኖሩ ይሰማኝ ነበር። ክርስቲያኖች እኔ የምወደውን አምላክ አይወዱትም ብየ ስለማስብ አብዝቼ እጣላቸው ነበር። እግዚአብሔርን እኔ በማመልክበት መንገድ ለምን አያመልኩትም? እነርሱ ከእግዚአብሔር የኮበለሉ ናቸው እያልኩ እጅግ እጠላቸው ነበር። ክርስቲያኖችን ከመጥላቴ የተነሣ እነርሱን ለማዋድ፣ ለመጉዳት እና በእነርሱ ላይ አንዳች ችግር ለመፍጠር ዘወትር እጥር ነበር። ይህንን የማደርገው ግን በውስጤ ለሰው ክፋት ስላለኝ ሳይሆን የምወደውን እና የማመልከውን አምላክ ለምን አያመልኩም፣ ለምንስ አይወዱም? ብየ ነበር። በርግጥ ሁልጊዜ የሚገርመኝና የሚያሳስበኝ አንድ ነገር አለ። እኔ ላገኘው የምጓጓለትን ውሳጣዊ ሰላም ክርስቲያኖች ገንዘብ አድርገውታል። እንዴት? ክፍል ሁለት ነገ 12:00 ይቀጥላል @Keraniyomedhanialem @Keraniyomedhanialemgroup
إظهار الكل...
ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና እውነተኛ ታሪክ ከ ናህድ ማሕሙድ ሙትዋሊ አርተር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሁሌም ማታ 12 ሰዓት በክፍል በክፍል ይቀርባል ዛሬ ማታ 12 ሰዓት ይጠብቁኝ ክፍል አንድ ይለቀቃል ሼር ይደረግ @Keraniyomedhanialem @Keraniyomedhanialemgroup
إظهار الكل...