cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

🇪🇹Ethiopia🇪🇹🇪🇹 News🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

True Breaking News

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
Advertising posts
153المشتركون
لا توجد بيانات24 hour
لا توجد بيانات7 يوم
لا توجد بيانات30 يوم

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ብሔራዊ ቡድኑ የማበረታቻ ሽልማት እና እውቅና ሊበረከትለት ነው -------------------------------------------- ግንቦት 04/2013 (ዋልታ) - የኢትዮጵያ ወንድ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ከ8 አመት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉን ተከትሎ በመንግስት እና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አማካኝነት የእውቅና እና ሽልማት ሊበረከትለት መሆኑን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮምሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በጋራ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉን ተከትሎ በወቅቱ በተለያዩ ምክንያቶች የሽልማት እና የማበረታቻ ፕሮግራም ባይካሄድም የሀገራችን ህዝቦች በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች አደባባይ በመውጣት በከፍተኛ ድምቀት የጀግና አቀባበል በማድረግ ደስታቸውን እንደገለፁ ኮምሽነሩ በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ወንዶች እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን ለ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በማለፉ ሀገርንና ህዝብን በማኩራታቸው እና በቀጣይ ባለው አፍሪካ ዋንጫም ሆነ በሌሎች ውድድሮች ላይ ተፎካካሪ ሆኖ እንዲቀርብ የዝግጅት ስራ ለመስራት ዓላማ ተደርጎ የተዘጋጀ ፕሮግራም እንደሆነ ታውቋል፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ለስፖርቱ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ፣ መነቃቃትን የፈጠረ ቢሆንም ቀጣይነት እንድኖረው ታዳጊ ወጣቶች ላይ መስራት እና ኤሊት ስፖርተኞችን በጥራትና በስፋት ማዘጋጀት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ የገለፁት ኮምሽነሩ ብሄራዊ ቡድኑ ቀጣይ ባሉት ውድድሮች ላይ ጠንካራ እና ተፎካካሪ እንዲሆን የወዳጅነት ጨዋታዎችን ጨምሮ ሀብት ተመድቦ ... https://www.facebook.com/489211707826282/posts/4275772712503477/
إظهار الكل...
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረችሁ መልዕክት አስተላለፉ ------------------------- ግንቦት 05/2013 (ዋልታ) -ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለ1ሺህ 442ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ ዓልፈጥር በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ፕሬዚዳንቷ በትዊተር ገጻቸው ላይ ለመላው ሙስሊም ኢትዮጵያውያን እንኳን ለኢድ አል ፈጥር በዓል በደህና አደረሳችሁ ብለዋል። በዓሉን በቤታቸው ለማክበር ዕድሉን ያላገኙትን ወገኖቻችንን በማስታወስ ፣ በመደገፍና ያለንን በማካፈል ልናከብር ይገባል ብለዋል ። በዓሉ የሰላምና የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡
إظهار الكل...
ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ከረመዳን ጾም በኋላም መልካምና በጎ ነገር ማድረጉን እንዲያስቀጥል ተጠየቀ ----------------------------------- ግንቦት 05/2013 (ዋልታ) - የደብረታቦር ከተማ ሙስሊም ማኅበረሰብ የ1 ሺህ 442ኛውን ኢድአልፈጥር በዓልን በቴዎድሮስ አደባባይ በሶላትና በእስላማዊ ትምህርቶች አክብሯል፡፡ በእለቱ በእንግድነት የተገኙት የደብረታቦር ከተማ ከንቲባ መሰረት ወንዴ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እስልምናና ክርስትና ሃይማኖቶች ለበርካታ ዓመታት አብረው ተከባብረው የኖሩ መሆናቸውን አስታውሰዋል። ይህንን መልካም እሴት ላቆዩን አባቶቻችን ክብር ይግባቸዋልም ብለዋል፡፡ ከንቲባው እስልምና ማለት ሰላም ማለት መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያ ከተጋረጠባት ችግር እንድታልፍ ሕዝበ ሙስሊሙ ዱኣ (ጸሎት) እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡ በበዓሉም የሶላት ሥነ ሥርዓትና ሌሎች አስተምህሮዎች ተከናውነዋል፡፡ በበዓሉ ለሕዝበ ሙስሊሙ ሃይማኖታዊ ትምህርት የሰጡት የሃይማኖቱ ዳኢ (አስተማሪ) ሸህ አብዱል ሃዲ ሁሴን ከእስልምና መሰረቶች ውስጥ አንዱ ጾም መሆኑን ጠቅሰው በጾም ወቅት እዝነት፣ መረዳዳት፣ ያለው ለሌለው ማካፈልና በጎ ስራ መስራት ከፈጣሪ ጋር የሚያስታርቅ ነው ብለዋል፡፡ ሙስሊሙ ማኀበረሰብ ከሮመዳን ጾም በኋላም መልካምና በጎ ነገር መስራትን አጠናክሮ በመቀጠል ከአላህ ምንዳውን ለማግኘት ሃይማኖቱን መኖር እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ (ምንጭ፡- አሚኮ)
إظهار الكل...