ar
Feedback
ቲቪ ጥገና Tv maintenance , ቲቪ ቴክኒሻን ,Tv repair 🖥

ቲቪ ጥገና Tv maintenance , ቲቪ ቴክኒሻን ,Tv repair 🖥

الذهاب إلى القناة على Telegram

ይህ ቻናል በመቀላቀሎ የሚያገኝዋቸው ጥቅሞች ፩የኤሌክትሮኒክስ እውቀቶን ያዳብራሉ። ፪ቲቪ ፣ ሳተላይት ሪሲቨር ፣ ሞባይል ፣ ኮምፕዩተር ፣ ፍሪጅ እና የልብስ ማሺን ወዘተ ባለሙያዎችን የትም መሄድ ሳያስፈልጎ እዚህ ያገኛሉ። @Yilymj @newgroupmaintenance ለቲቪ መለዋወጫ Website : ysak-electronics.netlify.app

إظهار المزيد
2 914
المشتركون
-124 ساعات
-37 أيام
-130 أيام
أرشيف المشاركات
ሰላም ቤተሰቦቼ 🙏🙏🙏 እስካሁን የምለቃ ቸው ፅሁፎች ከተመቻቹ በዚ 👍like በማድረግ ግለፁልኝ

ሰላም 🙏🙏🙏 ጤና ይስጥልኝ በቀጣይ ስለ eprom programing (ሪሲቨር :ቲቪ :ዲቪዲ... on ፡ boot: hello ብለው የቀሩ እቃዎች) እንዴት እንደሚስተካከል ያወኩትን ለማሳወቅ እሞክራለሁ እናንተም ወደ ቻናላችን ተቀላቀሉን

💸💰💳ህንድ ውስጥ አብዛኛው ቴሌግራም ተጠቃሚ እየሰራው ያለው የየONLINE JOB ነው በወር ውስጥ እንደ እኛ ጥንካሬ በርካታ ዶላር ይታፈስበታል ከስር ያለውን ሊንክ በመንካት ብቻ ይሞክሩት ከዛም START በሉት ያላጣራሁትን አላወራም ይቺን ተጭነው ቤተሰብ ይሁኑ 👇👇👇

D stands for “liquid crystal display” and technically, both LED and LCD TVs are liquid crystal displays. The basic technology is the same in that both television types have two layers of polarized glass through which the liquid crystals both block and pass light. So really, LED TVs are a subset of LCD TVs. "Technically ፣ ሁለቱም LED እና LCD TVs Liquid crystal display (ፈሳሽ ክሪስታል ማሳያ) ናቸው።" LED, which stands for “light emitting diodes,” differs from general LCD TVs in that LCDs use fluorescent lights while LEDs use those light emitting diodes. Also, the placement of the lights on an LED TV can differ. The fluorescent lights in an LCD TV are always behind the screen. On an LED TV, the light emitting diodes can be placed either behind the screen or around its edges. The difference in lights and in lighting placement has generally meant that LED TVs can be thinner than LCDs, although this is starting to change. It has also meant that LED TVs run with greater energy efficiency and can provide a clearer, better picture than the general LCD TVs. LED TVs provide a better picture for two basic reasons. First, LED TVs work with a color wheel or distinct RGB-colored lights (red, green, blue) to produce more realistic and sharper colors. Second, light emitting diodes can be dimmed. The dimming capability on the back lighting in an LED TV allows the picture to display with a truer black by darkening the lights and blocking more light from passing through the panel. This capability is not present on edge-lit LED TVs; however, edge-lit LED TVs can display a truer white than the fluorescent LED TVs. Because all these LCD TVs are thin-screen, each has particular angle-viewing and anti-glare issues. The backlit TVs provide better, cleaner angle viewing than the edge-lit LED TV. However, the backlit. LED TV will usually have better angle viewing than the standard LCD TV. Both LED and LCD TVs have good reputations for their playback and gaming quality.።

1⃣LCD Monitor ወይም ቲቪ ምንድን ነው? 2⃣LED Monitor ወይም ቲቪ ምንድነው??

https://get.cryptobrowser.site/10135959?s=tg&f=android&og=m13 How to use your PC wisely? Let it earn some BTC for you! CryptoTab Browser is the easiest way to start mining and make your path to the world of cryptocurrency. Completely free and ready for instant mining — try it and you’ll see the result!

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ኢብራሂም ነኝ ክፍል ሁለትን ታደሙልኝ ። ከቦታ ቦታ ወድቀውም ሆነ በአስቸጋሪ ሁኔታ ተገኝተው በመነሳት አሁን በገበያ ላይ ከሚገኙ የተንቀሳቃሽ ስማርት ስልኮች የላቀ አቅም እንዳለቸው ያስመሰከሩ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን መያዝ፡፡ የስማርት ስልከ መያዝ ወቅቱ ያፈራቸውን መረጃዎች በአቅራቢያችን እንዲኖሩንና ሌሎች ተጨማሪ ነገሮችን ያለ ብዙ ድካም ለማግኘት ስለሚረዱን በጥንቃቄ ከተያዙ የማይከፉ ቢሆንም ከላይ በተጠቀሱት ምክኒያቶች አብዝቶ መጠቀሙ ጉዳቱ የሚያመዝን መስሎ ስለሚታየን በተገልጋዮች ዘንድ የሚገኘውን የሲምካርድ ቁጥር በኖርማል ሀንድሴትዎ፣ ለግላዊ ጉዳይ የሚጠቀሙበትን ሲም ካርድዎ ደግሞ በስማርት ስልክዎ በማድረግ የተለመደ ህይወትዎን ከቢዝነስ ህይወትዎ በተለያዩ ሁለት ሲም ካርዶች አማካኝነት እንዲመሩ እንመክራለን፡፡ -አንድ ባለ አንድ አውትፑት (ገመድ ተቀባይ) LNB እና አንድ ባለ ሁለት አወትፑት LNB ዎች ብንይዝ ለስራ በምንጓጓዝበት ወቅት የተቃጠሉ፣ ጉዳት የደረሰባቸውን፣ የደከመ የምስል ጥራት የሚያወጡ LNB ዎችን ለመለየትና በምትኩ በመግጠም ከአላስፈላጊ ድካምና ወጪ ራሳችንን ማዳን እንችላለን፡፡ ያስታውሱ ሁሌም የተቃጠለ፣የተጎዳ ወይም የደከመ የምስል ጥራት የሚያወጣ LNB በአዲስ በምንተካበት ወቅት ወዲያውኑ በምትኩ ለራሳችን መግዛት እንዳለብን በፍፁም መዘንጋት የለብንም፡፡ -በቤት ኪራይ ምክኒያት ሰዎች ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱ ከዚህ ቀደም የነበረው የዲሽ ገመድ ሳህኑን ከምንተክልበት አዲስ ቦታ ራቅ ያለ ሊሆን ስለሚችልና በተለያየ አጋጣሚ ገመዶች የመተጣጠፍና የመቀጥቀጥ አደጋዎች ስለሚደርስባቸው ለመቀጠያና ለመተኪያ የሚሆን ከ20 ሜትር ያላነሰ የዲሽ ገመድ ለአያያዝ አመቺ በሆነ መልኩ መያዝ፡፡ ከገመዱ የሚጠቀሙትን በሜትር አስልተው ከሙያ ዋጋ ክፍያዎ ጋር ማስከፈልዎንና በምትኩም አዲስ ገመድ መግዛትን አይርሱ፡፡ -ነፃ የኳስ ቻናሎችን ወይም ሁለት LNB የሚጠይቁ ስራዎችን በምንሰራበት ወቅት ለተጨማሪው LNB ትክክለኛ መቀመጫ ቦታ ይሆን ዘንድ በጋራጅ ቤቶች ለዚሁ አገልግሎት የተሰራ ዘንግ (የገበያ ስሙም ዘንግ ነው) መግዛትና መያዝ፡፡ በተለያዩ ቦታዎች ለማጠናከሪያነት ሊጠቅሙን የሚችሉ የተለያዩ አይነት ሚስማሮችን መያዝ፡፡ -ገመዶች እንዳይጠላለፉና ውበታቸውን ጠብቀው በግድግዳዎች ላይ እንዲሄዱ የሚያስችሉንን ትክክለኛ መጠን ያለቸውን የገመድ ክሊፖች መያዝ፡፡ የገመዶችን ርዝመት ለመለካትና ከዚያም በላይ ለተጨማሪ የሚለኩ ነገሮች የሚያገለግል ሜትር፡፡ – የሳህኑን አናትና እግር ካሰርንና እንዳይነቃነቅ ካጠባበቅን በኋላ በትንሽ መነካካት ኳሊቲያቸው ሊወርዱና ሊወጡ የሚችሉ ሳህኖች በንፋስ ሀይል በቅርቡ ሙሉ በሙሉ ኳሊቲያቸው ሊወርድ ስለሚችል ይህንን እንዲቋቋምልን የሚያስችለንን ሽቦ ከተመታው የቆርቆሮ ሚስማር ጋር መወጠር፡፡ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች ሊበዙ ስለሚችሉ የተጠቀለለ ሽቦ መያዝ፡፡ -ከላይ የተጠቀሱትን መሳሪያዎችና አንዳንድ ከቦታ ቦታ ስንንቀሳቀስ የሚያስፈልጉንን የግል ንብረቶቻችን መያዣ የሚሆን የጀርባ ሻንጣ ሊኖረን ይገባል፡፡ ከዚህ የጀርባ ሻንጣ አንድ በአንድ የምናወጣቸውን የተለያዩ መሳሪያዎች ስራችንን ከጨረስን በኋላ መልሰን ማስገባታችንን ሁሌም ቢሆን ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡ -ለማስተካከል ወይም አዲስ ለመትከል እየተዘጋጀንለት ያለናቸው ሪሲቨሮች አጠቃቀማቸውን በራሳችን ፍለጋ ማግኘት ወይም አሰራሩ የተዋሀደው የዲሽ አሰሪ አካል ትብብር መጠየቅ (ብዙ ጊዜ እጅግ ያረጁና አጠቃቀማቸው ግራ የሚያጋባ ሪሲቨሮች ይገጥሙናል በዚህ ጊዜ ማድረግ የሚገባን አንድ ነገር ቢኖር መጀመሪያ ራሳችንን ማረጋጋት ሲሆን ሲቀጥል እንደየ እድሜያቸውና እንደኛ አቅም፣እና እንደየ ፋብሪካ ስሪታቸው የሪሲቨሮቹን አሰራር መረዳት ሲሆን ብዙዎቹ ቆየት ያሉ ሪሲቨሮች በመጠኑ አዳጋችና ለመረዳት ሰፋ ያለ ጊዜን የሚወስድ ሶፍትዌር የተጫነባቸው ናቸው ይሁንና ያለንን መጠነኛ የእንግሊዝኛ አቅም በመጠቀም እኚህን ሶፍትዌሮች በቀላሉ ከ 5 ደቂቃ ባለነሰ መልኩ ከራሳችን ጋር ማዋሀድ እንችላለን፡፡) ይህንንም ድርጊት ማከናወን የአሰራር ፍጥነታችንን እጅግ የሚያዳብረው ይሆናል፡፡ -በተለያዩ ምክኒያት የሚፈጠሩ የምስል ጥራት መጓደል፣ የኳሊቲ ማነስና ሎሎች ተዛማች ችግሮችን በፍጥነት ለመለየት የሚያስችል ከተለያዩ ምንጮች የተገኘ እውቀትና ራስን ሙሉ በሙሉ ከዘመኑ ጋር እኩል ለማድረግ የሚያስችል ተጨባጭ ክህሎት ለማዳበር ራስን በተለያየ መልኩ ማብቃት፡፡ -የዲሽ ስራ በባህሪው ከቦታ ቦታ መዘዋወርን የሚጠይቅ ስለሆነ ሁሉም ቦታዎች ላይ ደግሞ በሚኒባስ፣ በባጃጅ ወይም በጋሪ መድረስ ስለማይቻል የራሳችን የሆነ ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀሻነት የምንጠቀምበት ሞተር ሳይክል ቢኖረን ጥሩ ነው፡፡ አቅማችን ሞተር ለመግዛት የማይፈቅድ ከሆነ ደግሞ በኤሌክትሪክ የሚሰራ ቻርጅ ከተደረገ በኋላ ብዙ ኪሎሜትሮችን መጓዝ የሚችል ካቴና በተመታ ቁጥር ተጨማሪ ሀይል የሚሰጥ (Scooter) በመባል የሚታወቅ መንቀሳቀሻ በመግዛት መኪናና ባጃጆች ሊገቡባቸው የማይችሉ ጉራንጉሮች ውስጥ ሁሉ ሳይቀር የተቀላጠፈ ስራ መስራት ይቻላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ያሉበት ከተማ ዳገት የመይበዛበት ከሆነ ብስክሌት በመግዛት የፈለጉበት ቦታ ድረስ በመሄድ ስራዎን ማከናወን ይችላሉ፡፡ ማንኛውም የዲሽ ባለሞያ ለስራ በሚንቀሳቀስባቸው ጊዜያት ሊወስዳቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎችና የስነምግባር መመሪያዎች -ከምንም ከማንም በላይ ለራሳችን ህይወት ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ማድረግ፡፡ በመሰላል በምንወጣጣበት ወቅት ከሁሉም አስቀድመን የመሰላሉ ማንኛውም አካል ለአደጋ የሚያጋልጥ አለመሆኑን በተደጋጋሚ ማረጋገጥ፡፡ መሰላሉ የሚቆምበት ቦታ የተደላደለ መሆኑን ማረጋገጥ፡፡ በምንወጣበትና በምንወርድበት ጊዜ መሰላሉ ወደ ጎንና ወደ ኋላ እንዳይንሸራተት በሰው ማስያዝ፡፡ የተበላሹ የሚነቃነቁ፣ በርጥበት የተጎዱና በምስጥ የተበሉ መሰላሎች በሚኖሩበት ወቅት ከጎረቤት የተሻለና አስተማማኝ መሰላል እንዲመጣልን የዲሽ አሰሪዎችን መልካም ትብብር መጠየቅ፡፡ አስተማማኝ መሰላሎች በማይገኝበት ወቅት እራስን አደጋ ውስጥ ከማስገባት በፊት ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት አስተማማኝ መሰላል ሲገኝ ስልክ እንዲደወልልን ማድረግ፡፡ ብዙ የሆነ መውጣትና መውረድ ለአደጋ እንዳያጋልጠን ነገሮችን አስቀድመን መሬት ላይ መጨረስ ለምሳሌ የዲሹን እግር ከጣውላዎች ጋር መምታትና የመሳሰሉት፡፡ -እንደሚታወቀው የአብዛኞቻችን የሀገራችን ቤቶች የተሰሩት ከእንጨትና ከቆርቆሮ በመሆኑና የሚተከሉት የዲሽ ሳህኖችም ምርጥ ኳሊቲ እንዲገባልን ሲባል ጣራ ላይ በመሆናቸው ጣራ ላይ ከወጣን በኋላ አግዳሚ ማገር ላይ የተመቱትን የቆርቆሮ ሚስማሮች እንደ አመላካች በመጠቀም በጥንቃቄ መራመድ ይኖርብናል፡፡ ለሳህኑ እግር መቀመጫ ቦታ ስንመርጥም ሳህኑ እንዳይንቀሳቀስ ለማጠናከር የምንጠቀምበትን ድንጋይ ወይም ብሎኬት ጫና መቋቋም እንዲችል አግዳሚ ማገሩ ላይ መሆን ይኖርበታል፡፡ ሌላው መውሰድ ያለብን ጥንቃቄ የቆርቆሮ ጠርዞችን የተመለከተ ሲሆን በምንም አይነት መልኩ እንዲቆርጡን መፍቀድ የለብንም፡፡

ዲሽ አተካከል ለፍፁም ጀማሪዎችና ለተካኑ የዲሽ ቴክኒሺያኖች ሰላም ጤና ይስጥልኝ ኢብራሂም ነኝ ይህ ዛሬ ይዘን የመጣነው መረጃ በተለይ ለፍፁም ጀማሪዎች ከራሳቸውና ከዲሽ ሰሪ አጋሮቻቸው ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች ከሚወስዷቸው ትምህርት ተጨማሪ የተወሰነ ግን መሠረታዊ የሆነ ጠቀም ያለ መረጃ ነው ፡፡ ብዙ ሰላምታና ማብራሪያ ሳነበዛ ወደሚያጓጓው ትምህርታዊ ፅሁፋችን እናምራ፡፡ ዲሽ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመትከልና ለመግጠም የተሰማሩ የዲሽ ባለቤት ግለሰቦች ፡ ጀማሪ ወይም ልምድ ያላቸው ቴክኒሺያኖች መያዝ የሚገባቸው የሳተላይት ዲሽ መግጠሚያ መሳሪያዎችና አጠቃቀማቸው፡- – ማንኛውም የሳተላይት ዲሽ ቴክኒሺያን በቅድሚያ የሚገጥመውን የሳተላይት ዲሽ አይነትና አቅጣጫ በአትኩሮትና በበቂ ሁኔታ ከምንም በላይ መገንዘብ ይኖርበታል፡፡ – በአብዛኛው በሃገራችን የሚገጠሙና ስርጭታቸው በሰፊ ከሚገኙ የሳተላይት ዲሽ ቻናሎች ለመጥቀስ ያህል በየቤታችን የሚገኘውና እጅግ ብዙ ተጠቃሚዎች ያሉት የናይልሳትና ከ 5 እና 6 አመታት በፊት ሁሉም የሀገራችን ብሎም ተወዳጅ የውጭ ቻናሎች ይገኙበት የነበረው አሁን በአረቡ አለም ዘንድ ብቻ በስፋት በጥቅም ላይ የሚውለው የአረብሳት ቻናል እና ነፃ የኳስ ቻናሎች ማለትም ቨርዛሽ ቲቪ፣ ቶሎዶ ቲቪ እና ሌሎችን የእንግሊዝና ስፔን ላሊጋ ብሎም፣ የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎችን የሚያስተላልፉ ቻናሎች የሚገኙባቸው የያህሳት ቻናል ዲኤስቲቪ እና የ ፓወር ቪዩ ቻናሎች የሚገኙ ሲኖን እንደ አንድ የሳተላይት ዲሽ ጀማሪም ሆነ የተካነ ቴክኒሺያን ማወቅ ከሚገቡን ነገሮች መካከል የእያንዳንዱን ቻናል አቅጣጫና አቀማመጥ ነው፡፡ እነዚህን ቻናሎች በአግባቡ ለመትከል እንዲረዳን የአቅጣጫ ጠቋሚ ማለትም ኮምፓስ መጠቀም በብዛት የሳተላይት ዲሾችን ለመግጠም ጥቅሙ እጅግ ከፍ ባለ ደረጃ የሚረዳን ሲሆን አጠቃቀሙን በቀጣይ ፅሁፋችን ከፍተኛ አትኩሮት ወደምንሰጥበት መሰረታዊ ፅንሠ ሃሳቦች ጋር ይዘን በሰፊው እንመለስባቸዋለን፡፡ – ማንኛውም የሳተላይት ዲሽ ለመትከል የተዘጋጀ ጀማሪም ሆና የተካነ ባለሙያ መያዝ ያለባቸው እጅግ መሰረታዊና የምንጊዜም አጋዠ መሳሪያዎች መካከል የሚከተሉትን መዘርዘር ይቻላል፡፡ በተለምዶ አስር ቁጥር ብለን የመንጠራው የብሎን መፍቻ ለባለ 60 ሴንቲሜትር ሳህንና (ለ 90 ሲንቲሜትርና ከዛ ክፍ ለሚሉ የዲሽ ሳህኖች፣ 10 ቁጥርን ጨምሮ እንደአስፈላጊነቱ 10፣11፣12፣ እና ከዚያ በላይ ያሉት መፍቻዎች በተናጠል ወይም (በህብረት) ማለትም በአንድ የብረት ዘንግ ሶስቱንም በስሩ የያዘ መፍቻ ወይም ከአነስተኝ እስከ ከፍተኛ የብሎን አናት ቁጥሮችን በማጥበቅና በማላላት የምንጠቀምበት በተለምዶ ካበ እንግሊዝ (Wrench) ብለን የምንጠራውን ባለ አንድ ወጥ በጣት በማሽከርከር እንደ ብሎኑ አናት መጠን የሚጠብና የሚሰፋ መፍቻ በቅርብ ከሚገኝ የህንጻ መሳሪያ መደብር መግዛትና ሁሌም ዲሽ ለመትከልም ሆነ ለማስተካለል በምንቀሳቀስበት ጊዜና ቦታ መያዝ፡፡ የሚቻልና አቅማችን ከፈቀደ (በተለይ ዲሽ መትከልን እንደ ዘላቂ ሙያ ለያዡ) ሙሉ በሙሉ ዲጂታል የሆነ የሳተላይት ማሰሻ ወይም Finder በመግዛት ለአስፈላጊው ስራ መዘጋጀት፡፡ አቅም የማይፈቅድ ከሆነም ቆየት ያለውን ነገር ግን ላዩ ላይ ዲጅታል ፋይንደር የሚል ፅሁፍ ያለውንና ከ 0 እስከ 10.5 ዲ.ቢ የሚለካውን ባለ ሜትሩን የሳተላይት ዲሽ ማሰሻ ከ 400 ብር ባልበለጠ ገንዘብ በአካባቢያችን በሚገኙ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መሸጫ መደብሮች መግዛትና መያዝ፡፡ ለስራችን ቅልጥፍና የሚረዳን የመጀመሪያው አይነት ዲጅታል ፋይንደር ሲሆን የራሱ የሆነ የባትሪ ሀይል ስላለው መብራት እንኳን ቢጠፋ ጣራ ላይ ባለንበት ስራችንን ለመጨረስ ያስችለናል በተጨማሪም የፋይንደሩ ሰሌዳ ላይ ልክ ሪሲቨሩ ላይ እንደምናየው ሲግናልና ኳሊቲ ማንበቢያ ስላለውና የምንፈልጋቸውን የቻናል ፍሪኩዌንሲዎች ሞልቶ ስለሚይዝልን ስራችንን እጅግ ፈጣን ያደርግልናል፡፡ እጅግ በጣም የሚያስፈልገን ከሆነ ደግሞ በአንገት የሚንጠለጠል የምናስሰውን ቻናል በፋይንደሩ ሰሌዳ ላይ ልክ እንደ ቴሌቪዥን ምስሉን በጥራት የሚያሳይ ድምፁንም በጥራት የሚያሰማ ሲግናልና ኳሊቲ ማንበቢያ ያለው እጅግ ዘመናዊ የሆነ ፋይንደር ገዝተን ስራችንን በጣም በዘመናዊ መልኩ ማካሄድ እንችላለን፡፡ -ከ ፋደራችን አይነትና አቅም ጋር የሚሄድ ተወርዋሪ ገመድ ከዲሹ ጋር ከሚመጣው RG-6 Coaxial Cable (የዲሽ ገመድ) ወይም ከቴሌቪዥን የውጭ አንቴና ጋር ከሚመጡ በውስጣቸው ቀጭን የኮፐር ወይም መዳብ ዘንግ ከያዙ ገመዶች ቆርጦ ርዝመቱ ከ 60 ሳንቲሜትር ያላነሰ ተወርዋሪ ገመድ (Jump Caple) በሁለቱም በኩል የሴቴ ወይም (Female Connector) የያዘ ገመድ ማዘጋጀት፡፡ የገመዱ ጫፍ አንደኛው ወደ የዲሹ ጭንቅላት (LNB) ላይ የሚታሰር ሲሆን ሌሌኛው ጫፍ ፋይንደሩ ላይ (To LNB) በሚለው አቅጣጫ የሚታሰር ይሆናል፡፡ የፋይንደርን አጠቃቀም ወደ ፊት ሰፋ ያለ ትንታኔ የምንሰጥበት ስለሆነ ለዛሬው እዚህ ላይ እንግታው፡፡ -ተወርዋሪ ገመድ ወይም ከዲሹ ጋር አብሮ የሚመጣውን ገመድ ጫፎች ለመላጥ፣ Female Connector ችን ለማያያዝ፣ ገመዶችን ለማሳጠር ወይም ለመቀጠልና ለማስረዘም እንዲረዳን አንድ ጥሩ የሆነ ፒንሳ ያስፈልገናል፡፡ በአቅራቢያችን ማግኘት የምንችል ከሆነ ደግሞ ኬብል ስትሪፐር ወይም ኬብል ከተር መግዛት ስራችንን ቀልጣፋ ያደርግልናል፡፡ -የዲሹን LNB ማቀፊያ ለማጥበቅና ለማላላት ብሎም LNB ለመቀየርና አዳፕተሮችን ለመፈታታትና ለማጥበቅ ሊረዳን የሚችል በሁለቱም በኩል ሲቀያያር ጠፍጣፋና ባለ መስቀል አናት የሚሰጥ ካቻቢቴ መያዝ ይጠበቅብናል፡፡ -የዲሹን ሳህን እግር በሁለት አቅጣጫ ረዘም ካሉ ጣውላዎች ጋር መምቻና የዲሹን ገመዶች በየግድግዳው በኬብል ክሊፕ ለማያያዝና ሌሎች ጠንከር ያለ ሀይል የሚጠይቁ ስራዎችን ለማከናወን የሚጠቅመንን አጠርያለ የፕላስቲክ እጀታ ያለው መዶሻ ያስፈልገናል፡፡ ከላይ የጠቀስናቸው መሳሪያዎች እጅግ መሰረታዊና አስፈላጊ ሲሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ደግሞ አስፈላጊነታቸው በጣም ብዙም ባይሆን እንኳን መያዛችን ግን ጥቅሙ እጅግ ያመዘነ ይሆናል፡፡ -በማንኛውም ሁኔታ ቢሆን ሊጠቅሙን ስለሚችሉ በርከት ያሉ የ Female connector, Audio Video Splittor Conector ንና ከሁለት ያላነሱ Disqe Switch መያዝ፡፡ -እንደየ ፍላጎታችን የምንሞላውን ሳተላይት መሠረት ያደረጉ የተለያዩ ፊሪክዌንሲዎችና፣ ፖላራይዜሽሮች ዝርዝር በጥንቃቄ ለማወቅ ይረዳን ዘንድ እና አዳዲስ መረጃዎችን በማይረሱ መልኩ ለመፃፍና በአስፈላጊ ጊዜ ዋቢ ለማድረግ ለመፃፊያነት የሚረዱን መጠናቸው እንደየ ግል ፍላጎታችን በሚወሰኑ ማስታወሻ ደብተሮች ላይ ማስፈር፡፡ ለዚህም ይረዳን ዘንድ ለአያያዝ አመቺ የሆኑ ማስታወሻ ደብተሮችን በአቅራቢያችን ከሚገኙ የፅህፈት መሳሪያ መደብሮች ገዝቶ መያዝ፡፡ -የስራው ባህሪ ሆኖ ብዙዎች ተገልጋዮችን የምናገኛቸው በተንቀሳቃሽ ሞባይል ስልኮች ከመሆኑ የተነሳ የኔትወርክ ግኑኝነት በማይኖረበት ቦታ የኔትወርክ ግኑኝነትን አስሰውና ፈልገው የሚያመጡልንን ዘመኑ ኖርማል ሀንድሴት ብሎ የሚጠራቸውን ግን በባትሪ ቆይታቸውና

Kal begebahut meseret befoto amtchalew

30 ለማመን የሚከብዱ የአለም እውነታዋች 😱😱😱😱😱😱😱😱😱😱😱😱😱😱😱😱 1★ ወፎች አይሸኑም 2★ጉንዳኖች ፈፅሞ አይተኙም፤ሳንባ የላቸውም፤ሰራተኛ ጉንዳን እስከ 7 ዓመት ሊኖር ይችላል ንግስቶ ግን እስከ 15 ዓመት ልትኖር ትችላለች:: 3★ሻርክ ብቸኛው የማይታመም እንሰሳ ነው ምንም አይነት በሽታ አያጠቃውም ካንሰርን ጨምሮ:: 4★ፈረሶች እና ላሞች ቁመው ነው እሚያንቀላፉት:: 5★የማር ንብ ሁለት ሆድ ሲኖራቸው አንዱ ለማር ሲሆን ሁለተኛው ለሚመገቡት ምግብ ማስቀመጫ ያገለግላቸዋል:: 6★ትልቁ ነጭ ሻርክ ከሶስት ወር በላይ ሳይበላ መጎዝ ይችላል:: 7★አብዛኞቹ ዝሆኖች በክብደት ከስማያዊ አሳነባሪ(Blue whale) ምላስ ያንሳሉ:: 8★በረሮ በርሀብ እስኪሞት ድረስ ለሳምንት ያህል ጭንቅላቱ ተቆርጦ በሂወት መቆየት ይችላል:: 9★የአህያ አይን አቀማመጥ በአንድ ግዜ አራቱንም እግሮች ማይት ያስችሉታል:: 10★ዶልፊን ውሀ ውስጥ ከ24ኪ.ሚ ርቀት ያለ ድምፅ በቀላሉ መስማት ይችላል:: 11★የወባ ትንኝ(Mosquito) 47 ጥርስ አላት:: 12★ማንኛውም ሁለት የሚዳ አህያ(zebra) እንድ አይነት መስመር አይኖራቸውም:: 13★ቢራቢሮ የሚቀምሱት(taste) በሆላ እግራቸው ነው:: 14★የወንድ ሸረሪት የወሲብ አካል በአንዱ የእግሩ ጫፍ ላይ ይገኛል:: 15★ንቦች አምስት አይን አላቸው:: 16★አሳማ በተፈጥሮ(physical) ወደ ሰማይ ማየት አያስችለውም:: 17★አይጥ ከተራበች የራሶን ጅራት ትበላለች 18★ ለሚስቱ ታማኝ የሆነ እንስሳ ቀበሮ ብቻ ነው 18★ሰማያዊ አሳነባሪ (Blue whale) በመጠን እስካሁን በአለማችን ከነበሩ እና ካሉ እንሰሳዎች ትልቁ ነው:: 20★ የለሌት ወፍ ብቸኛዋ ከአጥቢዎች መብረር የምትችል ሲሆን የእግር አጥንቶቾ ከመቅጠናቸው የተነሳ መብረር እንጂ መራመድ አትችልም:: 21★የለሌት ወፍ ምንግዚም ከዋሻ ሲወጡ ወደ ግራ ይበራሉ:: 22★እባብ አይኖቹ ቢከደኑም በአይኖቹ ቆብ ማየት ይችላል:: 23★ወንድ የወባ ትንኝ አይናደፍም ሴቶ ብቻ ናት መናደፍ የምትችለው:: /femal Anofiles mosqto/ 24★ የዱር አይጥ (Rat) በፍጥነት መራባት የሚችሉ ሲሆን በ18 ወራት ብቻ 2 አይጦች 1 ሚሊዮን ዘመዶችን ማፍራት ይችላሉ:: 25★አንድ ንብ አንድ የሾርባ ማንኪያ ማር ለማዘጋጀት ከ 4000 በላይ አበቦችን መጎብኝት አለባት :: 26★ቀንድ አውጣ ለ3 አመት መተኛት ይችላል:: 27★ አንድ ላይ የተያያዘ የሸረሪት ድር ተመሳሳይ ወፍረት ካለው አንድ ላይ ከተያያዘ የብረት ሺቦ ይጠነክራል:: 28★ዝሆኖች ከ3ማይል ላይ ያለ ውሀ ማሺተት ይችላሉ:: 29★ኦይሰትር(Oyster) የተባለ የአሳ ዝርያ ከአንዱ ፆታ ወደ ሊላኛው እንዲሁም ወደ ነበረበት ለወሲብ በሚመቸው ፆታውን መቀየር ይችላል:: 30★በየአመቱ 1/3 የሚሆነው የአለማችን ሰብል በተባይ/ነብሳት ይወድማል:: =>ስንት ቁጥር አግራሞትን ፈጠርባችሁ ?? የተመቸው ሼር፣ላይክ እንዳይርሳ 🎭🎭🎭🎭🎭🎭🎭🎭🎭🎭 ..................................................... #ጤናማና_ደስ_የሚል_ቀን _ይሁንላችሁ፡፡ Join @ysakelectronics

ኮምፒዉተር የሚዘጋበት ወይም ክራሽ የሚያደርግበት 5 ምክንያቶች 1. የሀርድዌር መቃረን ለ Windows ክራሽ የማድረግ ዋነኛው ምክንያት የ Hardware መቃረን ነው፡፡እያንዳንዱ Hardware ክፍሎች ለመግባባት IRQ(interrupt request channel) ያስፈልጋቸዋል፡፡ እነዚህ IRQ ለየሀርድዌሩ የተለዩ ወይም የተነጠሉ መሆን አለባቸው፡፡ ለምሳሌ አንድ ፕሪንተር IRQ 7 ሲኖረው ኪቦርድ ደግሞ IRQ 1፡፡እያንዳንዱ ሀርድዌር የራሱ የሆን IRQ ለመያዝ ጥረት ያደርጋል፡፡ ግን ብዙ የሀርድዌር እቃዎች ስንጠቀም ወይም የሀርድዌሩ ሶፍትዌር በስርዓት ካልተጫነ ሁለት ሀርድዌሮች ተመሳሳይ IRQ ሊጋሩ ይችላሉ፡፡ በዚህም ሰዓት ሁለት የሀርድዌር ዕቃዎች በተመሳሳይ ሰዓት ለመጠቀም ስንሞክር ክራሽ ሊከሰት ይችላል፡፡ 2. የተበላሸ ራም ራም Ram (random-access memory) ችግሮች ዋናው የብሉ እስክሪን ኦፍ ዴዝ (blue screen of death) ዋና መንስኤ ሲሆን የሚያሳየው መልእክት ፋታል ኤክሰብሽን ኢረር ( Fatal Exception Error) የሚል ነው፡፡ ፋታል ኢረር የሚነግረን አሳሳቢ የሀርድዌር ችግር አለ ማለት ነው፡፡ አንዳንዴ የሀርድዌር ክፍል ስለተጎዳ መቀየር እንዳለበት ይናገራል፡፡ በራም የሚመጡ ችግሮች ብዙ ግዜ የራሙ ከኮምፒዉተሩ ጋር ሳይጣጣም ሲቀር ነው፡፡ ይህም ማለት ለኮምፒዉተር የራም ስሎት ጋር ሳይመጣጠን ሲቀር ፤ የራሱ ያልሆነ ሞዴል ስንጠቀም እና የተለያየ አይነት ራም በአንድ Computer ውስጥ ስንጠቀም ነው፡፡ለምሳሌ 70ns ለይ 60ns ራም ስንጠቀም ኮምፒተሩን ፍጥነት ይቀንሳል፡፡ይሄ ደግሞ ራሙን ከአቅሙ በላይ ይጫነዋል በዚህ ግዜ window ክራሽ ያደርጋል፡፡ 3. ባዮስ ሴቲንግ( BIOS settings) እያንዳንዱ ማዘር ቦርድ ሲመረት የራሱ የሆነ የተለያዩ ቺፕሴት ሴቲንግ አብሮት ይጫናል፡፡ እነዚህን ሴቲንግ ለመጠቀም በኮምፒውተራችን ኪቦርድ ላይ F2 ወይም F10 (እንደ ኮምፒዉተሩ ይለያያል) ኮምፒዉተሩ ስንከፍት ከጥቂት ሰከንድ በኻላ በመንካት ሴቲንጉን አክሰስ ማድረግ ይቻላል፡፡ ነገር ግን አንዴ ባዮስ ዉስጥ ከገባን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ ማንኛውንም ሴቲንግ ከመቀየራችን በፊት ፎቶ ወይም ወረቀት ለይ ሴቲንጎቹን ማኖር አንድ ያበላሸነው ነገር ካለ በቀላሉ መቀየር ያስችለናል፡፡ብዙን ግዜ የባዮስ ችግር የራም ላተንሲ ችግር ነው፡፡ የድሮ ኮምፒዉተር ራም ላተንሲ 3 ሲሆን የቅርብ ግዜ ራሞች ደግሞ ላተንሲ 2 ናቸው፡፡ ይሄንን ሴቲንግ በምንቀይርበት ጊዜ ኮምፒዉተሩ ክራሽ ያደርጋል ወይም ፍሪዝ ይሆናል፡፡ 4. ቫይረስ ቫይረሶች የኮምፒዉተር ፕሮግራም ሲሆኑ እራሳችውን በማብዝት ወይም ኮምፒዉተር ፋይሎች ላይ በማጣበቅ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ ቫይረሶች የትእዛዞች ስብስብ ሆኖ እራሱን በሌላ የኮምፒዉተር ፕሮግራም ያጣብቃሉ(ብዙ ግዜ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን)፡፡ ኮምፒዉተራችን ውስጥ ቫይረስ ሲያጠቃ የኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ፋይል የመቀየር ሀይል ስላለው ኮምፒዉተሩን ክራሽ ወይም ፍሪዚ ሊያረግ ይችላል፡፡ 5. መጋል በኮምፒዉተራችን ዉስጥ ካሉ ሀርድዌሮች በጣም አስፈላጊው እና ዋናው ሲፒዩ ነው፡፡ ሲፒዩ በኤሌትሪክ ሃይል የሚሰራ ሲሆን ካለው ውስብስብ የትራዚስተር ብዛት አማካኝነት የሚፈጥረው ከፍተኛ ሙቀት ሲፒዩን ሊያበላሸው ወይም ከጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ሲፒዩ ብዙ ጊዜ ከማቀዝቀዣ ቬንትሌተር ከኮምፒዉተራችን አንድ ላይ ይመጣል፡፡ እነዚህ ቬንትሌተር ከተበላሹ ወይም ሲፒዩ ካረጀ የኮምፒዉተራችን ሲፒዩ መጋል ይጀምራል፡፡ ይህ ደግሞ በኮምፒዉተራችን ላይ የከርንል ኢረር ያስከትላል፡፡ ይሄ ችግር ብዙ ጊዜ የሚታየው በኦቩር ክሎኪንግ ጊዜ ነው፡፡ ይህ ማለት ሲፒዩን ከሚገባው በላይ በማሰራት ወይም ከፍተኛ ፍጥነት እንዲገባ በማድረግ ነው፡፡ሲፒዩ በጣም ሲግል ኮምፒዉተራችን ሳናስበው እራሱን ይዘጋል ወይም ክራሽ ያደርጋል፡፡ @ysakelectronics