cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Fun play mooder

Yobiity

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
142
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

إظهار الكل...
Awash Bank

🌟በዚህ Bot 25 ሰዉ ወደ ቦቱ በመጋበዝ የ500 ብር ከፈለጋችሁ ሞባይል ካርድ ካልፈለጋችሁ ደግሞ በባንካችን ተሸላሚ መሆን ይችላሉ። 💞መልካም እድል💞 💎Awash Bank💎

ዞራ ዞራ ያሬድ ነጉ @CARROTMUSIC.mp34.10 MB
አታምሪም! ግን.... (በላይ በቀለ ወያ) . . . "ፉንጋ አይፈቀርም"- የተባለ ይመስል ሁሉ ፍቅረኛውን.... "ቆንጆ ነሽ " - "ውብ ነች" ሲል ያፈቀራትን ሴት.... መልክ አግንኖ ሲስል ወዝ አልባ ወዝሽን - ከማፍቀሬ አርቄ የፍቅርን ትርጉም - ከረቂቅ አርቅቄ ባታምሪም ወደድሁሽ.... ፉንጋ ተፈጥሮሽ ላይ - ፍቅሬን ብቻ አድምቄ። ......................................................... "ሳቅዋ እንደ በገና - የተደረደረው ወገብዋ እንደ ሰበዝ - ቅጥነት የተቸረው ከባላባት መሬት - የሰፋ ጭን ያላት ሰማይ የሚታከክ - ጉም ቁመት ያደላት" ሌላም ሌላም ነገር - እንደሚባልላት... እንደ ሌሎች ሴቶች ቆንጆ አይደለሽም! ግን አፈቅርሻለሁ ግን ደሞ አልዋሽም። ................................................... በቃ አንቺ ማለት.... ሁሉ ቆንጆ ሲሆን ሁሉ ሲባል ሸጋ በቆንጆ ተከብበሽ.. ምትኖሪ ደ-ሴት ነሽ ውበት ሳይጋርድሽ ምትታዪኝ ፉንጋ። ግን አፈቅርሻለሁ!!! ( በላይ በቀለ ወያ ) 💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
إظهار الكل...
Barcelona fans right now😂😂😂
إظهار الكل...
What the difference😂😂😂
إظهار الكل...
እስቲ የገጣሚ ሶሎሞን ሳህለን "ያማል" ወደ ወቅታዊ ጉዳይ እንከርብታት (በላይ በቀለ ወያ) #ሼር ይደረግ ። እና እንደ ነገርኩሽ ሀገር አሸባሪን ወታደሮች ቀጥሮ ፣ልክ እንደማስጠበቅ በቄሮዎች ዱላ ፣ ተመቶ እንደመውደቅ ሬሳ ሲጎተት ፣ አይቶ እንደመሳቀቅ ለውጡ "ውጡ" ብሎ ፣ ጎዳና እንደመውደቅ ስቃይ በበዛባት ፣ በዚች ቧልተኛ ሀገር ከዚህ የበለጠ ፣ የለም ሚያም ነገር። ዘረኝነት ያማል የመንጋ ፍርድ ያማል ሜንጫ ዱላው ያማል ምስኪን መግደል ያማል ጳጳስ ሲያለቅስ ያማል መስጂድ ማፍረስ ያማል ካህን ማረድ ያማል መንገድ መዝጋት ያማል የማይጎድል ፣ የዘር ጎርፍ ፣ የደም ማዕበሉ የዕንባ ቅጥልጥሉ ቤተስኪያን ማጋየት ፣ ንብረት ማቃጠሉ በድንጋይ ተወግሮ ፣ ድሀ መገደሉ ምን ብዬ ልንገርሽ ፣ ያማል ይሄ ሁሉ! ።።። እና እንደ ነገርኩሽ ቄሮ ሚወደውን ፣ ሌላው ካልወደደ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ፣ ሌላ ሀገር ከሄደ ነገር ተበላሸ ፣ ሀገር ተረበሸ ጭካኔና በቀል ፣ በግፍ ተወለደ መንገዱ ተዘጋ ፣ ምስኪኑ ታረደ ተርፎ ይህን ያየ ፣ጨጓራው ነደደ አንጀቱ በገነ የሚሆነው ሳይሆን የማይሆነው ሆነ ተከበብኩኝ ብሎ አንድ ሰው በቃዠው ፣ ከእንቅልፉ ሳይነቃ ሁሉም ተቀይሮ ፣ ተተካ በሲቃ ምንብዬ ልንገርሽ? ይሄም ያማል በቃ! ።። ፈንካች ተፈንካቹ ገዳዩና ሟቹ እብሪቱ ጥጋቡ ያለምንም ምክንያት ፣ የጠፋበት ግቡ ከመርፌ ቀዳዳ ፣ አእምሮ መጥበቡ በቆራጭ ሜንጫ ፊት ፣ እልፍ አንገት መቅረቡ ውል የሌለው ቅዠት ፣የተኛን መክበቡ እልፍ አእላፍ በደል ፣ መግለጫን ማጀቡ ደሞ ለሱ ግጥም ፣እናቱን መግለጫ ምንብዬ ልንገርሽ ፣ ይሄ ሁሉ ነገር ፣ ያማል እንደ ሜንጫ። ።።። እና እንደ ነገርኩሽ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግራ ወይ ቀኝ እግሩ የሌላ ሀገር ምድርን ፣ ልክ እንደረገጠ አንዱ መንገድ ዘጊ ፣ ወደኔ አፈጠጠ ዱላ የጨበጠ ፣ አንድ እጁን ሰንዝሮ በአንድ እጁ ደግሞ ፣ ድንጋይ ተወራውሮ ምን ልታዘዝ ይላል…?? ፣ ደረቱን ወጥሮ! ምን ልታዘዝ ይላል? እንዴት መንገደኛ ፣ መንገድ ዘጊን ያዛል?! ክፍት መንገድ ልዘዝ? አንዲት ሀገር ልዘዝ? አንድ ፍቅር ልዘዝ? አንድ ሰላም ልዘዝ? መታዘዝ መናዘዝ እርግማን የሆነው ለእከሌ ሊያሳልፍ እራሱ ግን የሚያልፍ ደረቱን ገልብጦ የኔን አንገት ቀብሮ ምን ልታዘዝ? ይላል ነፃ የሆነች ሀገር ከሠላም ጋር ልዘዝ? ዲሞክራሲያወዊ ሀገር ከፍቅር ጋር ልበል? ዋናውን አንድነት ከጥጋብ ልበል? ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል የላስቲክ አበባ ያርቲ ቡርቲ ስዕል የ`ጭቃ እሾህ ወግቶት እዥ ያወጣ ቁስል ትልቁ ነቀዝ ሰው የማንቀዙን ያህል ብዙ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል እና እንደ ነገርኩሽ ለውጡ ቀስ እያለ ነገሩን አመጣ አመጣ አብይ ገባ ወጣ ሰላም ቀረት መጣ መግለጫ በዝታለች እናቷን ስላልኳት ደግሜ ሰድቤ ሺህ አመት እንዳይገርማት እ. . . .ና. . . .ቷን ! እናቷን መግለጫ ተይ አታስለፍልፊኝ ይህም ያማል በቃ ግን ኢትዮጵያን ስወዳት ይህን ሁሉ ችዬ - ነው እኔ ም'ጠብቃት ቢሆንም ግን ያማል !!! @Yobitty
إظهار الكل...
•••!ያማል!••• . እና እንደ ነገርኩሽ የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ የነብሰጡርን ሞት አይቶ እንደመሳቀቅ ከተስፋ ጉልላት ተገፍቶ እንደመውደቅ ታምር በበዛበት በዚች ቧልተኛ አለም ከዚህ የበለጠ ምንም ህመም የለም አውቶብሱ ያማል ሚኒባሱ ያማል ላዳ ታክሲው ያማል የማይጎል የሰው ጎርፍ ደራሽ ማዕበሉ የዕንባ ቅጥልጥሉ ምንብዬ ልንገርሽ ? ያማል ይሄ ሁሉ እና እንደ ነገርኩሽ የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ የሚያፈቅሩትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ ነገር ተበላሸ ህመም ተወለደ ጨጓራ በገነ እሳት በዕንፋሎት መልክ በእህታ ተነነ የሚሆነው ሳይሆን የማይሆነው ሆነ ሁሉም ተቀይሮ ተተካ በሲቃ ምንብዬ ልንገርሽ? ይሄም ያማል በቃ ወጪ ተራማጁ አስመሳይ ሰጋጁ ፀሀዩ ዝናቡ የለምን ምክንያት የለምን ሰበቡ ተቆራጭ አበባ ሊቆረጥ ማበቡ ውል የለሽ ደመና ተራራ መክበቡ እልፍ አዕላፍ ኮከብ ጨረቃን ማጀቡ ደሞ ለሷ ግጥም እናቷን ጨረቃ ምንብዬ ልንገርሽ ይህም ያማል በቃ እና እንደ ነገርኩሽ ጉንጭ የማትሞላ ኬክ አስር ብር የሸጠ የካፌ አሳላፊ ወደኔ አፈጠጠ ዘይት የነካውን መንታ እጁን አጣምሮ ምን ልታዘዝ ይላል ቁልቁል አቀርቅሮ ምን ልታዘዝ ይላል…?? እንዴት ቅጥሉ ሰው ቅጥሉን ሰው ያዛል ማኪያቶ ልዘዝ? ካፑችኖ ልዘዝ? ጥቁር ቡና ልዘዝ? ለምን ሰው አላዝም? መታዘዝ መናዘዝ እርግማን የሆነው ካፌውን ሊያሳልፍ እራሱ ግን የሚያልፍ ቁልቁል አቀርቅሮ ሞቱን ባንገት ቀብሮ ምን ልታዘዝ? ይላል አንድ ማኪያቶ ካንድ እሷ ጋር ልዘዝ? አንድ ካፑችኖ ካንድ እሷ ጋር ልበል? ከጥቁር ቡና ጋር እሷን አምጣልበል? ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል የላስቲክ አበባ ያርቲ ቡርቲ ስዕል የ`ጭቃ እሾህ ወግቶት እዥ ያወጣ ቁስል ትልቁ ነቀዝ ሰው የማንቀዙን ያህል ብዙ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል እና እንደ ነገርኩሽ ላንቺ የያዝኩት አበባ መጠውለግ አመጣ ፀሀይ ገባ ወጣ ዝናብ ቀረ መጣ ጨረቃም የለችም እናቷን ስላልኳት ደግሜ ሰድቤ ሺህ አመት እንዳይገርማት እ. . . .ና. . . .ቷን ! እናቷን ጨረቃ ተይ አታስለፍልፊኝ ይህም ያማል በቃ ግን አንቺን ስወድሽ ይህን ሁሉ ችዬ - ነው ም'ጠብቅሽ ቢሆንም ግን ያማል !!!
إظهار الكل...
I think i loved u before i knew u @yobitty
إظهار الكل...
🔱ምክር ለአስተዋይ ወዳጀ ሆይ ራስህን እወቅ ራስን ማወቅ የዕውቀቶች ሁሉ አልፋና ኦሜጋ ነው፡፡ ራስህን እወቅ የሚለው ምርጥ አባባል በርግጥ የፈላስፋው ሶቅራጥስ ዘመን ተሸጋሪ የጥበብ ንግግር ነው፡፡ ራስን ከማወቅ ታላቅ ጥቅምን ታገኛለህ፡፡ አንተ ራስህን አመድና ትቢያ እንደሆንክ ስታውቅ ትሁት ትሆናለህ፡፡ ሀጢያትህን ስታወቅ ተፀፃች እና የንስሀ ሰው ትሆናለህ፡፡ አንተ በውስጥህ ጦርነት ያለብህ ፍጡር እንደሆንክ ስታውቅ ጠላቶችህን ታሸንፋለህ፡፡ ፀጋዎችህን በውል ካወቅህ ፈጣሪህንና በአምሳሉ የተፈጠረውን ማንኛውንም ሰው ለማክበር ፈጥነህ ትጠቀምበታለህ፡፡ እናም ወዳጀ ሆይ ራስህን በማወቅ፣ አዕምሮህ ማንነትህንና አንተነትህን ለማጠናከር በሚረዳህ ፣ስሜቶችህን በአውንታዊ አካሄድ በሚያሳድጉ፣ ዓለማዊነትን በልክ በአግባብና በሀላፊነት እንዲሁም መንፈሳዊነትህን የሚያጎሉ ገንቢ ዕውቀቶችን በመያዝ ክፍ በል፡፡ ከዛም ለምትኖርበት ማህበረሰብ እና ለሰው ወገን ሁሉ በሚጠቅም ነገር ላይ ማንነትህንና አንተነትህን ለማዋል የሚበጅህ ዋናው ጉዳይ ራስን ማወቅ ነውና እንደዛው ለማድረግ ሞክር፡፡ ⏱⏱⏱⏱⏱⏱⏱⏱⏱ Share and join ❤️ ​✿➻┈┈🌹┈••✦🌹✦••┈🌹┈┈➻✿ 👇#Share\_and\_comment 👇 ✥----------------✥🌹✥----------------✥ ✥🌹 @yobityy 🌹✥ ✥----------------✥🌹✥----------------✥
إظهار الكل...
# በአንድ_ወቅት_እንዲህ_ሆነ .... በድህነት ውስጥ የሚኖር አንድ ቤተሰብ ነበር፡፡ በቤተሰቡ ውስጥ እናት፣ አባት እና አንድ ሴት ልጅ ነበረች፡፡ ከቤተሰቡ ውስጥ ገቢ የነበረው አባት ብቻ ነበር፤ ነገር ግን መሰረታዊ ፍላጎትን (ምግብ፣ ልብስ፣ መጠለያ) ለማሟላት በቂ ነበር፡፡ አባት ምንም እንኳን በቂ ገንዘብ ባይኖረውም ሁሌም የሚያልመው ልጁን የአለማችን ምርጥ ዶክተር ማድረግ ነበር፡፡ እጅግ ከሚባለው በላይ ይወዳታል፡፡ እሷም መልካም ልጅ ነበረች፡፡ የHigh School ውጤቷን በተቀበለችበት ቀን አባት ከሚባለው በላይ በመደሰቱ "ዛሬ በአንቺ ኩራትና ደስታ ተሰምቶኛል፤ እንድገዛልሽ የምትፈልጊውን ማንኛውንም ነገር ጠይቂኝ" አላት፡፡ ልጅ መለሰች አባ ባለፈው ያሳየውህን ቀሚስ እፈልጋለው፤ ግን ዋጋው 1500 Dollar ነው፤ የዛኔ እንድትገዛልኝ አልጠየኩህም፤ ነገር ግን አሁን ተገዛልኛለህ?" አለች፡፡ አባት በመደሰቱ እና ልጁ ተከፍታ ማየት ስለማይፈልግ ብቻ ያን ቀሚስ የሚገዛ ገንዘብ እንደሌለው እያወቀ እንኳን እንደሚገዛላት ቃል ገባ፡፡ በቀጣዩ ቀን አባት ያንኑ ቀሚስ ገዝቶ ስጦታ ሰጣት፡፡ እናት ይህን ስትመለከት ያን ያህል ገንዘብ እንደሌለው ስላወቀች ገንዘቡን ከየት እንዳመጣው ጠየቀችው፡፡ አባት እንዲህ ሲል ተደመጠ "ያጠራቀምኩት ትንሽ ገንዘብ ነበር፤ በተጨማሪ ደሜን ሸጬ ባገኘውት ገንዘብ ነው፡፡ ምክንያቱም ልጄን ማናደድ አልፈልግም፡፡" ከግዚያት በኀላ ልጁ የጤና ትምህርት ቤት ገባች፡፡ አባትም ለእሷ የሚያስፈልጉ ክፍያዎችን መክፈል ያስችለው ዘንድ ከወትሮው በበለጠ ጠንክሮ መስራት ጀመረ፡፡ የመጨረሻ አመቷ ላይ ደረሰች፡፡ ለሁሉም ነገር የሚከፈል 80000 Dollar ያስፈልጋታል፡፡ አባት በቂ ገንዘብ ባይኖረውም እንዴት እንደሆነ ባይታወቅም ያን ገንዘብ ከፈለ፡፡ እናት አሁንም ያን ያህል ገንዘብ እንደሌላቸው ስለምታቅ "ያን ገንዘብ ከየት ነው ያመጣኸው? ያን ገንዘብ ለማግኘት መጥፎ ነገር አረክ እንዴ?" በማለት ጠየቀች፡፡ "አይደለም የሆነ ኩላሊቱ ከጥቅም ውጭ የሆነበት ሰው ነበረ፤ እና አንዱን ኩላሊቴን ሸጥኩለት፡፡ አደራ ለልጃችን እንዳትነግሪያት፤ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማታል፡፡" አለ አባት፡፡ ዛሬ የልጃቸው የመመረቂያ ቀን ነው፡፡ እናትና አባት ሴት ልጃቸው ለመጀመሪያ ግዜ ዶክተር ሆና ወደ ቤቷ ልትመጣ በጉጉት እየጠበቋት ነው፡፡ ነገር ግን ልጃቸው ዶክተር ሆና ሳይሆን አሰከሬን ሆና ወደ ቤትnመጣች፡፡ የምታፈቅረው ሰው በእሷ ላይ ከሌላ ሴት ጋር ስለማገጠባት እራሷን አጠፋች፡፡ እስቲ መልሱልኝ አሁን የሞተው ማነው? እሷ ወይስ ቤተሰቦቿ? በተለይ አባቷ የሞት ሞትን ነው የሞተው፡፡ -ወዳጄ ህይወትክ ያንተ ብቻ መስሎክ ከሆነ ተሳስተሀል፡፡ መኖርክ እንኳን ባይጠቅማቸው መሞትክ የሚጎዳቸው ቤተሰቦች አሉክ፡፡ ስለዚህ እራስክን በሲጋራ፣ ጫት፣ አልኮል ውስጥ ደብቀህ በቁም ሞተክ በቁም አትቅበራቸው፡፡ ወዳንቺ ደሞ ልምጣ እህቴ፤ አንቺ እራስሽን ብታጠፊ ፍቅረኛሽ ሌላ ሴት ያገኛል፤ ቤተሰቦችሽ ግን ሌላ ልዕልት ልጅ አያገኙም፡፡ ስለዚህ ሁሌም በህይወታችን ላይ ለመወሰን ስንነሳ እኛን በማሳደግ የጎበጠችው እናታችን፤ እኛን በማሳደግ በውርጭና በፀሀይ ፊቱ የከሰመው ይታወሱን!! ሀሳብ አስተያችሁን ከታች ባለው ሊንክ አድርሱን @Yobityy
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.