cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 🚶‍♂️እንኳን ደህና መጡ👋 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶችን መዝሙሮች ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። 👥 ✅ @yemezmurgetemoche 📝ለማንኛውንም ሀሳብናአስተያየት ✅ @KIDAN_MEHRET_ENATEbot ለማስታወቂያ ስራዎች ✅ @gutaitagu16 የቻናላችን ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
19 721
المشتركون
+11024 ساعات
+4387 أيام
+1 64630 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ለምኚ ድንግል ለምኚ ለምኚ ድንግል ለምኚ /2× ለሀጣን /3×/ አኮ ለፃድቃን /አዝ / ለምኚ ታላቅ ስጦታዬ " " አዛኝ እሩሩሁ ነሽ " " የጌታዬ እናት " " ፀጋን የተሞላሽ " " የአምላክ ማደሪያ " " ለምነሽ አስምሪን " " አማናዊት ፅዮን " " ከኔ አትለይኝ /አዝ/ ለምኚ ሀዘንሽ ሀዘኔ " " ለኔ ይሁን ድንግል " " የተንከራተትሽውን " " በሀገር እስራኤል " " ትግስትሽን ሳየው " " ልቤ ይመሰጣል " " የሀዘን እንባ ጎርፍ " " አይኔን ይሞላዋል /አዝ/ ለምኚ በቀራኒዮ አምባ " " በዚያ የፍቅር ቦታ " " በእግረ መስቀሉ ስር " " በክርስቶስ ጌታ " " ለኛ ለሰተሻል " " እናት እንድትሆኚን " " ልጆችሽ ነንና " " ምልጃሽ አይለየን /አዝ/ ለምኚ አንደበቴን ጌታ " " በምስጋና ምላው " " ደስ ይበልሽ ብዬ " " እኔም ላመስግናት " " አንደበቴን ጌታ " " በምስጋና ምላው " " ደስ ይበልሽ ብዬ " " እኔም ላመስግናት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር
إظهار الكل...
ለምኚ_ድንግል__ለምኚ_ድንግል(128k).m4a5.25 MB
🥰 1
8
#ሰኔ_25 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሃያ አምስት በዚች ቀን ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ የፀራቢው ዮሴፍ ልጅ #ሐዋርያው_ይሁዳ በሰማዕትነት ሞተ፣ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አባ_ጴጥሮስ አረፈ፣ ሰማዕቱ #መስፍኑ_ጲላጦስ መታሰቢያው ነው፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ይሁዳ_ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት) ሰኔ ሃያ አምስት በዚህች ቀን ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ የፀራቢው ዮሴፍ ልጅ ሐዋርያው ይሁዳ በሰማዕትነት ሞተ። ይህም ሐዋርያ በብዙ አገሮች ሰበከ ወደ አንዲት ደሴትም ገብቶ በውስጧም ሰበከ ሰዎቿንም በጌታ አሳመናቸው ቤተ ክርስቲያንም ሠራላቸው በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው። ከዚያም ወደ ሮሃ ሀገር ሒዶ የሮሃ ንጉሥ አውጋንዮስን ከደዌው ፈወሰው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቀው ከዚያም ደግሞ ሐራፒ ወደሚባል አገር ሒዶ በውስጧ ሰበከ ከሰዎቿ ብዙዎቹን አጠመቃቸው ቤተ ክርስቲያንም ሠራላቸው። የዚያችም አገር ገዥ ይዞ ጽኑዕ ሥቃይ አሠቃየው ችንካር ያለው ጫማ በእግሮቹ ውስጥ አድርጎ አንድ ምዕራፍ ያህል አስሮጠው ከዚህም በኋላ ሰቅሎ በፍላፃ ነደፈው ክብር ይግባውና በጌታችን እጅ ነፍሱን ሰጠ። ከመከራውም አስቀድሞ ለምእመናን መልእክትን ጽፎ ላከ እርሷም ከሐዋርያት መልእክቶች ሰባተኛ የሆነች ምሥጢርን የተመላች ናት በእርሷም ብዙዎች አረማውያንን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን አስገባቸው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #አባ_ጴጥሮስ_ሊቀ_ጳጳሳት ዳግመኛም በዚህች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጰሳት አርባ አራተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባ ጴጥሮስ አረፈ። ይህም አባት ከመሾሙ በፊት የማርቆስ መንበር ያለ ሊቀ ጳጳሳት ለብዙ ዘመናት ኖረ የእስላሞች ንጉሥና መኳንንቶቹ አልፈቀዱላቸውም ነበርና። ከዚህም በኋላ ሃይማኖቱ የቀና ደግ መኰንን በእስክንድርያ ከተማ ላይ ተሾመ ያንጊዜም የአገር ሽማግሌዎች ወደ ርሱ ተሰብስበው ሊቀ ጳጳሳት እንደ ሌላቸው ኀዘናቸውን ነገሩት። እርሱም ደብረ ማሕው ወደሚባለው ወደ ደብረ ዝጋግ ወጥተው እንዲጸልዩ ለራሳቸውም ሊቀ ጳጳሳት እንዲሾሙ አዘዛቸው። በዚህም ነገር ደስ ብሏቸው ቀሲስ አባ ጴጥሮስን ወስደው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በእርሱም ደስ አላቸው። በዚያም ወራት የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሳዊሮስ ሞተ የአንጾኪያ አገርም ያለ ሊቀ ጳጳሳት ትኖር ነበር የአንጾኪያ ምእመናንም ለእስክንድርያ ከተማ አባ ጴጥሮስ እንደ ተሾመ በስሙ ጊዜ እነርሱም የተማረ ደግ ሰው ለአንጾኪያ ሾሙ ስሙም ታውፋንዮስ ይባል ነበር ። እርሱም ከአባ ጴጥሮስ ጋራ ተስማማ እነርሱም ስለ ቀናች ሃይማኖት በመልእክቶቻቸው ይገናኙ ነበር። ከእነርሱም እያንዳንዱ በባልንጀራው ምክር በጸሎትና በቅዳሴ ጊዜ ይሰብክ ነበር ወደ አገራቸውም መግባት አልተቻላቸውም ነበርና አባ ጴጥሮስም በግብጽ ደቡብ በአንባንያ ገዳምና በዝጋግ ገዳም ይኖር ነበር አባ ታውፋንዮስም ከአንጾኪያ ከተማ ውጭ በአፍቆንያስ ገዳም ይኖር ነበር። በዚያም ወራት ከእስክንድርያ ከተማ ውጭ ሰባት መቶ ገዳማትና ሃይማኖታቸው የቀና ምእመናንም ያሉባቸው ሠላሳ ሁለት መንደሮች ነበሩ በግብጽ አውራጃ ሁሉና በላይኛው ግብጽ በአስቄጥስ ገዳማት የሚኖሩ መነኰሳት እንዲሁም ኖባና ኢትዮጵያ በዚህ በአባ ጴጥሮስ ስልጣን ሥር ነበሩ። እኒህ ሁሉ ሃይማኖታቸው የቀና ነበር። በትእዛዙም ጸንተው ይኖሩ ነበር። እርሱም በቀናች ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ወደእርሳቸው መልእክቶችን መጻፍ አያቋርጥም ነበር። የእስክንድርያን ገዳማት ሁሉና መንደሮችንም እየዞረ ያስተምራቸውና ይመክራቸው ያጽናናቸውም ነበር። ከእርሱ በኋላ ሊቀ ጳጳሳት የሆነ ቅዱስና ዐዋቂ የሆነ ደቀ መዝሙር ነበረው እርሱም በሊቀ ጵጵስናው ሥራ ሁሉ ይራዳው ነበረ። ይህም አባት ጴጥሮስ አንዳንድ ጊዜ ወደ እስክንድርያ ከተማ ይገባ ነበር የሰዎቿንም ሥራቸውን ተመልክቶ ያስተምራቸውና በሃይማኖት ያጸናቸው ነበር። በዐሥራ ሁለቱ ዓመት የሹመቱ ዘመን እንደ ሐዋርያት መንጋዎቹን እየጠበቀ እንዲህ በሹመቱ ኑሮ በሰላም አረፈ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ሰማዕቱ_ጲላጦስ_መስፍን ዳግመኛም በዚህች ዕለት ሰማዕቱ ጲላጦስ እና የሚስቱ ቅደስት አብሮቅላም መታሰቢያ ነው፡፡ ብዙዎቻችን መስፍኑን ዺላጦስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጌታችን እንዳይሰቀል ከአይሁድ ጋር ሲከራከር እናውቀዋለን። የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ ነበርና አይሁድ እንቢ ሲሉት የክርስቶስን ንጽሕና መስክሮ: እጁንም ታጥቦ ሰጥቷቸዋል። የዺላጦስ ታሪክ ግን እዚህ ላይ አያበቃም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጐ ከተነሳ በሁዋላ ትንሳኤውን በራዕይ ገልጦለት አይሁድን ተከራክሯቸዋል። ውሸታም ወታደሮችንም ቀጥቷል። በመጨረሻ ግን በሮም ቄሳር ተጠርቶ ከእሥራኤል እስከ ሮም ድረስ ሰብኮ በሮም አደባባይ አንገቱ ተሠይፏል። ቅድስት እናታችን አብሮቅላም የዺላጦስ ሚስት ስትሆን ቁጥሯ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ነው። ጌታችንን ተከትላ ቤቷን ለሐዋርያት አስረክባ ቤተ ክርስቲያንንም በዘመኗ አገልግላ ዐርፋለች። ዛሬ ሁለቱም ቅዱሳን ይታሠባሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
إظهار الكل...
✝️ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ማነው ብዬ ጠየቅሁ በረከት ፈልጌ ልሳለመው ናፈቅሁ ክብሩን ልመሰክር ተፈታ ምላሴ በደጁ ደርሼ ፍቅሩን በመቅመሴ/፪/ በኢቲሳ ምድር ዘር ሆነህ በቅለህ ተለየህ ለአምላክ ዓለምን ጥለህ ደብረ ሊባኖስ ህያው ምስክር ስለ አንተ ዝና ስለ አንተ ክብር ተክለሃይማኖት ወዳጄ ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ አዝ____ አክባሪው አምላክ ስላከበረህ ዛሬም ከኛ ጋር በመንፈስ አለህ ደጅ እንጠናለን በትህትና የጻድቅ ጸሎት ኃይል አላትና ተክለሃይማኖት ወዳጄ ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ አዝ____ ወደ ለምለም መስክ ሰብከህ መራኸን የቃሉን ወተት አጠጥተኽን ያቀጣጠልከው የወንጌል ችቦ የአምላክ አድርጓል ትውልዱን ስቦ ተክለሃይማኖት ወዳጄ ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ አዝ____ ሠላሳ ሥድሳ መቶ ያፈራህ በደብረ አስሶ ቆመህ በአንድ እግርህ የሞተለሚ መሻት ቀረና የጌታ መንገድ ጥርጊያውም ቀና ተክለሃይማኖት ወዳጄ ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ https://t.me/EthiopianOrthodoxTewahdoMezmurs
إظهار الكل...
ኢትዮጵያው ፃዲቅ .mp35.27 MB
17👍 9🙏 6🔥 5👏 3😘 1
✝️ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ማነው ብዬ ጠየቅሁ በረከት ፈልጌ ልሳለመው ናፈቅሁ ክብሩን ልመሰክር ተፈታ ምላሴ በደጁ ደርሼ ፍቅሩን በመቅመሴ/፪/ በኢቲሳ ምድር ዘር ሆነህ በቅለህ ተለየህ ለአምላክ ዓለምን ጥለህ ደብረ ሊባኖስ ህያው ምስክር ስለ አንተ ዝና ስለ አንተ ክብር ተክለሃይማኖት ወዳጄ ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ አዝ____ አክባሪው አምላክ ስላከበረህ ዛሬም ከኛ ጋር በመንፈስ አለህ ደጅ እንጠናለን በትህትና የጻድቅ ጸሎት ኃይል አላትና ተክለሃይማኖት ወዳጄ ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ አዝ____ ወደ ለምለም መስክ ሰብከህ መራኸን የቃሉን ወተት አጠጥተኽን ያቀጣጠልከው የወንጌል ችቦ የአምላክ አድርጓል ትውልዱን ስቦ ተክለሃይማኖት ወዳጄ ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ አዝ____ ሠላሳ ሥድሳ መቶ ያፈራህ በደብረ አስሶ ቆመህ በአንድ እግርህ የሞተለሚ መሻት ቀረና የጌታ መንገድ ጥርጊያውም ቀና ተክለሃይማኖት ወዳጄ ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ https://t.me/EthiopianOrthodoxTewahdoMezmurs
إظهار الكل...
ኢትዮጵያው ፃዲቅ .mp35.27 MB
06:43
Video unavailableShow in Telegram
إظهار الكل...
e042cb3c595014acce98f1029670d7eb.mp429.57 MB
👏 6 5🙏 3👍 2🥰 1💯 1
✞ እያለፈ ነው ዘመኔ ✞ እያለፈ ነው ዘመኔ ትእዛዙን ሳልፈጽም ወየው ለእኔ/፪/  በጠራኝ ጊዜ ምን እላለሁ ና ብሎ ወደእኔ/፪/  በወጣትነቴ ሳልሠራ እያየሁ አለፈኝ ብዙ አዝመራ/፪/  ከእንግዲህ በመሥራት ጌታ ሆይ ልኑር ከአንተ ጋራ/፪/    የማስብበት በየለእቱ ንጹሕ ልብን ስጠኝ አቤቱ /፪/  ከትእዛዝህ ውጪ በመሆን እዳልቀር በከንቱ /፪/    እንደየሥራው ለመስጠት በግርማ መንግሥቱ ሲመጣ/፪/  ማን ይሆን የሚቆም ከፊቱ ፊተናን የወጣ/፪/    እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ እየተማራችሁ ከቃሉ/፪/  ይመጣሉና በእርሱ ስም አምላክ ነን የሚሉ/፪/    ትእግሥትን በመያዝ ሁላችሁ እስከመጨረሻው ጠንክሩ/፪/  ያን ጊዜ ይሆናል በእርሱ ዘንድ የማዳን ተግባሩ/፪/ 
إظهار الكل...
4_5852448804057386225.mp31.99 MB
🙏 22 14👍 8😢 8🥰 7👏 6
25🥰 4👍 3🕊 2
#ሰኔ_24 #ቅዱስ_ሙሴ_ጸሊም_ኢትዮጵያዊው አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሃያ አራት በዚች ቀን አባ ሙሴ ጸሊም በሰማዕትነት ሞተ። ሰዎች ከገድሉ የተነሣ ይህን ቅዱስ ያደንቁታል እርሱ አስቀድሞ መንግሥተ ሰማያትን ገፍቷት ነበረና እርሱ በሥጋው ጠንካራ በሥራውም ኃይለኛ ነበር ይበላና ይጠጣ ይቀማና ያመነዝር ነበር ይገድልም ነበር ማንም ሊቋቋመው አይችልም ነበር። አንድ በግ በአንድ ጊዜ ጨርሶ እንደሚበላና አንድ ፊቀን ወይን ጠጅ እንደሚጠጣ ስለ እርሱ ተነግሮአል። እርሱም ፀሐይን ለሚያመልኩ ሰዎች አገልጋይ ነበረ ብዙ ጊዜም ወደ ፀሐይ እያንጋጠጠ ፀሐይ ሆይ አንተ አምላክ ከሆንክ አነጋግረኝ ይል ነበር ደግሞም በልቡ የማላውቅህ ሆይ ራስህን አሳውቀኝ ይል ነበር። ከዚህም በኋላ በአስቄጥስ ገዳም ያሉ መነኰሳት እግዚአብሔርን ያውቁታል ያዩታልም እያሉ ሲነጋገሩ ሰዎችን ሰማቸው። ያን ጊዜም ተነሣ ሰይፉንም ታጥቆ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ በደረሰም ጊዜ አባ ኤስድሮስን አገኘው። አባ ኤስድሮስም ፈራው ሙሴ ጸሊምም እውነተኛውን አምላክ ታሳውቁኝና ታስረዱኝ ዘንድ ወደ እናንተ መጣሁ አለው። አባ ኤስድሮስም ወደ አባ መቃርስ ወስዶ አገናኘው። እርሱም ተቀብሎ ሃይማኖትን አስተማረው እንዲህም አለው ታግሠህ የማስተምርህን ከጠበቅህ እግዚአብሔርን ታየዋለህ። ከዚህም በኋላ የክርስትና ጥምቀትን አጥምቆ አመነኰሰው ከብዙዎች ገድለኞች ቅዱሳን ይልቅ ብዙና ጽኑዕ ገድልን መጋደል ጀመረ። ሰይጣንም ቀድሞ ሲሠራው በነበረ በመብሉና በመጠጡ በዝሙቱም ይዋጋው ነበረ እርሱም በራሱ ላይ የሚደርስበትን ሁሉ ለአባ ኤስድሮስ ይነግረው ነበር እርሱም አጽናንቶ ሊሠራው የሚገባውን ያስተምረው ነበር። ከገድሉ ብዛትም የተነሣ አረጋውያን መነኰሳት በሚተኙ ጊዜ ቤቶቻቸውን በመዞር ውኃ መቅጃዎችን ወስዶ ውኃ መልቶ በየቤታቸው ደጃፍ ያኖር ነበር። ውኃው ከእነርሱ ሩቅ ነበረና እንዲህም እያደረገ በመጋደል ለብዙ ዘመናት ኖረ። ሰይጣንም በእርሱ ቀንቶ በእግሩ ውስጥ አስጨናቂ የሆነ አመታትን መታው ተኝቶም እየተጨነቀ ብዙ ቀን ታመመ። ከዚህም በኋላ የመታውና የሚፈታተነው ሰይጣን እንደሆነ ዐውቆ ሥጋው በእሳት ተለብልቦ እንደ ደረቀ ዕንጨት እስቲሆን ድረስ ተጋድሎውንና አገልግሎቱን አበዛ። እግዚአብሔርም ትዕግስቱን አይቶ ከደዌው ፈወሰው የሰይጣንንም ጦር ከእርሱ አራቀለት የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ አደረበት ወደርሱም አምስት መቶ ወንድሞች መነኰሳት ተሰበሰቡ በእነርሱም ላይ አበ ምኔት ሆነ። ከዚህ በኋላ ቅስና ሊሾሙት መረጡት በቤተ መቅደስም በሊቀ ጳጳሳቱ ዘንድ በአቆሙት ጊዜ ሊቀ ጳጳሳቱም አልፈቀደም ነበር አረጋውያኑንም ይህን ጠቋራ ለምን አመጣችሁት ከዚህ አውጡት አላቸው እርሱም መልክህ የከፋ ጠቋራ ሆይ መልካም አደረጉብህ በማለት ራሱን እየገሠጸ ወጣ ከዚህ በኋላ ዳግመኛ ሊቀ ጳጳሳቱ ጠራውና እጁን በላዩ ጭኖ ቅስና ሾመው እንዲህም አለው ሙሴ ሆይ እነሆ በውስጥም በውጭም ሁለመናህ ነጭ ሆነ። በአንዲትም ዕለት ቅዱሳን አረጋውያን ወደርሱ መጡ በእርሱም ዘንድ ውኃ አልነበረም እርሱም ከበዓቱ ብዙ ጊዜ ወጣ ገባ ይል ነበር ከዚህ በኋላም ብዙ ዝናም ዘንሞ ጕድጓዶችን ሁሉ ሞላ። አረጋውያንም ለምን ብዙ ጊዜ ወጣ ገባ ትል ነበር ብለው ጠየቁት እርሱም እግዚአብሔርን ውኃ ካልሰጠኸኝ ቅዱሳን አገልጋዮችህን ምን አጠጣቸዋለሁ እለው ነበር በቸርነቱም ዝናምን ልኮልን ውኃን አገኘን አላቸው። በአንዲትም ዕለት አባ ሙሴ ከአረጋውያን ጋራ ወደ አባ መቃርስ ሔደ አባ መቃርስም የሰማዕትነት አክሊል ያለው ከእናንተ ውስጥ አንዱን እነሆ አያለሁ አላቸው አባ ሙሴም አባቴ ሆይ ምናልባት እኔ እሆናለሁ በሰይፍ የገደለ በሰይፍ ይገደል ዘንድ አለው የሚል ጽሑፍ አለና ብሎ መለሰ። ከዚህም በኋላ የበርበር ሰዎች መጡ አባ ሙሴም ከእርሱ ጋራ ያሉትን መነኰሳት እነሆ የበርበር ሰዎች ደረሱ መሸሽ የሚፈልግ ይሽሽ አላቸው እነርሱም አባታችን አንተስ አትሸሽምን አሉት እርሱም በሰይፍ የገደለ በሰይፍ ይገደላል ስለሚለው የእግዚአብሔር ቃል እነሆ ያቺን ቀን ለብዙ ዘመናት ስጠብቃት ኖሬአለሁ አላቸው። ወዲያውኑም የበርበር ሰዎች ገብተው በሰይፍ ገደሉት መሸሽ ስለ አልፈለጉ ከእርሱ ጋራ ሰባት መነኰሳትም ተገደሉ አንዱ ግን ከምንጣፍ ውስጥ ተሠወረ የእግዚአብሔርንም መልአክ አየ በእጁም አክሊል ነበር እርሱም ቆሞ ይጠብቅ ነበር። ይህንንም በአየ ጊዜ ከተሠወረበት ወጣ የበርበር ሰዎችም ገደሉት የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለ። ወንድሞች ሆይ ከሀዲና ነፍሰ ገዳይ ቀማኛና ዘማዊ የነበረውን ለውጣ ደግ አባት መምህርና የሚያጽናና ለመነኰሳትም ሥርዓትን የሠራ ካህን እንዳደረገችው በሁሉም አብያተ ክርስቲያን ስሙ እንዲጠራ እንዳደረገችው የንስሐን ኃይሏን ተመልከቱ። ሥጋውም በአስቄጥስ ገዳም ደርምስ በተባለ ቦታ ለዘላለም ይኖራል ከእርሱም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ይታያሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ_24)
إظهار الكل...
5🙏 4👍 2🕊 1
አለብኝ ውለታ መክፈል የማልችለው አለብኝ ውለታ ተነግሮ የማያልቅ አለብኝ ውለታ አምላክ ተመስገን የኔ ጌታ ይቺው ነች አቅሜ ለስጦታ /አዝ/ በዘመኔ ሁሉ የደገፍከኝ በእጆችህ ጌታ ዘርዝሬ አልጨርሰው ውለታህ ምስኪን ባሪያህ ለውለታህ አሁን ምን እከፍላለሁ ሌላ አትሻም አንተ ያቅሜን ይኸው አመሰግናለሁ /አዝ/ ስናቅ እንዳልነበር እኔ በሰዎች ተጥዬ ከውድቀቴ አንስተህ ሰው አረከኝ ቸር ጌታዬ ነፍሴ ለውለታህ በምስጋና ተሞልታለች ጠዋት ማታ ስምክን እያነሳች ታመሰግናለች /አዝ/ ነፍሴ መሸሸጊያ አጥታ አንተ ስላየሀት ከለምለም መስክ ወስደህ አሳረፍካት የከበዳት ሸክም ቀሎ በአንተ እረፍት አገኘች ይኸው በሰዎች ፊት ያንተን ክብር ትሐሰክራለች /አዝ/ አይቸኩልም እግዚአብሔር ለሱ አለው ጊዜ ሲጠሩት ይሰማል ደግሞ ያወጣል ከትካዜ የፅድቅንም መንገድ እያሳየ ይመራናል ወደ ህይወት መንገድ እረኛችን ወስዶ ያሳርፈናል ዘማሪ ሊቀ ልሳናት ቸርነት ሰናይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር
إظهار الكل...
AUD-20190730-WA0032-1.mp34.11 MB
12👍 7
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.