ሁለ ገብ😘😘😘
الذهاب إلى القناة على Telegram
እዚህ Channel ላይ ማንኝውንም ነገር ማግኘት ይችላሉ ብቻ የምትቁዋቸውን ሁሉ ወደዚህ channel ይጋብዙ group መቀላቀል አይርሱ !!
إظهار المزيد463
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
+3030 أيام
أرشيف المشاركات
463
ፋሲካመጣና → ወደ መርካቶ
መርካቶም → ስሄድ ዶሮ ሻጭ ሞልቶ
ከዶሮ ሻጩም → ዶሮ መርጬ
ዶሮ ስመርጥም → አገላብጬ
አገላብጬም → ዋጋውን መስማት
ዋጋውን ሠምቶ → ልቤ ማቅማማት
ልቤ ሲያቅማማ → ውድ ነው ማለት
ውድ ነው! ብዬ → ስመልስለት...
እሱው መልሶ → አንተው ገምተው
እኔ ስገምት → ማመን አቃተው
ማመን አቅቶት → ትንሽ ተቆጣ
ትንሽ ሲቆጣ→ ሌላ ሠው መጣ
ሌላ ሠው መጥቶ → ላስማማህ ቢለኝ
ላስማማህ ባዩ → ሌባ መሠለኝ
ቢመስለኝ → እሱንም ጠላው
መጥላቴ → ደሙን አፈላው
ደሙ ሲፈላ → ቡጢ ጨበጠ
ቡጢ ሲጨብጥ → አይኔ ፈጠጠ
አይኔ ሲፈጥም → ለነብሴ ሳሳሁ
ነብሴ ቢያሳሳኝ → እግሬን አነሳሁ
እግሬን አንስቼ → ባልጠፋ ኖሮ
ጠፍቼ ነበር እንደ → ጦስ ዶሮ።
ሰናይ ቀን 😂👐
#keld21
@keld21
@keld21
463
አንዳንዴ
(በዕውቀቱ ስዩም)
ባልተገራ ፈረስ
በፈጣን ድንጉላ
ኑሮ በአቦ ሰጠኝ
ህይወትን በመላ
በዚህ በኩል ሲሉህ
ንጎድ ወደ ሌላ ፤
እስከመቼ ድረስ
ዳርዳሩን መራመድ፤በጭምት ሰው ስሌት
በክብር ካልመጣ፤ሞክረው በቅሌት
ሰው ቅፅር አይደለም፤በእሾህ የታጠረ
እንድንጥሰው ነው ፤ ህግ የተፈጠረ።
አይሰለችህም ወይ
መኖር በመጠንቀቅ
አንዳንዴ
አየር ላይ ደንሰህ፤በግንባርህ ውደቅ
አንዳንዴ
ኮርቻህን እርሳት
ርካብህንም ሳት
ፋይዳ አይጠፋምና፤ወድቆ ከመነሳት !
በትቢያ ላይ ወድቀው
የተነሱ አሉና፤በሉል ባልማዝ ደምቀው !
አንዳንዴ
ልጓሙን ልቀቀው !
@keld21
@keld21
@keld21
@keld21
@keld21
463
አንተም አዳምን ሁን,,,,,,,
🙂🙂🙂🙂🙂
መሳሳት ቢኖርም አንድም ባለማወቅ፤
ወይም ቃል በመናቅ።
የትናንቱ አዳም,,,,,,,,,,
ስህተቷን በምህረት አይቶ ያሳለፈ፤
ምንም ቢሆን እንኳ ክብሩ የጎደፈ።
ስጠኝ ባለው ማግኘት ምን ዋጋውን ቢያጣ፤
ከርዕስቱ ቢሰደድ ከገነት ሲወጣ፤
እኛ አላየነውም,,,,,,,,,
ሔዋንን ሲያንቋሽሽ በብትር ሲቀጣ።
ስለዚህ አዳም ሆይ, ,,,,,,,,
መሳሳት ቢኖርም ያውም የገዘፈ፤
ለማየት ለመስማት ፍፁም የቀፈፈ።
ከማናናቅና ከመሳደብ ፀድተህ፤
በተግሳፅ መልሰኝ አንተም አዳም ሆነህ።🥹
#N
@keld21
@keld21
