cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

አዛርያ በምድር ሩፋኤል በሰማይ

#azarya #bemdr #rufael #besemay ይህ ቤት #መንፈሳዊ ድምፆች ፤ ፅሁፎች እንዲሁም #ጥሩ #መልዕክት ያላቸው ሌሎች ፅሁፎች ድምፆች #የሚቀርብበት ነው። ኑ አብረን እንማር።

إظهار المزيد
Ethiopia11 596Amharic9 728الفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
220
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

🙏?? #እግዚኦ_ነው_ሌላ_ምን_ይባላል 🙏🙏 🤔 በአመት 30 ሺህ ህጻናትን በሰው ሰራሽ ማህጸን የሚያመርተው ፋብሪካ የህጻናቱን እድገትም በሞባይል ስልካቸው መከታተል እንደሚችሉ የጀርመኑ ኩባንያ ኢክቶ ላይፍ ገልጿል በሳይንሱ አለም ተረት የሚመስሉ ነገሮች እውን ሆነው መታየት ጀምረዋል። 🤔 በተለያየ ምክንያት ጸንሰው መውለድ ለማይችሉ ሴቶች የአብራካቸውን ክፋይ እንካችሁ የሚል ኩባንያ በይፋ ተዋውቋል። ኢክቶላይፍ የተሰኘው የጀርመን ኩባንያ በአመት 30 ሺህ ህጻናትን በሰው ሰራሽ ማህጸን ለማቅረብ ተሰናድቻሉ ብሏል። 🤔 ከአምስት አስርት አመታት በላይ ምርምር ሲደረግበት የቆየውን ጉዳይ አሁን ወደተግባር ለመለወጥ ሙሉ ዝግጅት ማድረጉን ነው ሃሸም አል ጋይሊ የተሰኙት የኩባንያው የባዮቴክኖሎጂ እና የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ የተናገሩት። ቴክኖሎጂው በተፈጥሮ መጸነስ የማይችሉና የካንሰር ታማሚዎች በሰውሰራሽ ማህጸን ልጃቸውን እንዲያገኙ የሚያስችል ነው። 🤔 ከዚህም ባሻገር የልጃቸውን ከአይን ቀለም አንስቶ እስከ ቁመት እና የማስተዋል ብቃት እንዳሻቸው ማድረግ የሚያስችል አሰራርም ዘርተናል ብለዋል ሃሸም አል ጋይሊ። እነዚህ ችግሮች ከተቀረፉ ኢክቶላይፍ 400 ጽንስ በአንድ ጊዜ መያዝ በሚችሉ 75 ዘመናዊ ቤተሙከራዎቹ ወደ ስራ እንደሚገባ አስታውቋል። ሰውሰራሽ ማሕጸኖቹ ጽንሱ በእናቱ ሆድ የሚያገኘውን ሁሉ እንዲያገኝ ተደርገው የተሰሩ ናቸው። 🤔 የተጠሙላቸው ስክሪኖችም የጽንሱን አጠቃላይ መረጃ በየጊዜው ያሳያሉ፤ ወላጆችም እድገታቸውን በሞባይል ስልካቸው ባሉበት ሆነው መከታተል ይችላሉ ነው የተባለው። የሙቀት መጠናቸውን፣ የደም ግፊታቸውን እና አተነፋፈሳቸውን ጨምሮ አጠቃላይ ሁኔታቸውን የሚቆጣጥሩ ሴንሰሮችም ተገጠመውላቸዋል። 🤔 በሰውሰራሽ ማህጸኖች የሚያድገው ጽንስ እናቶች በማህጸናቸው ከሚያሳድጓቸው ይልቅ ለበሽታ የመጋለጥ እድላቸውም ዝቅተኛ መሆኑን ኩባንያው የሚጠቀመውን ቴክኖሎጂ በመጥቀስ ይገልጻል። የጽንሶቹ እድገት ከወላጆቹ ዘረመል ጋር በተያያዘ የእድገት ውስንነት የሚያስተናግድ ከሆነም በፍጥነት ለይቶ ያሳውቃል ተብሎለታል። 🤔 በሰው ሰራሽ ማህጸን የሚያድጉት ህጻናት ቋንቋ እንዲያውቁና ወላጆቻቸውን እንዲለዩ ሙዚቃዎች እና የወላጆቻቸውን ድምጾች እንዲሰሙ ይደረጋል። ዋነኛው አላማችን የወላጆችን ፍላጎት ማሟላት ነው የሚለው የጀርመን ኩባንያ የህግ ገደቦች መላላት ከቻሉ 30 ሺህ ህጻናትን በአመት በሰው ሰራሽ ማህጸን ለማቅረብ መሰናዳቱን አሳውቋል ሲል የዘገበው ሚረር ነው። ✍️ አል-ዓይን
إظهار الكل...
እሳተ_ጽርሁ እሳተ ጽሩሁ ማየ ጠፈሩ /2/  ደመና መንኮራኩሩ ለመድኃኔዓለም /4/ 
إظهار الكل...
እሳተ ፅሩህ.mp36.90 KB
የልቤን ጥልቀት መርምሮ ከሚያውቀው ከእርሱ በቀር ማንም ከህመሜ ሊፈውሰኝ ሚችል የለም። ስንት ጊዜ እራሴን ከኃጢያት የሚለይ ድንበርን አበጀሁ፥ ስንት ጊዜስ ከኃጢያት ለመጠበቅ ግንብን ገነባሁ! ሀሳቤ ግን ወደክፋት መንደር ጥሶ ገባ፥ ፈቃዴም ያቆምሁት ግንብ ሳይዘው፤ ያሰመርኩትም ድንበር ሳያቆመው በኃጢያት መንደር አደረ። ያሰመርኩት ወሰን ፈሪሃ እግዚአብሔርን ስላልያዘ፤ ያቆምኩት ግንብም ከልብ በሆነ ንስሐ እና ጸጸት ስላልተመሰረተ ሀሳቤን ከመባከን አልያዘውም። ደግሞም ነፍሴ መለስ ስትልልኝ፥ ቆም ብዬ አስብና በርህን አንኳኳለሁ፤ ልቤ ያሻውን እስክትሰጠኝ ሳላቆም እጠይቅኻለው፤ ቸርነትህን ያለማፈር እጠይቃለሁ። ከፍ ባለ ድምጽም ወዳንተ እንዲህ እያልኩ ጮኻለው: “አቤቱ ጌታዬ እና መድኃኒቴ ስለምን ተውኸኝ? ቸር ሰው ወዳጅ ሆይ ቸርነትን አድርግልኝ። በደል ፈጽሞ የሌለብህ ሆይ እባክህ አድነኝ! ጎድፌ እንዳልቀር ከኃጢያቴ ረግረግ መንጥቀህ አውጣኝ። እንደ አንበሳ ከሚያጋሳው ሊውጠኝም ከሚሻው ከጠላቴ መንጋጋ አድነኝ። አቤቱ ኃይልህን ይዘህ ተነስ፥ ወደኔም ታድነኝ ዘንድ ና! ጠላቴ ፈርቶ ከፊትህ ይሸሽ ዘንድ አቤቱ የክብርህን መብረቅ አንጎድጉደው፥ በኔም ላይ ያለውን የእርሱን ኃይል በትን! በአንተ እና አንተን በሚወዱ ፊት የመቆም ብርታት የለውምና፥ የጸጋህን በዚህ መኖር ባወቀ ጊዜ ፍርሃት ይይዘዋል፥ እያፈረም ወደ ጉድጓዱ ይሸሻል። አቤቱ ወዳንተ ምሸሽ እኔን አድነኝ፥ ጌታዬ አምላኬም ሆይ አንተን መሸሸጊያዬ አርጌያለሁና በእቅፋትህ አኑረኝ።” ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በከመ ተርጎሞ ዲያቆን እስጢፋኖስ ግርማ ጥቅምት 22፥ 2015 ዓ.ም.
إظهار الكل...
#ልጅሽ_ደጅ_ላይ_ቆሟል ከመስከረም 26 እስከ ሕዳር 6 ባሉ አንድ ቅዳሜ ማታ ከ3 ሰዓት በኋላ ማሕሌተ ጽጌን ለመቆም ወደ የካ ደብረ ሳሕል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እየሄድኩ ነው...መንገዱ ጭር ብሏል፤ አንድ ሱቅ ላይ ግን ደምበኛ (ገዢ) ቆሟል፤ እኔ መንገዴን እየቀጠልኩ ነው፡፡ ደንበኛው ቀጥ ብሎ ወደኔ መጣ እና ‹‹አባ ይበርኩኝ?›› አለኝ። ‹‹ካህን አይደለሁም›› አልኩት፣ በለበስኩት ነጠላ ጋቢና በእጄ የያዝኩት የጸሎት መጽሐፍ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደምሄድ አውቆ ነው፡፡ ‹‹አውቃለሁ›› አለኝ እና ‹‹ወደየትኛው ቤተ ክርስቲያን ነው የምትሄደው?›› ጠየቀ መለስኩለት፤ ‹‹እባክህን ልሸኝህ?›› አለኝ አዲስ ቪ 8 መኪና እያሳየኝ፣ ‹‹ብዙም ሩቅ ስላልሆነ በእግሬ ነው የምሄደው›› አልኩት.... ግለሰቡ የጠጣ ይመስላል፣ በእርግጥም የመጠጥ ሽታ ሸትቶኛል፤ በእጁ ፓኬት ሲጋራ ይዟል፣ ከሱቁ ሲመጣ ከፓኬቱ ውስጥ አንዱን አውጥቶ ከንፈሩ ላይ አድርጎ ነበር ሲቀርበኝ በጣቶቹ መሃል ያዘው፣ ምልከታዬን አስተውሎ ነው መሰለኝ የያዘውን ሲጋራ በሙሉ ጣለና በእግሩ ረጋገጠው፡፡ ‹‹አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ ልትል ነው አይደል?›› አለኝ ከዚህ ንግግር በኋላ ስካሩ ሙሉ ለሙሉ ሲጠፋ በግልጽ ይታያል፡፡ ሁሉንም የመኪናውን በሮች ከፈተና ‹‹እንዲናፈስ ፈልጌ ነው...በሲጋራና በመጠጥ ሽታ የታጠነ መኪና ውስጥ እንዳትገባ›› አለኝ፤ በግርምት ቆምሁ፤ ‹‹እባክህ አሁን እንሂድ?›› የጋቢናውን በር ብቻ ትቶ ሌሎቹን ዘጋጋና መኪናውን ለመንዳት ተዘጋጀ፤ በእምነት ገባሁና ተቀመጥኩ። መንገድ ስንጀምር በጣም ባዘነ ድምጸት ‹‹ሽሮ ሜዳ ነው ያደግሁት...ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን...ጽጌን በፍቅር ቆሜ ነው ያደግኩት...ለረጅም ዓመታት...አክሊለ ጽጌ ብዬ...ክበበ ጌራ ወርቅ ብዬ›› ዓይኖቼን ከመንገዱ ነቅዬ ወደርሱ ሳዞር መንታ መንታ ሆነው የሚወርዱ እንባዎቹን ይጠርጋል፤ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም መስማት ብቻ ‹‹ዲግሪዬን ከያዝኩ በኋላ አንድ ዓለም አቀፍ ኤን ጂ ኦ ገባሁ...በከፍተኛ ደመወዝ በቃ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ተለያየሁ...አልሳለም፣ ኪዳን አላደርስ፣ አላስቀድስ፣ አላድር፣ አላነግስ ከሀገር ሀገር መዞር ከጓደኞቼ ጋር መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ...ይኸውልህ ሚስትና ልጆች እያሉኝ ነው እዚህ ያገኘኸኝ፣ የመጠጥና የሲጋራ ጓደኞቼ በልጠውብኝ ነው ያገኘሁህ...ውስኪአቸውን ይዘው እየጠበቁኝ ነው ›› ያለቅሳል፣ እንባዎቹን ይጠርጋል፤ ግን በሥርዓት ረጋ ብሎ ይነዳል፤ መናገሩን ይቀጥላል ‹‹ተረጋግቼ ማሰብ አልፈልግም...ምክንያቱም ከተረጋጋሁ ልጅነቴን ማሰብ እጀምራለሁ...ልጅነቴን ማሰብ ከጀመርሁ ቤተ ክርስቲያንን ማሰብ እጀምራለሁ...ደጀ ሰላሟን ማሰብ እጀምራለሁ...መቅደሷን ማሰብ እጀምራለሁ፣...የዕጣኑን ሽታ ማሰብ እጀምራለሁ...ማልቀስ እጀምራለሁ...ፍቅሯን አስባለሁ....የጸናጽሉ፣ የከበሮው ድምጽ ይሰማኛል፣ በመሃል ሰይጣኔ ይመጣና እውነቴን ነው ስጠራው ነዋ የሚመጣው....ለጓደኞችህ ደውል ይለኛል....በመጠጥ ራስህን ደብቅ ይለኛል እታዘዘዋለሁ ልጆቼንና ሚስቴን ጥዬ እወጣለሁ›› አሁን ወደ ቤተክርስቲያን ታጥፈናል፤ ወደ ግቢው የሚያስገባ በር ጋር ስንደርስ ቆመ፣ ወደውስጥ ለመግባት በሮቹ የተከፈቱ ቢሆንም አልገባም፤ ‹‹ወደ ውስጥ ገብተህ ትንሽ ቆይተህ አትሄድም?›› አልኩ ሀዘኑ ተጋብቶብኝ ‹‹አልገባም ግን ድሮ የሚወድሽ ልጅሽ ደጅ ቆሟል በላት›› አለና ሳግ ተናንቆት መሪውን ተደግፎ ድምጽ አሰምቶ አለቀሰ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ለምን እንዳለቀሰ፣ እንዴት እንዳለቀሰ በዓይኔ ያየሁ መሰለኝ፤ ‹‹እባክህን ግባና አልቅስ›› አልኩ፣ የቻለውን ያህል አልቅሶ እንዲወጣለት ፈለግሁ፣ ‹‹ማን....እኔ? አልገባም ግን ንገርልኝ አሁንም ይወድሻል በልልኝ....እዚህ በር ላይ ቆሟል በልልኝ›› አለኝ፣ እያለቀሰ ወረድሁ ቅዱስ ዳዊት ‹‹በኃጥአን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ›› መዝ 84፣10 ያለው ለምን እንደሆነ ይበልጥ ገባኝ። ሳላውቀው የእኔም እንባ መንገዱን ጀምሯል፤ ‹‹ማን ስለሆንኩ ነው እንዲህ በፍቅርህ የተሸከምከኝ›› አልኩ አምላኬን፣ በላዔ ሰብዕ ትዝ አለኝ በልጅነቱ የሚያስታውሳትን የድንግልን ድንቅ ስሟን ሲሰማ ከክህደት እንደተመለሰና ለመዳን ምክንያት እንደሆነችው፡፡ እናም ‹‹በልጅነቱ ይወድሽ የነበረውን ልጅሽን አስቢው ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢለት›› አልኳት (#ዲያቆን_አብርሃም_ይኄይስ እንደጻፈው)
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ጽንስ በማኅጸን ከተቋጠረ ከአርባኛው ቀን ጀምሮ ቅዱስ ሩፋኤል በጥበቃው የማይለየው ሲሆን፣ አንዲት ሴትም የመውለጃዋ ቀን ደርሶ ምጥ በያዛት ጊዜ ሕመሙን የሚያቀልላት እና ማኅጸኗን የሚፈታው ይኸው መልአክ ነው፡፡ ከዚህም ሥራው የተነሣ ‹ፈታሔ ማኅጸን› በመባል ይጠራል፡፡ እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ወርሀዊ በዓል በሰላም አደረሰን!
إظهار الكل...
የሚያነብ ሰው vs የማያነብ ሰው! ~ October 18, 2022 by ዲ/ን : ዳዊት : ሰሎሞን ፡፡ የሚያነብ ሰው እና የማያነብ ሰው አእምሮ ልክ ደጋ ላይ በእንክብካቤ እንዳደገ ትልቅ የዋርካ ዛፍ እና በረሃ ላይ እንደበቀለ የቀነጨረ ዛፍ ይመስላሉ። ስለመኖር ካነሳን ሁለቱም ዛፎች ይኖራሉ። የደጋው ዋርካ ዛፍ በቂ እርጥበት እና ለም አፈር ስለሚያገኝ አድጎ ይንሰራፋል። ለአእዋፋት ጎጆ መስሪያ መጠለያ፣ ለእንስሳት ከፀሐይ መጠለያ፣ ለደከመው ሰው ማረፊያ ይሆናል። የሚያነብ ሰው አእምሮም እንደዚሁ ነው። ለሰዎች በችግራቸው ጊዜ መፍትሔ ይዞ የሚገኝ የለፉበትን ያህል የሚክስ ሰዎች የሚተማመኑበት እና ራሱን የሚጠቅም ይሆናል። ለዛፉ ሁሉንም ፈሳሽ ብንደፋበት ሊያደርቁት የሚችሉትን ፈሳሽ ኬሚካሎችን ልንደፋ ስለምንችል መጠንቀቅ እንዳለብን ሁሉ ለአእምሮአችንም የሚጠቅመውን ነገር መመገብ አለብን መምረጥም አለብን። በሌላ በኩል ምንም ለም አፈር እና እርጥበት በሌለበት በረሃ ላይ የበቀለች ዛፍ ትቀነጭራለች እንጅ አታድግም። የግድ እንድታድግ እና እንድትንሰራፋ የምትመገበው ነገር ያስፈልጋታል። የምትመገበው ከሌላት ለራሷም የምትጠቅም አትሆንም ብዙም ሳትቆይ ልትደርቅ ትችላለች ወይም ጨርሳ እስከምትጠፋ እንደ ቀነጨረች ትቀራለች። የማያነብ ሰውም ራሱን አይጠቅምም ለሌሎችም መፍትሔ መሆን አይችልም አእምሮው እንደቀጨጨ ሳይጠቀም ሰው ሳይጠቅም ሕይወቱ ያልፋል። ኃይለመለኮት መዋዕል  (ዋልያ መጻሕፍት መደብር እና ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ ባዘጋጁት መርሐ ግብር ላይ ስለ ንባብ ከተናገሩት)
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.