cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Ethiopia amhra

ሰላም ፍቅር አንድነት ለሁላችን ሰላም ለንፁሀኑ ወገኔ ያላግባብ ለሚታረድ ለሚታገተዉ! በዚህ ቻናል ዜና እና ወቅታዊ መረጃዎችን እናደርሳለን። @Ethiopiaamhra

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
313
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Good news #Ethiopia : የኮሮና ክትባት በመጪው ሚያዝያ ወር ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባ ተገለጸ! ክትባቱ 20 ከመቶ ለሚሆኑ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ይዳረሳል ተብሏል፡፡ የክትባት ስራውን የሚያስተባብር ግብረሃይል በብሄራዊ ደረጃ መቋቋሙንም የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ @Ethiopiaamhra
إظهار الكل...
ዶ/ር ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል ከሁለት ወራት ዝምታ በኋላ በትናትናው ዕለት በድምፂ ወያነ ትግራይ ፌስቡክ ገፅ በቀጥታ ለህዝቡ መልዕክት አስተላለፉ! ዶ/ር ደብረፅዮን በትግራይ ላይ የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት አስመልክቶ "ህዝቡ ራሱን በራሱን የማስተዳደር መብቱን በተግባር ለማረጋገጥ በፅናት ስለታገለ የተቃጣበት ጦርነት" ያሉት ሲሆን አራት መንግሥታትና የክልሎች ልዩ ኃይሎች ተሳትፈውበታል ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል ያለው ትግል እንደቀጠለና በክልሉ ከነበረው ሰሜን እዝ የተገኘውን ኃይል በመጠቀም እየታገሉ መሆናቸውን አስታውሰው " በኃይል አለመመጣጠን ምክንያት ጊዜያዊ ወታደራዊ ብልጫ ስላገኙ ይህንን ሚዛን ለመለወጥ የመመከት ትግላችንን አጠናክረን እያስቀጠልን እንገኛለን።" ብለዋል። ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) በጠቀሱት ትግል "ከፍተኛ ዋጋ ጠይቋል" ያሉ ሲሆን። "የህወሃት መስራች አባላት ከሚባሉት ላለፉት 45 ዓመታት ከያዙት ህዝባዊ መስመር ፈቀቅ ሳይሉ የታገሉና የመሩ፣ ያታገሉና ብዙ ድል ያስመዘገቡ አዛውንት ነባር ታጋዮች በዚህ የወረራ ጦርነት፣ በጠላት እጅ ተጎድተውብናል። ከባድ መስዋዕትነት ከፍለዋል። አሁንም እየከፈሉ ይገኛሉ። የነዚህ ጀግኖቻችን መስዋዕትነት የበለጠ ቁጭትና እልህ ያስንቀናል እንጂ ፈፅሞ ከትግላችን የሚያቆመን አይሆንም።" ብለዋል። "እኛ ከመሬታችን እና ከቀያችን ለቀን የምንሄድበት ሌላ ቦታ የለንምና የተሟላ ድል እስክንቀዳጅ ህዝባዊ ጦርነት ከማፋፋም ወደ ኋላ እንደማንል ወዳጅም ጠላትም ሊያውቀው ይገባል።" በማለት አፅንኦት ሰጥተዋል። የደብረ ፅዮንን ንግግር በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም። (Via BBC Amharic) @Ethiopiaamhra
إظهار الكل...
ዶ/ር ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል ከሁለት ወራት ዝምታ በኋላ በትናትናው ዕለት በድምፂ ወያነ ትግራይ ፌስቡክ ገፅ በቀጥታ ለህዝቡ መልዕክት አስተላለፉ! ዶ/ር ደብረፅዮን በትግራይ ላይ የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት አስመልክቶ "ህዝቡ ራሱን በራሱን የማስተዳደር መብቱን በተግባር ለማረጋገጥ በፅናት ስለታገለ የተቃጣበት ጦርነት" ያሉት ሲሆን አራት መንግሥታትና የክልሎች ልዩ ኃይሎች ተሳትፈውበታል ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል ያለው ትግል እንደቀጠለና በክልሉ ከነበረው ሰሜን እዝ የተገኘውን ኃይል በመጠቀም እየታገሉ መሆናቸውን አስታውሰው " በኃይል አለመመጣጠን ምክንያት ጊዜያዊ ወታደራዊ ብልጫ ስላገኙ ይህንን ሚዛን ለመለወጥ የመመከት ትግላችንን አጠናክረን እያስቀጠልን እንገኛለን።" ብለዋል። ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) በጠቀሱት ትግል "ከፍተኛ ዋጋ ጠይቋል" ያሉ ሲሆን። "የህወሃት መስራች አባላት ከሚባሉት ላለፉት 45 ዓመታት ከያዙት ህዝባዊ መስመር ፈቀቅ ሳይሉ የታገሉና የመሩ፣ ያታገሉና ብዙ ድል ያስመዘገቡ አዛውንት ነባር ታጋዮች በዚህ የወረራ ጦርነት፣ በጠላት እጅ ተጎድተውብናል። ከባድ መስዋዕትነት ከፍለዋል። አሁንም እየከፈሉ ይገኛሉ። የነዚህ ጀግኖቻችን መስዋዕትነት የበለጠ ቁጭትና እልህ ያስንቀናል እንጂ ፈፅሞ ከትግላችን የሚያቆመን አይሆንም።" ብለዋል። "እኛ ከመሬታችን እና ከቀያችን ለቀን የምንሄድበት ሌላ ቦታ የለንምና የተሟላ ድል እስክንቀዳጅ ህዝባዊ ጦርነት ከማፋፋም ወደ ኋላ እንደማንል ወዳጅም ጠላትም ሊያውቀው ይገባል።" በማለት አፅንኦት ሰጥተዋል። የደብረ ፅዮንን ንግግር በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም። (Via BBC Amharic) @Ethiopiaamhra
إظهار الكل...
የህወሃት ሊቀመንበር የሆኑት ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ከሁለት ወራት ዝምታ በኋላ በትናትናው ዕለት፣ ጥር 22፣ 2013 ዓ.ም በድምፂ ወያነ ትግራይ ፌስቡክ ገፅ በቀጥታ ለትግራይ ህዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል። ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) በትግራይ ላይ የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ በተቋረጠው ድምፂ ወያነ ትግራይ የፌስቡክ ገፅ በቀጥታ ለ13 ደቂቃዎች በድምፅ ባስተላለፉት መልዕከት ክልሉ ላይ ደርሷል ስለተባሉ ውድመቶች፣ ቀጥሏል ስላሉት ትግል ሁኔታ እንዲሁም ለትግራይ ህዝብና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥሪ አቅርበዋል።"የትግራይ ሴቶች በተናጠልና በደቦ ይደፈራሉ። የትግራይ ሰዎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችና ነጻነቶች በከፋ መገለጫና አኳሃን ይጣሳሉ፣ ይገፈፋሉ። የትግራይ መንደሮችና ዓብያተ እምነቶች፣ የትግራይ ሰራዊት ይኑርበት አይኑርበት ሳይገዳቸው የቦምቦችና የመድፎ ዒላማ ይደረጋሉ። ውድና መተኪያ የሌላቸው ቅርሶችም ይወድማሉ፣ ይዘረፋሉ። በሚልዮን የሚቆጠር ህዝብ እንዳለ ከቀየው ወጥቶና ተፈናቅሎ የመከራ ኑሮ ይኖራል።" ብለዋል። በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፌደራል ፖሊስ በበርካታ የህወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣታቸው ይፋ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው። ከነዚህም አመራሮች አንዱ የህወሃት ሊቀ መንበር ደብረ ፅዮን ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት ያሉበት አይታወቅም።ለእስር ማዘዣው ዋነኛ ምክንያቶቹ በትግራይ ክልል በሚገኘው በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ የአገር ክህደት ወንጀል በመፈፀም፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት እንዲታገቱ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው ነው። (BBC) @Ethiopiaamhra
إظهار الكل...
#በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ64 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል መድኃኒት፣ የምግብ ምርቶች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ የትምባሆ ውጤቶች፣ አደንዛዥ ዕፆች እና የኤልክትሮኒክስ ዕቃዎች ይገኙበታል ተብሏል፡፡ @Ethiopiaamhra
إظهار الكل...
የህዳሴው ግድብ ግንባታ በታቀደለት ጊዜና በሚፈለገው መንገድ እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ እና የኢትዮጰያ ኤሌክትሪክ ቦርድ አባላት በትናንትናው ዕለት በስፍራው በመገኘት ግምገማ አድርገዋል። ከጉብኝቱ በኋላ ፣ የግድቡ ግንባታ በታቀደለት ጊዜ እየተከናወነ እንደሆነና የግንባታ ሂደቱም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡ ሚንስትሩና የቦርድ አባላቱ የግንባታ ስራውን ከሚያከናውኑ ኮንትራክተሮች ፣ ከባለሙያዎችና አማካሪዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡ ለግድቡ መጠናቀቅ መላው ኢትዮጵያውያን ከሃገር ውስጥና ውጪ እያደረጉት ያለው ድጋፍ ከምን ግዜውም በላይ ተጠናክሮ ቀጥሏልም ነው ያሉት። @Ethiopiaamhra
إظهار الكل...
የኢትዮጵያ ትልቁ ዘይት ፋብሪካ! በ4 ነጥብ5 ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የዘይት ፋብሪካ በቅርቡ ይመረቃል ተባለ! በኢትዮጵያዊው ባለሀብት አቶ በላይነህ ክንዴ በአራት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የዘይት ፋብሪካ በቅርቡ እንደሚመረቅ ባለሀብቱ ገለጹ።የበላይነህ ክንዴ ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ በላይነህ ክንዴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ ፕሮጀክት ላለፉት ስድስት ዓመታት ግንባታ ላይ መቆየቱንና አጠቃላይ ወጪውም 4ነጥብ5 ቢሊዮን ብር ደርሷል።ፋብሪካው በአሁኑ ወቅት የሙከራ ምርት የጀመረ መሆኑንና የሚመለከተውን የመንግስት አካል ይሁንታ ሲያገኝ በቅርቡ ምርቱ ወደ ገበያ እንደሚቀርብም አቶ በላይነህ አስታውቀዋል። በአገሪቱ 45 ከመቶ በላይ የሚሆነውን የዘይት ፍላጎት ከመሸፈን ባሻገር ለውጭ ገበያ ምርቶችን መላክን ያነገበው የዘይት ፋብሪካ በቅርቡ ይመረቃል ብለዋል፤ አቶ በላይነህ።እንደ አቶ በላይነህ ገለፃ፤ ፋብሪካው ዘይት ብቻ አያመርTም። ሰባት ፋብሪካዎችን በውስጡ ያቀፈ ሲሆን፤ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ የሚዘልቁ ዘመናዊ ግንባታዎች የተካተቱበት ነው። በርካታ ማሽኖችም በትልቅ ኃላፊነት የተገዙ ሲሆን ጥራታቸውን የጠበቁ እና ለቀጣይ ትውልድ ጭምር ግልጋሎት የሚሰጡ ይሆናሉ ያሉት አቶ በላይነህ፤ የዚሁን ሥራ ለማፋጠን ሲባልም 160 ከባድ መኪናዎች ገላን በሚገኘው የድርጅቱ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካው ተገጣጥመው ለሥራ ዝግጁ ተደርገዋል ብለዋል። ፋብሪካው በቀን 1ነጥጥብ5 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ያመርታል ያሉት አቶ በላይነህ፤ ፋብሪካው በዓመት 20 ሚሊዮን ኩንታል የቅባት እህሎችን የሚፈልግ ቢሆንም የአገሪቱ ዓመታዊ የማምረት አቅም ከሦስት ሚሊዮን ኩንታል የሚበልጥ እንዳልሆነ ገልጸዋል።የግብአት ችግሩን ለመፍታት ከውጭ ድፍድፉን በማምጣት ምርት በማምረት ላይ እንደሆነ የገለጹት አቶ በላይነህ፤ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ከአርሶ አደሮች እና መንግስት ጋር የተቀናጀ አሰራር በመዘርጋት ምርቱን በአገር ውስጥ መሸፈን እንደሚቻል አስረድተዋል፡፡ @Ethiopiaamhra
إظهار الكل...
ሀገር መከላከያ ሰራዊት ከአባሉ እስከ ከፍተኛ አመራሩ የኢትዮጵያ ብሄር ብሔረሰቦችን እንዲመስል እና ከወቅቱ ጋር እንዲዘምን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ ተናገሩ ። ከጊዜያት በኋላ ወደ ሰራዊቱ የሚቀላቀሉ ወጣቶች ፍላጎት መጨመሩን የገለፁት ጄኔራል ብርሀኑ ከመላ ሀገሪቱ በተመለመሉ ከፖለቲካ ወገንተኝነት የፀዱና ለሙያው ፍቅርና ክብር ያላቸው ተተኪ ወታደሮችን ለማፍራት ከፍተኛ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል ። በዚህም አበረታች ለውጦች እየተገኙ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ሠራዊቱ ዘመኑ ከደረሰበት ቴክኖሎጂ ጋር አብሮ እንዲዘምንም ሁለንተናዊ ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ጀነራል ብርሀኑ ጁላ መግለፃቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያመላክታል። @Ethiopiaamhra
إظهار الكل...
በቄለም ወለጋ ዞን 5 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ፤ 5 ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ! በቄለም ወለጋ ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ በተደረገው የሕግ የበላይነት የማስከበር እና ሰላምን የማረጋገጥ ሥራ 5 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፣ ሌሎች 5 ታጣቂዎች ደግሞ ከቆሰሉ በኋላ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡ በተያያዘ ዜና፣ በዞኑ ጃል ያዴሳ ለተባለ የኦነግ ሸኔ አባል በባንክ በኩል ሊላክ የነበረ 122 ሺህ 950 ብር ከተጠርጣሪው ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን የዞኑ ፖሊስ ገልጿል፡፡ በቄለም ወለጋ ዞን እነዚህ ፀረ ሰላም ኃይሎች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በመግታት የኅብረተሰቡን ሰላም ለማረጋገጥ የኦሮሚያ ፖሊስ በትጋት እየሠራ እንደሆነ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ @Ethiopiaamhra
إظهار الكل...
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስክ ያስተማራቸውን ከ7 ሺህ በላይ ተማሪዎቹን አስመረቀ! ዩኒቨርሲቲው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ባለፈው አመት ሳይመረቁ የቀሩትን ተማሪዎቹን ነው ዛሬ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በ3ኛ ዲግሪ እያስመረቀ የሚገኘው። ከተመራቂ ተማሪዎቹ ውስጥ 4 ሺህ 804ቱ ወንዶች ሲሆኑ 2 ሺህ 489ኙ ደግሞ ሴቶች ናቸው። @Ethiopiaamhra
إظهار الكل...