ራስን መለወጥ
الذهاب إلى القناة على Telegram
እንዴት ናችሁ? ቢዝነስ ፕላን(ቢዝነስ ዕቅድ) እንዲሰራለት የሚፈልግ በተመጣጣኝ ዋጋ ቢዝነስ ፕላን እንሰራለን! በውስጥ መስመር ያናግረን! ለውጥ በትክክልም ይመጣል። 💪ዕድገታችንም ይሳካል!!! Hello everyone, we make best Business plan. In good price contact us inside! just pick a what kind of business plan! We can chang
إظهار المزيد9 785
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-337 أيام
-8230 أيام
أرشيف المشاركات
9 785
መምህሩ ወደክፍል ሲገባ ተማሪዎቹ የሚቀመጥበትን ወንበር በገመድ ጣራ ላይ አንጠልጥለው ጠበቁት፡፡ ምንም የመገረምም የመናደድም መልክ አላሳየም፡፡ ወደተማሪዎቹ ፊቱን አዙሮ በፈገግታ አያቸውና ቃል ሳይተነፍስ ብላክቦርዱ ላይ መጻፍ ጀመረ፡፡
የሙከራ ፈተና -
የተሰጠው ጊዜ 15 ደቂቃ
የሚይዘው ነጥብ - 30 ማርክ
1. ጣራ ላይ ከተንጠለጠለው ወንበር እስከወለሉ ድረስ ያለው ርቀት ሲለካ በሴንቲሜትር ምን ያህል ይሆናል? (1 ማርክ)
2. በተንጋደደው ወንበር እና በጣራው መካከል ያለው አንግል ስንት ነው? ሙሉ ስሌቱን ከነፎርሙላው አሳዩ፡፡ (1 ማርክ)
3. ወንበሩን ጣራ ላይ በገመድ ያንጠለጠለውን ተማሪ ስም እንዲሁም ይህንን ሲያደርግ ያገዙትን ተማሪዎች ስም በሙሉ ጻፉ (28 ማርክ)
ተማሪዎች ከ30 ማርክ 28 አግኝተው አለፉ፡፡ መምህሩም አምስት ተማሪዎችን አስወጥቶ ወላጅ ካላመጡ በርሱ ፔሬድ እንደማይገቡ ነግሮ አባረራቸው፡፡
አንዳንድ ጊዜ ጓደኛዬ “ የነገርኩትን ምስጢር ሁሉ ይጠብቅልኛል ፣ በምንም አይነት ሁኔታ አሳልፎ አይሰጠኝም” ብለህ እርግጠኛ እንዳትሆን፡፡ ብዙ ሰዎች ከጓደኝነት በላይ የግል ጥቅም በልጦባቸው ተገኝተዋል፡፡
መጽሃፈ ሲራክ ምዕራፍ 8 እንዲህ ይላል፡፡ “ የሰማውን ነገር ማስቀረት አይችልምና ከቀላል ሰው ጋራ አትማከር…ዋጋህ እንዳይጠፋብህ ለሰው ሁሉ የልብህን ምስጢር አታውጣ”
በመጨረሻም "ምንም ነገር ስታደርግ ሁለቴ አስብ!"
t.me/changeitwow
ራስን መለወጥ
#Ethiopian@changeitwow
9 785
1) በማያገባህና አንተን በማይመለከትህ ጉዳይ አትግባ፣ የራስህን ኑሮ በደንብ አድርገህ እወቅና በጥበብ ኑር፣
2) በማህበራዊ ሚዲያ ለምታየው ማንኛውም ልጥፍ ርዕሱን ብቻ አይተህ ቀድመህ መልስ አትስጥ፣ አትፍረድ፣ አትፈርጅ። አስተያየት መስጠት ካለብህ በደንብ ካየህ በኋላ ስጥ። ያለበለዚያ ግልብ፣ ተናዳጅ፣ ፈራጅ፣ እና ምንም ግንዛቤ የሌለው ደደብ ሰው ተደርገህ እንድትሳል ያደርግሃል።
3) ስለ ምንም ነገር ይሁን ለመማር ዝግጁ ሁን፣ የሰውን ሀሳብ እንደየሁኔታው ለመቀበል፣ ወይም በልዩነት ለመስማማት ብልህነትን ተማር። የአንተ አላዋቂነት ድፍረት ለልጅህም እንደሚተላለፍ እወቅ። (ይህን ወደፊት በስፋት እነግርሃለሁ)
4) አንዳንድ ሰዎች በየትኛውም ነገር ላይ አውቃለሁ የሚሉ ናቸውና ራቃቸው። ከእንደዚህ አይነት ሰዎች ጋር አትከራከር ምክንያቱም ብዙ ደጋፊዎች አሏቸው።
5) ሰዎች ሁለት አይነት ማይንድሴት (ሥሪተ አዕምሮ) ያላቸው እንደሆኑ ተገንዘብ። አንደኞቹ አዳጊ አዕምሮ፣ ሌሎቹ ደግሞ ውስን(የተገደበ)። የውስን አዕምሮ ባለቤቶችን በጥበብና በሥልጠና ካልሆነ አትቀይራቸውምና ከነርሱ ጋር ስለ ለውጥ አትከራከር።
6) ራስህን ለውጥ፣ በገንዘብ፣ በሥራ፣ በአካባቢ እና በጓደኛ የተሻልክ ሁን። ለመለወጥ እንቅፋት የሆኑብህን ነገሮች ቀድመህ ለውጥ።
7) ልጅ በአጋጣሚ አትውለድ፣ ከወለድክም ብቸኛው ኃላፊነት ያለብህ አንተ (ወላጁ) ብቻ እንደሆንክ እመን። ትውልድን በተመለከተ አስተያየት ከመስጠትህ በፊት ከራስህ ልጅ ጀምር።
8) አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች በቡድን ሲሆኑ መጥፎዎች፣ በግለሰብ ደረጃ ደግሞ ጥሩዎች የመሆን እድላቸው ሰፊ ነው። ሰዎችን በግለሰብ ደረጃ ተመልከት።
9) የራስህን ኑሮ በእርጋታ ለመኖር ከሚጠቅሙህ ነገሮች አንዱ ግላዊ መሆን ነው። ለዚህም በማህበራዊ ሚዲያ ስለ ግል ሚስጥርህ፣ ስለምታደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ እየወጣህ አትለጥፍ፣ አትዘርዝር። አንዴ እንደዚያ ካደረግህ በኋላ መመለሻው ከባድ ነውና ተጠንቀቅ።
10) በልጅነትህ የደረሰብህ ቀውስ በማንኛውም መልኩ አሁን ላለህበት ሕይወት ወሳኝ ነውና ልጅህ ላይ ሌላ ቀውስ ከመፍጠርህ በፊት እሱን ችግር ለመፍታት ሞክር። በጊዜው ያልተፈታ ቀውስ ኋላ ላይ በአስቀያሚ ሁኔታ ይወጣልና።
በተጨማሪም ማህበረሰብ ከቤተሰብ እንደሚመሰረት፣ ሰዎች ደግሞ የቤተሰብ ውጤት መሆናቸውን አውቀህ ቤተሰብህ ላይ ሥራ።
ሶሻል ሚዲያ
t.me/changeitwow
ራስን መለወጥ
#Ethiopia@changeitwow
9 785
ሃያ ምርጥ የማርቲን ሉተር አባባሎች
1. ‹‹ ሕልም አለኝ! ››
2. ‹‹ መብረር ካልቻልክ ሩጥ፡፡ መሮጥ ካልቻልክ ተራመድ፡፡ መራመድ ካልቻልክ ዝግ ብለህም ቢሆን ሂድ፡፡ ምንም ነገር ስታደርግ ወደፊት መሄድህን አታቋርጥ፡፡ ››
3. ‹‹ ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግ ጊዜ ሁል ጊዜ ትክክለኛው ሠዓት ነው፡፡ ››
4. ‹‹ ከፍቅር ጋር ለመጣበቅ ወስኛለሁ፡፡ ምክንያምቱም ጥላቻ ሊሸከሙት የማይችሉ ታላቅ ቀንበር ነውና፡፡ ››
5. ‹‹ በስተመጨረሻ ከጠላቶቻችን ንግግር ይልቅ የወዳጆቻችንን ዝምታ ነው የምናስታውሠው፡፡ ››
6. ‹‹ በየትኛውም አካባቢ ያለ ህገወጥነት ለዓለም ፍትህ አደጋ ነው፡፡ ››
7. ‹‹ እምነት ምንም እንኳን ሙሉው የሕይወት መሰላል ባይታይህም የመሠላሉን የመጀመሪያውን እርካብ መርገጥ ነው፡፡ ››
8. ‹‹ እውነተኛው የትምህርት ዓላማ አዋቂነት እና መልካም ባህሪን አንድ ላይ ማድረግ ነው፡፡ ››
9. ‹‹ የማያልቀውን ተስፋ አጥብቀን በመያዝ የበዛውን ውድቀታችንን በፀጋ መቀበል አለብን፡፡ ››
10. ‹‹ ብርሃን ጨለማን ያሸንፋል እንጂ ጨለማ ጨለማን አይገፍም፡፡ ጥላቻም በጥላቻ አይሸነፍም፡፡ ያን ማድረግ የሚቻለው ፍቅር ብቻ ነው፡፡ ››
11. ‹‹ በዓለም ላይ ከመሃይምነት እና ከጅልነት የበለጠ አደገኛ ነገር የለም፡፡ ››
12. ‹‹ ጠላትን ጓደኛ ማድረግ የሚችለው ሃያሉ ፍቅር ብቻ ነው፡፡ ››
13. ‹‹ ማንም ሠው ቢሆን ሕገወጥ ለሆኑ ህጎች ያለመገዛትና ያለመታዘዝ ሞራላዊ ሃላፊነት አለበት፡፡ ››
14. ‹‹ ሁላችንም አብረን ተስማምተን ለመኖር መማር አለብን፡፡ አልያ ግን ልክ እንደ ጅል እርስበራስ መጨራረስ ሊኖርብን ነው፡፡ ››
15. ‹‹ ይቅርታ ማድረግ በሆነ ጊዜ ላይ ብቻ የምናደርገው ሳይሆን ቋሚ የሆነ የሁልጊዜ አመለካከት መሆን አለበት፡፡ ››
16. ‹‹ በዓለም ላይ እንደ ፍቅር ፅኑ እና ቋሚ ሃይል ምንም የለም፡፡ ››
17. ‹‹ ታሪክ ሠሪዎች ሳንሆን በታሪክ የተሠራን የታሪክ ፍጡራን ነን፡፡ ››
18. ‹‹ ጥላቻ ጠዪውን አጥፊ ነው፡፡ ››
19. ‹‹ ነፃነት በጨቋኞች ነጻ ፈቃድ የሚገኝ ሳይሆን በጭቁኖች የሚፈለግና ሚጠየቅ ነው፡፡ ››
20. ‹‹ ክዋክብቶችን ማየት የሚቻለው በጨለማ ብቻ ነው፡፡ ››
ተጨማሪ ካለ ይጨምሩበት...
t.me/changeitwow
ራስን መለወጥ
9 785
እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ 1926 አንድ ታዋቂ የሩሲያ ደራሲ በድብርትና በሐዘን ስሜት በመሰቃየቱ ህክምና ለማግኘት ወደ ስነ ልቦና ሐኪም ጎራ አለ።
.
.
ከምርመራው በኋላ የሐዘን ስሜት የሚያጭሩ ተረቶችን ከማንበብ ታቅቦ በምትኩ ደስታና ሳቅ የሚፈጥሩትን እንዲያነብ ሐኪሙ መከረው። እንዲያውም አስቂኝ የሆኑትን የሚኻኤል ዞሼንኮን (Mikhail Zoshchenko) ድርሰቶች ቢያነብ በጤናው ላይ አመርቂ ለውጥ እንደሚያመጣ አበክሮ አስረዳው።
ግና ደራሲው የሰጠው መልስ ሐኪሙን በድንጋጤ እንዲዋጥ አደረገው- "ሚኻኤል ዞሼንኮ ማለት እኔ ነኝ" ብሎ።
.
.
አሜሪካዊው ጸሐፊ አልበርት ሐበርድ
"ለሌሎች የመጽናኛ እና የደስታ ስሜት ፈንጣቂ የሆኑ ብቁ ሰዎች ብዙ ጊዜ ራሳቸውን ለማጽናናት ሳይቻላቸው ይቀራሉ" ይለናል። ራስህ የፈጠርከው መድሃኒት ለሌሎች ፍቱን ሆኖ ያንተን በሽታ ለማርከስ ሲሰንፍ እንደማለት ነው።
ሶሻል ሚዲያ
ራስን መለወጥ
t.me/changeitwow
9 785
በናይጄሪያ ውስጥ ይሄን ህፃን ልጅ አንዲት እንግሊዛዊት... በሰባዊነት ይሄ ልጅ ረዳችው ወስዳም በማሳደግ አገዘችው። አድጎና
ከነበረበት ወደ ተሻለ ደረጃ ደርሶ ተመርቆ ...
👉አሁን ላይ ይሄን ይመስላል
A Nigerian orphan once rescued from the streets by a compassionate British woman, has triumphantly graduated from university. Heartfelt congratulations to him on this remarkable achievement! ❤️
ራስን መለወጥ
#Ethiopia@changeitwow
9 785
" ድሀ በበዛባት አገር ሀብታምም ደሀ ነው "
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ
ጋዜጠኛ ፦ በውጭ ሀገር እንደምናውቀው አትሌቶች
ቅንጡ Super Car የሚባሉትን መኪናዎች ነው
የሚያሽከረክሩት ቀነኒሳስ?
ቀነኒሳ ፦ እውነት ለመናገር በሀገራችን አለኝ ብለህ ዘመናዊና ቅንጡ መኪና ይዘህ ለመውጣት ህሊናህ አይፈቅድም::
ምክኒያቱም ከቤትህ ወጥተህ እስክትመለስ በየመንገዱ ተቸግሮ ማደሪያና የሚበላው አጥቶ የሚለምንህ አለ።
በዚህ ሁሉ ውስጥ አንተ አለኝ ብለህ በዚህ ህዝብ ላይ ልታይ ልታይ ማለት ምን ያደርጋል? አንድ አባባል አለ 'ድሀ በበዛባት አገር ሀብታምም ደሀ ነው' ።
©️ ኢትዮ አዲስ
ሁሌም ስሰማው ይመቸኛል።
ራስን መለወጥ
T.me/changeitwow
9 785
በግሪክ የሚነገር አፈታሪክ አለ፡፡ ሚዳስ የሚባል ንጉስ ነበር፡፡ ይሄ ንጉስ በሃብት የበለፀገ፣ ግዛቱም የተስፋፋ ቤተመንግስቱም በዘመኑ ቅንጡ የሚባል ነበር፡፡
ነገር ግን ካለው ሀብት ይልቅ ብዙ ወርቅ ቢኖረው በጣም ይወድ ነበር፡፡ የደስታው ጣራ ፤ የእርካታው ከፍታ መድረሻው ወርቅ በወርቅ መሆን ብቻ ነው፡፡
የሚነካው ነገር ሁሉ ወደወርቅ ይለወጥለት ዘንድ ምኞት ነበረው፡፡ ታዲያ አንድ ቀን ዳዮንይሰስ የተባለ የወይንና የፈንጠዝያ አምላክ በእሱ ቤተመንግስት አቅራቢያ ሲያልፍ ከንጉሱ ጋር ተገናኘ፡፡
ንጉሱም የነካው ነገር ሁሉ ወደወርቅ ይለወጥለት ዘንድ ለአምላኩ ጥያቄ አቀረበለት፡፡
አምላኩ ጉዳዩን በደንብ እንዲያስብበት በማስጠንቀቅ በሚቀጥሉት ቀናት ጥያቄህ መልስ ያገኛል ብሎት ተሰነባበቱ፡፡
በበነጋታውም ንጉሱ የነካው ነገር ሁሉ ወደወርቅ መለወጥ ጀመረ፡፡
ጠረጴዛው ፣ ወንበሩ ሁሉ ወርቅ ሆነለት፡፡ ችግሩ የመጣው ወደ በኋላ ነው፡፡ ምግብ ለመመገብ ቁጭ ሲል ምግቡ ወርቅ ሆነበት፡፡ ከሆነለት ወደሆነበት ተቀየረ፡፡
የሚወዳት ልጁ ወደክፉሉ ገብታ ሊያቅፋት እጁን ሲዘረጋ የወርቅ ሃውልት ሆና ተለወጠችበት፡፡
ታዲያ ንጉሱ በዚህ ጊዜ ልመናው ወደ እርግማ እንደተለወጠበት ተገነዘበ፡፡
ያ ያስደስተኛል ብሎ ያሰበው ነገር ፍርሃት ለቀቀበት፡፡ ሰቀቀኑ አላስቀምጥ አላስተኛ አለው፡፡
በመጨረሻ ወደአምላኩ ጮሆ የሰጠውን እንዲተውለትና እንደቀድሞው እንዲሆን ጠየቀ፡፡ አምላኩም ጥያቄውን ተቀብሎ ወደወንዝ ሄዶ ቢታጠብ ሁሉ ነገር ወደቀድሞው እንደሚመለስ ነገረው፡፡
ከታጠበ በኋላም የሚወደውን ይበላ ዘንድ ቻለ፡፡ ያቺን የሚወዳትን ልጁንም አቀፈ ይለናል ተረኩ፡፡
የተረቱ ዋና ቁምነገር የምንጠይቀውን ማወቅና የበዛ ስግብግብነት ሌላ ጣጣ ውስጥ ሊከትተን እንደሚችል የሚያስተምር ነው፡፡
ለአዲስ ዓመት ብዙ ሰው ብዙ ነገር ይመኛል ፣ ያቅዳል፡፡ አምላኩን የሚጠይቀው ነገር የትየለሌ ነው፡፡
ነገር ግን የሚመኘው ፣ ያቀደው ሁሉ ቢሳካለት ፤ የጠየቀውን ቢያገኝ የሚያስደስተው ላይሆን ይችላል፡፡
የሚመኘውንና ያቀደውን ነገር ከማግኘቱ በፊት የአዕምሮ ሰላም ፣ ደስታና እርካታ አገኝበታለሁ ወይ ብሎ ቀድሞ መጠየቅና መመርመር ካልቻለ ከላይ እንደተገለፀው ንጉስ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡
የምንንገበገብለት ነገር ሁሉ ሰላም የሚሰጥ ነው ወይ ብሎ መጠየቅ ብልህነት ነው፡፡ በአዲስ ዓመት አዲስ ነገር ማሰብ የተለመደ ነው፡፡
ነገር ግን አዲስ ነገር ለማሰብ ዓመት መጠበቅ አይገባም፡፡ እያንዳንዱ ቀን ሁሌም አዲስ ነው፡፡
ግሪካዊው ፈላስፋ ዲሞክሪተስ ‹‹ሁልጊዜ አዳዲስ ነገሮችን አስብ (Think new things everyday)›› የሚለው አዳዲስ ነገሮችን ማሰብ አዲስ ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን ውስጥን የሚለውጡ ፣ ህሊናን የሚያነቁ ፣ ልቦናን የሚያሞቁ፣ መንፈስን የሚያበረቱ መሆን አለባቸው ማለቱም ነው፡፡
አዲስ ነገር ሁሉ ሁሌ ጠቃሚ አይሆንም፡፡
ለውጥ ሁሉ የእውነት የሚለውጥ ላይሆን ይችላል፡፡
በርግጥ ለውጥ በግዴታም ቢሆን የማይቀር ነው ፤ ዕድገት ግን ወድደህና ፈቅደህ ፤ አስበህና ተግብረህ የምታመጣው ነው፡፡
ምንም ነገር ያለምርጫ እውን አይሆንም፡፡ የመረጥከውን በእጅህ ለማድረግ ስትጥር ነው ያንተ የሚሆነው፡፡
አዲስ ዓመት የሚለውጥህ የእውነት ስትሰራበት ነው፡፡ ዘመን በራሱ ከሃሳብ በሽታህ ፤ ከአመለካከት ደዌህ አይፈውስህም ፤ አንተ ነህ በዘመን ውስጥ መዳንን ታገኝ ዘንድ የምታደርገው፡፡
‹‹የመዳን ቀን ዛሬ ነው›› ማለት ለመዳን የፈቀድክበትና ያመንክበት ፤ የወሰንክበትና በተግባር ድነት የጀመርክበት ዕለት ነው ማለት ነው፡፡
እንደገና መጀመር ለሰው ሁሉ በነፃ የተሰጠ ነፃ ፈቃድ ነው፡፡
ስለዚህ አስበህ ፣ አሰላስለሀ ፣ ለክተህና መዝነህ እንደገና ጀምር!
በድጋሚ Happy new year!
፡
ከቀስቃሽ አሳቦች
ራስን መለወጥ
9 785
🎹 በጣም ጠቃሚና አስተማሪ ነውና ይነበብ
በድሮ ዘመን አንድ ልዑል የንግስና ዘውዱን ከመድፋቱ በፊት ሚስት እንዲያገባ የሚያስገድድ ባህል ነበር፡፡
እናም የንግስና ዘውዱን ለመድፋት የተቃረበ አንድ ልኡል ታማኝና ሚስት የምትሆነው ሴት ማግኘት ፈለገና በመላ ሀገሪቱ አዋጅ አስነግሮ ወጣት ሴቶችን ለማወዳደር ሰበሰበ፡፡
በዛች ሀገር ውስጥ የምትኖር የአንዲት አገልጋይ ሴት ልጅ ነበረች፡፡ ልጅቱም ልዑሉን አጥብቃ ታፈቅረው ነበር፡፡ እናም ይቺ ልጅ
ውድድሩን እንደሰማች ከመላ ግዛቲቱ ተሰባስበው የልኡሉ ሚስት ለመሆን ከሚፎካከሩት መካከል አንዷ ለመሆን ወሰነች፡፡
ነገር ግን አገልጋይ እናቷ “ተይ ወደ ቤተ-መንግስት ገብተሽ አትወዳደሪ፤ ከመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ቆነጃጅትና ሀብታም ሴቶች
ናቸው የሚመጡት፡፡ ሞራልሽን ይነኩታል፡፡ ተይ ልጄ እሱን ማግባት አትችይም አንቺ ደሀ ነሽ” አለቻት፡፡
ልጅቷ ግን አሻፈረኝ አለች፡፡ “ከእነዛ ሁሉ ቆነጃጅትና ሀብታም ሴቶች እኔን እንደማይመርጥ አቃለው፤ ነገር ግን ቢያንስ ለመጨረሻ ግዜ ከእሱ ጋር ማውራት እችላለው፡፡” ብላ ወደ ውድድሩ ገባች፡፡
በቀጣዩ ቀን ሁሉም ቆነጃጅቶች በቤተ-መንግስት ተሰበሰቡ፡፡ ከደሀዋ ወጣት ሴት በስተቀር ሁሉም በሚያማምሩ ልብሶችና ጌጣጌጦች ተውበው ነበር፡፡
🎋 በመቀጠል ልኡሉ “ለሁላችሁም የአበባ ዘር እሰጣችኀለው፤ ከ6 ወር በኀላ በጣም የሚያምር አበባ አሳድጋ ያመጣችልኝ ሴት ሚስቴ
ትሆናለች” አለ፡፡ ሁሉም ሴቶች የሚተክሉትን የአበባ ዘር ወሰዱ፤ ደሀዋ ወጣትም እንደዛው፡፡
⚡️ወጣቷ ዘሩን በአበባ መትከያ ውስጥ ከተከለችው 3ወራት አለፈ፤ ነገር ግን አበባው ሊበቅል አልቻለም፡፡ በጣም ተረበሸች፡፡
የግብርና ባለሙያዎችን አማከረች፡፡ ነገር ግን አበባው ሊበቅል አልቻለም፡፡
6ኛው ወር ደረሰና ሴቶቹ ሁሉ ዳግም በቤተ-መንግስት ተሰበሰቡ፡፡ ከደሀዋ ልጅ በስተቀር ሁሉም በአበባ መትከያ የሚያማምሩ አበቦችን ይዘዋል፡፡
🧺 ደሀዋ ልጅ ደሞ የአበባ መትከያውን ብቻ ይዛለች፡፡
⚡️ በመቀጠል ልኡል ውሳኔውን አስተላለፈ፡፡ “ሚስቴ የምትሆነውን ሴት መርጫለው፡፡ የአበባ መትከያ ብቻ የያዘችው ወጣት ሚስቴ ትሆናለች” አለ፡፡
🎋 ሁሉም ሴቶች “እኛ የተጠየቅነውን አበባ ይዘን መተን እሷ ባዶ እጇን እንዴት ትመረጣለች?” እያሉ አጉተመተሙ።
ልዑሉ ቀጠለና “የሰጠኃችሁ ዘር የማይበቅል ነበር፤ ሁላችሁም ግን ከየት እንደሆነ ባላቅም አበባ ይዛችሁ መጣችሁ፡፡
❤ይቺ ሴት ግን የታማኝነት አበባን ነው ይዛ የመጣችው” አለ፡፡
⚡️ብዙ ግዜ የሆነ ነገር ለማግኘት በጣም ከመጓጓታችን የተነሳ አብዛኞቻችን እውነታውን በሀሰት እንቀይራለን፡፡
ልባም ሴት
ራስን መለወጥ
t.me/changeitwow
9 785
በመድረክ ስሙ Gucci Mane። ተብሎ የሚጠራው ራፐር ራድሪክ ዴቪስ በ2014 ለእስር ይዳረጋል ታዲያ እስር ቤት ከመግባቱ በፊት ለሚስቱ ኬይሺያ ካኦየር 2 ሚሊዮን ዶላር ይሰጣትና እሱ የተፈረደበትን ፍርድ ለመቀበል ወደ እስር ቤት ያመራል። ዶላሩንም ለሚስቱ የሰጣት እሱ በሌለበት ጊዜ በቀጣይ ህይወታቸውን ለማስተካከል በደንብ እንደምታስተዳድር ስላመነባት ነው እሷም አመኔታዋን ሳታጓድል በታማኝነት በጥበብ አዋለችው ። እ.ኤ.አ. በ2016 ከእስር ሲለቀቅ በተሰጣት2 ሚሊዩን ዶላር የተለያዩ ስራዎችን በመስራት 6 ሚሊዮን ዶላር አድርጋ ጠበቀችው በዚህ የተነሳም ግንኙነታቸው የበለጠ እንዲጠብቅና በአደባባይ ታሪካቸው የተከበረ አካል ሆኖ ብዙዎችን ከማነጋገሩም በላይ ይህ አስደናቂ እውነተኛ ታሪካቸው The Mane Event የተባለ reality show ላይ ቀርቦ ብዙ ተመልካችም አግኝቷል ምን ለማለት ነው ለወር አስቤዛ መግዣ የሚሆን ብር ሰጥተህ አለቀ ስትባል" የት አድርሰሽው ነው ?"ብለህ ከመጠራጠር ይልቅ ሙሉ በሙሉ ሚስትህን አምነህ እድሉን ከሰጠሀት እጥፍ አድርጋ ትሰጥሀለች ሚስት ያልታመነች ማን ይታመናል ? ለማለት ነው !!!
In 2014, rapper Gucci Mane gave his last $2 million to his girlfriend, Keyshia Ka'oir, before heading to prison! Instead of spending it, she multiplied it — turning that $2 million into $6 million through savvy business moves and smart investments. When Gucci came home, she handed it all back.
🙏ይሄ ግን ሁሉንም ሚስት አይመለከትም❗️
t.me/changeitwow
ራስን መለወጥ
9 785
ትንሹ ልጅህ እንዲህ ብሎ ቢመልስል...
"ያንን የተከመረውን የጓሮውን ሳር ቁረጥና 300ብር እከፍልሃለሁ" ስትለው። ልጅ አሰብ በማድረግ
"ለሌላው ሰው በ150አሰርቼ 150ብሩን ለራሴ ማስቀረት ይቻላል።" ብሎ ሲመልስህ ስለልጅ ምን ታስባለህ?
ራስን መለወጥ
t.me/changeitwow
9 785
1. ‹‹ ሠላምን በጉልበት ማስጠበቅ አይቻልም፡፡ ሠላምን ማስጠበቅ የሚቻለው በመግባባት ብቻ ነው፡፡ ››
2. ‹‹ ስህተት ሠርቶ የማያውቅ ሠው ምንም ነገር ሞክሮ አያውቅም ማለት ነው፡፡ ››
3. ‹‹ ሁሉም ሠው ብሩህ ጭንቅላት አለው፡፡ ነገር ግን አሣን ዛፍ መዝለል አይችልም ብለህ ችሎታውን ካጣጣልከው በህይወትህ ሙሉ አሣ ደደብ እንደሆነ ታስባለህ፡፡ ››
4. ‹‹ ዓይነ ሕሊና ከዕውቀት የላቀ አስፈላጊ ነው፡፡ ››
5. ‹‹ ትምህርት አዕምሯችን የበለጠ እንዲያስብ እንጂ ጥሬ ሃቆችን ለመለማመድ አይደለም፡፡ ››
6. ‹‹ ሙከራህን እስከምታቆም ድረስ በህይወት አትሸነፍም፡፡ ››
7. ‹‹ አንድን ነገር በቀላል ቋንቋ መግለፅ ካልቻልክ ነገሩን አልተረዳኸውም ማለት ነው፡፡ ››
8. ‹‹ እብደት ማለት አንድን ነገር በተመሳሳይ ዘዴ ደግሞ ደጋግሞ በመስራት የተለየ ውጤት መጠበቅ ነው፡፡ ››
9. ‹‹ ደስተኛ ሕይወት ለመኖር ከፈለግክ አንተነትህን ከሠዎች ወይም ከነገሮች ጋር ከማወዳደር ይልቅ ከግብህ ወይም ከዓላማህ ጋር ራስህን እሠር፡፡ ››
10. ‹‹ ስኬታማ ለመሆን ከፈለግክ የስኬት ፍላጎትህ እወድቃለሁ ብለህ ከምትፈራው ፍርሃትህ በእጅጉ የበለጠ መሆን አለበት፡፡ ››
11. ‹‹ መቀራረብ በፍቅር ለመውደቅ ዋስትና አይሆንም፡፡ ››
12. ‹‹ ዋጋ ያለህ ሠው ለመሆን ሞክር እንጂ ስኬታማ ብቻ ለመሆን አትሞክር፡፡ ››
13. ‹‹ ምክንያታዊነት ከአንድ ቦታ አንስቶ ወደሌላ ቦታ ሊወስድህ ይችላል፡፡ ዓይነ ሕሊና ግን የትም ይወስድሃል፡፡ ››
14. ‹‹ ጎበዝ ሠው ችግሮችን ይፈታል፡፡ ብልህ ሠው ግን ችግሮቹ መልሠው እንዳይፈጠሩ ያስወግዳቸዋል፡፡ ››
15. ‹‹ ተፈጥሮን በጥልቀት ተመልከት፡፡ ያን ጊዜ ሁሉንም ነገሮች በተሻለ ትረዳለህ፡፡ ››
16. ‹‹ ሴቶች ብዙ ጊዜ የሚጨነቁበት ወንዶች ጨርሠው በረሷቸው ነገሮች ላይ ነው፡፡ ወንዶችም ብዙ ጊዜ የሚጨነቁበት ጉዳይ ሴቶቹ በማያስታውሷቸው ነገሮች ላይ ነው፡፡ ››
17. ‹‹ ቅዱሱን ጉጉትህን አትጣለው፡፡ ››
18. ‹‹ የአመለካከት ድክመት እየቆየ ሲሄድ የባህሪ ድክመት ይሆናል፡፡ ››
19. ‹‹ ሞትን መፍራት ማለት ተገቢ ባልሆኑ ፍርሃቶች መንቦቅቦቅ ነው፡፡ ምንም ስጋት የሌለበት ሠው ቢኖር የሞተ ሠው ብቻ ነው፡፡ ››
20. ‹‹ ፍፁም የማይመስለውን የሚሞክሩ የማይቻለውን የሚችሉ ናቸው፡፡
t.me/changeitwow
#ሼርርርር #life #Wow #post #tiktok #trend #viral #like #new #share #best #Ethiopia #love
9 785
👍12. ነገሮች ሁልጊዜም ማስታወስ ያለብን!
1ኛ ትላንት አይቀየርም
2ኛ አማራጭ አሳቦች እናንተን አይገልፁም
3ኛ የሁሉም ሰው ጉዞ ይለያል
4ኛ ሁልጊዜም ነገሮች በጊዜ ውስጥ ይሻላሉ
5ኛ መፍረድ የማንነታችን መገለጫ ነው
6ኛ በጣም ተጨንቆ ማሰብ ወደ ሀዘንተኛ ይቀይራል።
7ኛ ደስታ ከውስጥ የሚመጣ ነው
8ኛ በጎ አሳቦች በጎ ነገሮችን ይፈጥራሉ
9ኛ ሁሉም ነገር ወደ መጣበት ይመለሳል።
10ኛ ፈገግታ ይጋባል
11ኛ ቅንነት ነፃ ነው።
12ኛ የምታቋርጡ ከሆነ ትሸነፋላችሁ
t.me/changeitwow
9 785
➡ አንዳንድ የህይወት መርሆዎች፦💚💙🌱
🍄፩) ቸኩለህ ቃል አትግባ። ስትቸኩል
የገባኸውን ቃል ልታጥፍ ትችላለህ።
ብታከብረው እንኳን ባልገባሁ ብለህ
የምትጸጸትበት ሊሆን ይችላል። ማንኛውንም
ውሳኔ ከመወሰንህ በፊት አስተውል።
🍅፪) በሌላቸው ሰዎች መሃል ስለሌላቸው ነገር
አብዝተህ አታውራ። በማጣቴ ያላግጣል ሊሉህ
ይችላሉ።
🍓፫) በሰዎች ንግግርና የግል ህይወት ላይ ጣልቃ
አትግባ። ባያከብረኝ፣ ቢንቀኝ ነው ይሉሃል።
🍍፬) ከሰው ምንም አትጠብቅ፤ በሰው ላይም ተስፋ
አታድርግ። የሚቻልህን አድርገህ ሌላውን
ለፈጣሪ ንገር።
🌰፭) ለሁሉም ሰው ያለአድልኦ መልካም ሰው ሁን፤
መልካም ስትሆን እውነተኛ ደስታ ታገኛለህ።
🌵፮)የሰው እንባ፣ ላብ እና ደም ፈፅሞ አይኑርብህ።
በምድር ስትኖር ስጋህ፣ ስትሞት ደግሞ
ነፍስህ ስትደነግጥ ስትሸማቀቅ ትኖራለችና።
🍇፯) የራስህን ክብር እወቅ። ለሰው ክብርም
ተጠንቀቅ። ስታከብር የበለጠ ትከበራለህ።
🍑፰) አስተሳሰብህ ህይወትህ ነውና
አስተሳሰብህን ቀና ለማድረግ ጣር። ቀና
ስትሆን ሌላ ቀና ትፈጥራለህ። በቀልን፣ ቂምና
ጥላቻን አስወግድ። ይቅር ባይ እንጅ በቀለኛ
አትሁን።
🍇፱) ከፍቅር ጋር ኑር፣ የህይወት መርህህ ፍቅር
ይሁን። ፍቅር ሲኖርህ ሰብዓዊነትህ
ይጠነክራል፤ የበለጠ ፈጣሪን ትፈራለህ።
እውነተኛ፣ ሀቀኛ ትሆናለህ።
🍈፲) አጥፍተህ ከሆነ ይቅርታ ጠይቅ።
ይቅር ስትል ያንተንም የሌላውንም ልብ
ትጠግናለህ። ይቅር ማለት ትልቅነት እንጅ
ሽንፈት አይደለም።
🍓፲፩) አምላክህን አመስጋኝ ሁን። የምትኖረው
በፈቃዱ ነውና ምስጋናህ በሁኔታ ላይ
ሳይመሰረት፣ ብታገኝም ብታጣም ተመስገን
በል።
🍅፲፪) ፈጽሞ አትዋሽ። እውነተኛ ሁን። ህይወት
አጭር ናትና ዋሽተህ የምትኖረው በእውነት
ከምትኖረው አይበልጥም። በዋሸህ ቁጥር
ከራስህ፣ ከሰውና ከፈጣሪህ ጋር ትጣለህ።
🍄፲፫) በክፉ አትቅና። በጎ ነገር ለመስራት ካልሆነ
በስተቀር ቅናት ጥፋትን ያመጣል፤
ብዙ ቤተሰቦችን በትኗዋል።
🍅፲፬) አታመንዝር። ራስህን ግዛ። ይህን ስታደርግ
ስሜትህን ትቆጣጠራለህ፤ ራስህንና
ቤተሰብህን ታድናለህ።
ከተመቻችሁ Follow ,Like እና ሼር አድርጉ 👍
t.me/changeitwow
ራስን መለወጥ
#followmeplease@changeitwow
9 785
#_ይቺን_ጣፋጭ_ታሪክ_ተጋበዙልኝ
አንድ ጊዜ ባል ሚስቱን ሸዉዶ ጭፈራ ቤት ይገባላችኋል…ሲጋት ያመሽና ስክር ጥምብዝብዝ ብሎ ይወጣል..በጣም ስለመሸ እንደምንም እየተንገዳገደ ቤቱ ይደርሳል፡፡ከዛ እሱም እኔም ተራኪዉም አናስታዉስም፡፡
በሚቀጠለዉ ቀን ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነሳ ሃንጎቨር ጭንቅላቱን ሊያፈነዳዉ ደርሷል፡ አራሱን ያገኘዉ ግን አልጋዉ ላይ በትክክል አንሶላዉ ዉስጥ ገብቶ ተኝቶ ነዉ፡፡ገረመዉ…በቃ ሚስቴ ገደለችኝ እንደዛ ሰክሬማ አይታኝ መቼም ቢሆን አታናግረኝም እያለ ከራሱ ጋር ንትርክ ገጥሟል፡፡እንደምንም ተነስቶ ዞር ሲል አልጋዉ ጎን አስፕሪንና ዉሃ በብርጭቆ ተቀድቶ ተቀምጦለታል፡፡ግራ ገባዉ…እንዴ ሚስቴ ናት ይህን ያደረገችዉ ! እንዴት ኣላከበደችም ብሎ ተገረመ፡፡አስፕሪኑን ከዋጠ በኋላ ወደጠረጴዛዉ እየተጎተተ ሄደ በሚስቱ የተፃፈ አጭር መልእክት እንዲህ ይላል ‹የኔ ማር ቁርስ ስለደረሰ የታችኛዉ ክፍል ዉረድና ከልጅህ ጋር ቀማምስ…ዋ ሳትበላ እንዳትሄድ!›
ባል አሁን ተደነጋገረ…እነዴት ያለች ሚስት ነዉ ያገባሁት እያለ ወደታችኛዉ ክፍል ወረደ፡፡ የስምንት አመት ልጁ ቅርስ እየበላ ነበር…ልጁን ግንባሩ ላይ ሳም አድርጎ ‹ትላንት ቤት ሰክሬ ስገባ እናትህ ምን አለች? መቼም ንዴቷን መቆጣጠር እንደማትችል ይገባኛል › አለዉ፡፡
‹ኸረ አባዬ እሷ እንኳን ልትበሳጭ ሳቅ በሳቅ ሆና ነበረ…በሩን ስታንጓጓዉ ከአልጋዋ ብድግ ብላ በሩን ከፍታ አንተን እንደኅፃን ልጅ ተሸክማህ ማለት ይቻላል አልጋ ላይ አስተኛችህ፡፡ከዛ ልብስህን ልታወልቅልህ ስትሞክር ምን አንዳልክ ታዉቃለህ?›
‹ምን አልኩ ? › አለ አባት ተደናግሮ
‹ አንቺ ሴትዮ እንዳትነኪኝ…እኔ ባለትዳር ነኝ በፈጠረሽ አትንኪኝ አልካት።😊
ራስን መለወጥ
@changeitwow
9 785
አሉታዊ አስተሳሰብን እናስወግድ !"
____
አሉታዊ አስተሳሰብ ወይም Negative Thinking የተለያዩ አይነቶች አሉት። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ Over Generalization ይባላል። ለምሳሌ ፦ አንድ ሀገር ሄድኩና አንድ ናይጄሪያዊ አግኝቼው ጉዳት አደረሰብኝ እንበል። ያ ግለሰብ ያደረሰብኝን ጉዳት ከእርሱ ጋር በቀጥታ ከማገናኘት ይልቅ የናይጄሪያ ሰዎች እኮ ክፉዎች ናቸው፤ መጥፎዎች ናቸው! ብዬ እጠቀልላለሁ። ይህም የተሳሳተ መረዳት የአሉታዊ አስተሳሰብ አንዱ አካል ነው።
ሁለተኛው አይነት ደግሞ Polarization ይባላል።ፐለምሳሌ ፦ የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደርን በተመለከተ አንዳንዶች ፈጽመው ሙሉ በሙሉ ሲቃወሙት ሌሎች ደግሞ ሙሉ በሙሉ ይደግፉታል። የሚቃወሙት ይህ አስተዳደር አንድም በጎ ነገር አያደርግም ሲሉ፣ የሚደግፉት ደግሞ ይህ አስተዳደር አንድም ጥፋት አያጠፋም፣ ፍጹም ነው ይላሉ። ይህ ዋልታ ረገጥ አስተሳሰብ ነው Polarization የሚባለው።
ሶስተኛው አይነት Mental Filtering ይባላል። ለምሳሌ ፦ እኔ በአንድ አዳራሽ ውስጥ 2000 ሰዎች በተሰበሰቡበት ስልጠና ሰጠሁ እንበል። እያስተማርኩ እያለ አንድ ሰው ብድግ ብሎ አዳራሹን ጥሎ ወጣ። ማታ ቤቴ ስገባ የማስበው ሰለተማሩት እና ስለተደሰቱት 1999 ሰዎች ሳይሆን ጥሎ ስለወጣው አንድ ሰው ይሆናል። ይህ Mental Filtering ይባላል፡፡ ይጎዳል! በሌላ ምሳሌ ላስረዳ ፦ አንድ የእኔ ቪዲዮ ከወጣ በኃላ ብዙ አስተያየቶች ይሰጣሉ። 1000 ጥሩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል እንበል፤ ከእነሱ መሀከል ግን አንድ ሰው ጥሩ ያልሆነ መጥፎ አስተያየት ሰጠ። አስተያየቶቹን አንብቤ ስጨርስ አእምሮዬ ውስጥ የሚቀረው ያ መጥፎ አስተያየት ከሆነ Mental Filtering ይባላል። እነዚህ አሉታዊ አስተሳሰቦች ከአእምሮአችን ተጠርገው መውጣት አለባቸው፡፡
አራተኛው የአሉታዊ አስተሳሰብ አይነት Discounting the Positive ይባላል። በዚህ መገለጫ ማንኛውም እኛ ያለንን ጥሩ ነገር እናጣጥለዋለን። ለምሳሌ አንድ ሰው አንዲት ሴትን “ቆንጆ ነሽ" ካላት መልሷ "ምን ዋጋ አለው ቁንጅና? ታጥቦ አይጠጣ!" ትለዋለች። ጥሩ ተምረሃል" ከተባለ ሌላው ሰው “ምን ዋጋ አለው ብለህ ነው ትምህርት! ገንዘቡ ያለው እንደሆነ ያልተማሩት ጋር ነው" ይላል። የሚነገራቸውን ጥሩ አስተያየት ሁሉ ያጣጥሉታል፤ አይቀበሉትም ይህም Discounting the Positive ይባላል።
አምስተኛው የአሉታዊ አስተሳሰብ አይነት Jumping to Conclusion ይባላል። ለምሳሌ ፦ አንድ ሰራተኛ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደርጋል። ንግግሩን ከጨረሰ በኃላ አንድ ክፍል ሀላፊ የእርሱን ንግግር የሚቃወም የሚመስል ነገር ተናገረ እንበል። በሌላ ቀንም ባጋጣሚ ይህ ሰራተኛ ከተናገረ በኃላ ያው የቢሮ ሀላፊ የሰራተኛውን ሀሳብ የሚቃወም ሀሳብ ተናገረ። በዚህ ጊዜ ሰራተኛው ይሄ ሰውዬ በጣም ይጠላኛል ብሎ እርግጠኛ ይሆናል። ይህም Jumping to Conclusion ይባላል።
ስድስተኛው የአሉታዊ አስተሳሰብ መገለጫ ደግሞ Magnification ነው። ይህ ደግሞ ችግሮችን ከመጠን በላይ አጉልተን እንድናይ የሚያደርግ ነው፡፡ ለምሳሌ ፦ ቤት ውስጥ የምትሰራ ስራተኛ ስሀን ስታጥብ ከእጇ አምልጦ ተስበረባት እንበል፡፡ እመቤቲቱ መጥታ ለምን ስበርሽው? ትላታለች። ትቀጥልና እስከመቼ ነው እቃ እየሰበርሽ ምትኖሪው? ትላለች። አሁንም ትቀጥልና እኔ ገንዘብ ከየት የማመጣ ይመስልሻል? ወይስ አውቀሽ ነው ምትሰብሪው? ሰሀኑ መሰበሩ እውነት ነው እመቤቲቱ ግን በጣም ከመጠን አብልጣ ታጎላዋለች። ይህም Magnification ነው። እነዚህ ከአእምሮአችን መጸዳት ያለባቸው ነገሮ ናቸው፡፡
ሰባተኛው የአሉታዊ አስተሳሰብ አይነት Emotional Reasoning ይባላል። ይህም በስሜት ሆኖ መወሰን ነው። ለምሳሌ ፦ አንድ አለቃ በጣም ሚጠቅመውን ሰራተኛ በድንገት ተነስቶ ያባርረዋል፡፡ ይህ ግን የተሳሳተ ውሳኔ ነው! ያንን ሰራተኛ መልሼ ላግኝህ ቢለው እንኳን ያስቸግረው ይሆናል። ውሳኔውን በስሜት ነው የወሰነው። አስቦበት አይደለም የወሰነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ አንዲት ሚስት በባሏ ተበሳጨች እንበል፡፡ ድንገት ተነስታ ቀለበቷን አውልቃ ወርውራ፣ ሻንጣዋን ሽክፋ፣ በጣም መጥፎ ነገር ባለቤቷን ተናግራ ከቤት ትወጣለች፡፡ ይህም ትዳራቸውን ያናጋዋል ወይንም ያፈርሰዋል። ይህ ነው Emotional Reasoning የሚባለው።
ስምንተኛው የአሉታዊ አስተሳሰብ አይነት Shoulding ነው። በዚህም አስተሳሰብ እኔኮ እንዲ ላደርግ ይገባኝ ነበር (I should have done this and that) እያልኩ ራሴን እወቅሳለሁ። ወይም ደግሞ ከአቅም በላይ የሆኑ ነገሮች እያሰብኩ የግድ ላደርጋቸው ይገባል ብዬ ራሴን አስጨንቃለሁ፡፡ ይህ Shoulding ይባላል፡፡
ዘጠነኛው አሉታዊ አስተሳሰብ ደግሞ Labeling ነው ሚባለው። ለምሳሌ ፦ አንድ ተማሪ ዋሽ እንበል። መምህሩ “አንተ ዋሽተሀል! መዋሸትህ ልክ አይደለም!'' ብሎ ቢገስጸው ትክክል ነው። መልካም አደረገ! ነገርግን አስተማሪው “አንተ ውሸታም ነህ!'' ካለው በተማሪው ላይ ስም ለጥፎበታል፡፡ አስተማሪው ተሳስቷል። ይህ Labeling ይባላል። እከሌ ሰርቋል መታረም አለበት ማለት እና እከሌ ሌባ ነው ማለት በጣም ልዩነት አላቸው። በሰዎች ላይ እንዲህ ስም መለጠፍ Labeling ይባላል። እነዚህንም ሁሉ ከአእምሮአችን ጠርገን ማስወገድ አለብን፡፡
አስረኛው የአሉታዊ አስተሳሰብ አይነት Personalization ይባላል። ይህም ነገሮችን ሁሉ ሰዎች ከራሳቸው ጋር የሚያገናኙበት የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው። ለምሳሌ ፦ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ስለ ውፍረት ብናገር ምናልባት ትንሽ ወፈር ያለችው እህቴ “እኔን ለመናገር ፈልጎ እኮ ነው!'' ትላለች። ስለ እንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ባወራ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታው ደከም ያለው ወዳጄ “እኔን እኮ በአሽሙር ሊናገረኝ ፈልጎ ነው!' ይላል፡፡ ሰዎች እኔን ለማለት ፈልጎ ነው እኔን መንካት ፈልጎ ነው የሚል የተሳሳተ ሀሳብ ይኖራቸዋል፡፡
አስራ አንደኛው የአሉታዊ አስተሳሰብ አይነት ደግሞ Blaming Others ይባላል። ይህም ለእያንዳንዱ በህይወታችን ለሚፈጠሩ ጥሩ ያልሆኑ ነገሮች ሌሎችን መውቀስ ነው። ለምሳሌ ፦ አንድ እድሜው ከ 50 በላይ የሆነ ሰው “እኔኮ ያልተሳካልኝ እናቴና አባቴ ጨቁነው ስላሳደጉኝ ነው! ሰለቀጡኝ ነው!'' ይላል፡፡ ወይም ደግሞ አንዲት ያልተሳካላት ሚስት “እኔኮ ሁሉ ነገር ያልተሳካልኝ አንተን ስላገባሁ ነው" ትለዋለች ባሏን፡፡
አስራ ሁለተኛው አሉታዊ የአስተሳሰብ አይነት Catastrophizing ይባላል፡፡ ይህም አንድ ችግር ሲፈጠር መአት እንደመጣ አድርጎ ማሰብ ነው:: ለምሳሌ ፦ አንድ እናት ልጃቸው ማታ እስኪመጣ እየጠበቁት ይዘገይባቸዋል፡፡ ማታ 2 ሰአት መምጣት የነበረበት ልጅ እስከ 3 ሰአት ይቆያል። በዚህ ጊዜ እናት “በቃ ልጄን መንገድ ላይ ደፍተውታል፣ ገድለውታል፣ አወይ እድሌ ልጄን ልጄን እያሉ መጮህ ይጀምራሉ። ልጃቸው ያመሸው ግን ታክሲ ስላላገኘ ነው፡፡ እንዲህ ማሰብ Catastrophizing ይባላል።
------------------
ምንጭ = 101 የጥበብ ጠብታዎች መጽሐፍ 📖
ጸሐፊው = ዶክተር ወዳጄነህ መሐረነ 😘
t.me/changeitwow
ራስን መለወጥ
#Ethiopia #share #like #ethiopian_tik_tok #Wow #new
