ar
Feedback
HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

الذهاب إلى القناة على Telegram

❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️ 👇👇👇 http://www.youtube.com/@haileG2239

إظهار المزيد
2 277
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+47 أيام
+2930 أيام
أرشيف المشاركات
photo content

"የደስታችን ምንጭ ምን ይሆን?" ◈ ድንግል ማርያም ‘መንፈሴም በመድኃኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ይላታል’ አለች፡፡ የድንግሊቱን ጥበብ ተመልከቱ፡፡ ‘በመልአክ በመመስገኔ ደስ ይለኛል፣ ከሴቶች ሁሉ የተባረከች በመባሌ ደስ ይለኛል፣ አምላክን ለመውለድ በመመረጤ ደስ ይለኛል’ አላለችም፡፡ የእርስዋ የደስታ ምንጭ ከእግዚአብሔር የተሠጣት ነገር ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ◈ እግዚአብሔር የደስታህ ምንጭ ከሆነ በሕይወትህ ምንም ነገር ቢከሰት ደስታህን አይነካብህም፡፡ ድንግሊቱ ከሴቶች ሁሉ የተባረከች በመሆንዋ ደስ ያላት ብትሆን ኖሮ ከዚያ በኋላ ከሴቶች ሁሉ የተንከራተተች፣ ከሴቶች ሁሉ ያዘነች፣ ከሴቶች ሁሉ በዲያብሎስና ጭፍሮቹ የተጠላች፣ በሔሮድስ በአይሁድ የተነቀፈች መሆንዋን ስታይ ደስታዋ በጠፋ ነበር፡፡ ◈ እርስዋ ግን ደስታዋ የመነጨው ከአምላክዋ ብቻ ነበር፡፡ ፍጹም የሆነ ውስጣዊ ደስታን ማግኘት የሰው ልጅ ትልቅ ምኞቱ ነው፡፡ ሰዎች ደስታን ፍለጋ ብዙ ይደክማሉ፡፡ ድንግሊቱ ግን የደስታ ሁሉ ምንጭ የሆነው አምላክ ከእርስዋ ጋር ነውና በፍጹም ደስታ ደስ ይላታል፡፡ የድንግል ማርያም ደስታ ልጅዋ ‘ደስታችሁን የሚወስድባችሁ የለም’ ያለው ዓይነት ደስታ ነበር፡፡ ዮሐ. ፲፮፥፳፪ ◈ ‘ተፈሥሒ ፍስሕት’ (ደስተኛይቱ ሆይ ደስ ይበልሽ)፤ ሙኃዘ ፍሥሓ (የደስታ መፍሰሻ ሆይ) ብለን የምናመሰግናት እመቤታችን ከማንም የሚበልጥ ደስታ በእርስዋ ዘንድ ነበረ፡፡ ደስተኛ የነበረችው በምድር በነበራት ቆይታ የሚያስደስት ኑሮ ስለነበራት አይደለም፡፡ እንደ እርስዋ የተሰደደ፣ ያለቀሰ፣ የተጨነቀ ፍጡር የለም፡፡ እንደ ክርስቶስ መከራ የተቀበለ እንደሌለ እንደ ድንግል ማርያምም ያዘነ የለም፡፡ እርስዋ ግን ለሌሎች የሚተርፍ ወደ ኤልሳቤጥ የሚሸጋገር፣ ሆድ ውስጥ ወዳለ ፅንስ የሚጋባ ጥልቅ ደስታ ነበራት፡፡ ቅዱስ ያሬድ ‘ተፈሢሓ በነፍሳ ፆረቶ በከርሣ’ ‘በነፍስዋ ደስ ተሰኝታ በሆድዋ ተሸከመችው’ እንዳለ እርስዋ የተደሰተችው ሥጋዊ ደስታን አልነበረም፡፡ (ድጓ ዘቅዱስ ገብርኤል )ከመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች አንዱ ደስታ ነውና ቅድስቲቱ ማንም ጋር ያልነበረ ደስታ ነበራት፡፡ ገላ. ፭፥፳፪ ◈ በእርግጥም ደስታን ወልዳ ደስ ባይላት ይደንቅ ነበር፡፡ እርስዋ የወለደችው ‘የመላእክት ተድላ ደስታቸው’ ነው፤ እርስዋ የወለደችው መወለዱ ‘ለሰው ሁሉ ደስታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች’ የሚሆን ልጅን አይደለምን? ◈ እግዚአብሔር አብ ‘በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይህ ነው’ ያለውን አንድያ ልጁን ልጅዋ እንዲሆን ሠጥቶአታልና እርስዋም በምትወደው በልጅዋ ደስ ይላታል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ‘ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ’ ካለ እግዚአብሔር የዘጠኝ ወር ቤቱ አድርጎ ያደረባት ድንግል ምንኛ ደስ ይላት ይሆን? መወለዱ ሰውና መላእክትን በደስታ እንዲዘምሩ ካደረገ የወለደችው ድንግል ምንኛ ደስ ይላት ይሆን? ◈ ጌታ ለሐዋርያቱ ‘ስማችሁ በሰማይ ስለተጻፈ ደስ ይበላችሁ’ ካላቸው እግዚአብሔር ሁለተኛ ሰማዩ አድርጎ ዙፋን ያደረጋት በምድር ያለች የጠፈር ባልንጀራ፣ የአርያም እኅት ማርያም ምንኛ ደስ ይላት ይሆን? እመቤታችን ሆይ እባክሽን በአንቺ ላይ ከፈሰሰው ደስታ ቀድተሽ ወደ እኛ ወደ ኀዘንተኞቹ አፍስሺ፡፡ ኖኅ እንደ ላካት ርግብ የመከራችን ውኃ ጎደለ ብለሽ ታበሥሪን ዘንድ ወደ እኛ ነይ ‘ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ ኀዘነ ልብየ’ ‘ርግቤ ሆይ ከኀዘኔ ታረጋጊኝ ዘንድ ነይ’ እንዳለ ሊቁ፡፡ #ውድ_ቤተሰቦቼ_የዩቱብ_ቻናላችንን_ተቀላቁ! #Subscribe #Like #Share 👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@pagumentube

🙏 ለንስሐ ጥሪ ቀጠሮ አንስጥ። መጠየቅን ወደሚወድ አምላክ የምንሄድበትን ጊዜ አናውቅምና ዘወትር ለመልካም ነገር የተነሣሣ ልቡና ይኑረን። "ንስሐ ግቡ፣ ቁረቡ" ስንባል "ወጣት አይደለሁ? ገና ምኑን
🙏 ለንስሐ ጥሪ ቀጠሮ አንስጥ። መጠየቅን ወደሚወድ አምላክ የምንሄድበትን ጊዜ አናውቅምና ዘወትር ለመልካም ነገር የተነሣሣ ልቡና ይኑረን። "ንስሐ ግቡ፣ ቁረቡ" ስንባል "ወጣት አይደለሁ? ገና ምኑን አየኹትና? ቆይ ትንሽ!" እያልን መንፈሳዊነትን ከኃጢአት በተረፈ ጉልበት የሚሠራ የጡረታ ሥራ አናድርገው። የተመረጠውን የወጣትነት ዕድሜ ለበደል ሳይሆን ለጽድቅ እናውለው። #ውድ_ቤተሰቦቼ_የዩቱብ_ቻናላችንን_ተቀላቁ! #Subscribe #Like #Share 👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@pagumentube

🛑የስስት አጋንንት ፈተና በሕይወታችን የስስት አጋንንት ምንድነው? ብዙ በረከት የሚያሳጡን ክፉ መናፍስቶች #ethiopia #orthodox 🙏😭🙄 https://youtu.be/6ON2YeZ-3EE?si=FOeRPMKRnfpjPMeO

🛑በእውቀታችን እና በዕድሎቻችን ላይ የዓይነጥላ መንፈስ ሲያደፍጥ ስንቶቻችን ነን በልጆቻችን የተፈተነው በቅዳሴ ጊዜ የማይደረጉ ነገሮች #sibket 😭 https://youtu.be/Y3ocDKUELM8

🛑በጸሎት ሰዓት መንፈሳዊ ተመስጦን እንዴት እናዳብር መንፈሳዊ ተመስጦ ምን ማለት ነው ጸሎትና ተመስጦ #ethiopia #orthodox #sibket 🙏🙄 https://youtu.be/X10G0ZYdgKM?si=beH-JYf6vpHXU5PW

🛑በዝሙት፣ በግለወሲብ፣ በሌዝቢያንነት ሱስ ክፉኛ የሚያጠቁን መንፈሶች ፈተና የዝሙት መንፈስ በቀሲስ ሄኖክ ወ/ማሪያም || መምህር ተስፋዬ አበራ 🙏🙄😭 https://youtu.be/qRWdeX_huoU?si=L2GHK-5FWxan8RZM

🛑ቆርጥና የእኛ ሀገር ሀብታሞች ስውር ምስጥርና ደባ ቆርጥ ማን ነው? እንዴት ሀብታም ያደርጋል? መተት እና ሀብት በዚህ ዘመን #ethiopia 😰😭😭 https://youtu.be/dsPQ-TfJW7A

👇 ሰላም ውድ ቤተሰቦቼ "መናፍስትና የአካል ክፍሎቻችን በሚል ርዕስ የጀመርነውን ትምህርት ይሄው ዛሬ ክፍል 2 ይዠ ቀርቢያለሁ። ሁላችሁም ተከታተሉት። ቻናሉን ልይክና ሸር አድርጉ በእውነት። በዚህ ክፍል ደግሞ መናፍስት ዓይንን ሲቆጣጠሩና ሲይዙ የሚያሳዩትን ምልክቶች፣ መፍትሔዎቹን እንመለከታለን። የትኞቹ መናፈስቶች ናቸው ዓይን ላይ የሚቀመጡት የሚለው በዝርዝር ቀርቧል። https://youtu.be/kP6VD-4zasM?si=aIt901RfNIfE_lkW

🍂 #እስጢፋኖስም፦ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር። ተንበርክኮም፦ ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ፦ ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር። + / ሐዋ 7፥ 59 - 60 / + ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት ዲ/ን ጌታባለው አማረ የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ https://vm.tiktok.com/ZM6J5RYep/

🛑ፍሬያማ እንዳንሆን የዲያብሎስ ሴራ መንገድ ዳር የወደቁ ልቦች ባሕሪይ የቃለ እግዚአብሔር ፍሬ || ክፍል 1 በማለዳ ንቁ 2023 #ethiopia 🙏😭 https://youtu.be/STFTw-zo-1o

◈ መጽሐፈ ኢያሱን እንዲሁም ለሎችን በትረካ መልክ እና በዝርዝር ሀሳብ በወንድማችን ቻናል ላይ ይማሩ 🙏🙏 https://youtu.be/4lyLSHMtqWY?si=CiwtfZPatZqbzsBy

🙏 ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት... ወደ ቆላስይስ (1፡15-16) 🙏 እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። እግዚአብሔር ፍጥረትን ሁሉ በልጁ ፈጠረ...የተፈጠረ ነገር ሁሉ በኢየሱስ ከተፈጠረ መቼስ የኢየሱስን አምላክነት ግልፅ አድርጎ ያሳያል. ባይሆን የሚገርመኝ ግን በልጁ ፈጠረንና.. ይህ ፍጥረቱ ሲወድቅ ደግሞ በዛው በልጁ አደሰው ፈወሰው...ለዛ ነው ዝቅ ብሎ እንዲህ የሚለው.. ወደ ቆላስይስ (1፡19-20) እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፥ በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና። መልካም ሰንበት 🙏 #ውድ_ቤተሰቦቼ_የዩቱብ_ቻናላችንን_ተቀላቁ! #Subscribe #Like #Share    👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@pagumentube

🛑መቁጠሪያና የአባቶቻችን አስተምህሮ ንስሐ ገብቶ ቀኖና ፈጽሞ አለመቁረብ የመናፍቁ መንፈስ ፈተና #ethiopia #orthodox #sibket 😰🙏😭 https://youtu.be/XdCy_JxSvLY?si=4Rc838kOvrA4cBZT

🛑መቁጠሪያና የአባቶቻችን አስተምህሮ ንስሐ ገብቶ ቀኖና ፈጽሞ አለመቁረብ የመናፍቁ መንፈስ ፈተና #ethiopia #orthodox #sibket 😰🙏😭 https://youtu.be/XdCy_JxSvLY

◈ መንፈሳዊ ሰው በማየት ወይም በመስማት ወይም በመዳሰስ ኃጢአት እንዳይሠራ ስሜቶቹን መቆጣጣር ይችላል። ከዚህ በተጨማሪ የልቡን ስሜታዊነትና ፍላጎቱን መቆጣጠር ይቻለዋል። በኃጢአት የተሞላና አላስፈላ
◈ መንፈሳዊ ሰው በማየት ወይም በመስማት ወይም በመዳሰስ ኃጢአት እንዳይሠራ ስሜቶቹን መቆጣጣር ይችላል። ከዚህ በተጨማሪ የልቡን ስሜታዊነትና ፍላጎቱን መቆጣጠር ይቻለዋል። በኃጢአት የተሞላና አላስፈላጊ ቃል ከአንደበቱ ወጥቶ ሌሎችን እንዳያስቀይም ምላሱን መጠበቅ ይችላል። አንደበትን አስመልክቶ ሐዋሪያው ቅዱስ ያዕቆብ እንዲህ ብሏል "በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።" (ያዕ.3፡2) የመንፈሳዊው ሰው ውስጣዊ ጥንካሬ የሚገለጸው ራሱን፣ አስተሳሰቡን፣ ስሜቱን፣ ፍላጎቱንና አንደበቱን በመቆጣጠር ነው። እኛስ ቤተሰቦቼ እንዴት ነን .....? (ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ) #ውድ_ቤተሰቦቼ_የዩቱብ_ቻናላችንን_ተቀላቁ! #Subscribe #Like #Share 👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@pagumentube