ar
Feedback
Anwar Bilcha

Anwar Bilcha

الذهاب إلى القناة على Telegram

A learning software engineer

إظهار المزيد
1 367
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+27 أيام
-830 أيام
أرشيف المشاركات
በርካታ ቁጥር ያለው የዩኒቨርሲቲ መምህራን መታወቅያ እና ስልክ ልካቹልኛል:: ተነሳሽነታችሁ አስደስቶኛል:: ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ፒ ኤች ዲ ዲግሪ ያላችሁ ሰዎች እራሳችሁን ከሌላ ዘርፍ መጥታችሁ ለመለወጥ ያላችሁ ቁርጠኝነት አድናቆት ይገባዋል:: Together we can make a difference ‼️🙏

ቀጣዩ የፉልስታክ ሶፍትዌር developer ስልጠና. NET እና Reactን yatamere ሆኖ ምርጥ ዝግጅት አልቆዋል:: Application link will be announced in three days time.

ለproven government ዩኒቨርሲቲ መምህራን unconditionally የሙሉ .NET Core ስልጠና ማቴሪያሎቼን በነፃ መልቀቅ አስቤያለው:: ይህ ፖስት 1K reactions ካገኘ ሁሉም ጋር ይደርስ ይመስለኛል::

ሶፍትዌር ምንድነው? ብለን ጀምረን ሶፍትዌር አበልፅገን ለተጠቃሚ የምንለቅበት የታዳጊዎች ሶፍትዌር ማበልፀግ ስልጠና አሁንም ማመልከቻ እየተቀበልን ነው፡፡ ለማመልከት ይህንን ማስፈንጠሪያ ተጠቀሙ https://surveyheart.com/form/6867114d1adbb141ebc8cea1

የታዳጊዎች ሶፍትዌር ዴቨሎፕመንት ስልጠና የመጀመርያ ዙር የማመልከቻ ቅፅ እነሆ https://surveyheart.com/form/6867114d1adbb141ebc8cea1 ዌብ እንዴት ነው የሚከውነው? ከሚ
የታዳጊዎች ሶፍትዌር ዴቨሎፕመንት ስልጠና የመጀመርያ ዙር የማመልከቻ ቅፅ እነሆ https://surveyheart.com/form/6867114d1adbb141ebc8cea1 ዌብ እንዴት ነው የሚከውነው? ከሚለው እስከ ሶፍትዌር ሰርቶ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረግ ስልጠና ደግሰናል፡፡ ቅድሚያ ያመለከታችሁ ሰዎችም ቅፁን መሙላት ይጠበቅባችኋል፡፡

ለታዳጊዎች የሶፍትዌር አበልፃጊነት ስልጠና ፕሮግራማችን አጭር ማብራሪያ፡ =========================== 1) ፕሮግራሙ የክረምት ብቻ ስልጠና አይደለም፡፡ የ10 ወር ሙሉ ሶፍትዌር ዴቨሎፐር የሚያደርግ ስልጠና ነው፡፡ 2) ብቻቸውን ከሶፍትዌር ሀሳብ ወደ ሙሉ የሚሰራ ሶፍትዌር መቀየር የሚያስፈልጉትን ሙሉ ሂደቶችን መስራት ይችሉ ዘንድ የተቀረፀ ፕሮግራም ነው፡፡ 3) የምንቀበለው 12 ተማሪዎችን ብቻ ሲሆን በዚህ ፕሮግራም የምንቀበለው ከ 9ኛ እስከ 12 ክፍል የሚማሩ (12ኛ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ የተፈተኑት ዋና ትኩረታችን ናቸው) ተማሪዎች ብቻ ናቸው፡፡ ለዚህም የዘንድሮ አመት የትምህርት ሰነድ ማረጋገጫ እንጠይቃለን፡፡ 4) ወላጆች ለሂደቱ አጋዥ መሆን ካልቻሉ ስኬታማ ስለማይሆን ቅድሚያ ወላጆችን እንገመግማለን፡፡ 5) ኢንተርኔት ኮኔክሽን እና ላፕቶፕ በተጨማሪ የተማሪዎቹ ለፕሮግራሙ ምቹነትን አስቀድመን ፈትነን እንወስናለን፡፡ ለዚህ ዝግጁ የሆኑትን ብቻ ነው ወደ ፕሮሰሱ የምናስገባው፡፡ 6) ለስልጠናው የሚከፈለውን ክፍያ አማራጮች የ5 ወር ቅድመክፍያ እና የሙሉ ኮርስ ቅድመክፍያ አማራጮች ናቸው፡፡ 7) የተማሪ ቁጥር በ 1/4 እንደመቀነሱ መጠን ወርሀዊ ክፍያው ከዚህ በፊት ከነበረው መጠነኛ ጭማሪ ተደርጎበታል፡፡ እያንዳንዱ ተማሪ የሚያገኘው አገልግሎት በዛው ልክ ይጨምራል፡፡ 8 የወላጆች መመዝገቢያ ቅፅ ነገ ይለቀቃል፡፡ የክላስ መጀመሪያ እና ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳ በቅርብ ይፋ እናደርጋለን፡፡ የዚህ ዙር ሰልጣኞች በጣም እድለኞቹ ናቸው፡፡ ዝግጅቱ ሌላ ነው፡፡ ብዙ ያልነገርናችሁ በየመሀሉ የምንነግራችሁ ሌላም አለን ለዚህ ፕሮግራም፡፡ ጠብቁን!

ለታዳጊዎች የሶፍትዌር ማበልፀግ ስልጠና ዝግጅታችንን ጨርሰናል:: ነገ ሙሉ ዝርዝሩን እንገልፃለን ::

3ኛ ዙር የ.NET Core (C#) Full-Stack Development ስልጠና በተመለከተ ===≠=== ለ 3ኛ ዙር የ.NET Core የሶፍትዌር ዴቨሎፕመንት ስልጠና እጩነት ኮንሲደር የመደረግ ጥያቄን ትንሽ ለየት ባሌ መልኩ መያዝ ፈልገናል:: 1)የሰልጣኝ ቁጥር ከ 50 ወደ 12 መቀየር አስፈልጎዋል :: 2) የንፁህ ጀማሪ እና የባለሙያ ብቻ ማድረግ አስፈልጎዋል :: 3) 12 በደንብ የኮምፒዩተር ሳይንስ እና ተዛማጅ ባለሙያ የሆኑ ሰልጣኞችን ለብቻ እንቀበላለን :: ለዚህ ፕሮግራም ምልምሎች የስልጠናውን ክፍያ መክፈል የቻለ: ላፕቶፕ እና ኢንተርኔት ብሎም ፍላጎት ያለው የሚለው የቀድሞው ዙሮች መስፍርት እንደተጠበቀ ሆኖ የቃል እና የፅሁፍ ፈተና መፈተን እና ያስቀመጥነውን የማለፍያ ውጤት ያመጣ ይመረጣል:: 4) 12 ንፁህ ጀማሪ ከ 9-12ኛ ክፍል የሚማሩ ታዳጊዎችን ለብቻቸው እንቀበላለን:: ለዚህ ፕሮግራም ልዩ ትኩረት ሰጥተን ተምረናል ተዘጋጅተናልም:: 5) የስልጠናው ክፍያ ክለሳ ግድ ብሏል:: ለዚህ ፕሮግራም ምልምሎች የስልጠናውን ክፍያ ለ 10 ወር በሙሉ መክፈል የሚችል: ላፕቶፕ እና ኢንተርኔት ብሎም ፍላጎት ያለው የሚለው የቀድሞው ዙሮች መስፍርት እንደተጠበቀ ሆኖ መጀመሪያ ወላጅ ይመለመላል ወላጅን በስልጠናው ሂደት ውስጥ በጉልህ ተሳታፊ ስለምናደርግ ወላጁ ለምናስበው ሚና ይሆናል ወይስ አይሆንም የሚለውን እናጣራለን:: ወላጁ ካለፈው ብቻ ልጁ ይገመገማል :: ሰልጣኙ የቃል እና የፅሁፍ ፈተና ይፈተን እና እና ያስቀመጥነውን የማለፍያ ውጤት ሲያመጣ ይመረጣል:: ብዙ ሰዎች በውስጥ መስመር እየፃፋቹልኝ ነው :: አክባሪ ይስጥልኝ :: ሆኖም በወቅቱ የምናወጣው ማስታወቂያን ተከታትላችሁ አመልክቱ እንጂ እዚህ በኢንቦክስ ያወራቹኝ በሰዓቱ ካልተደገመ ይረሳል :: በሰሞኑ የታዳግዎቹን መርሐግብር ዝርዝር ጉዳዮች ይዤ እመለሳለሁ:: 🙏

ኮምፒዩተር በማስታወስ አቅም እና በክወና ፍጥነት የሰውን ልጅ እልፍ ያስከነዳል::ሎጂካሊ እስፒክንግ አስተውሎት (Intelligence) ዜሮ ነው:: ይህንን ዜሮ ለማከም የተጀመረው ሙከራ ነው Artificial intelligence (AI) ማለት:: ጥቅል አላማው የሚማር ማሽን መፍጠር ነው:: አንድ ጊዜ ፕሮግራም ከተደረገው እውቀት ብቻ ውሳኔ ከመውሰድ ይልቅ እየሰራ በሄደ ቁጥር ከልምዱና ከተጠቃሚው ፊድባክ በመነሳት ቀጣይ ውሳኔዎቹን ያለ ሰው ጣልቃ ገብነት በራሱ መቀየር መቻል ነው Learning Machine የሚያስብለው:: ዘርፉ በቅርብ ዓመት እያሳየ የመጣው እድገት ፈጣን ነው:: ከባዱ ነገር የሚመጣው AI agent ፕሮግራመሩን የበለጠ ጊዜ ነው:: በአንድ ወቅት ኮምፒዩተሩ ደደብ ሰዉ ምጡቅ ነበር:: ሰዉ ሀሳቡን ኮምፒዩተሩ ላይ ጥሎ እራሱን አያደደበ ነው:: ኮምፒዩተሩን ግን እያመጠቀው:: ይህ ጉዞ ስንተላለፍ ይከፋል:: The philosophy of AI የሚል ድንቅ መፅሐፍ አለ አግኝቶ የሚያነብ ሰው የዛሬ 20 ዓመት የተቀመጠው ትንበያን እየኖርን መሆኑ ግልፅ ይላል:: ነገንም ይጠቁማል::

ስራ እየሰራን በየመሃል ቆም ብለን አካሄዱን መገምገም ሸጋ ልማድ ነው:: ሲገመገም ስራ ተመጋጋቢ ወይንም synergized ሆኖ ሲገኝ እጅጉን አስደሳች ነገር ነው:: አልሃምዱሊላህ :: ክፍተቶችን ልየታ ሌላው ለቀጣይ አካሄድ አሳማሪ ነገር ነው :: የ. NET Core ስልጠና አሰጣጤ ላይ እና በእጄ ላይ ያሉ የሶፍትዌር ማበልፀግ ፕሮጀክቶች ላይ ሰሞኑን ባደረግኩት ግምገማ የተረዳሁት ይህንኑ ነው :: ስልጠናው በሚገርም ሁኔታ ለሥራዎች መጋቢ ሆኖልኛል :: አንድም ለማስተማር የማዘጋጀውን ማቴሪያል ፕሮዳክሽን ሌቭል ሶፍትዌር መስራት ተኮር በማድረግ ሁለትም ቀጣይ አብሬያቸው ልሰራቸው የሚችሉ እጩዎችን በመጠቆም:: በሌላ መልኩ አካሄዴ ላይ የተረዳሁአቸው ክፍተቶችንም አይቻለሁ:: ለምሳሌ ሰልጣኝ ልየታ ላይ ከፍተኛ ክፍተት አይቻለሁ:: በመሆኑም ቀጣይ ዙር ፈተና ፈትነን እና ቃለ መጠየቅ አድርገን መቀበል ግድ ብሎናል:: ሌላው በቀጣይ ዙር 12 ሰልጣኝ ብቻ ለመቀበል ወስነናል:: ተጨማሪ በቀጣይ ዙር ከ9-12 ክፍል ላሉ ልጆች ሁለንተናው ለየት ያለ ፓኬጅ አስበናል:: ዝርዝሩን በቅርቡ :: በሶፍትዌር ፕሮጀክቶች እና ዌብሳይት ማበልፀጉም ላይ ግምገማ እያደረግን ነው :: ምን ለማለት ነው? If done honestly, self assessment is the perfect one.

2001 (በኢትዮጵያ አቆጣጠር) ሀምሌ እና ነሐሴን አዲስ አበባ ለ2 ወር ኖርያለሁ፡፡ ያኔ ሁለተኛ አመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነበርኩ፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም ሊመረቁ አንድ አመት የቀራቸው ሰቃይ የኮምፒዩተር ሳይንስ ዲፓርትመንት ተማሪዎችን ከየዩኒቨርሲቲው አንድ ሰው "ፕራክቲካል አታችመንት" እራሱ ዩኒቨርሲቲው ድረስ ጠይቆ ይወስድ ነበርና በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ እንደመጣሁ መዲና ህንፃ ሰላም ፔንሲዮን አጠገብ አልጋ ይዤ ጥቂት ቀናት ቆየሁ፡፡ እዛው አልጋ ቤት ከጎንደር መጥቶ ስራ ይፈልግ የነበረ አብዱ ከሚባል ሰው ጋር ተዋወቅን፡፡ ከባህሪዬ በተቃራኒው በአጭር ቀን በጣሙን ተግባባን፡፡ በሳምንት ውስጥ አብረን ቤት ተከራይተን ከአልጋ ይዞ ማደር ለመገላገል ወሰንን፡፡ ጎጃም በረንዳ አባኮራን ቤት ተከራየን ሁለት ወር አብረን ቆየን፡፡ አብዱ ሰው አክባሪ ፤ ትሁት ፤ ታናሹን የሚያከብር (ቢያንስ በ10 አመት ይበልጠኛል ሳስታውስ) ፤ ቁምነገረኛ ሰው ነው፡፡ እኔ መስከረም ላይ ወደ ቤተሰብ ስሄድ አንድ ጓደናዬ ጋር አስተዋውቄው ከሱ ጋር አብረው መኖሩን ቀጠለ፡፡ ለወራት እንደዋወል ነበር፡፡ ከወራት ቡሃላ ስልኬን ጥዬ አዲስ ቁጥር ስላወጣው 2002 ላይ መደዋወል አቆምን ተረሳሳን፡፡ the long story short, ትላንት አንድ ማላውቀው ቁጥር ተደወለልኝ፡፡ አነሳሁት፡፡ እኔ፡ ሄሎ ደዋይ ፡ አሰላሙ አለይኩም አንዋር? እኔ፡ አዎ አንዋር ነኝ፡፡ ማነህ አላወቅኩህም አፍወን፡፡ ደዋይ ፡ አንዋር ብልጫ? እኔ ፡ አዎ አንዋር ብልጫ ነኝ፡፡ ከፈገግታ ጋር ደዋይ ፡ አብዱ ነኝ ፡፡ አብዱ ጎንደር፡፡ እኔ፡ አብዱ ጎንደር የኢቲቪው? ጎጃም በረንዳ? መዲና ህንፃ? ሰላም ፔንሲዮን? ደዋይ ፡ ረጅም ሳቅ ......። አዎ አብዱ የኢቲቪው ጎጃም በረንዳ መዲና ህንፃ ሰላም ፔንሲዮን በጣሙን አወራን፡፡ እንዴት እንዳገኘው ስልኬን ስጠይቀው ፡ ሁሌ አስብካለው ለምን አልፈልገውም ብዬ ቴሌግራም ላይ አንዋር ብልጫ ብዬ ሰርች ሳደርግ አገኘሁህ ደወልኩ፡፡ ከ16 አመት በኋላ ሰውን የሚያስታውስ ወዳጅ በጣሙን ይገርማል፡፡ እኔም አብዱ ጎንደር ሲል ባንዴ ማስታወሴ ገርሞኛል፡፡ የጠፋ ዘመድ እንደማግኘት ፤ የናፈቁትን ነገር እንደማግኘት ጮቤ ረገጥኩ፡፡ Jemal Mo Getu ያ ያልኩህ ያገርህ ሰው ነውኮ፡፡ አንዳንዱ ሰው ውብ ፍጡር ነው፡፡

ሀገራችን ታሪካዊ የሚባል የቢዝነስ እና ኢኮኖሚ ሽግግር ላይ ነች፡፡ በዚህ አይነት ወቅት business as usual ማስኬድ እራስን እና ከቢዝነስ ሜዳው ያለን ቆይታ ቀስ በቀስ ማምከንን ያስከትላል፡፡ ቢዝነሱ ወደ ምን እየተለወጠ ነው? የዛሬ አምስት አመት የወረቀት ገንዘብ ዛሬ ላይ ፍራንክ (የብረት ሳንቲሞች) ያላቸውን ዋጋ የሚኖረው ይመስላል፡፡ ይጠቅማል ግን ማንም አይጠቀመውም ቢያንስ በብዛት እና በዋናነት፡፡ ሰርቪስ ሴክተሩ በቀጣይ ሚናውን ከመቸውም በላይ ኢኮኖሚው ላይ እየጨመረ መሄዱ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ ሰርቪስ ሴክተሩን በማዘመን ረገድ የቴክኖሎጂን ሚና የሚስተካከል አይኖርም፡፡ ይህንን ለመረዳት እነ ቴሌብር እና ቻፓን መሰል ፕላትፎርሞች በአጭር ጊዜ እያንቀሳቀሱ ያሉትን ገንዘብ ቮልዩም እና እያካተተ የመጣውን አገልግሎት ስብጥር ብዛት ማየት ቀላል ነው፡፡ ዛሬ እኛ ኢሄን እያወራለን ሳለ እልፍ ቁጥር ያላቸው ሶፍትዌሮች እየበለፀጉ ነው፡፡ ላንዱ ቢዝነስን ሊፈጥሩ ካንዱ ሊነጥቁ፡፡ ይህ ሲሆን እንደ ሀገር ይህ ሽግግር በምን ያክል ባለሙያዎች እና ጥንቃቄ መመራት አለበት፡፡ ገዳቢ እና አደናቃፊ ያልሆነ ስርዓት (ሲስተም) እንዴት እንገንባ የሚለው አንድ ጉዳይ ነው፡፡ በነብስ ወከፍ እያንዳንዱ ዜጋ ሽግግሩ ከኔ ጋር ያለው አሉታዊ እና አዎንታዊ አልያም የሚያስከትለው እክል እና እድል ምንድነው ብሎ በሰፊው ማሰላሰል ግድ ይላል፡፡ ዛሬ ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽንን በጎበኘሁበት ወቅት ከኡስታዝ Ahmedin Jebel ጋር በዚህ ጉዳይ ላይ በሰፊው ውጤታማ ውይይት አድርገናል፡፡ ቴክኖሎጂን (በተለይ አይቲ እና ሶፍትዌርን) ለቢዝነሳችን ከመጠቀም በዘለለ ቴክኖሎጂን እንደ ኢንቨስትመንት አማራጭ መሳተፍ ወሳኝነት ላይ ሀሳብ ተለዋውጠናል፡፡ በዚህ ረገድ በቀጣይ በዘርፉ ላይ ምን ሊሰሩ ይገባሉ በሚለው ላይ የየግል እይታችንን አውርተናል፡፡ ውይይታችን ውጤታማ እና አነቃቂ ነበር፡፡ መሰል ውይይቶች ሊቀጥሉ እና ሲርየስሊ ሊወሰዱ ይገባል፡፡ ሚድያዎች የዚህን አጀንዳ ወሳኝነት ተረድተው ግንዛቤ አስጨባጭ ፕሮግራሞችን መስራት አለባቸው፡፡ ግለሰቦች ፤ የንግድ ባለቤቶች ፤ ወጣቶች ዘርፉ ይዞ እየመጣ ያለውን እዳ እና ፋይዳ በጊዜ ተረድተው እራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው፡፡ ኡስታዝ አህመዲን ጀበልን ለግብዣው እና ለፍሬያማ ውይይታችን አመሰግናለሁ፡፡ ===========

photo content
+1

የዴቨሎፐርስ ሮድማፕ - ቀን 10፡ የፕሮግራሚንግ መሰረታውያን ለ - ፈንክሽን እና ዳታ ታይፕን በጥልቅ መረዳት ====================== ዛሬ ደግሞ ሁለት ወሳኝ የፕሮግራሚንግ ፅንሰ-ሀሳቦችን ላወጋችሁ ነው፡ እነሱም ፈንክሽኖች እና ዳታ ታይፕስ ናቸው። እነዚህ ሁለቱ የፕሮግራሚንግን ዓለም ለመረዳትና ውስብስብ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉህ መሰረታዊ ጡቦች ናቸው። በመጀመሪያ ስለ ፈንክሽኖች እንመልከት። ፈንክሽን ማለት የተወሰነ ስራን ለማከናወን ተብሎ የተጻፈ የኮድ ስብስብ ነው። ልክ በሂሳብ ውስጥ እንደምትጠቀማቸው ፈንክሽኖች (ለምሳሌ f(x) = x + 2)፣ በፕሮግራሚንግ ውስጥ ያሉ ፈንክሽኖችም ግብዓት ይቀበላሉ (ፓራሜትር ይባላሉ)፣ የተወሰኑ ትዕዛዞችን ካከናወኑ በኋላ ደግሞ ውጤት ሊመልሱ ይችላሉ። የፈንክሽኖች ዋነኛ ጥቅም የኮድህን ድግግሞሽ ማስወገድ ነው። አንድን የተወሰነ ስራ በተደጋጋሚ በፕሮግራምህ ውስጥ ማስኬድ ካስፈለገህ፣ ስራውን አንድ ጊዜ በፈንክሽን ውስጥ ትጽፋለህ፤ ከዚያ በኋላ በፈለግህበት ቦታ የፈንክሽኑን ስም በመጥራት ብቻ መጠቀም ትችላለህ። ይህ ኮድህን የበለጠ ንፁህ፣ ለማንበብ ቀላል እና ለመጠገን ምቹ ያደርገዋል። ዳታ ታይፕስ በፕሮግራምህ ውስጥ የምትጠቀምባቸውን የዳታ አይነቶች የሚገልፁ ናቸው። ኮምፒውተርህ የተለያየ አይነት መረጃን ለምሳሌ ቁጥሮችን፣ ጽሑፎችን፣ እውነት ወይም ሐሰት የሚሉ እሴቶችን እንዴት ማከማቸትና ማስተናገድ እንዳለበት የሚነግሩት ዳታ ታይፕስ ናቸው። በአብዛኛዎቹ የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች ውስጥ የምናገኛቸው መሰረታዊ ዳታ ታይፖች ጥቂቶቹ እነሆ፡- • ኢንቲጀር (Integer): ሙሉ ቁጥሮችን (እንደ 5, -3, 0 ያሉ) ለማከማቸት ያገለግላል። • ፍሎት (Float): የአስርዮሽ ቁጥሮችን (እንደ 3.14, -2.5 ያሉ) ለማከማቸት ያገለግላል። • ስትሪንግ (String): የቁምፊዎችን ቅደም ተከተል ወይም ጽሑፍን (እንደ "ሰላም", "ፕሮግራሚንግ" ያሉ) ለማከማቸት ያገለግላል። • ቡሊያን (Boolean): ሁለት እሴቶችን ብቻ ሊይዝ የሚችል የውሂብ አይነት ነው፡ እውነት (true) ወይም ሐሰት (false)። ሁኔታዎችን ለመቆጣጠር በጣም ጠቃሚ ነው። • ሊስት በምሳሌያችን ላይ List • አሬይ ተመሳሳይ አይነት ያላቸው በርካታ ዳታን ይይዛል፡፡ • ሌላም እያንዳንዱ ዳታ ታይፕ የራሱ የሆነ ባህሪ እና አተገባበር አለው። ለምሳሌ በኢንቲጀር እና በፍሎት ላይ የሂሳብ ስራዎችን ማከናወን ትችላለህ፣ በስትሪንግ ላይ ደግሞ የጽሑፍ ማቀነባበሪያ ስራዎችን (እንደ ማዋሃድ፣ መቁረጥ ወዘተ) ማከናወን ትችላለህ። የቡሊያን እሴቶች ደግሞ የፕሮግራምን ፍሰት ለመቆጣጠር በውሳኔ አሰጣጥ (በምሳሌያችን ላይ ያሉ if statements ማየት ትችላላችሁ፡፡ ለምሳሌ grossSalary>10470) እና በሉፕ (loops) ውስጥ በስፋት ያገለግላሉ። የተለያዩ ዳታ ታይፖችን በጥልቀት መረዳት ለተለየ አላማ ትክክለኛውን የdata አይነት ለመምረጥ ይረዳል። ይህ ደግሞ ፕሮግራምህ የበለጠ ቀልጣፋና ትክክለኛ እንዲሆን አስተዋፅኦ ያደርጋል። ለምሳሌ የሰዎችን እድሜ ለማከማቸት ፍሎት ከመጠቀም ኢንቲጀርን መምረጥ የበለጠ ትክክል ይሆናል። ዳታ ታይፕ እና ፈንክሽንን ማወቅ ወሳኝ ፋይዳ አለው፡፡ በቀጣይ ክላስ እኛ መፍጠር ስለምንችለው የዳታ ታይፕ (ክላስ) አወራችኋለው፡፡ ያኔ የኔ ምርጥ የምለውን ኦብጀክት ኦረንቴሽንንም አወራችኋለው፡፡ በመረጣችሁት ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ ውስጥ ያሉ ዳታ ታይፖችን መጥልቅ ማወቅ የፕሮግራሚንግ አቅማችሁን ከማሳደግ አልፎ ልፋታችሁን በእጅጉ ያቀለዋል፡፡ ሊስትን ከተጠቀማችሁ ሰርች በቀላሉ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ሊስትን ማያውቅ ፕሮግራመር ግን ሰርችን ለፍቶ ይፅፋታል፡፡ በፅሁፍ ከዚህ በላይ ማስረዳት ወይ ያረዝመዋል አልያም ያወሳስባል፡፡ ግልፅ እንዲሆንላችሁ የምትፈልጉትን ኮሜንት ላይ ብትተዉልኝ መልካም፡፡

photo content

የጀማሪ ዴቨሎፐርስ ሮድማፕ - ቀን 9 ================ የፕሮግራሚንግ መሰረታውያን - ሀ አንድ ፕሮግራሚንግ ላንጓጅ መማር የሚጀምር ሰው ከምን ይጀምር? አቅልሎ ከማየት፡፡ የምትማሩት ቋንቋ ነው፡፡ ፕሮብለም ሶልቪንግ የናንተ ፈጠራ ነው፡፡ ቋንቋ ስትማሩ አይቀሬ መሰረታውያን አሉት እነ variable ፤ data type ፤ control flow ፤ Function ፤ working with file ፤ database connection ወዘተ፡፡ በዚህ ውስጥ የምትማሩት ህግጋቱን ነው፡፡ ለምሳሌ ቁጥር ተቀብዬ የምይዝበት መያዣ number የሚባል (variable) ለመፍጠር በC# int number ; እላለው፡፡ ለሁሉም የፕሮግራሚንግ መሰረታውያን ከላይ የዘረዘርናቸው ስየማ (declaration) ፤ ትመና (initialization) እና አጠቃቀም (usage) syntax (ህግ) አለው ትማራላችሁ፡፡ በፕሮግራሚንግ ውስጥ በአጠቃላይ የምትማሩት ችግር የመፍታት አቅማችሁን ተጠቅማችሁ ኮምፒዩተሩን ለማዘዝ የሚያስችላችሁን ህግጋት ነው፡፡ ከፕሮግራሚንግ ቋንቋ ጀርባ ያደፈጠ ትልቅ ኮንሰፕት ካለ ኦብጀክት ኦሬንቴሽን ነው፡፡ ይህ አጠቃላይ አስተሳሰብ ፤ ችግር አፈታት ዘዬአችሁን የሚቀይር እሳቤ ስለሆነ ለብቻው በጥልቀት አጥኑት፡፡ ያያያዝኩት ምስል ላይ ምታዩት ፕሮግራም የኤክሴል ፋይል አድራሻ ተሰጥቶታል፡፡ ከተሰጠው የኤክሴል ፋይል ሶስተኛ ኮለመን ሁለተኛ መስመር ጀምሮ ዳታ እስኪያልቅ እያመጣህ ካልኩሌት ግሬድ ለሚባለው ፈንክሽን ላክና ሰርቶ የመለሰልህን ግሬድ የኤክሴል ፋይሉ አራተኛ ኮለመን ላይ አስቀምጥ ፡፡ ይህንን ሰርተህ ስትጨርስ ፋይሉን ሴቭ በለው የሚል ፕሮግራም ነው፡፡ ይህንን የመባያ ህግጋትን ነው የምትማሩት ባጭሩ፡፡ የተተቀሱትን ኮዶች ሁሉ አስምሬባቸዋለው፡፡ በቀኝ በኩል ደግሞ የተሰራውን ግሬድ የሚያሳይ ኤክሴል ፋይሉን አያይዠዋለሁ፡፡ የፕሮግራሚንግ መሰረታውያንን ማጥናት በሁሉም ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ ግድ ነው፡፡

የጀማሪ ዴቨሎፐርስ ሮድማፕ ፤ ቀን 8 የቱን ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ ልምረጥ? ======== ቀላል እና ቀጥተኛ መልስ የሌለው ጥያቄ ነው፡፡ ከመወሰናችሁ በፊት የቋንቋውን አገልግሎት እና ከናንተ ዝንባሌ
የጀማሪ ዴቨሎፐርስ ሮድማፕ ፤ ቀን 8 የቱን ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ ልምረጥ? ======== ቀላል እና ቀጥተኛ መልስ የሌለው ጥያቄ ነው፡፡ ከመወሰናችሁ በፊት የቋንቋውን አገልግሎት እና ከናንተ ዝንባሌ ጋር ይስማማል ወይ የሚለውን ፤ የመማር ቀላልነት ፤ የማህበረሰብ እና ዶኩመንት ሀብቱን ፤ የግል ፕሮዳክት ልስራ ብል ያሰራል ወይ፤ ተፈላጊነቱ እና የስራ እድልስ ፤ ወዘተ የሚሉትን ማገናዘብ ይፈልጋል፡፡ ዝርዝሩን በዚህ ሰንጠረዥ ከልሼ አቅርቤላችኋለው፡፡ ሌሎች በርካታ ቋንቋዎች አሉ፡፡ ቋንቋ እና ፍሬምዎርክ መለየት ጥሩ ነው፡፡ ሪአክት ፤ አንጉላር ፤ ወዘተ ጃቫስክሪፕት ውስጥ ይወድቃሉ (ከፍ ቢል ታይፕስክሪፕት)፡፡ ሀሳብ እና አስተያየታችሁን እንደተለመደው በኮሜንት አሳውቁኝ!