ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

تُعد قناة Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 16 126 مشتركاً، محتلاً المرتبة 5 230 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 226 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 16 126 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 31 أكتوبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 520، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 7، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 22.41‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 10.30‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 3 597 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 653 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 28.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 01 نوفمبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

16 126
المشتركون
+724 ساعات
+197 أيام
+52030 أيام
أرشيف المشاركات
የዓለም ኹሉ መምህር የኾነው #ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ባረፈ በ35 ዓመቱ (በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን) በዛሬዋ ዕለት ኅዳር 17 ሥጋው ፈልሶ በቊስጥንጥንያ በክብር ያረፈበት ነው፤ የቅዱሱ ሥጋውም ቀና ብሎ ሕዝቡን ባርኳል፡፡ ✣✣✣ስለ ቀዳማዊው ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዳግማዊው ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ) እንዲህ ብሎ ገልጾታል፡፡ ✤አፈ ዕንቊ ✤አፈ ጳዝዮን ፤(/ስለ እመቤታችን ፍቅር/ የወር አበባ ያላትን ሴት አንቀጸ ሥጋ ለመሳም ያላፈረ) ✤አፈ ባሕርይ (በድርስቶቹ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስጌጣት) ✤አፈ መዐር ✤አፈ ሦከር (በቃሉ ጣፋጭነት ምእመናንን የሚያለመልማቸው) ✤አፈ አፈው /ሽቱ/ (በትምህርቱ መዐዛ የምሥጢር በጎችን ደስ የሚያሰኛቸው) ✤አፈ ርኄ ✤አፈ ሰይፍ (በውግዘቱ ሥልጣን ከሀዲዎችን የሚቆርጥ) ✤አፈ መጥባሕት ✤የማይነዋወጥ ዐምድ ✤የማይፈርስ መሠረት ✤ከሞገዶች መነሣት የተነሣ የማይሰበር መርከብ ✤በሃይማኖት ባሕር ውስጥ የሚዋኝ ዋናተኛ ✤የማይፈርስ ግንብ ✤በጠላት ፊት የሚፀና አዳራሽ /መጽሐፈ ምሥጢር፣ ዘጌና ምንባብ/ በተጨማሪም፤ በሚከተሉት ስሞችም ይጠራል፡፡ ፨አፈ ወርቅ /የእመቤታችን ስዕል አፍ አውጥታ ነው ዮሐንስ አፈወርቅ ብላ የሰየመችው/ ፨አፈ በረከት ፨ልሳነ ወርቅ ፨የዓለም ሁሉ መምህር ፨ርዕሰ ሊቃውንት ፨ዐምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ) ፨ሐዲስ ዳንኤል ፨ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው ሊቀ ጳጳሳት) ፨መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ ፨ጥዑመ ቃል ~~ ምስጋና ለአምላካችን ይሁንና ንስጥሮስ በምፍቅናው የአንዲት ሴትን ኀፍረት ሥጋ ገልጦ እግዚአብሔር ወልድ በዚህ ማሕፀን ተፀንሶ አልተወለድም ብሎ በሕዝቡ ፊት ተናገረ፤ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም፤ * ‹‹እኔ እግዚአብሔር .. በዚህ ሥጋ ከሴት እንደተወለደ አምናለሁ፤ * እኔ እግዚአብሔር በመዋለጃ ማኅፀን እንደተወሰነ አምናለሁ፤ * እኔ እግዚአብሔር በድንግልና ወተት እንዳደገ፣ በሕፃናትም ሥርዐት ሕፃናትን እንደመሰላቸው፣ ከብቻዋ ከኀጢአትም በቀር የሰውን ሕግ ሁሉ እንደፈጸመ አምናለሁ፡፡›› ብሎ የዚህችን ሴት ኀፍረተ ሥጋ ስለ እመቤታችን ፍቅር ብሎ ሳመ፤ ከእመቤታችን ሥዕል አንደበትም ከዚህ በኋላ ስምህ ዮሐንስ ብቻ ሳይኾን ‹‹ዮሐንስ አፈወርቅ›› ይሁን ብላ ሰይመችው፤ አርሱም ‹‹እሰግድ ለኪ፥ እሰግድ ለኪ ወእዌድሰኪ … ›› ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም የሚነበበውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት፡፡ *በ347 ዓ.ም. በሶርያ ዋና ከተማ በአንጾኪያ ሲኾን የተወለደው፤ አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ አትናስያ ይባላሉ፡፡ *ገና የ15 ዓመት ሕፃን ሳለ በሕፃንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና) በሙሉ ተምሮ ተመልሷል፤ በዚህም በመንፈሳዊውም ኾነ በዘመናዊው ይፍልስፍና ይህ ቀረህ የማይባል ሊቅ ኾነ፡፡ *ቅዱሱ በ16 ዓመቱ ኃብትና ንብረቱን ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ፤ በበርሃ ሳለም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጥተው፤ ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን ሰጡት፡፡ የመጻሕፍት ድርሰት ተገለጹለት፤ በዚህም ቅዱስ በትጋትና በንቃት እጆቹ ታመው በክር አስሮ እስኪጽፍ ድረስ ዐሥር ሺህ የሚደርሱ ድርሳናትን መልዕክታትንና ትርጓሜያትን ጻፈ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅስና ተሹሞ በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ፤ በቅድስናው ወደውታልና የቊስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት፡፡ በሚያስተምርበት ጊዜም ከጣዕመ ትምህርቱ የተነሣ ሕዝቡ ተመስጠውና ተደመው ይሰሙት ነበር፤ ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር፡፡ በሠርጓ ቀን በሞት ሊወስዳት የመጣውን መልከአከ ሞት ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ ገዝቶ 10 ዓመት አቁሞታል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: በተሰደደበት ሃገር ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ.ም. አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ:: /ምንጭ፤ መጽሐፈ ምሥጢር፣ ማኅሌተ ጽጌ፣ ተአምረ ማርያም፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሕይወቱና ትምህርቱ በዲ.ን. ያረጋል አበጋዝ፣ የቃል ትምህርት፣ የዲ.ን. ዮርዳኖስ መጽሐፈ ገጽ፣ በእንተ ምክንያተ ሐውልታት በገብረእግዚአብሔር ኪደ/ ✤✤ #በአንበሳ ላይ የምትጫነው ኢትዮጵያዊቷ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ዕረፍቷ ነው፡፡ * በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን በምሥራቅ ኢትዮዽያ ደዋሮና ፈጠጋር አካባቢ ሲኾን የተወለደችው፤ አባቷ ባሕር አሰግድና እናቷ ክርስቶስ ዕበያ ይባላሉ፡፡ * በወግ በማዕረግ ባል አገባች፤ ግን ወዲያው አፄ ያዕቆብ ገደሉባት፤ ወላጆቿም ግድ ብለው ስዕለ ክርስቶስ የተባለ የሱስንዮስን የጦር መሪ አጋቧት 24 ዓመት እስኪኾናት ድረስም 3ት ልጆችን ወለደች፡፡ አፄ ሱስንዮስ ካቶሊክ በኾነ ጊዜ ባሏ ወደ ንጉሡ እምነት ወደ ካቶሊክነት ገባ፡፡ ልጆቿም እግዚአብሔርን የማያስደስቱ ከኾነ በሞት ውሰዳቸው ብላ ለፈጣሪ በመንገሯ ሦስቱም ልጇቿ ሞቱ፤ ባሏም ክዶ ወደ ካቶሊክነት ስለገባ ተለይታው ወደ ጣና ገዳማትና ወደ ታላቁ ገዳም ዋልድባ ገብታ ብዙ ተጋደለች፡፡ * ንጉሡንም በካቶሊክ እምነቱ ከሌሎች ቅዱሳን ጋራ ኾና ስለተቃወመችው 2 ጊዜ ወደ በርሃ አግዟታል፤ ወደ ጉሙዝ ባጋዛት ወቅት ወደ እሳት ውስጥ ቢከታትም እሳቱ ሳያቃጥላት ወጥታለች፡፡ * ፋሲል ነግሶ ሃይማኖት ተመልሶ ሃገር ሲረጋጋ ወደ ምጽሌ ከዚያም ወደ መንዞ መጥታ 7ት ገዳማትን አቅንታለች፡፡ ከ700 በላይ ለሚኾኑ መነኰሳትና መነኰሳይያት እመ ምኔት ኾናም አስተዳድራለች፡፡ ምግቧም የመረረ ቅጠልና ኮሶ ነበረ፡፡ በስተመጨረሻም የሬማ መድኀኔ ዓለምን አቅንታ በተወለደች በ50 ዓመቷ ብዙ ቃል ኪዳንን ተቀብላ በ1630ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ዐርፋ በዚሁ ገዳም በክብር አርፋለች፤ በበዓለ ዕረፈቷም የብርሃን ምሰሶ ከምድር እስከ ሰማይ ተተክሎ ታይቷል፡፡ ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ ሰማዕትም ጻድቅም ናት፡፡ /ምንጭ ገድለ ወለተ ጴጥሮስ፣ የዲ.ን ዮርዳኖስ መጽሐፈ ገጽ/ (ጽሑፎቹን ከቃል ትምህርት፣ ከመጻሕፍትና ከመጽሐፈ ገጽ አውጣትቶ ለጻፈልን ወንድማችን የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ የዳግማዊ ዮሐንስ አፈወርቅ (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ)ና የቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ረድኤት በረከታቸው ይደርበት፡፡) እኛንም አንባቢዎቹን በረከታቸው ትድረሰን፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/joinchat/AAAAAE2hgYCjGkwz9N1jIw

ሰላም ለከ ሚናስ ኅሩይ፥ ዘታዕካ ሰማይ፥ ዘኀረየከ አዶናይ፨ (አዶናይ አምላክ በሰማይ አዳራሽ የመረጠህ ሚናስ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን) በገባሬ ተዓምርነቱ የሚታወቀው ወጣቱ ሰማዕት ቅዱስ ሚናስ ዛሬ ኅዳር 15 በዓለ ዕረፍቱ ነው፨ በኢትዮጵያ በአተር ቆሎ ብዙ ገቢረ ተዓምራት የሚያደርገው ገዳሞቹ ደቡብ ጎንደር ከባሕር ዳር ከተማ አጠገብ (ከአቡነ ሐራ ድንግል አቅራቢያ) ጢያ ላይ ይገኛሉ፨ በአ.አ. መርካቶ ራጉኤል ጋር ማኅበሩን የሚጠጡ አሉ፤ በሕመም የምትሰቃዩ ማኅበሩን ፈልጋችሁ የአተር ዝክሩን ቅመሱ፥ በእርግጠኝነት ትፈወሳላችሁ፨ በግብፅ ግን በጣም ታዋቂ ሰማዕት ነው፨ * ዛሬ የቅዱስ ቂርቆስ በዓለ ልደቱ ነው፨

መኑ የኃድገነ ፍቅሮ ለክርስቶስ (ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል?) /ሮሜ ፰፥፴፭/ ከኅዳር 14 - 16 ሰማዕታተ ጅጅጋን የምንዘክርበት ጉባኤ፤ በእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ከቀኑ 10 ሰዐት ጀምሮ፨

አዋጅ፤ የ2011ዓ.ም. የገና (የነቢያት) ጾም ቅበላው ሐሙስ ኅዳር 13 ድረስ ብቻ ነው፤ ጾሙ ዐርብ ኅዳር 15 ይጀምራል!!! ላልሰሙት Share/like በማድረግ ይተተባበሩ፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት፡፡/

እንኳን ለቅዱስ እግዚአብሔር አብና ለእልፍ አእላፋት፥ ትዕልፊት አእላፋት (ለቅዱሳን መላእክት በዓለ ሢመት)፤ በሰላምና በጤና አደረሰን፤ አደረሳችሁ፡፡ (ከእልፍ አእላፋት አለቃዎች ስሞች በጥቂቱ)፡፡ ጸሎትነ ትብጻሕ (ሰላም ለክሙ) ለመላእክተ ምሕረት፤ ፨ ሚካኤል ወገብርኤል፥ ፨ ሱራፌል ወኪሩቤል/፬ቱ እንስሳ/፥ ፨ ዑር(ራ)ኤል ወሩፋኤል /፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ/፥ ፨ ሱርያል ወፋኑኤል፥ ፨ አፍኒን ወራጕኤል፥ ፨ ሳቁኤል ወአቅናኤል፥ ፨ ብርናኤል ወሱባኤል፥ ፨ ፍናኤል ወሰላታኤል፥ ፨ ሰዳካኤል ወኤልናኤል፥ ፨ አናንኤል ወኢየሩማኤል፥ ፨ ግርማኤል ወድርማኤል ፥ ፨ ድማህኤል ወአድማኤል፥ ፨ ሙራኤል /ምናቴር አብያቴር/፥ ፨ ሱታ(ስቱ)ኤል ወሱርያል፤ ……. ፎቶዎቹ፤ ክብረ በዓሉ ከሚከበርባቸው ቦታዎች ጥቂቶቹ፤ …. 1. ግሸን ደብረ ከርቤ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ (መስቀሉ የሚገኝበት)፤ 2. ጠዳ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ (ጎንደር፤ ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ)፤ 3. ጎርዶማ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን (በሰሜን ሸዋ)፤ 4. ደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ (አዲስ አበባ)፤ 5. ቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤ.ክ (አዲስ አበባ) 6. ቦሌ ቡኒ ደብረ ቤቴል ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤ.ክ (አዲስ አበባ) /የቀ.ደ.ሰ መድኀኔ ዓለም ወደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

መንበረ ክብር ደብረ ታቦር ቅዱስ ሚካኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም /ኋላ ወቅድስት አርሴማ በሚል እየተጠራ የሚገኝ/፤ (በቀጨኔ አዲሱ ገበያና በእንጦጦ መሃል ጉብታ ላይ የሚገኝ)፤ የታላቁ ደብር የቀጨኔ መድኀኔ ዓለም አፅመ ርስት (ከ108 ዓመታት በፊት መጀመሪያ የተወደሰበት፥የተሠለሰበት ቦታ)፨ እውነትም ደብረ ታቦር፤ ከየትኛውም የአዲስ አበባ ቦታ በቀንም ኾነ በማታ ጉብ ብሎ የሚታይ፨

ኅዳር 12 ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ፥ በእግዚአብሔር የጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ ለምስጋና የሚቆም፥ ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ፥ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሢመቱና እስራኤላውያንን በባሕረ ኤርትራ ያሸገረበት በዓል ነው፡፡ (እንኳን አደረሳችሁ) በዓለ ሢመቱ፤ ሚካኤል ማለት ማን እንደ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ በእለተ እሁድ ካለመኖር ወደ መኖር የመጣ ሲሆን እርሱም የነገደ ኃይላት አለቃቸው ነው በተጨማሪም ከሳጥናኤል ውድቀት በኋላ የአጋእዝትን ነገድም በአለቅነት ደርቦ የያዘ ሲኾን፡፡ ለ100ውም(99ኙም) ነገደ መላእክት አለቃቸውም ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ለሰው ልጆች ምሕረትን ከኅዳር 12 (በዓለ ሢመቱ) ጀምሮ እስከ 13 (የአእላድ መላእክት) በዓል ድረስ ከአምላኩ ምሕረትን የሚለምንበት ነው፡፡ በዚህ ቀን የሚከበረው እስራኤልን ከግብጽ ባርነት እያመራቸው ማውጣቱን ለማዘከር ነው፡፡ ይህም የሆነው ያዕቆብ በረሃብ 70 ኹኖ ወደ ግብፅ ከወረደ በኋላ በ215 ዓመታት (አብርሃም ወደ ግብፅ በተሰደደ በ430 ዓመታት) በኋላ፤ የዮሴፍን ዝና ያልሰማ ፈርኦን በግብፅ ነገሠ፡፡ እስራኤል ከእኛ ይልቅ በዝተዋል ጠላቶቻችን ቢነሱብን ተደርበው ያጠፉናል በማለት አገዛዝ አጸናባቸው ፍርድ አጓደለባቸው፡፡ የእስራኤል ሴቶች ልጅ ሲወልዱ ወንድ ከሆነ እንዲገደል በማረግ መከራ አጸናባቸው፡፡ 430 ዘመን በባርነት ከቆዩ በኋላ ከእብራውያን ወገን የሆነችው ራሔል ጭቃ እያቦካች ምጥ በያዛት ጊዜ እንዲያሳርፉዋት ጠየቀች ግብጻውያን ግን የሕፃናቱ ደም ጡቡን ያጠነክራል ርገጭ አሉዋት፡፡ ከመሐጸኗ የወጡ ሁለት መንትያ ልጆቿን እያየች ከጭቃ ጋር ረገጠች፡፡ ራሔልም አለቀሰች ስለ ልጆቿም መጽናናትን እንቢ አለች፡፡ የእስራኤል ንጉሥ ሆይ የሆነብንን እይ ስትል ራሷን ይዛ ታለቅስ ጀመር እንባዋንም ወደ ሰማይ ንጉሥ ወደ እግዚአብሔር ረጨች፡፡ የራሔል እንባ የሕዝበ እስራኤል ሁሉ ጩኸት እሮሮ ይዛ ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰች፡፡ “. . . ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናት እንቢ አለች” /ኤር 31፥5፤ ማቴ 2፥17/ እንዲል፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን አስነሳና፤ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መሪነት፤ 10 ተዓምራትን በምድረ ግብፅ በ11ኛ ተዓምር ደግሞ በኅዳር 12 (ፈርዖንን ከነሠራዊቱ በኤርትራ ባሕር አስጥሞ) በማድርግ ወደ ተስፋይቱ ምድረ መራቸው፡፡ ባሕረ ኤርትራን እስራኤላውያን እንደተሻገሩም የእስራኤል ልጆች የሙሴ የአሮን እኅት ማርያም ከበሮ እየመታች ንሴብሆ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው እያሉ ጠላታቸውን የመታላቸውን እነሱንም በተአምራቱ ያሻገራቸውን ከጠላታቸው እጅ ያዳናቸውን እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ ከዚህ በኋላ መጋቢ ብሉይ ቅዱስ ሚካኤል እየመራቸው መና ከሰማይ እያወረደላቸው ውሃ ከጭንጫ እያፈለቀላቸው ቀኑን በደመና ሌቱን በብርሃን መርቷቸው አርባ ዘመን ተጉዘው የቃል ኪዳን አገራቸው ምድረ ርስት ከነዓን ገብተዋል፡፡ /ዘጸ 15/ ከሙሴ በኋላ እስራኤልን የመራው ነቢዩ ኢያሱም እስራኤልን በሚመራበት ጊዜ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እስራኤልን ይረዳቸው ነበር፡፡ ከጠላቶቻቸው ጋር ሲዋጉም ሰልፉን ይመራ የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ለምሳሌ እስራኤላውያን ከኢያሪኮ አጠገብ በነበሩበት ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ኢያሱን አነጋግሮታል፡፡ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ቀና ብሎ ሲመለከት የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ አንድ ሰው ከፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም “አይደለሁም ነገር ግን የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ በመሆኔ መጥቻለሁ” ብሎታል /ኢያሱ 5፥13-15/፡፡ ይህ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ከኢያሱ ፊት ለፊት የቆመው መልአክ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ይህን ለአብነት አነሣን እጅ እስራኤል በሚበድሉበት ጊዜ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር የሚማልድላቸው ይህ ታላቅ መልአክ መጋቢ ብሉይ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላክ በእደ መልአኩ ይጠብቀን፤ ከበዓሉ በረከት ይክፈለን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

ኅዳር 9፤ የሠለስቱ ምዕት ክብረ በዓል ነው፡፡ ሐመረ ኖኅ ሠለስቱ ምዕት ቤ.ክ፤ በሃገራችን በሠለስቱ ምዕት (በ31ቱ ሊቃውንት ስም) ብቸኛ የሆነውና ከ310 ዓመታት በፊት በአፄ ቴዎፍሎስ (ስመ መንግሥት አጽራር ሰገድ) ታንጾ የነበረ ሲኾን ንጉሡ ሲያንጹትም የሠለስቱ ምዕት የአእላፍ መላእክትና የነቢያት ቤተ ከርስቲያን አድርገው ነው፤ ድርቡሽ ጎንደርን ከ129 ዓመታት በፊት በወረረ ጊዜ ጠፍ ኹኖ ቆይቶ በ2007 ዓ.ም. ቤተ ክርስቲያኑ ድጋሚ ተሠርቶ፤ እነሆ ዘንድሮ ለ5ኛ ጊዜ ተከብሮ ውሏል፡፡ ይህ ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ጕባኤ ቤትም ሲኖረው፤ ቀድሞ የ4ቱ ጕባኤያት ዋና ማስመስከሪያ ኹኖ ቆይቷል፤ ከአፄ ኀይለ ሥላሴ ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ ደረጃ የመጻሕፍተ መነኰሳት ዋና ማስመስከሪያ ኹኖ ይገኛል፡፡ /ፎቶ ላይ የምትመለከቱት የሠለስቱ ምዕት የመጻሕፍተ መነከኰሳት ጕባኤ ቤት በእሳት አደጋ በተቃጠለበት ወቅት፤ በጎንደር የሚገኙ የመጻሕፍተ ብሉያት፣ የመጻሕፍተ ሐዲሳት፣ የመጻሕፍተ ሊቃውንት የማጽናኛና የምክክር መርሐ ግብር እያካሄዱ የሚያሳይ ነው፡፡)

ለተዝካረ አበው /ኅዳር ፰/ (በታላቁ ገዳም በዋልድባ/ዋሊ/ ብቻ በዛሬው ዕለት ለሚደረገው የአበው መታሰቢያ አደረሳችሁ፨ በኢትዮጵያ በብቸኝነት ጌታችን በመሠረተው በዚህ በታላቁ ገዳም በዋልድባ ብቻ ከሚደረጉ ሥርዐቶች መካከል አንዱና ከቀድሞ አባቶች ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣው መካከል፤ የወጣ ሳይገባ፥ የገባ ሳይወጣ (መርፌም ቢኾን ከሱባዔው በፊት ወደ ገዳሙ ካልገባ ሱባዔው እስኪያልቅ ጥቅም ላይ አይውልም)፨ የ158 ቀናት ሱባዔ ይደረጋል፤ (ከ143 ቀናት በኃዋላ ዛሬ ኅዳር ፰ በተዝካረ አበው ቀን በማኅበር ደረጃ ቢሰባሰቡም መልሰው እስከ ኅዳር ፳፬ ወደ ሱባዔ ገብተው በ፳ወ፬ቱ ካህናተ ሰማይ ትልቁ ሱባዔ ያበቃል፨ በእነዚህ ቀናት ከቀባሪ በስተቀር ወደ ገዳሙ መግባትም አይቻልም፨ ፠፠ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ከአበው አንድነት፥ ከአቡነ ሳሙኤል ልጅነት፥ ከገዳመ ዋሊ ረድኤት በረከት ይክፈለን፨ /ከዋልድባ ዋሊ ገጽ የተወሰደ/