ar
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

تُعد قناة Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 15 519 مشتركاً، محتلاً المرتبة 5 399 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 209 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 15 519 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 04 أكتوبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار -21، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 3، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 16.52‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 4.39‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 2 564 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 682 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 19.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 05 أكتوبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

15 519
المشتركون
+324 ساعات
-47 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
እንኳን ፤ለብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ በዓለ ዕረፍት  እንዲሁም  ለሐዋርያት (የሰኔ) ጾም ፍቺ አደረሳችሁ፡፡ ✤✤ #ብርሃናተ_ዓለም_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ_ወሥርዐተ_ማኅሌት_ዘሐምሌ_፭፡፡ ✼#ሐዋርያው_ቅዱስ_ጴጥሮስ ፤ በገሊላ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው በቤተሳይዳ ተወለደ፡፡ የአባቱ ስም ዮና የእናቱ ስም ሃውኒን ይባላል፡፡ ከ 5 ዓመቱ ጀምሮ ያደገው በቅፍርናሆም ከተማ ነው የመጀመሪያው ስሙ ስምዖን ሲሆን ይህንንም እናቱ በነገዷ ስም እንዳወጣችለት ይነገራል፡፡ ✼#ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ፤ ነገዱ ከዕብራውያን ከብንያም ነገድ ነው አባቱ ዮስአል ሲሆን የተወለደውም በጠርሴስ ከተማ ነው፡፡ ጠርሴስ በንግድ የታወቀች የኬልቅያ ዋና ከተማ ናት፡፡ ሮማውያን በሥራቸው ለሚተዳደሩት ሕዝቦች ሮማዊ ዜግነት ይሰጡ ስለነበር የቅዱስ ጳውሎስ አባት በዜግነት ሮማዊ ነበር፡፡ ይህም ለቅዱስ ጳውሎስ ተላልፎለታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ  በ15 ዓመት ዕድሜው ወደ ትውልድ ሐገሩ በመመለስ በኢየሩሳሌም ከነበረው የታወቀ የገማልያል ትምህርት ቤት ገባ፡፡ በዚያም የአይሁድን ሕግና ሥርዐት እየተማረ እስከ 3ዐ ዓመቱ ቆየ፡፡  በ3ዐ ዓመቱ የአይሁድን ሸንጐ አባል ሆኖ ተቈጠረ፡ ...#ለአገልግሎት_አጠራራቸው ✤✼ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በጐልማሳነቱ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሣ ማሥገር ጀመረ፡፡ ለደቀመዛሙርትነት ሲመረጥ እድሜው 55 ዓመት ሲሆን ወደጌታችን ያመጣውም ወንድሙ እንድርያስ ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት ሲጠራ መተዳደሪያው የነበረውን መረቡን ታንኳውን እንዲህም አባቱን ትቶ ጌታውን የተከተለ ሐዋርያ ነው፡፡ በቂሳርያ ከተማ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ በጠየቀ ጊዜ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብሎ ለአይሁድ ሊቃውንት የተሰወረ ምሥጢረ ተዋሕዶ ገልጦ በመመስከሩ ጌታችን አንተ ጴጥሮስ ነህ ብሎታል ይህን በጽርዕ ቋንቋ «ዐለት» ማለት ነው በአረማይክ ደግሞ ኬፋ ይባላል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታን ይወድ ነበር፡፡ ፍቅሩ ግን ቅንዓት የተቀላቀለ በመሆኑ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ የሞቱን ነገር ቀድሞ ሲነግራቸው አይሁንብህ በማለት ተከራክሯል፡፡ ማቴ 16፥23 በኋላም ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም ብሎ በራሱ ቅንዓት ተማምኖ ተናግሮ ነበር፡፡ ጌታችን ዶሮ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለው እንኳን ከአንተ ጋር መሞት እንኳ የሚያስፈልገኝ ቢሆን ከቶ አልክድህም በማለት የተናገረ ሐዋርያ ነው፡፡ ማቴ 26፥34 ነገር ግን 3 ጊዜ ጌታችንን አላውቀውም ብሎ ካደ፤ ዶሮ በጮኸና አምላኩን መበደሉን እንዳወቀ ከግቢው ወጥቶ አለቀሰ ንስሐ ገባ፡፡ ጴጥሮስ በዕድሜው ታላቅነት በሐዋርያት ዘንድ እንደ አባት ይታይ ስለነuር ጌታ በተለየው ጊዘ? ሐዋርያቱን ሊመግብ ወደሚያውቀው ሙያ ዓሣ ወደማስገሩ ተሠማራ ጌታም አስቀድሞ የመረጠው እርሱ ነውና ቢከዳው እንኳን በንስሐ በመመለሱ ንስሐውን መቀበሉን ዛሬም እንደሚወደው ይገልጽለƒም ዘንድ በጥብርያዶስ ባሕር ተገለጠለት፡፡ ሦስት ጊዜ ክዶት ነበርና ቀኖና ሰጠው፡፡ አሁን ቅዱስ ጴጥሮስ በራስ መተማመኑ እንዳላዋጣው አውቆ ትወደኛለህ ተብሎ ሲጠየቅ አንተ ታውቃለህ ነበረ መልሱ የራሱ እውቀት የት እንዳደረሰው ያውቃልና ጌታችንም ኀዳጌ በቀል /በቀልን የሚተው/ ነውና ዛሬም እንደሚወደው በንሰሐ ተመልሷልና ዛሬም ለእርሱ የሰጠውን ክብር እንደማያጐልበት ሲነግረው ግልገሎቼን አሠማራ ጠቦቶቼን ጠብቅ በጐቼን አሠማራ በማለት አደራውን አስረከበው፡፡ ዮሐ 21፥15-17 ✼#ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ዘመን ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም ስለነበረ በአይሁድ ሸንጐ አባልነት ለ2 ዓመታት በሠራበት ወቅት እምነቱ ቀናተኛ ፈሪሳዊ በመኾኑ ክርስቲያኖችን በማናቸውም አጋጣማ> ይቃወም ነበር፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ ተወግሮ በሰማዕትነት ሲያርፍም የወጋሪዎችን ልብe ይጠብቅ የነበረው እርሱ ነው፡፡  በ32 ዓመት ዕድሜው ከኢየሩሳሌም 223 ኪ.ሜ ርቀት በስተሰሜን በኩል በምትገኘው የደማስቆ ከተማ ብዙ ክርስቲያኖች መኖራቸውን ሲሰማ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቀርቦ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት የሚያስችKውን የፈቃድ ደብዳቤ ጠይቆ ካገኘ በኋላ ጭፍሮችን አስከትሎ ወደ ደማስቆ አመራ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ከተማዋ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረው ነበር ከሰማይ የወረደው ብርሃን አካባቢውን ያለበሰውና ሳዖል፥ ሳዖል ስለምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምፅ የሰማው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስም ጌታ ሆይ ማን ነህ? ብሎ ጠየቀ የምታሳድደኝ እኔ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል ሲል መድኀኒታችን ተናገረው፡፡ ያንን በወደቀበት ሆኖ እየተንቀጠቀጠ ጌታ ሆይ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ ሲል ጠየቀው ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ወደ ደማስቆ እንዲገባ ተነገረው፡፡ የሐዋ 9፥1     የሐዋርያው ዓይኖች ለማየት አልቻሉም፡፡ እየተመራ ወደ ደማስቆ ገባ ለ3 ቀናት ያህልም እህል ሳይቀምስ ቆየ በዚያች ዕለት እግዚአብሔር አምላክ በደማስቆ ለሚገኘው እና ሐናንያ ለተባለው አባት በራዕይ ተገለጠለት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ያለበትን አድራሻ ነገረውና  እንዲያጠምቀው አዘዘው፡፡ ሐናንያ አስቀድሞ የቅዱስ ጳውሎስን ማንነት ያውቃል፡፡ አብዛኞቹ በደማስቆ የሚገኙት ክርስቲያኖች ከኢየሩሳሌም በስደት ጊዜ የመጡ ናቸው፡፡ ያን ስደት ያስነሳው ደግሞ በቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ የደረሰው መከራ ነው፡፡ በዚህ በቅዱስ እስጢፋኖስ ሰማዕትነት ደግሞ ዋናው ተዋናይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ነበርና ነው፡፡ ሐናንያ ቅዱስ ጳውሎስን ካጠመቀውና ካስተማረውም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ዓረብ ሐገር መሄዱን ^c< }“ÓbM:: ÑL 1፥17 ለሦስት ዓመታት በዓረቢያ በረሃ ከቆየ በኋላ ወደ ደማስቆ ከተማ ተመለሰ፡፡ በዚያም በነበሩ አይሁድ መካከል በፊት ያሳድደው የነበረውን ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ጀመረ፡፡ ከዚያ በፊት በፈሪሳዊነቱና ለአይሁድ ሕግ በነበረው ቅንዓት የሚታወቀው ጳውሎስ ዛሬ ወንጌል ሲሰብክ በማየታቸው አይሁድ ተነሡበት፡፡ በዚያም የተነሣ የደማስቆ ክርስቲያኖች በቅርጫት አውርደው ወደ ኢየሩሳሌም ላኩት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ አይሁድ ጳውሎስን እንደሚያውቁት እና እንደለመዱት ሆኖ ስላላገኙት ሊገድሉት ተነሱ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ክርስቲያኖች የቅዱስ ጳውሎስን መመለስ ሊያምኑ አልቻሉም፡፡ በመጨረሻ ግን በርናባስ ወደ ሐዋርያት ዘንድ ወስዶ የጳውሎስን መመለስ በመተረክ እንዲያምኑት አደረጋቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም በድፍረት በማስተማሩ አይሁድ ስለተቃወሙት ከተማዋን ትቶ በቂሳርያ በኩል ወደ ትውልድ ሐገሩ ጠርሴስ ተመለሰ፡፡

፰. ፀዶበር ዮሐንስ መጥምቅ፤ አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ መንዝ ፥ ቀያ ገብርኤል፤ ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መንዝ → ቀያ ገብርኤል፡፡ ፱. አርባ ምንጭ ገረሴ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ፤ (ፈዋሴ ድውያን የሆነ ፈዋሽ ጠበል ያለበት) አድራሻ፤ አርባ ምንጭ ሀገረ ስብከት፥ ገረሴ፤ ታክሲ፤ ከአ.አ. አለም ባንክ አውቶቡስ ተራ → አርባ ምንጭ → ገረሴ (ከአርባ ምንጭ 55 ኪ.ሜ.)፡፡ ፲. ወንጪ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ፤ አድራሻ፤ ደቡብ ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ወንጪ፤ ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ ውቶቡስ ተራ → ወንጪ፡፡ ፲፩. ደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) ዳግማዊ ሸንኮራ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ፤ (ፈዋሴ ድውያን ጠበል ያለበት) አድራሻ፤ ደቡብ ሸዋ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ አድአ ወረዳ ቤተ ክህነት ፥ ከታ፤ ታክሲ፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ዘይት → ከታ፡፡ ፲፪. ተንታ ደብረ ብርሃን ቅዱስ ሚካኤል፤ (ንጉሥ ሚካኤል በሚያስደንቅ ሁኔታ ያሠሩት) አድራሻ፤ ደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት፥ አምባሰል፥ ተንታ ወረዳ፥ ጠዓት ቀበሌ፥ እሜገኝ፤ ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ጻድቃኔ፡፡ ፲፫. ሰበታ ፈለገ ዮርዳኖስ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ሰበታ፤ ታክሲ፤ ከአ.አ. አስኮ አውቶቡስ ተራ → ሰበታ፡፡ ፲፬. ሰበታ ፈለገ ዮርዳኖስ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት፥ ቨርጂኒያ፤ ታክሲ፤ ከአ.አ. ቦሌ አየር መንገድ → አሜሪካ /ቨርጂኒያ/፡፡ አቅጣጫ ምንጭ ዋሊ.. /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ::  ꔰ   #share Contact: https://t.me/finotehiwot1927 .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .Telegram...  https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot  .YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w                    www.finotehiwotsundayschool.com ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት . Telegram (https://t.me/finotehiwot1927)

#ሰኔ #፴ ፤ #በዓለ_ልደቱ_ለቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ_፡፡ #በመላው_ዓለም_ክብረ_በዓሉ_የሚከበርባቸው_ #፴፰ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ #በአዲስ_አበባ_የቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ_በዓለ_ልደት_ክብረ_በዓል_የሚከበርባቸው_ #፳፬ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ (ሌሎች ያልጠቀስናቸው ካሉ ጨምሩበት፡፡) ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ፩. ቦሌ ደብረ ሳሌም ዮሐንስ መጥምቅ (ኋላ መድኀኔ ዓለም ወዮሐንስ መጥምቅ) ቤ/ክ፤ አድራሻው፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ቦሌ መድኀኔ ዓለም፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ(መገናኛ) → ቦሌ፤ ፪. ፉሪ ፈለገ ዮርዳኖስ ቅዱስ ዮሐንስና ማርያም ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ጀሞ 3፥ መስታወት ፋብሪካ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ሜክሲኮ → ጀሞ፡፡ ፫. ደብረ ሰሊሆም መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስና መድኀኔ ዓለም ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ በርታ ሰፈረ ሰላም፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ(4ኪሎ) → ቃሊቲ፡፡ ፬. ቱሉ አቦ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ዑራኤልና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ፤ አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ቱሉ አቦ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ቃሊቲ → ቱሉ አቦ፡፡ ፭. ጎፋ መብራት ኀይል ደብረ መዊዕ ቅዱስ መርቆሬዎስና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ ጎፋ፥ መብራት ኀይል፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ጎፋ መብራት ኀይል፡፡ ፮. ላፍቶ ኢያሪኮ መድኀኔ ዓለም (ለብቻው የቅዱስ ዮሐንስ ሕንፃ ቤ/ክ አለ)፤ አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ ቀርሳ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ሜክሲኮ → ኢያሪኮ መድኀኔ ዓለም፡፡ ፯. ቦሌ ቡልቡላ ፍኖተ ሕይወት ማርያምና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ፤ አድራሻው፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ቡልቡላ ኮንዶሚንየም፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ሳሪስ → ቡልቡላ፤ ፰. ቤተል ጌቴሴማኒ ቅድስት ማርያም ወዮሐንስ ፤ አድራሻው፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ቤቴል፥ መኪና መለማመጃ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ኮልፌ → መኪና መለማመጃ፤ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ #እንዲሁም_በድርብነት_፤ ፱. ጉለሌ ሸጎሌ ኪዳነ ምሕረት ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ አዲሱ ገበያ ፥ ቶታል፥ ወደ ዊንጌት በቀለበት መንገገዱ ትንሽ ሄደው፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (አስኮ) → አዲስ ገበያ፡፡ ፲. አንቆርጫ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት ማርያም ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ አንቆርጫ፤ ታክሲ፤ ከጊዮርጊስ (4 ኪሎ) (6 ኪሎ) → ፈረንሳይ → አንቆርጫ፡፡ ፲፩. ፈረንሳይ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ፈረንሳይ ፥ ብረት ድልድይ፤ ታክሲ፤ ከጊዮርጊስ (4 ኪሎ) (6 ኪሎ) → ፈረንሳይ → ብረት ድልድይ፡፡ ፲፪. ቦሌ ሰሚት መካነ ሰላም መድኀኔ ዓለም ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ሰሚት፥ ወጂ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ሰሚት፡፡ ፲፫. ገዳመ ኢየሱስ፤ አድራሻ፤ ልደታ ክፍለ ከተማ፥ ሆላንድ ኤምባሲ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ኮልፌ አጣና ተራ፡፡ ፲፬. አውግስታ ደብረ ጽዮን ማርያም ቤ/ከ፤ አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ አውግስታ፥ ሸሚዝ ፋብሪካ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ጦር ኃይሎች → አውግስታ፡፡ ፲፭. አስኮ ደብረ መድኀኒት መድኀኔ ዓለምና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ አስኮ፥ አዲስ ሰፈር፤ ታክሲ፤ ከአራዳ (ፒያሳ) → አስኮ አዲስ ሰፈር፡፡ ፲፮. መዝገበ ምሕረት ቅዱስ ፋኑኤል ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ፋኑኤል ሰፈር፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ(ከመርካቶ) → ካራቆሬ፡፡ ፲፯. ምዕራፈ ቅዱሳን ፈለገ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስና አቡነ አረጋዊ ገዳም፤ አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ሳሪስ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ሳሪስ ፲፰. ሳሪስ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ሳሪስ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ሳሪስ ፲፱. ቀርሳ ፈለገ ብርሃን ቅድስት ልደታ ለማርያምና አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፤ አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ገላን ኮንዶሚኒየም፥ ቀርሳ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ቃሊቲ → ቀርሳ፡፡ ፳. ኮልፌ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ዊንጌት፥ ጠሮ አራት መንታ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ አራዳ → ዊንጌት፡፡ ፳፩. ካራ አሎ ደብር ቅዱስ ደብረ ቀርሜሎስ መደኀኔ ዓለምና አቡነ ገሪማ ገዳም፤ አድራሻው፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ኮተቤ፥ ካራ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ(4 ኪሎ) → ሾላ መገናኛ → ኮተቤ ካራ፤ ፳፪. ምሥራቀ ፀሐይ ገብርኤል፤ አርሴማና አቡነ አዳም ቤ/ክ ፤ አድራሻው፤ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ መካኒሳ፥ ጀርመን ዐደባባይ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → መካኒሳ /ጀርመን ዐደባባይ/፤ ፳፫. ሰርጢ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ቤ/ክ፤ አድራሻው፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ሰርጢ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ቃሊቲ/አቃቂ → ሰርጢ፤ ፳፬. አቃቂ ፈንታ ደብረ ጽጌ ሩፋኤልና አርሴማ፤ አድራሻው፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ፈንታ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ቃሊቲ/አቃቂ → ፈንታ፤ #እንዲሁም_ ፈዋሴ ድውያን ወገባሬ ተአምራት የሆኑ #ጠበሎቹ፤ መካነ ሰማዕት ደብረ ፍስሓ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ (ለገሃር ምድር ባቡር ጣቢያ ጀርባ)፤ ፈዋሽ የፍልውኃ ጠበል በላፍቶ ኢያሪኮ መድኀኔ ዓለም ቤ/ክ አለ፡፡ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ #በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ጥንታውያን #፲፬ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. ደብረ ቢዘን ዘንባባ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ገዳም፤ (የቅዱሳን መናኸሪያ) አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ተጉለት፤ ትራንስፖርት፤ ከጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን → በኩክ የለሽ መስመር የ1 ሰዐት የእግር ጕዞ፤ ወይም፤ ከጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን → ይዞሽ አሞራ → የ1 ሰዐት እግር ጕዞ፡፡ ፪. ጎንደር ደብረ ጽጌ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር፡፡ ፫. ሸንኮራ ደብረ መንክራት ቅዱስ ዮሐንስ ፤ (ዮሐንስ ጌታን ሲያጠምቀው በሚስል ሁኔታ ከደረቅ አለት መሃል በተሰቈረ ቀዳዳ የሚፈልቅ አስደናቂ ጠብል ያለበት) አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ምንጃር፤ ታክሲ፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ሞጆ → ሸንኮራ፤ ፬. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤ/ክ፤ (በሸንኮራ ዮሐንስ መስመር መንገድ ዳር ላየይ የሚገኝ) አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ምንጃር፤ ታክሲ፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ሞጆ → ሸንኮራ (ሳማ ሰንበት) መንገድ አጠገብ የሚገኝ፤ ፭. ደብረ አናጕግ ቅዱስ ሚካኤል ወዮሐንስ መጥምቅ ፤ አድራሻው፤ አኵሱም (ማዕከላዊ ትግራይ) ሀገረ ስብከት፥ አኵስም አጠገብ፤ ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → አኵስም → አናጕግ፡፡ ፮. መርሐ ቤቴ አሮጋንዳ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ፤ አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ መርሐ ቤቴ → ዓለም ከተማ፤ ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → መርሐቤቴ /አሮጋንዳ/፤ ፯. አዲስጌ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ፤ አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ እንሳሮ፤ ታክሲ፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ለሚ → እንሳሮ፡፡ / ፍ.ሕ.ሰ.ት.ቤት /

#ሰኔ_21 ሰኔ ጎልጐታ ወሕንፀተ ቤተክርስቲያን እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስተ ቅዱሳን ለድንግል ማርያም ሰኔ ጐልጐታና ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን (ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ለታነጸበት) ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ፡፡ ✤✤ ሰኔ ጎልጐታ ፤ ‹‹ ሰኔ ጎልጐታ ችግር የምትፈታታ፡፡›› ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም በዚህች ቀን (ሰኔ 21) ልጇን ወዳጇን ጐልጐታ በሚባል ቦታ ላይ እንባዋ እንደ ጅረት እስኪፈስ ድረስ ለኃጥአን ምሕረትን ለምናዋለች:: ጌታችንም ‹‹ስምሽን የጠራውን፤ በቃል ኪዳንሽ ያመነውን ሁሉ እምርልሻለሁ፡፡›› ብሎ ቃል ኪዳን ሰጥቷታል፡፡ ሰኔ ጐልጐታን ተመልከት ✤✤ ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን፤ ሰኔ 21 ከእመቤታችን #33ቱ በዓላት አንዱ ሲኾን፤ ሕንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል፡፡ በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በአምላክ እናት ስም የታነጸችው በዚሁ እለት በሰኔ 20 ቀን ነው፡፡ አናጺውም ደግሞ እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ ቦታው በፊልጵስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው፤ ጥንተ ነገሩስ (ታሪኩ) እንደምን ነው ቢሉ፤ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና አምላካችን መደኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ‹‹ሑሩ ወመሐሩ ኵሎ አሕዛበ፤ አሕዛብን ሁሉ ሒዱና አስተምሩ፡፡›› /ማቴ. 28፥19/ ባላቸው ቃል መሠረት ሐዋርያት በወንጌል ያርሷት ዘንድ በዕጣ ተካፍለዋታል:: የሰው ልጅ ድኅነቱ የሚፈጸመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበል ነውና (ዮሐ. 6፥ 56) አበው ሐዋርያት ቊርባንን በተመረጡ ሰዎች ቤት እያዘጋጁ ቀድሰው ያቆርቡ ነበር:: በመጀመሪያ በጽርሐ ጽዮን፣ቀጥሎም በተለያዩ ሰዎች ቤት እንዲህ ይከናወን ነበር፡፡ ለጸሎት ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ምኵራበ አይሁድን ይጠቀሙ ነበር:: እየቆየ ሲሔድ ግን ከአሕዛብ ያመኑ ሰዎች ቊጥር እጅጉን በመብዛቱ /በተለይ ቅዱስ ዻውሎስ ያሳመናቸው ለጸሎት እያሉ ወደ ጣዖት ቤት መግባት አመጡ::/ በዚህ ምክንያት መምህራን ሕዝቡን ‹‹ካመናችሁ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት ቤት ትገባላችሁ?›› ቢሏቸው ‹‹እኛ ምን እናድርግ! የምንጸልይበት ቤት የለን››ሲሉ መለሱላቸው:: ነገሩ ሲያያዝ ከደጋጉ ሐዋርያት ዻውሎስና በርናባስ ደረሰ:: ወዲያውኑ አንዳንድ ወንድሞች ቤት ‹‹ለምን አናንጽም?›› ብለው ነበር:: ቅዱስ ዻውሎስ ግን ‹‹ሊቀ ሐዋርያቱ ሳይፈቅድ አይሆንም›› አለ:: (ለዚህ ነው ዛሬም ሊቀ ዻዻስ ካልፈቀደ ቤተክርስቲያን የማይታነጸው፡፡) ከዚያ ቅዱሳን ዻውሎስና በርናባስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ሔደው ነገሩን ለቅዱስ ዼጥሮስ አስረዱ:: ሊቀ ሐዋርያቱ ቅዱስ #ዼጥሮስም ‹‹የጌታችን ፈቃዱመኾኑን እናውቅ ዘንድ ተያይዘን ሱባዔ እንግባ›› ብሎ አዋጅ ነገረ:: በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድ ልብ ሱባዔ ገቡ:: በሱባዔያቸው መጨረሻም ክብር ይግባውና ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መላአክትን አስከትሎ በግርማ ወደ እነርሱ ወረደ፤እመቤታችን በቀኙ ነበረች፡፡ ኹሉንም ሐዋርያት በሩቅም በቅርብም ያሉትን ደቀ መዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ ፊልጵስዩስ በሚባል ሃገር ሰበሰባቸው፡፡ ከዚያም በስተምሥራቅ ከከተማ ወጣ ወዳለ ሥፍራ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ፡፡ 3ቱንም ድንጋዮችን በተአምራት አቀራርቦ አንሥቶ ጎተታቸው፡፡ ድንጋዮቹም እንደሰም ተለጠጡ፣ እንደ ግድግዳም ሆኑ፡፡ ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ለሐዋርያቱ ሰጣቸው፡፡ እነርሱም እሳት እንዳየው ሰም በእጃቸው እየለመለሙ (እየሳቡ) ቁመቱን 24፥ ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ዕጽብት፥ ግርምት የምትኾን 3 ክፍል ያላትን የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን በ52 ዓ/ም ሰኔ 20 ቀን አነጹ፡፡ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ፤ ጌታችንም በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም አምሳያ አድርጎ አነጻት፤ ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ለሐዋርያቱ ‹‹እንግዲህ እናንተም እንዲህ አድርጋችሁ ሥሩ፡፡›› ብሏቸው ዐረገ፡፡ ✜ በማግስቱ ሰኔ 21 ዕለት ደግሞ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክትን፣ ሰማያውያን ቅዱሳንን እና እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን ይዞ ወረደ:: ሐዋርያቱ አብዛኞቹ እዛው ሲጸልዩ አድረው ነበርና ጌታችን ከቅዳሴው በፊት 2 ነገሮችን አሳየ፤ አስቀድሞ ቤተክርስቲያኗን በድንግል እናቱ ስም አክብሮ ሥርዐተ ቤተክርስቲያንን አሳየ:: ቀጥሎ ደግሞ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስን ከመካከል አቁሞ ‹‹አርሳይሮስ›› ሲል ሾመው:: ይኼውም የዓለም ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት (ፓትርያርክ) ማለት ነው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ‹ ‹‹አክስዮስ››(አክዮስ)እያሉ 3 ጊዜ አሰምተው ጮሁ:: አክዮስ ማለት በግዕዙ ‹‹ይደልዎ›› በአማርኛው ደግሞ ‹‹ይገባዋል፤ ያስምርለት›› እንደ ማለት ነው:: ጌታችን ይህን ከከወነ በኋላ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ:: አማናዊት ማኅደሩን ድንግል ማርያምን መንበር አድርጎ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ ተራዳኢ ካህን ቆሞ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሠራኢ ዲያቆን ኾኖ፣ ሐዋርያት ድንግልን ከበው፣ መላእክተ ብርሃን በክብራቸው ቆመው ጌታችን ቀድሶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወዳጆቹ አቀበለ:: በዚያች ዕለት በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የማይችል ደስታ ተደረገ:: ከቅዳሴ በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን አዘዛቸው:: ‹‹ከዚህ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም በእናቴ በማርያም ስም አብያተ ክርስቲያናትን አንጹ፤ ይህችን እለት የሚያከብራትን አከብረዋለሁ::›› ብሏቸው ከድንግል እናቱና ከመላእክቱ ጋር ዐረገ:: ✤✤ ሥርዐተ ማኅሌቱ እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትጠቀሙበበት ዘንድ አስቀምጠንላችኋል፤ ✼ የድንግል እመቤታችን ልመናዋ ክብሯ፣ ጣዕመ ፍቅሯና በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን:: አሜን! /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ :: ꔰ #share Contact: https://t.me/finotehiwot1927 .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .Telegram... https://t.me/finotehiwott http://tiktok.com/@finotehiwot .YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w www.finotehiwotsundayschool.com ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት . Telegram (https://t.me/finotehiwot1927)

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት - إحصائيات وتحليلات قناة تيليجرام @finotehiwott