ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

تُعد قناة Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 16 041 مشتركاً، محتلاً المرتبة 5 280 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 239 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 16 041 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 28 أكتوبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 512، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -6، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 25.18‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 10.37‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 4 039 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 663 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 30.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 29 أكتوبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

16 041
المشتركون
-624 ساعات
+917 أيام
+51230 أيام
أرشيف المشاركات
✣✣✣ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች የጾም ምግብ ይዘጋጅልን በማለታቸው፣ ነጠላ ለብሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲሔዱና እንዲመለሱ በመጠየቃቸው፤ ተማሪዎችን እንዳይማሩ ቀሰቀሳችሁ ተብለው አምስት ተማሪዎች እንደተባረሩ፤ ከ20 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ለመባረር ስማቸው ተዘርዝሮ መያዙን ተማሪዎች ገለጡ። ✣✣✣ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ተማሪዎች በሃይማኖታቸው ምክንያት በተደጋጋሚ ችግር ያጋጥማቸዋል፤ ለምሳሌ ያህልም ከዓመት በፊት አንድ ተማሪ ትልቅ መስቀል አደረግህ ተብሎ ተባርዋል።

የዓለም ኹሉ መምህር የኾነው #ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ባረፈ በ35 ዓመቱ (በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን) በዛሬዋ ዕለት ኅዳር 17 ሥጋው ፈልሶ በቊስጥንጥንያ በክብር ያረፈበት ነው፤ የቅዱሱ ሥጋውም ቀና ብሎ ሕዝቡን ባርኳል፡፡ ✣✣✣ስለ ቀዳማዊው ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዳግማዊው ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ) እንዲህ ብሎ ገልጾታል፡፡ ✤አፈ ዕንቊ ✤አፈ ጳዝዮን ፤(/ስለ እመቤታችን ፍቅር/ የወር አበባ ያላትን ሴት አንቀጸ ሥጋ ለመሳም ያላፈረ) ✤አፈ ባሕርይ (በድርስቶቹ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስጌጣት) ✤አፈ መዐር ✤አፈ ሦከር (በቃሉ ጣፋጭነት ምእመናንን የሚያለመልማቸው) ✤አፈ አፈው /ሽቱ/ (በትምህርቱ መዐዛ የምሥጢር በጎችን ደስ የሚያሰኛቸው) ✤አፈ ርኄ ✤አፈ ሰይፍ (በውግዘቱ ሥልጣን ከሀዲዎችን የሚቆርጥ) ✤አፈ መጥባሕት ✤የማይነዋወጥ ዐምድ ✤የማይፈርስ መሠረት ✤ከሞገዶች መነሣት የተነሣ የማይሰበር መርከብ ✤በሃይማኖት ባሕር ውስጥ የሚዋኝ ዋናተኛ ✤የማይፈርስ ግንብ ✤በጠላት ፊት የሚፀና አዳራሽ /መጽሐፈ ምሥጢር፣ ዘጌና ምንባብ/ በተጨማሪም፤ በሚከተሉት ስሞችም ይጠራል፡፡ ፨አፈ ወርቅ /የእመቤታችን ስዕል አፍ አውጥታ ነው ዮሐንስ አፈወርቅ ብላ የሰየመችው/ ፨አፈ በረከት ፨ልሳነ ወርቅ ፨የዓለም ሁሉ መምህር ፨ርዕሰ ሊቃውንት ፨ዐምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ) ፨ሐዲስ ዳንኤል ፨ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው ሊቀ ጳጳሳት) ፨መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ ፨ጥዑመ ቃል ~~ ምስጋና ለአምላካችን ይሁንና ንስጥሮስ በምፍቅናው የአንዲት ሴትን ኀፍረት ሥጋ ገልጦ እግዚአብሔር ወልድ በዚህ ማሕፀን ተፀንሶ አልተወለድም ብሎ በሕዝቡ ፊት ተናገረ፤ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም፤ * ‹‹እኔ እግዚአብሔር .. በዚህ ሥጋ ከሴት እንደተወለደ አምናለሁ፤ * እኔ እግዚአብሔር በመዋለጃ ማኅፀን እንደተወሰነ አምናለሁ፤ * እኔ እግዚአብሔር በድንግልና ወተት እንዳደገ፣ በሕፃናትም ሥርዐት ሕፃናትን እንደመሰላቸው፣ ከብቻዋ ከኀጢአትም በቀር የሰውን ሕግ ሁሉ እንደፈጸመ አምናለሁ፡፡›› ብሎ የዚህችን ሴት ኀፍረተ ሥጋ ስለ እመቤታችን ፍቅር ብሎ ሳመ፤ ከእመቤታችን ሥዕል አንደበትም ከዚህ በኋላ ስምህ ዮሐንስ ብቻ ሳይኾን ‹‹ዮሐንስ አፈወርቅ›› ይሁን ብላ ሰይመችው፤ አርሱም ‹‹እሰግድ ለኪ፥ እሰግድ ለኪ ወእዌድሰኪ … ›› ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም የሚነበበውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት፡፡ *በ347 ዓ.ም. በሶርያ ዋና ከተማ በአንጾኪያ ሲኾን የተወለደው፤ አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ አትናስያ ይባላሉ፡፡ *ገና የ15 ዓመት ሕፃን ሳለ በሕፃንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና) በሙሉ ተምሮ ተመልሷል፤ በዚህም በመንፈሳዊውም ኾነ በዘመናዊው ይፍልስፍና ይህ ቀረህ የማይባል ሊቅ ኾነ፡፡ *ቅዱሱ በ16 ዓመቱ ኃብትና ንብረቱን ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ፤ በበርሃ ሳለም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጥተው፤ ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን ሰጡት፡፡ የመጻሕፍት ድርሰት ተገለጹለት፤ በዚህም ቅዱስ በትጋትና በንቃት እጆቹ ታመው በክር አስሮ እስኪጽፍ ድረስ ዐሥር ሺህ የሚደርሱ ድርሳናትን መልዕክታትንና ትርጓሜያትን ጻፈ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅስና ተሹሞ በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ፤ በቅድስናው ወደውታልና የቊስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት፡፡ በሚያስተምርበት ጊዜም ከጣዕመ ትምህርቱ የተነሣ ሕዝቡ ተመስጠውና ተደመው ይሰሙት ነበር፤ ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር፡፡ በሠርጓ ቀን በሞት ሊወስዳት የመጣውን መልከአከ ሞት ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ ገዝቶ 10 ዓመት አቁሞታል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: በተሰደደበት ሃገር ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ.ም. አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ:: /ምንጭ፤ መጽሐፈ ምሥጢር፣ ማኅሌተ ጽጌ፣ ተአምረ ማርያም፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሕይወቱና ትምህርቱ በዲ.ን. ያረጋል አበጋዝ፣ የቃል ትምህርት፣ የዲ.ን. ዮርዳኖስ መጽሐፈ ገጽ፣ በእንተ ምክንያተ ሐውልታት በገብረእግዚአብሔር ኪደ/ ✤✤ #በአንበሳ ላይ የምትጫነው ኢትዮጵያዊቷ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ዕረፍቷ ነው፡፡ * በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን በምሥራቅ ኢትዮዽያ ደዋሮና ፈጠጋር አካባቢ ሲኾን የተወለደችው፤ አባቷ ባሕር አሰግድና እናቷ ክርስቶስ ዕበያ ይባላሉ፡፡ * በወግ በማዕረግ ባል አገባች፤ ግን ወዲያው አፄ ያዕቆብ ገደሉባት፤ ወላጆቿም ግድ ብለው ስዕለ ክርስቶስ የተባለ የሱስንዮስን የጦር መሪ አጋቧት 24 ዓመት እስኪኾናት ድረስም 3ት ልጆችን ወለደች፡፡ አፄ ሱስንዮስ ካቶሊክ በኾነ ጊዜ ባሏ ወደ ንጉሡ እምነት ወደ ካቶሊክነት ገባ፡፡ ልጆቿም እግዚአብሔርን የማያስደስቱ ከኾነ በሞት ውሰዳቸው ብላ ለፈጣሪ በመንገሯ ሦስቱም ልጇቿ ሞቱ፤ ባሏም ክዶ ወደ ካቶሊክነት ስለገባ ተለይታው ወደ ጣና ገዳማትና ወደ ታላቁ ገዳም ዋልድባ ገብታ ብዙ ተጋደለች፡፡ * ንጉሡንም በካቶሊክ እምነቱ ከሌሎች ቅዱሳን ጋራ ኾና ስለተቃወመችው 2 ጊዜ ወደ በርሃ አግዟታል፤ ወደ ጉሙዝ ባጋዛት ወቅት ወደ እሳት ውስጥ ቢከታትም እሳቱ ሳያቃጥላት ወጥታለች፡፡ * ፋሲል ነግሶ ሃይማኖት ተመልሶ ሃገር ሲረጋጋ ወደ ምጽሌ ከዚያም ወደ መንዞ መጥታ 7ት ገዳማትን አቅንታለች፡፡ ከ700 በላይ ለሚኾኑ መነኰሳትና መነኰሳይያት እመ ምኔት ኾናም አስተዳድራለች፡፡ ምግቧም የመረረ ቅጠልና ኮሶ ነበረ፡፡ በስተመጨረሻም የሬማ መድኀኔ ዓለምን አቅንታ በተወለደች በ50 ዓመቷ ብዙ ቃል ኪዳንን ተቀብላ በ1630ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ዐርፋ በዚሁ ገዳም በክብር አርፋለች፤ በበዓለ ዕረፈቷም የብርሃን ምሰሶ ከምድር እስከ ሰማይ ተተክሎ ታይቷል፡፡ ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ ሰማዕትም ጻድቅም ናት፡፡ /ምንጭ ገድለ ወለተ ጴጥሮስ፣ የዲ.ን ዮርዳኖስ መጽሐፈ ገጽ/ (ጽሑፎቹን ከቃል ትምህርት፣ ከመጻሕፍትና ከመጽሐፈ ገጽ አውጣትቶ ለጻፈልን ወንድማችን የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ የዳግማዊ ዮሐንስ አፈወርቅ (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ)ና የቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ረድኤት በረከታቸው ይደርበት፡፡) እኛንም አንባቢዎቹን በረከታቸው ትድረሰን፡፡ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ HYPERLINK "https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/" የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔዓለምና ደ/ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት፡፡ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ HYPERLINK "https://t.me/medihanaelem" https://t.me/medihanaelem

ለ 2ት ዓለም ሰዎች ትምህርት የሚሆኑ፤ ታሪካቸው እጅጉን ከመሚሰጠውና በስንክሳር ላይ ከተጻፉት መካከል አንዱ ዛሬ ኅዳር 16 በዓለ ዕረፍታቸው የሆነው የመነኰስ #አባ_ዳንኤል_ገዳማዊና_ጻድቁ_ንጉሥ_አኖሬዎስ_ናቸው፡፡ ፠ #አባ_ዳንኤል_፤ የተባለው ጻድቅ፣ ታላቅ ገድለኛ ሲኾን እንጀራን ዓሣንም ቢሆን ማርንም ዘይትንም ቢሆን ከብቻው ቅጠል በቀር ሳይቀምስ አርባ ዓመት ተኩል በአስቄጥስ ገዳም ኖረ፡፡ ከብዙ ዘመንም በኋላ መነኰሳትን የሚፈትን የመመካት ጾር መጣበት። ይህ ፈተና አንድ ጊዜ ታላቁን ቅዱስ አባ መቃርስን በፈተነው ጊዜ ሰውን የሚወድ ቸሩ አምላካችን አባ መቃርስን ወደ ከተማ እንዲኼድና የወንድማማች ሚስቶችን ኹነው ልጆቻቸውን እያሳደጉ በከተማ ከሚኖሩት ኹለት ገድለኛ እናቶች እንዲማርና ጾሩ እንዲጠፋለት አድርጓል። አሁንም ይህ ታላቅ ቅዱስ አባ ዳንኤል የመጣበትን ጾር ቢመለከት መልአከ እግዚአብሔር ተገለጠና ወንድሜ፣ ቸሩ አምላካችን ክርስቶስ እንዲህ ያለውን የመመካት ከትሕትናና ከፍቅር በቀር አይወድምና ተው አለው። አባ ዳንኤልም ጌታዬ ይህን እንድተውና ጦሩም እንዲጠፋልኝ ከኔ የሚበልጥ ጻድቅ አሳየኝ አለው፡፡ መልአኩም በሮሜ የነገሠ ንጉሥ ኹኖ ሳለ ነገር ግን በገድሉ ጽኑዕ ታጋይ ተጋዳይ መነኰስ የሆነውን #የጻድቁን_አኖሬዎስን_ ነገር ነገረው። አባ ዳንኤልም ይህን ሲሰማ በምድር ላይ ተደፋና በራሱ ላይ አመድ ነስንሶ አለቀሰ፤ በኋላም ይህን ገድለኛ ንጉሥ ሊያየው ወደደና ጸለየ። ብርህት ደመናም መጣችለትና ተጭኖ ወደ ሮሜው ንጉሥ ዘንድ ኼደ። እንደደረሰም አገልጋዩን ጠርቶ እባክህ ወንድሜ ንጉሡን ማግኘት እሻለሁና የሚያገናኘኝን መኰንን አገናኘኝ አለው። እርሱም እኔ ባስገባህስ አትገባምን? አለው። እግዚአብሔር ይባርክህ ልጄ አስገባኝ አለው። አባቴ ሆይ ግን ምድራዊ የሆነ ሟች ፈራሽ ንጉሥን ስለምን ማየትን ወደድህ አለው፣ እርሱም ቸሩ ጌታዬ ስላዘዘኝ እንጂ ነው አለው። በኋላም ቆየን ለጌታዬ የሚሻውን ገዝቼ ልምጣ ብሎ ወጣና ጥቂት ጨው አምባሻና እና መጻጻ ገዝቶ መጣ። ይህንም ይዞ አብማሻ ጨው መጻጻና የጎመን ቅጠልም ገዝቶ ወደ ጌታው ወደ ንጉሡ እና ወደ ንጉሡ መምህር አባ አውሎጊስ ዘንድ ገባ፣ አባ ዳንኤልንም በውጭ ተወው። ንጉሡም ረዳቱን አንተ አላዋቂ ነህን? ስለምን አባ ዳንኤልን በአፍአ ተውኸው አለውና ከመምህሩ ከአውሎጊስ ጋራ ወጣ። ለአባ ዳንኤልም ሰገዱለት። ሰላምታም ተሰጣጥተው ወደ ቤተ መንግሥት አስገቡትና በአንድነት ተቀመጡ። ዘጠኝ ሰዓትም በሆነ ጊዜ ለማዕድ ሲሰየሙ አባ ዳንኤል እንዳይታመም ፈርቶ ጌቶቼ እንጀራን ባለመብላቴ በእኔ ላይ አታጒረምርሙ፣ እንዳልታመም ፈርቼ ነው አላቸው። ጸሎትንም ጸለዩ፣ ከዚህም በኋላ ንጉሥ አኖሬዎስ አባ ዳንኤልን ስለአመጣጡ መረመረው፣ አባ ዳንኤልም የሚቻልህስ ከሆነ ከንጉሡ ዘንድ አስገባኝ፣ በጌታ ክርስቶስ ትእዛዝ መጥቻለህይና አለው፣ ነገ አስገባሃለሁ አለው። በማግስቱም አኖሬዎስ ዐይን የሚበዘብዝ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፣ አባ ዳንኤልንም አስገቡት በአየውም ጊዜ ፈርቶ ተንቀጠቀጠ፣ ረዳቱም መፍራቱን አይቶ ወደ ማደሪያው መለሰው። ንጉሡም ችሎቱን ሲጨርስ ልብሰ መንግሥቱን ጨርሶ ልብሰ ምንኲስናውን ለብሶ ወደ አባ ዳንኤል መጣ፣ እርሱም ወንድሜ ሆይ በልቤ ያለውን ነግሬው ወደ ቦታዬ እመለስ ዘንድ ወደ ንጉሡ ለምን አላስገባኸኝም አለው። አኖሬዎስም አባቴ ሆይ አልገ አልገባህምን? ለዚህች ምድር ንጉሥ ብለው የሰየሙኝ እኔ ነኝ አለው፣ አባ ዳንኤልን በሰማ ጊዜ ከእግሩ በታች ሰገደለትና አኗኗሩን ሁሉ ይነግረ ዘንድ በጌታችን ስም አማጸነው። አኖሬዎስም በጅግ ሥራው ፈክሞ ከሚያገኘው በቀር (ይህም ሰሌን መታታት ነው) ሳይበላ ሳይለብስ አርባ ዓመታት እንደሆነው፣ የሚተርፈውንም ለድኆች እንደሚሸጥ ምግቡም እንጀራና ጨው ቅጠል መጻጻም እንደሆነ፣ የማንንም ገንዘብ ለመቀማት እንዳልደፈረ ድንግልናውንም መጠበቁን ነገረው። አባ ዳንኤልም ከእግሩ በታች ሰገደለትና አባቴ በአንተ ላይ ስለተመካሁ ይቅር በለኝ አለው። ከዚህም በኋላ አባ ዳንኤል ፈጽሞ እያዘነ ወደ ቦታው ተመለሰ። ከኹለት ወራትም በኋላ ጻድቁ ንጉሥ አኖሬዎስ ከመምህሩ ተማክሮ መንግስቱን ጥሎ ወደ አባ ዳንኤል ኼደ። መልአከ እግዚአብሔርም ተሸክሚ አደረሰው። እነርሱም በአንድነት ሲጋደሉ በፍቅር ኑረው በዚህች ቅድስት እለት በአንድነት አረፉ። እንዲሁም መምህሩ አውሎጊስና ረዳቱ በዚያች ዕለት በአንድነት አረፉ። አባ ጽጌ ድንግልም በማኅሌተ ጽጌ እንዲህ ሲል አውስቷቸዋል፡፡ እንበይነ አውሎጊስ ለዳንኤል አመ አርአዮ ስቅለተ፤ ከመ እገሪሁ ሰዓምኪ ወሰአልኪዮ ምሕረተ፡፡ ለተአምረ ሣህል ወልድኪ በእንተ ፍቅረ ሰብእ ዘሞተ፤ እንዘ ታዘክሪዮ ድንግል ይምሐረኒ ሊተ፤ ከናፍሪሁ ጽጌ አንኂ ስዕመተ፡፡

የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን #ፍኖተ_ሕይወት_የንዋያተ_ቅድሳት_መሸጫ_ ፠ ቅዱሳት መጻሕፍት ፠ ዕጣን፣ ጧፍ፣ ሻማ፣ ዘቢብ፣ ….. ፠ ንዋያተ ቅድሳት (ጥላ፣ መጎናጸፊያ፣ መስቀል፣
የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን #ፍኖተ_ሕይወት_የንዋያተ_ቅድሳት_መሸጫ_ ፠ ቅዱሳት መጻሕፍት ፠ ዕጣን፣ ጧፍ፣ ሻማ፣ ዘቢብ፣ ….. ፠ ንዋያተ ቅድሳት (ጥላ፣ መጎናጸፊያ፣ መስቀል፣ …….) ፠፠ እንዲሁም ሌሎችንም በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ፡፡ አድራሻ፤ ከቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ቤ/ክ በዋናው በር አጠገብ፡፡

፠##፠ ሰላም ለከ #ሚናስ_ኅሩይ፥ ዘታዕካ ሰማይ፥ ዘኀረየከ አዶናይ፨ (አዶናይ አምላክ በሰማይ አዳራሽ የመረጠህ ሚናስ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን) በገባሬ ተዓምርነቱ የሚታወቀው ወጣቱ ሰማዕት ቅዱስ ሚና
+1
፠##፠ ሰላም ለከ #ሚናስ_ኅሩይ፥ ዘታዕካ ሰማይ፥ ዘኀረየከ አዶናይ፨ (አዶናይ አምላክ በሰማይ አዳራሽ የመረጠህ ሚናስ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን) በገባሬ ተዓምርነቱ የሚታወቀው ወጣቱ ሰማዕት ቅዱስ ሚናስ ዛሬ ኅዳር 15 በዓለ ዕረፍቱ ነው፨ **በኢትዮጵያ በአተር ቆሎ ብዙ ገቢረ ተዓምራት የሚያደርገው ገዳሞቹ ደቡብ ጎንደር ከባሕር ዳር ከተማ አጠገብ (ከአቡነ ሐራ ድንግል አቅራቢያ) እንዲሁም በደቡብ ሸዋ ጢያ ላይ ይገኛሉ፨ **በአ.አ. መርካቶ ራጉኤል ጋር ማኅበሩን የሚጠጡ አሉ፤ በሕመም የምትሰቃዩ ማኅበሩን ፈልጋችሁ የአተር ዝክሩን ቅመሱ፥ በእርግጠኝነት ትፈወሳላችሁ፨ **በግብፅ ግን በጣም ታዋቂ ሰማዕት ነው፨ ፠##፠ እንዲሁም፤ ዛሬ የቅዱስ ቂርቆስም በዓለ ልደቱ ነው፨ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔዓለምና ደ/ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት፡፡ https://t.me/medihanaelem

ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኃ ሰማይ፤ ከመ መዐዛ ሠናይ ሊቀ መላእክት፡፡ (ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል እንደ መልካም መዓዛ ጸሎታችንን በሰማይ ተቀበል፡፡)
ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኃ ሰማይ፤ ከመ መዐዛ ሠናይ ሊቀ መላእክት፡፡ (ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል እንደ መልካም መዓዛ ጸሎታችንን በሰማይ ተቀበል፡፡)

#ጸሎተ_ምሕላ_ከኅዳር_15 - 17፡፡ ፠፠፠ በአጠቃላይ ስለ ሃገራችን ሰላም በመላው ዓለም የምንገኝ ምዕመናን ከሰኞ እስከ ረቡዕ (ከኅዳር 15 - 17/2012 ዓ.ም.) ማለዳ ከጸሎተ ኪዳን ጋር ጸሎተ ምሕላ እንድናደርግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

፠፠፠ ለቡ (ልዩ ማስታወሻ!!!) (N.B.) ፠ በዘመነ ዮሐንስም ሆነ በሌሎቹ 3ት ዘመናት፤ ማለትም (#ሁልጊዜም_በየዓመቱ_የገና_ጾም_የሚገባው_ኅዳር_15_ነው)፤ ፠ አንዳንድ ዓይናማ የጕባኤ መምህራን በዘመነ ዮሐንስ ኅዳር 14 ነው ጾሙ የሚገባው ይላሉ፤ ነገር ግን ቅዱስ ሲኖዶስ ከዚህ በፊት በጥቅምት 17/1980 ዓ.ም. በ4ቱም ዘመናት (ዘመነ ዮሐንስን ጨምሮ) የጾሙ መግቢያ ኅዳር 15 እንዲሆን ስለደነገገ፤ እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ደግሞ የጾምን ሥርዐት ፥ ሰዐት፥ መግቢያና መውጫ ውሳኔ የሚያስተላልፍ ቅዱስ ሲኖዶስ ስለሆነ ጾሙ የሚገባው ኅዳር 15 ፤ ቅበላው ኅዳር 14 ነው፡፡

#ጾመ_ነቢያት_ (#የገና_ጾም_) የ2012 ዓ.ም. የገና (የነቢያት) ጾም፤ ፠#ቅበላው_እሑድ_ኅዳር_14_ድረስ_ብቻ_ነው_፤ ፠ #ጾሙ_ሰኞ_ኅዳር_15_ይጀምራል_!! ላልሰሙት Share/like በማድረግ ይተተባበሩ፡፡ ፠ ከ7ቱ አጽዋማት (ዐቢይ ጾም፣ ጾመ ፍልሠታ፣ ጾመ ሐዋርያት፣ ጾመ ነቢያት፣ ጾመ ድኅነት፣ ጾመ ነነዌ ና ጾመ ገሃድ) መካከል አንዱ ነው፡፡ ፠ ኅዳር 15 ቀን ተጀምሮ እስከ ልደት ለአርባ ሦስት ቀናት የሚጾም ጾም ነው፡፡ ፠ ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል፤ በዚህም ምክንያት የሚከተሉት ስያሜዎች አሉት፡፡ እነርሱም፤ † ፩. #ጾመ_አዳም_፤ አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከገት ከተባረረ በኋላ; በፈጸመው በደል አዝኖ ፥ ተክዞ፤ አለቀሰ (እንባ ቢያልቅበት እዥ እስከሚያፈስ፤ እዥ ቢያልቅበት ደም በዓይኑ እስከሚፈስና ዓይኑ ይቡስ ወይም ደረቅ እስከሚሆን ድረስ አለቀሰ) ፥ ጾመ፣ ጸለየ፡፡ ከልብ የሆነ ጸጸቱን፣ ዕንባውን፣ በራሱ መፍረዱንም እግዚአብሔር አይቶ ተስፋ ድኅነት ሰጠው፡፡ ‹‹ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ፣ በደጅህ ድኼ፣ በዕፀ መስቀል ተሰቅዬ፣ ሞቼ አድንሃለሁ፡፡›› የሚል ነው፡፡ /ገላ. ፬፥፬፣ መጽ.ቀሌምንጦስ/ ስለዚህ ጾሙ የተሰጠው ተስፋ ፥ የተቆጠረው ሱባኤ ስለተፈጸመበት ‹‹ጾመ አዳም›› ይባላል፡፡ † ፪. #ጾመ_ነቢያት_፤ ነቢያትም የምሥጢረ ሥጋዌ ነገር ተገለጦ ስለታያቸው፣ ክርስቶስ ለሰው ልጅ የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ በትንቢት ተመልክተው ጾመውታልና ጾመ ነቢያት ይባላል፡፡ ይህ ጾም ከአባታችን አዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ የተነሱ አበውና እናቶች: ድኅነትንና ረድኤትን ሲሹ የጾሙት ጾም ነው:: በተለይ አባታችን አዳም: ቅዱስ ሙሴ: ቅዱስ ኤልያስ፣ ቅዱስ ዳንኤል ና ቅዱስ ዳዊት በጾማቸው የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው:: (ዘዳ 9:19, ነገ. 19:8, ዳን. 9:3፣ መዝ. 68:10, 108:24) ቅዱሳን ነቢያት በጭንቅ በመከራ ሆነው የጾሙት ጾም ወደ መንበረ ጸባኦት ደርሶ: ወልድን ከዙፋኑ ስቦታል:: ለሞትም አብቅቶታል:: † ፫. #ጾመ_ሐዋርያት_፤ ሐዋርያት ‹‹ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብራለን፣ ልደትን ምን ሥራ ሠርተን እናከብረዋለን?›› ብለው ከልደተ ክርስቶስ በፊት ያሉትን ፵፫ ዕለታት ጾመዋልና፡፡ † ፬. #ጾመ_ማርያም_፤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ቅድስናዋን አይቶ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ አምላክን ያለ ሰስሎተ ድንግልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ ጸንሳ እንደምትወልደው ቢነግራትም የትሕትና እናት ናትና ‹‹ምን ሠርቼ የሰማይና ምድርን ፈጣሪ እችለዋለሁ?›› ብላ ጌታን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማለችና ‹‹ጾመ ማርያም›› ይባላል፡፡ † ፭. #ጾመ_ፊልጶስ_፤ ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ እያስተማረ ሳለ በሰማዕትነት ሲሞት፤ አስክሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ፤ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስክሬን እንዲገለጽላቸው ከኅዳር ፲፮ ጀምረው ጾመው በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስክሬን ተመልሶላቸዋል፤ ነገር ግን አስከሬኑ ቢመለስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል፡፡ † ፮. #ጾመ_ስብከት_፤ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት፥ የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበት፥ የምስራች የተነገረበት ስለሆነ ጾመ ስብከትም ይባላል፡፡ † ፯. #ጾመ_ልደት_፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት ስለሆነ ‹‹ጾመ ልደት›› ይባላል፡፡ ጾምን ትእዛዝ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን የፍቅርና የበረከት ምንጭ በመሆኑ ጭምር ደስ እያለን ብንጾመው የቅዱሳኑ በረከት ያድርብናል፡፡ ከቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት በአጭሩ የተዘጋጀ፡፡ https://t.me/medihanaelem የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔዓለምና ደ/ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት፡፡

ኅዳር ፲፫፤ እንኳን ለቅዱስ እግዚአብሔር አብና ለእልፍ አእላፋት፥ ትዕልፊት አእላፋት (ለቅዱሳን መላእክት በዓለ ሢመት)፤ በሰላምና በጤና አደረሰን፤ አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡ (ከእልፍ አእላፋት አለቃ
+8
ኅዳር ፲፫፤ እንኳን ለቅዱስ እግዚአብሔር አብና ለእልፍ አእላፋት፥ ትዕልፊት አእላፋት (ለቅዱሳን መላእክት በዓለ ሢመት)፤ በሰላምና በጤና አደረሰን፤ አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡ (ከእልፍ አእላፋት አለቃዎች ስሞች በጥቂቱ)፡፡ ጸሎትነ ትብጻሕ (ሰላም ለክሙ) ለመላእክተ ምሕረት፤ ፨ ሚካኤል ወገብርኤል፥ ፨ ሱራፌል ወኪሩቤል/፬ቱ እንስሳ/፥ ፨ ዑር(ራ)ኤል ወሩፋኤል /፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ/፥ ፨ ሱርያል ወፋኑኤል፥ ፨ አፍኒን ወራጕኤል፥ ፨ ሳቁኤል ወአቅናኤል፥ ፨ ብርናኤል ወሱባኤል፥ ፨ ፍናኤል ወሰላታኤል፥ ፨ ሰዳካኤል ወኤልናኤል፥ ፨ አናንኤል ወኢየሩማኤል፥ ፨ ግርማኤል ወድርማኤል ፥ ፨ ድማህኤል ወአድማኤል፥ ፨ ሙራኤል /ምናቴር አብያቴር/፥ ፨ ሱታ(ስቱ)ኤል ወሱርያል፤ ……. ፎቶዎቹ፤ ክብረ በዓሉ ከሚከበርባቸው ቦታዎች ጥቂቶቹ፤ …. 1. ግሸን ደብረ ከርቤ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ (መስቀሉ የሚገኝበት)፤ 2. ጠዳ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ (ጎንደር፤ ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ)፤ 3. ጎርዶማ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን (በሰሜን ሸዋ)፤ 4. ደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ (አዲስ አበባ)፤ 5. ቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤ.ክ (አዲስ አበባ) 6. ቦሌ ቡኒ ደብረ ቤቴል ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤ.ክ (አዲስ አበባ) /የቀ.ደ.ሰ መድኀኔ ዓለም ወደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

#የሕይወት_ፈተና_ምንጮች_ክፍል_፫፡፡ Shareee, Like … እንዳያመልጥዎ በጕባኤው ላይ ይገኙ፡፡ ለምን እንፈተናለን፤ ፈተናዎች ለምንና እንዴት ይመጣሉ፤ ፈተናዎችን እንዴት አድርገን ድል እናድርጋ
+1
#የሕይወት_ፈተና_ምንጮች_ክፍል_፫፡፡ Shareee, Like … እንዳያመልጥዎ በጕባኤው ላይ ይገኙ፡፡ ለምን እንፈተናለን፤ ፈተናዎች ለምንና እንዴት ይመጣሉ፤ ፈተናዎችን እንዴት አድርገን ድል እናድርጋቸው፤ …. ……እንዳያመልጣችሁ፤ በሌሎችም ርዕሶች ዙሪያ በብዙ ጕባኤያት ላይ ያልተዳሰሱ ርዕሶች የሚዳሰሱበት ጕባኤ ስለሆነ እንዳያመልጣችሁ፤ #ደግመን_እንላለን_ይህ_ትምህርት_በፍጹም_እንዳያመልጣችሁ!!!!! ለ፬ ተከታታይ ሳምንታት፤ ትምህርቱ ተከታታይነት ስላለው መቅረትና ማርፈድ አይመከርም!!፡፡ (፻፶፪ኛ ሳምንት የዐርብ ጕባኤ) ዐርብ ኅዳር ፲፪ ጀምሮ ከ፲፪-፪ ሰዓት አሁንም በድጋሚ እንላለን ለሕይወታችን ወሳኝና በብዙ የትምህርት ጕባኤያት ላይ የማይዳሰሱ ትምህርቶች ስለሆኑ እንዳያመልጣችሁ!!!! የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት፡፡

በመዲና ከተማችን የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል የሚከብርባቸው ገዳማትና አድባራትን እንጠቁማችሁ፡፡ /ፎቷቸውን ያልለጠፍናቸውና ስማቸውን ያልጠቀስናቸውን እንድትልኩልን በሊቀ መልአኩ ስም እንጠይቃለን) 1) *የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን (ሾላ፤ መገናኛ) 2) *አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል /ጭቁኑ/፤ ፈረንሳይ 3) *ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል (አዲሱ ሚካኤል)፤ አውቶብስ ተራ 4) *ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል፤ /ቦሌ/ 5) *ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል፤ /ላፍቶ/ 6) *ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል፤ (መካኒሣ) 7) *ኮተቤ ደብረ ጽባሕ ቅዱስ ሚካኤል /ሳጠራው/ (ቀድሞ ኮተቤ አሁን ሲምሲ) 8) *ደብረ ምሕረት ሚካኤል (ቀድሞ ወህኒ ቤት ሚካኤል) 9) *መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል 10) *ገነተ አምባ ቅዱስ ሚካኤል 11) *ደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል 12) *ካራ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤልና 24ቱ ካህናተ ሰማይ 13) *ሐያት ጨፌ ኢያሪኮ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን (በ1980ዓ.ም ጽላቱ ከነ ድርሳናቱ ተቀብሮ የተገኘበት) 14) *መንበረ ክብር ቅዱስ ሚካኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም /ኋላ ወቅድስት አርሴማ በሚል እየተጠራ የሚገኝ/፤ (በቀጨኔ በአዲሱ ገበያና በእንጦጦ መሃል ጉብታ ላይ የሚገኝ) እንዲሁም በድርብነት 15) *እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት 16) *መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ (ስድስትኪሎ) 17) *ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ (መስቀል አደባባይ) 18) *ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ቤ.ክ (ኋላ ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል በሚል እየተጠራ የሚገኘው)፤ (ኢምግሬሽን አጠገብ) 19) *ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ (ኋላ ወመካነ ጎልጎታ ቅድስት ድንግል ማርያም በሚል እየተጠራ የሚገኝ)

እንኳን ለቅድስት ሐና በዓለ ዕረፍት አደረሳችሁ፡፡ ፎቶዎቹ፤ በአ.አ. የሚገኙ የቅድስት ሐና አብያ ክርስቲያናት ፠ ጽርሐ ንግሥት ቅድስት ሐና ቤ/ክ ፠ ኮተቤ መካነ ቀረዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤ/ክ እንዲ
+4
እንኳን ለቅድስት ሐና በዓለ ዕረፍት አደረሳችሁ፡፡ ፎቶዎቹ፤ በአ.አ. የሚገኙ የቅድስት ሐና አብያ ክርስቲያናት ፠ ጽርሐ ንግሥት ቅድስት ሐና ቤ/ክ ፠ ኮተቤ መካነ ቀረዱሳን ኢያቄም ወሐና ቤ/ክ እንዲሁም፡ ፠ ደብረ ንግስት መንዝ ቅድስት ሐና::

ኅዳር ፲፪፤ ቅዱስ ሚካኤል በእልፍ አእላፍ መላእክት ላይ የተሾመበትና እስራኤልን የመራበት ክብረ በዓል ነው፡፡ #በዓለ_ሢመቱ_፥#ወበዓለ_መራኄ_ፍኖቱ_ለቅዱስ_ሚካኤል_ሊቀ_መላእክት_፨ ኅዳር ፲፪ ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ፥ በእግዚአብሔር የጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ ለምስጋና የሚቆም፥ ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ፥ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሢመቱና እስራኤላውያንን በባሕረ ኤርትራ ያሸገረበት በዓል ነው፡፡ (እንኳን አደረሳችሁ) ፠ #፩ በዓለ ሢመቱ፤ ሚካኤል ማለት ማን እንደ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ከሌሎች መላእክት ጋር በእለተ እሑድ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የተፈጠረ ሲሆን፤ እርሱም መጀመሪያ ከ100ው ነገደ መላእክት የ10ሩ ነገደ መላእክት (የኃይላት) አለቃቸው ነበር፤ በተጨማሪም ከሳጥናኤል ውድቀት በኋላ የኃይላት አለቅነቱን እንደያዘ የአጋእዝትን ነገድም (ሳጥናኤል/ሰማልያል/) ይመራቸው የነበሩትን 10 ነገዶችም በአለቅነት ደርቦ አለቃ ኾኗል፤ እንዲሁም በዛሬው ዕለት ለ100ውም(99ኙም) ነገደ መላእክት (ለእልፍ አእላፋት መላእክት) አለቃቸውም ቅዱስ ሚካኤል ኾኖ የተሾመበት ዕለት ነው፡፡ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር ያሰኘውም ይኸው ነው፡፡ ቅ/ሚካኤል ለሰው ልጆች ምሕረትን ከኅዳር 12 (ከበዓለ ሢመቱ) ጀምሮ እስከ ኅዳር 13 (የአእላፍ መላእክት) በዓል ድረስ ከአምላኩ ለፍጥረታት ሁሉ ምሕረትን የሚለምንበት ዕለታት ናቸው፡፡ ፠#፪ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት እየመራቸው ማውጣቱን የሚዘከርበት በዓል ነው፡፡ ይህም የሆነው ያዕቆብ በረሃብ 70 ኹኖ ወደ ግብፅ ከወረደ በኋላ ከ215 ዓመታት (አብርሃም ወደ ግብፅ በተሰደደ ከ430 ዓመታት) በኋላ፤ የዮሴፍን ዝና ያልሰማ፥ ዮሴፍን የማያውቅ ፈርዖን በግብፅ ነገሠ፡፡ እስራኤል ከእኛ ይልቅ በዝተዋል ጠላቶቻችን ቢነሱብን ከጣለቶቻችን ጋር ተደርበው ያጠፉናል በማለት አገዛዝ አጸናባቸው፥ ፍርድ አጓደለባቸው፡፡ የእስራኤል ሴቶች ልጅ ሲወልዱ ወንድ ከሆነ እንዲገደል በማድረግ መከራ አጸናባቸው፡፡ ለ215 ዓመታት በግብፅ በባርነት ከቆዩ በኋላ ከዕብራውያን ወገን የሆነችው ራሔል ጭቃ እያቦካች ምጥ በያዛት ጊዜ ከሥራዋ እንዲያሳርፏት ጠየቀች፤ ግብጻውያን ግን የሕፃናቱ ደም ጡቡን ያጠነክራል ርገጭ አሏት፡፡ ከማሕፀኗ የወጡ ሁለት መንትያ ልጆቿን እያየች ከጭቃ ጋር ረገጠች፤ ራሔልም መሪር ልቅሶን አለቀሰች፤ ስለ ልጆቿም መጽናናትን እንቢ አለች፡፡ የእስራኤል ንጉሥ ሆይ የሆነብንን እይ ስትል ራሷን ይዛ ታለቅስ ጀመር ፥ እንባዋንም ወደ ሰማይ ንጉሥ ወደ እግዚአብሔር ረጨች፡፡ የራሔል እንባዋ የሕዝበ እስራኤልን ሁሉ ጩኸት ፥ እሮሮ ይዛ ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰች፡፡ “. . . ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች የሉምና ስለ ልጆቿ መጽናናት እንቢ አለች” /ኤር 31፥5፤ ማቴ 2፥17/ እንዲል፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን አስነሳና፤ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መሪነት፤ 10 ተዓምራትን በምድረ ግብፅ በ11ኛ ተዓምር ደግሞ በኅዳር 12 (ፈርዖንን ከነሠራዊቱ በኤርትራ ባሕር አስጥሞ) ወደ ተስፋይቱ ምድረ መራቸው፡፡ ባሕረ ኤርትራን እስራኤላውያን እንደተሻገሩም የእስራኤል ልጆች የሙሴ የአሮን እኅት ማርያም ከበሮ እየመታች ‹‹ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ ፤ እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው እያሉ፡፡›› ጠላታቸውን የመታላቸውን ፥ እነሱንም በተአምራቱ ያሻገራቸውን ፥ ከጠላታቸው እጅ ያዳናቸውን እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ ከዚህ በኋላ መጋቤ ብሉይ ቅዱስ ሚካኤል እየመራቸው ፥ መና ከሰማይ እያወረደላቸው ፥ ውሃ ከጭንጫ እያፈለቀላቸው ፥ ቀኑን በደመና ፥ ሌቱን በብርሃን መርቷቸው አርባ ዘመን ተጕዘው የቃል ኪዳን አገራቸው ምድረ ርስት ከነዓንን (የዛሬዋ ኢየሩሳሌምን) ወርሰዋል፡፡ /ዘጸ. 15/ ከሙሴ በኋላ እስራኤልን የመራው ነቢዩ ኢያሱም እስራኤልን በሚመራበት ጊዜ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እስራኤልን ይረዳቸው ነበር፡፡ ከጠላቶቻቸው ጋር ሲዋጉም ሰልፉን ይመራ የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ለምሳሌ እስራኤላውያን ከኢያሪኮ አጠገብ በነበሩበት ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ኢያሱን አነጋግሮታል፡፡ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ቀና ብሎ ሲመለከት የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ አንድ ሰው ከፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም “አይደለሁም ነገር ግን የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ በመሆኔ መጥቻለሁ” ብሎታል /ኢያሱ 5፥13-15/፡፡ ይህ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ከኢያሱ ፊት ለፊት የቆመው መልአክ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል (እንዲሁም መልአኩ ቅዱስ ራጕኤል) ነው፡፡ ይህን ለአብነት አነሣን እጅ እስራኤል በሚበድሉበት ጊዜ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር የሚማልድላቸው ይህ ታላቅ መልአክ መጋቤ ብሉይ ቅ/ሚካኤል ነበር፤ እግዚአብሔር አምላክ በእደ መልአኩ ይጠብቀን፤ ከበዓሉ ረድኤት ፥ በረከት ይክፈለን፤ አሜን፨ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔዓለምና ደ/ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት፡፡ https://t.me/medihanaelem