ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

تُعد قناة Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 16 129 مشتركاً، محتلاً المرتبة 5 230 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 226 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 16 129 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 31 أكتوبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 520، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 7، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 22.41‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 10.30‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 3 597 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 653 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 28.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 01 نوفمبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

16 129
المشتركون
+724 ساعات
+197 أيام
+52030 أيام
أرشيف المشاركات
#ታኅሣሥ_29_ልደታቸው_ከጌታችን_ልደት_ጋር_የተባበረላቸው_ቅዱሳን፤ #አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ፤ #ቅዱስ ላሊበላ፤ #ቅዱስ ነዓኵቶ ለአብ፤ #አቡነ አብሳዲ ዘደብረ መጕና #ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ፤ #ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃ፤ #አቡነ አካለ ክርስቶስ፤ #አቡነ መዝራእተ ክርስቶስ፤ #መስፍኑ ኢያሱ፤ #የገርአልታው አቡነ ዳንኤል፤ #ዳግማዊ ቂርቆስ ዘቡልጋና ሌሎችም ቅዱሳን አሉ፤ ነገር ግን ከቅዱሳን በዓል በላይ የጌታ በዓል መከበር ስለሚገባው የቅዱሳኑ ዋና በዓላቸው በሌላ ቀናት /በዕረፍታቸው…../ ቀን ይታሳባል፡፡ #የጌታችን_ልደት_በዋናነት_የሚከበርባቸው_ዐበይት_መካናት፤ #በኢየሩሳሌም_ቤተ_ልሔም፤ ጌታችን በተወለደባት #በማኅበረ_ሥላሴ_ገዳም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ጌታ በተወለደባት ዕለት የጌታችን መወለድ የተበሠረባት /ቋራና መተማ/ #ሰረባር_በዓለ_እግዚአብሔር፤ ቅዱስ ላሊበላ ከሕፃዎቹ ሁሉ መጀመሪያ ያነጸው ውቀር ቤ.ክ. /ስሜን፤ ደረስጌ አጠገብ/ #ደብረ_ሮሐ_ላስታ_ላሊበላ #ርዕሰ_አድባራት_አደባባይ_ኢየሱስ ቤ.ክ. /እጅግ ጥንታዊ ታሪክ ያለው ጽላቱ ከደበቡ ኢትዮጵያ የሄደና ኋላ ቊጥሩ ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ የሆነ፤ ጎንደር ከተማ/ #ደብረ_ስብሐት_ቀሃ_ኢየሱስ /ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱ፤ ጎንደር ከተማ/ #አዲስ_አበባ_መካነ_ሥላሴ_ቅዱስ_በዓለ_ወልድ /በ1883ዓ.ም. የተመሠረተ፤ 4ኪሎ፤ አዲስ አበባ/

#እንኳን_ደስ_አላችሁ፡፡ #ገዳማትና_አድባራት #አዲስ_መርሐ_ግብር፤ #እንደ_መድኀኔ_ዓለም_ፈቃድ_ከጥር_10_ጀምሮ_ይጠብቁን፤ #በየወሩ_በ10_በመስቀለ_ኢየሱስና_በ27_በመድኀኔ_ዓለም_ቀን_የሚቀርብ #አንዱ ከአዲስ አበባ አንዱን ከአ.አ ውጭ ያሉ ገዳማትና አድባራትን የምንዘግብበት አዲስ መርሐ ግብር ይከታተሉ፡፡ #ያሏችሁን መረጃዎች ብትልኩልን የምናቀርበው መርሐ ግብር ያማረ ይኾናል፤ ለዚህም ይረዳን ዘንድ አስቀድመን የምንዘግባቸውን ገዳማትና አድባራት ስም ቀድመን ስናሳውቅ በአጥቢያው ያላችሁን ስለቤተ ክርስቲያኑ የምታውቁ ካላችሁ እንድትጠቁምን እንጠይቃለን፡፡ በዚሁ መሠረት፤ #ጥር_10_መካነ_ሥላሴ_ቅዱስ_በዓለ_ወልድ (የ128ዓመት የእድሜ ባለጸጋና) #መንበረ_ጸባዖት_ቅድስት_ሥላሴ(የ75ት ዓመት ዕድሜ) #ጥር_27_ገዳመ_ደብረ_መጕና፤ በታች አርማጭሆ የሚገኝ የገዳሞች ሁሉ ፈርጥና አቡነ አብሳዲና ልጆቻቸው ቅዱሳን #የካቲት_10_ደብረ_ኤረር_በዓታ_ወልደታ #የካቲት_27_ማኅበረ_ሥላሴ፤ ታላቁ ገዳም፤ በቋራና በመተማ አካባቢ የሚገኝ፤ የገዳማት ራስ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

ልዩ የገና በዓል የዐርብ ጕባኤ፤ #የ፻፲፫ኛ #ሳምንት_ታኅሣሥ_፳፮_፳፻፲፩ዓ.ም_ከ፲፪-፪ ሰዓት በሰዐቱ ይገኙ!!!!! እንዳያመልጥዎ! እንዳያመልጥዎ! ላልሰሙት ያሰሙ፤ <<Like, Share>> በማድረግ ይተባበሩ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል፡፡ ‹‹#የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተ_ክርስቲያን_የስብከተ_ወንጌል_አገልጋዮችና_አገልግሎታቸው፡፡›› አቅራቢ፤ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (MPM, MA)፥ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አወያይ፤ መዝገቡ ካሣ(ቀሲስ ዶ.ር.) ቦታ፤ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ(4ኪሎ) ቀን፤ #ቅዳሜ_ታኅሣሥ_27_2011ዓ.ም. ሰዐት፤ ከ7፡30-11፡00 መርሐ ግበሩን በአካል ለመከታትል የማትችሉ #በፌስ_ቡክ_አድራሻ_ ‹‹#EOTC_Tga›› መከታተል ትችላላችሁ፡፡ /የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር የጥናታዊ ጽሑፍ መድረክ፡፡/

#ሰበር_ዜናናናና ✤#አስግሩ ለነ ቈናጽለ ንኡሳነ፤ እለ ያማስኑ ባሕረ ጥምቀትነ(ዓፀደ ወይንነ)፡፡ #የባሕረ_ጥምቀታችንን_የወይናችንን_ቦታ_የሚያጠፉትን_ጥቃቅኑን_ቀበሮዎች_አጥምዳችኹ_ያዙልን፡፡ #መሓ._፪፥፲፭፡፡ ✤በደቡብ ኢትዮጵያ ጎፋ ዞን (በቀድሞው ጋሙጎፋ ዞን) ጎፋሳውላ ወረዳ /ከወላይታ ሶዶ 135 ኛው ኪ.ሜ /መሎ ለሃ ከተማ/ ከጎፋ ሳውላ 105 ኪ.ሜ/ ላይ የሚገኝ የጥምቀት ታቦት ማደሪያ ቦታ የመንግሥትን ሥልጣን እንደ መመኪያ ባደረጉ የመንግሥት ሰዎች የጥምቀት ቦታው በመወሰዱ፤ ታቦተ ሕጉ ከመንበሩ ተነሥቶ ከአካባቢው ምዕመናን ጋር 85ኪ.ሜ. ላይ ወደምትገኘው የጎፋ ሳውላ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በእግር ጕዞ እያመራ ነው፡፡ ታኅሣሥ 23 የተጀመረው ጕዞ ማምሻውን ባስኬቶ ማርያም ደርሷል፡፡ ✤#በሐኪ_በሐኪ_ቤተ_ክርስቲያን_እምነ፤ #ግበሪ_ጸሎተነ_በእንቲአነ፤ #እምኀይለ_ጸላዒ_ወፀር_ዕቀቢ_ኪያነ፤ #ትንባሌኪ_የሃሉ_ምስሌነ፡፡ ✤#ዓቃቤ ቅዱሳን ሚካኤል ለሳሙኤል ፍና ሕይወቱ፤ ዕቀበነ ከመ ዓቀብኮ በምድረ ዋሊ ጾማዕቱ፤ እምንድፍተ አርዌ እኩይ ዘቀቲል ሥምረቱ፡፡ ✤#እለ ትነብሩ ተንሥኡ…….ስለ ቅድስቲቱ ሃይማኖታችንና ቤተ ክርስቲያናችን ሁላችንም በንቃትና በትጋት እንቁም፤ እንጽና፡፡ ✤#የአባቶቼን ርስት አልሰጥህም፡፡ ፩ኛ.ነገ.፳፥፬፡፡ ✤#በመሎ ለሃ ያለች ጽዮን ቤተ ክርስቲያንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን፤ በመሎ ለሃ ያለሽው ጽዮን ቤ/ክ ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ፡፡ ✤#ጋዳ_ጋዳ_ጋዳ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ ነዓ ከመ ትምርሐ ለቤተ ክርስቲያንከ ቅድስት በሠናይ ፍኖት፨

✤✣✤ #በዓለ_ልደቱ_ለሐዲስ_ሐዋርያ_ፀሐይ_ማር_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት #ታኅሣሥ_24_1196ዓም_በሰሜን_ሸዋ_ቡልጋ_ጽላልሽ_እቲሣ_ተወልደው_በአጠገቡ_በምትገኛወ_ደብረ_አጋዕዚት_ክርስትና_ተነሡ፡፡ #አባታቸው ቅዱስ ጸጋ ዘዓብና እናታቸው ቅድስት እግዚእ ኀረያ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲያስተምሯቸው በአካባቢያቸው ደግሞ በዘመኑ የነበሩ ልጆች ይማሩ የነበረውን ፈረስ መጋለብን፣ ቀስት መወርወርን፣ እርሻንና አደንን አስተምረዋቸዋል፡፡ #በ7ት ዓመታቸው ከግብፃዊው ጳጳስ አቡነ ቄርሎስ ዲቁናን ከተቀበሉ በኋላ እግዚአብሔር በክህነት ሕዝቡን እንዲያገለግሉ መረጣቸው፡፡ ከዮዲት ጉዲት በኋላ ሃገራችን ሰሜኑና ደቡቡ ተቆራርጧል፤ የሐሳብን ልዕልና የሚያመጣው የመንፈስ ልዕልና ተዳክሟል፡፡ ለዚህም ኢትዮጵያን የሚዋጅ ሐዲስ ሐዋርያ ያስፈልግ ነበርና አምላካችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ጠራ፡፡ #አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቅስናን ከአቡነ ቄርሎስ ተቀብለው በጽላልሽ አካባቢ በክህነት ከአባታቸው ጋር አገልግለዋል፡፡ አባታቸው ሲያርፉ በወንጌሉ ማንም ሊከተለኝ የሚወድድ ቢኖር ያለውን ሁሉ ትቶ መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ ያለውን በመከተል ሀብታቸውን ለድኾች መጽውተው በሸዋና በዳሞት በስብከተ ወንጌል አገለገሉ፡፡ ከዚያም፤ #በመጀመርያ ደቡብ ወሎ ቦረና ላይ ገዳማቸውን ደብረ ጎል ገድመው ወደሚገኙት ታላቁና ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን ወደኾኑት ጻድቅ አባት አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ገብተው ዐሥር ሁለት ዓመታት በትምህርትና በሥራ (በአርድእትነት) አሳልፈዋል፡፡ በዚያም ዋሻ ፈልፍለው አስደናቂ ሕንፃ ሠርተው ነበር፡፡ #በ1216 ዓ.ም. አካባቢ ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገሳም ገብተዋል፤ በዚሁ ገዳምም ከመመንኰሳቸው በፊት ሰባት ዓመት ከመነኰሱም በኋላ ሦስት ዓመት በድምሩ ለ10 ዓመታት በትምህርት፣ በእደ ጥበብ ሥራ፣ በአገልግሎትና ሥርዐተ ምንኵስናን እያጠኑ ቆይተዋል፡፡ #ከሐይቅ ወጥተው በዘመኑ በሥርዐተ ምንኵስናና በትምህርት ብሎም በጥበበ እድ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ወደ ነበረው ወደ ደብረ ዳሞ በመሄድ በየገዳሙ አበምኔት ከሆኑት ከአቡነ ዮሐኒ ዘንድ መንፈሳዊ ትምህርት፣ ሥርዐተ ምንኵስናና ጥበበ እድ ሲማሩ ለ12 ዓመታት ቆዩ፡፡ ያነጹት ፍልፍል ድንጋይ ዋሻ፣ መጻሕፍት ሲጽፉ ቀለማቸውን ያስቀምጡባቸው የነበሩትን ሽንቁሮች ዛሬም በደብረ ዳሞ ማየት ይቻላል፡፡ #በደብረ ዳሞ የነበራቸውን ቆይታ ጨርሰው በገመድ ሲወርዱ ሰይጣን በቅንዐት መጥቶ ገመዱን በጠሰባቸው እግዚአብሔር አምላክ በዚህ ወቅት የሚበሩበትን እንደ መላእክት ክንፍ ሰጣቸው፡፡ #ለአምስት ዓመታት #አኵስምን_ዋልድባን እንዲሁም ሎሎች የትግራይ ገዳማትን እየተዘዋወሩ ሲመለከቱ ቆዩ #ከሸዋ በወጡ በሃያ ሁለት ዓመት (እድሜያቸው ሃምሳ ሁለት ሲሆን) ለበለጠው ክብር እና ርእይ በግብጽ በኩል ወደ ኢየሩሳሌም ተሻገሩ፡፡ #ከኢየሩሳሌም ሲመለሱ በሐይቅ በኩል አድርገው ደብረ ጎልን ተሳልመው በሚዳ እና በመርሐ ቤቴ በኩል ወደ ሸዋ በመምጣት ከዮዲት ዘመን በኋላ በመንፈሳዊ ሕይወት የተጎዳውን ሸዋን እና ደቡብ ኢትዮጵያን በመዘዋወር ለዐሥር ዓመታት ያህል አስተምረዋል፡፡ #አቡነ ተክለ ሃይማኖት ተግተው በማስተማራቸው የተኛው ሁሉ ነቃ፣ የደከመው በረታ፣ የጠፋውም ተገኘ፡፡ ሐዋርያትን ለማፍራት እንዲችሉ አንድ ገዳም ለመመሥረትና ደቀ መዛሙርትን ለማስተማር አሰቡ፡፡ እናም ወደ ደብረ አስቦ ገዳም ገቡ፡፡ ቦታውን አስተካክለው እና ከደብረ ዳሞ እና ከሐይቅ የተከተሏቸውን ጥቂት ደቀ መዛሙርት ይዘው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ልክ እንደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ሁሉ ሦስቱን ነገሮች ያካተተ አገልግሎት ጀመሩ፡፡ ምንኵስና፣ ትምህርትና ሥራ፡፡ መነኰሳቱ መንፈሳዊ ትምህርት ይማራሉ፤ በሕገ ገዳም ይመራሉ፤ ለራሳቸው እና ለአካባቢው ሕዝብ ርዳታ የሚሆን እርሻ ያርሳሉ፡፡ #ደቀ መዛሙርትን አፍርተው፣ ገዳማቸውን አደራጅተው፣ ስብከተ ወንጌልንም አስፋፍተው ካደላደሉ በኋላ በሕይወታቸው የመጨረሻ ዓመታት ወደ ደብረ አስቦ ዋሻ ገብተው በአንድ እግራቸው በጾም እና በጸሎት ተወሰኑ፡፡ #አገልግሎታቸውን ፈጽመው ነሐሴ 24 ቀን 1297 ዓ.ም. በ99 ዓመታቸው ዐረፉ፡፡ ጸሎትና በረከታቸው፤ ረድኤትና ምልጃቸው በመላው ሕዝበ ክርስቲያንና በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ሁሉ አድሮ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ /ከቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለምና ደ.ት ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሰሌዳ መጽሔት የተወሰደ/ ✤✤ #እቲሣ_ገዳም #በቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃና አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የተመሠረተ፤ ሲመሠረትም በታቦተ ኢየሱስና አርባዕቱ እንስሳ ነው፤ #ሊቀ ካህናት አበይድላ ከአኵስም 300 ታቦታትና 300ካህናት ይዞ መጥቶ በጽላልሽ የተቀመጠባት ናት፤ #ፀሐይ አቡነ ተክለሃይማኖት የተወለዱባት (የተወለዱባት ጠፍጣፋ ደንጊያ አሁንም በቦታው አለች)፣ #አባታቸውና ጸጋ ዘአብና እናታቸው እግዚእኀረያ የተወለዱበት፤ ኋላም ክብሩ አጽማቸው ያረፈበት ነው፡፡ #ቅዱስ ያሬድ 3 ዓመት ጸልዮባታል፤ #ቅዱስ ላሊበላ 7 ዓመት ጸልዮባታል፤ #ተሰዓቱ ቅዱሳን 20 ዓመት የጸለዩበት፤ #ሐርቤ በሚባለው ቦታ ላይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ 7 ዓመት ጸልየውበታል፤ #ታቦተ ጽዮን 12 ዓመት (ከ9ሺህ ሕዝብ) ጋር መጥታ ኖራበታለች፤ #በአምሳለ ሲዖል የተሠራ አስደናቂ የጨለማ ዋሻ ያለበት ነው፤ #ብዙ የታሪክ ቅርስ ያለበት ነው፤ #በቅዱስ ሚካኤልና ጸጋ ዘአብ ቤተ ክርቲያን ውስጥ ካየን በኋላ፤ እዚሁ ቦታ በሚገኘው ፈዋሽ ጠበል ተጠምቀንና ጠጥተን ጕዟችንን ወደ #ቦታው_ከአአ_በቅርብ_ርቀት_በደብረ_ብርሃን_መንገድ_አሌልቱ_ከተማ_ላይ_በመታጠፍ_ይገኛል፡፡ ✤✤ #በአዲስ አበባ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ልደት የሚከበርባቸው፤ 1.#በዳግማዊት ደብረ ሊባኖስ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም 2.#በመንበረ ክብር ደብረ ታቦር ቅዱስ ሚካኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም 4.#በጥንታዊው በየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም 5.#በደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ #ሥርዐተ_ማኅሌቱን_እንደየደብራችሁ ይትበሃል እንድትጠቀሙበት በማሰብ ሁሉንም (በላይ ቤትና በታች ቤት) (#ዘአባጃሌ_ተክለ_ሃይማኖትና_ዘአደባባይ_ተክለሃይማኖት) አዘጋጅተነዋል፡፡

3ት ሰንበት ት/ቤቶችን ያጣመረ አዲስ ቴአትር #የደም_ደመወዝ>>፤ #ዛሬ_እሑድ_ታኅሣሥ_21_ቀን_በ9_ሰዐት * ድርሰት፤ ተምሮ ማስተማር ሰ/ት/ቤት * ዝግጅት፤ የቀ.ደ.ሰ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ከኑብያ የቴአትር ጥበባት ጋራ በመተባበር * አስተባባሪ የመንበረ ክብር ደ/ታ ቅዱስ ሚካኤል ወአቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ደብረ ታቦር ሰ/ት/ቤት ...ቦታ በቀ.ደ.ሰ ሰ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት አዳራሽ፨

#ታኅሣሥ_፲፱ #በዓለ_ቅዱስ_ገብርኤል፤ #ወሥርዐተ_ማኅሌት፡፡ #ሊቀ_መላእክት_በመላእክት_ሁሉ_ላይ_የተሾመ_ነው_ሄኖክ_10፥14 #መልአከ_ራማ_ዘራማ_ልዑል_ነው፤ #አብሣሬ_ትስብእት_ነው፤ #መጋቤ_ሐዲስ_ነው፤ #የአርባብ_የ10ሩ_ነገደ_መላእክት_አለቃ_ነው #ከከበሩ_መላእክት_አንዱ_ነው_ሄኖክ_6፥7፤ #በእግዚአብሔር_ፊት_የሚቆም_መልአክ_ነው_ሉቃ_1፥19፤ #ለቅዱሳን_እውቀትን_የሚገልጽላቸውና_ከአላውያን_የሚታደጋቸው_ነው_ድርሳነ_ገብርኤል #መልአከ_ሰላሞሙ_ወመልአከ_ኪዳኖሙ_መልአከ_አድኅኖ_መልአከ_ኀይል_መልአከ_ፍስሐ #ናዛዜ_ኅዙናን_ያዘኑትን_የሚያጽናና_ መልአክ_ነው፨ ✤ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ማለት ነው፤ የወልደ እግዚአብሔርን መወለድ አብሥሯልና፨ አንድም የሁለት ቃለት ጥምር ነው እነዚህም ገብር እና ኤል ሲሆኑ ትርጕማቸውም ገብር አገልጋይ ማለት ሲሆን ኤል ማለት ደግሞ አምላክ ማለት ነው፤ በተገኛኘ ገብርኤል ማለት የአምላክ አገልጋይ /የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል የአምላክ አገልጋይ/ ማለት ነው። ✼ ነቢዩ ዳንኤል “ዐይኖቼንም አነሣሁ” አለና አስከትሎ “እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡… ይህንንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኃይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኃይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡(ዳን.10፥5-9) ነቢዩ ዳንኤል እንዲህ ብሎ የተናገረው የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ ነበር፡፡ ፠ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል “እነሆ ከዋነኞቹ አለቆች” አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ”(ዳን.10፥13) ብሎ በተናገረው ንግግሩ በመላእክት ላይ የተሾሙ ሌሎች አለቆች እንዳሉ ማስተዋል እንችላለን፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በቅዱሳን መላእክት ዘንድ ስላሉት ነገዶች ሲገልጽ “… በሰማይ ያለውን በምደር ያለውን የሚታየውንና የማይታየውን መናብርትም ቢሆኑ አጋእዝትም ቢሆኑ መኳንንትም ቢሆኑ ቀደምትም ቢሆኑ ሁሉም በእጁ ሆነ፤ ሁሉም በእርሱ ለእርሱ ተፈጠረ” (ቈላ.1፥16) በማለት ይዘረዝራቸዋል፡፡ ከዚህ ተነሥተን መላእክት በተለያዩ ዐበይት ነገዶች የተከፈሉና ለእያንዳንዱም ነገድ የራሱ የሆነ አለቃ እንዳለው ማስተዋል እንችላለን፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ከእነዚህ ዐበይት የመላእክት ነገዶች መካከል አንዱ በሆነው አርባብ በሚባለው ዐቢይ ነገድ ላይ የተሾመ ሲሆን ከ100ው ነገደ መላእክት መካከል ከበታቹ የሚመራቸው ዐሥር ነገደ መላእክት አሉት፤ ከተማቸውም በሰማየ ራማ ነው፡፡ ✼ ቅዱሳን መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ፊት አውራሪነት የሰው ልጆች ጠላት የሆነውን ዲያብሎስን ተዋግተው ድል ከመንሳታቸው አስቀድሞ ቅዱስ ገብርኤል፣ እንደ አምላክ ሊመለክ የወደደውን ሳጥናኤልን በመቃወም ‹‹ንቁም በበህላዌነ እስከ ንረክቦ ለአምላክነ - “አይዟችሁ ፈጣሪያችን እስክናገኘው፣ እስክናውቀው ድረስ በያለንበት ጸንተን እንቁም፡፡” (አክሲማሮስ ገጽ.35) በማለት መላእክትን ያረጋጋ መልአክ ነው፡፡ በተወዳጁ መልአክ በቅዱስ ሚካኤል መሪነት የሰው ልጆች ጠላት የሆነውን ዲያብሎስን ተዋግተው ድል እንዲያደርጉ ወደ ጥልቁ እንዲጣል አድርጓል ራእ12፥7፤ ነቢዩ ኢሳይያስ በሰማያት የሳጥናኤል ትዕቢትና ውድቀት ምን እንደሚመስል ሲጽፍልን “አንተ በንጋት የሚወጣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ አሕዛብ መልእክትን የላክ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ! አንተም በልብህ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደረጋለሁ፤… በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወድቃለህ፤ ወደ ምድር ጥልቅም ትወርዳለህ” (ኢሳ.14፥16) በማለት ገለጠልን፤ ወደ ምድር የጣሉት በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል መሪነት እነ ቅዱስ ገብርኤል ነበሩ፡፡ ✼ ቅዱስ ገብርኤል ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ከሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው ብሏል ሉቃ 1፥19፤ ታላቁ ነቢይ ሄኖክም ስለ ነገረ መላእክት በተናገረበት አንቀጽ እንዲህ ሲል መስክሯል ‹‹በአበቦች ላይ በገነትም በጻድቃን ላይ በኪሩቤልም ላይ የተሾሙ ከከበሩ መላእክት አንዱ ገብርኤል ነው፡፡›› ሄኖክ 6፥7፤ ‹‹በሦስተኛውም በመላእክት ሁሉ ላይ የተሾመ ቅዱስ ገብርኤል ነው››ሄኖክ 10፥14 እያለ የመልአኩን ክብር ተናግሯል፡፡ **ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን ይሆኑ ዘንድ ለተጠሩት መንፈሳዊ እውቀቱን የሚያካፍላቸው መልአክ ብቻ አይደለም፤ ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው፡፡ ነገር ግን ያደረጋቸው ተዓምራቶች በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በመልክኡ፣ በድርሳኑ፣ በገድሉ፣ በተዓምሩ የተጻፉ ቢሆንም ✤✼ ታኅሣሥ 19 ካደረጋቸው ተራዳኢነት ከብዙው በጥቂቱ እንደከሚተለው እናያለን፡- ፠ አናንያና(ሚሳቅ)፣ አዛርያ(ሲድራቅ) እና ሚሳኤል(አብደናጎ) ያዳናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ አናንያና(ሚሳቅ)፣ አዛርያ(ሲድራቅ) እና ሚሳኤል(አብደናጎ) የፋርስ ባቢሎን ንጉሥ የነበረው ናብከደነፆር በዱራ(አዱራን) በሚባል ስፍራ ላይ ላቆመው ጣዖት አንሰግድም በማለታቸው ወደ እቶን እሳት እንዲጣሉ አድርጓቸዋል፤ በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት ግን ከእቶን እሳቱ የልብሳቸው ዘርፍ እንኳን እሳት ሳይነካው ድነዋል፡፡ ©/የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

✤ #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_ዘገዳመ_ዋሊ፤ #ክቡር_መምህር፥ #የከበረ_መምህር፤ #መልአክ_ዘበምድር፥ #የምድር_መልአክ፤ #ካህን_ወድንግል፥ #ካህንና_ድንግል፤ #ፍጹም_ንጹሕ_ወልዑል፥ #ፍጹም_ንጹሕና_ልዑል፤ #ትጉህ_ወኅሩይ፥ #ትጉህና_ኅሩይ_የተመረጠ)፤ #ብእሴ_እግዚአብሔር፥ #የእግዚአብሔር_ሰው፤ #ለባሴ_ንጽሕና፥ #ንጽሕናን_የተላበሰ፤ #ወለብሰ_ብርሃናዌ፥ #ብርሃንን_የለበሰ፤ #ዘፈጸመ_ገድሎ_በሠናይ፨ #ገድሉን_በመልካም_ተጋድሎ የፈጸመ፨ #እናታቸው ዓመተ ማርያም በሕፃንነታቸው በሞተ ሥጋ ስትለያቸው ጌታችን ጣቶቹን ያጠባቸው ናቸው፨ <<መንኮብያቲሁ አጥበዎ ወልደ ማርያም ድንግል፤ ሳሙኤል፥ ሳሙኤል፥ ሳሙኤል ዘዋልድባ መነኮስ ኀያል>> እንዲል፨ #ታኅሣሥ ፲፪ በበዓለ ዕረፍታቸው ጊዜም፤ ሮም በጴጥሮስና በጳውሎስ ዕረፍት እንዳለቀሰች፤ ቅድስት ገዳማቸው ገዳመ ዋልድባ (ዋሊ) አልቅሳለች፨ <<በከየት ወለሀወት ገዳምከ በሞትከ ዮም፤ ሃሌ ሉያ፥ ሃሌ ሉያ፥ ሃሌ ሉያ፤ ምድረ ዋልድባ ቅድስት ሰሚዓ ዜና ሞትከ፤ እንዘ አንተ ሰብእ ምድራዊ ወመልአክ ተሠመይከ፤ ካህነ አርያም ሳሙኤል መንበረ ሥላሴ ዘአጠንከ፤ አንበሳ ወነምር ይሰግዱ ለከ፤ ወይልህሱ ጸበለ እግርከ፤ ዕንቆ ወዕጣነ ማርያም አምጽአት ለከ፤ በቅዳሴሃ ሶበ ጸለይከ፤ በከየት ወለሐወት ገዳምከ፥ በከየት ወለሐወት ገዳምከ።>> እንዲል፨

✤✤✤ #ፀሐይ_ማር_አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_ዘገዳመ_ዋሊ)፤ (ለኢትዮጵያ ርዕሰ ገዳማትና ምክኾን (መመኪያ) የኾነው፤ በሃገራችን በኢትዮጵያ ከሚገኙ ገዳማትና አድባራት በብቸኝነት በጌታችን የተመሠረተውና በ485ዓ.ም. በሸዋ አበው የተስፋፋው ገዳመ ዋልድባ፤ ኋላ በአሕዛብ ጠፍቶ ነበርና በ13ኛው ክፍል ዘመን እንደ መሶብ ከፍ አድርገው በ4ቱም አቅጣጭ በ4 ወንዞች (በሰሜን ተከዜ፥ በምሥራቅ እንስያ፥ በምዕራብ ዘሪማ ፥ በደቡብ እንዞና ወይቦ) ዙሪያውን ከልለውና አጥረው ያስባረኩ አባት ናቸው፡፡ ( አዲስ አበባንና አካባቢዋን ከ700ዓመታት በፊት በአንበሳ እየተጓጓዙ በስብከተ ወንጌል እርሻነት፥ በሥነ ምግባር ማለስለሻነት ያረሱ አባት ናቸው፡፡ ( ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን፣ ወላዴ መምህራን ወሊቃውንት የኾኑ ናቸው፤ ( አቡነ ሳሙኤልን ከቅዱሳን ሊቃውንት አንዱ የኾኑት ታላቁ አባት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በ40ቀን ዕረፍታቸው በመካነ መቃብራቸው ተገኝተው መልክአቸውን የደረሱላቸው፤ በርካታ ቅዱሳን ደራስያን በየድርሰታቸው ያነሷቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ( የከበረ መምህር፤ የምድር መልአክ፤ ካህንና ድንግል፤ ፍጹም ንጹሕና ልዑል፤ ትጉህና ኅሩይ(የተመረጠ)፤ ብእሴ እግዚአብሔር፤ ንጽሕናን የተላበሰ፤ ብርሃንን የለበሰ፤ ( እምቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዕንቊና ዕጣን የሰጠቻቸው ናቸው፤ ( ቅዳሴ ማርያምን ከተከዜ ወዲህ ያመጡና የቅዳሴ ትምህርትን በደብረ ዐባይ የጀመሩ ናቸው፡፡ ቅዳሴ ማርያን ሲደግሙ ከምድር ክንድ ከስንዘር ከፍ ብለው ይታዩ ነበር፡፡ ( ገባሬ ተዓምራት ወመንክራት የኾኑ፤ ⴲ ዝናብ በኾነ ጊዜ ዝሆኖች መጥተው አስጠልለውታል፤ ‹‹ሳሙኤል አቡነ ሠረገላ ጸሎት፤ ጊዜ ርደቶሙ ለዝናማት፤ ዘከለሉከ ነጌያት፡፡›› እንዳለ መጽሐፈ ሰዐታት፤ ⴲ ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር መንበረ ጸባዖትን ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋር አጥነዋል፤ ‹‹ሳሙኤል አቡነ ትሩፈ ምግባር፤ ዓምድ ጽኑዕ ፀወነ ሃገር፤ ወመልአክ ዘበምድር፡፡›› እንዲል መጽሐፈ ሰዐታት፣ ⴲ በዋልድባ ምድር ላይ ቀድሞ ውኃ የለም ነበርና፤ ፸ የሚጠጉ ምንጮችን በተለያዩ ቦታዎች አፍልቀዋል የምንኵስና ተወረዱም፤ አባት አባትን ሲወልድ፤ ገዳም ገዳምን ሲወልድ ነውና ቅሉ፤ የምንኵስና ተዋረዱም ርእሰ መነኰሳት አቡነ እንጦንስ አባ መቃርስን፤ አባ መቃርስ አባ ጳኵሚስን፤ አባ ጳኵሚስ አባ ቴዎድሮስን፤ አባ ቴዎድሮስ አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞን፤ አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ አባ ክርስቶስ ቤዛነነ፤ አባ ክርስቶስ ቤዛነ አባ መስቀል ሞዐን፤ አባ መስቀል ሞዐ አባ ዮሐኒን፤ አባ ዮሐኒ ፀሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን፤ ፀሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አቡነ መድኃኒነ እግዚእን፤ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ 7ቱን ከዋክብት /ፀሐይ አቡነ ሳሙኤልንና ሌሎች ቅዱሳንን/፤ ከ7ቱ ከዋክብት አንዱ ፀሐይ አቡነ ሳሙኤል ደግሞ ደቀ መዛሙርቶቻቸውን (አባ ተሥፋ ሐዋርያትን፥ አባ ዘሩፋኤልን፥ አባ ብንያሚን፥አባ በኪሞስን፥ አርሴማን (ሰማዕቷ አይደለችም)፥ …… ሌሎች እልፍ አእላፋት መነኰሳትን አምንኵሰዋል፣ ሊቃውንትን አስተምረዋል፤ መምህራንና ደራስያንን ተክተዋል ….፤ በዚህም ወላዴ አእላፍ አባ ሳሙኤል በመባልም ይታወቃሉ)፡፡ ፨ታሪኩንና ፎቶዎቹን ለሰበሰበልን ወንድማችን አምላከ አበው መድኀኔ ዓለም በረድኤት በበረከት ይጎብኝልን፨ /ከቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/