ar
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

تُعد قناة Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 15 382 مشتركاً، محتلاً المرتبة 5 568 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 195 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 15 382 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 04 يوليو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 23، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -1، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 22.11‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 9.42‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 3 401 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 1 449 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 20.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 05 يوليو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

15 382
المشتركون
-124 ساعات
-107 أيام
+2330 أيام
أرشيف المشاركات
#በቤተክርስቲያናችን_በር_ላይ_ለጥፈን_የነበረው_ባነር_በአስተዳደሩ_መመመርያ_ሰጪነት_በመውረዱ_ምክንያት_ስብሰባው_ቀርቶ_ነው_ወይ_ብላችሁ_ለጠየቃችሁን_የአካባቢ_ወጣቶች በሙሉ በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃ
+1
#በቤተክርስቲያናችን_በር_ላይ_ለጥፈን_የነበረው_ባነር_በአስተዳደሩ_መመመርያ_ሰጪነት_በመውረዱ_ምክንያት_ስብሰባው_ቀርቶ_ነው_ወይ_ብላችሁ_ለጠየቃችሁን_የአካባቢ_ወጣቶች በሙሉ በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል አብያተ ክርስቲያናት አጥቢያ የምትገኙ ወጣቶች ቅዳሜ 10/04/2013 ዓ.ም የዘንድሮውን የጥምቀት በዓል በደመቀ ሁኔታ ለማክበር የተጠራው ስብሰባ የተጠበቀ ነው፡፡ ሰንበት ት/ት ቤቱ በየዓመቱ የጥምቀትን በዓል የአካባቢውን ወጣት እያስተባበረ በዓሉን በሰላም እና በፍቅር እንደሚያከብር ይታወቃል፡፡ስለሆነም በዘንድሮውም ዓመት በቤተክርስቲያናችን በር ላይ ለጥፈን የነበረው ባነር በአስተዳደሩ መመመርያ ሰጪነት በመውረዱ ምክንያት ስብሰባው ቀርቶ ነው ወይ ብላችሁ ለጠየቃችሁን የአካባቢ ወጣቶች ስለ ጥምቀት በዓል ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ የተጠራው ስብሰባ የተጠበቀ መሆኑን እንገልጻለን::

#ታኅሣሥ 7/2012 ዓ.ም. #ለመጀመሪያ_ጊዜ_የቅዱስ_ያሬድ_ዜማ_በቤተ_ክርስቲያናችን_አገልግሎት_የተጀመረበትን በማስመልከት፤ ‹‹#የዜማ_ቀን_ክብረ_በዓልን_›› #በደብረ_ይባቤ_ቅዱስ_ያሬድ_ቤ/ክ #ለመጀመሪያ_ጊዜ_ክብረ_በዓሉ_ታቦቱ_ወጥቶ_መክበሩን እናስታውሳለን_፡፡ አነሆ ዘንድሮም👉👉 አሑድ #ታኅሣሥ_11_በ2013 ዓ.ም ለሁለተኛ ጌዜ ታቦተ ሕጉ ወጥቶ ይከብራል 👉👉#በዓሉ_ግን_ታኅሣሥ_7_ነው፡፡ (አድራሻ፤ ጎተራ ከአጎና ሲኒማ ከ,ወደ መስቀል ፍላወር በሚወስደው መንገድ፡፡) ፠ (#ቅዱስ_ያሬድን_ያልዘከረ_ኢትዮጵያዊ_ምኑን_ኢትዮጵያዊ_ኾነ!?) ፠ (#ቅዱስ_ያሬድን_ያልዘከረ_ካህን_ምኑን_ካህን_ኾነ!?) ፠ (#ቅዱስ_ያሬድን_ያልዘከረ_ሰንበት_ተማሪ_ምኑን_ሰንበት_ተማሪ_ኾነ!?) ፠ ጥዑመ ልሳን፤ ፠ የሱራፌል አምሳያ፤ ፠ የቤተ ክርስቲያን እንዚራ፤ ፠ የቤተ ክርስቲያን ብርሃን፤ ፠ መዓርዒረ ዜማ፤ ፠ ካህን (ካህነ ስብሐት) ፠ ማኅሌታይ፤ ፠ መዘምር ዘበድርሳን፤ ፠ ሊቅ (ርእሰ ሊቃውንት) ፠ ዓርከ ሊቃውንት፤ ፠ ደራሲ፤ ፠ የመጽሐፍ መምህር፤ (ብሉያትንና ሐዲሳትን የሊቃውንትንም መጻሕፍት አስማምቶ የተረጐመ) ፠ ባለቅኔ (የቅኔ ጀማሪ)፤ ፠ የቤተክርስቲያን ጌጧና መሠረቷ ሕይወቷና እስትንፋሷ ፠ ልዑለ ስብከት፤ ፠ ሰማዕት፤ ፠ ባሕታዊ፤ ፠ መናኝ ፠ የዜማ አባት፤ ፠ የኢትዮጵያ ብርሃን፡፡ ፠ አንደበቱ ጣፋጭ (ጥዑም) የኾነ:: ፠ እግሮቹ በመልካም መንገድ የሚጓዙና ወደ መልካም መንገድ የሚያስጕዙ ፠ ልቡናው የቅድስና ማኅደር የኾነ:: ፠ ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ የኾነ:: ፠ አእምሮው የመጠቀ፤ ፠ ድርሰቱ የተራቀቀ፤ ፠ እስከ አርያም ተነጥቆ ዕፁብ ድንቅ ምሥጢራትን የተመገበ፤ …… ማን እንደርሱ:: …... •፠ሃሌ ሉያ ንዑ ንትፈሣህ በመኃልይሁ፤ ወንንግር ለካህን ውዳሴሁ፤ ከመ ሱራፌል ለያሬድ ክላሁ፤ ለክርስቶስ ሰበከ ትንሣኤሁ፤ ማኅበረነ ይባርክ በእዴሁ፡፡ •፠ሶበ ኤዶምሃ መሠጥዎ፥ ግናየ ትንሣኤ መልዕዎ፤ ለያሬድ ካህን አስተብፅዕዎ፡፡ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔዓለምና ደ/ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት፡፡ Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

#ታኅሣሥ_6_የአርሴማ_ቅድስት_ወሰማዕትና_የእርሷ_ማኅበርተኞች_ድል_አድራጊዎች_27_ሰማዕታት_ሥጋቸው_በክብር_የፈለሰበትና_ቤተ_ክርስቲያኗ_ቅዳሴ_ቤት_የተከበረበት_ዕለት ነው፡፡ 1ኛ. አርሴማ፤ ቅድስት ወሰማዕት ኃያል ተጋዳሊት 2ኛ. ኢያሚኖስ፤ ጸሎትን የሚያሳርግ ካህን 3ኛ. አፍጢኖስ፤ ከብዙዎች የተመረጠ 4ኛ. በርቲኖስ፤ ጻድቅና ቸር 5ኛ. ጢሞና፤ በመላላክ ሥራ አገልጋይ የኾነ 6ኛ. ጢሞዓና፤ ተአጋሽና ጸዋሚ 7ኛ. ዘኬዎስ፤ ከከበሩ የከበረ 8ኛ. እስጢፋኑ፤ ተጋዳይና የበደሉትን ይቅር ባይ 9ኛ. አርሞና፤ ከጎልማሶች ይልቅ ደም ግባቱና መልኩ ያማረ 10ኛ. ኪርያኮስ፤ ሥጋውን ያላረከሰ ንጹሕ 11ኛ. አንጥያኮስ፤ ቡሩክ የኾነ የአቡሪ ልጅ 12ኛ. ያዕቆብ፤ የእግዚአብሔር ታማኝ የኾነ 13ኛ. ቡራኬሌስ፤ በሰው ዘንድ ተወዳጅ የኾነ 14ኛ. አስቂርያቆስ፤ ክርስቶስን የሚወደው 15ኛ. አስኪርያኖስ፤ ባለሟል የኾነና ግርማው የሚያስፈራ 16ኛ. ሚርያኖስ፤ ፊቱና መልኩ ደስተኛ የኾነ 17ኛ. ትትግርጦስ፤ ወደ ንስሐ የተመለሰ 18ኛ. ያስቲኖስ፤ የሚፈርድና የሚበይን 19ኛ. ጥልያኖስ፤ ያላመኑ ሰዎችን የሚገስጽ 20ኛ. ዑልያኖስ፤ የዚህ ዓለም ጥበብ መምህር የኾነ 21ኛ. ጴርቅላስ፤ በስም አጠራርና በሽምግልና መልካም የኾነ 22ኛ. ኬብያኖስ፤ ተጋዳይ የኾነ 23ኛ. ጴጥሮስ፤ የጠራ የባሕርይ ዕንቊ 24ኛ. ጰኵንዮስ፤ የሮምያ ሹም 25ኛ. ሐናንያ፤ የዋህና ሽንገላ የሌለው 26ኛ. ሐሊባኖስ፤ ጾምና ጸሎትን የሚወድ 27ኛ. ኤስያኖስ፤ በመንፈስ ቅዱስ ጎልማሳ የኾነ 28ኛ. ኤልያብ፤ በረኛና የሰማዕት መጀመሪያ፡፡ ሰላም ለዘአዕረፉ ምስሌኪ ፳ወ፯ቱ ሰማዕታት፤ ረድኤቶሙ ትረድ ላዕሌየ ዘምስለ ብዙኅ ምሕረት፡፡ ወኀበ ሀለወ ስሞሙ ምስለ ስምኪ ቅድስት፤ ዓዲ ኢይቅረብ አርሴማ ሕማመ ብድብድ ወሞት፤ በኵሉ አዝማን ወበኵሉ ዓመታት፡፡ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔዓለምና ደ/ትጉሃን ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ፡፡ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w https://t.me/medihanaelem

እንኳን አደረሳቹህ #✤#በኣታ_ለማርያም፤ እመቤታችን አባትና እናቷ ኢያቄምና ሐና በስዕለት(ለቤተ መቅደስ ሊሰጡ ብፅዓት ገብተው) ያገኟት ናት፡፡ በአባት በእናቷ ቤትም ፫ ዓመት ተቀመጠች፤ ከእንግዲህ ወዲያማ ስእለት መብለት ይሆንብን የለምን ወስደን እንስጥ ብለው ይዘዋት ወደ ቤተ መቅደስ ሲሄዱ ዘካርያስም ሕዝቡን ሰብስቦ ጉባኤ አድርጎ ቆያቸው። **ከዚያውም ደርሰው እነሆ ተቀበሉን አሏቸው እነርሱም እንቀበላለን ብለው ቢያዩዋት ከፀሐይ ፯ እጅ አብርታ፥ ከመብረቅ ፯ እጅ አስፈርታ፥ ዕንቈ ባሕርይ መስላ ታየቻቸው፤ እነርሱም እኛ ይህችን የመሰለች ፍጡር ምን እናደርጋታለን? ምን እናበላታለን? ምን እንጋርድላታለን? ብለው ሲጨነቁ በዚህም መካከል እመቤታችንን እግዝእትነ ማርያም መንፈሳዊ ረኀብ ተነስቶባት ምርር ብላ አለቀሰች። ያን ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል በመሶበ ወርቅ ኅብስት ሰማያዊ፤ በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወት ይዞ ረቦ ታያቸው፡፡ ሕዝቡም ዘካርያስን አባታችን ይህ የወረደው ክብር ላንተ ነው የሚኾነውና ተነስተህ ታጥቀህ እጅ ነስተህ ሰግደህ ተቀበል አሉት፤ ዘካርያስም እሽ ብሎ እጅ ነስቶ ሰግዶ እቀበላለሁ ብሎ ሲጠጋ ወደ ሰማይ ራቀው፥ መጠቀው፡፡ ከሕዝቡም እያንዳንዱ እየተነሱ እንቀበላለን ብለው ቢያዩ ወደ ሰማይ ራቃቸው፥ መጠቃቸው፡፡ **ከዚህም በኋላ ዘካርያስ ሐናን ጠርቶ ለናንተ ለእንግዶች የወረደ ክብር እንደሆነ ሕፃኒቱን ይዘሽ ወደዚያ ፈቅ ብለሽ ተቀመጪ አላት፡፡ እርሷም ሕፃኒቱን ይዛ ወደዚያ ፈቅ ብላ ተቀመጠች፡፡ መልአኩም ከራሳቸው ላይ ረቦ አልወርድም አለ፡፡ ***ሁለተኛም ዘካርያስ ሐናን ጠርቶ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ነገር የሚያውቅ የለም፤ ሕፃኒቱን ከዚያው ትተሽ አንቺ ወዲህ ነዪ አላት፤ እሽ ብላ ሕፃኒቱን እዚያው ትታ ወደነሱ ሄደች፡፡ ያን ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል ወርዶ ፩ ክንፉን ጋርዶ ፩ ክንፉን አጎናፅፎ ኅብስቱን አብልቷት፥ ወይኑን አጠጥቷት፤ እመቤቴ ሆይ መንገድ ባስመታሁሽ ማሪኝ ብሎ የብርሃን መሶብ፥ የብርሃን ጽዋ ይዞ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ **ሕዝቡም የምግቧማ ነገር ከተያዘ ከሰው ጋራ ምን ያጋፋታል፤ ቦታዋ ከቤተ መቅደስ ይሁን እንጂ ብለው ዙፋኑን ዘርግተው፥ ምንጣፏን አንጥፈው፥ መጋረጃውን ግራና ቀኝ ጋርደው ከቤተ መቅደስ አኖሯት፡፡ ***ይኸውም የተደረገው ታኅሣሥ ፫ ዕለት ነው፤ በአታ የሚለው ስያሜም የተሰጠው በዚሁ ነው፡፡ ‹‹አመ ፫ ለታኅሣሥ በኣታ›› እንዳለ መቅድመ ተአምር፡፡ በዚህም፤ #መቅደሲቱ_ወደ መቅደስ ገባች፤ #ቅድስቲቱ_ወደ ቅድስት ገባች፤ #ክብርቲቱ_ወደ ክብርት ቤቷ ገባች፤ #ልዩ_የሆነችው_ወደ ልዩ ሥፍራ ገባች፤ #ቅድስተ_ቅዱሳኗ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ገባች፤ #ንጽሕተ_ንጹሐኗ ወደ ንጽሕ አዳራሽ ገባች፤ #ቤተ_መቅደሷ ወደ ቤተ መቅደስ ገባች፡፡ ሊቃውንትም ‹‹መቅደስ ዘኢትትነሠት /የማትፈርሺ መቅደስ ነሽ››/ እያሉ አመሠገኗት፡፡ **እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ኅብስት ሰማያዊ እየተመገበች፤ ስቴ ሕይወት እየጠጣች ከመላእክት ጋራ እየተጫወተች 12 ዓመት በቤተ መቅደስ ተቀመጠች፡፡ ‹‹ከመዝ ነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ፤ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ ፲ተ ወ፪ተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት ወስቴኪኒ ስቴ ሕይወት ውእቱ። ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ››። እንዳለ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ***ምግቧ ከየት የተገኘ ነው ቢሉ በገበሬ እጅ ያልተዘራ በቤተ ሰብእ እጅ ያልተሠራ በእግዚአብሔር እጅ የተፈጠረ ያማረ የተመረጠ ነው እንጂ ፡፡ ‹‹ኦ ድንግል አኮ ኅብስተ ምድራዌ ዘተሴሰይኪ፤ አላ ኅብስተ ሰማያዌ እም ሰማየ ሰማያት ዘበሰለ፡፡ ኦ ድንግል አኮ ስቴ ምድራዌ ዘሰተይኪ አላ ስቴ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት ዘተቀድ›› (ድንንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለሽም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን እንጂ፡፡ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለሽም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጥን ነው እንጂ፡፡) /እንዳለ ሊቁ አባ ሕርያቆስ/። ***ስታድግም በንጽሕናና በቅድስና ነው፡፡ ‹‹ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም በንጽሕና በቅድስና ኖርሽ እንጂ።›› /እንዳለ ሊቁ አባ ሕርያቆስ/ ***እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ ሳለች አይሁድ ብዙ የክፋት ምክር ይመክሩ ነበር። ከዚህም ውስጥ አንዱ መጥቁል ወደሚባል ጠንቋይ ሄደው ‹‹ፍታሕ ማዕከሌነ ኢያቄም ወሐና›› ብለው እመቤታችንን እንዲያጠፋ እጅ መንሻን ሰጡት፤ መጥቁልም በመካከል አይሁድ በኋላ ሁነው ነጋሪት እየጎሰሙ፥ እምቢልታ እየነፉ እመቤታችንን እግዝእትነ ማርያምን ለመግደል ለቤተ መቅደስ ፪ ምንዳፈ ሐፅ ሲቀራቸው፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ እዚያ ድረስ ያልተደረገና ያልተነገረ መብረቅ ነጎድጓድ ወርዶ አጋንንትንም፥ መጥቁልንም፥ አይሁድንም ቀጥቅጦ አጠፋቸው። እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም በማግሥቱ ወጥታ አይታ መጥቁል ሆይ እኔን አጠፋ ብለህ መጥተህ አንተ እንዲህ ሆንህ ካንተ መከራ መዓት ያወጣኝ አምላክ ይክበር ይመስገን ብላ ፈጣሪዋን አመሰገነች፡፡ ከዚህ በኋላ በድኑ ለዝክረ ነገር የ፫ ቀን መንገድ እየሄደ ይሸት ጀመር። እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ‹‹ዮሰሜር፣ አድሜሽ፣ ድቸር፣ አዶናዊሮስ፣ ሰራሰቅሰሬል›› ብላ የአምላክ ኅቡዕ ስምን ብትደግም መሬት ተከፍቶ ዋጣቸው ከነሥጋቸውም ሲኦል ወረዱ፡፡ ከዚህ በኋላ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እጅግ ታፈረች የሚናገራት ጠፋ ‹‹ኦ ግርምት ድንግል›› /እንዳለ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም/። ✤#በዓለ_ሢመቱ_ለቅዱስ_ፋኑኤል_ሊቀ_መላእክት፤ #ሰዳዴ አጋንንት ነው፤ /ሄኖክ 10፥8፣ ድርሳን ዘፋኑኤል/ #መጋቤ ድንግል ነው፡፡/ተአምረ ማርያም/ #ማኅሌታዊ ነው፤ #በመንበረ መንግሥቱ ዙሪያ ከሚቆሙት ሊቃነ መላእክት አንዱ ነው፡፡ /ሄኖክ 20፥39/ #በአራቱ የዓለም ማዕዘናት ሹም አንዱ ነው፡፡ #ለመልካም ነገሮች ከሚራዱ መላእክት አንዱ ነው /መዝ. 33፥7/ #ካህነ ንስሐ ነው /ሄኖክ 10፥5/ #ዐቃቤ ጻድቃን ነው፡፡ /2ኛ ነገ. 6፥14/ #ምስለ_አብያጺሁ_ከመ_አብ_እንዘ_ይሴስየኪ_መና፤ #ፋኑኤል_ጽጌ_ነድ_ዘይከይድ_ደመና፡፡ ✤#ኢትዮጵያዊው_አቡነ_ዜና_ማርቆስ_በዓለ_ዕረፍታቸው ነው፡፡ እኒህ ታላቅ አባት በምድረ ጉራጌ በሚገኘው በምሁር ኢየሱስ ገዳም 40 ዓመታትን ሱባኤ የገቡ፤ ምድረ ጉራጌን (ሙሉ ሸዋን ጨምሮ እስከ ደቡብ) እንዲሁም በሌሎችም የሃገራችን ክፍሎች ያስተማሩ፤ በርካታ ሊቃውንትን /አባ ጽጌ ድንልንና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታን ጨምሮ ሌሎችን ሊቃውንትም/ ያፈሩ ፈርጥ ሲኾኑ፤ በስተመጨረሻ በተአምራት የተሞላውን ታላቁን ገዳም ደብረ ብሥራትን (ጅሩ) መሥረተው በክብር አርፈዋል፡፡ #ከዋይዜማው_ጀምሮ_የሚቆመውን_የበኣታ_ለማርያም_ሥርዐተ_ማኅሌትንም_አቅርበንላችኋል_፡፡ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w https://t.me/medihanaelem

"የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን " ነህ 2፥20 #ሰ/ት/ቤታችን የአካባቢውን ወጣቶች እና ህጻናት ሊማሩበት የሚችሉበትን #የህንጻ_ዲዛይን ይፋ አደረገ
+3
"የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን " ነህ 2፥20 #ሰ/ት/ቤታችን የአካባቢውን ወጣቶች እና ህጻናት ሊማሩበት የሚችሉበትን #የህንጻ_ዲዛይን ይፋ አደረገ ✤ ✤ ✤ ሰ/ት/ቤታችን በተፈቀደለት #600 ካሜ ቦታ ላይ መማርያ ህንጻ ለመገንባት የሚያስችል ቅድመ ሁኔታዎችን አጠናቋል፡፡ ✤ ✤ ✤ ይህ ህንጻ የሰንበት ት/ት ቤታችን አገልግሎት ሊያፋጥኑ የሚችሉ በውስጡ #_8 ቢሮዎች፣_በመንበረ_ፓትርያሪክ_ጠቅላይ_ቤተክህነት የጸደቀው አዲሱን ስርዓተ ትምህርት ለማስተግበር የሚያስችሉ #_12 መማርያ_ክፍሎች ፣ 1 መሰብሰቢያ እና ለተለያዩ ጉባኤያት የሚሆን #_አዳራሽ ፣ #_1ዘመናዊ_ቤተመጻህፍት ፣ #_1_ለንብረት_ማስቀመጫ የሚሆን እቃ ቤት(store) የያዘ ነው ፡፡ የአካባቢ ወጣቶች እና ህጻናት ካላቸው ቁጥር የተነሳ አሁን ላይ የምናስተምርበት የመማርያ ቦታ እጥረት በዚህ ህንጻ ይቀረፋል የሚል ሙሉ እምነት አለን፡፡ ቤተክርስቲያን “ሁሩ ወመሐሩ” (ሂዱና አስተምሩ) ብላ የጣለችብንን ሃላፊነት በሚገባ ለመወጣት ሁላችንም #_ማህበረ ካህናት፣_የሰንበት ት/ት_ቤት_ወጣቶች፣ #_የአካባቢው_ወጣቶች እና ምዕመናንን #_በጸሎትም_በሀሳብም_በጉልበትም እያገዛችሁን ጫፍ እናደርሰዋለን ለዚህም እግዚአብሔር አምላክ ይርዳን አሜን!፡፡ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w https://t.me/medihanaelem

#ታኅሣሥ_1 #ክብረ_በዓሉ_የሚከበርባቸው፤ *በጥንታዊው ደብረ ኃይል እንጦጦ ቅዱስ ራጕኤል ወኤልያስ፤ *በደብረ ኤልያስ ጎጃም፤ *በገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን (በድርብነት አለ) *በብሥራተ ገብርኤል ቅዱስ ኤልያስ (ኋላ ብሥራተ ገብርኤል በመባል በሚጠራው) *በሻሸመኔ ልደታና በሌሎችም የቅዱስ ኤልያስ አድባራትና ገዳማት ይከበራል፡፡ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w https://t.me/medihanaelem /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

#እንኳን_ለቅዱስ_ኤልያስ_ዓመታዊ_ክብረ_በዓል (የልደት ቀን) በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡ በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ነቢያት ዝናም በማቆም ብቸኛ ነቢይ፡፡ ✤ የሰማርያው ነቢይ ኤልያስ ከቅዱሳን አበው ነቢያት አንዱ ሲኾን አባቱ ኢያሴዩ ይባላል፡፡ በነቢይነትም ሆነ በብቃት ኤልያስን የሚያክል፤ በሥራው የሚወክል ከእሱ በፊትም ኾነ በኋላ በተአምራት የተሞላ እሳት ለበስ ነቢይ እሱ ከመረጠው ከደቀ መዝሙሩ ከኤልሳዕ በቀር አልተነሳም፡፡ ነቢዩ ኤልያስ ከኢዮርብዓም እስከ እርሱ ድረስ ለአያሌ ዓመታት በሰይጣን ግፊት በሰው ሠራሽ ጣዖት የተመረዘ በኃጢአትም ረዘረዘ፣ የግፈኛው አክአብና የዘማዊቷ ኤልዛቤልን መንግሥት በሦስት ዓመት ከመንፈቅ በከባድ ድርቅ በመናጥ፣ እንዲሁም አፈር እንደበላው ብረት የዛገ አስተሳሰባቸውን በሰው ደምና በቅሚያ ገንዘብ የተሞላ ሰውነታቸውን በማን አለብኝነት ያበጠ ልባቸውን እንደሰም በማቅለጥ የሚይዙትንና የሚጨብጡትን ያሳጣ በፈጣሪው ለዚህ ሥራ የተመረጠ ሰመ ጥር ነቢይ ነው፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ነውና፡፡ ኤልያስ የከተማ ነቢይ ብቻ አይደለም ባሕታውያን ተብለው ከሚጠሩት ነቢያተ ጽድቅም አንዱ እንደነበር ሕልውናው ምስክር ነው፡፡ (( ኤልያስ ብዙ ነገር ስለሚያስተምር የቀና እምነቱን ውጤት ጥቂት መመልከት እኔ ማነኝ ለሚሉት እጅ ይዞ ይመራል፡፡ ✤ 1. ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ ሰማይ ዝናም ለዘር ጠል ለመከር ከመስጠት እንዲከለከል ምድርም የተከሉባትን እንዳታጸድቅ የዘሩባትን እንዳታበቅል ለባለንብረቱ አመለከተ ይህም ጥያቄው ከእግዚአብሔር መልስ አግኝቷል፡፡ ነገሥ 17፥1-2፡፡ ከዚህ ላይ የሊቀ ነቢያት ሙሴንና የኢሳይያስን ቃል ያስጠቅሳል ዘዳ 32፥1-4፣ ኢሳ 1፥2-5፡፡ በእነዚህ እስከፊ ዓመታት ውስጥ በመሪዎች አመፅ በኤልያስ ተግሣጽ የሚመለከተውም የማይመለከተውም የሚልሰውና ሚቀምሰው አጥቶ በዋለበት እንደ ቅጠል ረገፈ እንደሻሸተ ነጠፈ፡፡ የኀጥአን ፍዳ ጻድቅ ይደፋ ይሏል ይህ ነው፡፡ ዛሬም በአምስቱ ክፍለ ዓለም የብዙኃኑ እልቂት ሲፈጸም የሚታየው በጥቂት እግዚአብሔር የለሽ ሰይጣን ጁንታዎች ሽፍቶች መሆኑን ከአክአብና ኤልዛቤል ይማሯል፡፡ ይህን የኤልያስን ጠበቅ ያለ እገዳ ከስምንት መቶ አምሳው ነቢያተ ሐሰት ካህናተ ጣዖት አንዱም ወደ ሚመለከተው በጸሎቱም ሆነ በመሥዋዕቱ አመልክቶ ሊያስነሳ ወይም ለማስነሳት የቻለ የለም፡ ጠንቋዮችና አታላዮች በብሉይ ኪዳን ብዙ ጊዜ ከቤተ መንግሥት ተለይተው አይርቁም፡፡ 1ኛ ነገሥ 18፥22፣ዳን 2፥1-14፡፡ ✤ 2. አመጸኞች አክአብንና ኤልዛቤልን ምንነታቸውን ካሳወቀ በኋላ የዘጋውን ለመክፈት ወደ ፈጣሪው በመጸለይ ዝናም አዝንሟል፡፡ 1ኛ ነገሥ. 18፥41-46፣ ያዕ 5 17-18 እግዚአብሔር ለወዳጆቹ የገባውን ቃል ኪዳን አያጥፍም አቁም ሲሉት ያቆማል ስጥ ሲሉት ይሰጣል እንጂ ምን አገባቸው ብሎ እንደፈለገው አያደርግም፡፡ የእግዚአብሔር ሐዋርያ ስለ ኤልያስ ማንነት ሲያደንቅ ኤልያስ እንደኛ ሰው ነበር ዝናም እንዳይዘንም ከለከለ እንደገናም እንዲዘንም አደረገ በማለት በዘመኑ የነበሩ ክርስቲያኖች ከቀና ክርስትናቸው ምን እንደሚጠበቅባቸው ከእምነታቸው ምን ማግኘት እንዳለባቸው ይጠይቃል ያዕ.5፥13-20፡፡ ዛሬስ ምን ይመስሎታል፡፡ ኤልያስ በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ነቢያት ዝናም በማቆም ብቸኛ ነቢይ ነው፡፡ ነገር ግን በረዶ ያዘነመላቸው አንደኛ ሙሴ ዘፀ 9፥13-21 ሁለተኛ ኢያሱ 10፥9-12 ሦስተኛም ሳሙኤል 1ኛ ሳሙ 12፥1-19 ይመለከታል፡፡ ✤ 3. በተፈጥሮ የማይመስላቸው በቋንቋም የማይግባባቸው እንኳን ለሰው ሥጋ ሊያመጡ ከሰው ሥጋ የሚነጥቁ አሞራዎች ከየት እንደሚያመጡት የማይታወቅ እንጀራና ሥጋ ለምግብ እንዲያመላልሱለት አደረገ 1ኛ ነገሥ 17፥6-7፡፡ እነዚህ አሞራዎች ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ በጋ ከክረምት የለምንም እረፍት ኤልያስን ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡ እምነት ካለ ተአምር መሥራት አይገድም ይህንም ከኤልያስ ይማራል፡፡ ✤ 4.ለአንዲት መበለት ዱቄትና ዘይት አበረከተ፡፤ ኤልያስ ቁራሽ እየለመነ ያደረገውን ተአምር ልብ ይሏል፡፡ 1ኛ ነገሥ. 17፥16-24፡፡ ✤ 5. ዱቄትና ዘይት ያበረከተላት ሴት ልጇ ቢሞት ከሞት አስነሳው 1ኛ ነገሥ. 17፥20-23 ይህች ሴት በእምነቷ አርአያነት ያላት ደገኛ ሴት ናት፡፡ ኤልያስን የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ፣ ኀጢአቴንስ ታስብ ዘንድ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን ብላዋለች፡፡ ኤልያስም በእግዚአብሔር ኀይል ማንኛውንም ችግር ለመፍታት ሙሉ መብት ነበረውና ወዲያውኑ የሞተውን ብላቴና ጠጋ ብሎ ወደ ፈጣሪው በጸሎት በማመልከት አስነስቶ የብላቴናውን እናት አስደስቷል 1ኛ ነገሥ 17 17-24 ሐዋርያ እምነት ጀግኖችን በመዘገበበት አንቀጽ ይችን ሴት ልብ ይሏል፤ ዕብ 11፥35፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ያሉ እናቶች ያስፈልቷል፡፡ ይህችን ሴት የሚመስሉ እናቶች 2ኛ ነገሥ. 4፥18-38 ፣ሉቃ 7፥11-17 ተመዝግበዋል፡፡ በሐዋርያት ሥራም ያሉት እናቶች ከእነዚህ ጋር ያነጻጽሯል የሐዋሥ 9 36-43፡፡ ✤ 6. ለብዙ ጊዜ በቤተ መንግሥት ተሰግስገው አክአብና ኤልዛቤልን በሐሰት ሲደልሉ ግብዝ ሕብረተሰቡን ሲያታልሉ ለፍቶ ያገኘው ገንዘቡን ሲሸልጉ በኀጢአት ሊያስወጉ የነበሩ ነቢያተ ሐሰትና ካህናተ ጣዖትን በሕብረተሰቡ ፊት እስከ መምህራቸው ሰይጣን በቅሌት አከናንቦ ሲያስቅባቸው ውሏል፤ 1ኛ ነገሥ 18 20 -29፡፡ ሰይጣን በሰማርያ በምድር እንደዚያ ቀን ሰው መዘባበቻ በመሆን የውርደት ቀን ገጥሞት አያውቅም፡፡ በገዛ አገሩና መንደሩ፡፡ 7. ወደ ፈጣሪው በጸሎት በማመልከት ያቀረበው ንጹሕ መሥዋዕቱን ከሰማይ እሳት ወርዶ በሰው ፊት በላለት 1ኛ ነገሥ 18 30-40፡፡ በዚህም ማንነቱን በሰይጣንና በሰይጣን አቀንቃኞች ፊት አስመስክሯል፡፡ ✤ 8. ምግብና መጠጥ መልአክ ከሰማይ አመጣለት ያንን ተመግቦ ለአርባ ቀን ያለምንም ምግብ መጠጥ ተጉዟል 1ኛ ነገሥ 19፥5-7 ✤ 9. እሳት ከሰማይ በማዝነም ሊጣሉት የመጡትን መምለኪያነ ጣኦት ምሉአነ ኀጢአት የሰይጣን ሠራዊት በሰው ደም የሰከሩ በዲያብሎስ የሚመሩ ጠላቶቹን አጋይቷል 2ኛ ነገሥ 1 9-13 ✤ 10. በመጎናጸፊያው የዮርዳኖስን ባሕር ከፍሎ ከነ ደቀመዝሙሩ በደረቅ ተሸግሯል 2ኛ ነገሥ. 2፥11 ✤ 11. ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ918 ዓመተ ዓለም ሳይሞት በሕይወቱ መራራው ሞት ዕያየው በብርሃን ሠረገላ ወደሰማይ አርጓል 2ኛ ነገሥ. 2 6-9 ✤ 12. እንደ እያስፈላጊነቱ ከፈጣሪው ጋር ለብዙ ጊዜ ተነጋግሯል ከአንድ እስከ አስራ አንድ ያደረጋቸውን ተአምራት የፈጸመለት ታማኝ ፈጣሪው ሰው በሆነበት ወራት በተራራ ከጓደኞቹ ጋር ብርሃነ መለኮቱን ገለጠለት ማቴ 17 ፥3 ፡፡ ከዚህ ዓለም ከተሰናበቱ በኋላ ወደዚህ ዓለም መጥተው የፈጣሪጣቸውን ሰው መሆን ያዩ ከነቢያተ ጽድቅ ሙሴና ኤልያስ ብቸኞች ናቸው ብፁዓን ከተባሉት ሐዋርያትም ተቆጥረዋል፤ በዚህም ቅዱሳን ከሞት በኋላ እንደሚያማልዱም መስክሯል፡፡ ማቴ 13፥16-17፡፡ ኤልያስ ሰው መባል ወይም ተብሎ በመጠራት እንደማንኛውም ሰው መሆኑ መልአክ አለመሆኑን ሐዋርያ ነግሮናል ያዕ 5፡17-20፡፡ ከኤልያስ ብዙ ነገር ወይም ተግባር ስለሚማሩ ከቅዱስ መጽሐፍ ከ 1ኛ ነገሥ 17፡1 ጀምረው እስከ 2ኛ ነገሥ 2፡11 ረጋ ብለው ይመርምሩ ክርስትናዎትንም ይፈትሹ፡፡

ኀዳር ፳፱ በዓለ ልደቱ ለአቡነ አጨጌ ዮሐንስ ዘፀገሮ ✤ጨረቃና ፀሐይን ይዘው ይሚጸልዩ ✤ከሰማይ መስቀል የወራደላቸው ቡዙ ቃልኪዳን የተሰታቸው ጻድቅ ናቸው፡፡ ——ገዳማቸውም ሰሜን ሸዋ መንዝ ይፋት መ
+2
ኀዳር ፳፱ በዓለ ልደቱ ለአቡነ አጨጌ ዮሐንስ ዘፀገሮ ✤ጨረቃና ፀሐይን ይዘው ይሚጸልዩ ✤ከሰማይ መስቀል የወራደላቸው ቡዙ ቃልኪዳን የተሰታቸው ጻድቅ ናቸው፡፡ ——ገዳማቸውም ሰሜን ሸዋ መንዝ ይፋት መዘዞ ይገኛለወ ( ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ ገዳም) በዚህ ዕለት 500 ዓመት የያዙት መስቀል እና መቋማያቸው በቀስተ ደመና ታጅቦ ጸበል ቦታውን ይባርካል ፡፡ ✤ልደታቸው ህዳር ፳፱/29 ✤እረፍታቸው ሐምሌ ፳፱/29 ምልጃቸው አይለየን በረከታች ይደርብን አሜን ! https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w https://t.me/medihanaelem

ብፁዕ አቡነ ገብርኤል (ዶ/ር) ሊቀ ጳጳስ ከ1933 - 2013 ዓ/ም ✤የመጀመሪያ ስማቸው ሣህለ ማርያም ይባል ነበር፡ ✤በ1961 ዓ.ም ወደ ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሃይማኖት አንድነት ገዳም በመሔድ በጻድቁ ቃልኪዳንና በአበው መነኰሳት ፈቃድ መነኰሱ፡፡ ✤ለስብከተ ወንጌል ካላቸው ፍቅርና የማስተማር ጉጉት የተነሣ የራሳቸው ማይክሮፎን (ድምጽ ማጉያ) ይዘው በየወቅቱ ወደ #ደብራችን #ቀጨኔ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ✤ብፁዕነታቸው በ1962 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ አባታዊ ፈቃድና ከብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የወለጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቅስና እና ቁምስናን ተቀብለዋል፡፡ 1972 ዓ/ም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ ዶር አባ ኢያሱ ይባሉ የነበሩት ብፁዕ አባ ገብርኤል ተብለው የመንፈሳዊ ኮሌጅ ኤጲስ ቆጶስ (ዲን)፤ የድሬዳዋ እና አካባቢው ኤጲስ ቆጶስ ተብለው ተሾሙ፡፡ ✤በድሬዳዋ ሀገረ ሰብከት ለአንድ ዓመት ፤ላ በ1973 ዓ/ም የኤርትራ ክፍለ ሀገር ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ለሦስት ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ✤በ1976 ዓ/ም ወደ አዲስ አበባ በመዛወር የትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት ኃላፊ ሆነው በመሥራት ላይ እያሉ የኤርትራ ሀገረ ሰብከት ካህናትና ምእመናን አባታችን ይመለሱልን እንፈላጋቸዋለን የሚል አቤቱታ ለቅዱስ ሲኖዶስና በወቅቱ ለነበሩት ፕሬዝዳንት በማቅረባቸው ለሁለተኛ ጊዜ ወደ አስመራ በመመለስ የኤርትራ ክፍለ ሀገር (ሀገረ ሰብከት) ሊቀ ጳጳስ በመሆን እስከ 1983 ዓ/ም ድረስ አገልግለዋል፡፡ ✤ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ሰብከት ካረቢያን ሀገራት ሜን ወሎ ወልዲያ ሀገረ ሰብከት ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ✤የኢትዮጵያ የሃይማኖት ጉባኤ መሥራችና ለተከታታይ ስድስት ዓመታት ያህል የጉባኤው የቦርድ ሰብሳቢ የካውንስል ጉባኤው ሰብሳቢ በመሆን ከሐዋሳ አዲስ አበባ ድረስ እየተመላለሱ ቤተ ክርስቲያን የሰጠቻቸውን ኃላፊነት በብቃት በመወጣት ያለመሰልቸው አገልግለዋል፡ ✤ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሲዳማ፣ ጌድኦ አማሮና ቡርጂ ዞን ሀገረ ስብከት ተልከው እስከ አሁን ማለትም እስከ ጥቅምት 2013 ዓ.ም በዚያ እያገለገሉ ይገኙ ነበር፡፡እጅግ በርካታ ሀገሮች እና ተጨማሪ አገልግሎቶች አገልግለዋል፡፡ ✤ብፁዕ አቡነ ገብርኤል (ዶ/ር) ሊቀ ጳጳስ ባደረባቸው ሕመም በምክንያት በተወለዱ በ80 (፹) ዓመታቸው ኅዳር 26 ቀን 2013 ዓ/ም ከድካም ወደ ዕረፍት ተሻግረዋል፤ ) ሥርዓተ ቀብርራቸው በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ኅዳር ፳፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም ተፈጽሟል ። እግዚአብሔር አምላክ ከአብርሃም ከይሰሐቅ ጋር ይኑርልን አሜን ! ምንጭ ኢኦቲሲ መ.ብ.አ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w https://t.me/medihanaelem