ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك 👈

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

تُعد قناة Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 15 622 مشتركاً، محتلاً المرتبة 5 302 في فئة الدين والقيم الروحية والمرتبة 2 181 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 15 622 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 08 أكتوبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 67، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 14، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 8.25‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 4.62‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 1 288 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 721 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 12.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 09 أكتوبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الدين والقيم الروحية.

15 622
المشتركون
+1424 ساعات
+867 أيام
+6730 أيام
أرشيف المشاركات
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጠ! የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በዛሬው ዕለት በወቅታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል። በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የተከሰተው ክስተት አየተባባሰና እየተካረረ መሄዱ በእጅጉ እንዳሳሰበው ተቋሙ በመግለጫው አሳውቋል። የስድስቱ አባል የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ስለጉዳዩ በመጨነቅ አብዝተው ከመጸለይ ባለፈ ከቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ጋር ችግሩ በሰላማዊ ሁኔታ ስለሚፈታበት ሁኔታ መወያየታቸውም ተገልጿል። በተያያዘም በዚህ ሂደት ተቋሙ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል። ቤተክርስቲያኒቱ ለዘመናት የኖረ ሕገ ቤተክርስቲያን፣ ቀኖና እና ሥርዓት ያላት አንጋፋ ተቋም ከመሆኗ አንጻር ያጋጠማትን ውስጣዊ ችግር በቤተክርስቲያኒቱ ሕግና ሥርዓት ሊፈታ እንደሚችል እንጠብቃለን በማለት ገልጿል። የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሰላም ጉዳይ የሁሉም ጉዳይ መሆኑን ጠቅሶ ባለ አምስት ነጥብ መግለጫም አውጥቷል። ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አማኞች በተጨማሪ የሌላ ሃይማኖት ተከታይ የሆነ ሁሉ ፊቱን ወደ ፈጣሪ በመመለስ ጸሎት ወይም ዱዓ እንዲያደርግ አደራ ብለዋል። የቤተክርስቲያኒቱ አባቶችም ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ከማክበር ጎን ለጎን የችግሩን ስፋትና ጥልቀት ተገንዝበው ውይይትን፣ ይቅርታንና እርምትን እንዲያስቀድሙ በፈጣሪ ስም በማሳሰብ ይህም ሊደርስ የሚችለውን አደጋ አስቀድማችሁ እንድትከላከሉ ሲል ገልጿል። የፌዴራልና የክልሎች መንግሥታት በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ የተፈጠረው ችግር በራሷ በቤተክርስቲያኒቱ ሕግ፣ ቀኖና እና ሥርዓት ብቻ ተመሥርቶ እንዲፈታ ኃላፊነታቻውን በአግባቡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 11 እና አንቀጽ 27 መሠረት እንዲወጡ ተቋሙ አሳስቧል። ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ አመራሮችና አባላት፤ የማኅበረሰብ አንቂዎች ወቅታዊ የቤተክርስቲያኒቱን ውስጣዊ ችግር ከማባባስ እንዲጠበቁ ተቋሙ አደራ ብሏል። የመገናኛ ብዙኋን ባለሙያዎች፣ ዘጋቢዎችና ተንታኞች የሚያስተላልፏቸው መልእክቶችና ንግግሮች ችግርን የሚያባብሱና ሌላ ግጭትና ሁከት የሚቀሰቅሱ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስቧል።

‹‹#መሐረነ_አብ (#የምሕላ_ጸሎት)፤ #በግእዝና_በአማርኛ፡፡ በግእዝና በአማርኛ፡ ፠ ‹‹ሳታቋርጡ ጸልዩ›› እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ በ፩ኛ ተሰ. ፭፥፲፯ ጌታችንም ‹‹ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ›› ማቴ ፳፬፥፬ ብሎ አርአያ ሆኖ እንዳስተማረን፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ከምንገለገልባቸው ጸሎቶች አንዱና ዋነኛው ‹‹መሐረነ አብ›› ጸሎት ነው፡፡ ፠ መሐረነ አብ የሚወለውን ስያሜውን ያገኘው ጸሎቱ ሲጀምር ‹‹መሐረነ አብ ፥ መሐረነ ወልድ፥ መንፈስ ቅዱስ መሐሪ ተዘከረነ በሣህልከ፡፡›› (አብ ሆይ ማረን፥ ወልድ ሆይ ይቅር በለን፥ ይቅር ባይ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በይቅርታህ አስበን) ብሎ ስለሚጀምር ነው፡፡ ፠ የመሐረነ አብ ጸሎትን ያዘጋጀው ከ40 መጻሕፍት በላይን የደረሰውና ካልዓይ ቅዱስ ያሬድ ፥ ካልዓይ ቄርሎስ የተባለው ቅዱሱ #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ ነው፡፡ ሲያዘጋጀውም ከተለያዩ ቅዱሳት መጻሕፍትና እንደ ቅዱስ ያሬድ ካሉ ሊቃውንት ድርሰቶች ኀይለ ቃላት ያላቸውንና ለጸሎት ተስማሚ የሆኑ ቃላትን እንደ ንብ ቀስሞ ነው ያዘጋጀው፡፡ ፠ ቅዱሱ ያዘጋጀውም በመጽሐፈ ሰዐታት ድርሰቱ ላይ በስተመጨረሻ ከኪዳን በፊት እንዲደረስ አድርጎ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ከዓመት እስከ ዓመት በየዕለቱ ኪዳን በሚደርስባቸው ማንኛውም የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክንና ገዳማት ‹‹የመሐረነ አብ ጸሎት››ም ከኪዳን በፊት ይደርሳል፡፡ ፠ የመሐረነ አብ ጸሎት ከኪዳን በፊት ብቻ ሳይሆን፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከመጀመሩ በፊት በዋይዜማው የሚደርስ፣ ለግል ጸሎት፣ ረሃብ ጦርነት፥ አባር ቸነፈር፥ ተስሕቦና ወረረሽኝ በሽታ እና የተለያዩ ችግሮች በመጡ ወቅት የሚደረስ ሲሆን ከእግዚኦታ ጋር አብሮ ስለሚባልም ‹‹የምሕላ ጸሎት›› በመባልም ይጠራል፡፡ ፠ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ በ14ኛው ክፍለ ዘመን ‹‹መሐረነ አብ››ን ከደረሰው በኋላ የተነሡ ቅዱሳንንና አባ ጊዮርጊስ ያላካተታቸውን በየጊዜው የተነሡ ሊቃውንት አካትተውታል፤ (ነገር ግን ሊቃውንቱ አሻሽለው ያዘጋጁት‹‹የመሐረነ አብ›› ጸሎት የሚደርሰው በታላላቅ ገዳማትና አድባራት ነው፡፡ ፠ የጸሎቱ አደራረስም በመሪና በተመሪ (በቀኝና በግራ) በተራ ስለሆነ በጋራ የሚጸለይና ዜማው የሚመስጥ፤ የቃሉ አሰዳደርም የሚያስደንቅ፤ የያዘው ኀይለ ቃል እንባን የሚያስነባ ነው፡፡ በተለይም በገዳም ያሉ አባቶች በጋራ(በማኅበር)ና በግል ጸሎት ዕለት ዕለት ያደርሱታል፡፡ ፠ በቤተክርስቲያናችን በተከሰተው ምክንያት የነነዌን ጾም እስመልክቶ በቅዱስ ሲኖዶስ(ከጥር 29 - የካቲት 1 ) ድረስ ጸሎት እንዲደረግ ባስተላለፈው ጥሪ መሠረት፤ ቤተ ክርስቲያናችንም ዘወትር ጠዋት እና ማታ የመሐረነ አብ ጸሎት ከዛቴ ጀመሮ እያደረሰች ትገኛለች፡፡ ፠እኛም በመደበኛ የሚጸለየውን ‹‹የመሐረነ አብ›› ጸሎት በግእዝና በአማርኛ አዘጋጅተንላችኋል፡፡ እንዲኁም በኦሮሚፋ ይዘንላችኁ ቀርበናል ፡፡ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com

በቅዱስ ሲኖዶስ በወጣው መመርያ መሠረት ሥርዓተ ጸሎቱ (ምሕላው) በደብራችን ተዠምሯል። #ኢንፈርህ_ሞተ ሞትን አንፈራውም

በኦሮምያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔና አካባቢው; በጅማ በምሥራቅ አርሲ አሰላ በምዕራብ ሐረርጌ ጭሮ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ አዲስ አበባ አዋሳኝ ከተሞች በሃይማንታቸው ምክንያት በእሥር ላይ የሚገኙ ምእመናን ምግብና ውሃ እንዳያገኙ ተደርገዋል። ++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ "ሕገ ወጡን ቡድን በሃይማኖት አባትነት ተቀበሉ በነፍሳችሁ ላይ ሹሟቸው" በሚል በኦሮምያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔና አካባቢው; በጅማ በምሥራቅ አርሲ አሰላ በምዕራብ ሐረርጌ ጭሮ የሃይማኖት አባቶቻችን; የወረዳ ሊቃነ ካህናት; የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች የሰበካ ጉባኤ አመራሮች ሰባክያንና ዲያቆናት እንዲሁም ወጣቶች በሃይማንኖቸው ምክንያት በጸጥታ ኃይሎች እየታደኑና እየታፈሱ በእሥር ላይ ይገኛሉ። ከየአህጉረ ስብከቱ በሚደርሱን መረጃዎች ምእመናን ምግብና ውሃ እንዳያገኙ ተደርገዋል። በሀገራችን ሕገ መንግሥትና ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች በሕግ ጥላ ሥር የሚገኙ ዜጎች ሕጋዊ መብታቸው ሊጠበቅ ይገባል። አስተያየት ሰጪዎች ከሕግ ውጪ በቤተመቅደሳቸው ደጃፍ የተገደሉብን ኃዘን ሳያንስ የሃይማኖት አባቶቻችንና ቤተሰቦቻችን በግፍ ታሥረውብናል ሲሉ አስተያየት ሰጥተውናል። የሰብአዊ መብት ኮሚሽንና የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ኃላፊዎችን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። EOTC TV +++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

በኮምቦልቻ ከተማ ሕገ ወጡ ደም አፍሳሽ ቡድን ወደ ከሚሴ ለማምራት ገብቷል የሚል መረጃ በከተማው በመሰራጨቱ ከፍተኛ የሆነ የህዝ ቁጣ ቀስቅሷል! ሕገ ወጡ ቡድን ወደ ከሚሴ ለማምራት በኮምቦልቻ አየር ማረፊያ በከሰአት በረራ ከተማው ውስጥ ገብተዋል የሚል መረጃ በከተማዋ በመሰራጨቱ የአብያተ ክርስቲያናት ደውል በከተማዋ ተደውለዋል። ተሚማ ጉዳዩን ለማጣራት ባደረገችው ጥረት በከተማዋ በከሰአት በረራ የገቡት የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት ባለ ስልጣናት እንደሆኑ ማረጋገጥ ቢቻልም ነገር ግን የቤተ ክርስቲያኗን ልብስ አውልቀው ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው ገብተዋል የሚል ስጋት በመፈጠሩ የከተማዋ ነዋሪ በቁጣ ወደ አደበባዮች እና ወደ አብያተ ክርስቲያናት ወጥቷል። በአሁን ሰአት በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ጸሎት እና ትምህርተ ወንጌል እየተሰጠ ይገኛል።

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ እና ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በትናንትናው ዕለት በጸጥታ ኃይሎች በተወሰደው እርምጃ የተጎዱ ምእመናንን ጎብኙ። ጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ እና ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በትናንትናው ዕለት በጸጥታ ኃይሎች በተወሰደው እርምጃ የተጎዱ ምእመናንን ጎብኙ። ጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) ++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ የሻሸመኔ ኦርቶዶክሳውያን በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሰረት የሕገ ወጡን ቡድን ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አናስገባም በማለት ቅጽራቸውን ሲጠብቁ ቢውሉም ለሕገ ወጡ ቡድን ከለላ የሰጠው የጸጥታ ኃይል በንጹሃን ላይ እርምጃ መውሰዱ ይታወቃል። በዚህም ሰማዕትነትን የተቀበሉ ምእመናን እንዳሉ ሁሉ በርካቶች ከፍታኛ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሐዋሳ የተለያዩ ሆስፒታሎች ተወስደዋል። እስካሁን ባለን መረጃም በሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል 6፣ በያኔት ሆስፒታል፣ በአላቲዮን ሆስፒታል 8 ምእመናን ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛሉ። የሲዳማ፣ ጌዲዮ፣ አማሮ፣ ቡርጂና ምዕራብ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ እና ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የጆርጂያና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እነዚህን ምእመናን በሐዋሳ በመገኘት አጽናንተዋል፤ ሀዘናቸውንም ገልጸዋል ሲል የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ዘግቧል።

በኦሮሚያ ያለችውን ቤተ ክርስቲያን በኃይል እየተቆጣጠረ የሚገኘው ሽብርተኛውና ወራሪው ስብስብ በሻሸመኔ ከተማ 35 ምዕመናንን በከባድ መሳሪያ በማስጨፍጨፍ በዛሬው ዕለት ወደ ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመግባት ፎቶ የመነሳት መርሐግብር ማካሄዱን ለመገንዘብ ተችሏል ! በምዕራብ አርሲና በሌሎች አካባቢዎች በየአብያተ ክርስቲያናቱ ፎቶ ትነሱ ይሆናል እንጂ ያስጨፈጨፋችሁት እና የልጆቹን ደም ረግጣችሁ በመግባት የቀለዳችሁበት ኦርቶዶክሳዊ ምዕመን የደረሰበትን ሰቆቃ መቼውንም አይረሳውም ! ለሕግ የበላይነት በእጅጉ እቆረቆራለሁ የሚለው የኢትዮጵያ መንግስት ሽብርተኞችን እና ወራሪዎችን መደገፍ ሊያቆም ይገባል !