cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

World Media

world media

إظهار المزيد
السويد884لم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
181
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ትምህርት ቤቶችን ዳግም መክፈት በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ! የ8ኛና የ12 ክፍል መልቀቂያ ፈተናዎችን በተመለከተ፡- - የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሕዳር 22 እና 23 ቀን 2013 ዓ.ም ይሰጣል ተብሏል፡፡ - የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሕዳር 28 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ይሰጣል ተብሏል፡፡ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለመክፈት በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ መሰረት፡- - በገጠር ወረዳ እና ቀበሌ ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት እንዲጀምሩ - በሁሉም የዞን እና የክልል ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት እንዲጀምሩ - በአዲስ አበባና በፊንፊኔ ዙሪያ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችም ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት እንዲጀምሩ የውሳኔ ምክረ ሀሳብ ቀርቧል። Readmore @world7INFORMATION
إظهار الكل...
ዩኒቨርሲቲዎች እንዴት ተማሪዎችን ይጠራሉ ? (ከMoSHE ያገኘነው ተጨማሪ መረጃ) - ዩኒቨርሲቲዎች እስከ መስከረም 25 ደረስ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን /ዝግጅት ማድረጋቸውን/ ለMoSHE ያሳውቃሉ። - ከዚህ በመቀጠልም የዩኒቨርስቲዎችን ዝግጁነት የሚያረጋግጠው ግብረ-ኃይል በዩኒቨርስቲዎቹ በአካል በመገኘት ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን ይመለከታል /ያረጋግጣል/። - ግብረ ኃይሉ ጤና ሚኒስቴር ባወጣው ፕሮቶኮል መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች ዝግጁ መሆናቸውን ካረጋገጠ በኃላ ተማሪዎቻቸውን እንዲጠሩ ፍቃድ ይሰጣል። - ይህ ማለት ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በአንድ ቀን/በተመሳሳይ ጊዜ ተማሪዎቻቸውን አይጠሩም፤ እንደየ ዝግጅታቸው ተረጋግጦ ተማሪዎችን ለመቀበል ፍቃድ ሲሰጣቸው ብቻ ይጠራሉ። - ቅድሚያ የሚሰጣቸው የ2012 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎች ሲሆኑ ሌሎች ተማሪዎች ደግሞ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ጥሪ ይደረግላቸዋል። @world7INFORMATION
إظهار الكل...
إظهار الكل...
TIKVAH-ETH

ችሎት! የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከትላንት በስቲያ ለአቶ ልደቱ አያሌው የፈቀደው የ100,000 ብር የዋስትና ፈቃድ መታገዱን ኤፍ ቢ ሲ (FBC) ዘገበ። ዋስትናውን ያገደው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ሸዋ ተዘዋዋሪ ምድብ ችሎት ነው፡፡ እግዱ በአዳማ ፍትህ ቢሮ አቃቤ ህግ ዋስትናው ላይ ይግባኝ ተብሎ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ያስቀርባል ሲል ዋስትናውን በማገድ መስከረም 19 በቀጠሯቸው እንዲቀርቡ አዟል፡፡ @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ለአቶ ልደቱ አያሌው የተፈቀደው የ100 ሺህ ብር የዋስትና ፈቃድ ታገደ፡፡ ዋስትናውን ያገደው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ሸዋ ተዘዋዋሪ ምድብ ችሎት ነው፡፡ እግዱም በአዳማ ፍትህ ቢሮ አቃቤ ህግ ዋስትናው ላይ ይግባኝ ተብሎ ሲሆን÷ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ያስቀርባል ሲል ዋስትናውን በማገድ መስከረም 19 በቀጠሯቸው እንዲቀርቡ አዟል፡፡ አቶ ልደቱ አያሌው ያልተፈቀደ የጦር መሳሪያ በመያዝ ወንጀል ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ (Fbc)
إظهار الكل...
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመክፈት የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡ የጤና ሚኒስትር የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች በመተግበር ትምህርት ቤቶችን መክፈት ይቻላል የሚል ምክረኃሳብ ማቅረቡን ተከትሎ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በጅማ ዩኒቨርስቲ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እየመከሩ ይገኛሉ፡፡ በውይይታቸው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች እንደሚመክሩና የዩኒቨርስቲዎች ትምህርትን መልሶ ለማስጀመር የተደረገ የዝግጅት ምዕራፍ ስራ ያለበት ደረጃ ገምግመው በአፋጣኝ መሰራት ያለባቸው ሁኔታዎች ላይ አቅጣጫ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡ በቆይታቸው ከዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ጋር በጋራና በጥልቀት በመወያየት ዩኒቨርስቲዎችን መልሶ መክፈት ላይ ስምምነት እንደሚደርሱ ተገልጿል፡፡
إظهار الكل...
#MOE የግል ትምህርት ቤቶች ምንም አይነት ተጨማሪ ክፍያ ማድረግ እንደማይችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል! የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ ከ ነሃሴ 20 ጀምሮ እንዲከናወን ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁን ተከትሎ ከተማሪዎች ምዝገባ እና ከትምህርት ክፍያ ጋር ተያይዞ ወላጆች ቅሬታን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ይህንንም ተከትሎ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን የትምህርት ቤት ምዝገባ ክፍያ መመሪያን ተላልፈው ምዝገባ እያከናወኑ ያሉ ትምህርት ቤቶች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እና ከመመሪያ ውጪ የሰበሰቡትን ገንዘብ ለወላጆች ተመላሽ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡ ሚኒስተር ዴኤታዋ አክለውም የ2013 የትምህርት ዘመን ምዝገባ ላይም ምንም አይነት የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል እና እንደሚያስጠይቅም ተናግረዋል፡፡ ትምህርት ቤቶችም ምዝገባ ሲያከናውኑ ከዚህ በፊት ይጠቀሙበት የነበረውን የክፍያ አቀባበል ዘዴ መቀየር የማይችሉ መሆኑን እና ከዚህ በፊት በነበረው የክፍያ ስርዓት መቀጠል እንዳለባቸውም ተገልጿል።፡ ከዚህም በተጨማሪ ትምህርት ቤቶች ከመደበኛ የትምህርት ክፍያ እና ከመመዝገቢያ ክፍያ ውጪ ሌሎች ተጨማሪ ክፍያ ማስከፈል ማይቻል መሆኑም ተነግሯል፡፡ የቀጣይ አመት ትምህርት የሚጀመርበትን ቀን በተመለከተም ሚኒስትር ዴኤታዋ ትምህርት ሚኒስቴር እስከሚያሳውቅ ድረስ ማንኛውም ትምህርት ቤት ትምህርት መጀመር እንደማይችል አስታውቀዋል፡፡ ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር
إظهار الكل...
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,545 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ የ17ሰዎች ህይወት አለፏል፡፡ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 18,778 የላብራቶሪ ምርመራ 1545 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡ባለፋት 24 ሰዓታት የ17 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 709 አድርሶታል። በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 534 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው የገገሙ ሰዎችን ቁጥር 15,796 አድርሶታል፡፡በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 43,688 ደርሷል፡፡ ምንጭ : ጤና ሚንስተር @ethio_mereja @ethio_merejabot
إظهار الكل...
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,638 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ፣ 16 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል! ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው 20,153 የላብራቶሪ ምርመራ 1,638 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪም 515 ሰዎች አገግመዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 40,671 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 678 ደርሷል፤ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 14,995 ደርሷል
إظهار الكل...
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 23,035 የላብራቶሪ ምርመራ 1,829 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 377 ሰዎች አገግመዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 37,665 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 637 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 13,913 ደርሷል።
إظهار الكل...