cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Saved by Grace️

ዓላማችን የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሣፍር ሠራተኛ ሆኖ የተፈነውን ራሳችንን ለእግዚአብሔር ማቅረብ ነው። ለአስተያየትዎ @biniamsol

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
893
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-47 أيام
-930 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

#ዛሬ_ከተማረኩት_በጥቂቱ ብዙ ጊዜ በመክብብ መጽሐፍ ዘገባ መሠረት በዚህ ዓለም መኖር ሕይወት ከንቱ እንደሆነች እንረዳለን ነገር ግን ችግሩ ከንቱ የምለውን ቃል በተረጎምንበት መሠረት ይመስለኛል ፣ #ከንቱ የምለው ቃል ጥቅም የሌለዉ ማለት ሳይሆን የማይጨበጥ ወይም መገመት የማንችለው እንደማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ፣ መክብብ መጽሐፍ ጨምሮ በዚህ ምድር ላይ ስንኖር በጣም ደስተኞች ሆነን እንድንኖር ያስተምረናል ፣ እንዲሁም መክብብ መጽሐፍ ዋናው መልዕክት ሕይወት አጭር መሆኗን እና እግዚአብሔር በሰጠን በዚህች አጭር ዕድሜ ተደስተን እንድንኖር ነው። እግዚአብሔር በሰጠን ነገር በመደሰት መኖር እግዚአብሔርን ያከብረዋል በተቃራኒው እየተጨነቅን የምንኖር ከሆነ እግዚአብሔርን ይበድለዋል ፣ ቃሉም እንደሚያስተምረን ሁሌም በጌታ ደስ ይበለን በመደሰት ሕይወታችን እንኑር። “ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ።” — ፊልጵስዩስ 4፥4 #መልካም_ሣምንት 🥰
إظهار الكل...
ጸሎት በጣም አስፈላጊ መሆኑን ያወኩት ኢየሱስ ዘውትር በመጸለዩ ነው ፣ ሁሉን የምችል አምላክ ዘውትር የሚጸልይ ከሆነ እኛ ደካማ ፍጥረታት ሳንጸልይ ሕይወታችን መምራታችን እጅግ የሚያስገርም ነው ፣ ያለ ጸሎት የሚመራው ሕይወታችን ትርጉም የሌለው መሆኑ ግልጽ ነው። እኛ ደካማ ስዎች በእግዚአብሔር ኃይል መኖር ከፈለግን ጸሎት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። እንዲህ እንዳልነው ፣ የ10 ደቂቃ ጸሎት ከዓመታት ማጉረምረም ይበልጣል።
إظهار الكل...
እግዚአብሔር ሉዓላዊ፣ በማንም የማይደገፍ ፈጣሪ እንደመሆኑ መጠን ማንንም የማዳን ግደታ አልነበረውም ፣ ኩነኔ ብቻ ለሚገባን ለእኛ ኃጢአተኞች ቸርነትን እና ምሕረትን የማሳየት ግዴታ የለበትም። ነገር ግን እግዚአብሔር #በምሕረቱ_ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ ምንም ኃጢአተኞች ብንሆንም እንኳን በክርስቶስ ሕይወትን ሰጥቶናል ፣ አሁንም በሕይወት የመኖራችን ምስጥር የእግዚአብሔር ምህረት ነው ፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ እንደሚል ፦ ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና( ሰቆ. 3፥22)።” እንዲሁም መዝሙረኛው እንዲሁ ብሎ እንደዘመረው" እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው፥ ከቍጣ የራቀ ምሕረቱም የበዛ።ሁልጊዜም አይቀሥፍም፥ ለዘላለምም አይቈጣም(መዝሙር 103፡8-9)"።
إظهار الكل...
ወንጌል ማለት ምን ማለት ነው? ወንጌል የምስራች ነው። ምክንያቱም እኔና አንተ እንደ ሰው ያለብንን ከባድ ችግር የሚመለከት ነው ፣ እና ችግሩ በቀላሉ ይህ ነው ፦ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው እርሱ ጻድቅ አምላክ ነው ፣ እና እኔ አይደለሁም። እና በህይወቴ መጨረሻ በጻድቅ እና በተቀደሰ አምላክ ፊት እቆማለሁ እና ይፈርድብኛል። እና የሚፈረድብኝ በራሴ ፅድቅ ወይም በራሴ ኃጢአት ነው ፣ ኃጢአተኛ በመሆነ መድረሻያ ሲኦል እንደምሆን እርግጥ ነው። የወንጌሉ መልካም ዜናው ኢየሱስ የኖረው ፍጹም ጽድቅ ሕይወት እና ፍጹም ለእግዚአብሔር መታዘዙ ለራሱ ደህንነት ሳይሆን ሕዝቡን ለማዳን ነው። ለራሴ ማድረግ የማልችለውን አድርጎልኛል። ነገር ግን ያን ፍጹም የመታዘዝ ሕይወት የኖረ ብቻ ሳይሆን፣ የእግዚአብሔርን ፍትሕና ጽድቅ ለማርካት ራሱን ፍጹም መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበ ነው። እናም እርሱን በማመኔ ለዘለዓለም በሲኦል ከመቃጠል ተርፍያለው ፣ የዘለዓለም ሕይወት ወራሽ ሆኛለሁ። እናንተም ብታምኑበት ከማናቸውም ኃጢአት ነጻ ያወጣችኃል ፣ ደግሞም የዘለዓለምን ሕይወት ይሰጣችኋል።
إظهار الكل...
እግዚአብሔር ታማኝ አምላክ ነው ፣ ለቃሉ እውነተኛ ነው ፣ በእርሱ ዘንድ ውሸት ወይም መለዋወጥ የለም። የእርሱ ታማኝነት ታማኝ እንድንሆን ሊያነሳሳን እና ሊያበረታታን ይገባል ፣ እናም እኛ ለእርሱ ከገባነው ቃል ይልቅ እርሱ በክርስቶስ በኩል ለእኛ በገባው ቃል ላይ መታመን አለብን። ምንም የዘገየ ቢመስልም እግዚአብሔር ለቃሉ ታማኝ ነው።
إظهار الكل...
#ምክር ምንም እንኳን ለመምከር የበቃሁ ባልሆንም በውስጤ ያለውን ትንሿን ነገር ላካፍላችሁ ፣ በሚቀጥሉት ቀናት የኢየሱስ ክርሰቶስ የስቅለት እና የትንሳኤ በዓል በአብዛኛው ክርስቲያኖች ዘንድ እንደሚከበር ሁላችንም እናውቃለን ፣ አንዳንድ ክርስቲያኖች ግን በየዋህነት ሆነ ባለማወቅ ይህንን በዓል በመቃወም ስቀርቡ ተመልክተናል ፣ እናም ለእነርሱ የማስተላልፈው መልዕክት እልከኛ ባለመሆን ከእኛ ጋር የጌታን ሞትና ትንሳኤ እንድታከብሩ ጥርዬን አቀርባለሁ ፣ እንዲሁም የበዓሉ ሐሳብ የጌታን ሞትና ትንሳኤ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ እናስብ ሳይሆን ፣ በየቀኑ እያሳብን በዓመት የተቸገሩትን እየረዳን በአንድነት እንድናስብ የምገልጽ ነው። ቢንያም ነኝ ጸጋ ይብዛላችሁ 🙏
إظهار الكل...
“ይቅር በለን፤ ... ይቅር እንደምንል” ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ኅብረት ኀጢአት ያበላሸዋል። ኹላችንም በደለኞች ነን። እግዚአብሔር ምሕረት ካላደረገለት በስተቀር ወደ እርሱ መቅረብ የሚችል ማንም የለም። “ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል? በቅድስናውስ ስፍራ ማን ይቆማል?” (መዝ. 24፥3)፤ እንዲሁም፥ ከመዓርግ መዝሙራት መካከል በአንዱ እንዲህ እናነባለን፤ “አቤቱ፥ ኀጢአትንስ ብትጠባበቅ፥ አቤቱ፥ ማን ይቆማል? ይቅርታ ከአንተ ዘንድ ነውና” (130፥3-4)። . ይቅር ማለትና ይቅርታ መለመን የዕለት እንጀራችንን ያህል ለመኖር የሚያስፈልገን ነገር ነው። ሰው በበደሉ የታሰረ ባለ ዕዳ ፍጡር ነው። ዕዳውን ልክፈለው ቢል፥ ሕይወቱም አይበቃው፤ የኀጢአት ደመወዝ ሞት ነውና። ሰው ምሕረት ያስፈልገዋል። እግዚአብሔርም፥ ወደ እርሱ በንስሓ ለሚመለሱ ምሕረት አድራጊ ነው። “በደላችንን ይቅር በለን” ብለን የምንጸልየው ለዚያ ነው። . ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረት ስንጠይቅ ታዲያ እኛም ሌሎችን ይቅር በማለት እንዲኾን የጌታችን ጸሎት ቀጣይ ክፍል ይህን አጽንዖት ይሰጣል። ተማጽኖው እንዲህ ነው የሚለው፤ “እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል፥ በደላችንን ይቅር በለን” … . ምሕረት በዋናነት አጽንዖት ሰጥቶ የሚያውጀው የእኛን የተቀባይነት ዋጋ ሳይኾን የክርስቶስ ኢየሱስን ግርማዊ ክብር ዋጋ ነው። እግዚአብሔር ኀጢአተኛውን በምሕረቱ ይቅር በሚልበት ጊዜ፥ የክርስቶስን የመልካም ሥራ ትሩፋት በሰማያት ሰሌዳ ላይ ይጽፈዋል እንደ ማለት ነው። እኛንም ከአሸናፊው የእግዚአብሔር በግ ጀርባ አሰልፎ በድል ነሺነት ይመራናል። ሰሎሞን አበበ
إظهار الكل...
መጽሐፍ ቅዱሳችን ዘግተን በእግዚአብሔር እናምናለን ብንል ሐሰተኛ እንሆናለን ፣ መጽሐፍ ቅዱስ "እምነት ከመስማት ነው ፣ መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው ይላል" የምናምነው ቃሉን ሰምተን ወይም አጥንተን ነው ፣ እናም መጽሐፍ ቅዱሳችንን እናምብብ በእግዚአብሔርም እንመን።
إظهار الكل...
ህይወት አጭር ናት ---- Life is short. ሞት እርግጥ ነው ---- Death is sure. ፍርድ እየመጣ ነው -----Judgment is coming. መንግሥተ ሰማያት የከበረች ናት ---- Heaven is glorious. ሲኦል አስፈሪ ነው ---- Hell is dreadful. ኢየሱስ አዳኝ ነው ---- Jesus is Savior. ስቲቭ ላውሰን
إظهار الكل...
“እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።”   — 1ኛ ጴጥሮስ 5፥7 “ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።”   — ፊልጵስዩስ 4፥6
إظهار الكل...