cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Inspire Ethiopia ✊

የተግባር ሰው እንሁን! 🛑 advice contact me 👉 @natanim_27

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
3 076
المشتركون
-424 ساعات
-107 أيام
-5130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

በፍጹም አታቁም! “አንድ ጊዜ ነገሮችን በቀላሉ የማቆም ልምምድ ከጀመርክ ሁኔታው ልማድ ይሆንብሃል” - Vince Lombardi በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ! ጠቃሚና ዋጋ ያለው ግብን የምትከታተል ከሆነ፣ የሆነ ጊዜ ላይ ከዚህ በታች ያሉትን ሃሳቦች ማስተናገድህ አይቀርም፡ • “ይህ ነገር ካሰብኩት በላይ ከባድ ነው፡፡” • “ለምንድን ነው ይህ ነገር ይህን ያህል ረጅም ጊዜ የወሰደብኝ?” • “ይህ ነገር ወደፊት አላራምድ አለኝ፡፡” • “ይህ ግብ ደጋግሞ እየተበላሸብኝ ነው፡፡” • “ይህንን ነገር መቀጠል የምችል አይመስለኝም፡፡ ምን አስቤ ነው የጀመርኩት?” በእዚህና በመሰል ስሜቶች ከጀመርከው ነገር እንዳትገታ ከፈለክ “በፍጹም አላቆምም” የሚልን አመለካከት አዳብር፡፡ ተስፋ አለመቁረጥ የአመለካከት ጉዳይ ነው፡፡ ይህም አመለካከት ልታዳብረው የምትችለው አመለካከት ነው፡፡ ይህንን አመለካከት ለማዳበር ከሚረዱህ ልምምዶች መካከል የሚከተሉትን ሃሳቦች ደግመህና ደጋግመህ ለራስህ መናገር ነው፡- • ነገሮች ሲከብዱብኝ በዓላማዬ ጸንቼ እቀጥላለሁ፡፡ • መንገድን እፈልጋለሁ ወይም እፈጥራለሁ፡፡ • ማንኛውም ችግር መፍትሄ አለው፣ እኔ ደግሞ መፍትሄውን ለማግኘት ብቃቱ አለኝ፡፡ • በየቀኑ የሚሰራውንና የማይሰራውን የመለየትን እውቀትና ግንዛቤ እያገኘሁ ነው፣ ይህም ማለት በጥንካሬና በጥበብ እየጨመርኩኝ ነው ማለት ነው፡፡ • መሰናክሎች ጊዜያዊ ናቸው፡፡ ከላይ ያሉትን ሃሳቦች ለራስህ ከተናገርክ በኋላ ቆም ብለህ አስብ! እንደገናም ወደፊት ቀጥል! (“ጀምሮ መጨረስ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)
إظهار الكل...
👍 8👎 1
ሕልሜን ላጫውታችሁ አንድን ሕልም አለምኩ፡፡ አንድን በአለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ተፈላጊነት ያለውን ጥበበኛ አዛውንት ያገኘሁት ይመስለኛል፡፡ ይህ ጥበበኛ ሰው ምንም አይነት ጥያቄ ከብዶት አያውም፣ ለማንኛውም አይነት አስቸጋሪ ሁኔታ መፍትሄ በመስጠት የታወቀ ነው፡፡ ለዚህም ነው ሰዎች ቢያንስ ከአንድ አመት በፊት ቀጠሮ በማስያዝ ከአለም ዙሪያ ወደእርሱ የሚመጡት፡፡ ጠቢቡ አስተርጓሚ አያስፈልገውም፡፡ የአለምን ሁሉ ቋንቋ ጥንቅቅ አድርጎ ያውቃል፡፡ ፈገግተኛ፣ የደስ ደስ ያለውና ከአጠገቡ መለየትን የማያስመኝ መረጋጋት ያለው ሰው ነው፡፡ እንዴት እንደሆነ ባላውቀውም ካለምንም ቀጠሮ ለብቻዬ ጠቢቡን የማግኘት እድል ያገኘሁ ይመስለኛል - በሕልሜ፡፡ ሁኔታው ድንገተኛ ስለሆነብኝ ይመስለኛል፣ ምንም እንኳን ጊዜ ቢሰጠኝ ብዙ የምጠይቃቸው ጥያቄዎች ቢኖሩኝም የምለውን አጣሁ፡፡ ሰዎች ከአለም ዙሪያ በብዙ ትግል የሚያገኙትን ይህንን ጠቢብ የማግኘት እድል አግኝቼ ምንም ነገር ሳላገኝ ሄጄ በኋላ እንዳይጸጽተኝ የመጣልኝን ሁሉ ለመጠየቅ ወሰንኩ፡፡ እንዲህ ስል ጠየኩት፣ “ሰዎች ወደአንተ ይዘው ለሚመጡት ጥያቄ በሙሉ ለመፍትሄ የሚሆንን ምክር የመለገስ ጥበብ እንዳለህ ዝናህን ሰምቻለሁ፡፡ እስቲ እስካሁን ድረስ ለመምከር ወይም መፍትሄ ለመስጠት ከባድ ሆኖ ያገኘኸውን ቀንደኛ ሁኔታ ንገረኝ” አልኩት፡፡ አንዴ እኔን፣ አንድ ጊዜ ደግሞ መሬት መሬት ከቃኘ በኋላ፣ እንደገና ወደ እኔ ከዚያም ልክ አንድ አዲስ ሃሳብ ሰማዩ ላይ የሚያነብ እስኪመስልበት ድረስ ወደላይ ከተመለከተ በኋላ እንዲህ አለኝ፡- “ፈጣሪ አድሎኝ ለብዙ ሰዎች መፍትሄ የሚሆኑ ምክሮች የመለገስ ብቃት አለኝ፡፡ በዚህም ደስተኛ ነኝ፡፡ ምክር ፍለጋ ወደእኔ የሚመጡት በአብዛኛው በወጣትነትና በመካከለኛው የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ናቸው፡፡ እስካሁን ድረስ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን አማክሬአለሁ፡፡ እስካሁን የሰጠኸኝ ምክር አልሰራልኝም በማለት የተመለሰ ሰው አላጋጠመኝም፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ሁለት ነው፡፡ አንደኛው በወጣትና በጎልማሳ እድሜአቸው ላይ የሚገኙት ሰዎች ምክሩን ተግባራዊ አድርገው መፍትሄ በማግኘታቸው ምክንያት ወደ እኔ አይመለሱም፡፡ ከዚህ ለየት የሚለው ሁኔታ ግን እንደ እኔ እድሜያቸው እጅግ የገፋ አዛውንቶች ይዘው የሚመጡት ጥያቄ ነው፡፡ የእነዚህ ሰዎች ጥያቄ በአብዛኛው የጸጸት ጥያቄ ነው፡፡” ጠቢቡ ንግግሩን ቀጠለ፡- “ያሳለፏቸውን አመታቶቻቸው መቼ መጥተው መቼ እንደሄዱ ማሰብ እስከሚያስቸግራቸው ድረስ ግር የሚላቸው አዛውንት ጥቂት አይደሉም፡፡ አሁን መለስ ብለው ሲያስቡት ሕይወታቸውን ወደማይፈልጉበት አቅጣጫ እንዲሄድ ያደረገውንና አሁን የሚጸጸቱበትን ውጤት ያስከተለባቸውን የመነሻ ችግር በሚገባ ያውቁታል፡፡ በወቅቱ እርምጃ ወስደው ሊያርሟቸው የሚገቡ ቀላል የሚመስሉ ሁኔታዎች ዛሬ ምንም ቢጸጸቱ እንኳን ሊቀለብሱት የማችሉትን ሰበብ አጠራቅሞ አገኙት፡፡” ጠቢቡ ፍላጎቴን አይቶ የኋላ ኋላ እንዳልጸጸት ምን ማድረግ እንዳለብኝ ምክርን ለገሰኝ፡፡ የሰጠኝ ምክሮች ከብዙ አዛውንት የጸጸት ሁኔታ በመነሳት በብዙ ሰዎች የሚንጸባረቁትን የጸጸት መንስኤዎች በመጭመቅ እንደሆነ ገምቻለሁ፡፡ ወዲያውኑ ከእንቅልፌ ባነንኩኝና ሳልረሳቸው ጠቢቡ በምክሩ የጠቆመኝን የሚከተሉትን መመሪያዎች መዘገብኳቸው፡፡ 1. “ሁል ጊዜ አንተው ያመንክበትን ሕይወት መኖርህን እርግጠኛ ሁን፡፡” 2. “ልክህን እወቅ፣ ለስራህና ለሕይወትህ መርህና ገደብ ይኑርህ፡፡” 3. “ማንነትህን፣ ኑሮህንም ሆነ የሰራሃቸውን ስህተቶች አሻሽላቸው እንጂ አትፈርባቸው፡፡” 4. “ከወዳጆችህ ጋር ነጻ የሆነን ግንኙነት መስርት፣ ግልጽነትና የቀረበ ወዳጅነት ቢጎዳህም ከጉዳቱ ጥቅሙ ይበልጣልና በፍጹም አትሽሽ፡፡” 5. በመጨረሻ፣ ሁል ጊዜ ደስተኛ መሆንን ምረጥ፡፡ የሕይወት ቀንደኛ ዓላማዎች ከሚባሉት ውጤቶች መካከል ደስተኛነት አንዱ ነውና፡፡ (“የሕይወት ጸጸቶች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ) @inspire_ethiopia4 @inspire_ethiopia4 #Dreyob #dehna_sew #dehna_sew inspire_ethiopia4
إظهار الكل...
👍 11 3
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች! እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳች !
إظهار الكل...
👍 11 3🥰 1
መፍራትን አትፍራው! እንደ ፍርሃት፣ ድንጋጤና ስጋት አይነት ስሜቶች ሰው ከአደጋ እንዲጠነቀቅ ከፈጣሪው የተሰጡ ስጦታዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ስሜቶች በአግባቡ ልንጠቀምባቸውና ከአደጋ ልንጠበቅባቸው ሲገባን ለአንዳንድ ሰዎች የኑሮ ዘይቤ ሆነዋል፡፡ የመውደቅ ፍርሃት፣ የመክሰር ፍርሃት፣ ያለመወደድ ፍርሃት፣ ብቻ የመቅረት ፍርሃት፣ … ጣጣችን ብዙ ነው፡፡ በፍርሃት ስንወረስ፣ ሕይወታችንን በራእይ መምራት እናቆምና ለፍርሃት ምላሽ በመስጠት መምራት እንጀምራለን፡፡ ከአንዱ ራእይ ወደሌላኛው በማለፍ ሕይወትን “ልናጠቃት” ሲገባን የመጣው ሁሉ የኑሮ ገጠመኝ የሚያጠቃን ቋሚ ኢላማዎች እንሆናለን፡፡ ቆመን ለመጣው ወይም የመጣ ለመሰለን ጥቃት ምላሽ በመስጠት ጊዜአችንን እናባክናለን፡፡ ይህ ሲሆን የቆመ ኢላማ ሆንን ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው ከአንዱ ግብ ወደሌላኛው በአላማ የምንንቀሳቀስ ሰዎች ስንሆን አይኖቻችን ከችግሩ ላይ ይነሱና መፍትሄው ላይ ማረፍ ይጀምራሉ፡፡ የፍርሃትህ ጥልቀት አእምሮህ የፈቀደለት ያህል ነው” - Unknown Source ፍርሃት በሕይወትህ ብቅ ጥልቅ ማለቱ አያስፈራህ፡፡ በዚያ ፍርሃት ምክንያት ግን መንቀሳቀስ እስኪያቅትህ ድረስ እንዳትታሰር ፍራ፡፡ ማንኛውም ሁኔታ አንተን የማስፈራራት ሙከራ የማድረግ ሙሉ መብት አለው፡፡ አንተ ካልፈቀድክለት ግን ሊያስፈራራህ አይችልም፡፡ ትፈራለህ፣ ፈሪ ግን አይደለህም፡፡ “በፍጹም አልፈራም” ብለህ ካሰብክና ከተናገርክ ከፍርሃት የተደበቅህ ሰው እንደሆንክ አመልካች ነው፡፡ በሌላ አባባል፣ የፍርሃት ስሜት እንዳይመጣ መከልከል አትችልም፣ ይህንን ስሜት ለማስተናገድ የተፈጠረ ማንነት ስላለህ፡፡ ሆኖም፣ የፍርሃትን ጥልቀትና በአንተ ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ጉዳት የመወሰን ሙሉ መብትም ሆነ ብቃት አለህ፡፡ #dehna_sew
إظهار الكل...
👍 9 1
Photo unavailableShow in Telegram
ላላገቡ . . . ልጅ፡- “እማዬ፣ ሃብታም ሰው ባገባ ይሻላል ወይስ ቆንጆ ሰው ባገባ ይሻላል?” እናት፡- “ልጄ፣ እውነተኛ ሰው አግቢ
إظهار الكل...
👍 2 2
ጥገኝነት ጥገኝት ማለት በራሳችን ለመቆም ካለመቻላችን ወይም ካለመፈለጋችን የተነሳ በሰዎች ላይ ተደግፈን ስንኖር ማለት ነው፡፡ ለጊዜውና አንድን አስቸጋሪ ሁኔታ እሰከምናልፍ ድረስ በሰው ላይ ጥገኛ መሆን ችግር የሌለውናሁሉም ሰው የሚልፍበት የሕይወት እውነታ ነው፡፡ ነገር ግን ጥገኛ የምንሆንባቸውን ሁኔታዎች መለየት፣ ለምን በሰዎች ላይ ጥገኛ ለመሆን እንደተገደድን መገንዘብና እስከመቼ በዚህ ሁኔታ እንደምንኖር አስበንበት ከሁኔታው የመላቀቅ እቅድ ማውጣት አስፈላጊ ነው፡፡ የሰው ጥገኛ ሆኖ በራሱ ላይ ያለውን ግምት ትክክለኛና ሚዛናዊ አድርጎ ለማቆየት የሚችል ሰው ማግኘት ያስቸግራል፡፡ ጥገኝነት በራሳችን ላይ ያለንን ግምት ስለሚያወርደው ማለት ነው፡፡ ጥገኝነት መራራ ያደርገናል፣ እኛን ለሚጎዱ ሰዎች አጋልጦ ይሰጠናል፣ የራሳች የሆነ ነገር እንድንገነባ አይፈቅድልንም፡፡ ከላይ እንደጠቀስነው አንዳንድ ጊዜ ምንም እንኳን ካለንበት አስቸጋሪ ሁኔታ የተነሳ ለተወሰነ ጊዜ የሰው ጥገኛ ብንሆንም ከዚያ የመውጣት ፍላጎቱ፣ እቅዱና ጥረቱ ሲኖረው ውስጣችንን ጠንካራ ያደርገዋል፡፡ ሁል ጊዜ ልንሰራባቸው የሚገቡን የጥገኝነት አይነቶች፡- 1. የገንዘብ ጥገኝነት፡- ራስን ችሎ ለመኖር ካለመፈለግ ወይም ካለመቻል ራስን ወደመቻል ለመሻጋገር እንስራ፡፡ 2. የስሜት ጥገኝነት፡- በሰዎች ላይ የስሜት ጥገኛ ከመሆናችን የተነሳ እንደ እነሱ ወቅታዊ ሁኔታ የሚዘባረቀውን ስሜታችን በማስተካከል የራሳችን ስሜት የምንቆጣጠረው ራሳችን ወደመሆን እንደግ፡፡ 3. የእውቀት ጥገኝነት፡- ሁልጊዜ ሰዎችን በመጠየቅና ከእነሱ በምናገኘው መልስ ላይ ብቻ በመደገፍ ከመኖር በራሳችን እውቀትን ወደመቅሰምና በእውቀት ወደመሻሻል ደረጃ ለመድረስ እንስራ፡፡ @inspire_ethiopia4 #dehna_sew#inspire_ethiopia
إظهار الكل...
👍 8
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ። ዒድ ሙባረክ ! በዓሉ #የሰላም፣ #የአንድነት፣ #የፍቅርና #የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።
إظهار الكل...
9👍 5
“ከዛሬ ሃያ አመት በኋላ ይበልጥ የምትበሳጨው ባደረካቸው ነገሮች ሳይሆን ሳታደርጋቸው በቀረሀቸው ነገሮች ነው፡፡ ስለዚህ ከፊትህ የተጋረጡትን ሳንካዎች አንሳና ወርውራቸው፡፡ ከተረጋጋው ወደብ ተነስተህ ቅዘፍ፡፡ የምስራቁን ነፋስ በመርከብ ሸራህ ተቆጣጠረው፡፡ አስስ ፤ አልም ፤ እናም አግኝ፡፡”                    -  ማርክ ትዌን 📚 #Bemnet_Library
إظهار الكل...
👍 19 6👎 1🔥 1
ሀጥያቴን ሳትመለከት በይቅርታህ ሸፍነህ ዛሬን ያነጋህልኝ ምነኛ ትወደኛለህ??? - ምን ላድርግልህ ? ምንስ አለኝና ምን ላደርግልህ እችላለሁ? - ተመስገን ብቻ ነው!!! ተመስገን! ተመሰገን! 🙏
إظهار الكل...
32🙏 9
ባለው ያልጀመረ ቢኖረው አይሰራም። አሁን ባለህ ስልክ 📲ጀምር አሁን ባለህ እውቀት📚 ጀምር አሁን ባለህ ጊዜ⏰ ጀምር አሁን ባለህ ገንዘብ 💵 ጀምር አሁን ባለህ ሰው👨‍👨‍👧‍👦 ጀምር አሁን ባለህ እምነት ጀምር... በቃ አሁን ባለህ ነገር ጀምር... . አትጠብቅ! . ጀምር!!! 👉 @inspire_ethiopia4
إظهار الكل...
👍 29🙏 3 1