ar
Feedback
ኮሮጆ bags 💼 & Gift shop 🎁

ኮሮጆ bags 💼 & Gift shop 🎁

الذهاب إلى القناة على Telegram

👉plexiglass 👉engraving 👉orginal cosmotics 👉 natural face products like Kesil 👉Gift packages 📞0942410512 metis_bag 🏠🏠 Megenagna 3M Mall 1st floor

إظهار المزيد
1 896
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-47 أيام
-2830 أيام
أرشيف المشاركات
በዐማራ ክልል ለግማሽ ሚሊዮን ሴቶች ከመጋቢት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የማኅፀን በር ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት ይሠጣል። ዕድሜያቸው 14 ዓመት የሞላቸውና ከስድስት ወራት በፊት የመጀመሪያውን ዙር ክትባት የወሰዱትንም ያጠቃልላል። አብክመ ጤና ቢሮ

ፆም ከ ሀይማኖታዊ ስርዓት ባለፈ በርካታ የጤና ጥቅሞች አሉት ሼር ያድርጉ የመጾም 8 ጥቅሞች እነሆ፡- ➊ ስብን ለማቃጠል እና ክብደት ለመቀነስ ➋ ዝቅተኛ የኢንሱሊን ደረጃ እንዲኖር ያደርጋል ➌ የእ
ፆም ከ ሀይማኖታዊ ስርዓት ባለፈ በርካታ የጤና ጥቅሞች አሉት ሼር ያድርጉ የመጾም 8 ጥቅሞች እነሆ፡- ➊ ስብን ለማቃጠል እና ክብደት ለመቀነስ ➋ ዝቅተኛ የኢንሱሊን ደረጃ እንዲኖር ያደርጋል ➌ የእድገት ሆርሞንን ይጨምራል ➍ የደም ግፊትን ያስተካክላል ➎ የተጎዱ ህዋሳትን ይጠግናል ➏ ሜታቦሊዝምን ይጨምራል ➐ ፀረ-እርጅና ➑ የበሽታ ተጋላጭነትን ይቀንሳል ለሶስት ቀናት ያህል መጾም ሴሎች አዲስ ነጭ የደም ሴሎችን እንደገና እንዲያድሱ ያነሳሳቸዋል።ይህም መላውን በሽታ የመከላከል ስርዓት ያድሳል። በተጨማሪ በየሳምንቱ ቢያንስ ለአንድ ወይም ለሁለት ቀናት መጾም አእምሮን ከአልዛይመርስ፣ ፓርኪንሰንስ እና ከሌሎች በሽታዎች ሊከላከል ይችላል።

የልብ ድካም ማስጠንቀቂያ ምልክቶች 1.ድካም፦ ከተለመደው የተለየ ድካም መሰማት፤ ልብ ሰውነት እና አንጎል የሚፈልገውን በቂ ኦክሲጅን ባለማድረሱ የሚከሰት ምልክት ነዉ። 2. የእንቅስቃሴ ገደብ፦ብዙውን
የልብ ድካም ማስጠንቀቂያ ምልክቶች 1.ድካም፦ ከተለመደው የተለየ ድካም መሰማት፤ ልብ ሰውነት እና አንጎል የሚፈልገውን በቂ ኦክሲጅን ባለማድረሱ የሚከሰት ምልክት ነዉ። 2. የእንቅስቃሴ ገደብ፦ብዙውን ጊዜ የልብ ድካም ያለባቸው ሰዎች በቀላሉ ስለሚደክሙ እና የትንፋሽ እጥረት ስለሚሰማቸው መደበኛ ተግባራቸውን ማከናወን አይችሉም። ይህ ከ 60 ዓመት እድሜ በኋላ በሰዎች ላይ በጣም ስለሚከሰት ይህንን የማስጠንቀቂያ ምልክት በማሰናከል "እርጅና" እንደሆነ ያስባሉ። 3.ሰዉነት ማበጥ ( ኤድማ)፦ ጥቅም ላይ የዋለው ደም ከታችኛው ዳርቻ ወደ ላይ እንዲመለስ ለማስገደድ ልብ በቂ የፓምፕ ሃይል ከሌለው ፈሳሽ በቁርጭምጭሚት ፣ እግሮች ፣ ጭኖች እና ሆድ ውስጥ ሊሰበሰብ ይችላል። ከመጠን በላይ ፈሳሽ በውሃ ክብደት መልክ ፈጣን ክብደት እንዲጨምር ሊያደርግ ይችላል። 4.የትንፋሽ እጥረት፦በሳምባ ውስጥ ያለው ፈሳሽ ጥቅም ላይ የዋለውን ካርቦን ዳይኦክሳይድ ወደ አዲስ ኦክሲጅን ለመለወጥ አስቸጋሪ ያደርገዋል። በእንቅስቃሴ ላይ ብቻ ሳይሆን ተቀምጦም ሆነ ተኝቶ መተንፈስ ከባድ ይሆናል። ከእነዚህ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች አንዱን ስለተሰማዎ፣ የልብ ድካም አለቦት ማለት አይደለም። ነገር ግን 2 ወይም ከዚያ በላይ ከሆኑ ዶክተር ጋር መሄድ አለብዎት። ለበለጠ ጤና መረጃ የቴሌግራም ቻላናችንን እንሆ👇👇👇 https://t.me/+6X9O71L_Vu1iY2Y0

#ትዳር##ወሲብ( + 18 ) በግልፅነት በጨዋነት እንወያይ #መረጃ #ሼር #ብናደረግ #ትዉልድ #እናስተምራለን ከጋብቻ በኋላ ወሲብ ለብዙዎች ቀዝቃዛ ወላፈን ነው። የጋብቻ ቀለበት አጠለቃችሁ ማለት ወሲብን ልጅ ለመውለድ ብቻ ተጠቀሙበት ማለት አይደለም። ከጋብቻ በፊት በቀን ሦስት፣ አራት ጊዜ ሲደረግ የነበረው ወሲብ፤ ከጋብቻ በኋላ በቀን አንዴ፣ በሳምንት ሁልቴ፣ በሁለት ሳምንት አንዴ፣ በወር አንዴ፣ በስድስት ወር አንዴ፣ በአመት አንዴ እያለ ደብዛው ይጠፋል። የልጆች ኃላፊነትና ሥራ ሲደራረቡ የወሲብ ጣሙ መረሳት ይጀምራል። ብዙ ወንዶች ካገቡ የወሲብ ጥማታቸው ላይ ቀዝቃዛ ውሃ እንደሚፈስበት አድርገው ያስባሉ። ነገር ግን ጋብቻ የወሲብን ወላፈን የሚያጠፋ ቀዝቃዛ ውሃ አይደለም። የወሲብ ጥማት ሳይበርድ ለብዙ ዓመታት ቀጣይነት ያለው እንዲሆን የባልና ሚስትን ያላሳለሰ ጥረት ይጠይቃል። ያ ካልሆነ በሆነ ሰዓት ከሁለቱ አንዱ ወደ ውጭ ማየት ይጀምራል። ይህ ደግሞ ጋብቻን ለአደጋ ያጋልጣል። ቃልኪዳንን ያስፈርሳል። ታማኝነትን ያስረሳል። የወሲብ ህይወትን በማደስና እንደድሮም ጣፋጭ ለማድረግ ዘዴዎችን በማፈላለግ ትዳር እንዳይፈርስ ማድረግ ይቻላል። እሷን እንደሚስትህ ብቻ አትያት። እርግጥ ነው በህግ ያገባሃት ሚስትህ ነች። ግን የወሲብ ህይወታችሁን ለማጣፈጥ እሷን እንደ ሚስትህ ብቻ ማየት አቁም። እንደዚያ ካደረግህ ከሷ ጋር ለዘላለሙ ከርቼሌ የገባህ አድርገህ ራስህን ከማየት ትቆጠባለህ። ስለሆነም እሷን ከሚስትነት ባሻገር የወሲብ ንግስትህ እንደሆነች ቁጠራት። መንገድ ላይ እንዳየሃት ቆንጆ ልጅ ባምሮህ ቅረጻት። በአዕምሮህ ያልሆነችውን ነች ብለህ ሳል። እሷም እንደዚያው። የተለያዩ ገጸባህርያትን ተላብሳቹ አብራችሁ ተውኑ። በየጊዜው ለየት ወዳለ ቦታ ይዘሃት ሂድ። ከልጆች ከጓደኛ ከዘመድ ከሥራ ርቃችሁ ለብቻችሁ ጥሩ ጊዜን አሳልፉ። ቤት ስትሆኑ ደግሞ ክፍላችሁን የግላችሁ አድርጉት። ልጆቻችሁን ከክፍላችሁ ውጭ አግኟቸው። ፒጃማ ለብሰህ አትተኛ። አንቺም እንዲሁ። ሰዎች ከተጋቡ በኋላ ፒጃማ ለብሰው መተኛት ያዘወትራሉ። አይታወቃቸውም እንጂ በቆየ ቁጥር የወሲብ ፍላጎታቸውን ይቀንሳል። ሁሌም ፒጃማ እየለበስክ የምትተኛ ከሆነ እንደድሮው ማራኪ ሆነህ አትታያትም። ዕድሜዋ እየገፋ መምጣቱን ነው የምታስታውሳት። ሳትጋቡ በፊት የነበረህን የአልጋ ውስጥ ባህሪ ብዙም አትቀይር። በፓንት (ቦክሰር) ብቻ ከነበረ የምትተኛው አሁንም በፓንት ብቻ ተኛ። እሷ የምትወደውን ከነቴራ ለብሰህ ከነበረ የምትተኛው አሁንም ያንኑን ከነቴራ የሚመስል ለብሰህ ተኛ። ፒጃማ ደራርበህ የምተኛ ከሆነ ግን አንተም እንቅልፍ ይወስድሃል እሷም የወሲብ ፍላጎቷ አይቀሰቀስም። ከሁሉም በላይ ጋብቻን ከሌላው ግንኙነት የሚለየው ዘላቂነቱ አስተማማኝ መሆኑ ነው። ስለሆነም ባለቤትህን ልታምናት ይገባል። እሷም አንተን ልታምንህ ይገባል። እናም የወሲብ ምኞትህንና ፋንታሲህን ሳትደብቅ ንገራት። እሷም የራሷን ፋንታሲ ትንገርህ። ከዚህ በኋላ የሚቀረው ነገር ፋንታሲያችሁን በፈለጋችሁት ሰዓት እውን ማድረግ ነው። ፋንታሲህን እውን ካደረገችልህ አንተም የሷን እውን ካደረግህላት ሌላ ፍለጋ ሾልኮ መውጣቱ የማይታሰብ ይሆናል። የማትተማመኑና የወሲብ ፍላጎታችሁን ግልጽ አውጥታችሁ የማትወያዩ ከሆነ የወሲብ ወላፈናቹ ሳይቆይ እየተዳፈነ ይሄዳል ትዳራችሁም መቀዝቀዝ ይጀምራል። ሀሳብ ስጡበት ። ለበለጠ ጤና መረጃ የቴሌግራም ቻላናችንን እንሆ👇👇👇 https://t.me/+6X9O71L_Vu1iY2Y0

✍️ #የሃባብ #የጤና #ጥቅሞች 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ 🔹 ለሰውነት እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ቪታሚኖችን፣ ማዕድንና ሳይበዛ ለሰውነት በሚያስፈልግ መጠን ካሎሪንም የያዘ ፍሬ ነው 🔹 ውፍረት ለመቀነስ 🔹 ከስኳር በሽታ 🔹 ለኩላሊት ጤንነት 🔹 ለልብ ህመም ችግር እንዳንጋለጥ ይረዳል 🔹 ለሰውነት ተጨማሪ ሃይል መስጠት 🔹 ለጤናማ የጸጉር እድገት 🔹 ለጤናማ የምግብ መፈጨት ስርአት እና የሰውነት ድርቀትን ለመከላከል 🔹 ደም ግፊትን ለመቆጣጠር ያግዛል 🔹 ሰውነት ላይ የሚፈጠሩ አላስፈላጊ ነገሮችን ለማስወገድ 🔹 የካንሰር ተጋላጭነትን መቀነስ

✍️ #የሮዝመሪ (#የጥብስ #ቅጠል) #ቅጠል #ምግብን #ከማጣፈጥ #ባለፈ #ምን #የጤና #ፋይዳ #አለው? 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ 🔹 ለቁርጥማት እጅግ ጠቃሚ ነው 🔹 የስኳር መጠንን በደም ውስጥ ያስተካክላል 🔹 የትውስታ ችሎታን ለማሻሻል 🔹 የአእምሮ ጤናን ይጠብቃል 🔹 ክብደትን ለመቀነስ 🔹 ለጸጉር እድገት 🔹 ለልብ ጤንነት 🔹 የስርአተ ልመትን ለማሻሻል ይጠቅማል 👉👉 #ታዲያ #ይህን #ቅጠል #መጠቀም #የሌለባቸው #እነማናቸው? 🔹 የደም ማቅጠኛ የሚወስዱ ሰዎች 🔹 ደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች 🔹 ዳዩሬቲክ መድሀኒቶችን የሚወስዱ ሰዎች 🔹 ለስነ-ልቦና ጫና የሚታዘዙ መድሀኒቶችን የሚወስዱ ሰዎች መጠቀም የለባቸውም፡፡ !

በጥያቄአቹ መሰረት ስለጤናችን የምንወያይበት Dr. Jano የቴሌግራም ግሩፑ ከፍተናል ተቀላቀሉን!! በተጨማሪም ወዳጅ ዘመዶን ወደ ግሩፑ አድ አድርጉ!! 👇👇👇👇 https://t.me/+AShRrcxs3KZhMjlk

photo content

የጨጓራ በሽታ አለብዎት? እንግዲውስ መፍትሄዎቹን እነሆ ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድ የኢትዮጤና ገጽ ተከታታዮች ለጨጓራ ህመም መፍትሄ የሚሆኑ ሃሳቦችን ይዘን ቀርበናል እንዲያነቡት ተጋብዘዋል፡፡ የጨጓራ በሽታ መፍትሄ ወይም ህክምና የሚሆነው በመጀመሪያ የጨጓራ ህመማችን ምን ዓይነት ምግቦች ስንመገብ ወይም ምን ዓይነት ተግባሮች ስናደርግ ሊነሳብን እንደሚችል ለይተን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ የጨጓራ ግድግዳ መድከም ወይም መሳሳት በቀላሉ ግድግዳው ለምግብ መፍጫ አሲዶች እንዲጋለጥ ስለሚደርገው ለቁስለት ይዳረጋል በዚህ አማካይነት የጨጓራ በሽታ ይከሰታል፡፡ የተጐዳ እና ስስ የጨጓራ ግድግዳ ካለዎት በጨጓራ በሽታ የመያዝ ዕድልዎ ይጨምራል፡፡ በተጨማሪም ሌሎች የጨጓራ በሽታ መነሻ ምክንያቶች አሉ፡፡ የጨጓራ ባክቴሪያ በመባል የሚጠራው ኤች. ፓይሎሪ (H.Pylori) አንዱ የጨጓራ በሽታ መነሻ ነው። ይህ ባክቴሪያ የጨጓራ ግድግዳን የሚያጠቃ ሲሆን በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል በተጨማሪም በተበከለ ውሃ እና ምግብ ይተላለፋል፡፡ ☑️ ሌሎች ለጨጓራ ሊያጋልጡ ከሚችሉ ምክንያቶች መካከል፦ 🔹 ከመጠን ያለፈ አልኮል መጠጣት 🔹 በመደበኛ ሁኔታ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቴች መጠቀም ለምሳሌ፦ ኢቡፕሮፊን፣ አስፕሪን እና ኮኬይን መጠቀም 🔹 ዕድሜ (የጨጓራ ግድግዳ ዕድሜ በጨመረ ቁጥር እየሳሳ ይመጣል) ሌሎች ለጨጓራ ህመም መነሻ ዝቅተኛ አስተዋጽኦ ካላቸው ምክንያቶች መካከል፤ በህመም፣ በአደጋ ወይም በቀዶጥገና ጊዜ በሚፈጠር ጭንቀት፣ በቫይረስ ኢንፌክሽን እና በምግብ ስልቀጣ ወይም መፈጨት ችግሮች ሊከሰት ይችላል፡፡ ☑️ ጨጓራን በቤት ውስጥ እንዴት ልንከላከለው ወይም ልናክመው እንችላለን? 🔺 ሲጋራ ማጨስዎን ያቁሙ። 🔺 ከመጠን ያለፈ አልኮል አይጠጡ። 🔺 ካፌይን ያላቸው መጠጦችን አይጠጡ። ለምሳሌ ቡና እና ሻይ። 🔺 ሲትሪክ አሲድ ያላቸውን የፍራፍሬ ጭማቂዎችን አይጠጡ። ለምሳሌ፦ ብርቱካን፣ ሎሚ፣ ወይን ወዘተ 🔺 ከፍተኛ የቅባት ወይም ፋት ይዘት ያላቸውን ምግቦች አይመገቡ፡፡ 🔺 በፋይበር እና ፍላቮኖይድ የበለፀጉ ምግቦች ኤች. ፓይሎሪ (H. Pylori) የተባለውን የጨጓራ ባክቴሪያ ዕድገት ስለሚገቱ በጣም ጠቃሚ ናቸው። 👉 ከእነዚህ ምግቦች መካከል:- 🔸 ቀይ ሽንኩርት 🔸 ነጭ ሽንኩርት 🔸 አበባ ጐመን 🔸 የምግብ ማጣፈጫ ተክል 🔸 ጦስኝ 🔸 ሽምብራ እና 🔸 አንዳንድ የሻይ ዓይነቶች ይጠቀሳሉ፡፡

ሞቅ ያለ ውሃን መጠጣት አስገራሚ ጠቀሜታዎች አብዛኛዎቻችን ከአልጋችን ከተነሳን በኋላ ሰውነታችንን ለማነቃቃት እራሳችንን በትኩስ ቡና ወይም ሻይ ቀኑን እንጀምራለን፡ ውሃ በምንጠጣበት ጊዜም ቀዝቃዛ እንዲሆን እንመርጣለን ነገር ግን በአዩርቬዲክ ህክምና መሰረት ሁሉም ስህተት ናቸው። በተለይም በጠዋቱ ሞቅ ያለ ውሃን መጠጣት ሰውነታችን የተፈጥሮ በሽታ ተከላካይ ሕዋሳችን ውስጥ ሊገነባ የሚችል ሜታክቢክ ፈሳሽ በመፍጠር ሰውነታችንን መዳን ይችላል ሞቅ ያለ ውሃ መጠጣት አፋችን ባይጣፍጠንም ካፌይን እና ሻይ የመሳሰሉትን ለጤንነትዎ በእጅጉ መቀነሱ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።. ለዚህም ስድስት ምክንያቶችን ማስቀመጥ ይቻላል። 1. ጠዋት ላይ አንድ ሞቅ ያለ ኩባያ ዉሃ ከሰውነትዎ ዉስጥ መርዛማ ነገሮችን ለማፅዳት ይረዳል። ውሃ እና ሌሎች ፈሳሾች በሆድዎ ውስጥ ያለውን ምግብ ይሰብራሉ እና የምግብ መፍጫ ስርዓቱ በሂደት ላይ ያስጉዛሉ። 2.በባዶ ሆድ የሞቀ ዉሃ መጠጣት የሆድ ድርቀትንም ይከላከላል 3. ተፈጥሯዊ ከፍተኛ ኃይል ያለው የቤት ውስጥ መድሐኒት ተብሎ የሚጠራው የሞቀ ውሃ, ከወር አበባ እና የራስ ምታ ህመምን ለማስታገስ ሊረዳ ይችላል። 4. አንድ ብርጭቆ ሞቃት ውሃን ማለዳ ማለዳ መጀመሪያ ላይ መጠጣት ክብደትን ለመቀነስ ሊረዳ ይችላል። ከዚህ በተጨማሪም የጨጓራና ትራክት እና ኩላሊት የተሻለ ጤንነት ወይም አገልግሎት እንዲኖረው ይረዳል 5. የደም ዝውውርን ያሻሽላል፡ ይህም ጡንቻዎች ዘና እንዲሉ በማድረግ, ደካማ የደም ዝውውርን እና ፍሰትን ያስወግዳል 6. ከእድሜ ቀድሞ የሚመጣን እርጅና ያዘገያል። በሰውነታችን ውስጥ መርዛማ ነገሮች መኖራቸው ወደ እርጅና በፍጥነት እንዲያመራ ያረገዋል, ነገር ግን የሞቀ ውሃው ሰውነታችንን ከነዚህ መርዛማ ንጥረ ነገሮች ለማጽዳት ይረዳል። የቆዳ ሴሎችን በመጠገን የቆዳችንን የመሳብ /elasticity ይጨምራል

photo content

photo content

✍ #በወንዶች #ላይ #የሚከሰት #ያልተለመደ #የብልት #ፈሳሽ 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #የወንድ ብልት ፈሳሽ ውሃ ወይም ደመናማ (መግል የያዘ) ሊሆን ይችላል ሆኖም ፈሳሹም በደም የተሞላ ሊሆን ይችላል፡፡ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን (UTI) ወይም በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች (የአባላዘር ህመም) የወንድ ብልት ፈሳሽ መንስኤዎች ናቸው ፡፡ የወንድ ብልት ፈሳሽ ብዙውን ጊዜ ሽንት በሚሸኑበት ወቅት ህመም ወይም ማቃጠል እና ቶሎ ቶሎ ሽንት መምጣት አብሮ ይመጣል እንዲሁም ማሳከክ አብሮ ሊኖር ይችላል፡፡ ⏩ #መንስኤዎቹ 🔺 የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን 🔺 የአባላዘር በሽታ 🔺 የዘር ፍሬ ማቀፊያ ውስጥ የተከሰተ ኢንፌክሽን ካለ በዋነኛነት ይጠቀሳል ⏩ #ምን #አይነት #ምልክቶች #ሊታዩ #ይችላሉ? 🔺 በግንኙነት ወቅት ህመም መኖር 🔺 በውሀ ሽንት ጊዜ የማቃጠል ስሜት 🔺 የብልት ማሳከክ 🔺 ትኩሳት 🔺 የወገብ ህመም 🔺 የውሀ ሽንት ማጣደፍ 🔺 የብልት ጫፍ መቅላት ⏩ #ህክምናው 🔺 ጸረ-ባክቴሪያ መድሀኒቶች 🔺 ጸረ-ፈንገስ መድሀኒቶች 🔺 እንዲሁም የአባላዘር መድሀኒቶች ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ⏩ #ይህን #ችግር #እንዴት #መከላከል #እንችላለን? 🔺 ኮንዶም መጠቀም 🔺 በቂ ውሀ መጠጣት 🔺 ሽንት ረጅም ሰአት አለመቋጠር 🔺 እንዲሁም የብልት እና የውስጥ ሱሪ ንጽህና መጠበቅ፡፡