ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

ኮሮጆ bags 💼 & Gift shop 🎁

ኮሮጆ bags 💼 & Gift shop 🎁

الذهاب إلى القناة على Telegram

👉plexiglass 👉engraving 👉orginal cosmotics 👉 natural face products like Kesil 👉Gift packages 📞0942410512 metis_bag 🏠🏠 Megenagna 3M Mall 1st floor

إظهار المزيد
1 890
المشتركون
-124 ساؚات
-27 أيام
-2230 أيام
أرشيف المشاركات
የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሕዳር 22 እና 23 ቀን 2013 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን ፈተና ላይ መቀመጥ የሚችሉት 7ኛ ክፍልን ተምረው ያጠናቀቁና የ8ኛ ክፍልን የአንደኛ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ ብቻ
የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሕዳር 22 እና 23 ቀን 2013 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን ፈተና ላይ መቀመጥ የሚችሉት 7ኛ ክፍልን ተምረው ያጠናቀቁና የ8ኛ ክፍልን የአንደኛ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ ብቻ ናቸው። በተመሳሳይ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መውሰድ የሚችሉት የ11ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀቁና የ12ኛ ክፍልን የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ ብቻ ናቸው ተብሏል። የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሕዳር 28 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥም በምክረ ሀሳቡ ላይ ተጠቅሷል። #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

ትምህርት ቤቶችን ዳግም መክፈት በሚቻልበት የውሳኔ ሃሳብ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው! ትምህርት ቤቶችን ዳግም መክፈት በሚቻልበት የውሳኔ ሃሳብ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኙበት
ትምህርት ቤቶችን ዳግም መክፈት በሚቻልበት የውሳኔ ሃሳብ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው! ትምህርት ቤቶችን ዳግም መክፈት በሚቻልበት የውሳኔ ሃሳብ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኙበት ውይይት እየተካሄደ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እየተካሄደ ባለው ውይይት የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች ሚኒስትሮችም ተገኝተዋል። ውይይቱ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለመክፈት ለውሳኔ የቀረበ ምክረ ሃሳብ፣ የ8ኛ እና 12ኛ ከፍል ብሄራዊ ፈተናና የግል ትምህርት ቤቶችን የትምህርት አሰጣጥ ሂደት የተመለከተ ነው። የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለመክፈት ስለቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ገለፃ አድርገዋል። ባለፉት ሁለት ቀናት ከሁሉም ክልሎች የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ውይይት መካሄዱንና የውሳኔ ሃሳብም መቅረቡን አንስተዋል። በዚሁ መሰረት የትምህርት ቤት አከፋፈት ሂደቱ በሶስት ዙር እንደሚከናወን አስታውቀዋል ፦ በመጀመሪያው ዙር ማለትም ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም በገጠር ወረዳና ቀበሌ ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንዲጀምሩ የውሳኔ ምክረ ሃሳብ ቀርቧል። በ2ኛ ዙር ጥቅምት 16 ቀን 2013 ደግሞ በሁሉም የዞንና የክልል ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንዲጀምሩ ነው ምክረ ሃሳብ የቀረበው። በአዲስ አበባና በፊንፊኔ ዙሪያ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችም ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት እንዲጀምሩ የውሳኔ ምክረ ሀሳብ ቀርቧል #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

ቀድመው ዝግጅት ያጠናቀቁ ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም 25 ጀምሮ ለተመራቂ ተማሪዎች ጥሪ ማድረግ እንደሚችሉ ተወስኗል! የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጥነትን ሳይጠብቁ ቀድመው ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ዩኒቨር
ቀድመው ዝግጅት ያጠናቀቁ ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም 25 ጀምሮ ለተመራቂ ተማሪዎች ጥሪ ማድረግ እንደሚችሉ ተወስኗል! የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጥነትን ሳይጠብቁ ቀድመው ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም 25 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ለተመራቂ ተማሪዎች ጥሪ በማድረግ ወደ መማር ማስተማር ሥራው እንዲገቡ በጅማ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው የውይይት መድረክ ውሳኔ ተላልፏል። ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ጥሪ ከተደረገ በኋላ ከመጓጓዣ ሂደት ጀምሮ በየዩንቨርሲቲዎቹ በሚኖራቸው ቆይታ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዳይዛመት ከፍተኛ ዝግጅት መደረግ እንዳለበትም ተገልጿል። በቀጣይነትም ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሁኔታ ጋር በሚስማማ መልኩ ተለዋዋጭ እቅዶችን በመያዝ ቀሪዎቹ ተማሪዎች ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ እንደሚሠራ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደቻሳ ጉሩሙ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ተናግረዋል። #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

የትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ጉዳዮችን ዳይሬክተር ሐረጓ ማሞ ለቲ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና የክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች በቀጣይ የትምህርት ሁኔታ ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ እያካሄዱት ያለው ው
የትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ጉዳዮችን ዳይሬክተር ሐረጓ ማሞ ለቲ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና የክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች በቀጣይ የትምህርት ሁኔታ ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ እያካሄዱት ያለው ውይይት ዛሬ አልተጠናቀቀም ፤ ነገ ጥዋት መግለጫ ይሠጣል። ለተፈጠፈው ነገር ለተማሪዎች እና ለተማሪ ቤተሰቦች ይቅታ እንጠይቃለን። #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

በትግራይ የግእዝ ቋንቋ በመደበኛ ትምህርት መርሀግብር ሊሰጥ ነው በትግራይ ክልል የግእዝ ቋንቋን በመደበኛ የትምህርት መርሀ ግብር ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ቋንቋዎች አካዳሚና ትምህርት ቢሮ አስታወቁ። የትግራይ ቋንቋዎች አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዳንኤል ተክሉ ለኢዜአ እንደገለፁት በሀገሪቱ በግእዝ ቋንቋ የታተሙ በሺህዎች የሚቆጠሩ ጥንታዊ የብራናና የመጽሀፍት ህትመቶች አሉ። “አዲሱ ትውልድ ፅሁፎችን በማንበብ የሀገሩን ባህልና ቋንቋ እንዲሁም ታሪክና ማንነት ጠንቅቆ እንዲያውቅ ለማበረታታት የቋንቋውን ትምህርት መስጠት አስፈልጓል” ብለዋል። በተያዘው 2013 አመት በክልሉ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ትምሀርቱን ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን አመላክተዋል ። ከትግርኛ፣ ኩናምኛና ሳሆኛ ቋንቋዎች ቀጥሎ ግዕዝ አራተኛ ቋንቋ ሆኖ በክልሉ በሚገኙ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊነት ወስዶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል ። ቢሮው የመማር ማስተማር ስራውን እንዲጀምር በክልሉ ምክር ቤት በአዋጅ መጽደቁንም አስታውቀዋል። የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ባህታ ወልደሚካኤል በበኩላቸው የግዕዝ ቋንቋ ትምህርትን በክልሉ በሚገኙ ከ2 ሺህ በላይ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለማስጀመር የመምህራንና የመማሪያ መፃፍት ዝግጅት እየተደረገ ነው። ከስድስት ወራት በኋላ ትምሀርቱን ለመጀመር እቅድ መያዙን አመላክተዋል ። በመቐሌ የሃወልት ክፍለ ከተማ ነዋሪና የሰላም አካዳሚ የትግርኛ ቋንቋ መምህር ሃዱሽ አታክልቲ የግዕዝ ቋንቋ በመደበኛ የትምህርት መርህ ግብር እንዲሰጥ መታቀዱ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል። የትምህርቱ መሰጠት በየአብያተ ክርስትያናትና ገዳማት ውስጥ የሚገኙና በግዕዝ ቋንቋ ተጽፈው የታተሙ ጥንታዊና ታሪካዊ መፃህፍቶችን በቀላሉ አንብቦ ለመገንዘብ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል ። ለኢትዮጵያ የቱሪዝም ልማት እድገትም ያለው አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል። “አዲሱ ትውልድ በመጤ ቋንቋዎችና ባህሎች ከመበረዝ ይልቅ የሀገሩን ባህልና ቋንቋ በሚገባ እንዲያውቅና እንዲጠብቅ ያስችለዋል” ሲሉም መምህር ሃዱሽ አስታውቀዋል። #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

photo content

sticker.webp0.06 KB

ማስታወሻ ⬇️ በሀገር አቀፍ ደረጃ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን ዛሬ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ይፋ ይደረጋል ! መረጃውን በዚሁ በቻናላችን ይጠብቁ!! #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

ተጠሪነታቸው ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሆኑት ዩኒቨርስቲዎች ከ91 ሚሊየን ብር በላይ ለገበታ ለአገር ፕሮጀክት አበረከቱ፡፡ ዩኒቨርስቲዎቹ በጎርፍ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖችም ከ14 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ፡፡፡፡፡፡ ከመስከረም 10 እስከ መስከረም 12 ቀን 2012 ዓ.ም በጅማ ዩኒቨርስቲ መሰብቢያ አዳራሽ ሲካሄድ የነበረው የከፍተኛ ትምህርት ማስቀጠያ ቅድመ ዝግጅት እና የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምላሽ ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ በማጠቃለያው ውይይት ዩኒቨርስቲዎቹ ለገበታ ለአገር ፕሮጀክት 91.3 ሚሊየን በገንዘብ፣24 ሚሊየን በአይነትና በሙያ እንዲሁም በጎርፍ ለተጎዱ ወገኖች 14.35 ሚሊየን በገንዘብና 1.1 ሚሊየን በአይነት ለማበርከት ቃል ገብተዋል፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በድጋፉ ተሳትፎ ያደረጉት 32 ዩኒቨርስቲዎች ናቸው፡፡ ፕሮጀክቱ በአዲስ አበባ ከተመረቁት በተጨማሪ በጎርጎራ፣ ወንጪ እና ኮይሻ ደቡብ ኮንታ ልዩ ወረዳ ውስጥ እንዲስፋፋ እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ቀደም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ጨምሮ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ፣ የከፍተኛ ትምህርት ስትራቴጂ ማዕከል፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ እና ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለዚሁ ዓላማ እንዲውል መስጠታቸው ይታወሳል፡፡ በማጠቃለያው መልዕክታቸው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ የትምህርት፣ የምርምር ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር ጥራትን ለማምጣት የመምህራን አቅም ግንባታ ላይ እንሰራለን። አቅሙ መፈጠሩን ደግሞ በምዘና በማረጋገጥና የሙያ ፍቃድ በመስጠት አሟልተው የተገኙትን የሚበረታቱበት ስርዓት እንፈጥራለን ሲሉም አክለዋል፡፡ ዩኒቨርስቲዎችን በተልዕኮ መለየትን አስመልክቶም በሰጡት አቅጣጫ ዩኒቨርስቲዎች በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ራሳቸውን በመለካት የትኛው ላይ እንደሚያርፉ መለየትና ከወዲሁ መዘጋጀት ያስፈልጋቸዋል ብለዋል፡፡ በቀጣይም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተቋማዊ ዳሰሳ በማድረግ ልየታውን ሰርቶ ይፋ የሚደርግ ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡ በተቋማት መካከል ጤነኛ የሆነ ፉክክር እንዲኖርና ቀልጣፋ የሆነ የአሰራር ስርዓት መገንባት ላይ እንዲያተኩሩ አሳስበዋል፡፡ ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ እንዳሉት ኮቪድን እየተከታተልን የለውጥ ስራዎቻችን ላይ ትኩረት አድርገን መስራት አለብን። የህግ አሰራርና የአሰራር ክፍተቶችን እየለዩ መሙላት ይጠበቃል ብለዋል፡፡ አመራሮች በተሰጣችሁ ኃላፊነት የአመራር አሻራችሁን ለማስቀመጥና ልዩነት ፈጣሪ ተግባራትን ለማከናወን ተግታችሁ እንድትሰሩ አደራ እላለሁ ብለዋል፡፡ ዩኒቨርስቲዎችን መልሶ ለመክፈት የሚያስችሉ ቅደመ ዝግጅት ሰራዎችንም በአፋጣኝ ለማጠናቀቅ እንደዲሰሩ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡ ለሶስት ቀናት በተካሄደው ጉባኤ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታዎች ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ፣ ዶ/ር ሙሉ ነጋና ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የተለያዩ መልዕክቶችን ያስተላለፉ ሲሆን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስራ ኃላፊዎች፣ አማካሪዎች፣ የዩኒቨርስቲዎች ፕሬዚዳንቶች፣ የተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት እና ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኙ ተሳታፊዎች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡ #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

በሀገር አቀፍ ደረጃ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን ነገ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ይፋ ይደረጋል ! መረጃውን በዚሁ በቻናላችን ይጠብቁ!! #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

✅ ሁለተኛ ሴሚስተር ያልጀመሩ ተማሪዎችን በሁለት ወር፣ የሴሚስተሩን 25 በመቶ የተማሩትን ደግሞ በ45 ቀናት ማካካሻ ለማስጨረስም ታሳቢ ተደርጓል። እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ ነባር ተማሪዎችን በሶስት መርሃ ግብር፤ ተመራቂ ተማሪዎችን ደግሞ እስከ ሁለት ወር ለማሰጨረስ ነው የታሰበው። ተመራቂ ያልሆኑ ነባር ተማሪዎች ጉዳይ እየታየ የሚቀጥል ሲሆን ትምህርት ማስቀጠያው ከጥቅምት እንዲጀምርም ታስቧል። በአንድ ክፍል ውስጥ ከ25 እስከ 30 ተማሪዎችን ለማስተማር ታቅዷል፤ ሌሎች መማሪያ ክፍሎች ደግሞ የመያዝ አቅማቸውን ግማሽ ብቻ እንዲይዙ ይደረጋል። #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

የትምህርት ሚኒሰቴር የ 2013 ዓ.ም በጀት። #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE
የትምህርት ሚኒሰቴር የ 2013 ዓ.ም በጀት። #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት መጀመር በሚቻልበት ላይ የምክክር ጉባኤ እየተካሄደ ነው:: በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት ለመጀመር በሚቻልበት ላይ የሚመክር ጉባኤ በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄ
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት መጀመር በሚቻልበት ላይ የምክክር ጉባኤ እየተካሄደ ነው:: በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት ለመጀመር በሚቻልበት ላይ የሚመክር ጉባኤ በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው ፡፡ በጉባኤው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2012 የስራ ዘመን ኮሮናን ለመከላከል ያከናወኗቸው አበይት ተግባራትና ያስገኙት ውጤት ይገመገማል። ትናንት በተጀመረው በዚሁ ጉባኤ የዘንድሮ ትምህርት በሚጀመርበት ሁኔታ ላይ ጉባኤው እንደሚመክረና መረሃ ግብሩ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል። ከጉባኤው ጎን ለጎን ኮሮናን ለመከላከል በዩኒቨርስቲዎች የተሰሩ የፈጠራ ምርቶችን የሚያሳይ አውደ ርዕይ በጅማ ዩኒቨርሲቱ ዋናው ግቢ ተከፍቷል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በምርምር፣ በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ያከናወኗቸውን አበይት ተግባራት ይዘው ቀርበዋል። አውደ ርዕዩ ለአንድ ሳምንት እንደሚቆይ ከኢዜአ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በመክፈቻ ስነ-ስርዓት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርካቶ እንዲሁም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቴክኖሎጂና የሰው ሃብት ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ እምዬ ቢተው እንዲሁም ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል። #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

ትምህርት በፈረቃ እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ! ትምህርት ሲጀመር የትምህርት አሳጣጥ ሂደቱ በፈረቃ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። በፈረቃ የሚሰጠው ትምህርት እንደየአካባቢው ሁኔ
ትምህርት በፈረቃ እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ! ትምህርት ሲጀመር የትምህርት አሳጣጥ ሂደቱ በፈረቃ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። በፈረቃ የሚሰጠው ትምህርት እንደየአካባቢው ሁኔታ ከ2 እስከ 3 ፈረቃ ተከፍሎ ሊሰጥ እንደሚችልም ተገልጿል። የመማር ማስተማር ሥራው በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንደሚጀመር ትምህርት ሚኒስቴር አመልክቷል። ሚኒስቴሩ እንዳለው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለሰባት ወራት ተቋርጦ የቆየው መደበኛ ትምህርት አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ዳግም ለማስጀመር አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል። መንግስት በትምህርት ቤቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ፣ ውሃ እና የእጅ ማጽጃዎችን በማሟላት እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን በማጽዳት መደበኛው ትምህርት እንደሚጀመር አስታውቋል #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

✋ሰላም የትምህርት ሚኒስተር የቴሌግራም ላይብራሪ ተቀላቅለዋል? ካልተቀላቀሉ @MOE_Library በመጫን ይቀላቀሉ!! ሁሉም አይነት መፅሀፎች በሁሉም ቋንቋዎች ያገኙበታል። @MOE_Library @MOE_Library ለጓደኞቻቹ ሼር በማድረግ ውለታ ይዋሉላቸው!!

የጤና ሚኒስቴር የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል እየተወሰዱ ያሉ የጥንቃቄ እርምጃዎችን በአግባቡ በመተግበር ትምህርት ቤቶች ቢከፈቱ የሚል ምክረ ሀሳብ አቀረበ። --------------------------
የጤና ሚኒስቴር የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል እየተወሰዱ ያሉ የጥንቃቄ እርምጃዎችን በአግባቡ በመተግበር ትምህርት ቤቶች ቢከፈቱ የሚል ምክረ ሀሳብ አቀረበ። -------------------------------------- የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽና ቀጣይ እርምጃዎች ላይ ያተኮረ ሪፖርትና ምክረ ሀሳብ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል። ሚኒስትሯ ያቀረቡት ምክረ ሃሳብ ወረርሽኙን ለመከላከል እየተወሰዱ ያሉ የጥንቃቄ እርምጃዎችን በመተግበር ትምህርት ቤቶች ቢከፈቱ የሚል ነው፡፡ ትምህርት ለመጀመር ከመወሰኑ በፊት ግን ጠንካራ ግብረ ኃይል በየደረጃው ተቋቁሞ ወደ ሥራ መገባት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ምክር ቤቱ በቀረበው ምክረ ሃሳብ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ ለሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የውሳኔ ሃሳብ እንዲያቀርብ መርቷል። የትምህርት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በመተባበር ትምህርት ለመጀመር የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ጥናቶችን እያካሄደ መሆኑ ይታወሳል፡፡ #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምዝገባ ቀን አሳወቀ በተከሰተዉ የኮቪድ 19 ምክንያት ሁሉም የትምህርት እንቅስቃሴ ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል። ነገር ግን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ Regular Gr
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምዝገባ ቀን አሳወቀ በተከሰተዉ የኮቪድ 19 ምክንያት ሁሉም የትምህርት እንቅስቃሴ ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል። ነገር ግን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ Regular Graduate ተማሪዎችን መዝግቦ ትምህርት የሚያስጀምርበትን ቀን ቆርጦ በድህረ ገጹ እና በ ማህበራዊ ገጹ ላይ  አሳውቋል።  በዚህም መሰረት ሁሉንም ተማሪዎች ባይሆንም ከ ሁለተኛ ዓመት በላይ የሆኑ Regular Graduate ተማሪዎችን ምዝገባ እና ትምህርት የሚጀመርበትን ቀን አሳውቋል። ምዝገባ የሚጀመርበት ቀን በ September 21, 2020 እና September 22, 2020  ሲሆን ትምህርት የሚጀመረዉን ደግሞ በ September 23, 2020 እንደሆነ የዩኒቨርሲቲዉ ሬጅስትራር ገልጿል። ተማሪዎቹም  ለምዝገባዉ ስኬታማነት ተገቢዉን ትብብር እንዲያደርጉም አሳውቋል። ምንጭ፡- የዩኒቨርሲቲዉ ድረ ገጽ:: (www.aau.edu.et ) #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

ዶ/ር ዑባህ አደም የድሬደዋ ዩኒቨርስቲን እንዲመሩ ተሾሙ፡፡ ለዩኒቨርስቲው የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ ዶ/ር ዑባህ አደም በድሬደዋ ዩኒቨርስቲ የተካሄደውን የፕሬዘዳንትነት ውድድር አሸንፈው
ዶ/ር ዑባህ አደም የድሬደዋ ዩኒቨርስቲን እንዲመሩ ተሾሙ፡፡ ለዩኒቨርስቲው የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ ዶ/ር ዑባህ አደም በድሬደዋ ዩኒቨርስቲ የተካሄደውን የፕሬዘዳንትነት ውድድር አሸንፈው በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ተሹመዋል፡፡ በዚህም ዩኒቨርስቲው የመጀመሪያዋን የሴት ፕሬዚዳንት አግኝቷል፡፡ ከጥር 2012 ዓ.ም ጀምሮ ድሬደዋ ዩኒቨርስቲን ተወካይ ፕሬዚዳንት ሆነው ሲመሩ የቆዩት ዶ/ር ዑባህ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ያገኙት ከህንድ አንድራ ዩኒቨርስቲ ነው፡፡ ዶ/ር ዑባህ በአገራችን የዩኒቨርስቲዎች ታሪክ ሁለተኛዋ ሴት ፕሬዚዳንት ሲሆኑ የመጀመሪያዋ የሴት ፕሬዚዳንት ባህርዳር ዩኒቨርስቲን ከመስከረም 2001 እስከ ጥር 2003 ዓ.ም የመሩት ዶ/ር የሺመብራት መርሻ ካሳ ናቸው፡፡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለዶ/ር ዑባህ መልካም የስራ ዘመን ይመኛል፡፡ #JOIN & #SHARE @FDRE_MOE @FDRE_MOE

photo content