cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

The best fiction is far more true than any journalism 📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ 👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56 👉 https://www.facebook.com/mik0Man

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
34 496
المشتركون
+1024 ساعات
+677 أيام
+1 38730 أيام
أرشيف المشاركات
Photo unavailableShow in Telegram
ኬቨን ደ ብረይነ በፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያውን የግምባር ኳስ በመግጨት አስቆጥሯል 😲 ሁሉንም ማሳካት ተችሎታል... ብራይተን 0-3 ማን ሲቲ ጎሎቹን ለመመልከት 👉 @mikoethio #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
👍 19🔥 8😁 3👏 2👎 1
የቡርኪናፋሶ ጦር በ223 ሰዎች ላይ የበቀል እርምጃ መውሰዱን የሰብዓዊ መብት ድርጅት አስታወቀ በተያዘው አመት ከ220 በላይ ንፁሀን ዜጎች፣ ቢያንስ 56 ህፃናት በቡርኪናፋሶ ጦር በአንድ ቀን ተጨፍጭፈዋል ሲል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂውማን ራይትስ ዎች አስታውቋል። በሰራዊቱ ላይ የተፈፀመው ጥቃት ለመበቀል ጦረ በሶሮ መንደር 179 ሰዎች ሲገድል 44 ሌሎች  ሰዎች ደግሞ በአቅራቢያው በሚገኘው ኖንዲን መንደር ውስጥ መገደላቸውን የመብት ተሟጋች ቡድሙ ያደረገው ምርመራ አረጋግጧል።የጅምላ ግድያው "በሀገሪቱ ከአስር አመታት ወዲህ ከተከሰቱት እጅግ የከፋ የጦር ሰራዊት ጥቃት" ሲል ገልጿል። የቡርኪናፋሶ ባለስልጣናት በሪፖርቱ ላይ አስተያየት እስካሁን አልሰጡም። ባለፈው ወር የህዝብ አቃቤ ህግ አሊ ቤንጃሚን ኩሊባሊ ከጅምላ ግድያው ጀርባ ያለውን ቡድን ለመለየት ምስክሮች እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። በወቅቱ የሟቾችን ቁጥር 170 አድርሶታል። ከጥቃቱ የተረፉ መንደርተኞች ለሂውማን ራይትስ ዎች እንደተናገሩት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች እንዳለፉ  ከ30 ደቂቃ በኋላ ወታደራዊ ኃይሉ ወደ ኖንዲን መንደር መውረዱን ተናግረዋል። ወታደሮቹ ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ ነዋሪዎችን ከቤታቸው እያባረሩ ወንጀሉን ፈፅመዋል ሲሉ ተደምጠዋል። በመቀጠል 5 ኪሜ ርቀት ላይ ወደምትገኘው ሶሮ መንደር ደርሰው ከአንድ ሰአት በኋላ በመንደሩ ሰዎች ላይ ተኩስ መክፈታቸውን ከጥቃቱ  የተረፉት እማኞች ገልጸዋል። በሁለቱም መንደሮች ወታደሮቹ ለመደበቅ ወይም ለማምለጥ በሞከሩ ሰዎች ላይ መተኮሳቸውን እማኞቹ አክለዋል። የጅምላ ግድያው በወታደሮች የተወሰደው በታጣቂ ቡድን ለተፈፀመባቸው ጥቃት የበቀል እርምጃ ነው ተብሎ ታምኖበታል። የመንደሩ ነዋሪዎች የታጠቁ ተዋጊዎችን ይረዱ ነበር በሚል ተከሰዋል። በሰሜናዊ ያትንጋ ግዛት አቅራቢያ በሚገኝ የጦር ካምፕ ላይ ታጣቂ ቡድኖች ጥቃት ሰንዝረዋል።የሂዩማን ራይትስ ዎች ዋና ዳይሬክተር ቲራና ሃሰን እንዳሉት በኖንዲን እና በሶሮ መንደር የተፈፀመው እልቂት የቡርኪናፋሶ ወታደሮች በፀረ-ሽምቅ ዘመቻቸው በሰላማዊ ሰዎች ላይ የፈፀሙት የቅርብ ጊዜ የጅምላ ግድያ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። በአበረ ስሜነህ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
👍 17👎 15😢 5 3🤩 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 2🥰 2😱 1
አቶ ታዬ ደንደአ የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍ እና የጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ የነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍና ጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው። ክሱ የተመሰረተው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሕገ-መንግስትና ሕገ-መንግስት ሥርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮችን በሚመለከተው ችሎት ነው። የፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሽ ታዬ ደንደአ ላይ ሶስት ክሶችን አቅርቧል። በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 251/ሐ እና አንቀጽ 257/ሰ ስር የተመላከተውን ድንጋጌ እና የጦር መሳሪያ አዋጅን መተላለፍ የሚል ክስ አቅርቦባቸዋል። በክሱ ላይ እንደተመላከተው÷ተከሳሹ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ሆነው ሲሰሩ የሀገርን፣ የመንግስትንና የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደጎን በመተው  ፀረሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችን በማስተላለፍ በስማቸው በተከፈተ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ድጋፍ የሚገልጹ መልዕክቶችን  ሲያስተላልፉ ነበር የሚል ነው፡፡ እንዲሁም ፍቃድ ሳይኖራቸው የጦር መሳሪያ አዋጁን በመተላለፍ በታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም  ከረፋዱ 5 ሰዓት  ላይ በልደታ ክ/ከ ወረዳ 6  በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በተደረገ ብርበራ አንድ ታጣፊ ክላሽን ኮቭ  መሳሪያ ከ2 ክላሽ ካዝና  እና ከ60 ጥይት ጋር ይዘው መገኘታቸው ተጠቅሶ ክስ ቀርቦባቸዋል። ተከሳሽ አቶ ታዬ ደንደአ በአራት ጠበቆቻቸው ተወክለው ችሎት ቀርበው የክስ ዝርዝሩ ተነቦላቸዋል። ክሱ ከተነበበ በኋላ በጠበቆቻቸው በኩል የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጥያቄ ቀርቧል። ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ የዋስትና ጥያቄያቸውን ሊያስከለክሉ የሚችሉ ነጥቦችን ጠቅሶ ተከራክሯል። ሰበር ሰሚ ችሎት ዋስትናን በልዩ ሁኔታ ሊከለክል የሚችልባቸው ነጥቦች ማለትም በተደራራቢ ክስ መከሰሳቸውን እና የተከሰሱት ድንጋጌ ከፍ ያለ ቅጣት የሚያስጥል ከሆነ ዋስትና ሊያስከለክል ይችላል በማለት ተከራክሯል። የተከሳሽ ጠበቆችም ሰበር ሰሚ ችሎት ያስቀመጣቸው ዋስትናን ሊያስከለክሉ የሚችሉ ድንጋጌዎች ተከሳሹ ላይ በቀረበው ክስ የሚመለከቱ አለመሆናቸው ጠቅሰው መልስ ሰጥተዋል። በተጨማሪም  ህጻን ልጃቸውን ጥለው የታሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰው÷ በሕገ-መንግስቱ የተቀመጠው የሕጻናት መብት ታሳቢ ተደርጎ በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ጠይቀዋል። አቶ ታዬ ደንደአ በበኩላቸው÷በቁጥጥር ስር ሲውሉ በራሳቸው እና በቤተሰባቸው ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደደረሰባቸው ገልጸው አቤቱታ በቃል አቅርበዋል። ምርመራው ታሕሳስ 24 ማለቁንና ዘግይቶ ክስ መቅረቡንም ተቃውመዋል። ዐቃቤ ሕግ ሌሎች ምርመራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ገልጾ መልስ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱም  በአያያዝ ላይ ያቀረቡትን የመብት ጥያቄ በሚመለከት በጽሑፍ በዝርዝር ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጿል። ዋስትናውን በሚመለከት መርምሮ ብይን ለመስጠትም ለሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። Via FBC #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
👎 47👍 19😁 3 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ ዛሬ ጠዋት ከቤተሰብ እና ጠበቃው ጋር መገናኘቱ ተዘገበ ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ "እብደት በሕብረት" የተሰኘ የአንድ ሰው ቴአትሩን ለማሳየት ወደ እስራኤል አገር ሊጓዝ ሲል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች መያዙ ይታወሳል።በአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ ታስሮ የሚገኘው ተዋናዩ የቅርብ ወዳጅ የሆነው ያሬድ ሹመቴ እንደገለጸው አማኑኤል ሃብታሙ "እጁ ከተያዘበት ሰዓት አንስቶ የተከሳሽነት ቃል ሳይሰጥ እንዲሁ በእስር ላይ" እንደሚገኝ ቤተሰቦቹን ዋቢ አድርጎ ጽፏል። ይኹን እንጂ የቤተሰብ ጠበቃ የማግኘት መብቱ ተጠብቆለት ከቤተሰብ እና ከጠበቃ ጋር ዛሬ ጠዋት ሊገናኝ መቻሉን እና "በመልካም" ሁኔታ ላይ መኾኑ ተመልካቷል። በሕጉ መሰረት ወደ ቀጣይ ሕጋዊ ሂደቶች ለማምራት እስከ ነገ የሚሆነውን ለማየትም ቤተሰቦቹ እየተጠባበቁ ነው ተብሏል።  እያዩ ፈንገስ የአንድ ሰው ቴያትር 'ቧለቲካ' የተሰኘው ምዕራፉ ለዕይታ ከቀረበ ከእጭር ጊዜ በኋላ ማለትም ከጥር 2 ቀን 2016 ጀምሮ የመንግስት የፀጥታ አካላት ለዓለም ሲኒማ የስራ ሀላፊዎች ባስተላለፉት ትእዛዝ  ለህዝብ እንዳይታይ መከልከሉ አይዘነጋም። Via Addis Maleda #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
👍 36👎 11🤔 7🤬 7😁 4 3😢 2
Photo unavailableShow in Telegram
ጀርመን በፍቅር ስም ሲያጭበረብር የነበረ የናይጄሪያ የማፍያ ቡድን አባላትን በቁጥጥር ስር ማዋሏን አስታወቀች የጀርመን ፖሊስ በማፍያ ቡድን ውስጥ ከፍተኛ  በፍቅር ስም የማጭበርበር ድርጊቶችን ያቀነባበሩ 11 ናይጄሪያውያንን በቁጥጥር ስር አውሏል። ይህው የብላክ አክስ የተሰኘው ቡድን በአለም አቀፍ ደረጃ "በርካታ የወንጀል ድርጊቶች" ውስጥ ይሳተፋል ሲል የባቫርያ ፖሊስ ባወጠው መግለጫ ገልጿል። በጀርመን ውስጥ ድርጅቱ የሚያተኩረው በፍቅር ቀጠሮ ማጭበርበር እና በገንዘብ ማጭበርበር ላይ ነው ሲል ሃይሉ አክሏል። መግለጫው “የውሸት መታወቂያዎችን በመጠቀም አጭበርባሪዎቹ ለምሳሌረ ለማግባት ፍላጎት እንዳላቸው በማሳየት ለተጨማሪ ግንኙነት በተደጋጋሚ በተለያዩ ሰበቦች ገንዘብ ይጠይቃሉ” ብሏል።በአለም አቀፍ ደረጃ የወሮበሎች ቡድን ዋና ዋና የስራ ቦታዎች "የሰዎች ህገወጥ ዝውውር፣ ማጭበርበር፣ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ የወሲብ ንግድ እና የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር" ናቸው። በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ሁሉም የናይጄሪያ ዜግነት ያላቸው እና ከ29 እስከ 53 ዓመት እድሜ ያላቸው እንደሆኑ ተመላክቷል። ከሁለት አመት በላይ የፈጀውን የፖሊስ ምርመራ ተከትሎ በተያዘው ሳምንት ማክሰኞ በባቫሪያ ክልል በተደረገው የፖሊስ ዘመቻ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል ። እ.ኤ.አ. በ 2021 በብላክ አክስ ላይ በተደረገው ምርመራ ቡድኑ ናይጄሪያ ውስጥ ፖለቲካ ውስጥ ዘልቆ በመግባት የግድያ ዘመሻ እንደፈጸመ የሚያሳይ ማስረጃ መገኘቱን መገናኛ ብዙሃን ዘግበው የነበረ ቢሆን የተወሰደበት እርምጃ ግን የለም። በቅድስት ደጀኔ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
👍 24 3😁 3👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
ከወላይታ ሶዶ - አዲስ አበባ የኤሌትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ ተሸካሚ ታወር ብረትን የሰረቀዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን  በሁልባራግ ወረዳ በዋጮ ሆቢሶ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሰላም መሊቅ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከወላይታ ሶዶ - አዲስአበባ የኤሌትሪክ ሀይል ማስተላለፊያ ተሸካሚ ታወር ብረትን የሰረቀዉ ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታዉቋል። ነሰሩ ወርቀ - ነጋ የተባለው ግለሰብ  ዋሚያዚያ 05 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 3:00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ ሆን ብሎ በህገወጥ መንገድ በአቋራጭ  ለመበልፀግ በማሰብ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሆነ  ከወላይታ ሶዶ -ገለን ወደ አዲሰ አበባ የተዘረጋውን ዋና የኤሌክትሪክ ኃይል 400 ኪሎ ዋት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ታወር ሰርቆ እጅ ከፍንጅ መያዙን የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሕዝብ ግንኙነትና ሚድያ ጉዳዮች ድቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ከድር  ኤርጎሻ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።                  ግለሰቡ ግምቱ እስከ 100 ሺህ ብር ሊያወጣ የሚችል የኤሌክትሪክ ሽቦ መሸከሚያ  ታወር ብረት ሰርቆ ለመውሰድ እያዘጋጀ እያለ  በአካባቢው ህብረተሰብ እጅ ከፍንጅ ተይዞ  ለሁልባራግ ወረዳ ፖሊስ ተላልፎ የተሰጠ ሲሆን ፖሊስም ተከሳሹንና የተሰረቀውን ንብረት በኢግዝቢትነት በመያዝ ቃል ከመቀበል ጀምሮ  አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን  ማስረጃዎች በማሰባሰብና ምርመራ  በማጣራት  መዝገብ  አደራጅቶ ለሁልባራግ ወረዳ  ዐቃቤ ህግ  አቅርቧል። ዐ/ህግም ተከሳሹ  በ1996  ዓ/ም  የወጣውን የኢፌዲሪ  የወንጀል  ህግ አንቀጽ  669(1)(ለ) ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ በፈጸመው  የስርቆት ወንጀል ክስ መስርቶ ለሁልባራግ ወረዳ ፍ/ቤት አቅርቧል። ፍ/ቤቱም ከዐ/ህግ የቀረበለትን  ይህንን የስርቆት ወንጀል  ክስ ከተገቢ ማስረጃዎች ጋር አገናዝቦ ከመዘነ በኋላ  በተከሳሹ ላይ  የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል። በዚህም መሠረት የሁልባራግ  ወረዳ  ፍ/ቤት  ሚያዚያ 16 ቀን 2016  ዓ/ም  ባስቻለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹን ነስሩ ወርቀነጋ ላይ የ5 አምስት ዓመት ከ6 ወር ጽኑ  ወስኖበታል ሲሉ የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሕዝብ ግንኙነትና ሚድያ ጉዳዮች ድቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ከድር  ኤርጎሻ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በበረከት ሞገስ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
👍 24😁 7👎 1👏 1🤬 1
ቬትናም የለስላሳ መጠጦች ባለሀብትን በ40 ሚሊየን ዶላር የማጭበርበር ወንጀል በስምንት ዓመታት እስራት ቀጣች የቬትናም ከፍተኛ የለስላሳ መጠጦች ባለሀብት ሐሙስ እለት በ40 ሚሊየን ዶላር የማጭበርበር ወንጀል ለስምንት አመታት በእስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል። የቬትናም መንግስት በቅርቡ በከፈተው የሙስና ዘመቻ ላይ ታዋቂው የቢዝነስ ሰው ወጥመድ ውስጥ ገብተዋል። የኮሚዩኒስት ሀገር የሆነችው ቬትናም ያለውን የሙስና ሰንሰለት ለማጥፋት በከፈተችው ሰፊ ዘመቻ ከ4,400 በላይ ሰዎች የወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል። ባለሥልጣት እና ከፍተኛ የንግድ ተቋማትን ጨምሮ የክስ ሂደት ተጀምሮባቸዋል። በመዲናዋ ሆቺ ሚን ከተማ የሚገኘው ፍርድ ቤት እ.ኤ.አ በ2019 እና በ2020 በተሰጡ ብድሮች ባለሀብቶችን በማጭበርበር የለስላሳ መጠጦች ባለ ሃብቱን ትራን ኪ ታን እና ሁለቱን ሴት ልጆቹን ጥፋተኛ ብሏቸዋል። የ71 አመቱ የመጠጥ ግሩፕ ሊቀመንበር ታን ሂፕ ፋት በብድር ላይ ዋስትና ተብሎ በተዘጋጀው ተገቢ ንብረት ላይ የማጭበርበር ወንጀል ፈጽመዋል ሲሉ የቬትናም የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። ተበዳሪዎች ገንዘቡን በወለድ ሲከፍሉ እንኳን ታህህ በተለያዩ ምክንያቶች ንብረቶቹን ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆን የመግዛት መብታቸውን ሳይቀር ጥሰዋል ብሏል። ፍርድ ቤቱ የታንህን የ 43 ዓመቷ ሴት ልጃቸውን ትራን ኡየን ፑኦንግ የኩባንያው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ስትሆን በአራት አመት እስራት እንድትቀጣ ወስኗል።የ40 ዓመቷ ታናሽ እህቷ ትራን ንጎክ በገደብ የሶስት አመት እስራት ተቀጥታች። ታን ሂፕ ፋት በታሸገ ሻይ እና በሃይል መጠጦች ከሚታወቁ የቬትናም ተቋማት መካከል ትልቁ የመጠጥ ኩባንያ ነው።አዛውንቱ ባለሃብት ታንህ በፍርድ ቤት በሰጡት የመጨረሻ ቃል በተፈጠረው ነገር ተጸጽቻለሁ እናም ሀላፊነቱን ለመውሰድ ዝግጁ ነኝ ብለዋል። ለቀጣይ ስራዬ እና ታማኝነቴ በቅርቡ ወደ ህብረተሰቡ እንድመለስ እድል እንዲሰጠኝ እፈልጋለሁ ሲሉ ታንህ ጠይቀዋል።አንዳንድ የቬትናም በጣም ስኬታማ የንግድ መሪዎች በሙስና ማጽጃ ወጥመድ ውስጥ ገብተዋል። በታሪክ ውስጥ ከታዩት ትልቅ የማጭበርበር ክሶች በአንዱ የንብረቱ ባለጸጋ ትሩንግ ማይ ላን በ27 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ኪሳራ ያስከተለውን ማጭበርበር በማቀነባበር የሞት ፍርድ ተበይኖባቸዋል። ከላን ጋር  85 ሌሎች ከፍተኛ የባንክ ባለስልጣናትን ጨምሮ ጉቦ በመቀበል እና ስልጣንን አላግባብ በመጠቀም እንዲሁም የባንክ ህግን በመጣስ ክሶች ተፈርዶባቸዋል። በመጋቢት ወር የሃኖይ ፍርድ ቤት የቅንጦት ንብረት ባለፀጋ ዶ አንህ ዱንግ በሺዎች የሚቆጠሩ ባለሃብቶችን በ355 ሚሊዮን ዶላር የቦንድ ማጭበርበር በሚል ክስ በስምንት አመት እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ማሳለፉ የሚታወስ ነው። ለሶስት አመታት በእስር ላይ የሚገኙት ዱንግ እና ልጃቸው 355 ሚሊየን ዶላር መክፈላቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
👍 23👏 5 3
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ስልክ እያነጋገሩ ያሽከረከሩ ከ6 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች መቀጣታቸው ተነገረ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመነት ባለስልጣን በ2016 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከፍጥነት ወሰን በላይ ያሽከረከሩ ከ25 ሺህ በላይ  አሽከርካሪዎችን መቅጣቱን አስታውቋል ። ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ 9 ወራት ውስጥ በ33 መንገዶች ላይ ከፍጥነት ወሰን በላይ ያሽከረከሩ 25 ሺህ 888 አሽከርካሪዎች የደህንነት ቀበቶ ያላሰሩ 3 ሺህ 800 አሽከርካሪዎች በደንብ መተላለፍ መቀጣታቸው ተገልጿል ። በተጨማሪም 204 ሞተረኞች የግጭት መከላከያ ቆብ ወይም ሄልሜት ሳያደርጉ ፣ 6504 አሽከርካሪዎች ስልክ እያነጋገሩ በመገኘታቸው በደንብ ቁጥር 395/2009 መሰረት ቅጣት እንደተጣለባቸው ተጠቁሟል ። በዚህም የተነሳ የሞት አደጋ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ6 ነጥብ 34 በመቶ  መሻሻል መታየቱን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣኑ ያገኘው መረጃ ያመላክታል ። በአበረ ስሜነህ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
👍 16😁 6 5👏 1🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
ጎማ የተገጠመለት ተንቀሳቃሽ የአስክሬን ሳጥን ተሽከርካሪ በ29 ሺ የአሜሪካን ዶላር ገደማ መሸጡ ተሰማ ጎማ የተበጀለት የአስክሬን ሳጥን በተሽከርካሪ መልክ መቅረቡን ተከትሎ በ28,750 የአሜሪካን ዶላር የተሸጠ ሲሆን ያልተለመደው የሳጥኑ ቅርፅ መኪና ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። እኤአ በ1965 ለእይታ ይቀርብ ከነበረው የቴሌቭዥን ተከታታይ ዘ ሙንስተር ትዕይንት ላይ ድራግ-ዩ-ላ የአስክሬን ሳጥን ተሽከርካሪ መነሳሻ ሆኖ እንደተሰራም ተሰምቷል።ይህ ያልተለመደ የአስክሬን ሳጥን ተሽከርካሪ የሳጥን-ፍሬም እና ስምንት የፋይበርግላስ ሳጥን በመጠቀም ስራ ላይ ውሏል። የሹፌሩ መቀመጫ የተበጀለት ሲሆን ለተመለከተው በሙሉ እውነተኛ አስክሬን የጫና እንዲመስል ሆኖ ተሰርቷል። የተሟላ ሰፊ የኋላ ጎማዎች በእሽቅድምድም ተንሸራታች ተደርገው የተሰሩ ሲሆን፣ ቀጥ ያሉ የጭስ ማውጫ ቱቦዎች እና የፋኖስ አይነት መልክ ያላቸው መብራት የተሞላው ይህ የሬሳ ሳጥን መኪና ከትክክለኛው ለመንገድ ብቁ ነው ከሚባለው ተሽከርካሪ ይልቅ ለፊልም የሚውል ንድፈ ሀሳብ ይመስላል። ነገር ግን ይህው የአስክሬን ሳጥን ተሽከርካሪ በኒውዮርክ ተመዝግቧል። በምዝገባውም በ1928 ፎርድ እና ትክክለኛ የሰሌዳ ቁጥር ተሰጥቶታል። የሹፌሩ ክፍል በሬሳ ሣጥኑ የኋላ ክፍል ላይ የሚገኝ ሲሆን አነስተኛ መቀመጫ በሰማያዊ ጨርቃ ተሸፍኗል። ቼቭሮሌት ቪ8 ሞተር በሻሲው ማእከሉ ወደ ኋላ ተቀምጧል። ባለአራት በርሜል ካርቡረተር፣ የኤደልብሮክ ማስገቢያ መያዣ እና ሪብብ ቫልቭ አሉት። የማርሽ ሳጥኑን በተመለከተ አውቶማቲክ ሲሆን በወርቅ ቀለም በተቀባ የጽጌረዳ ዘዬዎች ተቀርጿል። የነዳጅ ማጠራቀሚያው ወደ ተሸከርካሪው አፍንጫ አቅጣጫ ላይ ተቀምጧል ።ጎልቶ እንዲታይ ለማድረግ በወርቅ ቀለም የተቀባ ነው፤ ምክንያቱ ደግሞ ሌሎች ጎልተው እንዲታዩ የሚገባቸው የተሽከርካሪው ክፍል አካል ሲሆን ለምሳሌ እንደ መቃብር ላይ ሀውልት ከፊት ለፊት ያለው የመቃብር ድንጋይ እና ግዙፍ የጭስ ማውጫዎች ለማመሳሰል ተሞክሯል።ልዩ የሆነው ተሽከርካሪ ኦዶሜትር የተገጠመለት ስላልሆነ አጠቃላይ የኪሎሜትር ርቀት አይታወቅም። በሰዓት በምን ዓይነት ፍጥነት እንደሚጓዝ ምንም አይነት መረጃ ማግኘት አልተቻለም። ነገር ግን ተሽከርካሪው የውድድር መኪና እንዳልሆነ ይታወቃል ተብሏል።የአስክሬን ሣጥን መኪናው ባለፈው ሳምንት በ28,750 ዶላር የተሸጠ ሲሆን፥ መኪናውን በተለያዩ ዝግጅቶች ጨረታ በማሸነፍ እና ልዩ ልዩ ምርቶችን በመሰብሰብ የሚታወቅ ድርጅት የግሉ አድርጎታል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
👍 20😁 19🤔 7👎 2 1
አሜሪካ ዩክሬንን ለመርዳት የረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን በድብቅ መላኳ ተነገረ ዩክሬን ዩናይትድ ስቴትስ በድብቅ የሰጠችውን የረዥም ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን በሩሲያ ወራሪ ሃይሎች ላይ መጠቀም መጀመሯን የአሜሪካ ባለስልጣናት አረጋግጠዋል። መሳሪያዎቹ በመጋቢት ወር በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የፀደቀው የ300 ሚሊዮን ዶላር የእርዳታ ጥቅል አካል ሲሆኑ በዚህ ወር ዩክሬን ደርሰዋል። በሩሲያ በተያዘችው የዩክሬን ግዛት ክሬሚያ ድራስ ኢላማዎችን ለመምታት ቢያንስ አንድ ጊዜ ጥቅም ላይ ውለዋል ሲል የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋ። ባይደን በተመሳሳይ አሁንም ለዩክሬን የ61 ቢሊዮን ዶላር የእርዳታ ፓኬጅ ፈርመዋል። ዩናይትድ ስቴትስ ከዚህ ቀደም ለዩክሬን መካከለኛ ክልል የሚደርሱ የጦር ሃይል ታክቲካል ሚሳኤል ሲስተም አቅርባ ነበር። ነገርግን የበለጠ ኃይለኛ የጦር መሳሪያዎችን ለመላክ ፍቃደኛ ሳትሆን የቀረች ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ በከፊል የአሜሪካን ወታደራዊ ዝግጁነት ለመጉዳት ያሳስባል በሚል ነበር። ሆኖም ባይደን በየካቲት ወር እስከ 300 ኪ.ሜ የሚተኮሱ የረዥም ርቀት የሚሳኤል ስርዓትን ለዩክሬን ለመላክ አረንጓዴ መብራትን በድብቅ መስጠታቸው ተነግሯል። የስቴት ዲፓርትመንት ቃል አቀባይ ቬዳንት ፓቴል "ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የረጅም ርቀት ሚሳኤል መሳሪያብ በፕሬዝዳንቱ ቀጥተኛ መመሪያ እንደሰጠች አረጋግጠዋል። ከመሳሪያዎቹ ውስጥ ምን ያህሉ እንደተላከ ግልጽ ባይሆንም የዩናይትድ ስቴትስ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን ዋሽንግተን ተጨማሪ ለመላክ አቅዳለች ብለዋል። ረጅም ርቀት የሚጓዙ ሚሳኤሎች ባለፈው ሳምንት ለመጀመሪያ ጊዜ በክራይሚያ የሚገኘውን የሩሲያ አየር መንገድ ለመምታት ጥቅም ላይ መዋላቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ስማቸው ያልገለጻቸውን የአሜሪካ ባለስልጣን ጠቅሶ ዘግቧል። አዲሶቹ ሚሳኤሎች ማክሰኞ እለት በሞስኮ በተያዘችው የዩክሬን የወደብ ከተማ በርዲያንስክ ውስጥ በሩሲያ ወታደሮች ላይ በተሰነዘረ ጥቃትም ጥቅም ላይ ውለዋል ሲል ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል። በቅርብ ወራት ኪየቭ የጥይት ክምችቷ በመሟጠጡ እና ለሩሲያ ይህ ሁኔታ ቀጣይነት ያለው ትርፍ ስለሚያስገኝ በሚል ለምዕራቡ ዓለም የእርዳታ ጥሪዋን እያጠናከረች ትገኛለች። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
👎 17👍 14🤬 4
Photo unavailableShow in Telegram
👍 2
ባለፉት 9 ወራት ውስጥ በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ 392 ድንገተኛ አደጋዎች አጋጥመዋል በአደጋዎቹም  56 ሰዎች ህይወታቸውን ማጣቸውን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ አዲስ አበባና አካባቢዋ በዘጠኝ ወራት ውስጥ  392 አደጋዎች የተከሰቱ ሲሆን በአደጋውም 670 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን  የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዢን ተናግረዋል። የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአደረጉት ርብርብ ከ11.5 ቢሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳንም ተችሏል። የሞት አደጋ ካጋጠማቸው ውስጥ ሁለቱ ብቻ በእሳት አደጋ ሲሆን የሀምሳ አራቱ ህይወት ያለፈው በኮንስትራክሽን አደጋ፣ ተቆፍሮ ክፍቱን በተተዉና ዉሀ በአቆሩ ጉድጓዶች ዉስጥ እንዲሁም ምክንያታቸዉ በፖሊስ እየተጣራ ባሉ ጉዳዮች መሆናቸውን  አቶ ንጋቱ ጨምረውም  ተናግረዋል። ህይወታቸዉ አልፎ የተገኙትን  የሀምሳ አራቱን ሰዎችን አስከሬን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አንስተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል። በደረሱት አደጋዎች የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአደረጉት ጥረት 39 ሰዎችን ከእሳት አደጋ 85 ሰዎች ደግሞ ከሌሎች ድንገተኛ በድምሩ 125 በአደጋ ዉስጥ የነበሩ ሰዎችን ማትረፍ መቻሉን ኮሚሽኑ አስታውቃል። ከደረሱት የእሳት አደጋዎች ዉስጥ 41 የመኖሪያ ቤት 35 የንግድ ቤቶች ላይ የተከሰተ ሲሆን ሀያ ሁለቱ የጎርፍ አደጋዎች ናቸዉ ተብላል። በዘጠኝ ወሩ የደረሱ አደጋዎች ከአምና ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር የንብረት ወድመት መጠን በ37 ሚሊየን ብር የቀነሰ ሲሆን የአደጋ ቁጥር በ4 ጨምሯል። በትግስት ላቀዉ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
💔 6😢 4👍 2🤯 2
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
በአርጀንቲና መንግስት ለትምህርት የሚያደርገዉን ድጎማ በማቋረጡ ከፍተኛ ተቃውሞ ተነሳ በመላው አርጀንቲና የትምህርት ወጪ መቀነስን በመቃወም ታላቅ ሰልፎች ተካሂደዋል።የፕሬዚዳንት ጃቪየር ሚሌ አክራሪ የቁጠባ እርምጃዎች በህዝብ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የሚያስከትለውን ውጤት በመቃወም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አርጀንቲናዉያን ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮች ከሀገሪቱ ኃያላን የሰራተኛ ማህበራት እና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመቀላቀል ተቃዉሞ አሰምተዋል። የቀኝ አክራሪው ፕሬዝደንት በታህሳስ ወር ስልጣን ከያዙ በኋላ በደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ተከታታይ ተቃውሞዎች የተደረጉ ሲሆኑ የአሁኑ በተገኘዉ ህዝብ ብዛት ትልቁ ነዉ ተብሏል፡፡አስተባባሪዎች ዩንቨርስቲዎችን የመዝጋት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ያሉትን የበጀት ቅነሳን ለመቃወም ጥሪ አቅርበዋል። የቦነስ አይረስ ዩኒቨርሲቲ በዋና ከተማው ብቻ በተቃውሞው ላይ ከ500 ሺ በላይ ሰዎች መሣተፋቸውን ገልጿል።ሚሌ በምርጫ ዘመቻው ወቅት የህዝብ ወጪን ለመቀነስ እና የመንግስትን ከባድ የኢኮኖሚ ፈተናዎች ለመፍታት እየሰሩ ይገኛል፡፡ኢኮኖሚውን ለማስተካከል የተወሰኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን መዝጋት፣ የባህል ማዕከላትን ከጥቅም ውጪ ማድረግ፣ የመንግስት ሰራተኞችን ማሰናበት እና ድጎማዎችን ማቋረጠ ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከል ናቸዉ፡፡ በኤደን ሽመልስ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
👍 15🔥 4 2
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እቅድ እንዳላትና ለእርሱም እየሰራች ነዉ ተባለ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አመታት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድርን እንድታዘጋጅ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ታዝቧል። የአፍሪካ ዋንጫን እ.ኤ.አ በ 2029 ወይም በ2031 ለማዘጋጀት እየሰራን ነው ያሉት ሚኒስትሩ ለእቅዱ መሳካትም ቢያንስ ስድስት ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞች አስፈላጊ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ካፍ ከዚህ በፊት ያልነበሩ አዳዲስ መስፈርቶችን በማስቀመጡ ኢትዮጵያ አንድም ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም እንዳይኖራት አድርጓል ሲሉም አቶ ቀጀላ መርዳሳ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ የካፍን ደረጃ የሚመጥኑ ስታዲየሞች የሌላት በመሆኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ረዘም ላሉ ጊዜያት ከሀገሩ ዉጪ ለመጫወት ተገድዶ የነበረ መሆኑ ይታወቃል። የዉድድሩ አዘጋጅ ሀገራት ቢያንስ ስድስት ስታዲየሞችን እንዲያዘጋጁ ካፍ ቢያዝም ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ምን ያህል ዝግጁ ናት የሚለዉ ግን አጠያያቂ ነዉ። Via ዋልታ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
😁 157👍 26🤔 6👏 3
16 ሰው ጭኖ ከመቐለ ከተማ በመነሳት ወደ ውቕሮ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረ ተሽከርካሪ ላይ አደጋ ማጋጠሙ ተነገረ ቶዮታ ሚኒባስ ወይንም ሀይሩፍ በመባል የምትታወቅ ተሽከርካሪ በትናንትናው እለት ሚያዝያ 16 ቀን 16 ሰዎችን አሳፍራ ከመቀለ ከተማ በመነሳት ወደ ውቅሮ ከተማ በመጓዝ ላይ ሳለ አጉላዕ ተብሎ በሚታወቅ ስፍራ ባለ ቁልቁል መግቢያ ላይ የመገልበጥ አደጋ ደርሶበታል። አደጋው የደረሰው ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ሲሆን ተሳፋሪዎቹ ላይ ይህ ነው የሚባል ከባድ ጉዳት እንዳልደረሰባቸው እና ቀላል ጉዳት ያጋጠማቸውም ተሳፋሪዎች በውቅሮ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ተገልጿል ። የአደጋው መንስኤ ይፋ ያልተደረገ ቢሆንም ከተሳፋሪዎቹ በተገኘ መረጃ መሰረት የአደጋው መንስኤ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር ሊሆን ይችላል ተብሏል። በሚሊዮን ሙሴ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
👍 20😢 12🙏 6💔 3👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
የሊጉ ተፎካካሪዎች ሚኬል አርቴታ 🤝 ፔፕ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
💯 29👍 20👎 5 4
🇬🇧 29 ኛ ሳምንት እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታዎች                     የጨዋታ አጋማሽ ውጤት '        🇬🇧 ኤቨርተን 1-0 ሊቨርፑል 🇬🇧       🇬🇧  ማን ዩናይትድ 1-1 ሼፊልድ 🇬🇧      🇬🇧 ክሪስታል ፓላስ 0-0 ኒውካስትል 🇬🇧         ጎሎቹን ለመመልከት 👉 @mikoethio                        #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
👍 26🤩 10👎 1 1
ዘ-ሪፖርተር ጋዜጣ ያወጣው ዘገባ ፍፁም የተሳሳተ ነው - የትግራይ ጄኖሳይድ ኮምሽን ሰሞኑን ዘ-ሪፖርተር ጋዜጣ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር የሆኑት አቶ የማነ ዘርአይን በመጥቀስ የሰራውን ዘገባ በመቃወም ኮሚሽኑ በዛሬው ዕለት መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫውም ሚያዝያ 12 ቀን 2016 ዓ/ም ሪፖርተር ጋዜጣ የኢንግሊዘኛው እትም " የትግራይ ጄኖሳይድ ኮሚሽን ከፌደራል መንግስቱ እውቅና ተሰጠው" ፣ "የትግራይ ጄኖሳይድ ኮሚሽን ከፌደራል መንግስትና ከዓለም ባንክ ጋር በትብብር መስራት መጀመሩን ገለፀ" በማለት የተሰራጩት ዘገባዎችን ነው ሓሰተኛና ከእውነት የራቁ ሲል ኮሚሽኑ የገለፃቸው። አያይዞም ከፌደራል መንግስቱ ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግኑኙነት ኖሮት እንዲሰራ እሚጠበቀው በጊዝያዊ አስተዳደሩ ስር እሚገኘው የዳግም ግምባታ ፅህፈት ቤት ነው በዛ መሰረትም ከዓለም ባንክና ከገንዘብ ሚኒስተር ጋር አብሮ እየሰራ ነው ብሏል። እኛ እዚህ ላይ ማድረግ እሚጠበቅብን አስፈላጊ መረጃዎችንና ግኝቶችን ለፅሕፈት ቤቱ ማቅረብ ዠና ቴክኒካዊ እገዛ ማድረግ ነው እሱንም እየሰራን ነው ከዚህ ውጭ ግን የኮሚሽኑ በስልጣንም ሆነ ቅርፅ አልተቀየረም ሲል በመግለጫው አስታውቋል። አያይዞም ኮሚሽኑ ዘ-ሪፖርተር በሰራው ዘገባ ላይ ኮሚሽኑ ህግ ነክ የሆኑ ፆታዊ ጥቃትን እንዲሁም የሰብአዊ መብት ጥሰት የተመለከቱ ግኝቶች ከሪፖርቱ እንደቀነሳቸው ተደርጎ የተዘገውም ፍፁም ስህተትና እርማት እሚያሰፈልገው ነው ሲል ገልፆታል። ኮሚሽኑ በሰሜን ኢትዮጲያ ጦርነት መካከል በ2014 ዓ/ም በይፋ የተመሰረተ ሲሆን በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው አካላት በጥናት በመለየት ፍትህ እንዲያገኙ እንዲሁም ግኝቶቹን እንደመነሻነት በመጠቀም ለዳግመ ግንባታ ስራዎች ግብአት እንዲሆኑ አለሞ በመስራቶ ላይ ያለ እንደሆነ ተነግራል።
إظهار الكل...
👍 15 5👏 2🔥 1😁 1
ከኢትዮጵያ ከ 350 በላይ ስደተኞች ወደ አሜሪካ ማቅናታቸውን አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይኦኤም አስታወቀ በተያዘዉ 2016 ዓመት ሰኔ ወር 4ሺ6 መቶ 8 ስደተኞች ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አይ ኦ ኤም አስታውቋል። አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን በላከው መግለጫ እንደሚያሳያው ድርጅቱ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመነጋገር እና በመተባበር በኢትዮጵያ የሚገኙ የሶስተኛ ሀገር ስደተኛ ዜጎች ወደ አደጉ ሀገራት የማሸገር ስራ ይሰራሉ፡፡ አይኦኤም በመልሶ ማቋቋሚያ ስር  ውስጥ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደ አሜሪካ እንዲደርሱ ለማድረግ ተከታታይ የቻርተር በረራ እንቅስቃሴዎችን እና እንዲሁም በንግድ አየር መንገዶች ላይ የቡድን ምዝገባዎችን ያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ድጋፍ ያለው የዩናይትድ ስቴትስን የ2024 የስደተኞች መጤ ግብ ለማሳካት የስደተኞችን መልሶ የማቋቋም ስራ እያሰፋ ይገኛል።ዩናይትድ ስቴትስ በ2024 ከ4ሺ500 በላይ ስደተኞችን ከኢትዮጵያ ለመቀበል ቃል መግባቱን አይኦኤም አስታውቋል፡፡ ባለፉት አስርት አመታት ውስጥ ብቻ አይኦኤም ከ1.19 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን እና ሌሎች ስጋት ያለባቸውን በአለም ዙሪያ ካሉ 166 አካባቢዎች የመቋቋሚያ እንቅስቃሴዎችን አዘጋጅቶ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል።በ2023 አይኦኤም 5ሺ3 መቶ4 ስደተኞችን ኢትዮጵያ አስፍሯል። ከእነዚህ ውስጥ 1ሺ1መቶ 94ቱ ወደ አሜሪካ አቅንተዋል። በትግስት ላቀው #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
👍 28 6👎 1😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
3
ቻይናዊው የ88 ዓመት አዛውንት ጥንካሬያቸውን እንደጠበቁ በሞዴሊንግ ኢንዱስትሪው ላይ ተፅእኖ መፍጠር መቀጠላቸው ተሰማ ዋንግ ደሹን የሚባሉት አዛውንት እ.ኤ.አ በ2015 በቻይና ፋሽን ሳምንት በቤጂንግ በተካሄደው የመጀመሪያ የሞዴሊንግ ስራቸው ላይ ከታዩ ወዲህ 88ኛ ዓመታቸው ላይ እስኪደርሱ ድረስ በስኬት መቀጠላቸው አነጋጋሪ ሆኗል። በቻይና የፋሽን ሳምንት በ79 ዓመታቸው ብቅ ካሉ ወዲህ በሁሉም ሰው አእምሮ ውስጥ መቅረት ችለዋል። ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት ደግሞ በዓለም ላይ ካሉ ታላልቅ የፋሽን ተቋማት የአብረን እንስራ ጥያቄ እየቀረበላቸው ቀጥለዋል።እ.ኤ.አ በ 1936 መካከለኛ ገቢ ካላቸው እና ዘመናዊ ከሆነ ቤተሰብ ውስጥ የተወለዱት ዋንግ ዱሹን አስር ልጆች ላሉበት ቤተሰብ ሁለተኛ ትልቁ ልጅ ነበሩ። ወላጆቻቸው ህልሜን እንድከተል ያበረታቱኝ ነበር ሲሉ አዛውንቱ ይናገራሉ። ተዋናይ ሆነው ሰርተዋል በበርካታ የጥበብ ስራዎች ቢሳተፉም በፋሽን ሞዴሊንግ ላይ ግን የሚያስደንቅ ስኬት ላይ ደርሰዋል። እውቅናቸውን ተከትሎ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የአውሮፕላን አብራሪ ፈቃድ ማግኘትን ጨምሮ ሞተር ሳይክልና ፈረስ መንዳት ተምረዋል።ሰዎች በፈለጉት  ጊዜ ህይወታቸውን ለመለወጥ አቅም አላቸው ሲሉ ዋንግ ለታይምስ ተናግረዋል። በአእምሮ ጤናማ መሆን ማለት ምን ማድረግ እንዳለብህ ታውቃሉ ማለት ነው። ህልምህን ለመከታተል ዕድሜ በጭራሽ እንቅፋት ሆኖ አያውቅም ሲሉ ይደመጣሉ። ዋንግ ደሹን ወደ ፋሽን ሞዴሊንግ ኢንዱስትሪ የገቡት ስህተት በሆነ አጋጠሚ ነው። ቻይናዊቷ ዲዛይነር ሁ ሸጉዋንግ ከቻይና ፋሽን ሳምንት አዘጋጅ ዲጄ ጋር እየተጋገረች ነበር፣ በዚህ ውይይት ላይ ሌላ ኪው ኪው የምትባል ሴት በድንገት ስልኳ ይጠራል። ምላሽ ለመስጠት ለመስጠት ስልኳን ስታነሳ ስክሪኑ ላይ የአንድ አዛውንት ፎቶ ከወገብ በላይ ራቁታቸውን ሆነው ይታያሉ።ይህንን ምስል ደግሞ ዲዛይነሯ በድንገት ትመለከተዋለች እኚህ አዛውንት ደግሞ የኪውኪው አባት ዋንግ ነበሩ። ዲዛይነሯ እኚህ ሰው በፕሮግራሙ ላይ እንዲገኙ እፈልጋለው በማለቷ ስራውን ጀምረዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለተለያዩ ፋሽን ዲዛይነሮች በበርካታ ማስታወቂያዎች ላይ ኮከብ ሆነዋል ።ዋንግ ደሹን አሁንም በ88 ዓመታቸው ጠንካራ ሲሆኑ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በሻንጋይ ፋሽን ሳምንት ደምቀው ታይተዋል።አብዛኞቹ በ30ዎቹ መጀመሪያ ላይ ጡረታ በሚወጡበት የሞዴሊንግ ዘርፍ፣ ዋንግ ደሹን በህይወታቸው ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ስኬታቸውን ካገኙ ጥቂት ሞዴሎች መካከል አንዱ ሲሆኑ እንደ ካርመን ዴል ኦሬፊስ፣ የአለማችን አንጋፋ የፋሽን ሞዴል እና ከሌላኛዋ የእስያ አንጋፋ ሞዴል አሊስ ፓንግ ተርታ ተመድበዋል። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
👍 31👏 4 3😁 2
ኢትዮ ቴሌኮም በአገር አቀፍ ደረጃ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አስጀመረ ብሔራዊ መታወቂያ ዜጎች ታማኝነት ያለው መለያ እንዲኖራቸው የሚያስችል መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል። ዲጂታል  መታወቂያ አካታች ዲጂታል ኢኮኖሚን የሚፈጥር እንደሆነ የተናገሩት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዲጂታል መታወቂያው በሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ሁሉም ተሳታፊ እንዲሆን ያደርጋል ማለታቸውን ብስራት ሬዲዮና ቴሌቭዥን ሰምቷል። ሀገራት ለዜጎቻቸው ታማኝነት እና እውቅና ያለው መለያ የመስጠት ግዴታ አለባቸው። መለያዎቹ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ላይ ነዋሪዎች እኩል አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል ብለዋል። የንግድ ተቋማትም መለያውን መሰረት አድርገው አዳዲስ ምርቶችን ለገበያ ማቅረብ እንዲችሉ ያደርጋቸዋል።እንዲሁም ለኢትዮ ቴሌኮም የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያደርግ እንደሆነ እና በርካታ ችግሮችን ለመፍታት እድሎችን የሚፈጥር መሆኑን ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል። በምህረት ታደሰ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
14👍 11👎 8🔥 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
የግለሰብ መኖሪያ ተደርምሶ ከሞቱ 7 ሰዎች  መካከል የአራት አመት ህፃን መኖሩ ተነገረ 👉🏼 በአትክልት ተራ የሚሰሩት አባወራ አስቀድመው ለሊት 9 ሰአት ከቤት መውጣታቸው በህይወት ቢተርፉም በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን አጥተዋል በአትክልት ተራ የሚሰሩት አባወራም አስቀድመው ለሊት 9 ሰአት ከቤት መውጣታቸው በህይወት እንዲተርፉ ቢያደርጋቸውም በቤት ውስጥ ተኝተው ትተዋቸው በሄዱበት አጋጣሚ ሚስታቸውን እና ቤተሰባቸው የግንባታው እቃ ተደርምሶ እንደሞቱባቸው አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እያ ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ዛሬ በአዲስ አበባ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ጠሮ መስኪድ አካባቢ ለሊት 11:00 ሰዓት ላይ እየተገነባ ያለ የግለሰብ ቤት የግንባታ እቃ ተደርምሶ የ7ሰዎች ህይወት ማለፉን ብስራት መዘገቡ ይታወሳል። በአደጋው ከሞቱት ሰባት ሰዎች ውስጥ አራቱ ሴቶች ሲሆኑ የ28 ፤የ25 ፤የ12 አና የ11 ዓመት መሆናቸው አቶ ንጋቱ የተናገሩ ሲሆን ከሞቱት መሀከል የ30 የ12 እና የአራት አመት እድሜ ያላቸው ወንዶች ህይወታቸውን አተዋል። በትግስት ላቀዉ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
😢 42👍 11💔 4 1
Photo unavailableShow in Telegram
በጎርፍ የተከበበውን ኬንያዊ ህፃን በአስደናቂ ሁኔታ መታደግ መቻሉ ተነገረ ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ 120 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ያታ ከተማ በጎርፍ ለብቻው የታገተው የአምስት አመት ልጅ በፖሊስ ሄሊኮፕተር ህይወቱን መታደግ ተችሏል። የህፃኑ ልጅ "የውሃው መጠን መጨመር ሲጀምር ወላጅ አባቱ ጥለውት መሄዳቸውን" ፖሊስ ተናግሯል። የልጁን ቦታ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በመጠቀም የተቆጣጠረው አለማቀፉ የሰብአዊ እርዳታ በጎ አድራጎት ሴንተር ለፖሊስ ያሳወቀ ሲሆን ሄሊኮፕተሩን ከናይሮቢ በመላክ የነፍስ አድን ስራው ተግባራዊ ሆኗል። ህፃኑን በጀልባ ለማዳን የተደረገው የመጀመሪያ ሙከራ ምቹ ባልሆነ የአየር ሁኔታ ምክንያት ሳይሳካ መቅረቱን የኬንያ ቀይ መስቀል አስታውቋል። አክለውም “ሕፃኑ ለረጅም ጊዜ በጎርፉ ተከቦ በመቆየቱ የነፍስ አድን ስራው ከተከናወነ በኃላ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታል ተወስዷል። ከቀናት በፊት በኬንያ እና በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ እና  ውድመት አስከትሏል። በኬንያ የጎርፍ አደጋው በ 23 የሀገሪቱ 47 አውራጃዎች ተመዝግቧል ፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎችን በጎርፍ እንዲከበቡ ምክንያት ሆኗል። የጎርፍ አደጋ ከተከሰተ ውዲህ ከ188 በላይ ሰዎች መታደጉን የኬንያ ቀይ መስቀል አስታውቋል። የጎርፍ አደጋው ተከትሎ 11 ሺ 2 መቶ 6 አባወራዎችን ከመኖሪያ ቀያቸው ሲያፈናቅል 27 ሺ 7 መቶ 16 ሄክታር መሬት ውሰጥ የነበረ ምርትን አውድሟል።ከ4,800 በላይ የቤት እንስሳትን መሞታቸውንም የኬንያ ቀይ መስቀል ይፋ አድርጓል። በሚሊዮን ሙሴ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
👍 23 5👏 4🥰 1😁 1😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኢትዮጵያ የሚገኙ የሰባት አገራት ኢምባሲዎች የትግራይን ግዛቶችን "አወዛጋቢ ቦታዎች" በሚል ቃል መግለጣቸውን የትግራዩ ተቃዋሚ ሳልሳዊ ወያነ  ኮነነ ፖርቲው፣ "አወዛጋቢ" የተባሉት አካባቢዎች "በኃይል የተያዙ የትግራይ ግዛቶች እንጅ ውዝግብ የተነሳባቸው አይደሉም" ብሏል። ኤምባሲዎቹ የትግራይ ግዛቶችን በኃይል የያዙ ኃይሎች በመውጣታቸው አስፈላጊነት ላይ አጽንዖት እንዲያደርጉ ፓርቲው ጠይቋል። የአሜሪካ፣ ብሪታንያ፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያንና ጃፓን ኢምባሲዎች፣ በሰሜን ኢትዮጵያ "ውዝግብ ባለባቸው አካባቢዎች" የተፈጠረው አዲስ ውጥረት እንዳሳሰባቸው ቅዳሜ እለት ባወጡት መግለጫ መግለጣቸው አይዘነጋም። #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
😁 15👍 13 2💯 1
Photo unavailableShow in Telegram
ቦትስዋና የዩናይትድ ኪንግደም ስደተኞችን እንድትቀበል የቀረበላትን ጥያቄ ውድቅ አደረገች የቦትስዋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለደቡብ አፍሪካ የቴሌቭዥን ጣቢያ እንደተናገሩት የብሪታንያ መንግስት ከእንግሊዝ የተባረሩ ስደተኞችን ለመቀበል ሀገሪቱ ፈቃደኛ መሆን አለመሆኗን መጠየቃቸውን ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ይህ ጥያቄ መቼ እንደቀረበላቸው ከመናገር ተቆጥበዋል።የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት በቦትስዋና፣ አርሜኒያ፣ አይቮሪ ኮስት እና በኮስታ ሪካ ሩዋንዳ ስደተኞችን ለመቀበል የተስማማችበትን እቅዱን ለመድገም እንደሚፈልግ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በብሪቲሽ ፕሬስ ላይ ያልተረጋገጡ ዘገባዎች መውጣታቸው ይታወሳል። በኒውዝሮም አፍሪካ በተሰኘ ፕሮግራም ላይ በተደረገ የስልክ ቃለ ምልልስ ሚኒስትሩ ሌሞጋንግ ክዋፔ እንደተናገሩት ቦትስዋና የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ጉዳይ ሚኒስትር በ‹‹ዲፕሎማቲክ ቻናል›› በኩል የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ አድርጋለች ብለዋል። ክዋፔ ቦትስዋና ከብሪታንያ የሚመጡ ስደተኞችን መቀበል አትችልም ምክንያቱም የራሷን የኢሚግሬሽን ጉዳዮች እያስተናገደች ነው ብለዋል። "የብሪታንያ መንግስት እነዚህን ሰዎች በአገራቸው እንዲኖሩ ስለማይፈልግ በሩቅ አገር እንዲቀብሩአቸው ይፈልጋል ሲሉ ተደምጠዋል። በራሳችን ቀጠና ያለውን ችግር እየፈታን በመሆኑ ያልተፈለጉ ስደተኞችን ከሌላ ሀገር መቀበል ለቦትስዋና ፍትሃዊ አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል። በሌላ በኩል የዩናይትድ ኪንግደም ፓርላማ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ የሚሰደዱበትን መንገድ የሚከፍተውን አወዛጋቢውን ህግ በማፅደቁ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣናት ያለቸውን ስጋት አንስተዋል። ስደተኞች ወደ እንግሊዝ በህገ ወጥ መንገድ እንዳይገቡ ለማድረግ ያለመ የሩዋንዳ ሴፍቲ ወይን የጥገኝነት እና ኢሚግሬሽን ህግ ለወራት ከዘለቀው አለመግባባት በኃላ ሰኞ እለት ፀድቋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ቱርክ በጋራ በሰጡት መግለጫ የእንግሊዝ መንግስት እቅዱን እንደገና እንዲያጤነው ጠይቀዋል። ይህ ህግ በሰብአዊ መብቶች ላይ "ጎጂ ተጽእኖ ይኖረዋል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ህጉ "የስደተኞች ስምምነትን መጣስ" ነው ሲሉ አክለዋል ። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
إظهار الكل...
👍 17 1👏 1😁 1🤔 1