cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ሰላም ለኪ ቅድስት ቤ/ክ

የኢኦተቤክ ሥርዓት የጠበቀ መንፈሳዊአገልግሎት ቃለወንጌል;መዝሙር;ስነጽሁፎች እንድሁም የቤተክርስቲያን ጉዳይ እናወራበታለን Addsile ✞ewahidoeminet ቢያንስ21sew join$share

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
194
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

إظهار الكل...
EwnetMedia 2021

ኦርቶዶክስን በኦርቶዶክሳውያን የማዳከም አዲስ ስልት! ((ከ ‹‹ግንጊልቻ›› መጽሐፍ፣ ምዕ.4፥ ገጽ.89-92 ላይ ባለው ሐሳብ መነሻነት የተጠናቀረ)) ==================================  (ለተሻለ ግንዛቤ ሙሉውን ያንብቡት፤ ጽሑፉን #Share ቢያደርጉ ደግሞ ሌሎችንም ይጠቅማሉ!) `````````````````````````````````````````````````````````````````````` ባለፉት የታሪክ ገጽታዎቻችን ውስጥ በጉልበትና በይፋዊ ተቃርኖ ኦርቶዶክስን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ሲደረጉ የነበሩ እንቅስቃሴዎች ኹሉ አልተሳኩም፤ እንዲያውም የበለጠ ሲያጠናክሯትና ሲያስፋፏት ተስተዋሉ እንጂ፡፡ ለምሳሌ፡- በግራኝ አህመድ ወረራ ዘመን ኦርቶዶክሳውያኑን በግዳጅ የማስለም ድርጊቶች ተፈጽመው ነበር፤ ሕዝቡም ወደ እስልምና ሲገባ አምኖበት ሳይኾን ተገዶ ስለነበር ጊዜ እስኪያልፍ በትዕግሥት ሲጠባበቅ…

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን #በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን #አሰሮ ለሰይጣን #አግዐዞ ለአዳም ሰላም #እምይዕዜሰ #ኮነ ፍሥሐ ወሠላም #ለመሆኑ .ዘፈን ጥበብ ነዉን? አወን ጥበብ ነዉ ከእግዚአብሔር. ሳይሆን ከሰይጣን የተገኘ ጥበብ!! ቅዱስ ሳይሆን እርኩስ.ጥበብ ነዉ.መዳኛ ሳይሆን መጥፊያ ጥበብ ነዉ የህይወት ጥበብ ሳይሆን የሞት ጥበብ ነወ። ቅዱስ ጳዉሎስ የዚች ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞኝነት ነዉ። ብሏል !! እግዚአብሔር ድምፅ የሰጠን እርሱን እድናመሰግንበት እርሱን እንድናወድሰዉ እርሱ. የፈቀደላቸዉን እርሱ ያከበረላቸዉን ቅዱሳን. እንድናመሰግንበት.እንጅ ለሰዉ እንድንዘፍን. አይደለም ወይ የእግዚአብሔር ወይ የዓለም ልንሆን ግድ ይለናል ሁለት ጌታ የለም !!! ዘፈን መዝፈን ድብን ያለን ኃጢአት ነዉ። አሁን ባለንበት ዘመን ኃጢአት እንደሆነ የዲያቢሎስ ታላቅ መሳሪያ እንደሆነ. በግልፅ እየተመለከትን ነዉ። አንዳንዶቹ ዘፈን ስራ ነዉ የሚሉ አሉ. አወ ለሌባም መሰረቅ. ስራ ነዉ። ለዝሙት አዳሪዋም. ዝሙት ስራዋ ነዉ። ለቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይም መግደል ስራዉ ነዉ። ግን ደግሞ ኃጢአት ናቸዉ ስራ ነዉ ብሎ ኃጢአትን ማስቀረት አይቻለም። እንግዳዉስ ምን እንላለን ኃጢአት ስራ ነዉ ብለን ሙግት.እንገጥማለንን?? አንዳንዶች ደግሞ. ዋናዉ መልዕክቱ ነዉ የሚሉ አሉ እራሳቸዉን ሲያታልል ነዉ እንጅ. ማንም ይዝፈነዉ ዘፈን ኃጢአት ነዉ !!! መልከኛ በለዉ ድምፁ የሚያምር በለዉ የዘፈነዉ ዘፈን ነዉ እንጅ. መዝሙር አይሆንም !!! ስለሀገርም ቢሆንጸልየዉ አንጅ.ዘፍነዉ የዳኑ የለም!!! ጸልዮ እንጅ ዝፈኑ አልተባለም። ሞኞች ደግሞ ለእናት ቢዘፍንላትስ ይላሉ እድሜህ እድረዝም እናት እና አባትህን አክብር እንጅ ዝፈንላቸዉ አልተባለም!!! ዘፋኝነት.ይህንም የሚመስለዉ ነዉ አስቀድሜ እንድሁ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም(ወደ ገላትያ.ሰዎች 5፥12) አንድ ሌባ ሰርቆ የተራበ ቢያበላ ፅድቅ ነዉ ?? የተቸገሩ ሰዎችን ከተቸገሩት ከችግራቸዉ ያላቀቅ ዘንድ አጥብቆ የሚተጋ አንድ ሰዉ ሌሎችን ለመርዳት የሚያስፈልገዉን ገንዘብ ለማግኘት ዝሙት መፈፀም ግድ ቢሆንበትም ቢሆንበትም እርሱ ሰዉነቱን አርክሶ ዝሙት.ፈፅሞ.ገንዘብ ቢቀበል ችግረኞችን.ከችግር ቢያወጣ መልካም አደረገ እንለዋለን ??! ዘፈን ያስደስተናል ዘና ያደርገናል ደስታ ይፈጥራል.ወዘተ.ምክንያቶች እየደረደረን ጥብቅና አንቁም!! መልካም ነገር ማድረግ በኃጢአት ዉስጥ ማለፍ አይጠበቅብንም ኃጢኣት ያደረገ ኃጢኣተኛ እንጅ ፃድቅ ሊባል አይቻልም። ነገሩ ከዚንጀሮ ቆንጆ ምን ይምረጡ ነዉ። እንዲያ ካልሆነማ ከኃጢኣት ከተመረጠማ ለዘፈን ብቻ ለምን??? አንዳንዳቹ ደግሞ የዘፈነዉ ለመልካም ነዉ.ፍቅርክን ለመስበክ ነዉ የሚሉ ሞኞች አሉ.ፍቅር.ክርስቶስ ነዉ!!! እርሱን እግዚአብሔርን የሚያቅ ፍቅርን ያዉቃል.እርሱን የማያዉቅ ግን ፍቅርን አያቅም.!!! ቅዱስ ጳዉሎስም በቆሮንጦስ 13ላይ ቁልጭ አድርጎ አስቀምጦልናል.እንኳን አስረሽ ምችዉ በክርስቶስ ቃልም አልተገዛን ፍቅር አልገባን !!! ዘፈን አንድነትን ለማምጣት ነዉ.ከሌለን ደግሞ ሌባዉም የሰረቀዉ የተቸገሩትን ለማብላት ነዉ ሰዉየዉም ዝሙት.የፈፀመዉ ችግረኞችን ለመርዳት ነዉ። ነፍሰ ገዳዩም እንጀራ ሁኖበት ነዉ። ስለዚህ እነዚህም አብረዉ ይፅደቁ ?? እንዲህ ከሆነማ ደግሞ ኃጢኣተኛዉ ሁሉ ፃድቅ ሆኑ ማለት ነዉ። እራሳችንን ከማታለል እንዉጣ ከዚያም እንላቀቅ.አትግደል ከተባለ አትግደል ነዉ !!! አትስረቅም ከተባለ አትስረቅ ነዉ አትዝፈን ሲባል አትዝፈን ነዉ። በእግዚአብሔር ዘንድ ተመራጭ ሐጢኣት የለም ኃጢኣት ኃጢኣት ነዉ። እምየ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ባንች ፀንቸ በንሰሐ በስጋ በደሙ ልሙት.!መልካሙን ሁሉ ተመኘሁ ጆሮችሁ የተቀደሰ ነገር የሚሰማ ይሁን አፋችሁም የተቀደሰ የተባረከ ምስጋና ይወጣዉ ዘንድ የቅዱሳን አምላክ ይርዳን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቁሉ ክቡር ይቆየን መዝሙረ_ዳዊት ከምዕራፍ 11-50
إظهار الكل...
✝✝✝ እንኩዋን የመነኮሳት አባት ለተባለው "ቅዱስ ዻኩሚስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝ +*" ቅዱስ ዻኩሚስ (አባ ባኹም) "*+ =>ዛሬን አያድርገውና ምንኩስና ማለት መላእክትን መስሎ የሚኖርበት ሕይወት ነበር:: ምንኩስና በእግዚአብሔር ፈቃድ በአባ እንጦንስ ቢመሠረትም ሕይወቱን በማስፋፋት ደረጃ የቅዱስ ዻኩሚስን ያሕል የደከመና የተሳካለት ግን የለም:: +ቅዱሱ በትውልዱ ግብፃዊ እንደሆነ የሚነገር ሲሆን ከቀደመ ሕይወቱ ጋር በተያያዘ የሚተረክ ነገር በመጽሐፈ ገድሉ ላይ አለ:: ዻኩሚስ ወደ ምንኩስናው ዓለም የመጣ በታላቁ አባ ዸላሞን አማካኝነት ነው:: ለተወሰነ ጊዜም መንፈሳዊ አባቱን እየረዳ ሕይወተ መነኮሳትን አጥንቷል:: +በመንፈሳዊ ሕይወቱና በተጋድሎ እየበረታና እየደረጀ ሲሔድ ከአባ ዸላሞን ተለይቶ : ማሕበር መስርቶ ለመኖር አምላኩን ጠይቆ ፈቃድ በማግኘቱ በሕግ የሚመራ የመጀመሪያውን ገዳም መሥርቷል:: +ቅዱስ ዻኩሚስ ጸሎቱ አጋንንትን ከአካባቢው አያስቀርባቸውም ነበር:: አካሉ አልቆ በአጥንቶቹ እስኪቆም ድረስ ጾሟል:: ዓርብ ዓርብ የጌታችንን ሕማማት እያሰበ ከእንባ ጋር ይሰግዳል:: እንባውና ላበቱ ከፊቱ እየወረደ አካባቢው ጭቃ ይሆን ነበር:: ጌታችንም መስቀል ተሸክሞ ይታየው ነበር:: +ስለ ክብሩም መላእክት ወደ ሰማይ ወስደው ገነትና ሲዖልን አሳይተውታል:: አባታችን ቅዱስ ዻኩሚስ ከርሕራሔው የተነሳ አጋንንት ያደሩባቸውን ሰዎች ሲያገኝ በቀጥታ ከመፈወስ ይልቅ ደዌውን : ርኩሳን መናፍስቱንም ወደ እርሱ እንዲገለበጡ ያዛቸው ነበር:: +ከዚያም በጾም : በጸሎትና በስግደት ያማስናቸዋል:: ያኔ በግዳቸው እየጮሁ ሲወጡ ደጉ አባት "ምነው ትንሽ ቆዩ እንጂ" ይላቸዋል:: +አጋንንቱም እያደነቁ "ከገነት ካስወጣነው ከአዳም በቀር እንዲህ ዓይነት ፍጡርስ ዓይተን አናውቅም" ብለው እንደ ጢስ በነዋል:: አጋንንት ስለሚፈሩት "አርበኛው መነኩሴ" ይሉታል:: <<< የቅዱስ ዻኩሚስ ፍሬዎች >>> 1.በግብፅ በርካታ ገዳማትን አቁዋቁሟል:: 2.ለሁሉም ገዳማት አበ ምኔቶችን ሹሞ እየዞረ ይጠብቃቸው ነበር:: 3.የመጀመሪያውን ሥርዓተ መነኮሳት አዘጋጅቷል:: 4.መነኮሳት ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ሹመት እንዳይሾሙ ከልክሏል:: 5.መነኮሳት ከገዳማቸው በፍፁም እንዳይወጡ ከልክሏል:: 6.ከግብፅ ውጪ ምንኩስናን ያስፋፉ አባቶችን አስተምሮ አመንኩሷል:: (ለምሳሌ በኢትዮዽያ ምንኩስናን ያስፋፉት አቡነ አረጋዊ የዚህ አባት ደቀ መዝሙር ናቸው) +ከዚሕም ባለፈ በርካታ ሥራዎችን ሠርቷል:: ቅዱስ ዻኩሚስ ጫማ ሳይጫማ: እሾህን ሳይሰቀቅ ይረግጥም ነበር:: የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ እጥፍ ሆኖ የበዛለት ቅዱሱ መነኮስ ወደ ወደደው እግዚአብሔር በዚህች ቀን ሔዷል:: =>የጻድቁ መነኮስ ጸጋና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን:: =>ግንቦት 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ አባ ዻኩሚስ (አበ መነኮሳት ሣልሳዊ) 2.አባ ሲማኮስ ሰማዕት =>ወርሐዊ በዓላት 1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል) 2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ 3.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ 4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው) 5.አባ ስምዖን ገዳማዊ 6.አባ ዮሐንስ ጻድቅ 7.እናታችን ቅድስት ነሣሒት =>+"+ ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም:: በእናት ማሕጸን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ:: ሰውም የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ:: ስለ መንግስተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ:: ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው:: +"+ (ማቴ. 19:11) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
إظهار الكل...
ግንቦት 14 በዚህች ዕለት ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ከጫጉላ ቤቱ የመነነበት ዕለት ነው። ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ከአባቱ ከንጉሥ ቴዎዶስዮስና ከእናቱ ከንግሥት መርኬዛ በቁስጥንጥንያ ሀገር ተወለደ፤ስሙንም አብደል መሲህ ብለው ሰየሙት ትርጓሜውም የእግዚአብሔር አገልጋይ-ገብረ ክርስቶስ ማለት ነው፡፡ እድሜው ለትምህርት በደረሰ ጊዜ እናት አባቱ ተማክረው ወደ ቤተ መምህር ወሰዱት፡፡ ገብረ ክርስቶስም ሰውን ከእግዚአብሔር ከምታርቀው ከኃጢአት በስተቀር ጥበብ መንፈሳዊን ጥበብ ሥጋዊን ተማረ፡፡ አባትና እናቱ ትምህርትን ሁሉ ተምሮ እንደጨረሰ ባወቁ ጊዜ በሕይወት ሳለን አዱኛውን አይተን ደስ ይበለን በማለት ተማክረው የሮሙን ንጉሥ ልጅ ሚስት ትሆነው ዘንድ አጩለት፡፡ እንደ መንግሥታቸውም ስፋት መጠን ሰርግ አዘጋጁ፡፡ በቁስጥንጥንያው ሊቀ ጳጳስ በአባ ቴዎፍሎስም አማካይነት በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሰርጋቸው በቤተ ክርስቲያን ተፈጸመ፡፡ አባ ቴዎፍሎስም መረቃቸው አላቸውም ብዙ ተባዙ፤ቤተ እስራኤልን እንዳበዛ እንደያዕቆብ ያድርጋችሁ በታቦተ ጽዮን መግባት የአቢዳራ ቤት እንደተባረከ የተባረካችሁ ሁኑ፤ የብዙ ብዙ ሁኑ አትራቡ አትጠሙ በማለት፡፡ ያን ጊዜ የሰሙት ሁሉ አሜን አሜን ይሁን በማለት ቡራኬውን ተቀበሉ፡፡ በመሸም ጊዜ እናት አባቱ ሥርዓተ መርዓ ወመርዓዊ ያድርሱ በማለት በጫጉላ ቤት ትተዋቸው ሄዱ፡፡ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስም ወደ እርሷ ገባ ፊቱ በብርሃን ተሞልቶ እንደጸሐይ ሲያበራ አይታው ከፊቱ ወደቀች፤እጇን ይዞ ሙሽራይቱን እህቴ ሆይ ያልኩሽን ሁሉ ልትፈጽሚ ተነሽ እንጸልይ አላት፡፡ እርሷም ያላትን ሁሉ ልትፈጽም ተስማማች፡፡ተነስተውም የሃይማኖት ጸሎትን እስከመጨረሻው በአንድነት ጸለዩ፡፡ ጸሎትንም ከፈጸሙ በኋላ የሙሽርነት ልብሱን ጥሎ ተርታ ልብስ ለበሰ የሚችለውንም ያህል ብዙ ወርቅና ብር ያዘ፡፡ግንባሯንም ስሞ ወጣ፡፡ ውእተ ጊዜ መርዓት በከየት ወትቤ አይቴ ተሀውር ወለመኑ ተኃድገኒ-በዚያን ጊዜ ሙሽራይቱ እያለቀሰች ቅዱስ ገብረ ክርስቶስን ወዴት ትሄዳለህ ለማንስ ትተወኛለህ አለችው እርሱም እኔ ክርስቶስን ልከተለው እሄዳለሁ አንቺ ግን የተማማልነውን መሐላ አስቢ ለእግዚአብሔር አደራ ሰጥቼሻለው ብሏት በሌሊት ወጣ፡፡ያን ጊዜ ከሙሽራይቱ በስተቀር ያየውም የሰማውም አልነበረም፡፡ ሲሄድም መርከበኞችን አገኘ ዋጋቸውንም ከፍሎ አብሯቸው ተጓዘ፡፡ በነጋም ጊዜ እናት አባቱ ሰዎችን አስከትለው ከሙሽራይቱና ከሙሽራው ጋር ደስ ይላቸው ዘንድ በማሰብ ወደ ጫጉላ ቤት ገቡ ነገር ግን ከሙሽራይቱ በስተቀር ሙሽራውን አላገኙም፡፡ ያን ጊዜም ባልሽ ልጃችን ወዴት አለ ብለው ጠየቋት እርሷም የሆነው ሁሉ እያለቀሰች ነገረቻቸው፡፡ንጉሡ ቴዎዶስዮስም 500 የሚሆኑ አገልጋዮቹን ሰብስቦ ገብረ ክርስቶስ እየተባለ የሚጠራውን ልጁን ይፈልጉት ዘንድ ብዙ ብርና ወርቅ ስንቅም ሰጥቶ ላካቸው ገብረ ክርስቶስ ግን አንድ አመት ያህል ወደምታስሄደውም መንገድ በመሄድ በአርማን በእመቤታችን ስም በተሰራች ቤተ ክርስቲያን ኖረ፡፡ በእመቤታች ቤተ ክርስቲያንም ነዳያን ሁሉ ይኖሩ ዘንድ ሥርዓት ነበርና ቤተ ክርስቲያንን እያገለገለ ሲኖር ከአባቱ ቤት ይዞ የሄደውን ሁሉ ከሚለብሳት ከአንዲት ጨርቅ በስተቀር ለነዳያን ሰጠ፡፡የአባቱ ባሮችም እርሱ ወዳለበት በመድረስ ስለ ንጉሥ ልጅ መረጃ ቢጠይቁም ምንም አላገኙም ከያዙትም ለነዳያን ሲመጸውቱ ለገብረ ክርስቶስም አብረው ምጽዋትን ሰጡት እነርሱ አላወቁትም እርሱ ግን አውቋቸው ነበር፡፡ ምጽዋቱንም ተቀብሎ ወደ ማደርያው በመግባት አምላኬ ሆይ ከአባቴ ባያዎች ምጽዋትን ለመቀበል ስላበቃኸኝ አመሰግንሃለው አሁንም የተቀበልኩትን ይህን ምጽዋት ለሌሎች እሰጣለሁ በማለት አምላኩን አመስግኖ የተቀበለውን መልሶ ለሌሎች ነዳያን መጸወተ፡፡ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ የእመቤታችንን ቤተ ክርስቲያን እያገለገለ በጾምና በጸሎት ተወስኖ አስራ አምስት አመት ያህል በአርመንያ ኖረ፡፡ የብጹዕ ገብረ ክርስቶስ ጸሎቱና በረከቱ አይለየን፡፡ አጋንንትን እንዲያወጣ ዕውሮችን አንካሶችን ወር አይቶ የሚነሳባቸውን መስማት መናገር የተሳናቸውን ሰውነታቸው የደረቀውን ደዌ የጸናባቸውን ለምጻሞችን ደዌ ስጋ ያደረባቸውን ድውያኑን ሁሉ እንዲፈውስ ሥልጣን ልዩ ልዩ ደዌ ያለባቸውን ሁሉ በጸሎቱ ይድኑ ይፈወሱ ዘንድ በጸሎቱ የታመነውን በመታሰቢያው ዕለት ጸሎቱን ተስፋ በማድረግ በመዓልትም በሌሊትም ቢሆን በቤተ ክርስያን በሌላም ቦታ ቢሆን ዜናውን ሰምተው እንባቸውን ያፈሰሱትንዳግመኛም ለመታሰቢያው ስንዴ ወይን ዕጣን የሚሰጠውን በስሙም ቁራሽ እንጀራ ቀዝቃዛ ውሃም ቢሆን የሚሰጠውን በመታሰቢያው ቀን የተዘጋጀውን ፍርፋሪ የበላውን ወጭቱን አንስቶ ጥራጊውን የቀመሰውን ለቅዱሳን የተዘጋጀውን ምሳሓ ደብረ ጽዮን ከቅዱሱ ጋር እንዲገኙ ፤የጌታ ቸርነትም ትደረግላቸው ዘንድ እግዚአብሔር አምላክ ቃል ኪዳን ገብቶለታል፡፡ አምላካችን እግዚአብሔርም እንደ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ያለ ትዕግስትን ያድለን፡፡እርሱን የምንፈልግበት ልብን ያድለን፡፡ከቤቱም ሳንለይ በፍርሃት አገልግለነው ከቅዱሳን ማኅበር ይደምረን አሜን። ምንጭ፡- ገድለ ገብረ ክርስቶስ ተአምረ ማርያም ወመጽሐፈ ስንክሳር
إظهار الكل...
+የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል+ እግዚአብሔር ዓሣን ሲፈጥር "ሕይወት ያላቸውን አስገኝ" ብሎ ባሕርን ተናገረው እግዚአብሔር ዛፎችን ሲፈጥር ደግሞ ዛፍ እንድታበቅል መሬትን ተናገራት ሰውን ሲፈጥር ግን የተናገረው ለራሱ ነበር እግዚአብሔርም አለ "ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር" ልብ አድርጉ :- ዓሣ ከባሕር ከወጣ ወዲያውኑ ይሞታል ዛፍም ከምድር ላይ ከተነቀለም ይሞታል ሰውም ከእግዚአብሔር ከተለየ ይሞታል:: ባሕር ለዓሣ መሬት ለዛፍ ተፈጥሮአዊ መጠለያቸው እንደሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮአዊ መጠጊያችንም እግዚአብሔር ነው:: የተፈጠርነው ከእርሱ ጋር ልንኖር ነው:: ሕይወት ያለን ከእርሱ ጋር ነውና መኖር የምንችለው በእርሱ ብቻ ነው:: ይህንንም እናስታውስ ዓሣ ያለ ባሕር ምንም ነው:: ባሕር ግን ያለ ዓሣ ያው ባሕር ነው:: ዛፍ ያለ መሬት ምንም ነው መሬት ግን ያለ ዛፍ ያው መሬት ነው:: ሰው ያለ እግዚአብሔር ምንም ነው:: እግዚአብሔር ግን ያለ ሰው ያው እግዚአብሔር ነው:: ቅዱስ ባስልዮስ እንዲህ እንዳለ :- "ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም" ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
إظهار الكل...
❖❖❖ የሰኞ እንዚራ ስብሐት ❖❖❖ 🌹 አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ 🌹በፊደላት ሁሉ እመቤታችንን🌹 ያመሰገነበት ድርሰቱ በ ✨ ሑ ✨ ፊደል ትርጉም ✨ 🌼 የእስራኤል ንጉሥ መጎናጸፊያዉ የሆነ ስሟ ኢያዜር የተባለችዋ ሀገር ልብስ እመቤቴ ማርያም ሆይ የሊቀ ካህናቱ አዳራሽ የሆንሽ ቅድስተ ቅዱሳን አንቺ ነሽ 🌼 ✥የእጅ መንሻ ወይንን የሚቀዱብሽ የወርቅ ጽዋ አንቺ ነሽ ✥ 🌼 ጎስቋሎች የሚነጹብሽ መታጠቢያም አንቺ ነሽ 🌼 ✥ቡርክት (ደግ) ሆይ በየጥዋቱ ትመግቢኝ ዘንድም እለምንሻለሁ ✥ 🌼 በሕመሜ የሚደሰቱ ፣ እየተመኩ በእኔ ላይ የሚታበዩትንም ያፍሩ ዘንድ እማጸንሻለሁ 🌼 ❖❖❖ ለዘለዓለሙ አሜን ❖❖❖ ❖ ጣዕመ በረከቷ አይለየን የቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በረከት ይደርብን ❖ ❖ ስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር ❖ ❖🌹 የእመ ብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ፍቅሯ ይብዛልን 🌹 ❖ ❖🌹 የእመ ብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ፍቅሯ ይብዛልን 🌹 ❖ ❖🌹 የእመ ብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ፍቅሯ ይብዛልን 🌹 ❖ ❖❖❖ ፀጋ አብ ሂሩተ ዘወልድ ሱራፌል ዘመንፈስ ቅዱስ ይህድር በላዕሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡ (የአብ ፀጋ የወልድ ቸርነት የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ለዘለዓለም በላያችን ላይ ይደር አሜን፡፡ ❖❖❖
إظهار الكل...
አስደንጋጭ: ኢትዮጵያንና ሀይማኖቷን ለማክሰም የተስማሙት ኢትዮጵያዊን ባንዳዎች ኢትዮጵያ ከዓለም በተለየ መልኩ ለረጅም ሺህ ዓመታት ፈጣሪዋን አጥብቃ የያዘችና የምታመልክ ሀገር መሆኖ ይታወቃል። ከዛም ባለፈ ኢትዮጵያ ታላላቅ ሚስጥሮችን የያዘች ሀገር መሆኗም ይታወቃል። ከነዚህ ሚስጥራት መሃከል ፈጣሪ ከአዳም ነጥቆ በኪሩቤልና ሱራፌል ነበልባል እሳት የሚያስጠብቀው የህይወት ዛፍ አንዱ ነው። የህይወት ዛፍ አዳም ከፈጣሪ ትዕዛዝ በወጣ ጌዜ የተነጠቀው ዘላለማዊ ህይወትን የሚሰጥ ሞትን የሚያስቀር ዛፍ ነው።ይህ የህይወት ዛፍ በጣና ኢትዮጵያ ነው የሚገኝው። ይህን ጠንቅቆ የሚያቀው ዲያቢሎስ የህይወት ዛፍ መገኛ የሆነችውን ኢትዮጵያ በመቆጣጠር ለሰው ልጅ ዘላለማዊ ህይወት በመስጠት ለሱ የተገዙና ለሱ እየሰገዱ እንዲኖሩ ለማረግ አጥብቆ ይሻል። ያ ብቻም ሳይሆን በመጨረሻው የዓለም ፍፃሜ ውጊያ አርማጌዶን ፈጣሪን ረቶ መላ ፍጡርን ለመግዛት ያልማላ። ትላንትም ታላቅ ስልጣኑን አሳጥቶ ወደ ሲኦል እሳት ያስጣለውን ይህ ስልጣን ወዳድነቱና የፈጣሪን ቦታ መሻቱ ዛሬም አለቀቀውም። ታዲያ ይህን እቅዱን ለማሳካት ማለትም ፈጣሪን በአርማጌዶን ውጊያ ለመርታት ብሎም በጣና በስውር የሚገኘውን የህይወት ዛፍ በእጁ ለማስገባት ታላቅ ፈተና የሚሆኑብኝ የሚላቸው ለፈጣሪ የሚገዙ ህዝቦችን ነው። በመላ ዓለም ያሉ አማኝ ህዝቦችን በስልጣኔ ስም በተለያዩ ሴራዎች ከሀይማኖት አስተምህሮ እያራቀ ኢ አማኝ ይሆኑ ዘንድ ብዙ ተግቷል በብዙም ተሳክቶለታል። ታዲያ በመላ ዓለም ማፍረክረክ የቻለውን ሀይማኖት በኢትዮጵያ ብቻ ማሳካት አልቻለም። የህይወት ዛፍ በምትገኝበት ብሎም የመጨረሻው ውጊያ አርማጌዶን በሚካሄድባት ኢትዮጵያ ሀይማኖትና ሃይማኖተኞች እያሉ ፈፅሞ ህልሜን ማሳካት አልችልም የሚለው ሳጥናኤል ፤ ኢትዮጵያን ዋና ጎሌ ናት ብሎ ከተነሳ ረዘም ያሉ ዓመታት ተቆጥረዋል። በኢትዮጵያ ሀይማኖትን ለማፍረክረክና ህዝቡን እንደሌላው የአለም ህዝብ ኢ አማኝና የሱ ተከታይ ለማረግ በግብርአበሮቹ ኢሉሚናቲዎች አማካኝነት አንድ እቅድ ነድፎ በመሥራት ላይ ይገኛል። ይህም 'ኢትዮጵያንን በኢትዮጵያውያን የማፍረክረክ እቅድ ነው። ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ ሊአፍረከርኳቸው የመጡትን ጠላቶች ሁሉ በመመከትና በመደምሰስ ፍፁም መሆናቸውን የተረዱት እኒህ የሳጥናኤል አላማ አስፈፃሚዎች ኢትዮጵያን በራሷ ልጆች(ባንዳዎች) ለማፍረክረክ ወስነው ወደተግባር ገብተዋል። እኤአ ከ፳፻፲፬ 2014 በፊት የዓላማችን አስፈፃሚ ይሆናሉ ያሏቸውን ፩፻፹ 180 ኢትዮጵያውያን በየዘርፉ መልምለው በተለያየ ሽፋን ወደ አሜሪካ በመላክ በሲአይኤ በኩል ከፍተኛ የተባለ ስልጠና እንዲሰጣቸው አድርገዋል። ይህ በአይነቱ ረቀቅ ያለ ስልጠና እኒህን ሀገራቸውን ለማፍረክረክ ለተስማሙት ፩፻፷180 ባንዳዎች ትልቅ ችሎታን ያላበሰ ነበር። ከሰው ሳይኮሎጂና የማሰብ አቅም በላይ በሆነ መልኩ ተልኳቸውን ለመከውን የሚያስችላቸው ረቂቅ ስልጠናም እኤአ በ፳፻፲፬ 2014 ዓም አጠናቀው ለመመረቅ ችለዋል። ከዛ በኋላ ባለው ጊዜ ወደ ኢትዮጵያን በመግባት በመንግሥት ደረጃ የስልጣን መንበር ላይ በመቆናጠ በግል ደረጃ ደሞ በሁሉም ዘርፍ ወሳኝ ቦታዎችን በመያዝ ስራቸውን በረቀቀና በተናበበ መልኩ በመከወን ላይ ይገኛሉ። እኒህ ፩፻፹180 ሀገራቸውን ለማፍረክረክና ለመሸጥ የተመለመሉ ባንዳዎች ዋና አላማ የሚከተሉት ናቸው ፩ 1. በሀገሪቱ ያሉ ሀይማኖትና ሃይማኖተኞችን በተቻለ ሁሉ ማፍረክረክና ኢ አማኝ ማድረግ። የሀይማኖት ተቋማትን ማውደም አባቶችንና ሀይማኖተኛውን መግደል ወዘተ.... 👉 በሀገራችን ብዛት ያላቸው ገዳማት ፣ ቤተክርስቲያንናትና መስኪዶች በረቀቀ ሴራ በየቀኑ እየወደሙ እንደሚገኙ ልብ በሉ። 👉 በየጊዜው እንደ ቀልድ ከባባድ እሳቶች እየተነሱ ገዳማት ፣ አድባራትና ታላላቅ ቦታዎች እንዲወድሙ እየተደረገ ይገኛል። 👉 በርከት ያሉ የሃይማኖት አባቶች በጅምላ እየተረሸኑ ነው። በዚህ ሳምንት እኮ፹፱ 89 ቄሶች በትግራይ በአንድ ቦታ ብቻ ተረሽነዋል። ፪ 2. ጠንካራ ሀገራዊ ፍቅርና ስሜት ያለው ትውልድ እንዳይፈጠር ከስር ከስር መስራት። ሀገር ወዳዱን ማህበረሰብ መረሸን መጨፍጨፍ ማዳከም 👉 ስለ ሀገራችን ያገባናል ፣ ባህልና እሴቶቻችን አይሸርሸሩ የሚል ጠንካራ ማህበራዊ መሠረት ያላቸውን ህዝቦች የመጨፍጨፍ ስራ በብዛት እየተከናወነ ይገኛል። በሲአይኤ በኩል ባሰለጠኗቸው አክቲቪስት ኢትዮጵያዊን አማካኝነት እኒህን ሀገር ወዳድ ህዝቦች የተለያየ ስም በመስጠት ለማመን በሚከብድ ቁጥር በሌላው ህዝብ ይጨፈጨፉ ዘንድ የሴራ ስራቸውን እየሰሩ ይገኛሉ። ከሰሜን እስከ ደቡብ በብሄርና ፖለቲካ ግጭት ስም በገፈ የሚቆጠሩ ሀገር ወዳድ ማህበረሰቦች የጅምላ ጭፍጨፋ የሚደረግባቸው መንግስት አቅም አጥቶ ሳይሆን ስውር አላማቸው በማስፈፀም ላይ ስለሆኑ ነው። ፫ 3. የኢትዮጵያ እሴቶችን በነደፉት የተለያዩ የሴራ ስልቶች በመሸርሸር በሰይጣኒዝም ሀይማኖት እሴቶ መተካት። ማለትም ግብረሰዶማዊነት ፣ ልቅነት ፣ እራስ ወዳድነት፣ ገንዘብና ዝና ወዳድነት ወዘተ..... 👉 ትውልዱ ከሀገሩ እሴቶች ይልቅ በምዕራባውያኑ ልቅ ባህል ይሳብ ዘንድ ከ፴ 30 ያላነሱ ቻናሎችን በመክፈትና ሶሻል ሚዲያውን በመጠቀም ስልጠናውን በሰጧቸው አርቲስት አባሎቻቸው በኩል ከፍተኛ የሆነ የትውልዱን አእምሮ በማጠብ ላይ ይገኛሉ። ፬ 4. በኢንዱስትሪ ማስፋፋትና ስራ ፈጠራ ስም ለመጨረሻው የአርማጌዶን ውጊያ ይሆነናል የሚሉትን ቦታዎች በኢንዲስትሪ ፖርክ ስም ከልሎ በመያዝ የረቀቁ መሳሪያዎች ማምረት። እነዚህ ቦታዎች ወሳኝና እስትራቴጂካዊ ቦታዎች ከመሆን ባለፈ ከፍተኛ የሆኑ ረቂቅ ማዕድናት የያዙ ስፍራዎች ናቸው። 👉 በነገራችን ላይ አብዛኞቹ የኢንዱስትሪ ፖርኮች የተገነቡት ገዳማት አድባራትና መስኪዶች በነበሩበት ባሉበት ስፍራ ነው። አባቶቻችን እኒህን ስፍራዎች በመንፈስ እየተመሩ ቀድመው አውቀው የያዟቸው ለመጨረሻው ውጊያ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ስለሆኑ ነበር። ፭ 5. በቴክኖሎጂና ዘመናዊነት ስም ረቂቁንና መላ ህዝቡን በቁጥጥር ስር የሚከተውን ማይክሮ ቺፕ በመላ ኢትዮጵያዊያን መቅበር ይገኙበታል። 👉 በአሁኑ ሰዓት መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት የሰጠው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ግንባታ በዚች ደሃ ሀገር ቅድሚያ የሚሰጠው አለመሆኑ ግልፅ ነው። ነገር ግን ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ለማጥመድ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት እንጂ ፮ 6. ወዘተ.... @HISCULHEROFETHIOPA
إظهار الكل...
​​​​​​✝✥• ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ •✥✝ ✥• ለቤተ ክርስቲያን የብርሃን ምሰሶ ስለሆነላት ስለ ታላቁ ሐዋርያዊ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? እንደ እኔ ያለ ኃጥእ: ለባሴ ሥጋና ገባሬ ንስሃ ስለሱ ሊናገር አይቻለውምና:: አባቶቻችን እንደ ነገሩን ስለ አፈ ወርቅ ለመናገር አፈ ወርቅ መሆን ያስፈልጋል:: ግን እስኪ በቅዱሱ አባት ምልጃ ጥቂት ልሞክር:: 👉 ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው? ✥• ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ:: እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ አደገ:: ገና በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና) ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል:: ✥• ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮችም አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ በመንፈሳዊ ትምሕርት ይህ ቀረህ የማይሉት ሊቅ የሆነው ገና በ15 ዓመቱ ነበር:: በ2 ወገን የተሳለ ሰይፍ በመሆኑ ስንኳን በሕይወተ ሥጋ እያለ ዛሬም ለንፉቃን ትልቅ የራስ ምታት ነው:: ✥• ቅዱሱ ገና በ16 ዓመቱ ሃብት: ንብረት: ውበት: ክብርና እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበርሃ ሲኖር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ወደ እርሱ መጡ:: ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት:: ✥• ከዚህች እለት በኋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራዕየ ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጉዋሜ ተነተናቸው:: በተለይ ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው ሳይታክት: ንጹሕ እጆቹ ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት: መልዕክታትና ትርጉዋሜያት ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ አንክሮ ይገባል! የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና ለጋ: ማዕርጉም ዲቁና ነበር:: ✥• ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው ወደውታልና የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: አፈ ወርቅ ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኳን የሚያወራ ኮሽ የሚል የለም:: ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ በተደሞ ይሰሙት ነበር:: ✥• ሲያስተምር ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር:: አንዴም እመቤታችን በሕዝብ መካከል "አፈ-ወርቅ" ብላ ጠርታዋለች:: ለዛም ነው አፈ-ወርቅ የሚባለው:: ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ 10 ዓመት አቁሞታል:: ✥• + ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: ✥• በተሰደደበት ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ/ም አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ:: ✥• አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ አርቃድዮስ ግብር አገባ (ግብዣ አዘጋጀ :: በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ ታጥቆ ሲጸልይ ሳለ: አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ ከሰማይ 12ቱ ሊቃነ መላእክት (እነ ቅዱስ ሚካኤል) በግርማ ሲወርዱ ተመለከተ:: ✥• ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ: ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንገለጥልኝ መርቁኝ" አላቸው:: ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን ቀጠሉ:: ✥• በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ: መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ ነበር እንጂ አልበላም:: ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ" ብሎ በጉባኤ መካከል ጠየቀው:: ✥• "ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ አመ ወለደት ወለደ ዘበኩራ-የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም' ማለቱ (ማቴ. 1:25) ስለ ምን ነው?" ቢለው ቅዱሱ ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ይተረጉምለት ጀመር:: ✥• "ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ ይቀያየራል:: እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ መለኮቱ ሲለዋወጥ መልኳ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር:: ✥• 'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው' እያለ ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በኋላ ግን አንድ ሕብረ መልክ ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች አላወቀም:: ✥• አሁን ግን እርሷም ወላዲተ አምላክ: ልጇም አምላክ ዘበአማን መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም ሰምተው ሁሉም ሲያደንቁ: በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ "አፈ ወርቅ! ልሳነ ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች:: ✥• ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ! እሰግድ ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት:: ይህንን ምስጋናም ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው እያደነቁ ወደ ሰማይ ወጥተዋል:: ✥• ሊቁ ባረፈ በ35 ዓመቱ: በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን: ሥጋው ፈልሷል:: ወደ ቁስጥንጥንያ ሲደርስም ከናፍቆት የተነሳ ታላቅ ዝማሬና እንባ ተደርጓል:: አፈ ወርቅም ቀና ብሎ ሕዝቡን ባርኳል:: ✔ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው:- ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ አፈ በረከት አፈ መዐር (ማር) አፈ ሶከር (ስኳር) አፈ አፈው (ሽቱ) ልሳነ ወርቅ የዓለም ሁሉ መምሕር ርዕሰ ሊቃውንት ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ) ሐዲስ ዳንኤል ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው) መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ ጥዑመ ቃል - - - ✥• እግዚአብሔር ከቅዱሱ በረከት አብዝቶ: አብዝቶ: አብዝቶ ይክፈለን:: ✥• ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥጋቸው ፈልሷል:: ይሕ የተደረገው ጻድቁ ከረፉ ከ56 ዓመታት በኋላ ነው:: በዕለቱም ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተፈጽመዋል:: ✥• እናታችን ርሕርሕቷ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ደግሞ በዚሕ ቀን ስሟን ለጠራና መታሠቢያዋን ላደረገ የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች:: ✥• ቸር አምላካቸው ከሁለቱም ብሩሃን ቅዱሳኑ ክብር ያድለን:: •✥• ©ዝክረ ቅዱሳን •✥•
إظهار الكل...

#ግንቦት_12 የመምህር ወመገስጽ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የእረፍቱ ቀን፣ የአባታችን የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ፍልሰተ አጽም እና የእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የቃልኪዳን ዓመታዊ ክብረ በዓል ነወ። #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ባሕረ ምስጢራት የሆነ የሰውን ፊት አይቶ የማያደላ "መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ" (በርሱ ዘንድ ንጉሥ፣ ሐብታም፣ ደሃ፣ ነዳይ እኩል ነውና)፣ አፈ በረከት፣ አፈ መዐር (ማር)፣ አፈ ሶከር (ስኳር)፣ አፈ አፈው (ሽቱ)፣ ልሳነ ወርቅ፣ የዓለም ሁሉ መምሕር፣ ርዕሰ ሊቃውንት፣ ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)፣ የሐዲስ ኪዳን ዳንኤል፣ ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)፣ ጥዑመ ቃል... እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እረፍቱ ነው። #ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ ብፅዕት ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ሰይጣንን ከፈጣሪ ጋር ልታስታርቅ በሄደች ጊዜ ከሲኦል ቅዱስ ሚካኤል እየተራዳት ብዙ ነፍሳትን ያወጣችበት የቃልኪዳን በዓል ነው። #አቡነ_ተክለሃይማኖት የአባታቸንና የኢትዮጵያ ፀሐይ የፃድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ግንቦት 12 ከደብረ አሰቦ ወደ ደብረ ሊባኖስ አጽማቸው የፈለሰበት (ፍልሰተ አጽም) ይከበራል። አምላከ ቅዱሳን በቅዱሳኑ ጸሎት ልመናና ቃልኪዳን ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ከጭንቀትና ከመከራ ይጠብቀን። ©ቤተ ዮሐንስ አፈወርቅ
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.