📚منهج السلف طريقنا الى الله 📚
الذهاب إلى القناة على Telegram
↘️በዚህ ቻናል የሚተላለፉት ↘️በሱና ኡስታዞች የተቀሩ ደርሶች ↘️የሱና ኡስታዞች ሙሀደራዎች ↘️በመቀጠል አስተማሪ ፁሁፎች ➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/htt_asselfya
إظهار المزيد3 819
المشتركون
-524 ساعات
+1617 أيام
+15530 أيام
أرشيف المشاركات
Repost from MuhammedSirage M.Noor
قال ابن حجر رحمه الله :
من عجائب الاتفاق : أن الذين أدركهم الإسلام من أعمام النبي صلى الله عليه وسلم أربعة لم يُسلم منهم اثنان، وأسلم اثنان، وكان اسم من لم يُسلم ينافي أسماء المسلمين وهما :
أبو طالب واسمه عبد مناف
وأبو لهب واسمه عبد العُزّى
بخلاف من أسلم وهما : حمزة والعباس
ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:- 1️⃣2️⃣6️⃣
* የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
https://t.me/IbnuMunewor/3505
* የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 337፣ كتاب السلام
* የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን
* የሚሰጥበት ጊዜ:- ረቡዕ፣ ሐሙስ እና ጁሙዐ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
1- ክርስቲያን ጎረቤት ቢታመም መጠየቅ ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ነብያችን ﷺ የታመመን የሁዲ ጠይቀዋል። [ቡኻሪ፡ 1356]
2- የክርስቲያንን የግብዣ ጥሪ መቀበል ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ነብዩን ﷺ አንድ የሁዲ ጠርቷቸው ሄደዋል። [አሕመድ፡ 13201]
3- ክርስቲያን የሆነ ሰው ቤተሰብ ቢሞትበት ለተዕዚያ ወይም ለማፅናናት መሄድ ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ከላይ የተጠቀሱት መረጃዎች ለዚህ ድጋፍ መሆን ይችላሉ።
4- ለክርስቲያን ደሃ ሶደቃ መስጠት ይቻላል?
አዎ ይቻላል። [ቡኻሪና ሙስሊም]
5- በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ለክርስቲያን መልካም መዋል ይቻላል?
አዎ ይቻላል። [አልሙምተሒናህ፡ 8-9]
6- ለገና በዓል "እንኳን አደረሳችሁ" ማለት ይቻላል?
በፍፁም!
ከላይ የተዘረዘሩት የሚፈቀዱ ከሆነ ይሄኛው የሚከለክልበት ምክንያት ምንድነው?
የመጀመሪያዎቹ ነገሮች የተፈቀዱት እምነታዊ ሳይሆን ዱንያዊ ጉዳዮች ስለሆኑ ነው። ሃይማኖታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ግን ይሄ የሚፈቀድ አይደለም። በቃልም በተግባርም ማጀብ አይቻልም፡፡ የአላህ ነብይ ዒሳን ጌታ አድርጎ ሲገልፅ፣ ከዚያም "ጌታ ተወለደልኝ" ብሎ ሲደሰት "እንኳን ጌታ ተወለደልህ!" ትላለህ? የእምነታችን አንዱ መሰረትኮ "አላህ አልወለደም፣ አልተወለደም" ነው። በሌሎች ሃይማኖታዊ በአላትም ወይም ድግሶችም ላይ እንዲሁ ነው። እና ወንድሜ! የእምነትህን ህግ ለመጠበቅ ፈፅሞ ወኔ አይጠርህ። ጓደኝነት፣ ትውውቅ ሸብቦህ፣ አጉል እፍረት አስሮህ ከጌታህ ጋር አትጣላ። በነገራችን ላይ ይሄ "የጌታ መውሊድ" ብለው የሚያከብሩት የገና በአል መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የማይገኝ በቅድመ-ክርስትና ከነበረው የጣኦታውያን እምነት የተኮረጀ ነው። በዚያ ላይ ዛሬ የጎርጎሮሳዊውን አቆጣጠር የሚከተሉት የሚያከብሩበት December 25ም ሆነ "የኢትዮጵያውን" አቆጣጠር የሚከተሉት የሚያከብሩበት ታህሳስ 29ም በርግጠኝነት ዒሳ (እየሱስ) የተወለዱበት ቀን አይደለም።
-
መነሻ ሃሳቡ ዋትሳፕ ላይ ያገኘሁት 0ረብኛ ፅሁፍ ነው።
==
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የምንችለውን እናስተምር
~
ኢብኑል ሙባረክ - ረሒመሁላህ - "ከእድሜህ አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረህ ብትባል ምን ትሰራ ነበር?" ተብለው ተጠየቁ።
"ሰዎችን አስተምር ነበር" አሉ።
[አልመድኸል ኢለሱነን፣ አልበይሀቂይ፡ 309]
Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሁለት መልእክት
~
1ኛ፦ የነገው የደዕዋ ፕሮግራም ሳምንታዊ ደርስ በሚሰጥበት የሺ ደበሌ አካባቢ በሚገኘው ሑዘይፋ መስጂድ አይደለም። ይልቁንም ከአንፎ ወደ አለም ባንክ በሚወስደው መንገድ ላይ በቀኝ በኩል ድልድዩ አጠገብ በሚገኘው ሑዘይፋ መስጂድ ነው።
2ኛ፦ ዘወትር እሁድ የሚሰጠው ሳምንታዊ ደርስ ነገ አይኖርም።
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ክፉ ልክፍት!... ድንቅ መድሃኒት!
~
ሰውየው፡-
* “ቀድሞ (ለማጨት ሳስባት) በሚስቴ በምደነቅ ጊዜ … አላህ የሷ አይነት በዓለም ላይ የፈጠረ አይመስለኝም ነበር፡፡
* ካጨኋት በኋላ ብዙዎቹ ሴቶች የሷው አምሳያ ሆነው አገኘሁ፡፡
* ካገባኋት በኋላ #ብዙዎቹ ሴቶች ከሷ የበለጡ ቆንጆዎች እንደሆኑ ተገነዘብኩ፡፡
* ተጋብተን ጥቂት አመታት ካለፉ በኋላ ግን #ሁሉም ሴቶች ከሷ የሚበልጡ ቆንጆዎች እንደሆኑ ደመደምኩ” አለ፡፡
ሸይኹ በዚህን ጊዜ፡- “ይልቅ ከዚህ የከፋውን አልነግርህም?” አሉት፡፡
“ይንገሩኝ” አለ ሰውየው፡፡
“የዓለም ሴቶችን በሙሉ ብታገባም በየጎዳናው የሚልከሰከሱ ውሾች ከአለም ሴቶች ሁሉ በላይ ቆንጆዎች ይሆኑብሃል!!” አሉት።
ሰውየው፡- በስሱ ፈገግ አለና “ለምን እንዲህ አሉ?” ሲል ጠየቃቸው፡፡
ሸይኹ፡- “ምክንያቱም ችግሩ ከሚስትህ አይደለም፡፡ ችግሩ የሰው ልጅ ስግብግብ ልቦና፣ ልክስክስ አይን ሲኖረውና አላህን ከማፈር፣ ከሐያእ ሲራቆት ነው፡፡ በዚህን ጊዜ አይኑን የመቃብሩ አፈር እንጂ አይሞላውም፡፡ ልክ ነብዩ ﷺ ‘የአደምን ልጅ አፈር እንጂ አይኑን አይሞላውም…’ እንዳሉት፡፡ ሰውየ!! ችግርህ አይንህን አላህ ከከለከለው ነገር አለመስበርህ ነው፡፡ ይልቅ ሚስትህን ልክ እንደ ቀድሞዋ (ከአለም ሴቶች ሁሉ ቆንጆ) የምታደርግበትን ዘዴ እንድነግርህ ትፈልጋለህ?” አሉት፡፡
“አዎ” አለ ሰውየው፡፡
“አይንህን ስበር!!” አሉት ሸይኹ!!
ከአንድ ዐረብኛ ፅሑፍ የተቀዳ ነው፡፡
Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:- 1️⃣2️⃣5️⃣
* የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
https://t.me/IbnuMunewor/3505
* የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 332፣ ሐዲሥ ቁ. 831
* የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን
* የሚሰጥበት ጊዜ:- ረቡዕ፣ ሐሙስ እና ጁሙዐ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የሙሐደራ ዝግጅት
~~
1. ሐያእ - የኢማን ቀንዘል
በኢብኑ ሙነወር
2. ላኢላሀ ኢል-ለላህ - ትሩፋቶቿና መስፈርቶቿ
በኡስታዝ ናሲር ሙሐመድ (አቡል ዐባስ)
ቦታ :- ከአለም ባንክ ወደ 105 በሚወስደው መንገድ ላይ አንፎ ድልድይ ሑዘይፋ መስጂድ
ቀን:- የፊታችን እሁድ ታህሳስ 21 ከ 3:30 እስከ ዙሁር
Live : የሚለቀቅበት ቻናል ⬇️
https://t.me/iidhaeatu_leilm_shareii
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
በፀሐይ የተሞቀን ውሃ ለውዱእ / ለትጥበት መጠቀም ይቻላል?
~
ነብዩ ﷺ ለፀሀይ በተጋለጠ ውሃ ውዱእ ከማድረግ እንደከለከሉ የሚገልፅ ሐዲሥ አለ። ይህንን በመያዝም በፀሐይ የተሞቀን ውሃ ለውዱእ ወይም ለትጥበት መጠቀምን የሚከለክሉ ያጋጥማሉ። ይሄ ግን ትክክል አይደለም። ምክንያቱም በዚህ ላይ የመጣው ሐዲሥ በነብዩ ﷺ ስም የተቀጠፈ መሰረት የለሽ ወሬ ነውና። ተጨባጭ የተረጋገጠ መረጃ በሌለበት ደግሞ ለፀሀይ በተጋለጠ ውሃ ውዱእ ማድረግ ክልክል ነው ማለት አይቻልም። ጌታችን አላህ እንዲህ ይላል፦
(هُوَ الَّذِي خَلَقَ لَكُمْ مَا فِي الأَرْضِ جَمِيعاً)
"እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡" [አልበቀራህ፡ 29]
(وَسَخَّرَ لَكُمْ مَا فِي السَّمَوَاتِ وَمَا فِي الأَرْضِ جَمِيعاً مِنْهُ)
"ለናንተም በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ በመላ ከእርሱ ሲሆን ገራላችሁ።" [አልጃሢያህ፡ 13]
ስለዚህ ግልፅ ከልካይ መረጃ እስካልመጣ ድረስ የሰው ልጅ ሁሉንም ነገር እንዲጠቀም ተፈቅዶለታል። በፀሐይ የሞቀን ውሃ ከመጠቀም የሚከለክል ደግሞ አንድም ጠንካራ የሸሪዐ መረጃ የለም። የሰዑዲያ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ እንዲህ ይላል፦
" لا نعلم دليلا صحيحا يمنع من استعمال الماء المشمس "
"በፀሐይ የሞቀን ውሃ ከመጠቀም የሚከለክል ጤነኛ መረጃ አናውቅም።" [ፈታዋ አለጅነቲ ዳኢማህ፡ 5/74]
በዚህ ላይ የመጣውን ዘገባ በተመለከተም ሸይኹል አልባኒይ - ረሒመሁላህ - መሰረተ ቢስ ቅጥፈት ነው ብለዋል። [አልኢርዋእ፡ 1/53] ከሳቸውም በፊት አልዑቀይሊይ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ብለዋል፦
"ليس في الماء المشمس شئ يصح مسندا"
"በፀሐይ የሞቀን ውሃ በተመለከተ ከዘገባ መስመር አንፃር ትክክል የሆነ ምንም ነገር የለም።" [አዱዐፋእ፡ 2/176]
Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
እግሮችን ወደ ቂብላ አቅጣጫ መዘርጋት
~
ከዑለማእ ውስጥ እግሮችን ወደ ቂብላ አቅጣጫ መዘርጋትን የተጠላ ነው ያሉ አሉ። ነገር ግን ይህንን የሚከለክል አንድም ማስረጃ የለም። ሸይኽ ኢብኑ ሑመይድ - ረሒመሁላህ - "ከዚህ የሚከለክል የለም" ይላሉ። [ፈታወ ሸይኽ ኢብኒ ሑመይድ: 144]
ሸይኽ ኢብኑ ባዝም እንዲሁ ምንም ችግር የለበትም ብለዋል።
ኢብኑ ዑሠይሚንም እግሮችን በእንቅልፍ ጊዜ ወደ ቂብላ አቅጣጫ ስለማድረግ ሲጠየቁ እንዲህ ብለዋል፦
ليس على الإنسان حرج إذا نام ورجلاه في اتجاه القبلة .
"በአንድ ሰው ላይ እግሮቹ ወደ ቂብላ አቅጣጫ ሆነው ቢተኛ ችግር የለበትም።" [ፈታወ ሸይኽ ኢብኒ ዑሠይሚን፡ 2/976]
Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የጤና ባለሞያውን ህይወት እንታደግ!
አብዱ! ትላንት የጤና እክል ገጥሟቸው ድጋፉን እርዳታውን ለሹ ሁሉ ቀድሞ የሚደርስ ለህይወት መቀጠል ያለውን ሁሉ የሰጠ የጤና ባለሞያ ነበር።
ለአመታት በጤና ባለሞያነት በቆየባቸው አመታት አቅም የሌላቸውን ያለክፍያ እስከማስተናገድ ይደርስም ነበር!!
ዛሬ ግን ድጋፍ የሚጠይቅበት ጊዜ ላይ ደርሷል! ሁለቱ ኩላሊቶቹ ስራ በማቆማቸው፣ ህይወቱ አደጋ ላይ ነው! በዲያሌሲስ ለሶስት ወራት ቢቆይም ወጭውን መሸፈን ወደማይችልበት ደረጃ ተሻጋግሯል!!
ንቅለተከላ እንዲደረግለት አስገዳጅ ሆኗል!!
በአሁኑ ሰአትም በአዲስ አበባ ላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል(መገናኛ 24 አካባቢ) በሳምንት ሁለት ጊዜ ዲያሌሲስ እያከናወነ ይገኛል!
ካለን ላይ ቀንሰን እንታደገው ብላችሁ በተጠቀሰው አካውንት የላካችሁ፣ ስክሪን ሹት በውስጥ ላኩልን!!
ውድ ቤተሰቦቹ፣ ጌደኞቹና በስስት የሚናፍቃቸው ልጆቹ እንዲሁም የሱን የሞያ ድጋፍ የሚሹ ሁሉ ይጠብቁታልና ፣ አነሰ በዛ ሳንል የቻልነውን እናድርግ!!
1000584320323 Abdurehman seid/አብዱረህማን ሰይድ የሱፍ /የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ/
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ከኢማሙ አሕመድ ዱዓዎች ውስጥ አንዱ እንዲህ የሚል ነበር
اللهم مَن كان مِن هذه الأمة على غير الحق وهو يظن أنه على الحق ، فرُدَّه إلى الحق ؛ ليكونَ من أهل الحق
"አላህ ሆይ! ከዚህ ህዝብ ውስጥ ሐቅ ላይ እንደሆነ በማሰብ ከሐቅ ያፈነገጠን ሁሉ ከሐቅ ሰዎች ይሆን ዘንድ ወደ ሐቅ መልሰው።" [አልቢዳያ ወንኒሀያ: 10/329]
[አልቢዳያህ ወኒሃያህ፡ 10/329]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
የኢብኑ ምነወር የድምፅ ፋይሎች ለማግኘት
ጥያቄዎችን ለመከታተል ጎራ ይበሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/heyruabrar
https://t.me/heyruabrar
የኢብኑ ምነወር የድምፅ ፋይሎች ለማግኘት
ጥያቄዎችን ለመከታተል ጎራ ይበሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/heyruabrar
https://t.me/heyruabrar
የኢብኑ ምነወር የድምፅ ፋይሎች ለማግኘት
ጥያቄዎችን ለመከታተል ጎራ ይበሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/heyruabrar
https://t.me/heyruabrar
የኢብኑ ምነወር የድምፅ ፋይሎች ለማግኘት
ጥያቄዎችን ለመከታተል ጎራ ይበሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/heyruabrar
https://t.me/heyruabrar
የኢብኑ ምነወር የድምፅ ፋይሎች ለማግኘት
ጥያቄዎችን ለመከታተል ጎራ ይበሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/heyruabrar
https://t.me/heyruabrar
የኢብኑ ምነወር የድምፅ ፋይሎች ለማግኘት
ጥያቄዎችን ለመከታተል ጎራ ይበሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/heyruabrar
https://t.me/heyruabrar
የኢብኑ ምነወር የድምፅ ፋይሎች ለማግኘት
ጥያቄዎችን ለመከታተል ጎራ ይበሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/heyruabrar
https://t.me/heyruabrar
