📚منهج السلف طريقنا الى الله 📚
الذهاب إلى القناة على Telegram
↘️በዚህ ቻናል የሚተላለፉት ↘️በሱና ኡስታዞች የተቀሩ ደርሶች ↘️የሱና ኡስታዞች ሙሀደራዎች ↘️በመቀጠል አስተማሪ ፁሁፎች ➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/htt_asselfya
إظهار المزيد3 819
المشتركون
-524 ساعات
+1617 أيام
+15530 أيام
أرشيف المشاركات
Repost from Mohammed saied (ሙሐመድ ሠዒድ)
🌴ኢብኑ በጧል ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-
❝አንድ ባሪያ በዱዓ ላይ ትጋት ሊኖሮው ይገባል እንዲሁም መልሱን ለማግኘት ተስፋ ማደረግ እንጂ የሚገባው ከአላህ ራህመት ፈፅሞ ተስፋ መቁረጥ የለበትም ምክንያቱም የሚለምነው የልግስና ባለቤት የሆነውን ጌታ
አላህን ነውና።❞
📚شرح صحيح البخاري (١٠/ ٩٩)
═════ ❁✿❁ ═══
https://t.me/Mohammedseid21
Repost from Mohammed saied (ሙሐመድ ሠዒድ)
🌴ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-
❝አንድ ብልህ የሆነ ሰው ከግዴታ በኋላ ነዋፊሎችን ማብዛት ይኖርበታል ምክንያቱም አንድ ሰው በጤንነት ላይ እያለ ዘወትር ሲሰራቸው የነበሩ ተግባራት፡- በታመመና በአረጀ ጊዜ በጤንነቱና በወጣትነቱ ሲሰራቸው የነበሩ ተግባራት ሙሉ ተደርገው ይፃፉለታልና።❞
📚الشرح الممتع ( ٤ / ٨٠ ) 】
═════ ❁✿❁ ═══
https://t.me/Mohammedseid21
Repost from Mohammed saied (ሙሐመድ ሠዒድ)
🌴ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ብለዋል፡-
❝ሸሪዓዊ በሆኑ ግዴታዎች ብቻ ወደ አላህ የሚቃረቡት ሷሊሆች «ሙቅተሲዱን»መካከለኞች የቀኝ ጓዶች ናቸው።እንዲሁም ከግዴታዎች በኋላ «ነዋፊሎችን» አላህ የሚወዳቸውን ስራዎች በመስራት ወደ አላህ በተጨማሪ የሚቃረቡት በላጮች ሲሆኑ«አል-ሳቢቁን» ቀዳሚዎች እና
የአላህ ባለሟሎች ናቸው።ምክንያቱም
ነዋፊሎች ከግዴታዎች በኋላ ነውና
የሚገኘው።
📚مجموع الفتاوى (١٣٩/٢
═════ ❁✿❁ ═══
https://t.me/Mohammedseid21
Repost from Mohammed saied (ሙሐመድ ሠዒድ)
🌴ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡-
❝ከእስልምና በኋላ አንድም ባሪያ መልካምን አልተሰጠም መልካምን «ጥሩን» ወንድም
ቢሆን እንጂ።❞
📚قوت القلوب - (2 /178)
═════ ❁✿❁ ═══
https://t.me/Mohammedseid21
Repost from Mohammed saied (ሙሐመድ ሠዒድ)
🌴ኢብኑ ቁዳማህ አል-መቅዲሲይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡-
❝አብዘሃኞቹ ሰዎች የጠፉት የሰዎችን ነቀፌታ በመፍራት እና ውዳሴያቸውን በመፈለግ መሆኑን እወቅ! ስለዚህ አንድ ሰው እንቅስቃሴዎቹ ሁሉ ሰዎችን በመፍራት እና ወቀሳቸውን በመስጋት ላይ ከሆነ ይህ አጥፊ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ነው
በፍጥነትም ህክምና
ይፈልጋልና።❞
📚مختصر منهاج القاصدين ١/٢١٢ }
═════ ❁✿❁ ═══
https://t.me/Mohammedseid21
Repost from Mohammed saied (ሙሐመድ ሠዒድ)
🌴ኢማም አህመድ ኢብኑ ሀንበል ረሒመሁላህ እንዲህ አሉ፡-
❝አላህን ለሃምሳ አመታት ያህል «ተገዛሁኝ» አመለኩኝ ነገርግን ሶስት ነገሮችን እርግፍ አድርጌ እሰከምተው ድረስ የኢባዳ ጥፍጥና አላገኘሁም።የሰዎችን ውዴታ እርግፍ አድርጌ ተውኩኝ ሀቅ መናገርን እስከምችል ድረስ።ኃጢአተኞችን ፋሱቆችን እርግፍ አድርጌ ተውኩኝ ሷሊሆችን ጓደኞቼ አድርጌ እስከያዝኩኝ ድረስ። የቅርቢቱን ዓለም ጥፍጥና ተወኩኝ
የመጨረሻይቱን ዓለም ጥፍጥና
እስከማገኝ ድረስ።❞
📚« سير أعلام النّبلاء(11/ 34)
═════ ❁✿❁ ═══
https://t.me/Mohammedseid21
Repost from Mohammed saied (ሙሐመድ ሠዒድ)
"سبحان الله وبحمده"
مائة مرة
من قالها مائة مرة حين يصبح وحين يمسي لم يأت أحد يوم القيامة بأفضل مما جاء به إلا أحد قال مثل ما قال أو زاد عليه.
«ለአላህ ጥራትና ምስጋና ይገባው»
የሚለውን በጧት እና በማታ መቶ ጊዜ ያለ ሰው በቂያማ ቀን ማንም ሰው እሱን የበለጠው ሆኖ አይመጣም ከእርሱ የተሻለ ይዞ የመጣ ወይም አንዲትን የጨመረ ሰው ቢሆን
እንጂ።
📚مسلم، ٤/ ٢٠٧١ برقم ٢٦٩٢.
═════ ❁✿❁ ═══
https://t.me/Mohammedseid21
Repost from Mohammed saied (ሙሐመድ ሠዒድ)
🌴በክር ቢን አብደላህ አል-ሙዘነይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡-
❝አንድ ባሪያ አንድ ጊዜ «الحمد لله »“ምስጋና ለአላህ ይሁን” ብሎ አያመሰግንም በማመስገኑ ምክንያት የአላህ ፀጋ በእርሱ ላይ የሆነች ብትሆን እንጂ። የዚህች ፀጋ ዋጋ ሽልማቷ ምንድነው ለሚለው? ሽልማቷ ይህቺ “አላህን ያመሰገነባት ፀጋ”ከእርሷ ሌላም ተጨማሪ ፀጋ አመስጋኝ ለሆነው ሰው አለህ ይሰጠዋል ምክንያቱም የአላህ
ፀጋዎች አያልቁምና።❞
📚الشُّكر لابن أبي الدُّنيا(١٤)
═════ ❁✿❁ ═══
https://t.me/Mohammedseid21
Repost from Mohammed saied (ሙሐመድ ሠዒድ)
🌴አቢ ሱለይማን አል-ዳሪኒይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡-
❝የዱንያ ፍላጎትን የሚታገስ አንድም ሰው የለም በልቡ ውስጥ ከሞት በኋላ ላለው ህይወት የሚሰራና የሚተጋ ሰው
ቢሆን እንጂ።❞
📚موسوعة ابن أبي الدنيا 5/135].
═════ ❁✿❁ ═══
https://t.me/Mohammedseid21
Repost from Mohammed saied (ሙሐመድ ሠዒድ)
🌴አል-ፉዳይል ኢብኑ ኢያድ ረሒመሁላህ እንዲህ አሉ፡-
❝በምድር ላይ ለመተው የሚከብድ ነገር ምንም የለም «ስሜትን» ፍላጎትን መተው
ቢሆን እንጂ።❞
📚حليلة الاولياء(٩٨/٨)
═════ ❁✿❁ ═══
https://t.me/Mohammedseid21
Repost from Mohammed saied (ሙሐመድ ሠዒድ)
🌴ፉደይል ኢብኑ ኢያድ ረሒመሁላህ እንዲህ አሉ፦
❝ትክክለኛውን መንገድ ተከተል የተከታዮቹ ማነስ አይጎዳህምና ከጥመትም መንገዶች ተጠንቀቅ የጠፊዎቹ መብዛት
አያታልልህ።❞
📚الصَّواعق المرسلة لابن القيم 3/86
═════ ❁✿❁ ═══
https://t.me/Mohammedseid21
Repost from Mohammed saied (ሙሐመድ ሠዒድ)
🌴የአላህ መልእክተኛﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
لا يتوضأ رجل فيحسن وضوءه ثم يصلي الصلاة ، إلا غفر له ما بينه وبين الصلاة التي تليها
❝አንድ ሰው ውዱእ አሳምሮ አያደርግም ከዚያም አይሰግድም በእርሱ ሰላትና በቀጣይዋ ሶላት መካከል ያለውን ወንጀሉን አላህ የማረው
ቢሆን እንጂ።❞
📚صحيح مسلم/٢٢٧)
═════ ❁✿❁ ═══
https://t.me/Mohammedseid21
Repost from Mohammed saied (ሙሐመድ ሠዒድ)
🌴ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሒመሁሏህ እንዲህ ብለዋል፡-
❝በአዛን ጥሪ እና በኢቃማ መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ የሚደረግ ዱዓ ተቀባይነት የማግኘት እድሉ ሰፊ ነው ይህን እድል ተጠቅማችሁ በአዛን ጥሪ እና በኢቃማ መካከል ባለው ጊዜ አላህን ለምኑት አላህ ይቀበላችሁ ዘንድ ተስፋ
ይደረጋልና።❞
📚 شرح رياض الصالحين : (٤٢/٥)
═════ ❁✿❁ ═══
https://t.me/Mohammedseid21
Repost from Mohammed saied (ሙሐመድ ሠዒድ)
🌴ኢማም ኢብኑ ዑሰይሚን ረሒመሁሏህ እንዲህ ብለዋል፡-
❝ከጓደኞችህ መካከል የአንተ መጥፋት አልመጥፋት ግድ የማይሰጠው ሰው ይልቁንም ወደ ጥፋት የሚመራህ ሰው ከገጠመህ ተጠንቀቅ እርሱ በምግብ የሚወሰድ መርዝ ነውና። አላህ ይጠብቀን። እንዲህ ያሉ ሰዎችን አትቅረቡ እንደውም ከነሱ ራቁ ከአንበሳም እንደምትሸሹት ሁሉ ከእነሱም ሽሹ።❞
📚شرح رياض الصالحين٢/٣٨٨
═════ ❁✿❁ ═══
https://t.me/Mohammedseid21
Repost from Mohammed saied (ሙሐመድ ሠዒድ)
🌴ሸይኽ አብዱል አዚዝ ኢብኑ ባዝ ረሒመሁሏህ እንዲህ አሉ፡-
❝አንተ የመገለል ዕንግዳ የመሆን ዘመን ላይ ነው ያለኸው። እውቀት አናሳ የሆነበት ድንቁርና የበዛበት የቢድዓ ዱዓቶች የበዙበት በአጠቃላይ ፈሳድ የበዛበት ዘመን ላይ ነው ያለኸው።በሃቅ ላይ ፅና ሃቅን አጥብቀህ ያዝ የሃቅ ባለቤቶችን ጓደኛ አድርገኽ ያዝ። የጥፋት ባለቤቶችን ጓደኛ አድርገህ ከመያዝ ተጠንቀቅ።ኢልምን በመፈለግ ላይ አደራህን የመልካም ነገሮች ሁሉ መሰረት የሆነውን የታላቁ አላህን ኪታብ በመያዝ ላይ
አደራህን።❞
📚حديث المساء (ص٢٢٢)
═════ ❁✿❁ ═══
https://t.me/Mohammedseid21
Repost from Mohammed saied (ሙሐመድ ሠዒድ)
ነብዩﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
«من أكثرَ من الاستغفارِ جعل اللهُ لهُ من كلِّهمٍّ فَرَجًا ومن كلِّ ضيقٍ مخرجًا ورَزَقَهُ من حيثُ لا يحتسبُ
❝ኢስቲግፋርን ያበዛ ሰው አላህ ከሃሳብ እና ከጭንቅት ሁሉ መውጫን መንገድን
ያደርግለታል ካልጠበቀውም ቦታ ሲሳይን
ይለግሰዋል።❞
📚مسند أحمد [٥٦/٤]
═════ ❁✿❁ ═══
https://t.me/Mohammedseid21
Repost from Mohammed saied (ሙሐመድ ሠዒድ)
🌴ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-
❝«ተማኢም»ፅህፎች በተመለከተ በህጻናት እና በታመሙ ሰዎች አንገት ላይ የሚንጠላጠሉ ሲሆኑ ከሰው ልጆች ጋር የተያያዙ እንደ አንገት ቦርሳ ጨርቃጨርቅ እንዲሁም አንዳንድ የተሸፈኑ የተቋጠሩ ወይም ያልታወቁ ጽሑፎች የተጻፉባቸው እና የመሳሰሉት ናቸው። ከቁርኣን አንቀጾች የተፃፈውን በተመለከተ ከፊል ኡለማዎች አስተያየቶችን ቢሰጡም ትክክለኛ ይህ ሁሉ አይፈቀድም ይልቁንም ሽርክ ነው።ለዚህም ማስረጃው የመልዕክተኛውﷺ ሐዲሥ ነው፡- ‹‹ተማኢም ኺርዝ ሽርክ ናቸው›› የሚለው ሲሆን አሕመድና አቡ ዳውድ በጥሩ ሰንሰለት ውስጥ ዘግበውታል ሰነዱንም ሃሰን ብለውታል።
ነብዩﷺ እንዲህም ብለዋል፦ “ተማኢምን "(የተፃፈን ነገር) ያንጠለጠለ ሰው አላህ አያሟላለት(በዚያ ነገር የፈለገውን ነገር አያሳካለት እንዲሁም«ተሚመ» የተፃፈን ነገር ያንጠለጠለ ሰው በእርግጥም ሽርክን ፈጽሟልና።
የሚሉት ናቸዉ።❞
📚 (مجموع فتاوى
ومقالات متنوعة 9/454 )
═════ ❁✿❁ ═══
https://t.me/Mohammedseid21
Repost from Mohammed saied (ሙሐመድ ሠዒድ)
🌴ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-
❝ከሱና ጋር የሚቃረን አንድንም የቢድዓ ባለቤት አታገኝም የሃቅ መረጃዎችን የደበቀና የውሸት ማስረጃዎችን ግልፅ ያደረገ ቢሆን እንጂ።አንዳንድ ቀደምቶች እንዳሉት፡-አንድ ሰው ቢዳዓን አይፈጥርም የሃዲስ ጥፍጥና ከልቡ የወጣ ቢሆን እንጂ።❞
📚 درء تعارض العقل والنقل ٢٢١/١
═════ ❁✿❁ ═══
https://t.me/Mohammedseid21
Repost from Mohammed saied (ሙሐመድ ሠዒድ)
🌴ሸይኽ ረቢእ አል መድኸሊ አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ ብለዋል፡-
❝ጅኖችም ሆኑ ሌሎች ፍጥረቶች ይህንን ዱዓ ካልክ ፈፅሞ አይቀርቡህም፦
" أعوذ بكلمات الله التامات
من شر ما خلق
“ከፈጠራቸው ፍጡራን ተንኮል ሁሉ ፍጹምና ሙሉ በሆነው የአላህ ቃል እጠበቃለሁ።” ይህን ካልክ ጂኒዎችም ይሁኑ እባብ ወይም ሌላ ነገር ፈፅሞ አይጎዳህም አይቀርብህም።አላህ በረካ ያድርግህና ይህንን ስታደርግ በኢኽላስና በእርግጠኝነት መሆን አለበት።❞
📚رسالة في العقيدة والمنهج: (16)
═════ ❁✿❁ ═══
https://t.me/Mohammedseid21
