cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የብርሃን ፈርጦች

Created by Kaleab Bahta Welcome to our channel 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 ⭐⭐⭐⭐⭐⭐⭐  💛እንኳን ደህና መጡ💛  ⭐⭐⭐⭐⭐⭐⭐  🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች በዚህ ቻናል ከሳይንስ ማህደር #ከጤና ገፅ ፣ የቴክኖሎጂ ውጤቶች እና የጥበብ ስራዎች እንዲሁም ምርጥ ምርጥ ነገሮች ይቀርቡበታል። For any comments @Kal123awi

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
200
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

በድሮ ዘመን ነው አሉ አንድ ሰውዬ በእንጨት ጫፍ ላይ መፈክር አንጠልጥሎ ከተማዋን ይዞራል፡፡ ከመፈክሩ ፅሁፍ ""ነው!""የሚለው በጉልህ ይታያል፡፡ ታድያ ሰውየዉ ከተማ ውስጥ "ነው!" እያለ ሲጮህ ብዙ ተከታዮች አፍርቶ "ነው!" ሲል . . ."ነው!" ይላሉ፡፡ ሰውየው፡- "ነው!" ህዝብ፡- "ነው!" ሰውየው፡- "ነው!" ህዝብ፡- "ነው!" ሰውየው፡- "ነው!" ህዝብ፡- "ነው!" በመጨረሻም ፖሊሶች አስቁመዋቸው "ምንድነው "ነው!" ማለት?" ብለው ህዝቡን ጠየቁ፡፡ ግን የሚመልስ አልተገኘም፡፡ በመጨረሻም ሰውዬውን ይዘው ጠየቁት፡፡ ሰውየው ግን ዝም ብሎ "ነው!" እያለ ይጮሀል፡፡ ከዚያም እንጨቱን ተቀብለው በደንብ ሲያነቡ የሚለው "ይህ የእንጨቱ ጫፍ ነው!" የሚል ነበር፡፡ 💖✳️💖✳️💖✳️💖✳️💖✳️ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰 👍 @abogidastars
إظهار الكل...
መልካም የእናቶች ቀን ግንቦት 1/2013 አ.ም
إظهار الكل...
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ሀይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላም። ✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
إظهار الكل...
ዛሬ 'April the Fool' ነዉ❗ ለመሆኑ ይህ ቀን እንዴት ተጀመረ❓ የቀኑ አስገራሚ እዉነታዎች👇👇 April the Fool' መነሻዉ እ.ኤ.አ በ1582 ሲሆን ፈረንሳይ የጁሊያን የዘመን መቁጠሪያን ወደ ግሪጎሪያን መቀየሯ የፈጠረዉ ክስተት ነበር፡፡ በጊዜዉ የጁሊያን የዘመን መቁጠሪያ ልክ እንደ ሂንዱ የዘመን መቁጠሪያ በመሆኑ አዲስ ዓመት የሚጀምረዉ በወርሃ መጋቢት(አፕሪል 1)ነዉ፡፡ ታዲያ ፈረንሳይ ወደ ጥር ወር(ጃዉኗሪ 1 ስትቀይረዉ) ይህንን ያልተረዱ ሰዎች በመጋቢት ወር ማክበራቸዉን ይቀጥላሉ በዚህ የተነሳ የአፕሪል ሞኞች እየተባለ እንደቀልድ ተጀመረ፡፡ ይህንኑ ተከትሎ ታዲያ በዘመናዊዉ ዓለም ለቀልድ በሚል ታላላቂ የመገናኛ ብዙሃን የዉሸት ዘገባዎችን እየሰሩ ቀኑ ዉሸት እንዲበራከትበት አድርገዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ1957 ቢቢሲ የስዊዘርላንድ የሚገኙ ገበሬዎች ከዛፍ ላይ የስፓጌቲ ዘር አመረቱ ብሎ መዘገቡ በጊዜወ ሰዎች ቢያምኑትም በመጨረሻም ቢቢሲ የዉሸት ዜና መሆኑን በዚህ ቀን አጋርቷል፡፡ ናሽናል ጆግራፊ በዚህ በዉሸት ቀን ከአምስት አመት በፊት የሰራዉ ዜና የሚያዝናና ሲሆን ከዚህ በኃላ ለእይታ የምናበቃቸዉ እንስሳት ልብስ የለበሱ ብቻ ናቸዉ ሲል በራቁታቸዉ የሚታዩ እነ አንበሳ፣ነበርና ሌሎች እንስሳትን መብት እናከብራለን ሲል በኤፕሪል ዘ ፉል የቀረበ የዉሸት ዜማ አሰራጭቷል፡፡ በ2008 ሰን የተሰኘዉ ጋዜጣ በሰራዉ ዘገባ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት የሆኑት ኒኮላስ ሳርኮዚ ቁመታቸዉን ለመጨመር የቀዶ ጥገና ሊደረግላቸዉ ነዉ በዚህም የተነሳ ከምትበልጣቸዉ ከሞዴሏ ባለቤታቸዉ ካርላ ብሩኒ አንድ ኢንች ቁመታቸዉ ይጨምራል ሲል ዘግቧል፡፡ Via በስምዖን ደረጀ/ብስራት ሬዲዮ #SHARE @abogidastars
إظهار الكل...
🥰🥰ተመስገን ዛሬ ቀኑ ደስ ሲል🥰🥰 " ውድቀት ማለት መውደቅ ማለት ሳይሆን ከውድቀት ለመነሳት አለመሞከር ነው " የጀርመናውያን አባባል 🗒🗒🗒 ሳይወድቅ እና ሳይነሳ በሁለት እግሩ የሚቆም የሰው ልጅ የለም ዳዴ ማለታችን እየተንገዳገድን መራመዳችን በድጋፍ መቆማችን በትክክል ለመራመዳችን መነሻ ነው ። ያልሞከረ አይሳሳትም! ያልሞከረ አይቆምም! ያልሞከረም አይወድቅም ። 🗒🗒🗒 ባለመሞከር ውስጥ ካለው የዝግመት እና የመቆም ኑረት በሙከራ ውስጥ ያለው ውድቀት ይሻላል...ሙከራ ካለ ከውድቀት በኋላም መነሳት አለና ። መውደቅ የሚሞክር ሰው የሚገጥመው ነገር ነው እንደወደቁ መቅረት ግን ተስፋ የመቁረጥ ምልክት ነው ። 🗒🗒🗒 ስለዚህ መውደቅን ሳይሆን ከውድቀት ለመነሳት አለመሞከርን ፍራ ። ሞክሮ መሳሳትን ሳይሆን አለመሞከርን ፍራ ። @abogidastars
إظهار الكل...
እነሆ ለእናንተ 🧏 ልውጠት የጸሃይ መውጣት መግባት በድግግሞሽ የሚሆን ሁነት ቢሆንም ሹክ የሚለን ሃቅ አለ ። ተለዋዋጭነትን። ወጥታ አልቀረችም ። ገብታም አልቀረችም። (ወጣች ገባች ማለቴ ከእይታችን አንጻር ነው። በቀጥታ ምልከታ የሚታየን እንዲያ አይደል።) የሙቀት መጠኗ የብርሃን ልኳም በእያንዳንዷ ደቂቃ የተለያዬ ነው (ለኛ ስትደርስ)። ከፍ ዝቅ … ዝቅ ከፍ። በመውጣት መግባቷ ጊዜ ሲነጉድ የሃይልና የግዝፈት ለውጥ እውን ይሆናል። በጠብታ አለት ይፈረከሳል። ሰውም ክቡን ለመሙላት ይነጉዳል። ካለመኖር ወደመኖር ፥ ከማጎንበስ ወደቀና ማለት ፥ ከቀና ማለት ወደማጎንበስ ከዚያም ወደህልፈት። ለውጥ በጊዜ ስር ያለ የማይቀር እዳ ወይም እድል። (ለከጸሃይ በታች ኗሪዎች። … ) 🙏ሰላማችሁን ይብዛ! @abogidastars @abogidastars @abogidastars
إظهار الكل...
#ሕይወት #ከባድም #ቀላልም #ነች! “ዛሬ ሕይወት ከበድ ተደርጋ ስትያዝ ነገ ቀለል ትላለች፣ ዛሬ ቀለል ተደርጋ ስትያዝ ደግሞ ነገ ከበድ ትላለች” – Dave Kekich ሕይወትን ከበድ አድርጎ መያዝ ማለት የግል ዲሲፕሊንን በማዳበር ለመልካም ውጤት ሲባል ከበድ ያሉ ነገሮችን መጋፈጥና ማድረግ ማለት ነው፡፡ ሕይወትን ቀለል አድርጎ መያዝ ማለት ደግሞ ካለምንም ዲሲፕሊን የመጣልንን፣ የቀለለንንና ለጊዜው ብቻ ጥሩ ስሜት የሰጠንን በማድረግ መኖር ማለት ነው፡፡ ከላይ በተጠቀሰው አውድ መሰረት ዛሬ ሕይወትን ቀለል አድርጎ መኖር ማለት ዛሬ ለመደሰትና ዛሬ ሁሉም ነገር እንዲቀለን ስንል ከነገ የተቀማጭ ሂሳባችን አውጥቶ መክፈል እንደማለት ነው፡፡ ስለሆነም “ዛሬ” አልፎ “ነገ” ሲመጣና “ዛሬ” “ትናንት” ሲሆን አሁን የደረሰውን “ዛሬን” “ትናንትና” ቀላል ኑሮ ለመኖር ስንል ስለከፈልነው ኑሮ እጅጉን ይከብደናል፡፡ በጣም ደካማ ፈቃድ ያለውን ሰው አስቡት፡፡ አንድ ነገር ለማድረግ ያስብና ሁኔታው ከበድ ካለው ይተወውና ወደቀለለው ነገር ዞር ይላል፡፡ እንደዚህ አይነቱ ሰው ምንም ነገር ማከናወን ካለመቻም በላይ ዛሬ የቀለለው ሕይወት ነገ እንደሚከብደው ግልጽ ነው፡፡ በተቃራኒው ዛሬ ሆን ብሎ ከባባድ ምርጫዎችን በመምረጥ ተግቶ የሚማር፣ ጠንክሮ የሚሰራ፣ ወጥሮ የሚያጠራቅምና ታግሶ ችግርን የሚያልፈውን ሰው ተመልከቱት፤ ይህ ሰው ዛሬ ስለሚከፍል ቢከብደውም ነገ ግን ስለሚከፈለው ይቀለዋል፡፡ መልካም ውሎ! #Dr-Eyob-Mamo @abogidastars @abogidastars @abogidastars
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.