cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የህይወት ቅኔ💡

♥️ልቦች በዝምታ ነገራቶችን ያስተውላሉ አላህም የሁሉ ነገር አስተናባሪ መሆኑን ይረዳሉ...... ጥራት, ክብር ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ ይሁን 🌿

إظهار المزيد
Ethiopia12 008لم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
187
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

وَقَالَتِ الْيَهُودُ يَدُ اللَّهِ مَغْلُولَةٌ ۚ غُلَّتْ أَيْدِيهِمْ وَلُعِنُوا بِمَا قَالُوا ۘ بَلْ يَدَاهُ مَبْسُوطَتَانِ يُنفِقُ كَيْفَ يَشَاءُ ۚ وَلَيَزِيدَنَّ كَثِيرًا مِّنْهُم مَّا أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ طُغْيَانًا وَكُفْرًا ۚ وَأَلْقَيْنَا بَيْنَهُمُ الْعَدَاوَةَ وَالْبَغْضَاءَ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ ۚ كُلَّمَا أَوْقَدُوا نَارًا لِّلْحَرْبِ أَطْفَأَهَا اللَّهُ ۚ وَيَسْعَوْنَ فِي الْأَرْضِ فَسَادًا ۚ وَاللَّهُ لَا يُحِبُّ الْمُفْسِدِينَ (ሱረቱ አል-ማኢዳህ - 64) አይሁዶችም «የአላህ እጅ የታሰረች ናት» አሉ፡፡ እጆቻቸው ይታሰሩ ባሉትም ነገር ይረገሙ፡፡ አይደለም (የአላህ) እጆቹ የተዘረጉ ናቸው፡፡ እንደሚሻ ይለግሳል፡፡ ከጌታህም ወደ አንተ የተወረደው (ቁርኣን) ከእነሱ ብዙዎቹን ትዕቢትንና ክህደትን በእርግጥ ይጨምራቸዋል፡፡ በመካከላቸውም ጠብንና ጥላቻን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ጣልን፡፡ ለጦር እሳትን ባያያዙ (ባጫሩ) ቁጥር አላህ ያጠፋታል፡፡ በምድርም ውስጥ ለማበላሸት ይሮጣሉ፡፡ አላህም አበላሺዎችን አይወድም፡፡
إظهار الكل...
۞ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا الْيَهُودَ وَالنَّصَارَىٰ أَوْلِيَاءَ ۘ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ وَمَن يَتَوَلَّهُم مِّنكُمْ فَإِنَّهُ مِنْهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ (ሱረቱ አል-ማኢዳህ - 51) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ፡፡ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ረዳቶች የሚያደርጋቸው ሰው እርሱ ከነርሱ ነው፡፡ አላህ አመጸኞችን ሕዝቦች አያቀናም፡፡
إظهار الكل...
የዚክር ፋይዳ (መሀመድ ዓሊ) አንዳች በጎ ነገር እንዲያደርግልህ ያሰብከውን ሰው አትረሳውም። ጠዋት ማታ ታስታውሰዋለህ ምስጋናና አክብሮትህን ትገልፅለታለህ። ያስከፋሃው ሲመስልህም በፍጥነት ይቅርታ ትጠይቀዋለህ። ካጠገቡ አትርቅም። በዙሪያው እንዲያስታውስህ ታንዣባለህ። አንተነትህን ጭምር የሰራን አምላክ ግን ረስተህ ሙውጫ ባጣህ ጊዜ ብቻ አቤቱታህን ታቀርባለህ። አይከብድም? ረስተኸው የኖርከውን ሰው ቢያስፈልግህ እንኳ ልታማክረው ትፈራለህ ታፍራለህ። ከጎንህ እንዲሆን የምትፈልገውን ሰው አትርቀውም። ይህ ምድራዊ ነው፡ ሰዋዊ ነው አስበህ የምታረገው ነው። ከምድር ውጭ ፍፁም የሆነን ጌታ ግን አስልተህ አትቀርበውም። ውስጥህንም አዋቂ ጌታ ነውና። አምላክህ ማውሳት የልብ ዓለም ነው። ከአእምሮ አቅም መሻገር ማለት ነው። ፍፁምናውን ማብሰልሰል ምህረቱን መጠየቅ፡ ታላቅነቱን ማስተዋል፡ አምላክነቱን ማስረገጥ ወዘተ፡ የዚክር ክፍል ነው። እርግጠኝነት እንዲያብብ አዘውትረህ ማሰላሰል ስታበዛ፡ በልብ ውስጥ የምትሞላው እርጋታ አለ፡ የሰናይነት ፍካት አለ። አንተነትን የማወቅ እድል አለ። ሌላም ሌላም። ዚክር ውስጥ ሰው የመሆን እድገት አለ። በምግባር መላቅ አለ። በፍቅር ማበብ አለ። እዝነት አለ። መረጋጋት አለ። የህይወት ፋይዳ አለ። ራስን ማግኘት አለ። መስከን ማስተዋልም አለ። ልብን ማበልፀግ በስጋ፡ በስሜትና ችኩልነት ላይ የበላይ መሆን ነው። ሰው በማሰብ ችሎታው ከእንስሳ ይበልጣል ይሄ ነው ሰውን ከእንስሳ የሚለየው፣ የሚለው የዳርዊናዊ ዓለም ሰው መፈክር ነው። አያሳምንም። በማሰብ ቢሆን የሰለጠኑት ሀገራት ወራሪ ጦረኞች ባልሆኑ ነበር። ሰው እንደሰው ከሌላው የሚለየው በስነ ምግባር ሚዛኑ ነው። በጎና ክፉ ምግባር የሚል እሴት ያለው ሰው ብቻ ነው። በዚህ ማደግ ከፈለግን እውቀት ሳይሆን ዚክር ይሆናል መንገዱ። ፍፁም ኃያል ዳኛ እንዳለን ማሰብ ማሰላሰል። ማሰላሰል፡ መጥለቅ መፈከር ወሳኝ የምግባር ስልጣኔ ጎዳና ነው። ለምሳሌ የበደለህ ሰው ይቅርታ ቢጠይቅህ ይከብድህ ይሆናል። ስታስበው በድሎሃል። እንዴት ይቅር ልበለው ትላለህ። በደል በይቅርታ አይታለፍ በምክኒያት ካየኸው።ታዲያ እንዴት ይቅር ባይ ሆንን? ካሰብከው በምክኒያትህ ይቅር ላትል ትችላለህ ወይም ይቅር ባይነትህ የውሸት ይሆናል። ለዚህ በሽታ መድሃኒቱ ልብን ማበልፀግ ነው። ማህሌተ ዚክር። ልብን ማስፋት። የጌታህን ልቅና ማስተዋል። ሰው በፈጣሪው ማመኑ እሚጠቅመው እዚህ ላይ ነው። በታላቅነቱ ውስጥ የራስን ትንሽነት ያሳያል። የጠወለገ ምግባር በጠለቀ ውዳሴና ማስተንተን ይለመልማል። መሀመድ አሊ Burhan Addis
إظهار الكل...
لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ۚ قُلْ فَمَن يَمْلِكُ مِنَ اللَّهِ شَيْئًا إِنْ أَرَادَ أَن يُهْلِكَ الْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَأُمَّهُ وَمَن فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ۗ وَلِلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا ۚ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ (ሱረቱ አል-ማኢዳህ - 17) እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ የመርየምን ልጅ አልመሲሕን እናቱንም በምድር ያለንም ሁሉ ለማጥፋት ቢሻ ከአላህ ማዳንን የሚችል ማነው በላቸው፡፡ የሰማያትና የምድር የመካከላቸውም ንግሥና የአላህ ብቻ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡
إظهار الكل...
إِن تَجْتَنِبُوا كَبَائِرَ مَا تُنْهَوْنَ عَنْهُ نُكَفِّرْ عَنكُمْ سَيِّئَاتِكُمْ وَنُدْخِلْكُم مُّدْخَلًا كَرِيمًا (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 31) ከእርሱ ከተከለከላችሁት ታላላቆቹን (ኀጢአቶች) ብትርቁ (ትናንሾቹን) ኀጢአቶቻችሁን ከእናንተ እናብሳለን፡፡ የተከበረንም ስፍራ (ገነትን) እናገባችኋለን፡፡
إظهار الكل...
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا يَحِلُّ لَكُمْ أَن تَرِثُوا النِّسَاءَ كَرْهًا ۖ وَلَا تَعْضُلُوهُنَّ لِتَذْهَبُوا بِبَعْضِ مَا آتَيْتُمُوهُنَّ إِلَّا أَن يَأْتِينَ بِفَاحِشَةٍ مُّبَيِّنَةٍ ۚ وَعَاشِرُوهُنَّ بِالْمَعْرُوفِ ۚ فَإِن كَرِهْتُمُوهُنَّ فَعَسَىٰ أَن تَكْرَهُوا شَيْئًا وَيَجْعَلَ اللَّهُ فِيهِ خَيْرًا كَثِيرًا (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 19) እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! ሴቶችን ያስገደዳችሁ ኾናችሁ ልትወርሱና ግልጽን መጥፎ ሥራ ካልሠሩ በስተቀር ከሰጣችኋቸው ከፊሉን ልትወስዱ ልታጉላሏቸውም ለእናንተ አይፈቀድም፡፡ በመልካምም ተኗኗሩዋቸው፡፡ ብትጠሉዋቸውም (ታገሱ)፡፡ አንዳችን ነገር ብትጠሉ አላህም በእርሱ ብዙ ደግ ነገርን ሊያደርግ ይቻላልና፡፡
إظهار الكل...
إِنَّمَا التَّوْبَةُ عَلَى اللَّهِ لِلَّذِينَ يَعْمَلُونَ السُّوءَ بِجَهَالَةٍ ثُمَّ يَتُوبُونَ مِن قَرِيبٍ فَأُولَـٰئِكَ يَتُوبُ اللَّهُ عَلَيْهِمْ ۗ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 17) ጸጸትን መቀበል በአላህ ላይ የሚገባው ለእነዚያ ኀጢአትን በስህተት ለሚሠሩና ከዚያም ከቅርብ ጊዜ ለሚጸጸቱት ብቻ ነው፡፡ እነዚያንም አላህ በእነርሱ ላይ ጸጸትን ይቀበላል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡
إظهار الكل...
إِنَّ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ أَمْوَالَ الْيَتَامَىٰ ظُلْمًا إِنَّمَا يَأْكُلُونَ فِي بُطُونِهِمْ نَارًا ۖ وَسَيَصْلَوْنَ سَعِيرًا (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 10) እነዚያ የየቲሞችን ገንዘብ በመበደል የሚበሉ በሆዶቻቸው ውስጥ የሚበሉት እሳትን ብቻ ነው፡፡ እሳትንም በእርግጥ ይገባሉ፡፡
إظهار الكل...
كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۖ فَمَن زُحْزِحَ عَنِ النَّارِ وَأُدْخِلَ الْجَنَّةَ فَقَدْ فَازَ ۗ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُورِ (ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 185) ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሣኤ ቀን ብቻ ነው፡፡ ከእሳትም የተራቀና ገነትን የተገባ ሰው በእርግጥ ምኞቱን አገኘ፡፡ ቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ መሳሪያ እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡
إظهار الكل...
وَلَا يَحْسَبَنَّ الَّذِينَ يَبْخَلُونَ بِمَا آتَاهُمُ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ هُوَ خَيْرًا لَّهُم ۖ بَلْ هُوَ شَرٌّ لَّهُمْ ۖ سَيُطَوَّقُونَ مَا بَخِلُوا بِهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۗ وَلِلَّهِ مِيرَاثُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۗ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ (ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 180) እነዚያም አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ገንዘብ የሚነፍጉ እርሱ ለእነሱ ደግ አይምሰላቸው፡፡ ይልቁንም፤ እርሱ ለነሱ መጥፎ ነው፡፡ ያንን በርሱ የነፈጉበትን በትንሣኤ ቀን (እባብ ኾኖ) ይጠለቃሉ፡፡ የሰማያትና የምድርም ውርስ ለአላህ ብቻ ነው፡፡ አላህም በሚሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.