cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

❖በድሬዳዋ የሳባ ደ/ኃ/ቅ/ገብርኤል ካቴደራል ፍሬ አምደ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት ተማሪዎች ጉባኤ❖

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርሰቲያን ዶግማ ቀኖና ትውፊትን የጠበቀ ትምህርቶችና መዝሙሮች ወደእናንተ እናደርሳለን ☞✞ ❖ ❖ ✞☜ በድሬዳዋ የሳባ ደ/ኃ/ቅ/ገብርኤል ሰ/ት/ቤት ተማሪዎች ጉባኤ ☞✞ ❖ ❖ ✞☜ ለሀሳብ ☞ ❖ @Baalperazime

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
466
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+87 أيام
+730 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

እግዚአብሔር ይመስገን /2/ ኧኸ ለዚህ ያደረሰን /2/ እግዚአብሔር ይመስገን አዝ የጠላትን ወጥመድ ሰብሮ በህይወታችን ጌታ ከብሮ ሳይበላሽ ትናንታችን በእግዚአብሔር ዛሬን አየን አዝ በዝናቡ ያበቅልና በፀሀዩ ያበስልና አለበሰን በረከት መቆም ሆነ ለስጋችን አዝ አይነገር የእርሱ ስራ እናመስግን በእንዚራ በገናውም ይደርደር ለወደደን ለእግዚአብሔር አዝ ከፈላ ውሀ ከእሳቱ የታደገን በምህረቱ ያማልዳል እኛን ከአምላክ ቅዱስ ገብርኤል ድንቁ መልአክ
إظهار الكل...
አብርሃም ሶሪያዊም ያዘዘቺው እመቤታችን መኾንዋን ነገረው። ያ ሰው ስምዖን ጫማ ሰፊው ይባላል። አንዲት ሴት እየደጋገመች መጥታ፡ “ይህንን ዓይንህን እወድደዋለሁ" ብትለው ጫማ በሚሰፋበት ጉጠት አውጥቶ የሰጣት እርሱ ነው።“አባቴ ሆይ! እንኪያስ እኔንም እንዳትገልጠኝ እለምንሃለሁ። እኔ የዚህን ዓለም ክብር መሸከም አልችልምና። ነገር ግን የምልህን አድርግ። አንተም ንጉሡ ይነግልኝ በሚልህ ተራራ ትይዩ ከካህናቶችህና ከሕዝብህ ጋር ገብተህ ቁም። ወንጌሎችን መስቀሎችን ማዕጠንቶችን፡ የሰም መብራቶችን ያዙ። ንጉሡም ከነሠራዊቱ በአንዲት ዳርቻ ይቁም። እኔም ማንም እንዳያውቀኝ ከሕዝቡ ተደባልቁ በፊትህ እቆማለሁ። አርባ አንድ ጊዜ ኪርያላይሶን እያላችሁ በመጮኸ ወደ እግዚአብሔር ማልዱ። ይኸውም አቤቱ ክርስቶስ ማረን ራራልን ይቅር በለን ማለት ነው። ከዚህም በኋላ ዝም እንዲለ ሕዝቡን እዘዝ። እኔም ያን ጊዜ ስሰግድ አንተ ስገድ። እንዲህም ሦስት ጊዜ አድርግ። ከዚያም በዚያ ተራራ እንጻር ማኅየዊ በኾነ በመስቀል ምልክት በየስግደትህ ስታማትብ ተራራው ይነሣል” አለው። አብርሃም ሶሪያዊም ወደ ከሊፋው ሔዶ ተራራውን እንደሚያነሡት ነገረው። ኅዳር ዓሥራ አምስት ቀን 975 ዓ.እ. ላይ ሙስሊሞች፣ ክርስቲያኖች፡ አይሁድ ሌሎችም ተሰበሰቡ። በአራቱም አቅጣጫ ጸሎተ ዕጣን ተደርሶ ኪርያላይሶን ተባለ። ከዚያም ሕዝቡ ኹሉ ጸጥ አሉ። ሊቀ ጳጳሳቱም ሦስት ጊዜ ሰገደ፤ ሲነሣም ወደዚያ ተራራ አማተበ። ያን ጊዜ ኃይለኛ ድምፅ ተሰማና ተራራው ካለበት ተነሣ። ፈቀቅም አለ። እንደ ገና ከሕዝቡ ጋር ሰገዱ፤ አሁንም ተነሥቶ ፈቀቅ አለ። ለሦስተኛ ጊዜ ሰገዱ፤ ተነሥቶ ወደ ምሥራቅ ሔደ። በዚህ ጊዜ ከሊፋው በከፍተኛ ድምፅ ጮኸ። “በቃ፤ በቃ፤ በዚህ ከቀጠለ ከተማዋ ትፈርሳለች'' አለ። ክርስቲያኖች በደስታ አምላካቸውን አመሰገኑ። አባ አብርሃምንም ፈሩት። ከሳሾቻቸው አፈሩ። ስምዖን ጫማ ሰፊው ግን ተሰውሮ ጠፋ። አባ ኣብርሃም በብርቱ ቢፈልገውም ከዚያ በኋላ ሊያገኘው አልቻለም። ይህንን የእመቤታችንን ተአምር ለማስታወስም ከነቢያት ፆም ጋር ተያይዞ እንዲፆም አዘዘ። በገና ፆም የመጀመሪያዎቹ ሦስት ቀናት ይህንን ተአምር ለማስታወስ የምንፆማቸው ናቸው። ዛሬ ይህ ተራራ ከሦስት ቦታ ተከፍሎ ይታያል። በአሮጌዋ ካይሮም ይገኛል። ተፈልፍሎም የስምዖን ጫማ ሰፊው ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶበታል። ዓፅሙም በዚሁ ቤተ ክርስቲያን በክብር ዐርፏል።
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
.........በአንዲት ቀንም የጭፍራ አለቃው ያዕቆብ ወደ ከሊፋው በማምጣት፡ • “በክርስቲያኖች መጽሐፍ እንዲህ የሚል አለና ይህንን ፓትሪያሪኩ ያሳየን አለው። ከሊፋውም ፓትሪያሪኩን ጠርቶ “ስለዚህ ነገር ምን ትላላችሁ?" ብሎ ጠየቀው። አብርሃም ሶሪያዊም “እውነት ነው፤ የከበረ ወንጌል ይላል” አለው። ስለዚህም የክርስቲያኖች ሃይማኖት እውነት ይኹን ሐሰት ለመፈተኛ ይህ ጥሩ አጋጣሚ እንደ ኾነ አሰበና ለአባ አብርሃም አራት አማራጮችን አቀረበለት- የሙካተምን ተራራ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ማዛወር፣ ወይም እስልምናን ተቀብሎ ክርስትናን መተው፣ ወይም ግብፅን ትቶ ወደ ሌላ አገር መሔድ፣ ወይም በሰይፍ መሞት! ፓትሪያሪኩም ይህን በሰማ ጊዜ ደነገጠ። እጅግም ፈራ። ውሳኔውን ለማሳወቅ የሦስት ቀን ጊዜ እንዲታገሠውም ጠየቀ። በመኾኑም ከከሊፋው ፊት ወጥቶ በአቅራቢያው የሚገኙትን ጳጳሳቱን፣ መነኰሳቱን፣ ካህናቱን፣ ዲያቆናቱንና ምእመናኑን ሰበሰበ። ያጋጠመውን ነገር ኹሉ ነግሮም በግብፅ ውስጥ በመዓልቃ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በእነዚህ ሦስት ቀኖች እየፆሙና እየጸለዩ እግዚአብሔርን ሲማልዱ ቆዩ። በሦስተኛው ቀን በሌሊት እመቤታችን ለአብርሃም ሶሪያዊ ተገለጠችለትና፡- “ይህንን ነገር የሚያደርግልህ አንድ ሰው አለ። ወደ ከተማው ገበያ ስትወጣ እንድ ዓይና የኾነ በገንቦ ውኃ የተሸከመ ሰው ታገኛለህ። እርሱ ይህን ተአምር ያደርግልሃል አለቺው። አብርሃም ሶሪያዊም ከመንበረ ጵጵስናው ፈጥኖ ወጥቶ ወደ ከተማው ገበያ መንገድ ጀመረ። በመካከሉም አንድ ገንቦ ውኃ የያዘ ሰው አገኘ። ያም ሰው አንድ ዓይና ነበረ። ጠራውና ወደ ግቢው አስገባው። የኾነውንም ኹሉ ነገረው። ያ ሰው ግን፡- “አባቴ ሆይ! እኔ ኃጥእ በደለኛ ነኝና ይቅርታ አድርግልኝ፡ ይህን የምትለኝን ላደርገው የማልችል ነኝ" አለው።
إظهار الكل...
.........በአንዲት ቀንም የጭፍራ አለቃው ያዕቆብ ወደ ከሊፋው በማምጣት፡ • “በክርስቲያኖች መጽሐፍ እንዲህ የሚል አለና ይህንን ፓትሪያሪኩ ያሳየን አለው። ከሊፋውም ፓትሪያሪኩን ጠርቶ “ስለዚህ ነገር ምን ትላላችሁ?" ብሎ ጠየቀው። አብርሃም ሶሪያዊም “እውነት ነው፤ የከበረ ወንጌል ይላል” አለው። ስለዚህም የክርስቲያኖች ሃይማኖት እውነት ይኹን ሐሰት ለመፈተኛ ይህ ጥሩ አጋጣሚ እንደ ኾነ አሰበና ለአባ አብርሃም አራት አማራጮችን አቀረበለት- የሙካተምን ተራራ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ማዛወር፣ ወይም እስልምናን ተቀብሎ ክርስትናን መተው፣ ወይም ግብፅን ትቶ ወደ ሌላ አገር መሔድ፣ ወይም በሰይፍ መሞት! ፓትሪያሪኩም ይህን በሰማ ጊዜ ደነገጠ። እጅግም ፈራ። ውሳኔውን ለማሳወቅ የሦስት ቀን ጊዜ እንዲታገሠውም ጠየቀ። በመኾኑም ከከሊፋው ፊት ወጥቶ በአቅራቢያው የሚገኙትን ጳጳሳቱን፣ መነኰሳቱን፣ ካህናቱን፣ ዲያቆናቱንና ምእመናኑን ሰበሰበ። ያጋጠመውን ነገር ኹሉ ነግሮም በግብፅ ውስጥ በመዓልቃ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በእነዚህ ሦስት ቀኖች እየፆሙና እየጸለዩ እግዚአብሔርን ሲማልዱ ቆዩ። በሦስተኛው ቀን በሌሊት እመቤታችን ለአብርሃም ሶሪያዊ ተገለጠችለትና፡- “ይህንን ነገር የሚያደርግልህ አንድ ሰው አለ። ወደ ከተማው ገበያ ስትወጣ እንድ ዓይና የኾነ በገንቦ ውኃ የተሸከመ ሰው ታገኛለህ። እርሱ ይህን ተአምር ያደርግልሃል አለቺው። አብርሃም ሶሪያዊም ከመንበረ ጵጵስናው ፈጥኖ ወጥቶ ወደ ከተማው ገበያ መንገድ ጀመረ። በመካከሉም አንድ ገንቦ ውኃ የያዘ ሰው አገኘ። ያም ሰው አንድ ዓይና ነበረ። ጠራውና ወደ ግቢው አስገባው። የኾነውንም ኹሉ ነገረው። ያ ሰው ግን፡- “አባቴ ሆይ! እኔ ኃጥእ በደለኛ ነኝና ይቅርታ አድርግልኝ፡ ይህን የምትለኝን ላደርገው የማልችል ነኝ" አለው። አብርሃም ሶሪያዊም ያዘዘቺው እመቤታችን መኾንዋን ነገረው። ያ ሰው ስምዖን ጫማ ሰፊው ይባላል። አንዲት ሴት እየደጋገመች መጥታ፡ “ይህንን ዓይንህን እወድደዋለሁ" ብትለው ጫማ በሚሰፋበት ጉጠት አውጥቶ የሰጣት እርሱ ነው።“አባቴ ሆይ! እንኪያስ እኔንም እንዳትገልጠኝ እለምንሃለሁ። እኔ የዚህን ዓለም ክብር መሸከም አልችልምና። ነገር ግን የምልህን አድርግ። አንተም ንጉሡ ይነግልኝ በሚልህ ተራራ ትይዩ ከካህናቶችህና ከሕዝብህ ጋር ገብተህ ቁም። ወንጌሎችን መስቀሎችን ማዕጠንቶችን፡ የሰም መብራቶችን ያዙ። ንጉሡም ከነሠራዊቱ በአንዲት ዳርቻ ይቁም። እኔም ማንም እንዳያውቀኝ ከሕዝቡ ተደባልቁ በፊትህ እቆማለሁ። አርባ አንድ ጊዜ ኪርያላይሶን እያላችሁ በመጮኸ ወደ እግዚአብሔር ማልዱ። ይኸውም አቤቱ ክርስቶስ ማረን ራራልን ይቅር በለን ማለት ነው። ከዚህም በኋላ ዝም እንዲለ ሕዝቡን እዘዝ። እኔም ያን ጊዜ ስሰግድ አንተ ስገድ። እንዲህም ሦስት ጊዜ አድርግ። ከዚያም በዚያ ተራራ እንጻር ማኅየዊ በኾነ በመስቀል ምልክት በየስግደትህ ስታማትብ ተራራው ይነሣል” አለው። አብርሃም ሶሪያዊም ወደ ከሊፋው ሔዶ ተራራውን እንደሚያነሡት ነገረው። ኅዳር ዓሥራ አምስት ቀን 975 ዓ.እ. ላይ ሙስሊሞች፣ ክርስቲያኖች፡ አይሁድ ሌሎችም ተሰበሰቡ። በአራቱም አቅጣጫ ጸሎተ ዕጣን ተደርሶ ኪርያላይሶን ተባለ። ከዚያም ሕዝቡ ኹሉ ጸጥ አሉ። ሊቀ ጳጳሳቱም ሦስት ጊዜ ሰገደ፤ ሲነሣም ወደዚያ ተራራ አማተበ። ያን ጊዜ ኃይለኛ ድምፅ ተሰማና ተራራው ካለበት ተነሣ። ፈቀቅም አለ። እንደ ገና ከሕዝቡ ጋር ሰገዱ፤ አሁንም ተነሥቶ ፈቀቅ አለ። ለሦስተኛ ጊዜ ሰገዱ፤ ተነሥቶ ወደ ምሥራቅ ሔደ። በዚህ ጊዜ ከሊፋው በከፍተኛ ድምፅ ጮኸ። “በቃ፤ በቃ፤ በዚህ ከቀጠለ ከተማዋ ትፈርሳለች'' አለ። ክርስቲያኖች በደስታ አምላካቸውን አመሰገኑ። አባ አብርሃምንም ፈሩት። ከሳሾቻቸው አፈሩ። ስምዖን ጫማ ሰፊው ግን ተሰውሮ ጠፋ። አባ ኣብርሃም በብርቱ ቢፈልገውም ከዚያ በኋላ ሊያገኘው አልቻለም። ይህንን የእመቤታችንን ተአምር ለማስታወስም ከነቢያት ፆም ጋር ተያይዞ እንዲፆም አዘዘ። በገና ፆም የመጀመሪያዎቹ ሦስት ቀናት ይህንን ተአምር ለማስታወስ የምንፆማቸው ናቸው። ዛሬ ይህ ተራራ ከሦስት ቦታ ተከፍሎ ይታያል። በአሮጌዋ ካይሮም ይገኛል። ተፈልፍሎም የስምዖን ጫማ ሰፊው ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶበታል። ዓፅሙም በዚሁ ቤተ ክርስቲያን በክብር ዐርፏል። ©ትንሿ ቤተ ክርስቲያን
إظهار الكل...
የተከበራችሁ ወጣት መዘምራን ከሰኞ እሰከ አርብ ወረብ እንደተጀመረና ይታወቃል ስለሆነም ለአገልግሎት ወረብ ማጥናት መስፈርት መሆኑን አውቃችሁ መጥታችሁ እንድታጠኑ በጥብቅ እናሳስባለን:: ከዚህ ውጭ በአስገዳጅ ምክንያቶች የምትቀሩ ለመዝሙር ክፍሉ አሳውቁ።
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የተከበራችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች የእህታችን ወለተ ሚካኤል የ40 ቀን መታሰቢያ በዕለተ እሁድ በሰንበት ትምህርት ቤታችን እንደሚደረግ ይታወቃል ስለሆነም የመርሀ ግብር ሰአት ለውጥ ስለተደረገ በዚህ መሠረት ለሁሉም እድታደርሱ ስንል በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ::
إظهار الكل...
✞ አብሰራ ገብርኤል አብሰራ ገብርኤል ለማርያም ወይቤላ (2) ትወልዲ ወልድ ሚካኤል መላዕክ በክነፍ ፆራ መንጦላዕት ደመና ሰወራ ንፅህት በድንግልና አልባቲ ሙስና  ተወልደ ወልድ እምኔሐ          ትርጉም ገብርኤል ማርያም አበሰራት አበሰራት ወንድ ልጅም ትወልጃለሺ አላት ሚካኤል መላዕክ  በክንፋ ከለላት የሰማይ መጋረጃውን ሸፈናት ንፅህት ናትና በድንግልና (2) ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና አዝ__ አዳም በጥፋቱ ከገነት ሲባረር በሚካኤል ክንፎች ቀድሞ አይቶሽ ነበር ሔዋንን ሲጠራት ሕይወቴ ነሽ አላት እንደሚድን አውቆ ድንግል በአንች ምክንያት ንፅህት ናትና በድንግልና (2) ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና   አዝ__ እግዚአብሔር  የላከው የከበረው መላዕክ ድንግል ሆይ ለክብርሽ ዐየን ሲንበረከክ በፍቅር በትህትና በፍፁም ሰላምታ የጌታ ሰው መሆን የነገረሽ በደስታ ንፅህት ናትና በድንግልና (2) ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና አዝ__ ደስተኛዬቷ ሆይ ደስ ይበልሽ ድንግል የአብ ቃል ክርስቶስ ሥጋሽን ይለብሳል አንቺም ትይዋለሽ ስሙን ኢየሱስ መድኋኒት ነውና ለሥጋ ወነፍስ ንፅህት ናትና በድንግልና (2) ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና አዝ__ አንደ ኒቆዲሞስ ሳትከራከሪ አንደ ዘኬርያስ ሳትጠራጠሪ ይሁነኒ ብለሽ ቃልን ተቀበልሽ ከፍጥረት ማነው አንቺ የሚመስልሽ ንፅህት ናትና በድንግልና (2) ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና @webzema
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.