cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

🗞 ጣሀ አህመድ – Taha Ahmed 🗞

ይህ የተለያዩ ኢስላማዊ ትምህርቶች እና መልእክቶች የሚተላለፉበት መድረክ ነው። (ወደ መልካም አመላካች እንደ ተግባሪው ምንዳ አለው) በሚለው ነብያዊ ፈለግ መሰረት እርሶም ወደ ኸይር በማመላከትና እርሱን ለሌሎች በማስተላለፍ ስራ የበኩሎን አስተዎፅኦ እንዲያበረክቱ ተጋብዘዎል። (إن أريد إلا الإصلاح ما استطعت وما توفيقي إلا بالله عليه توكلت وإليه أنيب)

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 429
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
+2230 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
አላህን ማመስገን የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:– "አላህ ባሪያው ጥቂት ምግብን በልቶ እንዲያመሰግነው እንዲሁም ጥቂትን ጠጥቶም እንዲያመሰግነው ይወዳል።" (ሙስሊም ዘግበውታል) ኢማሙ አንነወዊ አላህ ይዘንላቸው ይህን ሐዲስ ሲያብራሩ "ጥቂት ምግብ" በሚለው ቃል ለማለት የተፈለገው እንደ ቁርስ ወይም እራት ያለውን አንድ የምግብ ወቅት መብል እንደሆነ ገልፀው፤ ሀዲሱ ከመብላት እና መጠጣት በኃላ አላህን ማመስገን እንደሚወደድ ያስረዳል ብለዋል። የምስጋናው አባባልም በቡኻሪ እንደተዘገበው "አልሀምዱ ሊላህ ከሲረን ጠይበን ሙባረከን ፊሂ ገይረ መክፊዬ ወላ ሙወዲዒ ወላ ሙስተግኒ ረበና" ቢሆን የተሻለ እንደሆነ ገልፀዋል። ነገር ግን "አልሀምዱ ሊላህ" ካለም በቂ እንደሚሆን አብራርተዋል። ✍️ *ጣሀ አህመድ* 🌐 https://t.me/tahaahmed9
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
መብላት፣ መጠጣት እና መልበስ እሰከ የት ድረስ ሊሆን ይገባል? የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:– " ብሉ፣ ጠጡ፣ ምፅዋትን ስጡ እንዲሁም ልበሱ ይህን ድርጊታችሁን ድንበር ማለፍ ወይም ኩራት እሰካልተቀላቀለው ድረስ።" (ሀዲሱን ነሳኢ ዘግበውታል አልባኒም ሀሰን ብለውታል) ኩራት (መኺላ):– የሚለው ቃል ትርጉም በዚህ አገባቡ ልታይ ማለትን እና በራስ ድርጊትም ይሁን ማንነት መገረምን ያካትታል። ✍️ ጣሀ አህመድ 🌐 https://t.me/tahaahmed9
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
መብላት፣ መጠጣት እና መልበስ እሰከ የት ድረስ ሊሆን ይገባል? የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:– " ብሉ፣ ጠጡ፣ ምፅዋትን ስጡ እንዲሁም ልበሱ ይህን ድርጊታችሁን ድንበር ማለፍ ወይም ኩራት እሰካልተቀላቀለው ድረስ።" (ሀዲሱን ነሳኢ ዘግበውታል አልባኒም ሀሰን ብለውታል) ኩራት (መኺላ):– የሚለው ቃል ትርጉም በዚህ አገባቡ ልታይ ማለትን እና በራስ ድርጊትም ይሁን ማንነት መገረምን ያካትታል። ✍️ ጣሀ አህመድ (ዙል–ሒጃ 1441 የተፃፈ) 🌐 https://t.me/tahaahmed9
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ከዙል–ሒጃ ወር 11ኛው፣ 12ኛው እና 13ኛው ቀናት የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:– "አያሙ አት‐ተሽሪቅ (ከዙል‐ሒጃ ወር 11ኛው፣ 12ኛው እና 13ኛው ቀናት) የመብላት፣ የመጠጣት እና አላህን የማውሳት ቀናት ናቸው።" (ሙስሊም ዘግበውታል) መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በዚህ ሐዲስ በነዚህ ቀናት የምንፈፅማቸውን ዋነኛ ነገሮች ጠቁመውናል። ትኩረት ልናድረግበት እና ልንተዋወስበት የሚገባው ትልቁ ነገር አላህን ማውሳት (ዚክር ማድረግ) እንዲሁም እርሱ በእኛ ላይ የዋለውን ውለታ በማስታወስ ማመስገን ነው። ይህን የሚታደሉ ጥቂቶች ናቸው። አላህ እርሱን ለማስታውስ፣ ለማመስገን እና አሳምሮ ለማመለክ ይርዳን! ✍️ ጣሀ አህመድ 🌐 https://t.me/tahaahmed9
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የእኛ የሙስሊሞች ዒዶች… የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: - "የዓረፋ እና የእርዱ  እለት እንዲሁም የተሽሪቅ (ከዙል‐ሒጃ ወር 11ኛው፣ 12ኛው እና 13ኛው) ቀናት የእኛ የሙስሊሞች ዒዶች ናቸው፤ እነሱም የመብላት እና የመጠጣት ቀናት ናቸው።" ( አቡዳውድ ዘግበውታል አልባኒም ሰሂህ ብለውታል) በዚህ ሐዲስ ውስጥ እነዚህ አምስት ቀናት ማለትም  ከዙል‐ሒጃ ወር 9ኛ፣ 10ኛው፣ 11ኛው፣ 12ኛው እና 13ኛው ቀናት ለሙስሊሞች ከሐጅ ስርአት ጋር ተያይዞ አላህ ለዚህ ቀጥተኛ እምነት ስለመራቸው በልዩ ሁኔታ እንዲደሰቱባቸው፣ የተለያዩ አላህና መልእክተኛው የደነገጓቸውን የአምልኮ አይነቶች በመፈፀም አላህን ሊገዙባቸው፣ እርሱን ሊያመሰግኑባቸው እና ሊያልቁባቸው የተለዩ የዒድ ቀናት መሆናቸውን እንረዳለን። ስለሆነም ዘጠነኛውን ቀን ሐጅ ላይ ላልሆነ ሰው መፆሙ ሲበረታታ፤ አስረኛውን ቀን መፆም ለሁሉም የተከለከለ ይሆናል። ከዚያ በኃላ ያሉትን የተሽሪቅ ቀናት ሐጅ ላይ ላልሆነ ሰው መጾሙ የማይፈቀድ መሆኑን ዑለማዎች ገልፀዋል። አላህን እርሱ በሚፈልገው መልኩ በመልእክተኛው መንገድ ከሚገዙት ያድርገን! ✍ ጣሀ አህመድ 🌐 https://t.me/tahaahmed9
إظهار الكل...
🔠🔠🔠 NesihaTv Live 2.0 App √ ተሻሽሎ በ 25 Mb ብቻ በቀረበው የሞባይል አፕ የነሲሓ ቲቪን ስርጭት ይከታተሉ ⬇️ ከቴሌግራም ለመጫን https://t.me/nesihatv/1013 ነሲሓ ቲቪ... ኢስላማዊ ዕውቀት ለሁሉም! @nesihatv
إظهار الكل...
NesihaTv live V 2.0 (9).apk24.80 MB
የዒድ አከባበር ደንቦች ክፍል 3 ከዒድ ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ ስህተቶችን በተመለከተ ከክፍል ሁለት የቀጠለ። 4⃣ኛ. ባዕድ በሆኑ ወንዶችና ሴቶች መካከል መቀላቀል፤ አልፎም መጨባበጥና መሳሳም፡፡ ይህ ሸሪዓው ክፉኛ የኮነነው ተግባር ነው፤ የአላህ መልእክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) ከእለታት አንድ ቀን ከመስጂድ በመውጣት ላይ ሳሉ ወንዶች ከሴቶች ጋር በመንገድ ላይ ተቀላቅለው ተመለከቱ ይህንን ክስተት በማስመልከትም "ከወንዶች ወደ ኋላ ሁኑ፤ የመንገዱንም መሀከል ይዛችሁ ልትጓዙ አይገባም" አሉ፡፡ ይህንን ሀዲስ የዘገበው ሰሃቢይ "ከዚህ በኋላ ሴቶች በጣም ወደ ዳር ከመውጣታቸው ልብሳቸው በአጥር ይያዝ ነበር፡፡" በማለት ይናገራል፡፡(አቡዳውድ ሱነናቸው ላይ ሲዘግቡት አልባኒ ሀሰን የሚል ደረጃ ሰጥተውታል) ይህ ሀዲስ ሸሪዓ በጥቅሉ ወደ ሀራም የሚያደርሱ ነገሮችን የከለከለ መሆኑን ከሚያሳዩ መረጃዎች አንዱ ነው፡፡ በሌላ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ (ሰላትና ሰለም በርሳቸው ላይ ይሁን) "እኔ ሴቶችን አልጨብጥም" ማለታቸው ሰፍሯል፡፡ ሀዲሱ አንድ ሰው ምንም እንኳ የተቀደሰ አላማና ንፁህ ልቦና ነው የያዝኩት ቢልም ባዕድ ሴቶችን ከመጨበጥ ሊቆጠብ እንደሚገባ የሚያመለክት ነው፡፡ 5⃣ኛ. እንደ ሙዚቃ እና መሰል የተከለከሉ ነገሮችን ከማድመጥ፣ ፊልሞችን በመመልከት ጊዜን ከማጥፋት መቆጠብ ያስፈልጋል:: እንዲሁም ሌሎችንም ሀራም የሆኑ ተግባራትን በሙሉ መጠንቀቅ ይገባል:: 6⃣ኛ. በዒድም ይሁን በሌላ ጊዜ በኢስላም ማባከን እጅጉን የተኮነነ ተግባር ቢሆንም በዒድ እለት በአንዳንዶች ዘንድ ከሚታዩት ስህተቶች መካከል ምግብና መጠጥን ማባከን ነውና ልንርቀው ይገባል:: ኢስላም በራሱ የተሟላ ነው! እንደሚታወቀው ሀይማኖታችን ኢስላም ምሉዕ ነው፡፡ ስለሆነም ለሁሉም የአምልኮ ዘርፎች እንዲሁም የህይወት መስኮች ደንቦችን ደንግጓል ስርዐቶችንም አስቀምጧል፡፡ ሕግጋቶቹ ፍትሀዊ እና ሚዛናዊ ስርዐቶቹም ለሁሉም ቦታ እና ዘመን የሚበጁ ናቸው፡፡ አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) እንዲህ ይላል:- {الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا} المائدة 3 ‹‹ዛሬ ሐይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ፤ ፀጋዬንም በእናንተ ላይ ፈፀምኩ፤ ከሀይማኖት በኩልም ለእናንተም ኢስላምን ወደደኩ...›› (አልማኢዳ፡ 3) ከዚህም በመነሳት መጨመርንም ይሁን መቀነስን አይቀበልም እንዲሁም ከሌሎች መኮረጅንም ሆነ መመሳሰልን ይከለክላል፡፡ ይህንን እዉነታ የአላህ መልእክተኛ (የአላህ ሰላምና ሰላት በርሳቸው ላይ ይሁን) በነዚህ ሁለት ነብያዊ አስተምህሮቶች ይገልፁታል፡፡ قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : ( من أحدث في أمرنا هذا ما ليس منه فهو رد ) رواه البخاري (2697) ومسلم (1718) "በዚህ በዲናችን ላይ ከርሱ ያልሆንን ያመጣ (ሰው) ስራው ተመላሽ ነው፡፡ (ተቀባይነት አይኖረውም)" (ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል) قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : ( مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ ) رواه أبو داود (4031) "ከህዝቦች የተመሳሰለ እረሱ ከነርሱ ነው፡፡" (አቡ ዳውድ ዘግበውታል) ስለሆነም ዒዳችንን ስናከብርም ይሁን ማንኛውንም አይነት ዒባዳ ስንፈጽም ከጭማሪ (ቢደዓ) እራሳችንን ልናርቅ እንዲሁም በማነኛውም የህይወታችን ክፍሎች ከሌሎች ጋር መመሳሰልን ትተን ሙሉ የሆነውን ሸሪዓን በማወቅ ወደ ተግባር ልንለውጥ ይገባል:: تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال. አላህ መልካም ስራችንን ይቀበለን!! ✍ *ጣሀ አህመድ (1431ሂ) የተፃፈ* 🌐 https://t.me/tahaahmed9
إظهار الكل...
🗞 ጣሀ አህመድ – Taha Ahmed 🗞

ይህ የተለያዩ ኢስላማዊ ትምህርቶች እና መልእክቶች የሚተላለፉበት መድረክ ነው። (ወደ መልካም አመላካች እንደ ተግባሪው ምንዳ አለው) በሚለው ነብያዊ ፈለግ መሰረት እርሶም ወደ ኸይር በማመላከትና እርሱን ለሌሎች በማስተላለፍ ስራ የበኩሎን አስተዎፅኦ እንዲያበረክቱ ተጋብዘዎል። (إن أريد إلا الإصلاح ما استطعت وما توفيقي إلا بالله عليه توكلت وإليه أنيب)

የዒድ አከባበር ደንቦች ክፍል 2 የተክቢራ አፈፃፀም 1⃣ ከመልክተኛው ትክክለኛ ሰነድን መሰረት ያደረገ እና የተክቢራን አባባል ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፅ መረጃ ባይገኝም ከሰሀቦቻቸው ግን "አላሁ አክበር አላሁ አክበር ወሊላሂልሀምድ" እና የመሳሰሉት አባባሎች በትክክለኛ ሰነድ ተዘግበዋል፡፡ ስለሆነም ሙስሊሞች እነዚህን አባባሎች የትኞቹ እንደሆኑ ማጥናትና እነርሱን ማዘውተር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ኢብኑ ሀጀር አል-ዓስቀላኒ ፈትሁል-ባሪ በተሰኘው ኪታባቸው እንዲህ ይላሉ "በዚህ ዘመን (ተክቢራን በተመለከተ) ብዙ መሰረት የሌላቸው ጭማሪዋች ተከስተዋል፡፡" ይህ በሂጅራ አቆጣጠር (ከ773-852) የኖሩት የኢስላም ሊቅ ንግግር ነው። ታዲያ ባለንበት ዘመን ምን ያህል ጭማሪ ተከስቶ ሊሆን እንሚችል ስናስተውል በጉዳዩ ላይ ከባድ ጥንቃቄ ልናደርግ እንደሚገባ ያመላክተናል፡፡ 2⃣ በአንድ ድምፅ ወይም አንድን ሰው አዝማች (አውጪ) ሌላው ተቀባይ ሆኖ የሚደረግ ተክቢራም ሱናን የሚቃረን ተግባር ነው። በዚህ ዙሪያ ተምሳሳይ ድርጊት ከሚፈጽሙት ወገኖች እንደ መረጃ የሚጠቀሰው የዑመር ተግባር (ሚና ላይ በድንኳን ውስጥ ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ተክቢራ ሲያደርግ ሰዎችም ተክቢራውን ሰምተው ተክቢራን ማድረጋቸው) የሚያመለክተው የእሱን ድምፅ ሲሰሙ ተክቢራን ማድረግ እንዳለባቸው በማስታወስ እነርሱም ተክቢራ ያደርጉ እንደነበረ እንጂ ሌላን አይደለም። ስለሆነም ይህ ክስተት፤ በጋራ ድምፅ እርሱን እንደ አዝማች እነርሱ እንደ ተቀባይ ሆነው ይቀጥሉ ነበር የሚለውን እንድምታ አያስጨብጥም ሲሉ ዑለማዎች ይናገራሉ፡፡ ጥቂት ከዒድ ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ ስህተቶች 1⃣ኛ. ዒድ መሆኑ ከታወቀበት ሰአት ጀምሮ ወንዶች ከሰላተል ጀመዓ መቅረት ብሎም በረመዳን ሲሰግዱት የነበረውን ዊትር ሰላት ማቋረጥ፤ አንዳንዴም አምልኮዎች በዚህ ያበቃሉ የተባለ ይመስል እርግፍ አድርጎ መተው ይስተዋላል፡፡ 2⃣ኛ. የዒዱን ዋዜማ ለሊት በተለያዩ ዒባዳዎች ህያው ማድረግን በተመለከተ የመጡት ሀዲሶች ከሰነድ አንፃር ደካማዎች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ለሊቱን በተለያዩ የሚጠቅሙም ይሁን ያማይጠቅሙ ነገሮች ላይ ማሳለፍ፤ በዚህም የተነሳ የፈጅር ሰላትን አለመስገድ እና ሰላተል-ዒድን እንደ ቀላል በመመልከት ችላ ብሎ መተው:: የዒድ ሰላትን በተመለከተ "ሰላተል-ዒድ በእያንዳንዱ ግለሰብ ላይ በነፍስ ወከፍ ግዴታ ነው" የሚለው የአቡ ሀኒፋ አቋም ሲሆን ከኢማሙ አሻፊዒይ እና አህመድም ከተዘገቡት ሁለት የተለያዩ አቋሞች አንዱ የሚጠቁመውም ይህንኑ ነው። ሸይኹል-ኢስላም ኢብኑ-ተይሚያህ እና ሌሎች ብዙ ዑለማዎችም ይህን አቋም የሚደግፉ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ 3⃣ኛ.በአለባበስና መቆነጃጀት ዙሪያ ከሚከሰቱ ስህተቶች መካከል ብዙ ወንዶች ፂማቸውን መላጨትና ማሳጠር እንዲሁም ልብሳቸውን ከቁርጭምጭሚታቸው በታች እነዲወርድ በማድረግ የሚፈፅሙት ስህተት ይገኝበታ። ሴቶች ደግሞ ሽቶን በመቀባት በመገላለጥ የሚፈፅሙት ስህተት እጅግ አደገኛ ነው፡፡ እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ የመጡት ነብያዊ አስተምህሮቶች በጣም አስፈሪና አስደንጋጭ ናቸው፡፡ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنْ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : ( مَا أَسْفَلَ مِنْ الْكَعْبَيْنِ مِنْ الْإِزَارِ فَفِي النَّارِ) رواه البخاري (5787) ከአቡሁረይራ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል:- "ከሽርጥ ከቁርጭምጭሚት የወረደዉ የእሳት ነው" (ቡኻሪና በቁጥር (5787) ዘግበዉታል) ይህ ሁሉንም የልብስ አይነት እንደሚያካትት ለመግለፅ አል-ኢማም አል-ቡኻሪይ ለሀዲሱ "ከቁርጭምጭሚት የወረደው እሱ የእሳት ነው" የሚል ርዕስ ሰጥተውታል። በሌላ ሴቶች ከቤት ሲወጡ ምን አይነት ስነ-ስርአት መከተል እንደሚገባቸው በሚጠቁም ሀዲስ ላይ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል:-"ማንኛዋም ሴት ሽቶን ተቀብታ ወደ መስጂድ የወጣች እንደሆነ እስክትታጠብ ድረስ ሰላቷ ተቀባይነት የለውም፡፡"(ኢብኑ ማጃህ እና አህመድ ዘግበውታል አልባኒም ሰሂህ መሆኑን ገልፀዋል፡፡) عن أبي هريرة قال: قال صلى الله عليه وسلم : "صِنفانِ مِن أهلِ النارِ لم أرَهما..... ونِساءٌ كاسياتٌ عارياتٌ مميلاتٌ مائلاتٌ، رؤوسُهُنَّ كأسنِمَةِ البُخْتِ المائلةِ لا يَدْخُلْنَ الجنةَ ولا يَجِدْنَ رِيحَهَا، وإن رِيحَهَا لَيوجَدُ مِن مَسيرةِ كذا وكذا". رواه مسلم(2128) ሙስሊም አቡ ሁረይራን ዋቢ አድርገው ባስተላለፉት ሀዲስ ላይ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል:- "ከእሳት ሰዎች መካከል ሁለት አይነት ሰዎች በእኔ (ዘመን) አላየኋቸውም (ወደፊት ይመጣሉ)" አሉና፤ የመጀመሪያዎቹ ምን አይነት ባህሪ እንዳላቸው ካብራሩ በኋላ "ሌለኞቹ ሴቶች ናቸው፤ ለብሰው ያልለበሱ አካሄዳቸው እና እንቅስቃሴያቸው ወደርካሽ አላማ ያዘነበለ፤ ሌሎችንም የሚያሳስቱ ፀጉራቸው ልክ እንደ ግመል ሻኛ የተከመረ ናቸው:: እንደነዚህ አይነቶቹ ጀነትን አይገቡም ሽታዋንም አያገኙትም" አሉ:: ክፍል 3 ይቀጥላል.… ✍ *ጣሀ አህመድ (1431ሂ) የተፃፈ* 🌐 https://t.me/tahaahmed9
إظهار الكل...
🗞 ጣሀ አህመድ – Taha Ahmed 🗞

ይህ የተለያዩ ኢስላማዊ ትምህርቶች እና መልእክቶች የሚተላለፉበት መድረክ ነው። (ወደ መልካም አመላካች እንደ ተግባሪው ምንዳ አለው) በሚለው ነብያዊ ፈለግ መሰረት እርሶም ወደ ኸይር በማመላከትና እርሱን ለሌሎች በማስተላለፍ ስራ የበኩሎን አስተዎፅኦ እንዲያበረክቱ ተጋብዘዎል። (إن أريد إلا الإصلاح ما استطعت وما توفيقي إلا بالله عليه توكلت وإليه أنيب)

* የዒድ አከባበር ደንቦች * ክፍል 1 በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው:: ምስጋና ለአለማት ጌታ ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ሰላትና ሰላም በመልእክተኛው ሙሀመድ፤ በቤተሰቦቻቸው እና በባልደረቦቻቸው ላይ ይሁን፡፡ * ዒድ ማለት ምን ማለት ነው? * ኢብኑል-ዓረቢይ ዒድ "ዒድ" ተብሎ ስለመሰየሙ ሲናገሩ በየአመቱ አዲስ ደስታን ይዞ የሚመለስ ከመሆኑ አንፃር መሆኑን እና "ዓደ" (ተመለሰ) ከሚለው ቃል የተወሰደ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ እዚህ ላይ ልብ ልንልን የሚገባው ዒድ ቂያማ እስኪቆም ተመላልሶ የሚመጣ ቢሆንም እኛ ግን የሚቀጥለውን ለመድረስ ምንም ዋስትና እንደሌለን ነው፡፡ ስለሆነም ከአላህ ህግ ፈፅሞ ልንወጣ አይገባም፡፡ አነስ ኢብኑ ማሊክ እንዲህ ይላሉ:- ‹‹የአላህ መልእክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) መዲና ከተማ ሲመጡ የመዲና ሰዎች በመሀይምነት ዘመን (ደስታቸውን የሚገልፁባቸው) የሚጫወቱባቸው ሁለት ክብረ-በዓላት ነበሮቸው። ይህንን ባዩ ጊዜ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፡፡ "አላህ በእነዚህ በሁለቱ ምትክ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ክብረ-በዓላትን ቀየረላችሁ፤ እነሱም "የፊጥር" እና "የአድሀ" በዓላት ናቸው፡፡" (አቡዳውድ እና አህመድ ዘግበውታል) ከዚህ ሀዲስ ዑለማዎች የተረዷቸዉን ሁለት ቁም ነገሮች ልናስተውል ይገባል። አንደኛ፡- ከእስልምና ውጭ ካሉ ማህበረሰቦች ጋር መመሳሰል የተከለከለ መሆኑ:: ሁለተኛ ፡- በኢስላም የተደነገጉ ክብረ-በዓላት ሁለት ብቻ መሆናቸውን ነው:: * ከዒድ ዋዜማ ጀምሮ ልንፈፅማቸው የሚገቡ ነገሮች * ከዚህ በላይ በአጭሩ ዒድ ማለት ምን ማለት እንደሆነና በኢስላም የተደነገጉ ክብረ-በዓላት ዒድ-አልፈጥር እና ዒድ-አልአድሀ ብቻ መሆናቸውን ከተረዳን፤ በእነዚህ ሁለት ዒዶች ዋዜማ እና በእለቱ ምን ማድረግ ይወደዳል? ምንስ ይፈቀዳል? ምን ከማድረግ ልንከለከል ይገባል? ወደ ሚሉት ነጥቦች እንሂድ፡፡ በመጀመሪያ ከዒድ ዋዜማ ጀምሮ ልንፈፅማቸው ከሚያስፈልጉ ነገሮች:- 1⃣በዒደል-ፊጥር ዒድ መሆኑ ከተረጋገጠበት ሰአት አንስቶ ሰላቱ እስኪጀመር በዒደል-አድሀ ደግሞ ከዙል-ሂጃ የዘጠነኛው እለት ፈጅር ሰላት አንስቶ የአስራ ሶስተኛው እለት ፀሀይ እስከትጠልቅ ድረስ ተክቢራን ማድረግ ይገባል፡፡ 2⃣መታጠብ እራስን ማሰማመር እና ከልብሶች መካከል የተሻለውን እና ቆንጆውን መልበስ ከሰለፎች የተዘገበ ተግባር ነው፡፡ 3⃣ሴቶችን በተመለከተ በዚህ እለትም ይሁን በሌላ ጊዜ ከቤታቸው እንዴት መውጣት እንዳባቸው በሸሪዓ የታወቀ ነው፡፡ እናም ከመገላለጥ እና ሽታ ያላቸውን ነገሮች ተጠቅመው ከመውጣት ተቆጥበዉ ከቤታቸው ወደ መስጊድ ወይም ወደ ዒድ መስገጃ ስፍራ ሊሄዱ ይገባል፡፡ የአላህ መልእክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) ለጋብቻ የቀረቡና የደረሱ እንዲሁም በወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶችን ጨምሮ ወደ ዒድ ሰላት መስገጃ ቦታ ስፍራ እንዲወጡ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ እንዲህ የሚል ጥያቄ ተጠይቀው ነበር ‹‹አንዳችን ጅልባብ ባይኖራት ምን ታድርግ?›› እሳቸውም እንዲህ አሉ ‹‹እህቷ (ጓደኛዋ) ታውሳት(ታልብሳት)››(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል) በሌላውም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል ‹‹ሴቶችን መስጊድ ከመሄድ አትከልክሏቸው ነገር ግን ከቤታቸው ሽታ ያለው ነገርን ተጠቅመው እንዳይወጡ፡፡››(አል-ኢማም አህመድና አቡዳውድ ሲዘግቡት አልባኒ ሰሂህ ብለውታል) 4⃣በዒደል-ፊጥር ሰጋጁ ወደ መስገጃው ከመውጣቱ በፊት ዊትር (አንድ፤ ሶስት፤ አምስት …..) ቁጥር ያላቸውን ተምሮች በልቶ ወደ ዒድ መስገጃው መሄድ። 5⃣ለዒድ ሰላት ከመሄድ በፊት ዘካተል-ፊጥርን ለተገቢው ወገን መስጠት። 6⃣የዒድ ሰላትን ለመስገድ ከፍተኛ ፍላጎትና ጉጉት ሊኖር ይገባል። ምክንያቱም ይህ ተግባር ከታላላቅ የኢስላም መገለጫዎች አንዱ ከመሆኑም ባሻገር የአላህ መልእክተኛ (ሰላትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁንና) የዒድ ሰላትን ከተደነገገበት ጊዜ አንስቶ እስከ ሕልፈታቸው ትተውት አያውቁም ነበር። ከዚህ በተጨማሪም በመሰረቱ ሰላትን መስገድ የተከለከሉትን የወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶች ሳይቀር በቦታው ላይ እንዲገኙ አዘዋል፡፡ 7⃣ሰላቱ ከተጠናቀቀ በኋላ በተቻለ አቅም ኹጥባን ማዳመጥ። 8⃣ወደ ዒድ ሰላት ከሄዱበት መንገድ በሌላ መንገድ መመለስ። 9⃣የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት መለዋወጥ፡፡ ይህም ”ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም" የሚል ሲሆን የተለያዩ የኢስላም ሊቃውንት ከሰሃቦች መገኘቱን አረጋግጠዋል። 🔟ከዒደል-ፊጥር ጋር በተያያዘ ዘካተል-ፊጥርን መስጠት መታዘዙ የተለያዩ ችግረኞችን ማስታወስ እና አቅም በፈቀደ መጠን ችግራቸውን ለመቅረፍ ጥረት ማድረግ የሚደገፍ ተግባር መሆኑን የሚያመለክት ነው። 1⃣1⃣በአጠቃላይ ሸሪዓው ያዘዘባቸውን እና የፈቀዳቸውን ተግባራት መፈፀም የሚፈቀድና የሚወደድ ይሆናል። ኢንሻ አላህ ክፍል 2 ይቀጥላል… ✍ *ጣሀ አህመድ (1431ሂ) የተፃፈ* 🌐 https://t.me/tahaahmed9
إظهار الكل...
🗞 ጣሀ አህመድ – Taha Ahmed 🗞

ይህ የተለያዩ ኢስላማዊ ትምህርቶች እና መልእክቶች የሚተላለፉበት መድረክ ነው። (ወደ መልካም አመላካች እንደ ተግባሪው ምንዳ አለው) በሚለው ነብያዊ ፈለግ መሰረት እርሶም ወደ ኸይር በማመላከትና እርሱን ለሌሎች በማስተላለፍ ስራ የበኩሎን አስተዎፅኦ እንዲያበረክቱ ተጋብዘዎል። (إن أريد إلا الإصلاح ما استطعت وما توفيقي إلا بالله عليه توكلت وإليه أنيب)

Photo unavailableShow in Telegram
ለኡዱሂያ ብሎ መበደር እንዴት ይታያል? ኢብኑ ዑሰይሚን አላህ ይዘንላቸው እንዲህ ብለዋል:– "ዒድ አል–አድሓ በሚቀርብበት ግዜ በእጁ ላይ አንዳች ነገር የሌለው ድሃ ነገር ግን ከተወሰነ ግዜ በኃላ የሚያገኘው ገቢ ያለው እንደ ወር ደሞዝተኛ ያለ ከሆነ ሊበደር እና ለኡድሂያ ሊያውለው ከዚያም ሊከፍል ይችላል። ነገር ግን በቅርቡ ሊከፍል እንደሚችል ተስፋ የሌለው ከሆነ ለኡድሂያ ብሎ ብድር ውስጥ መግባቱን አንወድለትም ምክንያቱም መበደሩ የእዳ ተሸካሚ ስለሚያደርገው ነው።" (መጅሙዕ ፈታዋ ኢብኑ ዑሰይሚን ይመልከቱ) ✍️ ጣሀ አህመድ 🌐 https://t.me/tahaahmed9
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.