Bule Hora University EvaSUE Fellowship
الذهاب إلى القناة على Telegram
ይህ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት ቻናል ነው። በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ - ርዕሰ ጉዳዮች ይነሳሉ - መልዕክቶችን እንለዋወጣለን - የጌታን ሀሳብ እንከፋፈላለን ✝️ BuleHora University Christian Fellowship 1000322391742
إظهار المزيد1 531
المشتركون
+124 ساعات
+87 أيام
+930 أيام
أرشيف المشاركات
🔴Now the signal is available to everyone! 🔴
❗️Read the post to the end and follow the instructions carefully.
🤗 I'm sharing something you normally wouldn't have access to—especially not in a free channel.
🫡You supported me in the past, and now it's my turn to give back and help you.
🟠Step 1: Buy ETH on Binance or any other exchange.
🟠 Step 2: Sell ETH on bitnax.io
✅The current price difference for ETH is approximately 9.5%.
✨✨#General_Fellowship ✨✨
"
አንዳንዶች ማድረጉን እንደተዉት መሰብሰባችንን አንተው፤ ይልቁንም ቀኑ እየተቃረበ መምጣቱን ስታዩ እርስ በርሳችን እንበረታታ" (ዕብ 10፥24-25)። ሰላም እንዴት ናችሁ የህብረታችን ቤተሰቦች በሙሉ ሳምንታችሁ እንዴት አለፈ? በእግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት ዛሬ ላይ ደርሰናል 🙏 የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን 🙌 ዛሬ ቅዳሜ ሁላችንም በጉጉት የምንጠብቀው ሳምንታዊው የGeneral Fellowship የሕብረት ጊዜያችንን ዛሬ እናት ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን የምናደርግ ይሆናል። ስለዚህም ሁላችንም በጋራ ህብረት ለማድረግና እግዚአብሔርን በመፈለግ መንፈስ ለማምለክ የምንገናኝ ይሆናል። በዛሬው ፕሮግራማችንም ላይ ፦ 🙏 የፀሎት ጊዜ ይኖረናል 🎹 ጌታን በዝማሬ እናመልካለን 📖 ከእግዚአብሔር ቃልም የምንካፈል ይሆናል። መፅሐፍ ቅዱስ እና ማስታወሻ ደብተር እዳይረሳ😊
+9
“The LORD hath done great things for us; whereof we are glad.” — Psalms 126፥3 ✨The first opening program of our fellowship for 2019 at Assemble Church. 🗓Date: 30/01/2019 EC
+9
“The LORD hath done great things for us; whereof we are glad.” — Psalms 126፥3 ✨The first opening program of our fellowship for 2019 at Assemble Church. 🗓Date: 30/01/2019 EC
+9
“The LORD hath done great things for us; whereof we are glad.” — Psalms 126፥3 ✨The first opening program of our fellowship for 2019 at Assemble Church. 🗓Date: 30/01/2019 EC
✨✨ #General_Fellowship✨
✨✨#Wellcome ✨✨
መዝሙር 34:3 3 ኑና ከእኔ ጋር እግዚአብሔርን አክብሩት፤ ስሙንም በአንድነት ከፍ ከፍ እናድርግ።የጌታ ሰላም እና ፀጋ ይብዛላችሁ ከ3 ወር የካፌ ምግብ እረፍት የተመለሳችሁ የተወደዳችሁ እህቶችና ወንድሞች እንዴት ናችሁ? ከረጅም ዕረፍት በኋላ (እድሜ ለቴክኖሎጂ በonline fellowship መገናኘታችን ናፍቆቱን ቀነሰልን እንጂ ባይሆንማ… እንጃ 🤷♀️🤷♂️) የመጀመሪያውን ፌሎሺፓችን ቅዳሜ መስከረም 30 እንጀምራለን። እኛ እናንተን ለማየት በጣም ጓጉተናል፤ እናንተም እንደኛው እርስ በእርስ ለመገናኘት እንደጓጓችሁ እርግጠኞች ነን። 😊 መቼም በአዲሱ ዓመት ካወጣናቸው ዕቅዶች መካከል አንዱ በሰዓት መገኘት እንደሚሆን እርግጠኞች ነን፤ እናናናና 😄 ቅዳሜ ያንን በተግባር ላይ እናውለው 💪 (planning needs action right? መቼም ይሄ ለናንተ አይነገርም )። 📌በእለቱ፡የፀሎት🙏 የአምልኮ🎤🎹 እና የቃል📖 ጊዜ ይኖረናል። ስለዚህ ቅዳሜ 11፡30 ⏰ በአሰምብል ቤተክርስቲያን⛪️ ተገናኝተን አብረን አምላካችንን እግዚያብሄርን 🙏 እናመልካለን፣ እናመሰግነዋለን። 🤍 ማስታውሻ ደብተራችሁንና መጽሐፍ ቅዱሳችሁን 📖 አትርሱ! እግዚአብሔር ይባርካችሁ! 🙏
Repost from EvaSUE |ኢቫሱ
ተስፋ | ክፍል 4
ተስፋ የሕይወት ሽታ የሚሆነው ምንጭ እና መሠረቱ እግዚአብሔር ሲሆን ነው ። ተስፋ የሕይወት ሽታ ብቻ ሳይሆን የሕይወት ውሃ ወንዝ ነው ። ወንዝ ደግሞ ምንጭ አለው ። ምንጩም እግዚአብሔር ነው ። ወንዝ የተጓዘበት መንገድ ሁሉ ልምላሜን ይቸራል ። ከወንዝ አጠገብ ያለ ተክል ፍሬያማ ፣ ቅጠሉም እንደማይረግፍ ሁሉ በተስፋ የሚደረግ ጉዞ ሕይወት እና ስኬታማነትን ይጎናጸፋል ። መሠረቱ ምንጭ የሆነ ወንዝ የማይቆም ወንዝ ነው ። የማይቆም ወንዝ ደግሞ ድንጋዩን ሰንጥቆ ያልፋል ። ድንጋዩን ሰንጥቆ የሚያልፈው ግን በጉልበቱ ሳይሆን በጽናቱ ነው ። ለዚህም ጽናትን ወልደ ተስፋ ልንለው እንችላለን ። ያለተስፋ ጽናት እንዲሁ የሚመጣ ነገር አይደለም ። የምንጸናው በተስፋ ነውና ። ተስፋ ከእግዚአብሔር ስለሚመነጭ ተስፋ ቢስ ሆኖ ለደከመው የሰው ልጅ ልምላሜ እንዲሆን እግዚአብሔር አስቀድሞ የማይጠፋ ተስፋን ሰጠው ።
ሙሉውን ለማንበብ ከታችህ ያለውን ሊንክ ይጫኑ!
https://telegra.ph/%E1%89%B0%E1%88%B5%E1%8D%8B-10-03
💫በአስቸኳይ ይነበብ
የጌታ ሰላም እና ፀጋ ይብዛላች የጌታ ቤተሰብ በዚህ ሳምንት የነበረን የwelcome መርሃ ግብራችን በአንዳንድ ምክንያቶች ለቀጣይ ሳምንት ተላልፎዋል። ይሄንን መልዕክት ያያቹ እህት እና ወንድሞች መልዕክቱን ላልሰሙት በማድረስ እድትተባበሩን በጌታ ፍቅር እናሳስባችዋለን።
Repost from EvaSUE |ኢቫሱ
የመንግሥቱ ተስፋ ለማን ነው የተሰጠው?
የማናውቀውን ነገር አንናፍቅም።
የማንወደውንም አንገዛለትም።
የማንፈልገውን አንጠብቅም።
ታዲያ የመንግሥቱን ተስፋ እየጠበቅን ከሆነ፣ የምንጠብቀውን መንግሥት በእውነት እናውቀዋለን?
የመንግሥቱ ተስፋ አውቀን፣ ወደን፣ በክርስቶስ አምነን ለዳንን የተሰጠ ተስፋ ነው። ድነን ብቻ ግን የቆምን አይደለንም፤ እንደ ፈቃዱ ለመኖር የወሰንንም ነን።
እዚህ ላይ ልንረሳው የማይገባን አንድ ነገር አለ፦ ኢየሱስ አዳኛችን ብቻ ሳይሆን ንጉሣችንም ነው።
ንጉሥ ከሆነ ደግሞ፣ የእርሱ ሕዝብ የሆኑት ሁሉ እንደ ፈቃዱ መኖር አለባቸው። ልንገዛለት፣ ልንቀደስ እና ሕይወታችንን ለእርሱ ፈቃድ ልንሰጥ የሚገባንም ለዚህ ነው። ተስፋ የምናደርገው መንግሥቱን ነውና።
እስቲ ቆም ብለን እናስብ፦ ኑሮአችን ለክርስቶስ የተገዛ ነው? ካልሆነስ፣ የመንግሥቱን ተስፋ መጠበቅ ምን ያህል ትርጉም ይኖረዋል?
በእርግጥም፣ በዚህ ተስፋ ስንኖር፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እያደረግን፣ በቃሉ ራሳችንን እየመገብን፣ ራሳችንን እየቀደስን፣ በማንኛውም ሁኔታ ከፊታችን ያለውን ተስፋ በደስታ መጠበቅ ይኖርብናል።
1 ጴጥሮስ 1:13, 15 — NASV
[13] ስለዚህ ልባችሁን አዘጋጁ፤ ራሳችሁንም ግዙ፤ ተስፋችሁን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ ለእናንተ በሚሰጠው ጸጋ ላይ ሙሉ በሙሉ አድርጉ።
[15] ነገር ግን የጠራችሁ እርሱ ቅዱስ እንደ ሆነ፣ እናንተም በኑሯችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።
እንደዚህ መኖር ይሁንልን!
አሜን።
—ምህረት
Repost from EvaSUE |ኢቫሱ
አብዛኛውን ጊዜ፣አንድን ሰው ስናጣ፣
ችግር ውስጥ ስንገባ፣ውጤት አልመጣ ሲለን፣
ብቸኝነት ሲሰማን እና ነገሮች እንዳሰብነው ሳይሆኑ ሲቀሩ፣
እግዚአብሔር እንደተወን እናስባለን፤ ተስፋ እንቆርጣለን።
አምላካችን ማን እንደሆነ እንረሳለን።
ይህ በእኛ አልተጀመረም። በኢሳይያስ ምዕራፍ 40:27ን
ብናይ፣ እስራኤላውያን መብታቸው በእግዚአብሔር እንደተዘነጋ፣
እንደተተዉ እና እንደተረሱ ስለተሰማቸው፣ በእግዚአብሔር ላይ
ተስፋ መቁረጣቸውን እናያለን።
እኔም ብዙ ጊዜ ይህን አድርጌያለሁ። ዓለም በዙሪያዬ እየፈራረሰ እንደሆነ
፣ እግዚአብሔር ግን የትም እንደሌለ የተሰማኝ ወቅቶች ነበሩ።
እግዚአብሔር ግን ለእስራኤላውያን የሰጠውን መልስ ቁጥር 28 ላይ እዩ።
የእስራኤላውያን ትኩረት ሁኔታቸው ላይ ስለነበር፣ እግዚአብሔር
ትኩረታቸውን ወደ እርሱ ማንነት መለሰ። ስለ ታላቅነቱ በማስታወስ፣
እርሱ የምድር ፈጣሪ መሆኑን፣ የማይደክም፣ የማይታክት፣ ብርታት ሰጪ
አምላክ እንደሆነ ዘርዝሮ፣ ተስፋ የሚጣልበት አምላክ መሆኑን አሳያቸው።
ቁጥር 31 ላይም፦
“እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፥
እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፥ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፥ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።”
በማለት መልእክቱን ደመደመው።
እስራኤል በወቅቱ የእግዚአብሔርን ማንነት ማስታወስ እንደነበረባት ሁሉ፣ እኛም እንዲሁ ማድረግ አለብን ብዬ አስባለሁ።
አዎ፣ ሁኔታዎቻችን እግዚአብሔር እንደረሳን ሊነግሩን ይችላሉ፤ ነገር ግን ባሕርዩ የሚነግረን ከዚህ በተቃራኒ ነው።
ለዛም ነው እርሱ ማን እንደሆነ ራሳችንን ማስታወስና ተስፋችንን በእርሱ ላይ ማድረግ የሚገባን።
ምክንያቱም እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ኃይላቸውን ያድሳሉና።
እግዚአብሔር ይህን ዓመት ዕለት ተዕለት ማንነቱን እንድናስታውስ ይርዳን!
አሜን።
—ምሕረት
💫እስካሁን አብራችሁን የጌታን ሃሳብ የተካፈላቹ ሁሉ ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ ፀጋውንም ያብዛላቹ🙏 የዛሬው የonline መርሃ ግብራችን የመጨረሻው ነው።ከጥቂት ቀናት በኋላ ደግሞ ጌታ ፈቅዶ በጊብ የህብረት ግዜያችንን በአካል እቀጥላለን።ጊብ እስክንገናኝ ድረስ በጉጉት እና በናፍቆት እንጠብቃችኋለን እንወዳችኋለን መልካም አዳር ይሁንላቹ።
#✊✊ለኛ ግን በመቅበዝበዝ ፈንታ በእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ መሰንበት ተሰጥቶናል!!
#እግዚአብሔርን መፈለግ
#በመመለስ
#በፅድቅ ኑሮ
#በመታመን
Repost from 📚መንፈሳዊ መጽሐፍት📔
📔ርዕስ፦ የበረሃው ሰይፍ፡ ሽብርተኝነትና አክራሪ እስልምና ምንጭ ዥረት
👤ደራሲ፦ ኑረዲን ኢብን አል-መሲህ
📑የገጽ ብዛት፦149
___
የደራሲው ሌሎች ስራዎች፦
*አይኤስ እስላማዊ ነውን?
@AmharicSpritualBooks
እስካሁን በonline ላይ መርሃ ግብሬችንን በጥሞና እየተከታተላቹ ያላችሁ ዛሬም የካርድ ስጦታ🎁 አለን ተዘጋጁና እንለቃለን
