cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

BBC PTVOT ETH

➟ስለ ወቅታዊ ጉዳይ ሙሉ መረጃ ➟ተአማኒ ያለው መረጃ ➟እንዲሁም በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተመረኮዙ አዝናኝ ነገሮች ያገኛሉ ። ለማንኛውም አስተያየት @penitome ያጋሩን #የናንተ ምርጫ BBC PTVOT ETH!

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
305
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ቀነ ገደብ የግድ ማከናወን እንዳለባቹ የምታውቁት ተግባር የቀን ገደብ(Deadline)የማታስቀምጡለት ለምንድን ነው? የቀን ገደብ ያስቀመጣችሁለትን ያንን አስፈላጊና መከናወን ያለበትን ተግባር በተቀመጠለት የቀን ገደብ የማታከናውኑት ለምንድን ነው? ዘመኑ ለንቁዎች እንጂ ለፈዛዞች እንዳልሆነ ላስታውሳቹ።
إظهار الكل...
ጊዜን ለራስህ ጨምር እስቲ አንድ ነገር አብረን እናስብ። ይህንን ሃሳብ ከግል ልማዴ በመነሳት እንነጋገረው። ከጥቂት ዓመታት በፊት ማድረግ በምፈልገው ነገር ዙሪያ ትኩረትና ዲሲፕሊን (ስነ - ምግባር) የሞላው ጎዳና መጀመር አለብኝ ብዬ ወሰንኩ። ይህንን ጎዳና ለመጀመር በመጀመሪያ የትኩረት ጉልበቴን ማቃጠል የምፈልግበት አስፈላጊ ነው የምለውን ነገር መምረጥ ነበረብኝ። ስለዚህ ጠቃሚ ጽሑፎችን በመፃፍ ለህብረተሰቡ ማበርከትን መረጥኩ። ውሳኔዬ ይህንን ይመስል ነበር ፤ በየቀኑ ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ተኩል ያህል በአንድ ነገር ዙሪያ መፃፍ አለብኝ። ይህ ውሳኔ ቀላል ውሳኔ አልነበረም። ማድረግም የማይቻል አልነበረም። ስንጀምር ትንሽ ጫና የነበረብኝ ቢሆንም ከትኩረቴ ሳልወጣ ስለደጋገምኩት ማድረግ ችያለው። ይህን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ ከየቀኑ አስፈላጊነቱ አናሳ ከነበረው ልማዴ ላይ አንድ ሰዓት ተኩል "መስረቅ" ነበረብኝ። ስለዚህ በመጀመሪያ ማድረግ የነበረብኝ ፤ ለመፃፍ የሚያስችለኝ ንቁ ሰዓቴና በምን ሁኔታና በማንም ሰው ትኩረቴ የማይሰረቅበት ጊዜና ሰዓት የትኛው እንደሆነ መለየት ነው። ንቁ ሰዓቴ ማለዳ ነው። በዚህ ሰዓት ደግሞ ከቤቴ የተለየ ምቹ ስፍራ የለም። ጉዳዩ የተጀመረው ያን ጊዜ ነው። ይህን ውሳኔ ከጀመርኩ ጀምሮ ከአቅም በላይ የሆኑ ጉዳዮች ካጋጠሙኝ ቀናት በስተቀር በየቀኑ ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ተኩል እፅፉለው። በዓመት ውስጥ የሰዓት ልማዴንና የእንቅልፍ ሁኔታዬን የሚያዛቡ የተለየ የጊዜ አቆጣጠር ያላቸው ሀገሮች በምጓዝበት ጊዜ እንኳ ይህንን ልማዴን በፍፁም ላለማቆም ጥረት አደርጋለው። ሂሳቡን እንስራው በየቀኑ የአንስ ሰዓት ተኩል ጊዜን በመወሰንና በማመቻቸት ቀድሞ አደርግ ያልነበረውን ነገር ማድረግ በመጀመሬ በዓመት 547 ሰዓታትን በአንድ ነገር ላይ በማተኮር መስራት ጀምሬያለው ማለት ነው። እነዚህን 547 ሰዓታት በሳምንት 40 ሰዓት ቢሄንም በተለመደ የስራ ሰዓት ሳሰላቸው የሁለት ወራትን(68 ቀናት) የስራ ጊዜ ጨምሬያለው ማለት ነው። በሌላ አባባል ከሌሎች የስራ ኃላፊነቴ ውጪ የሆኑና ማንም የማይነካብኝ የሁለት ወራት የስራ ጊዜ ፈጥሬያለው። ምናልባት ይህንን ስሌት በመስራትና ተመሳሳይ ውሳኔን በመወሰን በዓመት የተወሰኑ የስራ ጊዜይትን ለራስህ መጨመር ትችላለህ። ይህንን ለማድረግ የሚከተሉትን ደረጃዎች ይጠቅሙሃል ብዬ አስባለው። 1. መገንባት የምትፈልገውን ነገር ላይ ከላይ የዘረዘርኩትን ሃሳብ የትኩረት እውነታ ተግባራዊ ለማድረግ ስታስብ ምናልባት በአንድ የህይወት ሁኔታ ዙሪያ ትኩረት ሰጥተህ ለማዳበር የምትፈልገው ነገር ታይቶህ ይሆናል። ይህንን ጉዳይ በሚገባ አስበህበት አንድ ድምዳሜ ላይ በመድረስ ፣ ለመገንባት ወይም ለማሻሻል የመረጥኳቸውን ተግባራት ለይተህ እወቅ። 2. አመቺ ሰዓት ምረጥ ፦ ይህ ለመለወጥሰዓት ምርታማ ለመሆን ንቁ የሆንክበትን ከተለያዩ ሃሳብ ሰራቂ ሁኔታዎች ነፃ የምትሆንበት ሰዓት ሊሆን ይገባል። 3. አመቺ ሁኔታንና ቦታን ምረጥ፦ ለተግባር ስኬታማ ስፍራ ወሳኝ ነው። 4. እርምጃ ውሰድ፦ ይህንን አስታውስ አንድን ነገር እስክትጀምረው ድረስ አይጀመርም። ምንም እንኳን የመፃፍ ፅኑ ፍላጎት ቢኖረኝም ፣ አንድ ቀን ተነስቼ ይህንን ተግባር መጀመር አለብኝ ብዬ እስክጀምረው ድረስ አልተጀመረም። በምኞት ብቻ የቆምኩባቸው ጊዜያት እንደነበሩ ማስታወስ አስፈላጊ ነው። ምኞትና የቀን ህልም ግን የትም አያደርስም። አንድ ቀን ተነስቼ ከአንድ ዓረፍተ ነገር በመነሳት የጽሑፍን ስራ መጀመር ነበረብኝ። ሲጀመር ግር ይላል ፣ ሲቀጥል ግን እየጠራ ይሄዳል። አንተም ከምኞትህ ውጣና ያሰብከውን ጀምር። ትችላለህ!! ትችያለሽ!!
إظهار الكل...
የአርጅቻለው ፕሮፓጋንዳ "አንጅቻለው" ከማለት "በመለኮታዊ ህይወት አሁን ከመቼውም ይልቅ በጥበብ በስያለው" በል። እርጅና መውደቅና ተፈላጊ አለመሆን አድርገው የሚቆጥሩ ሰዎችን ፈፅሞ አትስሙ። በእንዲህ ዓይነቱ ፕሮፓካንዳ (ቅስቀሳ) አትታለሉ። በህይወት እስካላቹ ድረስ መቼም ቢሆን ድንቅ ተግባራትን ማከናወን እንደምትችሉ ለራሳችሁ አረጋግጡ ። ሁሌም ደስተኛ ፣ የተሳካለት ውጤታማ ሰው ልትሆኑ እንደምትችሉ አስቡ።
إظهار الكل...
የራዕይ ትልቅነት በፊትህ የተጋረጠውን የችግር ተራራ የመሻገርን ሁኔታ የሚወስነው ከተራራው ባሻገር ያለው የራዕይህ ትልቅነት ነው። ራዕይህ ከችግር ተራራ ካነሰ ተራራውን ለመሻገር ያለህ ፍቃድ ደካማ ስለሚሆን ፤ እንኳን መሻገር መሞከሩም ያስፈራሃል። ራዕይህ ከችግር ተራራ ከተለቀ ግን ተራራውን መውጣት ካለብህ ወጥተህና ወርደህ ትሻገረዋለህ። መውጣት ካልቻልክ በዙሪያውም ቢሆን አልፈህ ትሄዳለህ እሱም ካልታቻለ ቦርቡረከውም ቢሆን ታልፈዋለህ እንጂ ወደ ኃላ አትመለስም። ስለሆነም ፣ ስለራዕይህ ትልቅነት አስብ እንጂ ስለ ችግርህ ተራራ ግዝፈት አትጨነቅ። መልካም ቀን ይሁንላቹ።
إظهار الكل...
የማያፈቅራችሁን ፣ የሚንቃችሁንና ብትሄዱም ሆነ ባትሄዱ ምንም ግድ የሌለውን ፍቅረኛ ሁኔታ በትእግስት ለመልመድ ከምትታገሉ ይልቅ እንደገና ለብቻ መሆንን ለመልመድ ብትወስኑ የሚሻልበት ጊዜ እንዳለ አትዘንጉ።
إظهار الكل...
ስር ከሰደደ መጨነቅና መጨናነቅ መላቀቅ... መጨነቅና መጨናነቅ ማንንም ሰው ከችግሩ ሲያድነው ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም። በመጨነቅና በመጨናነቅ ምክንያት ግን ሰዎች ቀስ በቀስ ወደ ሞት ሊያዘግሙ እንደሚችሉ መረጃዎችና ማስረጃዎች ሞልተዋል። እናንተ ማድረግ የምትችሉትን አድርጉ እናንተ ማድረግ የማትችሉትን ደግሞ ሊያደርግላቹ የሚችል ሰው ካለ አስደርጉ። ማንም ሊያደርግላቹ የማይችለው ሁኔታ ውስጥ ካላችሁ ግን ጉዳዮን ለፈጣሪ አሳልፉችሁ ስጡና ኑሯችሁ ላይ አተኩሩ።
إظهار الكل...
ያለ ፍርሃት ጥንቁቅ ሁን አንድ ጊዜ አንድ ንጉስ ከጦር አጃቢዎቹ ጋር ሆኖ ወደ ሌላ ሀገር ጉዞ ሲያደርግ አንድ እጅግ አጥፊ አውሌ ንፉስ ወደ እሱ አቅጣጫ በመገስገስ ላይ እንዳለ ተመለከተና ባለው የጦር ሃይል አውሌ ንፉሱን አስቁሞ "ወደ እኔ ሃገር አቅጣጫ በመሄድ ላይ ነህ። ከእኔ ሃገር ሰው ማንንም እንደማታጠፉ ቃል ካልገባህ አታልፍም" አለው። አውሎ ንፉሱም፦ "እርግጥ ነው ወደዚህ አቅጣጫ ነው የምሄደው ፤ ነገር ግን የአንተ ሃገር ሕዝብ በፍፁም እንደማልነካ ቃል እገባልሃለው" አለው። ንጉሱ ከጉዞው ሲመለስ ከሃገሩ ሰዎች በርካቶች እንደሞቱ ሰማ። በጣም በመቆጣት አውሎ ንፉሱን ተከታትሎ ደረሰበትና "ማንንም እንደማትነካ ቃል ገብተህልኝ ለምንድ ነው ብዙ ሰው የገደልከው? " አለው። አውሎ ንፉሱም እንደዚህ ሲል መለሰለት፦ " እኔ በሃገርህ አጠገብ አለፍኩ እንጂ የሃገርህን ሕዝብ አንዱንም አልነካሁም። እንደሰማሁት ከሆነ ግን ከባድ አውሎ ንፉስ መጣ የሚል ወሬ ተወርቶ በፍርሃትና በድንጋጤ አንዳንዱ በልብ ድካም ፣ አንዳንዱ ሲሯሯጥ እርስ በእርሱ ተረጋግጦ ነው የሞተው" አለው። አንዳንዴ ከሚገጥሙን ችግሮች ይልቅ በችግሩ ላይ ያለን አመለካከትና በምንሰጠው ተገቢ ያልሆነ ምላሽ የድንጋጤ ስሜታችን ከማየሉም የተነሳ አዋቂዎቹ የሚነግሩንን መመሪያ በአዕምሯችን አስበን አለመከተላችን ነው የሚያጠፉን። ከሚከበን ምክንያት የለሽ ፍርሃት በመላቀቅ ያለ ፍርሃት ልባሞች እንሁን ።
إظهار الكل...
ለማስታወስ እይታህን ተጠቀምበህት "አዕምሮዬ" ይላል አብርሀም ሊንከን "እንደ ብረት ሰሌዳ ነው። በቀላሉ ልትጭረው አትችልም። ብትጭረው እንኩዋን በቀላሉ ለማጥፉት አስቸጋሪ ነው። " "አንድ ጊዜ ማየት ሺ ጊዜ የመስማት ያህል ነው።" ይላሉ ቻይናዎች ሲተርቱ። ለመስማት አንድን ነገር ማየት በጣም አስፈላጊ ነው። በአይነ ህሊና ወይም በአይነ ስጋ ያየነው ነገር በቀላሉ አይጠፉም። በአይናችን ወይም በአንጎላችን መልዕክት የሚወስዱ ነርቮች ብዛት ከጆሯችን ወደ አንጎላችን መልዕክት ከሚወስዱት ሃያ አምስት ጊዜ ዕጥፍ ይሆናሉ። ከሰማኸው ይልቅ ያየኸውን ስለምናስታውስ እይታህን ተጠቀምበት።
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.