cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Woldia University/ወልድያ ዩኒቨርሲቲ

ይህ ትክከለኛዉ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የቴሌግራም ቻናል ነዉ፡፡ This is Woldia University official Telegeram channel.

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
11 655
المشتركون
+2324 ساعات
+807 أيام
+8330 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

00:08
Video unavailableShow in Telegram
Exit Exam Finalized.mp46.96 KB
በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲሰጥ የነበረዉ የመውጫ ፈተና ተጠናቀቀ፡፡ (ሰኔ19/2016 ዓ.ም (የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት) የወልድያ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከሰኔ 14/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረውን የመውጫ ፈተና (Exit Exam) በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለነበሩ እና ከተለያዩ የግል ኮሌጆች ለተውጣጡ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች ያለምንም ችግር ውጤታማ በሆነ መንገድ አስፈትኖ አጠናቋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ባደረገው ጠንካራ የቅድመ ዝግጅት ሥራ የኢንተርኔት እና የመብራት መቆራረጥ ችግር ሳይከሰትና ተማሪዎች ከትምህርቱ ዝግጅት ባለፈ ጠንካራ የስነ-ልቦና ዝግጅት እንዲያደርጉ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመሰራታቸው ፈተናውን በስኬት መስጠት መቻሉንና በዛሬው እለት የጤና ተማሪዎችን በማስፈተን ማጠናቀቁን የዩኒቨርሲቲዉ የፈተና ክፍል አስተባባሪ የሆኑት መ/ር ስሜነው አስራት አስረድተዋል፡፡ የጤና ተማሪዎች ከመዉጫ ፈተና በተጨማሪ የሙያ ፈተና (licensure Exam) በዛሬዉ እለት ተፈትነዋል፡፡ አስተባባሪው አክለውም ይህ የመውጫ ፈተና ያለምንም እንከንና ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ በስኬት እንዲጠናቀቅ ከከፍተኛ አመራሩ ጀምሮ ሁሉም የግቢው ማህበረሰብ እና ለሱፐርቪዥን የመጡ እንግዶችን ጨምሮ ላደረጉት ያላሰለሰ ጥረት እናመሰግናለን ብለዋል፡፡ ---------------------------------------------------------------------------------------------- አእምሮ ሲከፈት አይኖች ማየት ይችላሉ / Open Mind. Open Eyes!
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ማስታወሻ (Notic) ⏰📢
إظهار الكل...
ምርታማነትን በሚያሻሽሉ የሰብል ዘር ብዜት ትኩረት ያደረገ ስልጠና ተሰጠ:: ሰኔ 18/2016 ዓ.ም (ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት) በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ፣ ቆቦና ጉባላፍቶ ወረዳዎች ለተውጣጡ በየደረጃው ለሚገኙ የግብርና ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና አርሶ አደሮች በሰብል ዘር ብዜት ላይ ያተከረ ስልጠና በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ በዛሬው ዕለት ተሰጥቷል። ስልጠናውን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩትና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር አማረ ቢሆን ከትኩረት መስኮቻችን መካከል አንዱ በሆነው ግብርና ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በዘር ብዜት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ የማህበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪና የፕሮጀክቱ አባል የሆኑት መምህር ስሜነህ ጌቴ እንደተናገሩት ስልጠናው በዋናነት ስለጤፍና ማሽላ ዘር አመራረትና ድህረ ምርት አያያዝ እንዲሁም በግብርና ቴክኖሎጂ ባጠቃላይ ከማሳ መረጣና ዝግጅት ጀምሮ ምርጥ ዘሩ እስከሚሰበሰብበት ድረስ የዘር ጥራትን የሚያስጠብቁ አሰራርች ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል። ምርትና ምርታማነትን ሊያሳድጉ የሚያስችሉ የግብርና ግብአቶችን በማቅረብና ስልጠናን በመስጠት እንዲሁም አዳዲስ አሰራሮችን ለአርሶ አደሮች በማስተዋወቅ ጥራቱን የጠበቀ ዘር በማምረት ማህበረሰቡ ገቢውን ከማሳደግ ባለፈ የዘር አቅርቦትን ለማስፋት ያለመ መሆኑን አሰተባባሪው አክለው ገልጸዋል። የማህበረሰብ አቀፍ የዘር ብዜት ስራ ከሌሎች አጋር ተቋማት ጋር በተለይም ከስሪንቃ ግብርና ምርምር ማዕከልና ከሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ጋር በመተባበር እየተሰራ እንደሚገኝ የተናገሩት መ/ር ስሜነህ ስልጠናው ከዚህ በተጨማሪ ከዋድላ ወረዳ ለተውጣጡ የግብርና ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና አርሶ አደሮች በትናንትናው ዕለት በጋሽና ከተማ መሰጠት መቻሉን ገልጸዋል። አስተያየታቸውን የሰጡ የስልጠናው ተሳታፊዎች በቴክኖሎጂ ታግዞ፤ አዳዲስ አሰራሮችን በመከተል በኩታ ገጠም ማምረት ምርትና ምርታማነትንም ሆነ ገቢን ለማሳደግ ያለው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል። አስተያየት ሰጭዎቹ አክለውም ወቅቱን የጠበቀ በቂ የግብዓት አቅርቦትና በቀጣይም የገበያ ትስስሩ ተጠናክሮ ቢቀጥል ጥሩ ነው ብለዋል። በስልጠናው ላይ 90 የሚደርሱ ተሳታፊዎች እንደተሳተፉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። ---------------------------------------------------------------------------------------------- አእምሮ ሲከፈት አይኖች ማየት ይችላሉ / Open Mind. Open Eyes! የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤ Web site: https://www.wldu.edu.et/ Facebook = https://www.facebook.com/WoldiaUniversity Telegram Channel = https://t.me/Woldia_University YouTube = https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw P.O.Box = 400 Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መሰጠት ተጀመረ። (ሰኔ14/2016 ዓ.ም (የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት) የ2016 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) በዛሬው እለት መሰጠት ተጀምሯል። በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የትምህርት ጥራትን ለማምጣት እየተሰሩ ካሉ ጉልህ ስራዎች መካከል የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና አንዱ ነዉ። ይህን ተከትሎ የዘንድሮውም የመውጫ ፈተና ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መርሐ-ግብር መሰረት ከሰኔ 14-21/2016 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ3ኛ ጊዜ እየተሰጠ ይገኛል። ወልድያ ዩኒቨርሲቲም በዩኒቨርሲቲው ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ እጩ ምሩቃን ተማሪዎቹንና ከተለያዩ ኮሌጆች የተውጣጡትን ጨምሮ 2365 ተማሪዎችን ለማስፈተን የቅድመ ዝግጅት ስራዎቹን ማጠናቁን ከፈተና አስፈጻሚ አካላት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የዛሬው የፈተና መርሀ-ግብርም የማኔጅመንት ተማሪዎችን በማስፈተን ተጀምሯል። ---------------------------------------------------------------------------------------------- አእምሮ ሲከፈት አይኖች ማየት ይችላሉ / Open Mind. Open Eyes! የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤ Web site: https://www.wldu.edu.et/ Facebook = https://www.facebook.com/WoldiaUniversity Telegram Channel = https://t.me/Woldia_University YouTube = https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw P.O.Box = 400 Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.
إظهار الكل...
ለ2016 ዓ.ም ክረምት በጎ ፍቃደኛ ተማሪዎች ስልጠና መስጠት ተጀመረ:: ሰኔ 11/2016 ዓ.ም (ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት) የሰላም ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር “ብዝሀነት ለአብሮነት” በሚል መሪ ቃል ለወልድያ ዩኒቨርሲቲ በጎ ፍቃደኛ ተማሪዎች ስልጠና መስጠት ተጀመረ። ስልጠናውን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አበበ ግርማ ኢትዮጵያ በርካታ ሀብት፣ ባህልና ቋንቋ ያላት ባለታሪክ ሀገር በመሆኗ ተማሪዎች ይህንን በማወቅና በመገንዘብ ሁላችንም በጋራ ለሃገር ዕድገት አስተዋጽኦ ለማድረግ መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ አክለውም ተማሪዎች ከትምህርት ጊዜ በኋላ በትርፍ ጊዜያችሁ በክረምት በጎ ፍቃደኝነት በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ችግሮችን በመፍታት እንዲሁም በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ባህሎችን ለማሳደግ የምታዩበት ፕሮግራም በመሆኑ ሁላችሁም በአገልጋይነት መንፈስ እንድትወጡ ሲሉ አሳስበዋል፡፡ በሰላም ሚኒስቴር በፌደራሊዝምና መንግስታት ግንኙነት ዘርፍ የፌደራሊዝምና ዲሞክራሲ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ጌታቸው በለጠ እንደተናገሩት በዋናነት ስልጠናው ከበጎ ፍቃደኝነት ገለጻ ጀምሮ የእዉቀት ክህሎት ፣ ተወዳዳሪ ዜጋ ከመሆን አንጻር እና ሀገር ግንባታ ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል። (Soft Skills, Competent citizen and nation building) አቶ ጌታቸው አክለውም በጎ ፍቃደኞቹ ከአምስት የስልጠና ቀናት በኋላ የስራ ስምሪት ይዘው ወደተመረጡ አካባቢዎች በመሄድና የማህበረሰቡን ችግሮች በመለየት በተለይም የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ትቦዎችን የማጽዳት፣ የጎዳና ተዳዳሪዎችን በተለያዩ ነገሮች የመደገፍ፣ የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠትም ሆነ ተያያዥ ጉዳዮች እንደየሙያ መስካቸውና እንደየአካባቢው ሁኔታ ለተከታታይ 25 ቀናት በበጎ ፍቃደኝነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ በ2016 ዓ.ም በሃገር አቀፍ ደረጃ በ32 ዩኒቨርሲቲዎች ከ20‚000 በላይ ተማሪዎችን አሰልጥኖ በክረምት በጎ ፍቃድ ስራ ለማሰማራት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለጹት ባለሙያው በተለያዩ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎችና በአካባቢው ማህበረሰብ መካከል አንድነትን ለማጎልበት፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በጎ ፍቃደኞች ከትውልድ ቀያቸው ውጭ ያለውን ማህበረሰብ ባህልና ቋንቋን ማስተዋወቅ እንዲሁም ለማህበረሰቡ አገልግሎት የመስጠት ባህልን በማሳደግ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ስልጠናው ከዛሬ ሰኔ 11/2016ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት ይቆያልም ተብሏል። ስልጠናውን ከሰላም ሚኒስቴር በመጡ ባለሚያዎች አቶ ጌታቸው በለጠ እና አቶ ስምረት ተፈራ አማካኝነት እንደሚሰጥና 465 የሚሆኑ የክረምት በጎ ፍቃደኛ ተማሪዎች በስልጠናው ላይ እንደሚሳተፉም ከስልጠናው አስተባባሪዎች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ---------------------------------------------------------------------------------------------- አእምሮ ሲከፈት አይኖች ማየት ይችላሉ / Open Mind. Open Eyes! የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤ Web site: https://www.wldu.edu.et/ Facebook = https://www.facebook.com/WoldiaUniversity Telegram Channel = https://t.me/Woldia_University YouTube = https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw P.O.Box = 400 Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.
إظهار الكل...

የዩኒቨርሲቲዉ የሴኔት አባላት ኢድ-አል -አድሀ (አረፋ) በአልን ከተማሪዎች ጋር በደማቅ ሁኔታ አከበሩ! ሰኔ 10፣ 2016 ዓ.ም (የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት) በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በደማቅ ሁኔታ የሚከበረዉን የኢድ-አል አድሀ (አረፋ) በአልን ምክንያት በማድረግ በትናንትናዉ እለት በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መመገቢያ ካፌ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡ በበአሉም የዩኒቨርሲቲዉን ፕሬዝደንት ዶ/ር አበበ ግርማን ጨምሮ ሁለቱ ምክትል ፕሬዝደንቶች፣ የተማሪዎች ዲን እና ሌሎችም የሴኔት አባላት በተማሪዎች ካፌ ተገኝተዉ ከተማሪዎች ጋር ማእድ በመጋራት እና ተማሪዎችን እንኳን አደረሳች በማለት አሳልፈዋል፡፡ ለዉድ የዩኒቨርሲቲያችን የሙስሊም ማህበረሰቦች በሙሉ በድጋሜ እንኳን ለኢድ-አል-አድሀ (አረፋ) በአል አደረሳችሁ! ኢድ ሙባረክ ማለት እንወዳለን! ---------------------------------------------------------------------------------------------- አእምሮ ሲከፈት አይኖች ማየት ይችላሉ / Open Mind. Open Eyes! የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤ Web site: https://www.wldu.edu.et/ Facebook = https://www.facebook.com/WoldiaUniversity Telegram Channel = https://t.me/Woldia_University YouTube = https://www.youtube.com/channel/UCHt88As5v2BmynWine1Oexw P.O.Box = 400 Woldia Town, Amhara Region, Ethiopia.
إظهار الكل...
أرشيف المشاركات
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.