cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

🌻ግእዝ🌻 🌻Tube🌻

✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ ✍መንሳፈሳዊ ታሪክ ✍ግእዝ ቋንቋ ✍መንፈሳዊ ትምህርቶችን ያገኙበታል @Geztub @Geztub ✍ #ሸር_Join_ማድረግ አይርሱ ✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝ ከታገሱት ሁሉም ያልፋል

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
289
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

══●◉ ደብረ ዘይት ◉●════ ✥ የአብይ ፆም አምስተኛ ሳምንት ✥ • በመምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ • ✥  ክፍል 5 ¶ ለመምህራችን ቃለ ህይወት ያሰማልን ╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮    @Geztub ╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
إظهار الكل...
ሼር 📍
1. ዘወረደ የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሰንበት ሲሆን ይህም ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን ፈጥሮ የሚኖር አልፋና ኦሜጋ ከሰማየ ሰማያት መውረዱንና ከእመቤታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመለክት ሥያሜ ነው፡፡ t.me/Geztub
إظهار الكل...
በ 5 ሰልፉ አይቀርም
إظهار الكل...
إظهار الكل...

ፀጉራችንን አንጨብርረን ሲያዩን በሱሪ ተጣብቀን ሲያዩን ስንጠጣ ስንጨፍር ሲያዩን ለተዋህዶ ለቤተክርስቲያናችን ዘብ የማንቆም መስሏቸው ነበር እንዴ 🙄 የትኛው ወጣት ነው ሰፈሩ ያሉ ደብሮችን ሳይሳለም የሚውለው የትኛው ሱሰኛ ነው ቤተክርስቲያን በር ላይ ቆሞ ይሄ ህይወት ሰልችቶኛል ብሎ የማይፀልየው የትኛዋ ሴት ነች ቤተክርስቲያን በር ላይ ቆማ የማታለቅሰው እምነታችን ላይ ደካማ ነን እንጂ አልተውነውም መቼም አንተወውም ሰው ከቤቱ ወዴት ይሄዳል ሌላ ቤት የት አለን እና አሁንም ቢሆን የሚጠብቅ እንጂ የሚላላ ማህተብ የለንም 🙏🙏 ተመስገን እንበትናቸዋለን ብለው ሰበሰቡን🙏🙏
إظهار الكل...
ምን እንጠይቅሎ?: በምስጢረ ጥምቀት ላይ ጥያቄዎች ጥያቄ:- ተቃዋሚዎች ያላመነ ይፈረድበታል እንጂ ያልተጠመቀ ይፈረድበታል አይልምና ለመዳን መጠመቅ አያስፈልግም ይላሉ መልስ:-ጥምቀት ለመዳን የማያስፈልግ ቢሆን ኖሮ ያመነ ብቻ ይድናል በተባለ ነበር። ወንጌሉ ግን በግልጽ ያመነ  ብቻ ሳይሆን "ያመነ የተጠመቀም" በማለት ነው የሚገልጸው። በመጀመርያ ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ስንመለከት ከቁጥር. 15 ላይ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ ወንጌልን ለፍጥረት እንዲሰብኩ ካዘዛቸው በኋላ ነው የተናገረው። ቅዱስ ጳውሎስም "እንግዲያስ እምነት ከመስማት  ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።" ሮሜ. 10:17 እንዳለ አንድ ሰው ለማመን የእግዚአብሔርን ቃል መማር መስማት አለበት። ለዚህም ነው "ያመነ የተጠመቀ ይድናል" ከማለቱ በፊት ጌታችን ወንጌልን  ለፍጥረት ስበኩ ብሎ ያዘዛቸው። ማር. 16:15:: ጌታችን ያመነ ብቻ አይደለም ያለው "ያመነ የተጠመቀም ይድናል" ነው ያለው:: ስለዚህ በመጀመርያ እምነትን ብቻ እንዳላለ እናስተውል። ቀጥሎ ያላመነ ይፈረድበታል ያለው ማመን ለሁሉ መሰረት በመሆኑ እንጂ ጥምቀት የማያድን [ለመዳን የማያስፈልግ] ስለሆነ አይደለም። ያላመነ ሰው ስለ መጠመቅ ሊያወራ አይችልምና ወንጌልን ስበኩ ብሎ የላካቸው የሐዋርያትን ቃል ሰምቶ ለማመን ያልበቃን ሲገልጽ ስለዚህ ያላመነ ይፈረድበታል አለ። በቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት ልባቸው ተነክቶ ካመኑ በኋላ ሕዝቡ የጠየቁት ጥያቄ "ምን እናድርግ?" የሐዋ.2:37 የሚል ነው። ቅዱስ ጴጥሮስም "ኃጢአታችሁ ይሰረይ ዘንድ ተጠመቁ በማለት ነው ያዘዛቸው። የሐዋ. 2:38:: ስለዚህ አንድ ለማመን የደረሰ ሙሉ የሆነ ሰው ከመጠመቁ በፊት ማመን ይቀድማልና ነው። ያላመነ ሰው ግን እንዴት ብሎ ይጠመቃል ስለዚህ ነው ያላመነ ይፈረድበታል ያለው። ማመን መሠረት ነውና። መጠመቅ ከውሃና ከመንፈስ መወለድ እንደሚያድን ጌታችንም "እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግስት ሊያይ አይችልም::" ዮሐ. 3:5 ብሏል:: ስለዚህም በጥምቀት ከውሃና ከመንፈስ በመወለድ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን ለመዳን የሚያስፈልግ ነው ማለት ነው። ቅዱስ ጴጥሮስም "ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል።" 1ኛ ጴጥ.3:21 በማለት ጥምቀት እንደሚያድን በግልጥ ቃል ነግሮናል። ይቀጥላል... ✍ ተክለማርያም [ጅማ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት] ጥያቄ :- ጌታችን በወንጌል "ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግስት ሊያይ አይችልም።" ዮሐ. 3:5 ያለው ምሳሌያዊ እንጂ  ጥምቀትን አይደለም የሚሉ አሉ፦ መልስ 👉 ውሃና ከመንፈስ መወለድ የተባለው በጥምቀት የእግዚአብሔር ልጅ መሆንንና ለመዳን የሚያስፈልግ መሆኑን የሚያመለክት ነው። እግዚአብሔር የሰጠንን ጸጋ ለመቀበል በጥምቀት የእግዚአብሔር ልጆች ሆነን ካልተወለድን በስተቀር  ከእናት ከአባት በተወለድነው ተፈጥሮአዊና ሥጋዊ ልደት መንፈሳዊና ሰማያዊ የሆነውን የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ አንችልም። ሐዋርያትና ከሐዋርያት የተማሩ ቅዱሳን ሊቃውንት ያስተማሩት በጥምቀት ዳግም ልደት መንግስቱን መወረስ የሚያስችል ምስጢር እንደሆነ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጥምቀት መንግስተ ሰማያት የሚያስወርስ ምስጢር እንደሆነ ሲገልጽ "ለማያምኑት አልቅሱላቸው የጥምቀትን ማሕተም ሳያገኙ ለሞቱት አልቅሱላቸው። እነርሱ ከመንግስተ ሰማያት ውጪ ናቸውና ልናለቅስላቸው ይገባናል። ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ  በስተቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም" ተብሏልና።" [ትርጓሜ ፊልጵስዩስ ክፍለ ትምሕርት 3] ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌምም "ማንም ሰው ካልተጠመቀ በቀር መዳንን አያገኝም፣ በውኃ ሳይሆን በደማቸው ከተጠመቁ ከሰማዕታት በስተቀር። ጌታችን ዓለምን በመስቀሉ ባዳነ ጊዜ ጎኑን ተወጋ ያን ጊዜም ደምና ውኃ ከጎኑ አፈለቀልን። ይህም በሰላም ጊዜ የሚኖሩ ሰዎች በውኃ ይጠመቁ ዘንድ በስደትና በመከራ ጊዜ የሚኖሩ ሰዎች ደግሞ በደማቸው ይጠመቁ ዘንድ ነው።..."።[ በእንተ ጥምቀት ትምሕርት 3 ቁ.10] ብሏል።" 👉 ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም" የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ይዘው ውኃው የተባለው ጥምቀት ሳይሆን በተቃዋሚዎች ዘንድ አንዳንዶቹ ውኃው ምልክት (symbolic) ነው ሌሎቹ  የእምነት ማጽኛ ነው ሌሎቹም የእግዚአብሔር ቃል ነው  የእምነት መመስከሪያ [አንዳንዶቹም ውኃ የተባለው ምሳሌያዊ ሲሆን መንፈስ ቅዱስን ያመለክታል ይላሉ።] በማለት ይተረጉማሉ። ማስረጃ 1:-ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ በመድሎተ ጽድቅ መጽሐፉ ይህን አስመልክቶ "በተቃዋሚዎች ዘንድ ርስ በርሳቸው እንኳ ይህ ሁሉ የአረዳድ ልዩነት የተፈጠረው ግን ሁሉም አንብቦ መተርጎም ይችላል በሚል የተሳሳተ ትምህርታቸው የተነሳ ነው። ይህን የጻፈልን የወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር የነበረው የቅዱስ ፖሊካርፕስ ደቀ መዝሙር ቅዱስ ሄሬኔዎስ "እኛ በኃጢአት ምክንያት አካላችን የተቆማመጠብን እንደመሆናችን የእግዚአብሔርን ስም በመጥራትና በተቀደሰው ውኃ በመጠመቅ ከክፉ በደሎቻችን ሁሉ እንነጻለን፤ አዲስ እንደተወለዱ ሕጻናትም በመንፈሳዊ ልደት ዳግመኛ እንወለዳለን ራሱ ጌታችንም እንዲህ ብሎ እንደተናገረ፦ "እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።" ዮሐ 3:5 (ቅሬታት፣ 34) ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀ መዝሙሩን ቅዱስ ፖሊካርፕስን ያስተማረው እንደዚህ ነበር። ቅዱስ ሄሬኔዎስም ከመምህሩ ከቅዱስ  ፖሊካርፕስ እግር ሥር ቁጭ ብሎ የተማረው ይህንኑ ነበር፣ በተግባር ያየውም እንደዚህ ነበር። ስለዚህ ቅዱስ ሄሬኔዎስም ሆነ ሌሎቹ ክርስቲያኖች ሁሉ የተረዱት ጌታችን በውኃ መጠመቅ ለዳግመኛ ልደትና መንግሥተ ሰማያት አስፈላጊ ነው ያለ መሆኑን ነው።በኒቂያውና በቁስጥንጥንያው የእምነት መግለጫ አንቀጽ ላይም "ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን።" ተብሎ የተገለጸው ከእነርሱ በፊት ከነበሩ አባቶችና እነዚያም ከሐዋርያት፣ ሐዋርያት ደግሞ ከጌታ የተቀበሉት አተረጓጎምና አረዳድ ነው። ከዚህ የቤተ ክርስቲያናዊ አረዳድ የወጡና መጽሐፍ ቅዱስን በራሳችን መንገድ እንተረጉመዋለን የሚሉ ፕሮቴስታንቶች ግን ከዚህ ተቃራኒ የሆነ ነገር ይዘው ብቅ በማለት አንዳቸው ትክክለኛው ይኸኛው ነው፣ ሌላቸው ደግሞ እርሱ ሳይሆን እንደዚህ ነው እያሉ ሁሉም የራሳቸውን ግምት በሰዎች ላይ ለመጫን ይደክማሉ። (መድሎተ ጽድቅ ቅጽ 2. ገጽ 99) ይቀጥላል... ✍ ተክለ ማርያም [ሐመረ ኖኅ ጅማ ኪዳነ ምሕረት] ከላይ እንደተገለጸው ተቃዋሚዎች "ውኃ" የተባለው ምሳሌያዊ እንጂ በቀጥታ አካላዊውን ውኃ አይደለም በማለት ተቃውሞን ያቀርባሉ። ውኃ ለመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ሆኖ "በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ። ይህ ግን በርሱ የሚያምኑት ሊቀበሉት ስላላቸው ስለ መንፈስ ተናገረ" ዮሐ. 7:38-39 ቀርቧል። ዳግመኛም "ውሃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት..." ዮሐ. 4:10-14 ውሃ በምሳሌያዊ መልኩ ተገልጿልና "ከውሃና ከመንፈስ ያልተወለደ..." ሲልም ውኃ" የተባለው ቀጥታ ውኃ ለማለት  ሳይሆን ምሳሌያዊ ነው መንፈስ ቅዱስን ወይም ጌታን ነው የሚያመለክተው ይላሉ
إظهار الكل...
ማስረጃ 2:-  በዮሐ. 3:5 ላይ "ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም።" የተባለው በውኃ ስለሚፈፀመው ጥምቀት እንጅ በምሳሌነት መንፈስ ቅዱስን ለማለት የተጠቀሰ አይደለም። ይህን ለመረዳት ጌታችን ይህን ለኒቆዲሞስ ሲነግረው "ውኃ" የተባለው በውኃ ስለሚፈጸመው ጥምቀት  ውጪ  ሌላ ትርጉም ቢኖረው ኖሮ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ  አብራርቶ በጻፈልን ነበር። ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን ሲጽፍ የተሳሳቱ ወይም ግራ የሚያጋቡ ሃሳቦች ሲኖሩ አስተካክሎ አርሞ ያልፋል እንጂ እንዲሁ አይተወውም። "...እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር" ዮሐ. 2:19-21፤ "...ስለ አብ እንደ ነገራቸው አላስተዋሉም።" ዮሐ.8:25-27 "እንቅልፍ ስለመተኛት የተናገረ መስሏቸው ነበር" ዮሐ. 11፡13:: "የአትክልት ጠባቂ መስሏት ነበር" (ዮሐ. 21፡33)  በማለት አብራርቶ ስሕተትም ካለ አርሞ የሚጽፍ ሐዋርያ ነው። ስለዚህም ከላይ 'ውኃ' የተባለው "መንፈስ ቅዱስ" ቢሆን ኖሮ በዮሐ. 7:37-39 ላይ እንደሰፈረው አብራርቶ ይጽፍልን ነበር። በዮሐ. 7:38 ላይ "የሕይወት ውሃ"  የተባለው መንፈስ ቅዱስ መሆኑን አብራርቶ ገልጾ ነበርና። ማስረጃ 3:- በዮሐ. 3:5 ላይም የተጻፈው በቀጥታ በውኃ ስለሚፈጸመው ጥምቀት ባይሆን ኖር አብራርቶ ይገልጸው ነበር። "በውኃና በመንፈስ"  የተባለው በቀጥታ በውኃ ስለመጠመቅ እንጂ ስለ መንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ሆኖ አለመቅረቡን ለመረዳት:- 1ኛ.  በዮሐ. 4:10-14 እና በዮሐ. 7:38-39 ላይ የሕይወት ውኃ (living water) እያለ ሲናገር በዮሐ. 3:5 ላይ ግን "ውኃ" በማለት ብቻ ነው የተባለው። ስለ መንፈስ ቅዱስ ሲናገር የሕይወት ውሃ እያለ ሲገልጸው በዮሐ.3:5 ላይ ደግሞ "ውኃ" ብቻ በማለት ምሳሌያዊ እንዳልሆነ ያስረዳናል። 2ኛ. በዮሐ. 4:10-14 እና በዮሐ. 7:37-39 ላይ በውኃና በሕይወት ውኃ (living water) መካከል በማነጻጸር ሲያስቀምጥ በዮሐ. 3:5 ግን እያነጻጸረ አልገለጸም ምክንያቱም "በውኃና በመንፈስ" በማለት የተገለጸው ምሳሌያዊ ሳይሆን በቀጥታ በውኃ ጥምቀት የሚፈጸመውን የሚያመለክት ነውና። 3ኛ. "በውኃና በመንፈስ" የተባለው ላይ "ውኃ" የተባለው ዮሐ. 7:38-39 ላይ "የሕይወት ውኃ" ተብሎ እንደተገለጸው መንፈስ ቅዱስን ለማመልከት ቢሆን ኖሮ "እና" በሚል አያያዥ ቃል ባልተጠቀመ ነበር። ምክንያቱም ውኃ የተባለው መንፈስ ቅዱስ ቢሆን ኖሮ "በውኃና በመንፈስ" በማለት አይገልጽም ነበር። ድግግምሽ ይሆናልና። ይልቁኑ በውሃና በመንፈስ የተባለው በጥምቀት የመንፈስ ቅዱስ ልጅነትን የምናገኝበትን የሚያመለክት ቃል ነው። ✍ ተክለ ማርያም [ጅማ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት]
إظهار الكل...
ጾመ ገሃድ /ጾመ ድራር ጥምቀት/ ገሃድ ማለት የቃሉ ትርጉም መግለጫ፣ ግልጥ፣ ልዋጭ፣ ይፋዊ በገሃደ የሚታወቅ ነገር ማለት ነው። የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ መገለጥን የምናስብበት ነው። አንድም ጋድ ተብሎም ይጠራል፤ ጥምቀት ረቡዕ ዓርብ ቢውል በዚያ ለውጥ ማግሰኞና ሐሙስ ይጾማልና። ጋድ /ጾመ ድራር ጥምቀት/ይህ ጾም የአምላካችን የጌታችንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀት በማሰብ የጥምቀትን ዋዜማ ከምግብ መከልከል ነው። የሚቆርብ ሰው አክፍሎ የሚያድር ስለሆነ የጥምቀት ድራር /ዋዜማ/ ጾም ነው። የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ዕለት በሚውልበት ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ ማግሰኞንና ሐሙስን በመጾማችን ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል። በዚህም የጾምና የበዓል ማክበር ይከናወንልናል የጥምቀት ዋዜማ ሰኞ ማግሰኞ፣ ሐሙስ ከሆነ ጾም ነው በአጋጣሚ ደግሞ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ከጥሉላት ምግቦች ብቻ ይጾማል። ሆኖም ጥምቀት በየትኛውም ዕለት ቢውል በየዓመቱ ሁልጊዜ የጥምቀትን ዋዜማ እስከ ዕርበተ ፀሐይ እንጾም ዘንድ አባቶቻችን በረከታቸው ይደርብንና ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ይሆን ዘንድ ሥርዓትን ሠርተውልናል። ስለሆነም በ2015 ዓ.ም የጌታችን በዓለ ጥምቀት ጥር 11 ቀን በዕለተ ሐሙስ ስለሆነ ጾመ ጋድ /ገሃድ/ ጥር 10 ቀን 2015 ዓ.ም በዕለተ ረቡዕ ይሆናል ማለት ነው። ዕለተ ረቡዕ ራሱን የቻለ የጾመ ድኅነት ቀን ሲሆን በዚህ ዓመት ጾመ ገሃድ በዚህ ዕለት ውሏልና ዕለቱ ጾመ ድኅነትና ጾመ ገሃድ የተገጣጠሙበት ዕለት ሆኗል። መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም’’ 1ኛ ቆሮ. 8፥8 በሰላም በጤና አድርሶ ጾሙን ጾመን የጌታችንን በዓለ ጥምቀት እናከብር ዘንድ የእርሱ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፤ አሜን ስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
إظهار الكل...
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሰን። መልካም በዓል ይሁንላችሁ።          🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀          🍀እ🍀🍀ሰ🍀🍀ይ🍀🍀🍀🍀          🍀የ🍀🍀ም🍀🍀ሥ🍀ራ🍀ች🍀          🍀ተ🍀🍀ወ🍀🍀ለ🍀🍀ደ🍀🍀          🍀🍀🍀ጌ🍀🍀🍀🍀ታ🍀🍀🍀
إظهار الكل...
ታህሳስ 19 ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሰለስቱ ደቂቅን ከዕቶን እሳት ያዳነበት ዕለት ፡ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል ጌታና አገልጋይ ማለት ነው፡፡ "ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?”ተብሎ እንደተፃፈው (ዕብ. 1፡14)፤ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ፤ ቅዱሳን ሰማዕታት ገድላቸውን እንዲፈፅሙ እሳቱን እና ስለቱን ፈርተው ወደኋላ እንዳይመለሱ ይረዳቸዋል። ከሰባቱ ሊቃነመላዕክት በተራዳዒነቱና በአማላጅነቱ ያዘኑትን ለማፅናናት ፤ የምስራች ለመናገር ከእግዚአብሔር የሚላከው አንዱና ዋነኛው በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው መልአክ ይህ  ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በዚህ ቀንም ሰለስቱ ደቂቅን ከዕቶን እሳት ያዳነበት እለት በመሆኑ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዓመታዊ በዓል በመባል በፀሎትና በምስጋና በደማቅ ሁኔታ ታከብራለች፡፡            የታሪኩ መነሻ እንዲህ ነው .      ባቢሎንን ይመራ የነበረው ናቡክደነፆር በእግዚአብሔር የማያምን ጣዖትን የሚያመልክ ንጉሡ ነበር፡፡ በወቅቱም ቁመቱ ስልሳ ወርዱ ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቅ ምስል በማሰራት ሕዝቡ እንዲሰበብ በማዘዝ ሁሉም ሰው ላሰራው ጣዖት መስገድ እንዳለባቸው ይህን በማይፈፅሙት ላይ ቅጣቱ ከባድ እንደሆነ አዋጅ አሳወጀ፡፡ የንጉሡ አስተሳሰብ ለእግዚአብሔር ወዳጆች ከባድ ፈተና ቢሆንም እውነተኛዎቹን አማኞች ግን በእግዚአብሔር ላይ ያላቸው እምነት ሊቀይረው አልቻለም፡፡  ቅጣቱንም በማሰብ እና በመፍራት ሁሉም እግዚአብሔርን በመካድ ለጣዖቱ ሰገዱ አረበረቡ፡፡ ✍️በዚህ ፈታኝ ዘመን ነበር አናንያ ፣ አዛርያን እና ሚሳኤል የተባሉ ሶስት ወጣቶች ግን ለእግዚአብሔር ያላቸውን መታመን አሳዩ፡፡ ለጣዖቱ ያልሰገደ ወደ እቶን እሳት ተጥሎ እንደሚሞት ቁርጥ ያለ ወሳኔ እንደሆነ ቢያውቁም ያለምንም ፍርሃት በአንሰግድም አቋማቸው በመፅናት "ንጉስ ሆይ የፈጠረንን አምላካችንን ክደን አንተ ላቆምከው ጣኦት አንሰግድም !" አሉት፡፡ በሶስቱ ወጣቶች ድርጊትና ድፍረት በጣም የተቆጣው ንጉስ ናቡክደነፆር አገልጋዮቹን ጠርቶ እሳቱ ሰባት እጥፍ እንዲነድ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ወደ እሳቱም እንዲከቷቸው አዘዘ፡፡ የንጉሱ አገልጋዮች ሶስቱን ወጣቶች አናንያን ፣ አዛርያን ፣ ሚሳኤልን እያንከበከቡ ወደ እቶን እሳቱ ወረወሯቸው፡፡ እሳቱ ከነበረው ኃይል የተነሳ ወላፈኑ አገልጋዮቹን እዛው እንደ ማገዶ አነደዳቸው፡፡ ✍️ሠለስቱ ደቂቅ ግን ከየት እንደመጣ ካልታወቀ እንግዳ ጋር በመሆን በዕቶን እሳቱ ውስጥ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በደስታ ይመላለሱ ጀመር፡፡ ይህም ተአምር ንጉሡን እና መኳንንቶቹን እንዴት ሊሆን ቻለ ብለው ተገረሙ፡፡ ንጉሡም በዚህ ወቅት በመደነቅ " እነሆ እኔ በእሳቱ መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች ይታዩኛል፡፡ እሳቱ ምንም አልጎዳቸውም ፡፡ አራተኛው ግን የአማልክትን(የእግዚአብሔርን) ልጅ ይመስላል፡፡ " አለ፡፡ ንጉሥ ናቡክደነጾር በግልፅ ተመልክቶ  እንደመሰከረው የነደደውን እሳት በማብረድ ለሠለስቱ ደቂቅ ቤዛ የሆናቸው ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ✍️እርሱ ስለመሆኑ ለነቢዩ ዳንኤል በተገለጠበት ግርማ ማረጋገጥ እንችላለን፡፡ ናቡከደነፆርም ወደ እሳቱ እቶን በመቅረብ እነዚህ ብላቴኖችን “እናንተ የልዑል አምላክ ባሮች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ኑ ውጡ ብሎ ተናገራቸው፡፡” እንዲል ! ✍️የቅዱስ ገብርኤል አምላክ ባሮች ማለቱ ነው!። እርሡም ስለ ሃይማኖታቸው መከራ የተቀበሉትን የአግዚአብሔር ወዳጆች በእምነት የሚያፀና ታላቅ መልአክ ነው፡፡ እኛስ ከዚህ  ቅዱሰ ታሪክ ምን እንማር? ዛሬስ ከነደደ እሳት ባልተናነሰ መከራና ችግር ውስጥ ገብተን በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ከሞት ስጋ ነፍስ ድነን በመልዓኩ ስም በፈለቀ ጸበል ተጠምቀን ደዌ በሽታ ጭንቀትና ሀዘን የራቀልን እጅግ ብዙዎች አይደለንምን ? ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን መንጎቹዋ የእምነትን ፍሬ ከእነዚህ ብላቴኖች ተምረው እግዚአብሔርን በማምለክ እንዲጸኑና የመልአኩን የቅዱስ ገብርኤልን ተራዳኢነት እንዲረዱ በታኅሣሥ 19 ቀን ይህን ዕለት ትዘክራለች፤ በታላቅ ድምቀትም ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እምነት በድርጊት ሊታይ የሚገባው ክርስቲያናዊ ተግባር ነው፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ አምናለሁ የሚል ሁሉ ካመነበት ጊዜ አንስቶ ክርስቶስን መስሎ ለመኖር ሊተጋና መስሎ ሊመላለስ ይገባዋል፡፡ ✍️በሠልስቱ ደቂቅ የታየው እምነት በአንድ ጀምበር የተገነባ እምነት ሳይሆን ከልጅነታቸው ጀምሮ በአንድ እግዚአብሔር ታምነው በቅድስና ሕይወት በመመላለስ የመጣ እምነት ነው፡፡ እነዚህ ብላቴኖች በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያገኙትን የድል አክሊል ተስፋ አድርገዋልና አርባ ዘጠኝ ክንድ ያህል የነደደውን የእሳት እቶን አላስፈራቸውም፤ በእግዚአብሔር ላይ ያላቸው ጽኑ እምነት በእሳት ተቃጥለው ለመሞት እንኳ አስጨከናቸው እንጂ፡፡ እንዲህም ሆነው በመገኘታቸው በእምነታቸው እግዚአብሔርን ደስ አሰኙት፤ ስለዚህም ነው እግዚአብሔር ባለሟሉን ቅዱስ ገብርኤልን በመላክ ከእሳቱ እቶን የታደጋቸው፡፡    ወስብሐት ለእግዚአብሔር !!! #የ፲፮ቷ ነኝ ✍✍✍✍✍ 💚@Geztub💚 💛@Geztub💛 ❤️@Geztub❤️ ✍✍✍✍✍
إظهار الكل...