cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

እስላማዊ እውቀት

▶በዚ ቻናል ♦የተለያዩ እስላማዊ አባባሎች ♦ያልተሰሙ ታሪኮች ፣ ♦ምክሮች ፣የሊቃውንት ንግግር፣ ♦የረሱላችን ሀዲስ ♦የታብዬች ታሪክ ይዘንላቹ እንመታለን ♠በተቻለን አቅም ቶሎ ቶሎ እናቀርባለን ። ያላችሁን አስተያየት @rexu65 @meqasid 👆👆👆

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
261
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

🚫:::::::::::ድንግል/ቢክራ አላገኘዉባትም:::::::🚫 ልጅ አገረድ አገባ ግን (ቢክራ) ድንግል አላገኘባትም ?? ሸይኽ ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ) ተጠየቁ :- ➪ ጥያቄ:- ሰውየው ልጅ አገረድ አግብቶ ድንግል ሁና ካላገኛት ምን ማድረግ ነው ያለበት ? ➪ መልስ:- ይሄ ብዙ ምክኒያቶች ይኖሩታል : ድንግሏ ምናልባት ያለ ዝሙት ሊፈርስ ይችላል። የልጂቱ ውጫዊ ስብዕናዋ መልካም ከሆነ እናም በዲኗ የተስተካከለች ከሆነች በሷ ላይ ጥሩ ግምትና መልካም ጥርጣሬን ማሳደር የግድ ነው። በዚያ ላይ ጥሩ ጥርጣሬን ማሳደር ግድ ይላል። - ወይንም አፀያፊውን ዝሙት ሰርታ ከዚያ አላህ መርቷት ከሰራችሁ መጥፎ ተግባር ተፀፅታና ቶብታም ሊሆን ይችላል። ከዚያም ወደ ጥሩነትና መልካምነት ከተቀየረች (ቢክራ) ድንግል አለመኖሯ እሱን አይጐዳውም። - ምናልባትም ድንግሏ በወር አበባ ብርታት ምከንያት ፈርሶ ሊሆን ይችላል። ጠንካራ (ሃይድ) የወር አበባ (ቢክራን)ድንግልን ያፈርሳል። ይሄህ ኡለሞች አውስተውታል። - ልክ እንደዚሁም በአንዳንድ ዝላዮች ድንግል ሊፈርስ ይችላል። ከሆነ ቦታ ወደሆነ ቦታ ስትዘል። ወይንም ከከፍተኛ ቦታ ወደ ዝቅተኛ ቦታ በምትወርድ ጊዜ በዚህ አጋጣሚ ድንግል ሊፈርስ ይችላል። ➪ ስለዚህ የድንግል መፍረስ የግድ በአፀያፊው ዝሙት ብቻ ሊሆን አይችልም። በጭራሽ። ከዝሙት ውጭ በሆነ ክስተት ነው ድንግል የፈረሰው ካለች ወይንም በዝሙት ነው ድንግሌ የፈረሰው ግን ተገድጄ እና ተደፍሬ ነው ካለች ይሄ እሱን አይጎዳውም። - ወይንም በፍላጎቷ ዝሙት ሰርታ ከሆነ ድንግሏ የፈረሰው ግን ያንን ያደረገችው በማታውቅበትና በመሃይምነቷ ጊዜ እንደሆነም እናም አሁን ከዚያ ቶብታና ተፀፅታ ከሆነ ይሄም እሱን አይጎዳውም። - ይሄን የሷን ሚስጥር ሊበትንባት እና ሊያሰራጭባት አይገባም ይልቁንስ ሊደብቅላት ይገባል። በእርሱ ግምት እውነተኛነቷንና ቅንነቷን እናም መስተካከሏን ካመነበት ከእርሱ ጋር ያስቀራታል። ካሎነ ግን በሷ ላይ ያደረበት ግምት ጥሩ ካልሆነ ይፈታታል የሷን ሚስጥር ከመደበቅና ከመጠበቅ ጋር በጭራሽ ሚስጥሯን ባደባባይ መግለፅ አይገባውም። ምንጭ፡- መጅሙዕ አል-ፈታዋ (287/286-30) @anesmuslim @anesmuslim
إظهار الكل...
እስላማዊ እውቀት ▶በዚ ቻናል ♦የተለያዩ እስላማዊ አባባሎች ♦ያልተሰሙ ታሪኮች ፣ ♦ምክሮች ፣የሊቃውንት ንግግር፣ ♦የረሱላችን ሀዲስ ♦የታብዬች ታሪክ ይዘንላቹ እንመታለን ♠በተቻለን አቅም ቶሎ ቶሎ እናቀርባለን ። ያላችሁን አስተያየት @rexu65 @meqasid 👆👆👆 https://t.me/anesmuslim
إظهار الكل...
እስላማዊ እውቀት

▶በዚ ቻናል ♦የተለያዩ እስላማዊ አባባሎች ♦ያልተሰሙ ታሪኮች ፣ ♦ምክሮች ፣የሊቃውንት ንግግር፣ ♦የረሱላችን ሀዲስ ♦የታብዬች ታሪክ ይዘንላቹ እንመታለን ♠በተቻለን አቅም ቶሎ ቶሎ እናቀርባለን ። ያላችሁን አስተያየት @rexu65 @meqasid 👆👆👆

ሙላ ነስሩዲን ክፍል 3 ሙላ ነስሩዲን ከሒወት ገጠመኙ ሁሉ ዘውትር አስበልጦ የሚማረርበት ነገር ቢኖር የትዳር ሂወቱ ነው ። ነፃነቱ በሚስቱ ፍላጎት በትዳሩ የተነጠቀ ሰው ሆኖ የምናገኘው ነስሩዲን እስኪ ጥቂት ወጎች ስንመለከት ብዙዎች በነስሩዲን የትዳር ቀልዶች " ትዳር " በሚባለውና አንድ ወንድ አና ሴት ወደው እና ፈቅደው የሚገቡበት ተቋም ላይ በድብቅ የሚብሰለሰለውን ጉዳይ ይፋ መውጣቱ ይመስለናል ። አንድ ቀን የነስሩዲን አህያ ጠፍቶ በከፋተኛ ሀዘን ተውጦ መጮህና ማልቀስ ይጀምራል ። በዙርያው የሉት ሰዎች ሊያፅናኑት ቢሞክሩም አሻፈረኝ ብሎ ማልቀሱን ቀጠለበት የቅርብ ጓደኛው ወደሱ ቀረብ ብሎ እጁን የዘው ። "ስማ ነስሩዲን "አህያህ በመጥፋቱ እደዚህ ያዘንከው ለምንድነው አልገባኝም ፤ የመጀመሪያዋ ሚስትህ አራሱ ስትሞት አንደዚ አዳላዘንክ ልብ ብለኸዋል" አለው። ነስሩዲንም ፦ "ነገር ግን ሚስቴ ስትሞት ሁላቹም ሌላ ሚስት እናመጣለን እያላችሁ ትፅናኑኝ ነበር፣ ዛሬ ግን ማንም ሌላ አህያ አመጣልሀለው የሚለኝ አላገኘሁም " በማለት ለቅሶውን ቀጠለ ። እንግዲህ የነስሩዲን የትዳር ዋጋ እንዲህ ዚቅ ያለበት ምክንያት ምናልባት የትዳር ህይወትን የተመለከተበት መነፅር ከሌሎች እጅጉን የተለየ መሆንን መገመት ይቻላል ። ወደ ቀጣዩ የነስሩዲን ወግ እንለፋ ። ነስሩዲን አንድ ቀን ወደሰፈሩ ዳኛ ዘንድ በመሄድ ከሚስቱ ጋር መፋታት እንደሚፈልግ ይነግራቸዋል ። ዳኛውም ነገሩን ካዳመጡ ቡሃላ የነስሩዲንን ጥያቄ በመቀበል እሳቸው በተራቸው ይጠይቁት ጀመር ። "ለመሆኑ የሚስትህ ስም ማን ይባላል ?ብለው ዳኛው ጠየቁት ። ነስሩዲንም "አለቃትም" ሲል መለሰላቸው ። በሰውየው ምላሽ የተደነቁት ዳኛው ግራ በመጋባት "አብራቹ ስትኖሩ ስንት አመት ሞላቹ? በማለት ጠየቁት " ነስሩዲንም ፦ ይ ቀ ጥ ላ ል ....ይቀጥላል ..... @anesmuslim @anesmuslim @anesmuslim
إظهار الكل...
💎"ትዕግስት ይኑርህ ሁሉም ነገሮች ቀላል እስኪሆኑ ከባድ ነበሩ" ይለናል ፐርዢያዊው ገጣሚ ሰዓዲ። የጎደለህ ትንሽዬ ትዕግስት ነው እንጂ የምትፈልገው ነገር ካንተ አያመልጥም! ታገስ ማለት ግን ቁጭ ብለህ ተመልከት አይደለም፤ ጥረትህን ሳታቆም ጠብቅ ነው። የእናንተው ምርጥ ጓደኛ! @anesmuslim @anesmuslim
إظهار الكل...
......💡💡💡ትኩረትህን💡💡💡.... 1 በየቀኑ ከምናደርጋቸውና ቅድሚያ ከምንሰጣቸው ነገሮች መካከል አብዛኞቹ ነገሮች ለምንፈልገው አላማና ለግባችን ምንም ግብአት የማይሆኑና ሲያልፍም አስፈላጊ ያልሆኑ እንደሆነ ያጠኑት ይናገራሉ። ግብን አስቀምጦ ወደ ስኬት የሚጓዝ ሰው አስፈላጊ እና ወደ ግቡ የሚመሩትን ተግባራት ቅድሚያ ተሰጥቶ የእለት እለት ተግባሩ ሊያደርጋቸው ይገባል። 2 በተመሳሳይ መልኩ አብዛኞቻችን በኛ ቁጥጥር ስር ባልሆኑ ነገሮች ስንያዝና ስንጨነቅ እንውላለን። በመሆኑም በኛ ቁጥጥር ስር ባልሆኑ ነገሮች ስንጠበብ በቁጥጥራችን ስር በሆኑትና ማስተካከል ለምንችላቸውን ነገሮች ሳናስተካክል እንቀራለን። . ስለዚህም የምታደርጋቸውን ነገሮች መርምር ፤ ውሎህን አስተውል። ትኩረትህን አስፈላጊ በሆኑና መቆጣጠር በምትችላቸው ነገሮች ላይ አድርግ። @anesmuslim @anesmuslim @anesmuslim
إظهار الكل...
ሙላ ነስሩዲን ክፍል 2 ነስሩዲን ፦" ሁለት" ፈላስፋው ፦"እዴት ሆኖ ?አስረዳኝ !" ነስሩዲን ፦ለኔ የመጀመርያው የአለም መጨረሻ ሚስቴ ስትሞት ነው ። ሁለተኛው ደግሞ እኔ ስሞት ይሆናል ። በቀልድ ተዋዝቶ በቀረበልን የነስሩዲን ምላሽ ውስጥ አንድ የምንረዳው ቁም ነገር እያንዳንዱ ሰው የአለም መጨረሻ መገለጫው የራሱ ህልፈተ ህይወት እጂ ሌላ አደለም የሚለውን ነው። አንድ ቀን በመንደሩ በጠቢብእነቱ የሚታወቅ አንድ ሰው ወደ ሙላ ነስሩዲን ቤት በመምጣት ስለ ሰፈሩ ፣ስለ ግል ህይወታቸው ፣ ስለ ቤተሰብ ፣ስለ ስራ እዳሁም ስለ ፍልስፍናዊ እርዕሰ ጉዳዮች ሲወያዩ ቆይተው ሰውየው ለመሄድ ተነሳ "ነስሩዲን "አሁን ወደቤት መሄድ ይኖርብኛል " አለ ሰውየው "ይቅርታ ወዳጄ " አለ ነስሩዲን በበኩሉ እየተነሳ "ግን አንተ መነህ ?በማለት ጠየቀው " "የኔን ማንነት አላቅም እያልክ ነው " በማለት ነስሩዲንን ግራ ተጋብቶ ይመለከት ጀመር ። "በፍጹም አላቅክም" አለ ሙላ ነስሩዲን በድጋሚ ። "እስካሁን በብዙ ጉዳዮች ላይ መውጋታችንንስ እረስተኸዋል?"በማለነት ነስሩዲንን ጠየቀው ። "በርግጥ ልብስህ ፣ጫማህ ፣አለባበስህ እና ድምፅህን ስመለከት የማቅቅ መስሎኝ ነበር ""አለው ነስሩዲን ፈርጠም ብሎ ። ""ማንን ይሁን" አለ ሰውየሙ ባለመታወቁ ቅር ብሎት። ""እኔን"አለ ነስሩዲን ። የነስሩዲን የሂወት ምልከታዎች ከማንኛውም ተራ ሰው የተለየ መሆናቸውን የምንረዳው በደነዚ አይነት አስተሳሰቦች ጢያጋጥሙን ነው ።ከዚ ጋር አብራ የምትሄድ ተመሳሳይነት ያላትን የነስሩዲን ፍልስፍና እዚህ ላይ እንመልከት ። አንድ ቀን ነስሩዲን በመንገድ ለይ አንድ ትልክ የሂዱይዝም መነኩሴ ያገኛል። ሰላምታ ከተለዋወጡ ቡሀላ" ይገርምሃል !"ከራሴ ፈፅሞ የመላቀቅ ደረጃ ላይ ደርሻለሁ ።በዚህም ስለ እራሴ ማሰብም ማሰላሰል በማቆመ አዕምሮዬ በሌላው የሰው ልጅ ነገር የተያዘ ሆኗል ።በእኔም ወስጥ የምመለከተው ሌሎችን ነው አሉት ። "ነስሩዲንም " ይገረሞታል እኔ ከዚ የበለጠ ደረጃ ላይ ጀርሻለው አለው " በዚ ጊዜ መምህሩ ተደንቀው" እንዴት ሆኖ !"አሉት። ነስሩዲንም "አንድ ሰው ተመልክቼ በእርሱ ውስጥ እራሴን ማየት ችያለሁ "።"በዚህም ከምንግዜውም በለይ ስለ እራሴ ብቻ መሰብ ችያለሁ ""አላቸው ። ኤንዲህም የቱንም ያህል በዕውቀት የማንቃት ደረጃችን የላቀ ይሁን የሰው ልጅ ከራሱ አስበልጦ ስለሌላው መሰብ የሚችል አቅሞ እደሌለው ነስሩዲን ተረዱ ይለናል ። ወደ ነስሩዲን የግል ህይወት ደግሞ አንምጣ ይ ቀ ጥ ላ ል @anesmuslim @anesmuslim @anesmuslim
إظهار الكل...
ሊነበብ የሚገባው ታሪክ ሱፊዝም ከሚለው መፅሐፍ የተወሰደ ከጲላጦስ መላ ነስሩዲን ታሪክ ክፍል 1 ነስሩዲን በተለይ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ዘንድ በጠቢብእነቱ የሚታወቅ እና 1300 ዓ.ም በተለይ በዛሬዋ ኢራን አብዛኛውን የሂወት ዘመኑ እደኖረ የሚታመን ጠቢብ ሰው ነበረ።ነስሩዲን በተለያየ የሂወት ገጠመኞቹ ውስጥ የሚሰጣቸው መልሶች ገጠመኞቹንም የሚመለከትበት አቅጣጫ እውነትም ጠቢብነቱንእና የተለየ አሳቢነቱን የሚያሳይ ነው። የሚሉ እስከዘመናችን ድረስ የዘለቁ አሳቢያን በርካታ ናቸው። ለዚህም ነው የነስሩዲን ቀልዶች እና ወጎች ሰምተን በፈገግታ ማለፍ ብቻ ሳይሆን በፍልስፍናዊ ምልከታም አንደነቅበት ዘንድ ግድ የሚለን። በነስሩዲን ዘመን በጥበብ የታነፀ በእውቀትም የነቃ ሰው በማህበረሰቡ የሚገባውን ቅብር የሚቸርበት መንገድ ዘንድ አንዱ ለስም የሚሰጠው ሌላ የክብር ወይም የማእረግ መጠርያ ነው። መላ፣ሆጃ ወይም ሆካ የሚሉት ማእረጎች ከስሙ በፊት መጠርያ የደረገ ሰው ጠቢብ ሰው መሆኑን ማህበረሰብ ለመለየት የሚቸገር አይሆንም ። ለዚህም ነበር "መላ " የሚለው ማእረግ ከመካከለኛው ምስራቅ ባሉ ሀገራት ሁሉ ተጎናጽፎ የኖረው። ይሁንና ነስሩዲን ጠቢብነት ደግሞ መገለጫው የተለያየ መልክ እደነበረው መስታወስ ያሻል። አንዳንድ ግዜ የእጅግ ጠቢብ ሆኖ የምናገኘው መላ ነስሩዲን በሌላ ቦታ ደግሞ ቀልደኛ ወይንም ሞኝ ሆኖ መየታችን የጠቢብ መምህር ወይም የፈሀላስፋ ባህሪ ከዚ የራቀ አለመሆኑን እንረዳለን ያደርገናል እጂ ለሱ ያለንን ግምት ዝቅ ለማየደርግ አይሆንም። አብዛኛውን የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የመላ ነስሩዲን ቀልዶች ፣ወጎች ተረቶች በስፋት ከመነገራቸው የተነሳ እደራሳቸው ሴጋ አርግተው ይናገሪሉ። መላ ነስሩዲን አንድ ቀን ስለ አለሞ መጨረሻ የተጠየቀውን እንመልከት ፦ ፈላስፋው ፦ መላ " የአለም መጨረሻ መቼ ነው ትላለክ? ነስሩዲን ፦ስለየትኛው የአለም መጨረሻ ነው የምትጠይቀኝ? ፈላስፋው ፦ስንት የአለም መጨረሻ ነው ያለው? ነስሩዲን ፦ ይ ቀ ጥ ላ ል @anesmuslim @anesmuslim @anesmuslim
إظهار الكل...
ማንኛውም ሰው ከሰው ልጅ የምላስ ጩቤ አያመልጥም። ለጋስ ቢሆን ብኩን ነው :ዝምተኛ ቢሆን ደደብ ነው:ጥሩ ተናጋሪ ቢሆን ወሬኛ ከማለት አይመለሱም። ስለዚህ የሰዎችን ስድብ ወይም ሙገሳ አታዳምጥ እናም ከሁሉም በላይ አላህን ፍራ ልቅናው የሱ ነው። @anesmuslim @anesmuslim
إظهار الكل...
ከኒካህ በፊት ያለ የፍቅር ቅዠት ማዕከላዊ እስር ቤት ሲሆን ከኒካህ በኃላ ያለው ንፁህ ፍቅር ግን ምድራዊ ጀነት ነው ሀላልን የመረጠ ሁሌም አላህ ኸይሩን እንዳገራለት ይኖራል ጌታዬ ሆይ ከቅዠቱ ፍቅር ጠብቀን አደራ በሀላሉ አብቃቃን። በእርሱም ሰትረን ልባችንን በኢማን አጽናልን ያኢላሂ። አላሁመ አሚን @anesmuslim @anesmuslim
إظهار الكل...
1442ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ ነገ ሀምሌ 13 ቀን 2013 ዓ/ም ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ ለዘጠኝ ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል❗️ ⚡️ህብረተሰቡ ይህንን አውቆ እንዳይደናገጥ እና የጸጥታ አካላትም የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል። @anesmuslim @anesmuslim
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.