cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Beshale # Grade 10 History class 2016 E.c

مشاركات الإعلانات
284
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Take Care !!
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም #በዛሬዋ_ዕለት ከ 93 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የንግሥ በዓል ዋዜማ ፤ የንጉሠ ነገሥት የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሐውልት በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ፤ ለበዓል የመጡት እንግዶች በተገኙበት ሥርዐት፣ የሐውልቱን መጋረጃ የመግለጥ ክብር ለብሪታንያ ንጉሥ ወኪል ለ(ዱክ ኦፍ ግሎስተር) ተሰጥቶ ሐውልቱ የተመረቀበት ዕለት ነበር። የዳግማዊ አጤ ምኒልክ መታሰቢያ ሀውልት የቆመው/የተተከለው ከዛሬ 93 ዓመታት በፊት ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም ነበር፡፡ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ የአባታቸውን የዳግማዊ አጤ ምኒልክን ስራና ውለታ ቀጣዩ ትውልድ ያስበውና ይዘክረው ዘንድ … ማስታወሻ የሚሆን የመታሰቢያ ሐውልት ለማሰራት አሰቡ፡፡ ሐውልቱንም በጀርመናዊው መሃንዲስ ሙሴ ሄንትል አማካኝነት አስጠንተው፤ ከጀርመን ተቀርፆ እንዲመጣ አዘዙ፡፡ ሀውልቱ የተመደበለት ቦታ ተደልድሎ ከተዘጋጀ በኋላ ገና ሳይተከል/ሳይቆም ንግሥቲቱ መጋቢት 22 ቀን 1922 ዓ.ም አረፉ፡፡ በመሆኑም የንግሥቲቱን እረፍት ተከትሎ ንጉሰ ነገሥት ለመሆን እየተዘጋጁ የነበሩት አልጋ ወራሽ ንጉሥ ተፈሪ መኮንን፣ ከዛሬ 93 ዓመታት በፊት (ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም) ሐውልቱ በታላቅ ክብረ በዓል እንዲተከል አደረጉ፡፡ በሐውልቱ ላይ አፄ ምኒልክ ካባ እንደለበሱ አንባር አጥልቀው በእጃቸው ጣምራ ጦር ይዘው በፈረሳቸው በ‹አባ ዳኘው› ላይ ተቀምጠው በግርማ ሞገስ ይታያሉ፡፡ የሐውልቱ ቁመት ከተፈጥሮ አካላዊ መጠን በላይ ሲሆን ‹አባ ዳኘው› ፊቱን ወደ ሰሜን መልሶ በኋላ እግሮቹ ቆሞ፣ የፊት እግሮቹን ወደላይ አንስቶ ይታያል፡፡ ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት በ 1929 ዓ.ም ወድቆ/ፈርሶ ነበር፡፡ ብርሃኑ ድንቄ ‹‹የአምስቱ የመከራ ዓመታት አጭር ታሪክ›› በሚለው መጽሐፋቸው ጣሊያኖች የአፄ ምኒልክን ሐውልት እንዴት እንዳፈረሱት እንደሚከተለው ገልፀውታል፡፡ ‹‹ … በቅድሚያ ሐውልቱ ያለበትን አካባቢ ረጅም እንጨት እየማገሩ በቆርቆሮ ሲያጥሩ ሰነበቱ …. ይህንን ያየው የአዲስ አበባ ሕዝብ ‹‹ሊያፈርሱት ነው›› ብሎ እርስ በእርሱ በሐዘን መነጋገሩን ቢሰሙ ‹‹ልናድስ›› ነው ብለው አስወሩ፡፡ ሁሉንም ነገር ካመቻቹ በኋላ ግን በየበሩ በታንክ ጭምር ጥበቃ አጠናክረው … ወደ ማታ የአራዳን አካባቢ በታንክ አጥረው በባውዛ ሌሊቱን ከተማውን እየተቆጣጠሩ በሌላ ኃይል ደግሞ ሐውልቱን ሲያፈርሱ አድረው ሲነጋጋ ወደ አልታወቀ ቦታ ወስደው ቀበሩት፡፡ ሕዝቡ እድሜና ፆታ ሳያግደው ሐዘኑን ይገልጽ እንደነበር አዛውንቶች ይመሰክራሉ … በጊዜው የአዲስ አበባ ነዋሪ የነበረው የሃንጋሪው ዶክተር ላዲ ስላስ ላቫ እንደፃፈው፣ ሐውልቱ ከፈረሰበት ቦታ ቆመው ያለቅሱ የነበሩትን ሰዎች የጣሊያን ወታደሮች በኃይል ይበትኑ እንደነበር ገልጿል፡፡ በሌላ ዘገባ ደግሞ አንድ ሕፃን ልጅ ሲያለቅስ ጣሊያኖች ደርሰው ለምን እንደሚያለቅስ ቢጠይቁት ‹‹የንጉሱን ምልክት ስላወረዳችሁ ነው›› ብሎ እንደመለሰላቸውና ጣሊያኖችም ከሙሶሊኒ ሌላ ንጉሥ እንደሌለው በመንገር ልጁን ገርፈው እንዳባረሩት ተገልጿል፡፡ ጣሊያኖች ሐውልቱን ካፈረሱ በኋላ ሰው ሳያይ ሸፍነው በመውሰድ በታላቁ ቤተ-መንግሥት አዳራሽ ጀርባ ቀበሩት …›› የፋሺስት ወራሪ ኃይል ከኢትዮጵያ ከተባረረ በኋላም፣ ሐውልቱ ከተቀበረበት ቦታ ወጥቶ እንደገና ታድሶና ተጠግኖ ሚያዝያ 27 ቀን 1934 ዓ.ም ቀድሞ በነበረበት ቦታ እንዲቆም ተደረገ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ በ1988 ዓ.ም የአድዋ ድል መቶኛ ዓመት ሲከበር ሐውልቱ ጥገና ተደርጎለት እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ #ታሪክን_ወደኋላ
إظهار الكل...
Repost from N/a
👉 በሀገራችን ኢትዮጵያ ታሪክ በየስራ ዘርፉ ቀደምት ፈር ቀዳጆች ፦ 1. የመጀመሪያው ሃኪም ሃኪም ወርቅነህ እሸቴ 2. የመጀመሪያው ኢትዮጵያ ሬዲዮ ዜና አንባቢ ክቡር ኮ/ር ከበደ ሚካኤል 3. የመጀመሪያው ዘመናዊ ሰዓሊ አቶ አገኘው እንግዳ 4. የመጀመሪያው ኢትዮጵያ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን አሰልጣኝ አቶ ገመዳ ጉተማ 5. የመጀመሪያው ህጋዊ የመንጃ ፈቃድ ያለው የኢትዮጵያ የመኪና አሽከርካሪ ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ 6. የመጀመሪያዎቹ አውሮኘላን አብራሪዎች አሰፋው አሊና ሚሽካ ባቢችፍ 7. የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፖትርያሊክ ቡፅዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ 8. የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት የኦሎምፒክ ባለወርቅ ሸለቃ ደራርቱ ቱሉ 9. የመጀመሪያው የህትመት ጋዜጠኛ ካንቲባ ደስታ ምትኬ 10. የመጀመሪያዋ ሴት አውሮኘላን አብራሪ ወ/ሮ ሙሉ እመቤት እምሩ 11. የመጀመሪያዋ የረጅም ልብወለድ ደራሲ ወ/ሮ ፀሀይ መላኩ 12. የመጀመሪያው የረጅም ልብ ወለድ ደራሲ ነጋድረስ አፈወርቅ ገብረየሱስ 13. የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ሃኪም ውዳድ ኪዳነ ማሪያም 14. የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ መሃንዲስ ብርነሽ አስፋው 15. የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ጋዜጠኛ ሮማን አስፋው 16. የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የትያትር ተዋናይ ሰላማዊት ገብረ ስላሴ 17. የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ዳኛ ዮዲት እምሩ 18. የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ አጭር ልብ ወለድ ደራሲ የዝና ወርቁ 19. የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የፖርላማ ተመራጭ ፣ የትምህርት ጥናት ዳይሬክተርና የመጀመሪያዋ በውጭ ሃገር የትምህርት እድል ያገኘች ስንዱ ገብሩ 20. በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙዚቃቸውን በሽክላ ያሳተሙት እሙሃይ ጽጌማሪያም ገብሩ 21. የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር አልማዝ እሸቴ 22. የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሚኒስተር አዳነች ተካ 23. የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ብስክሌት አሽከርካሪ እቴጌ ጣይቱ https://t.me/learntochangeatthischannel
إظهار الكل...
Study smart

Smart study is about studying effectively anything at anytime with dedication. For more information @Studysmart0205

ከቱሉ በቾ (ኦላንኮሚ) እስከ ዓለም ዳርቻ........ ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጃታ በ1942 በምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ኤጄርሳ ላፎ ወረዳ በጠላ እና ጤፍ እጅግ በሚትታወቀው ኦላንኮሚ ከተማ ልዩ ቦታ ቱሉ በቾ ተወለዱ። ከተማዋ "ኦሎንኮሚ ጣሳ ኮሞኮሚ "በመባልም ትታወቃለች። ከግንጪ ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ትርቃለች። በልጅነታቸው ወላጆቻቸው ስለተለያዩ እናታቸው ጤላ በመሸጥ አሣደጉት። ከዛሬ 20 ዓመት በፊት እኛም የአዴ ሞቲ አያኖን ጠላ ጎራ ብለን እንቀምስ ነበር። አዴ ሞቲ ታዲያ ምግብ በነጻም ይሰጡን ነበር። የልጃቸውን ታሪክ ያወጉን ነበር። ለመምህራን ትልቅ ክብር ነበራቸው። አሁን በህይወት የሉም። በወቅቱ ልጃቸው ለአቅሜ ትምህርት እንደ ደረሰ የት/ቤት ወርሃዊ ክፍያ 3 ብር ከፍለው ልጃቸውን ት/ቤት ማስገባት ስለአልቻሉ 1 ብር እንዲደረግላቸው ጠይቀው መምህሩም ተስማምተው ፕሮፌሰሩ ትምህርታቸውን ጀመሩ። እዚያው በኦላንኮሚ እስከ 7ኛ ክፍል ተምሯል። ካ8ኛ ክፍል በላይ በቅርበት ስለአላገኙ 20 ኪሜ በእግር ተጉዘውነው የተማሩት። ለሁለተኛ ደረጃ የጅማ ግብርና ኮሌጅ ተምሯል። የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ በዕፅዋት ትምህርት አግኝተዋል 1968 ፒኤችዲ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል። ከ200 በላይ ጥናቶችን ሰርቶ 4 መጽሃፍ ጽፏል። ከ28 ዓመታት በላይ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲን አገልግለዋል። በ70 ድርጅቶች ውስጥ አገልግለዋል። በስራው ከ17 በላይ የሀገር አቀፍ፣ አህጉራዊ እና አለም አቀፍ ሽልማቶችን አግኝቷል። እ.ኤ.አ. በ 2009 የዓለም ምግብ የኖቤል ሽልማት የተሸለመ ሁለተኛው አፍሪካዊ ሆነ። የአፍሪካ ዜግነት ሳይንስ ጀግና ሽልማትን ከተቀበሉ 7 ተመራማሪዎች አንዱ ናቸው። በቅርቡ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የታላቁ የአሜሪካ ዜጋ ሽልማት ሜዳሊያ ተቀብለዋል። የአለም ሎሬት ፕሮፌሰር ገቢሳ ኢጃታ🤙🥰💖
إظهار الكل...
إظهار الكل...
TikTok · tolemuleta12th8

355 likes, 17 comments. Check out tolemuleta12th8's video.

የትምህርት ትዝታ በእኛ ጊዜ 1. መምህራኖቻችንን በጣም እናከብራቸውና እንወዳቸው ነበር፤ 2. ቀን ቀን ጫካ ሄደን እናጠና ነበር፤ 3. በየሠፈሩ በቡድን የሚያጠኑ ልጆች ነበሩ፤ 4. ስፔሻል ክላስ የሚባል ቅዳሜና ዕሁድ እንማር ነበር፤ 5. ሌሊት ማጥናት የሁል ጊዜ ተግባር ነበር፤ 6. Guide የሚባል መፅሐፍ ለመግዛት ገንዘብ እንቆጥብ ነበር፤ ከልብስና ጫማ ይልቅ Guide መጽሐፍ እናስቀድም ነበር፤ 7. Guide የሚባል መፅሐፍ እንዋዋስ ነበር፤ 8. ፈተና ባለ ሰሞን እንቅልፍ እንዳይሸውደን በቀዝቃዛ ውኃ እግራችንን ዘፍዝፍን እናጠና ነበር፤ 9. በኩራዝ ነፍጣ ካልሞላና ካልተዘጋጀ ከቤተሰብ ጋር ሌሊት ቀውጢ ነበር፤ ጧት በአፍንጫችን የሚወጣው ጠቋራ ካርበን-ሞኖ-ኦክሳይድ ምንም አይመስለንም ነበር፤ 10, ክላስ ውስጥ harder problem ጥያቄ ከሠራህ ግቢው ሙሉ ያወራልሃል፤ 11. አንዳንድ ተማሪዎች በደንብ ለማጥናት ብለው ትምህርት ያቋርጡ ነበር፤ 12. የአስተማሪ ልጅ ከሆንክ አባትህ እቤት ያስጠንሃል፤ 13. የሀብታም ልጅ ከሆንክ ጎበዝ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተከፍሎ ያስጠኑሃል፤ 14. ሠፈር ውስጥ ሲኒየር ጎበዝ ተማሪ ካለ ያግዝሃል፤ 15. መምህር ክላስ የማይገባ ከሆነ ለዳይሬክተሩ ሄደህ ታመለክታለህ፤ ዳይሬክተሩ መልስ ካልሠጠህ ትምህርት ጽ/ቤት ሄደህ ታመለክታለህ፤ 16. ስፔሻል የሚባል (ከ1-5/ከ1-10) የወጡ ተማሪዎች የሚፈተኑበት የፈተና ክላስ ነበር፤ 17, መንገድ ላይ መምህር በስም ጠርቶ ሰላም ካለን አኩቻ እንሆን ነበር፤ 18, ሴት ተማሪ "አንድ ጊዜ እፈልግሃለው ወንድሜ" ካለች ሌላ ነገር ሳይሆን የሆነ ጥያቄ ልታስፈልጥህ ነው፤ 19, ሁለት ዓመት አንድ ክፍል የወደቀ ተማሪ ቀጥሎ አይመዘገብም፤ 20, የብሔራዊ ፈተና ውጤታችንን የሠፈር ሰው በሙሉ በጉጉት ይጠብቅ ነበር፤ 21, የዩኒቨርሲቲ ድልድል በጋዜጣ ነበር የሚታወጀው፤ 22, ልጄን ዪኒቨርሲቲ አስገባልኝ ተብሎ ስለት እና ፀሎት እናቶቻችን ያደርጉ ነበር፤ 23, መምህሩ ጥያቄ ከጠየቀን፣ መልስ ለመመለስ ሁሉም ተማሪ "እጅ ማንሳት ብቻ ሳይሆን ከመቀመጫም ብድግ እያልን ትቸር ትቸር" እያልን ነበር፤ 24, ስለ አርሴናልና ማንቼ ጨዋታ ጭቅጭቅ፣ ወይኔ አንድ በላኝ እያልን ስለ betting, ስለፑል ጨወታ፣ ስለቪርቿል ውሻና ፈረስ ሩጫ፣ ስለፌስቡክና ስለቲክ ቶክ፣ ስለተቃራኒ ጾታ ጅንጀና፣ - - - ወዘተ አልነበረም፤ ቢኖር እንኳን መስሚያችን ጥጥ ነበር፤ .
إظهار الكل...