cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

አርምሞ🧘🏽‍♂

ጥቂት ምናኔ 🧘🏽‍♂️ ©³ @thoughts_painting

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
4 508
المشتركون
+1224 ساعات
+1217 أيام
+25030 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

`` እያለቀሰ ተወልዶ: እያጉረመረ ኖሮ: አዝኖ የሚሞት የሰው ፍጡር ብቻ ነው.. `` 🙂 -ሳሙኤል ጆንሰን
إظهار الكل...
🔥 15🤣 9😢 1
`` ሴቶች በወንዶች ለመወደድ ውበት ያስፈልገናል፤ እኛ ግን እነሱን ለመውደድ ድድብና በቂ ነገራችን ነው። `` -ኮኮ ቻና
إظهار الكل...
😁 23👎 5🤔 5🔥 4
Photo unavailableShow in Telegram
ዶስቶይቭስኪ እንዲህ ይላል: "ህመምተኛ ባደረገ አካባቢ ላይ ድህነት ማግኘት አይቻልህም፤ ለቀ ውጣ ከዛም ራቅ!።"              %    አል-ሩሚ ደግሞ እንዲህ ይላሉ፡ "ከሚጎዳህ ነገር መሸሽ የበለጠ ይጎዳሃል፤ ይልቅ እስከፈውስህ ድረስ እንደፀና ታመም።" በማን ኣሳብ እንስማማ¿
إظهار الكل...
9👍 5🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
Discussion question፡ ከማን ጋር ትስማማላችሁ¿ ዶስቶይቭስኪ እንዲህ ይላል: "ህመምተኛ ባደረገ አካባቢ ላይ ድህነት ማግኘት አይቻልህም፤ ለቀ ውጣ ከዛም ራቅ!።"              %    አል-ሩሚ ደግሞ እንዲህ ይላሉ፡ "ከሚጎዳህ ነገር መሸሽ የበለጠ ይጎዳሃል፤ ይልቅ እስከፈውስህ ድረስ እንደፀና ታመም።"
إظهار الكل...
የበፊት ሰዎች የት ሄዳችሁ ነው፤ አሳብ ላይ አሳብ አሽከርክራችሁ ለሌላ ኣሳብ የምትጋብዙኝ። ስል ሰዎች ነበራችሁ ዝምታ መረጣችሁ ወይንስ.. እስቲ እንወቃቀስ 🤔
إظهار الكل...
2🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
  ^^                አ ስ ተ ም ሮ ፪          Become a Lake/ ሀይቅ ሁን 🧘🏽‍♂ አንድ እርጅና የተጫነው መምህር በተማሪው ቅሬታ ደከመና። አንድ ቀን ጠዋት ይህን ተማሪውን ጨው እንዲያመጣ ላከው። ተማሪውም ሲመለስ መምህሩ ያመጣውን አንድ እፍኝ ጨው በአንድ ብርጭቆ ውሃ ውስጥ  ቀላቅሎ እንዲጠጣ አዘዘው:: “እንዴት ነው ይጣፍጣል?” መምህሩ ጠየቀ:: `` ይጎመዝዛል `` አለ ተማሪው። መምህሩም ፈገግ አለና ወጣቱን ያንኑ እፍኝ ጨው ወስዶ ሐይቁ ውስጥ እንዲያስቀምጠው ነገረው።  ሁለቱም በጸጥታ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ሀይቅ ሄዱ እና  ተማሪው እፍኝ የሞላውን ጨው  ውሃው ውስጥ አስቀመጠው። መምህሩም “አሁን ከሐይቁ ጠጣ” አለው። ውሃው በወጣቱ አገጭ ላይ ሲንጠባጠብ “እንዴት ነው ይጣፍጣል?” መምህሩ ደግሞ ጠየቀው።        `` ምንም፤ ውሃ ውሃ ይላል``  አለ ተማሪው።    “ጨው ትቀምሳለህ?” በማለት መምህሩ እጁን እየዘረጋ ለሶስተኛ ጊዜ ጠየቀው። `` አይ! `` አለ ወጣቱ።  ከዛም መምህሩ ከዚህ ቁም ነገር በኋላ ወጣቱ ጎን ተቀምጦ በለሆሳስ ተናገረ፡- “የሕይወት ሥቃይ ንጹህ ጨው ነው፤ ከዚህ በላይ ያነሰ አይደለም።  በህይወትህ ውስጥ ያለው ህመም መጠን በትክክለኝነት ተመሳሳይ ነው።  ይሁን እንጂ የምትቀምሰው ምሬት ህመሙን በምናስገባው container ላይ የተመሰረተ ነው፤ ስለዚህ ህመም ሲሰማህ ማድረግ የምትችለው ብቸኛው ነገር የነገሮችን ስሜት ማስፋት ነው።  ብርጭቆ መሆን አቁም.. ሀይቅ ሁን!።”          
إظهار الكل...
🔥 10👏 4😢 1
የግጥሜ አርዕስት (የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ)       ''😩^^🤯''            -አመሰግናለሁ
إظهار الكل...
የግጥሜ አርዕስት (የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ) ``😩^^🤯 -አመሰግናለሁ
إظهار الكل...
This song is by Zerubbabel Molla. The maturity of the melody deepens the depth of the poem.. አገሬን የማንም ተባያዊ ባንዳ እድፉን በደሟ አጸዳድቶ ጉፋያነቱን ዘርፎ-ባዘረፋት ሀብት ለወጠ። አሯቅቷት እርቃንነቷ አልበቃውም እለት'ለት እንዳታገግም አድርጎ የሞት ስል ይሰድባታል። ዘፈኑ መድረክ ላይ የተጫወተው ነው፤ እንደዚህ  ያማረ ፐርፎርማንስ አዳምጬ አላውቅም። ምን እንደሆነ ዝምታው ባላውቅም ከዝማሬው ቀንበጥ ማቅረብ አልተቻለኝም።                              🎶       ' 'ላንቺም ለእኔም ከቶ ማይበጁ          ጥል ሸምነው ጋቢ እየቋጩ የአሞጋገሱሽ ምን እንኳን ቢመስልም     ነጠላቸው ብርድ አያስጥልም፤      እንኳንስ ለእኛ ለአገሩ ሊያውቁ          ለራሳቸው በ ተ ዋ ወ ቁ    ባንቺ ዝምታ ሆነው እየታከኩ        ጎጇችንን ስሩን ነ ካ ኩ! እናትዬ ጥንስሱን እይው ውብ አለሜ ድግሱን ለይው የሚያስቡልን እየመሰሉ ገብተው ከቤት ቅብ ሲያማስሉ ጥልን ከእንጀራ እያጎረሱ የስንቱን ቤት አፈራረሱ! ' '
إظهار الكل...
21👍 6😢 4🤔 1
ጥልቅ የግንኙነት ስሜት ከቃላት በላይ የሆነ ያልተነገረ ግንዛቤ ተሰምቷችሁ ያውቃል? Root Chakra (Muladhara) "I am grounded and secure" ይህ ቻክራ የእኛን መሠረታዊነት ብሎም ከምድር ጋር ያለንን ግንኙነት ይወክላል። Root Chakra በዩኒቨርስ ላይ የመረጋጋት፣ የደህንነት እና የመተማመን ዋነኛ መገለጫው ነው። እንደ መሬት ላይ ያሉ የልምድ ጉዞዎች፣ በተፈጥሮ ውስጥ ጊዜን ማሳለፍ፣ አካላዊ ሰውነታችንን በማቀፍ የመሳሰሉት ልምምዶች ጠልቀን ስር የሰደዱ የመቋቋም ስሜትን ማዳበር እንችላለን። Sacral Chakra (Swadhisthana): "I embrace my creativity and passion." ሳክራል ቻክራ ስሜታችንን፣ ፈጠራችንን እና ስሜታዊነታችንን ይቆጣጠራል። ስሜታችንን እንድናከብር፣ እውነተኛ ማንነታችንን እንድንገልጽ እና ወደ የፈጠራ ኃይላችን እንድንገባ መንፈሳዊነቱ ያበረታታናል። ጥበባዊ ስራዎችን በመዳሰስ፣ አስደሳች እንቅስቃሴዎችን በመስራት እና ጤናማ ግንኙነቶችን በመንከባከብ በውስጣችን ያለውን የመነሳሳት እና የህይወት ጉልበት ፍሰቷን መቀስቀስ እንችላለን። Solar Plexus Chakra (Manipura): "I trust in my personal power" ይህ ቻክራ በራስ የመተማመን አስተሳሰብ፣ ፍቃደኛ እና ራስን በራስ የመግዛት ስሜት ጋር የተያያዘ ነው። ሶላር ፕሌክስስ ቻክራ ልዩ ማንነታችንን እንድናከብር፣ ድንበሮቻችንን እንድናረጋግጥ እና ግቦቻችንን በድፍረት እና በቁርጠኝነት እንድንከተል ያሳስበናል። like self-empowerment affirmations፣ ግልጽ አላማዎችን በማዘጋጀት እና ወሳኝ እርምጃ በመውሰድ ውስጣዊ ጥንካሬን እና በራስ መተማመንን ማዳበር ያስችለናል። Heart Chakra (Anahata): "I embody unconditional love and compassion" የልብ ቻክራ ለራሳችንም ሆነ ለሌሎች ፍቅርን የመስጠት ብሎም የመቀበል ችሎታችንን ያስተዳድራል። ይህ ቻክራ ርህራሄን ይቅርታን እና ጥልቅ ግንኙነትን ማዳበር አስፈላጊ መሆኑን ጉሉ መገለጫው ብቻ ሳይሆን ማሳሰቢያው ነው። የደግነት ተግባራትን በመለማመድ፣ ምስጋናን በማዳበር እና ልባችንን ለሌሎች በመክፈት ጥልቅ ፈውስ ማግኘት እና ለፍቅር እና ርህራሄ ያለንን አቅም ማሳደግ ያስችለናል። Throat Chakra (Vishuddha): "I speak my truth with integrity." ይህ ቻክራ በግንኙነት ራስን የመግለጽ ትክክለኛነት ጋር የተያያዘ ነው። ጉሮሮው ቻክራ እራሳችንን በሐቀኝነት እንድንገልጽ፣ የውስጣችንን እውነት እንድናከብር እና ሌሎችን በተመስጦ እንድናዳምጥ እና የሰዎችን የንግግር ቃላት ሰምተን ምን አመል እንዳላቸው በጥልቀት እንድረዳ ያግዘናል። አስተውልት እንደሞላው ግንኙነት፣ እንደአፈ ትጉዋን አፈጥበባት ብሎም የድምፅ ቅላጼ አገላለጽ ባሉ ልምምዶች ቃላቶቻችንን ከውስጣዊ ጥበባችን ጋር በማጣጣም ለአዎንታዊ እና ትርጉም ያለው ውይይት እንድናበረክት ያስችለናል። Third Eye Chakra (Ajna): "I trust my intuition and inner guidance" ሦስተኛው አይን ቻክራ የእውቀት የማስተዋል እና የመንፈሳዊ ግንዛቤ ማዕከል ነው። ውስጣዊ ራዕያችንን እንድንመለከት፣ በማስተዋል እውቀት እንድንታመን እና ከፍ ካለ ማንነታችን ጋር ጥልቅ ግንኙነት እንድናዳብር ይጋብዘናል። ዊስጣዊ እይታችን እንዲሰፋ፣ ጥንቃቄ ባሉ ልምምዶች አማካኝነት ጥልቅ ጥበብን እንድንገነዘብ እና ከስጋዊ አይናችን በዘለለ ረቂቅ ነገሮችን እንድንመለከት ተመልክተንም እንድንገነዘብ ግልጽ በሆነ መመሪያን self-inner ከራስ ማግኘት ያስችለናል። Crown Chakra (Sahasrara): "I am connected to the divine" ይህ ቻክራ ከመላው ዩንቨርስ ጋር ያለንን መንፈሳዊ ግንኙነት እና ከፍተኛ ንቃተ ህሊናን ይወክላል። Crown ወይም ዘውዱ ቻክራ የኢጎ ድንበርን እንድንሻገር፣ ለህይወት ፍሰት እንድንገዛ እና ከሁሉም ጋር አንድነት እንድንለማመድ ወደቤቱ ይጋብዘናል። እንደ ጥልቅ ተመስጦ፣ ትክክለኛው የጸሎት መስመር direction ባሉ ልምምዶች ግንዛቤያችንን ማስፋት፣ የጊዜ ትልቅነት ወይም ወይም ከግዜ ማዕከላት የመውጣት ልምምዶች እና በውስጣችን እና በዙሪያችን ካለው መለኮታዊ ረቂዮት ጋር መስማማት ያስችለናል። (ከዚህ በፊት የለቀኩት የmudra ልምዶች ከቻክራ መንፈሳዊ ጥልቀት ጋር ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፤ በተጨማሪ የሙድራ ዮጋ ቴራፒ ግንኙነትን እና የሰባቱ ቻክራ ምንነት እንዴት መስራት እና ጠልቀን ከገባን በኋላ ምን ማድረግ እንዳለብን አብራራው ዘንድ React & share & comment ከፈላጊ ሰብ ይንጸባረቅ ናመስቴ..) @Armemo_offical
إظهار الكل...
👍 12 6