cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

🇪🇹የሕግ ጉዳይ

Legal matter, Ethiopia Legal Info, #ጠበቃና የሕግ አማካሪ We offer you Reliable services with a very high sense of responsibility. #ከጠበቃ ጋር ተነጋገሩ @TalkToLawyer [email protected]

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
5 076
المشتركون
+624 ساعات
+517 أيام
+18930 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ስለ ኢትዮጵያ የቤተሰብ ህግ የምንዳስስ ይሆናል፡፡ በዚህ ክፍል ላይ ስለ ጋብቻ አይነቶች እና ጋብቻ ለመፈጸም መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች እንመለከታለን፡፡ ቤተሰብ ትልቅ ተቋም በመሆኑ የህግ ጥበቃ የሚደረግለት ተቋም ነው፡፡ የቤተሰባዊ ግንኙነት ከሚመሰረትባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው ጋብቻ ነው፡፡ ጋብቻን እና ተያያዥ ጉዳዮች በፌደራል ደረጃ የሚዳኙት ወይም የሚገዙት በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 ዓ.ም ነው፡፡ በዚህ አዋጅ መሰረት በሶስተ አይነት መልኩ ጋብቻ ሊፈፀም እንደሚችል ተቀምጧል፡፡ እነዚህን የጋብቻ አይነቶች ከመመልከታችን በፊት ጋብቻ ለመፈጸመም ሊሟሉ የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎችን እናያለን፡፡፡ አንድ ሰው ጋብቻ ለመፈፀም በቅድሚያ ሊያሟሏቸው የሚገቡ አስፈላጊ እና አስገዳጅ ቅድመ ሆኔታዎች አሉ፡፡ የመጀመሪያ በተጋቢዎች መካከል ነጻ ፍቃድ መኖር ነው ፡፡ 2ኛው ተጋቢዎች 18 አመት እድሜ የሞላቸው መሆን ያለበት ሲሆን በልዩ ሁኔታ ግን በፍትህ ሚንስትሩ ፍቃድ ሲሰጥ 16 አመት ለጋብቻ የተፈቀደ ጊዜ ይሆናል፡፡ 3ኛው ደግሞ በተጋቢዎች መካከል የስጋ እና የጋብቻ ዝምድና አለመኖር ነው፡፡ 4ኛው ተጋቢዎቹ በሌላ ጋብቻ ውስጥ አለመሆናቸው ወይም በጋብቻ ላይ ሌላ ጋብቻ ያለመፈጸም ነው፡፡ 5ኛው ተጋቢዎች በፍርድ ያልተከለከሉ መሆን አለባቸው 6ኛው እና የመጨረሻው ቅድመ ሁኔታ ለሴት ልጅ አስቀድሞ የነበራት ጋብቻ ቀሪ ከሆነ በኋላ ወይም ጋብቻው ከፈረሰ በኋላ ለ180 ቀን ወይም ለ 6 ወር ያህል ሌላ ጋብቻ እንዳትፈፅም የተደነገገ ክልከላ ነው፡፡ ቀደም ሲል እንደገለፅኩላችሁ ሶስት የጋብቻ አይነቶች አሉ፡፡ 1ኛ. በክብር መዝገብ ሹም ፊት የሚፈፀም ጋብቻ ነው፡፡ ይህም ማለት ወሳኝ ኩነት በመሄድ የሚፈፀም ጋብቻ ነው፡፡ 2ኛው. በሃይማኖት ስርአት የሚፈፀም ጋብቻ ሲሆን ይህ ማለት ደሞ በቤተክርስቲያን ስርአት፤ በሼርያ ህግ እና በሌሎችም የሃይማኖት ስርአቶች ሊፈጸም የሚችል የጋብቻ አይነት ነው፡፡ 3ኛው እና የመጨረሻው የጋብቻ አይነት ደግሙ በባህላዊ ሰርአት የሚፈፀም ጋብቻ ሲሆን ይህም በተለያዩ አከባቢዎች በሚገኙ ባህላዊ ስርአቶች የሚፈፀም የጋብቻ አይነት ነው፡፡ በቀጣይ ክፍል ደግሞ ስለጋብቻ ውጤቶች የማቀርብላችሁ ይሆናል፡፡ የነጺ ሎው via Alternative legal enlightenment/ALE* አማራጭ የሕግ እውቀት🔴 #አለሕግ #Alehig @NegereHig https://t.me/NegereHig
إظهار الكل...
ነገረሕግ NegereHig

About laws Ethiopia.......ስለ ኢትዮጵያ ህግጋት.... ስለህጎችና ህግ ጉዳዮች ብቻ.......የህግ ነገሮችን It is All About Laws....Only Law Matters...... It is about law. ስለህጎች....... ጠበቃና የህግ አማካሪ ቢሮ አዲስ አበባ @AboutLaws_bot

👍 3
إظهار الكل...
Legal Manager - Re-Advertising

Bachelor's Degree in Law or in a related field of study with relevant work experience, out of which 2 years in a managerial level Duties & Responsibilities: - Provide updates and legal briefs on all changes to laws and regulations within Ethiopia - Planning, Organizing, coordinating and monitoring the legal service department

👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ውስጥ ያለ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም የፋይናንስ ኦዲት ሪፖርቱን ለሰላም ሚኒስቴር ማቅረብ እንደሚኖርበት ፤ ከውጭ አገር የሚመጣ የገንዘብ ዕርዳታ በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። " የሃይማኖት ጉዳዮች አዋጅ " የተሰኘው ረቂቅ አዋጁ የሃይማኖት ተቋማቱ ተቀባይነት ያለው የሒሳብ አያያዝና የኦዲት ሥርዓት መዘርጋት እንደሚኖርባቸው፣ የኦዲት ሪፖርታቸውን ለሰላም ሚኒስቴር ማቀረብ እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡  ረቂቅ አዋጁ ምን ይዟል ? - የሃይማኖት ተቋማት የሚጠቀሙት የሒሳብ አያያዝ ሥርዓት የገቢ፣ የወጪና አጠቃላይ የንብረት ዝርዝር የያዘ መሆን አለበት። - የገቢ አሰባሰብና የወጪ አስተዳደር በሕጋዊ መንገድ ማከናወን አለባቸው። - የሃይማኖት ተቋም በራሱ #የገቢ_ማስገኛ ሥራዎችን በሚያከናውንበት ጊዜ ለዚሁ ሥራ ሲባል የተለየ የባንክ ሒሳብ መክፈትና የተለየ መዝገብ መያዝ አለበት። - ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ አለበት። ሲያሳውቅም ፦ ° የለጋሹን ድርጅት ወይም ግለሰብ ስም እና አድራሻ፣ ° የተለገሰው የገንዘብ፣ ስጦታ ዓይነት እና መጠን ፣ ° ስጦታው / ድጋፉ የተሰጠበት ልዩ ዓላማ መካተት አለበት። - ማንኛውም  የሃይማኖት ተቋም  የበጀት ዓመቱ ባለቀ በ3 ወር ውስጥ የፋይናንስ እንቅስቃሴውን በገለልተኛ ኦዲተር ማስመርመር አለበት። የኦዲተሩን አቋም እና የውሳኔ ሐሳብም መያዝ ይኖርበታል። - የሰላም ሚኒስቴር የደረሰውን የኦዲት ሪፖርት አመቺ በሆነ መንገድ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ይኖርበታል። #ሪፖርተርጋዜጣ #tikvahethiopia https://t.me/NegereHig
إظهار الكل...
2
#AddisAbaba #ንግድ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ማህበረሰብ ያለወከባ በተረጋጋ መንፈስ የንግድ ተግባሩን ለማከናወን እንዲያስችል ዕድል ይፈጥርለታል የተባለ አዲስ መመሪያ ስራ ላይ መዋሉን ለማወቅ ተችሏል። አዲሱ መመሪያ  " በመንደር ንግድ ቁጥጥር አሰራር ስርዓት መመሪያ 159/2016 " እንደሚባል ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። መመሪያው በየትኛው አስተዳደር እርከን የትኛው አይነት እርምጃ እንደሚወሰድ በግልጽ ያስቀመጠ ሲሆን ይህም ሲታይ የነበረውን ግልጽ እና ፍትሃዊ ያልሆነ አሰራር ያስቀራል ተብሏል። በአዲሱ የመንደር ንግድ መመሪያ መሰረት የወረዳ የንግድ ቁጥጥር ባለሙያ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወስድ ህጉ የሚፈቅድለት በተመደበበት መንደር ላይ ፦ ➡ ያለ ንግድ ፍቃድ ➡ ባልታደሰ ፍቃድ ➡ በታገደ አልያም በተሰረዘ ንግድ ፈቃድ የሚነግድ የንግድ ድርጅት ላይ #ብቻ_ነው። ይህን ሲያደርግም ለቅርብ ኃላፊ ማሳወቅ አለበት። ከዚህ ወጪ ያሉት ጥፋቶች #በሙሉ እርምጃ ሳይወስድ ለቅርብ ኃላፊው በፅሁፍ በማሳወቅ ለውሳኔ ወደ ንግድ ቢሮ መላክ ይጠበቅበታል ፤ የተወሰነውን ውሳኔ የማስፈፀም ኃላፊነትም አለበት። መመሪያው ፦ https://t.me/tikvahethiopia/87886 #TikvahEthiopiaFamilyAA #tikvahethiopia አማራጭ የሕግ እውቀት 👉Telegram👈 https://t.me/lawsocieties 👉Facebook Page 👈 https://www.facebook.com/lawsocieties/ 👉 LinkedIn 👈 https://www.linkedin.com/company/lawsocieties/ 👉YouTube 👈 https://youtube.com/@Ale_Hig
إظهار الكل...
5. Blockchain technology is utilized to secure the storage and transmission of digital evidence, ensuring its authenticity and integrity. 6. China's smart court system also includes a "mobile court" service, offering judicial services via a smartphone app. 7. AI judges, like "Xiaofa" and "206 system," assist human judges in handling cases. 8. The system includes a public platform for searching court judgments and other legal information. 9. E-payment systems are integrated into the smart court system, enabling parties to pay court fees and fines electronically. 10. China's smart court system has inspired similar initiatives in other countries, such as Singapore and Malaysia. SO IS THIS GOOD FOR THE SYSTEM? The answer is: absolutely!! 1. There will be increased efficiency and speed in handling cases, reducing backlogs and delays. 2. It will enhance accessibility for parties to participate in court proceedings remotely, reducing travel costs and inconvenience. 3. It willalso improve transparency and accountability through the use of digital records and monitoring technologies. 4. It will help alleviate judges' workloads, allowing them to focus on complex cases. BUT THERE ARE CHALLENGES AS WELL: 1. How do they deal with privacy and data security concerns regarding the handling of sensitive personal and case information? 2. Whata bout the potential for system failures or technical glitches, which could disrupt court proceedings and compromise due process? 3. What about the risk of bias in data sets used to train these systems? WHAT ARE YOUR THOUGHTS? DOES ANYONE HAVE ANY EXPERIENCE WITH THIS?
إظهار الكل...
👍 6
Photo unavailableShow in Telegram
EVER HEARD OF THE SMART COURT SYSTEM IN CHINA? WELL HERE ARE SOMEINTERESTING FACTS: 1. China has implemented an advanced online litigation system that allows parties to file cases, submit evidence, and participate in hearings remotely using digital platforms. 2. Courtrooms are equipped with advanced technologies, including virtual reality (VR) systems, which allow judges and parties to recreate crime scenes or review evidence in a immersive digital environment. 3. Artificial intelligence (AI) is used to assist judges in processing large amounts of case data, identifying relevant legal precedents, and drafting legal documents. 4. Facial recognition technology is employed to identify individuals attending court proceedings and ensure proper security measures. 5. Blockchain technology is utilized to secure the storage and transmission of digital evidence, ensuring its authenticity and integrity.
إظهار الكل...
Check out this job at Mastercard Foundation: https://www.linkedin.com/jobs/view/3923626116
إظهار الكل...
Mastercard Foundation hiring Senior Legal Counsel in Addis Ababa, Addis Ababa, Ethiopia | LinkedIn

Posted 8:34:31 PM. About Mastercard FoundationMastercard Foundation seeks a world where everyone has the opportunity…See this and similar jobs on LinkedIn.

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ምድብ ችሎቶች እና አድራሻቸው
إظهار الكل...
በመቃወሚያ ላይ በተሰጠ ብይን ቅሬታ ያለው ወገን ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰበር/ይግባኝ አቤቱታ በሚያቀርብበት ጊዜ መጀመሪያ ጉዳዩን አይቶ ብይን የሰጠው ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን እና ብይኑ የጸናበትን ውሳኔ ከሰበር አቤቱታቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ እንደሚኖርበት፣ ቅሬታ የሚቀርበው በአፈጻጸም ላይ በተሰጠ ትዕዛዝ ላይ ሲሆን አፈጻጸሙ የተጠየቀበት ፍርድ፣ የአፈጻጸም ማመልከቻ እና በማመልከቻው መሰረት በአፈጻጸም ጉዳይ የተሰጠ ትዕዛዝ/ዞች ከአመልካች አቤቱታ ጋር ተያይዞ መቅረብ ያለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ወደ ሰበር ችሎት የሚቀርቡ ጉዳዮች የክርክር አመራር ሥርዓትን በተመለከተ ለግንዛቤ እንዲረዳችሁ ከዚህ በታች የተያያዘውን የሰበር ሥነ ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 17/2015 አያይዘናል፡፡ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት =========//======== 👉  @SAMUELGIRMA 👉 t.me/+TE8_8RXdfIsqGEKn 👉 t.me/+TE8_8RXdfIsqGEKn 👉 @ethiopian_law                                          🙏 👉 @tebeka #Ethiopia 🇪🇹 #ህግ #lawyer #ጠበቃ #ሳሙኤልግርማ #AddisAbaba #samuelgirma #law               አዲስ አበባ ኢትዮጵያ 🇪🇹
إظهار الكل...
#ኢትዮጵያ #አካልጉዳተኞች “ አጠቃላይ የሆነ የአካል ጉዳተኞች የህግ ማዕቀፍ እንፈልጋለን ” - የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማኀበር የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማኀበር  “ ስለረቂቅ የአካል ጉዳተኞች መብቶች አዋጅ አያያዝ በኢትዮጵያ የመወያያ መነሻ ሀሳብ ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከፍትህ ሚኒስቴር የሕግ ማርቀቅ ባለሙያዎቸ ጋር ከሰሞኑን የምክክር አውደ ጥናት አድርጓል። የምክክር አውደ ጥናቱ ዋነኛ ዓላማ በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ20 ሚሊዮን በላይ አካል ጉዳተኞች ተጠቃሚ ያልሆኑባተቸውን፦ - የኢኮኖሚ፣ - የትምህርት፣  - የቅጥር፣  - የማኅበራዊ ተሳትፎዎችና የመብት ጥሰቶች ችግሮችን እንዲቀረፍ “ ሁለንተናዊ የአካል ጉዳተኞች መብቶች አዋጅ ” ለማውጣት ማኀበሩ ከአጋር አካላት ጋር በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ማድረግ ነበር። በመርሀ ግብሩ የተገኘው ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ያሉት አካል ጉዳተኞችን የተመለከቱ ህጎችስ በትክክል እየተፈጸሙ ነው ወይ ? ይህ ረቂቅ አዋጅስ በዘርፉ  ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ ምን ጉልህ ሚና አለው ? ሲል ማኀበሩን ጠይቋል። የማኀበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሴ ጥላሁን በሰጡት ቃል፣ “ አካል ጉዳተኞችን የሚመለከቱ የተወሰኑ (ጥቅል/ግልፅ ያልሆኑ) ህጎች አሉ። በአጠቃላይ አካል ጉዳተኞችን በማስመልከት ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ ህጎች በርካታ ችግሮች አሉባቸው ” ብለዋል። የተወሰኑ ህጎች ቢኖሩም፦ - ጥቅል/ግልጽ ያልሆኑ፣ - አስፈጻሚ አካል የሌላቸው፣ - ተጠያቂነትን የማያሰፍኑ፣  - ዝርዝር መመሪያ የሌላቸው በመሆናቸው የነበሩት ህጎች አስቻይ ሁኔታ እንዳይፈጥሩ አድርጓቸዋል ” ነው ያሉት። “ ወቅቱን የዋጀ የወቅቱን የአካል ጉዳተኞች ጥያቄ ሊመልስ የሚችል ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች እንቅስቃሴን መሠረት ያደረገ አዋጅ የለም ” ያሉት አቶ ሙሴ፣ በሂደት ላይ ያለው “ ሁለንተናዊ የአካል ጉዳተኞች መብቶች አዋጅ ” ሲወጣ ችግሩን ሊቀርፍ እንደሚይችል አስረድተዋል። ረቂቅ አዋጁ፦ - የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ግልጽ የሆነ በጀት እንዲኖር፣ - የአካል ጉዳተኛ ቤተሰቦች የሚደርስባቸውን መገለልና አድሎ ችግር የሚቀርፍ፣  - አካል ጉዳተኞች በህንፃ፣ ትምህርት፣ በትራንስፖርት ተደራሽነታቸው እንዲረጋገጥ የሚያደርግ፣  - ከውጩ ሀገራት የሚገቡ አካል ጉዳተኞች የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ ጭምር የሚደነግግ መሆኑን ተናግረዋል። #TiavahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
إظهار الكل...
👍 5