cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

አዲስ ሪፖርተር - NEWS

🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው ! => በቻናሉ 📌 ፈጣን ፥ 📌 ትኩስ ፥ 📌 ወቅታዊ እና 📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል ! 🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል ! For promotion @Addis_reporter_bot #ADDIS ABABA, ETHIOPIA

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
40 231
المشتركون
-2424 ساعات
-797 أيام
-41530 أيام
توزيع وقت النشر

جاري تحميل البيانات...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
تحليل النشر
المشاركاتالمشاهدات
الأسهم
ديناميات المشاهدات
01
ብሄራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን፣ በቀጣዮቹ ኹለት ወራት በትግራይ በመጀመሪያው ዙር 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት መልሶ ለማቋቋም እንዳቀደ መናገሩን ዶይቸቨለ ዘግቧል። ኮሚሽኑ ይህን የገለጠው፣ በትጥቅ ማስፈታትና መልሶ ማቋቋም ሂደቱ ዙሪያ መቀሌ ላይ አገር ዓቀፍ ምክክር መካሄዱን ተከትሎ ነው። ኮሚሽኑ በአገር ዓቀፍ ደረጃ ለሚተገብረው ዕቅድ ባጠቃላይ 750 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል ይላል። ባጠቃላይ በመልሶ ማቋቋም መርሃ ግብሩ የሚታቀፉት የቀድሞ ተዋጊዎች 274 ሺህ 800 ያህል መኾናቸውንም ኮሚሽኑ ገልጧል። @Addis_Reporter
1 0811Loading...
02
መንግሥት ያቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ ትናንት በሦስት የአውሮፕላን በረራዎች በአስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 141 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ከሳውዲ ዓረቢያ መልሷል። ከትናንት ተመላሾች መካከል፣ 744ቱ ወንዶች ሲኾኑ፣ 377ቱ ሴቶች እንዲኹም 20ዎቹ ጨቅላ ሕጻናት እንደኾኑ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ገልጧል። ኮሚቴው ከሳዑዲ ዓረቢያ ለመመለስ ካሰባቸው 70 ሺህ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች፣ ከሚያዝያ መጀመሪያ ጀምሮ ከ24 ሺህ 500 በላይ የሚኾኑትን መልሷል። @Addis_Reporter
1 2180Loading...
03
የስዊድኗ ስቶክሆልም ከተማ በአገሪቱ የሚኖሩ ኤርትራዊያን የዘንድሮውን የኤርትራ የባሕል ፌስቲቫል እንዲያካሂዱ መፍቀዷን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘገበዋል። ባለፈው ዓመት ነሃሴ በስቶክሆልም በተከበረው የኤርትራዊያን ፌስቲቫል ላይ የኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ተጋጭተው፣ ብጥብጥና ኹከት መፈጠሩ ይታወሳል። የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ብዙ ተቃውሞዎች ቢቀርቡበትም ኤርትራዊያን ፌስቲቫሉን እንዲያከብሩ የፈቀደው፣ በስዊድን ሕገመንግሥት ጥበቃ የሚደረግለት መብት በመኾኑ እንደኾነ ዘገባዎቹ አመልክተዋል። በአውሮፓ አገራት በየዓመቱ የሚከበረው የኤርትራዊያን ፌስቲቫል፣ በተለይ ካለፉት ኹለት ዓመታት ወዲህ በጎራ የተከፈሉ ኤርትራዊያን ኹከት የሚፈጥሩበት መድረክ ኾኗል። @Addis_Reporter
1 1702Loading...
04
፨✝✝ መርጌታ  የባህል ህክምና አዋቂና ቀማሚ✝✝፨                          📞0952400019                            📞0952400019 ከሀገር ውጭም ሆነ ከሀገር ውስጥ ላላችሁ በርቀት ምክንያት መምጣት ላልቻላችሁ ባላችሁበት መስራት እና መላክ እችላለሁ።                                ↘️ የምንሰጣቸዉ የጥበብ አገልግሎቶች : 1 =ለሀብት 2 =ለገበያ 3  =ለወሲብ ስንፈት (ለውፍረት:ለቁመት) 4 =ለመስተፋቅር 5 =ጥይት ለማያስመታ 6 =ለቁማር 7 =ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር) 8 =ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ) 9 =ለዓቃቤ ርዕስ 10 =ለመክስት 11 =ቡዳ ለበላው 12 =ሰላቢ የማያስጠጋ 13 =ለመፍትሔ ሀብት 14 =ለመፍትሄ ስራይ 15 =ለሁሉ ሠናይ 16 =ለህማም 17 =ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ) 18 =ለመድፍነ ፀር 19 =ለማንኛውም አይነት ቁስል መሻሪያ 20 =ለበረከት 21 =ለከብት መስተሐድር(ከብት እንዳይጠፋ) 22= አፍዝዝ አደንግዝ(እፀ_መሰውር) 23 =ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ) 24 =ለግርማ ሞገስ 25 =መርበቡተ ሰለሞን 26 =ለዓይነ ጥላ 27 =የሌባ ገትር(ሌባ የማያስገባ) 28 =ለሁሉ መስተፋቅር 29 =ለፊት ማዲያት 30 =ለእድል(ለቁማርም ቢሆን) 31 =ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ) 32 =ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ 33 =ለመካንነት መሻሪያ 34 =ለኪንታሮት በሽታ(በሚቀባ የሚሰጥ) አገልግሎት(ምናልባት ያለ ኮከባቸው የተጋቡ ካሉ አስማምቶ የሚያኖር መድሀኒት ማሳሰቢያ፦🌿የሰውን ልጅ ለመጣል ለማሳበድ በ አጠቃላይ ከህይወት መስመር ለማውጣት አንሰራም🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿               📞0952400019 ለጥያቄዎ 📞0952400019ይደውሉልን::
1 1490Loading...
05
በ10 አመታት ውስጥ ሰዎችን ማርስ ላይ ማስፈር እንጀምራለን-ኤለን መስክ በቀጣይ 10 አመታት ውስጥ ሰዎችን ማርስ ላይ ማስፈር እንደሚጀመርና በ30 አመት ውስጥ ማርስ ላይ ዘመናዊ ከተማ እንደሚገነባ የስፔስ ኤክስ መስራች ኤለን መስክ ገልጿል። የማርስ ከተማ ግንባታን እውን ለማድረግ ስፔስ ኤክስ በርካታ የቅኝት ሳተላይቶችን በቅርቡ እንደሚልክ ማስታወቁን የዴይሊ ስታር ዘገባ ያመላክታል። "በጥቂት አመታት ውስጥ ሰዎችን በማርስ ላይ የማስፈር ዕቅዳችንን ዕውን እናደርጋለን" ብሏል የ52 ዓመቱ ቢሊየነር ኤለን መስክ። "ከ10 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሰዎችን ማርስ ላይ ማስፈር እንጀምራለን፤ ከበረታን እስከ 20 ዓመት፣ በእርግጠኝነት ግን በ30 ዓመት ውስጥ ዘመናዊ ከተማ በማርስ ላይ እንገነባለን" ብሏል ኤለን መስክ። እ.አ.አ 2002 የተመሰረተው ስፔስኤክስ ወደ አለማቀፉ የህዋ ጣቢያ ለመጀመሪያ ጊዜ መንኮራኩር እና ጠፈርተኞችን የላከ የግል ኩባንያ ነው። @Addis_Reporter
2 32210Loading...
06
የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ መንግሥት የአሜሪካው አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ከትናንት ወዲያ ባደረጉት ንግግር ላይ የታጠቁ ኃይሎችን በስም ጠቅሰዋል በማለት መውቀሱ "ለችግሮች እውቅና ለመስጠት" እና ግጭቶችን በንግግር ለመፍታት ፍላጎት እንደሌለው ያሳያል" ሲል ዛሬ ምላሽ ሰጥቷል። ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በአምባሳደሩ ንግግር የተንጸባረቁ "ስህትቶችን" ለማስተካከል ከኢምባሲው ጋር እንደሚሠራ መግለጡን በተመለከተም፣ መንግሥት የሚፈልጋቸውን ጉዳዮች ብቻ ኢምባሲው እንዲናገርለት ስለሚፈልግ ነው በማለት አማጺው ቡድን ተችቷል። Via:ዋዜማ @Addis_Reporter
2 5312Loading...
07
የኮሪደር ልማት ሥራዎችን የክረምቱ ወቅት ከመግባቱ በፊት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ተባለ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን የክረምቱ ወቅት ከመግባቱ በፊት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ገለጹ። በአዲስ አበባ በአምስት አቅጣጫ የኮርደር ልማት ሥራ ከተጀመረ ከሁለት ወር በላይ ያስቆጠረ ሲሆን አራዳ፣ ልደታ፣ ቂርቆስ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶና ቦሌ ክፍለ ከተሞች ፕሮጀክቱ የሚሸፍናቸው አካባቢዎች ናቸው። የኮሪደር ልማቱ ከአራት ኪሎ ፒያሳና የአድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ፣ ከ4 ኪሎ አደባባይ በእንግሊዝ ኤምባሲ መገናኛ፣ ከሜክሲኮ ሳር ቤት በጎተራ ወሎ ሰፈር አደባባይ፣ ከ4 ኪሎ መስቀል አደባባይና ቦሌ ድልድይ እና በመገናኛ እስከ አዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን/ ኤግዚቢሽን ማዕከል/ ሥራው የሚከናወንባቸው ኮሪደሮች መሆናቸው ተጠቅሷል። የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ በኮሪደር ልማቱ የሚካሄዱት የፍሳሽ ማስወገጃ፣ የእግረኛና የተሽከርካሪ መንገድ፣ የታክሲና የአውቶቡስ መናኸሪያዎች ከተማዋን በሚመጥን መልኩ እየተገነቡ ነው። የኮሪደር ልማቱ በቀጣይ ለሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ትልቅ ልምድና ተሞክሮ የተገኘበት መሆኑንም አንስተዋል። @Addis_Reporter
3 0080Loading...
08
ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሏል! የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረችው ደራርቱ ለሜሳ ግድያ ወንጀል የተጠረጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ። የወረዳ አንድ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር በላቸው ፈረደ እንደገለጹት የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸው በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ልዩ ቦታው ሰላም ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ዕለቱ ረቡዕ ግንቦት 07/2016 ዓ/ም ከጧቱ በግምት 2:45 ላይ በሟች እና በተጠርጣሪው መካከል በተፈጠረው በሀሳብ ያለመግባባት ምክንያት በአሰቃቂ ሁኔታ ጀርባዋ ላይ በጩቤ በመውጋት የተማሪዋ ህይወት ሊያልፍ ችሏል ሲሉ ተናግረዋል። ምክትል ኮማንደሩ አክለውም ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ወንጀሉን የፈጸመውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ የሚገኝ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ የምርመራ ውጤቱን በአጭር ጊዜ ለህዝብ እንደሚገለጽም ተናግረዋል። በመጨረሻም የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ከዩኒቨርስቲው ግቢ ውጪ እና ተጠርጣሪው ከአዲስ አበባ ዱከም ከተማ አቋርጦ ወደ አሶሳ ከተማ ለስራ ጉዳይ በመምጣት የወንጀል ድርጊት የፈፀመ ሲሆን ነገር ግን በአንዳንድ ማህበራዊ ሚድያዎች ድርጊቱ የተፈጸመው በግቢ ውስጥ ነው በሚል የሚሰራጨው እና የብሔር ግጭት አስመስለው የሚወራው ፍጹም ከእውነት የራቀ እና ሁለቱም የአንድ ብሔር ተወላጅ እንዲሁም በጓደኝነት አብረው እየኖሩ የነበሩ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል። @Addis_Reporter
3 5540Loading...
09
ቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና ፐርፐዝ ብላክ አለመግባባታቸውን በስምምነት ፈቱ     ቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና ፐርፐዝ ብላክ በፍርድ ቤት መር አስማሚ በኩል አለመግባባታቸውን በስምምነት ፈተዋል።   የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሁለቱ ወገኖች መካከል የተፈፀመውን ስምምነት አፅድቆ ክሱን በመዝጋት እግዱም እንዲነሳ አዟል፡፡   በስምምነቱ መሰረት ቢጂአይ-ኢትዮጵያ የተከፈለውን የቀብድ ክፍያ ለፐርፐዝ ብላክ የመለሰ ሲሆን ፐርፐዝ ብላክ በፍርድ ቤት የጀመረው ክስም ተቋረጦ እግዱ ተነስቷል። @Addis_Reporter
3 2900Loading...
10
“ከ274 ሺህ በላይ የትግራይ ሠራዊት አባላት ትጥቅ ይፈታሉ” - ብሔራዊ የተሐድሶ ኮሚሽን የትግራይ ኃይል አባላትን ትጥቅ ለማስፈታት፣ ለማሰናበትና ከማህበረሰቡ ጋር ዳግም እንዲቀላቀሉ የሚያስችል የቅድመ ትግበራ ውይይት በመቀለ ተካሂዷል። በዚህ ሳምንት መጀመርያ ላይ በተካሄደው ምክክር ላይ የፌደራል መንግሥት ተወካዮች፣ የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት አመራሮች እና የአፍሪካ ኅብረት የስምምነት ክትትል፣ አረጋጋጭ እና አስከባሪ ኮሚቴ አባላት መገኘታቸውን የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ተመስገን ጥላሁን በኤክስ ገጻቸው አስታውቀዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዚህ ምክክር ላይ የትግራይ ተዋጊዎችን በመበተን እና ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ወደ ኅብረተሰቡ የማዋሃድ ፕሮግራም፣ ፕሮጀክቶች መንደፍ እንዲሁም የመጀመሪያው የትግበራ እቅድ ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተጠቅሶ ነበር። @Addis_Reporter
3 1210Loading...
11
የኬንያ መንግሥት፣ ከአዲሷ ላሙ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የሚገነባው አማራጭ መንገድ በዘጠኝ ወራት ውስጥ እንዲጠናቀቅ ለተቋራጩ ኩባንያ ትዕዛዝ መስጠቱን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ሰሞኑን በኬንያ የተከሰተው ከባድ ጎርፍ፣ ከላሙ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ የሚወስደውን መንገድ እንደቆረጠው ተገልጧል። መንገዱ በጎርፍ የተቆረጠው፣ ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት ለመጀመሪያ ጊዜ ላሙ ወደብ ላይ ያራገፈችው 60 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሞያሌ ከመጓጓዙ በፊት ነው። የኬንያ ትራንስፖርት ሚንስትር፣ ኪምቹምባ መርኮነን፣ ኢትዮጵያ በላሙ ወደብ እንድትጠቀም ካግባባን በኋላ፣ መንገዱ በጎርፍ መቆረጡ ለኬንያ ትልቅ ጉዳት ነው ማለታቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። @Addis_Reporter
2 8010Loading...
12
የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ባለሥልጣን፣ በአዲሱ የሲቪል ማኅበራት አዋጅ መሠረት በድጋሚ ያልተመዘገቡ 1 ሺህ 554 ሲቪል ማኅበራትን ፍቃድ ከሐምሌ 1 ጀምሮ እሰርዛለኹ በማለት አስጠንቅቋል። ሲቪል ማኅበራቱ ለዳግም ምዝገባ የሚያስፈልጓቸውን መስፈርቶች እስካሁን ማሟላት እንዳልቻሉ የጠቀሰው ባለሥልጣኑ፣ ማኅበራቱ እስከ 30 ድረስ ብቻ መስፈርቶችን አሟልተው መመዝገብ እንደሚችሉ ገልጧል። ባለሥልጣኑ፣ በሕጉ መሠረት የሚጠብቅቧቸውን ወቅታዊ ሪፖርቶች ያላቀረቡ 293 ሲቪል ማኅበራትን ሕጋዊ ሰውነት እንደሠረዘም አስታውቋል። በአዲሱ የሲቪል ማኅበራት አዋጅ መሠረት እስካኹን 2 ሺህ ማኅበራት ዳግም ምዝገባ አካሂደዋል ተብሏል። @Addis_Reporter
2 6024Loading...
13
0952400019 ሰላም እዴት ቆያቹ ቤተሰቦቼ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚኖሩም 1 � ለመፍትሄ ሀብት 2 � ለህማም 3 � ለመስተፋቅር 4 � ቡዳ ለበላው 5 � ለገበያ 6 � የዛር ውላጅ ለተዋረሰው 7 � ሚስጥር የሚነግር 8 � ራዕይ የሚያሳይ 9 � ለዓቃቤ ርዕስ 10�ለመክስት 11� ለቀለም(ለትምህርት) 12� ሰላቢ የማያስጠጋ 13� ለመፍትሔ ስራይ 14� ጋኔን ለያዘው ሰው 15� ለሁሉ ሠናይ 16� ለቁራኛ 17� ለአምፅኦ 23� ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ 24� ለግርማ ሞገስ 25� መርበቡተ ሰለሞን 26�ለዓይነ ጥላ 27�ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ 28� ለሁሉ መስተፋቅር 29� ጸሎተ ዕለታት 30� ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ 31� ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ) 32� ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ 33� ለድምፅ 34� ለብልት ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ 1� የመኖሪያ ፍቃድ ላላገኙ  መፍትሄ 2.� ከሀገር ውጪ ስራ እድል ላጡ 3.� ንግድ ጀምረው አልሳካ ላላቸው 4.� ገንዘብ ለሚያባክኑ 5� ሰውፊት መቆም መናገር ለሚፈሩ  6.� ለሀብት  ለንብረት ሚሆንም አለን 7�  ለስንፈተ ወሲብ መፍትሄ ለውጪ ሀገር ለሚኖሩትም እየሰራን ነው 8� ፍቅረኛ አልያዝ ላላቸውም አለን 9.� ትምህርት አልገባ ላለው 10� መስተፋቅር ፣የህዝብ መስተፋቅር 11.� ከሀገር መውጣት እየፈለጉ ላልተሳካላቸው ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን  ይምጡ ይደውሉ ያማክሩን ። ለምንኛውም ጥያቄዎ ይደዉሉ �0952400019   ባላቹህበት እንሰራለን ሰላም እዴት ቆያቹ ቤተሰቦቼ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን  የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል 1 � ለመፍትሄ ሀብት 2 � ለህማም 3 � ለመስተፋቅር 4 � ቡዳ ለበላው 5 � ለገበያ 6 � የዛር ውላጅ ለተዋረሰው 7 � ሚስጥር የሚነግር 8 � ራዕይ የሚያሳይ 9 � ለዓቃቤ ርዕስ 10�ለመክስት 11� ለቀለም(ለትምህርት) 12� ሰላቢ የማያስጠጋ 13� ለመፍትሔ ስራይ 14� ጋኔን ለያዘው ሰው 15� ለሁሉ ሠናይ 16� ለቁራኛ 17� ለአምፅኦ 23� ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ 24� ለግርማ ሞገስ 25� መርበቡተ ሰለሞን 26�ለዓይነ ጥላ 27�ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ 28� ለሁሉ መስተፋቅር 29� ጸሎተ ዕለታት 30� ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ 31� ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ) 32� ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ 33� ለድምፅ 34� ለብልት ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ 1� የመኖሪያ ፍቃድ ላላገኙ  መፍትሄ 2.� ከሀገር ውጪ ስራ እድል ላጡ 3.� ንግድ ጀምረው አልሳካ ላላቸው 4.� ገንዘብ ለሚያባክኑ 5� ሰውፊት መቆም መናገር ለሚፈሩ  6.� ለሀብት  ለንብረት ሚሆንም አለን 7�  ለስንፈተ ወሲብ መፍትሄ ለውጪ ሀገር ለሚኖሩትም እየሰራን ነው 8� ፍቅረኛ አልያዝ ላላቸውም አለን 9.� ትምህርት አልገባ ላለው 10� መስተፋቅር ፣የህዝብ መስተፋቅር 11.� ከሀገር መውጣት እየፈለጉ ላልተሳካላቸው ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን  ይምጡ ይደውሉ ያማክሩን ። ለምንኛውም ጥያቄዎ ይደዉሉ �0952400019☎️☎️☎️☎️🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
2 9110Loading...
14
የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በጩቤ ተወግታ ህይወቷ ማለፉ ተሰማ በአሶሳ ዩኒቨርስቲ በማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ በጅኦግራፊ ትምርት ክፍል ዉስጥ የ4ኛ ዓመት ተማሪ የነበረችዉ ደራርቱ ለሜሳ በስለት ተወግታ ህይወቷ ማለፉ ተሰምቷል። የአሶሳ ዩኒቨርስቲ የተማሪዋን ህልፈት ተከትሎ ባወጣዉ የሀዘን መግለጫ ግንቦት 07/2016 ዓ.ም ተማሪ ደራርቱ ህይወቷ ያለፈበትን ምክኒያት ሳይጠቅስ በድንገት ህይወቷ አልፏል ብሏል። ዩኒቨርስቲው በተማሪ ደራርቱ ለሜሳ ድንገተኛ ህልፈት የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በሙሉ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻልም ብሏል። እንደተሰማው መረጃ ከሆነ ግን ተማሪዋ በስለት ጥቃት ደርሶባት ህይወቷ ማለፉን ነዉ። የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ለተማሪ ደራርቱ ቤተሰቦች እና ወዳጆች ሁሉ መጽናናትን ተመኝቷል። @Addis_Reporter
3 8872Loading...
15
በመዲናዋ በዘጠኝ ወራቱ በተሽከርካሪ ግጭት ሳቢያ ከ7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የመንገድ መሰረተ ልማት ተጎድቷል በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በተሽከርካሪ ግጭት ሳቢያ ከ7 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ባለው የመንገድ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ። ባለፉት ዘጠኝ ወራት በመዲናዋ በደረሱ 286 የተሸከርካሪ ግጭት አደጋዎች ምክንያት በመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት መድረሱንም ነው ያስታወቀው። ከእነዚህ መካከል 89 አደጋዎች በቀለበት መንገድ ላይ እንዲሁም 197 ግጭቶች ደግሞ ከቀለበት መንገድ ውጪ የደረሱ ናቸው ብሏል። በተሽከርካሪ ግጭት ሳቢያ ጉዳት ከደረሰባቸው የመንገድ ሀብቶች መካከል የመንገድ መብራት ምሶሶዎች፣ የትራፊክ ምልክቶች፣ የአቅጣጫና ርቀት አመላካች ሰሌዳዎች፣ የእግረኛ መከላከያ አጥሮች፣ የመንገድ ማካፈያ ግንቦች እና የማንሆል ክዳኖች ይገኙበታል። ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በመንገድ ሃብት ላይ ጉዳት ያደረሱ ግለሰቦች የንብረት ውድመት ካሣ ክፍያ እንዲፈፀሙ እያደረገ እንደሚገኝም አራዳ ዘግቧል። @Addis_Reporter
3 6560Loading...
16
በሻሸመኔ ከተማ ንፋስ በቀላቀለ ከባድ ዝናብ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በከተማዋ ሙሉ በሙሉ ተቋረጠ በሻሸመኔ ከተማ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ መስመር ላይ ጉዳት በመድረሱ የኃይል አቅርቦት መቋረጡ ተገልጿል። በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን እሮብ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለ ከባድ ዝናብ በኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመርና የኃይል መስመር ተሸካሚ ምሶሶዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የሻሸመኔ ከተማ ዲስትሪክት ሃላፊ የሆኑት አቶ ጣሂር አህመድ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በዚሁ ምክንያት ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ጀምሮ በሻሸመኔ ከተማ እና በዙሪያው በሚገኙ ከተሞችና አካባቢዎች የሃይል አቅርቦቱ ተቋርጧል። የተቋረጠውን የሃይል አቅርቦት ለመመለስ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን በሻሸመኔ ከተማ እና በከተማዋ ዙሪያ የሚገኙ ደንበኞቻች አገልግሎቱ እኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቅ እናበአካባቢው የወደቁ ምሰሶዎች ጉዳት እንዳያደርስ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አቶ ጣሂር አህመድ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። @Addis_Reporter
3 6540Loading...
17
ፑቲን ቻይና ገብተዋል፡፡ የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለሁለት ቀናት ጉብኝት ቻይና መግባታቸው ታውቋል፡፡ ለአምስተኛ ጊዜ የፕሬዝዳንትነት ስልጣን የተረከቡት ፑቲን ከቻይናው ፕሬዝዳንት ሺጂንፒንግ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ለመነጋገር ነው ቻይና የገቡት፡፡ የዩክሬን ጉዳይ እና የኒዩክሌር ሃይል ልማት ፑቲን በቤጂንግ ቆይታቸው ከሚመክሩባቸው አበይት ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል። በቻይና ጉብኝት ከማድረጋቸው በፊት ከቻይና የዜና አገልግሎት ሺንዋ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሩሲያ ለንግግር ክፍት መሆኗን እና ሁለት አመት ያስቆጠረው ግጭት በሰላም እንዲፈታ እንደምትፈልግ ገልጸዋል። ፑቲን እንደገለጹት በፕሬዝደንት ሺ አማካኝነት ባለፈው ወር ይፋ የሆነው የቻይና እቅድ ከግጭቱ ጀርባ ያሉ ጉዳዮችን ከግምት ያስገባ ነው። "ቻይና የዩክሬይንን ቀውስ ለመፍታት ባላት አቀራረብ ላይ አዎንታዊ እይታ አለን" ብለዋል ፑቲን። ፑቲን ወደ ቻይና ያቀኑት የሁለቱን ሀገራት ግኑኝነት የተመለከተ ነው ቢባልም የዩክሬን ጦርነት በሰላም ለመቋጨት ስምምነት እንዲደረግ መንገድ ለመጥረግ ያለመ መሆኑም ተነግራል። ቭላድሚር ፑቲን በቻይና እና ሩስያ መካከል ዲፕሎማሲያዊ ግኑኝነት የተጀመረበት 75ኛ ዓመት እንደሚያከብሩም ነው የተገለጸው፡፡ ባለፉት 75 ዓመታት የሲኖ-ሩስያ ግኑኝነት በከባድ ግዜያት እየጠነከረ እና ተለዋዋጭ አለምአቀፋዊ ሁኔታዎችን ተቋቁሞ፤ አሁን ለሃያላን እና ጎረቤት ሀገራት ሞዴል እየሆነ ይገኛል ተብሏል፡፡ የቻይናው መሪ ሺጂምፒንግ እና ፑቲን በስልጣን ዘመናቸው ከ40 በላይ ግዜ እንደተገናቹ ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡ @Addis_Reporter
3 6691Loading...
18
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በአቃቂ ግዙፉን ዋና መስሪያ ቤት ግንባታ በ 1.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ሊገነባ ነዉ መንግስታዊዉ ነዳጅ አቅራቢ የሆነዉ ድርጅቱ 1.6 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚያደርግበትን ግዙፉን ህንፃ ለመገንባት የኮንትራት ዉል ስምምነት ማድረጉ ታዉቋል። በአቃቂ የሚገነባው 2B+G+14 ስማርት የችርቻሮ ጣቢያ ዋና መስሪያቤት በ 24 ወራት ዉስጥ ለማጠናቀቅ ዕቅድ መያዙን ካፒታል ሰምቷል። ኢኢአይጂ ከተባለው ተቋራጭ ጋር የዉል ስምምነት ያደረገው የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ አማካሪ ነዉ። @Addis_Reporter
3 6331Loading...
19
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ'ለት የተወያየበት የመንግሥት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ፣ የሠራተኞች የደመወዝ ቦርድ እንዲቋቁም የሚጠይቅ ድንጋጌ መያዙን ሪፖርተር ዘግቧል። አዲስ የሚቋቋመው የደመወዝ ቦርድ፣ ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ ከዘጠኝ በላይ አባላት እንደሚኖሩት በረቂቅ አዋጁ ላይ እንደተጠቀሰ ዘገባው አመልክቷል፡፡ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን፣ መንግሥት የሠራተኞችን ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚወስን ቦርድ እንዲያቋቁም በተደጋጋሚ ሲጠይቅ እንደቆየ አይዘነጋም። @Addis_Reporter
3 5253Loading...
20
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለሥልጣናት ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ጋር ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ ተወያይተዋል። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ፣ ውይይቱ በግጭት ማቆም ስምምነቱ አተገባበር ዙሪያ ባጋጠሙ ተግዳሮቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች ዙሪያ እንደኾነ በ"ኤክስ" ገጻቸው ገልጸዋል። ኹለቱ ወገኖች፣ በስምምነቱ አፈጻጸም ያጋጠሙ ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት የእስካኹኑን ሂደቶች መገምገም እንደሚያስፈልግ አጽንዖት እንደሰጡ ጌታቸው ጠቅሰዋል። @Addis_Reporter
3 5921Loading...
21
ባለፈው ሳምንት እሁድ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት አራት ሰላማዊ ሰዎች ተገድለው ሌሎች አምስት ሰዎች እንደቆሰሉ የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ነዋሪዎችን ጠቅሰው ዘግበዋል። ኹለቱ ሟቾች ተሬ ቀበሌ ጉሎ በተባለ ትምህርት ቤት ከመምህራን ጋር በወላጆች ስብሰባ ላይ የነበሩ ሲኾን፣ ሌሎቹ ኹለቱ ግን በአካባቢው የነበሩ አርሶ አደሮች እንደኾኑ ዘገባዎቹ አመልክተዋል። በጥቃቱ፣ ኹለት ሴት መምህራን እና አንድ ወንድ መምህር እንደቆሰሉ እንዲሁም በትምህርት ቤቱ ላይ ጉዳት እንደደረሰ ተገልጧል። ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት፣ በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግሥት ወታደሮች መካከል ግጭት እንዳልነበር እና የፋኖ ታጣቂዎችም ባካባቢው ሲንቀሳቀሱ እንዳልታዩ ነዋሪዎች ተናግረዋል ተብሏል። @Addis_Reporter
3 3661Loading...
22
ቻይና በቤልት ኤንድ ሮድ የመሠረተ ልማት መርሃ ግብር ከኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ጋር ትብብሯን እንደምትቀጥል የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዋንቢን ትናንት በሰጡት መግለጫ መናገራቸውን የቻይና ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ቃል አቀባይ ዋንቢን፣ ቻይና የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ኮርፖሬሽን አስተዳደርን ሰሞኑን ለኹለቱ አገራት ከማስረከቧ በፊት ከ2 ሺህ 800 በላይ ኢትዮጵያዊያን እና ጅቡቲያዊያን ሠራተኞችን ማሰልጠኗንና የባቡር ሐዲዱ ለኹለቱ አገራት ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማድረጉን መግለጣቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ሐዲዱን የገነባው የቻይናው የባቡር ሐዲድ ኮርፖሬሽን ሃላፊዎች በበኩላቸው፣ ቻይና ለባቡር ኮርፖሬሽኑ የቴክኒክ ድጋፍ መስጠቷንና ለባቡር ሐዲዱ ደጋፊ የኾኑ መሠረተ ልማቶችን መገንባቷን እንደምትቀጥል ተናግረዋል ተብሏል። ባቡሩ፣ በስድስት ዓመታት አገልግሎቱ ከ680 ሺህ በላይ ተጓዦችንና 9 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ካርጎ አጓጉዟል። @Addis_Reporter
3 0250Loading...
23
የገዢው ብልጽግና ፓርቲ እና ሕወሃት ከፍተኛ አመራሮች መቀሌ ውስጥ ሦስተኛውን ዙር የፖለቲካ ንግግር ጀምረዋል። ኹለቱ ወገኖች፣ በፖለቲካዊ ንግግር አጀንዳዎች ቅደም ተከተል ዙሪያ እንደመከሩና ዘላቂ ሰላም እንዲሠፍን በቁርጠኝነት ለመስራት እንደተስማሙ ገልጸዋል። የኮሚንኬሽን ሥራዎች የተጀመረውን የሰላም ሂደት የሚደግፉ እንዲኹም ግጭት ቀስቃሽ ከኾኑ ንግግሮች የተቆጠቡ እንዲኾኑ መግባባት ላይ መድረሳቸውንም ኹለቱ ወገኖች ጠቅሰዋል። በቅርቡ በራያ አላማጣ ወረዳ የተከሰተው ግጭት መከሰት ያልነበረበትና የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት የሚጣረስ መኾኑን የጠቀሱት ኹለቱ ወገኖች፣ ወደፊት ተመሳሳይ ችግሮችን በንግግር ለመፍታት መስማማታቸውንም አውስተዋል። ኹለቱ ወገኖች የግጭት ማቆም ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ፣ አመቺ ፖለቲካዊ ኹኔታዎችን ለመፍጠርም ከስምምነት መድረሳቸውንም ገልጠዋል።  @Addis_Reporter
2 6651Loading...
24
0952400019 ሰላም እዴት ቆያቹ ቤተሰቦቼ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚኖሩም 1 � ለመፍትሄ ሀብት 2 � ለህማም 3 � ለመስተፋቅር 4 � ቡዳ ለበላው 5 � ለገበያ 6 � የዛር ውላጅ ለተዋረሰው 7 � ሚስጥር የሚነግር 8 � ራዕይ የሚያሳይ 9 � ለዓቃቤ ርዕስ 10�ለመክስት 11� ለቀለም(ለትምህርት) 12� ሰላቢ የማያስጠጋ 13� ለመፍትሔ ስራይ 14� ጋኔን ለያዘው ሰው 15� ለሁሉ ሠናይ 16� ለቁራኛ 17� ለአምፅኦ 23� ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ 24� ለግርማ ሞገስ 25� መርበቡተ ሰለሞን 26�ለዓይነ ጥላ 27�ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ 28� ለሁሉ መስተፋቅር 29� ጸሎተ ዕለታት 30� ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ 31� ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ) 32� ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ 33� ለድምፅ 34� ለብልት ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ 1� የመኖሪያ ፍቃድ ላላገኙ  መፍትሄ 2.� ከሀገር ውጪ ስራ እድል ላጡ 3.� ንግድ ጀምረው አልሳካ ላላቸው 4.� ገንዘብ ለሚያባክኑ 5� ሰውፊት መቆም መናገር ለሚፈሩ  6.� ለሀብት  ለንብረት ሚሆንም አለን 7�  ለስንፈተ ወሲብ መፍትሄ ለውጪ ሀገር ለሚኖሩትም እየሰራን ነው 8� ፍቅረኛ አልያዝ ላላቸውም አለን 9.� ትምህርት አልገባ ላለው 10� መስተፋቅር ፣የህዝብ መስተፋቅር 11.� ከሀገር መውጣት እየፈለጉ ላልተሳካላቸው ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን  ይምጡ ይደውሉ ያማክሩን ። ለምንኛውም ጥያቄዎ ይደዉሉ �0952400019   ባላቹህበት እንሰራለን ሰላም እዴት ቆያቹ ቤተሰቦቼ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን  የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል 1 � ለመፍትሄ ሀብት 2 � ለህማም 3 � ለመስተፋቅር 4 � ቡዳ ለበላው 5 � ለገበያ 6 � የዛር ውላጅ ለተዋረሰው 7 � ሚስጥር የሚነግር 8 � ራዕይ የሚያሳይ 9 � ለዓቃቤ ርዕስ 10�ለመክስት 11� ለቀለም(ለትምህርት) 12� ሰላቢ የማያስጠጋ 13� ለመፍትሔ ስራይ 14� ጋኔን ለያዘው ሰው 15� ለሁሉ ሠናይ 16� ለቁራኛ 17� ለአምፅኦ 23� ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ 24� ለግርማ ሞገስ 25� መርበቡተ ሰለሞን 26�ለዓይነ ጥላ 27�ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ 28� ለሁሉ መስተፋቅር 29� ጸሎተ ዕለታት 30� ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ 31� ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ) 32� ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ 33� ለድምፅ 34� ለብልት ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ 1� የመኖሪያ ፍቃድ ላላገኙ  መፍትሄ 2.� ከሀገር ውጪ ስራ እድል ላጡ 3.� ንግድ ጀምረው አልሳካ ላላቸው 4.� ገንዘብ ለሚያባክኑ 5� ሰውፊት መቆም መናገር ለሚፈሩ  6.� ለሀብት  ለንብረት ሚሆንም አለን 7�  ለስንፈተ ወሲብ መፍትሄ ለውጪ ሀገር ለሚኖሩትም እየሰራን ነው 8� ፍቅረኛ አልያዝ ላላቸውም አለን 9.� ትምህርት አልገባ ላለው 10� መስተፋቅር ፣የህዝብ መስተፋቅር 11.� ከሀገር መውጣት እየፈለጉ ላልተሳካላቸው ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን  ይምጡ ይደውሉ ያማክሩን ። ለምንኛውም ጥያቄዎ ይደዉሉ �0952400019☎️☎️☎️☎️🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
2 8301Loading...
25
የስሎቫኪያ ጠቅላይ ሚኒስትር በጥይት ተመቱ፡፡ * የስሎቫኪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ፊኮ በተተኮሰባቸው ጥይት ቆስለው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተሰምቷል፡፡ ዛሬ ከሰአት በኋላ በሀንድሎቫ ከተማ በተተኮሰባቸው ጥይት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መቁሰላቸውን የስሎቫኪያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ከጥቃቱ ጋ በተያያዘ አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሉንም የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ገልጸዋል፡፡ @Addis_Reporter
3 7983Loading...
26
ባለፉት 9 ወራት ከ1ሺህ በላይ ሃሰተኛ ሰነዶች ለአገልግሎት ቀርበው እንደነበር የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አስታወቀ አገልግሎቱ ባለፉት 9 ወራት በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተማ በሚገኙ ቅርንጫፎቹ በቀን በአማካይ ከ6 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተገልጋዮች አገልግሎት ሲሰጥ እንደቆየ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡ የተቋሙ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አለምእሸት መሸሻ፤ባለፉት 9 ወራት ከ715 ሺህ በላይ ጉዳዮች ያለቀጠሯቸው እንደተስተናገዱ ገልጸው፤ በአጠቃላይ ከ1 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ተገልጋዮች አገልግሎት መሰጠቱን አስታውቀዋል፡፡ ከገቢም አንፃር ከአምናው የተሻለ አፈጻጸም እንደተመዘገበ ነው የተናገሩት፡፡ በተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጥ ሒደት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት መሰረታዊ ችግር እንደነበር የተናገሩት ባለሙያው፤ በ9 ወራት አፈጻጸም ከ1ሺህ በላይ ሃሰተኛ ሰነዶች እንደተገኙ እና ከእነዚህም ውስጥ የማንነት መታወቂያ ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዝ ገልጸዋል፡፡ ከሀሰተኛ ማንነት ጋር ተይይዞ የሚቀርቡ ሰነዶች ለተቋሙ ስራ ተግዳሮት እንደፈጠሩበትም ነው የአገልግሎቱ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚው የተናገሩት፡፡ ተቋሙ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ማሻሽያ እንዳደረገ የገለጹት አቶ አለምእሸት፤ በቀጣይ ጊዜያት ከሃሰተኛ የሰነድ ስርጭት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ዘመናዊ አሰራሮች ተግባራዊ መደረጋቸው ይቀጥላል ብለዋል፡፡ Via፡ መናኸሪያ ሬዲዮ @Addis_Reporter
3 3421Loading...
27
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የሚያዚያ ወር ሀገር አቀፍ የዋጋ ግሽበቱ 23.3 በመቶ ሆኖ መመዝገብን አስታውቋል የዋጋ ግሽበቱ በመጋቢት ወር ከነበረበት 26.2 በመቶ ወደ 23.3 በመቶ በመሆን ቅናሽ አሳይቷል ብሏል። በወሩ ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ምግብ ነክ ዕቃዎች 27 በመቶ እንዲሁም ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች ደግሞ 18 በመቶ ድርሻ መያዛቸዉ ታዉቋል ። @Addis_Reporter
3 6401Loading...
28
አሜሪካ ከቻይና በሚገቡ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ቀረጥን በሶስት እጥፍ አሳደገች የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ከቻይና በሚገቡ የኤሌክትሪክ መኪናዎች፣ በፀሃይ ብርሃን የሚሰሩ ባትሪዎች እንዲሁም ብረቶች ላይ የሚጣለውን ቀረጥ በሶስት እጥፍ መጨመሩን አስታውቋል፡፡ በተለይም በድንበር በሚገቡ የቻይና የኤሌክትሪክ መኪናዎች ላይ የሚጣለው ቀረጥ ከነበረበት 25 በመቶ አራት እጥፍ ከፍ እንዲል የተደረገ ሲሆን በባትሪዎች እና ኮምፒውተሮች ላይ የሚጣለው ታሪፍ ደግሞ ከ25 በመቶ በእጥፍ እንዲያድግ መደረጉ ተገልጿል። ውሳኔው ቻይና በመኪና ንግድ ለምትከተለው ፖሊሲ ምላሽ ለመስጠት እና በአሜሪካ ከመኪና ምርት ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ የስራ እድሎችን ለማስጠበቅ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ ቻይና በበኩሏ በአሜሪካ መንግስት የተላለፈውን ውሳኔ እንድምትቃወም ጠቅሳ፤ ለዚህ ያተገባ የታሪፍ ውሳኔ የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ አስታውቃለች፡፡ በውሳኔው መሰረትም አሜሪካ ከቻይና ከሚገቡ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ተጨማሪ 18 በሊዮን ዶላር የቀረጥ ገንዘብ ልታገኝ እንደምትችል ተጠቁሟል፡፡ ፕሬዚዳንት ባይደን በቻይና ላይ ያሳለፉት ከፍተኛ የቀረጥ ጭማሪ በአሜሪካ በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የቻይናን ከፍተኛ የመኪና ሽያጭ ከሚቃወሙ አሜሪካውያን ድምፅ ለማግኘት ነው መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ @Addis_Reporter
3 5770Loading...
29
የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ሰዉ ሰራሽ የነዳጅ እጥረት እንዲፈጠር በሚያደርጉ ነዳጅ ማደያዎች ላይ ከማሸግ የዘለለ እርምጃ መዉሰድ የሚያስችለውን አዋጅ ማዘጋጀቱ ተነገረ ባለስልጣኑ ባዘጋጀው በዚህ አዋጅ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት በሚፈጥሩ ሕገ ወጦች ላይ እስራትና የገንዘብ ቅጣት እርምጃ መውሰድ የሚያስችሉ አንቀጾች መካተታቸውን ተጠቁመዋል። አዋጁ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡን ተከትሎ በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ስራ እንደሚገባ የተነገረ ሲሆን በነዳጅ ማደያዎች ነዳጅ እያለ እንደሌለ ማስመሰል፣ የነዳጅ ግብይትን በጥሬ ገንዘብ መሸጥ፣ ነዳጅን በተለያዩ ስፍራዎች ደብቆ ማስቀመጥና የመሳሰሉትን ህገወጥ አሰራሮችን ሊያስቀር እንደሚችል ካፒታል ከተቋሙ ያገኘው መረጃ ያመለክታል ። @Addis_Reporter
1890Loading...
30

3 4272Loading...
31
በኢትዮጵያ 95 በመቶ የሚሆኑት የቴሌቭዥን ተጠቃሚዎች በኢትዮ-ሳት ስርጭት እያገኙ መሆኑ ተገለፀ በኢትዮጵያ ከ18.2 ሚሊዮን ቲቪ ተጠቃሚዎች መካከል 17 ሚሊዮን ወይም 95 በመቶ የሚሆኑት በኢትዮ-ሳት ስርጭት እያገኙ መሆኑን የዓለም አቀፉ የሳተላይት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢ (SES) አስታወቀ። በኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ተጠቃሚዎች ቁጥር በ 2017 ከነበረበት በ400% አድጎ ተጠቃሚዎቹ 18.2 ሚሊዮን መድረሳቸው ሲገልፅ ከ2021 ጀምሮ የኢትዮ ሳት የኤችዲ ቲቪ ቻናሎች ከ15 በመቶ ወደ 62 በመቶ ማደጉ ተነግሯል። በአሁኑ ወቅት በሳተላይቱ 136 ቻናሎች ለ17 ሚሊዮን የቴሌቪዥን ባለቤቶች እየተሰራጩ ሲሆን ከ136 የሬዲዮና የቴሌቪዥን ቻናሎች መካከል ደግሞ 70 የሚሆኑት የሀገር ውስጥ ቻናሎች መሆናቸው ተጠቁሟል። 'ኢትዮ-ሳት' ን የኢትዮጵያ ሚዲያ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ)፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስተሮች ማህበር (ኤቢቢ) እና SES በጋራ በመሆን ከ4 አመት በፊት ይፋ እንዳደረጉት ይታወሳል። @Addis_Reporter
3 2620Loading...
32
በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ ባለፈው ዕሁድ'ለትና ሰኞ'ለት በተፈጸመ ጥቃት 9 ሰዎች እንደተገደሉ መስማቱን ዶይቸቨለ ዘግቧል። በወረዳው ባንድ ቀበሌ ውስጥ ታጣቂዎች የከፈቱትን ጥቃት ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት ከተገደሉት መካከል፣ ሦስቱ የክልሉ ጸጥታ ኃይል ባልደረቦች እንደኾኑ የክልሉ ፖሊስ ማረጋገጡን ዘገባው አመልክቷል። በጥቃቱና ግጭቱ ሳቢያ፣ ጋምቤላ ከተማን ከኢታንግ ከተማ ጋር በሚያገናኘው መንገድ ላይ የትራንስፖርት ግንኙነት ተቋርጧል ተብሏል። የአኝዋክና ኑዌር ብሄረሰቦች የሚኖሩባት ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ ካለፈው ዓመት ጀምሮ የበርካታ ንጹሃን ሰዎች ሕይወት የጠፋባቸው ግጭቶች ተከስተዋል። @Addis_Reporter
3 2080Loading...
33
መንግሥት የመንግሥት ሠራተኞች ቅጥርና ምደባ የአገሪቱን ብሄረሰቦች ብዝኀነትና የጾታና የአካል ጉዳተኞችን ተዋጽዖ የጠበቀ እንዲኾን የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል። ምክር ቤቱ፣ በረቂቅ አዋጁ ላይ ትናንት ተወያይቷል። ረቂቅ አዋጁ፣ በመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ ጭማሪ፣ ደሞዝ እርከን፣ ክፍያና ጥቅማጥቅሞች ላይ ማሻሻያ እንዳደረገም ተገልጧል። የአነሳ ብሄረሰቦችና የማኅበረሰብ ክፍሎች በመንግሥት መስሪያ ቤቶች በቅጥር፣ ምደባ፣ ዝውውር፣ በሥራ ደረጃ እድገት፣ በትምህርትና ሥልጠና ረገድ ተጨማሪ መንግሥታዊ ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ረቂቅ አዋጁ ይደነግጋል። ምክር ቤቱ፣ ረቂቅ አዋጁን ጉዳዩ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል። @Addis_Reporter
3 26010Loading...
34
ካናዳ፣ ኢትዮጵያ የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ ለማስፈታት፣ ከኅብረተሰቡ ጋር ለማቀላቀልና መልሶ ለማቋቋም የሚውል 14 ሚሊዮን ዶላር መለገሷን በኢትዮጵያ የካናዳ ኤምባሲ አስታውቋል። ካናዳ ይህን ያስታወቀችው፣ የዓለማቀፍ ልማት ሚንስትሯ አሕመድ ሁሴን ዛሬ በትግራይ ተገኝተው የትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎች ትጥቅ ፈትተው የሚገቡበትን ካምፕ በጎበኙበት ወቅት ነው። ሚንስትሩ፣ የቀድሞ ታጣቂዎችን ከግጭት ማግስት የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች እንደሚገነዘቡ መናገራቸውን ኢምባሲው ገልጧል። ሚንስትሩ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ የፕሬቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲኾን ካናዳ ድጋፍ እንደምታደርግ ቃል መግባታቸው ተገልጧል።  @Addis_Reporter
3 3640Loading...
ብሄራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን፣ በቀጣዮቹ ኹለት ወራት በትግራይ በመጀመሪያው ዙር 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት መልሶ ለማቋቋም እንዳቀደ መናገሩን ዶይቸቨለ ዘግቧል። ኮሚሽኑ ይህን የገለጠው፣ በትጥቅ ማስፈታትና መልሶ ማቋቋም ሂደቱ ዙሪያ መቀሌ ላይ አገር ዓቀፍ ምክክር መካሄዱን ተከትሎ ነው። ኮሚሽኑ በአገር ዓቀፍ ደረጃ ለሚተገብረው ዕቅድ ባጠቃላይ 750 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል ይላል። ባጠቃላይ በመልሶ ማቋቋም መርሃ ግብሩ የሚታቀፉት የቀድሞ ተዋጊዎች 274 ሺህ 800 ያህል መኾናቸውንም ኮሚሽኑ ገልጧል። @Addis_Reporter
إظهار الكل...
መንግሥት ያቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ ትናንት በሦስት የአውሮፕላን በረራዎች በአስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 141 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ከሳውዲ ዓረቢያ መልሷል። ከትናንት ተመላሾች መካከል፣ 744ቱ ወንዶች ሲኾኑ፣ 377ቱ ሴቶች እንዲኹም 20ዎቹ ጨቅላ ሕጻናት እንደኾኑ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ገልጧል። ኮሚቴው ከሳዑዲ ዓረቢያ ለመመለስ ካሰባቸው 70 ሺህ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች፣ ከሚያዝያ መጀመሪያ ጀምሮ ከ24 ሺህ 500 በላይ የሚኾኑትን መልሷል። @Addis_Reporter
إظهار الكل...
👍 2
የስዊድኗ ስቶክሆልም ከተማ በአገሪቱ የሚኖሩ ኤርትራዊያን የዘንድሮውን የኤርትራ የባሕል ፌስቲቫል እንዲያካሂዱ መፍቀዷን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘገበዋል። ባለፈው ዓመት ነሃሴ በስቶክሆልም በተከበረው የኤርትራዊያን ፌስቲቫል ላይ የኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ተጋጭተው፣ ብጥብጥና ኹከት መፈጠሩ ይታወሳል። የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ብዙ ተቃውሞዎች ቢቀርቡበትም ኤርትራዊያን ፌስቲቫሉን እንዲያከብሩ የፈቀደው፣ በስዊድን ሕገመንግሥት ጥበቃ የሚደረግለት መብት በመኾኑ እንደኾነ ዘገባዎቹ አመልክተዋል። በአውሮፓ አገራት በየዓመቱ የሚከበረው የኤርትራዊያን ፌስቲቫል፣ በተለይ ካለፉት ኹለት ዓመታት ወዲህ በጎራ የተከፈሉ ኤርትራዊያን ኹከት የሚፈጥሩበት መድረክ ኾኗል። @Addis_Reporter
إظهار الكل...
🥰 1
፨✝✝ መርጌታ  የባህል ህክምና አዋቂና ቀማሚ✝✝፨                          📞0952400019                            📞0952400019 ከሀገር ውጭም ሆነ ከሀገር ውስጥ ላላችሁ በርቀት ምክንያት መምጣት ላልቻላችሁ ባላችሁበት መስራት እና መላክ እችላለሁ።                                ↘️ የምንሰጣቸዉ የጥበብ አገልግሎቶች : 1 =ለሀብት 2 =ለገበያ 3  =ለወሲብ ስንፈት (ለውፍረት:ለቁመት) 4 =ለመስተፋቅር 5 =ጥይት ለማያስመታ 6 =ለቁማር 7 =ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር) 8 =ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ) 9 =ለዓቃቤ ርዕስ 10 =ለመክስት 11 =ቡዳ ለበላው 12 =ሰላቢ የማያስጠጋ 13 =ለመፍትሔ ሀብት 14 =ለመፍትሄ ስራይ 15 =ለሁሉ ሠናይ 16 =ለህማም 17 =ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ) 18 =ለመድፍነ ፀር 19 =ለማንኛውም አይነት ቁስል መሻሪያ 20 =ለበረከት 21 =ለከብት መስተሐድር(ከብት እንዳይጠፋ) 22= አፍዝዝ አደንግዝ(እፀ_መሰውር) 23 =ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ) 24 =ለግርማ ሞገስ 25 =መርበቡተ ሰለሞን 26 =ለዓይነ ጥላ 27 =የሌባ ገትር(ሌባ የማያስገባ) 28 =ለሁሉ መስተፋቅር 29 =ለፊት ማዲያት 30 =ለእድል(ለቁማርም ቢሆን) 31 =ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ) 32 =ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ 33 =ለመካንነት መሻሪያ 34 =ለኪንታሮት በሽታ(በሚቀባ የሚሰጥ) አገልግሎት(ምናልባት ያለ ኮከባቸው የተጋቡ ካሉ አስማምቶ የሚያኖር መድሀኒት ማሳሰቢያ፦🌿የሰውን ልጅ ለመጣል ለማሳበድ በ አጠቃላይ ከህይወት መስመር ለማውጣት አንሰራም🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿               📞0952400019 ለጥያቄዎ 📞0952400019ይደውሉልን::
إظهار الكل...
🤔 1
Photo unavailableShow in Telegram
በ10 አመታት ውስጥ ሰዎችን ማርስ ላይ ማስፈር እንጀምራለን-ኤለን መስክ በቀጣይ 10 አመታት ውስጥ ሰዎችን ማርስ ላይ ማስፈር እንደሚጀመርና በ30 አመት ውስጥ ማርስ ላይ ዘመናዊ ከተማ እንደሚገነባ የስፔስ ኤክስ መስራች ኤለን መስክ ገልጿል። የማርስ ከተማ ግንባታን እውን ለማድረግ ስፔስ ኤክስ በርካታ የቅኝት ሳተላይቶችን በቅርቡ እንደሚልክ ማስታወቁን የዴይሊ ስታር ዘገባ ያመላክታል። "በጥቂት አመታት ውስጥ ሰዎችን በማርስ ላይ የማስፈር ዕቅዳችንን ዕውን እናደርጋለን" ብሏል የ52 ዓመቱ ቢሊየነር ኤለን መስክ። "ከ10 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሰዎችን ማርስ ላይ ማስፈር እንጀምራለን፤ ከበረታን እስከ 20 ዓመት፣ በእርግጠኝነት ግን በ30 ዓመት ውስጥ ዘመናዊ ከተማ በማርስ ላይ እንገነባለን" ብሏል ኤለን መስክ። እ.አ.አ 2002 የተመሰረተው ስፔስኤክስ ወደ አለማቀፉ የህዋ ጣቢያ ለመጀመሪያ ጊዜ መንኮራኩር እና ጠፈርተኞችን የላከ የግል ኩባንያ ነው። @Addis_Reporter
إظهار الكل...
👍 10🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ መንግሥት የአሜሪካው አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ከትናንት ወዲያ ባደረጉት ንግግር ላይ የታጠቁ ኃይሎችን በስም ጠቅሰዋል በማለት መውቀሱ "ለችግሮች እውቅና ለመስጠት" እና ግጭቶችን በንግግር ለመፍታት ፍላጎት እንደሌለው ያሳያል" ሲል ዛሬ ምላሽ ሰጥቷል። ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በአምባሳደሩ ንግግር የተንጸባረቁ "ስህትቶችን" ለማስተካከል ከኢምባሲው ጋር እንደሚሠራ መግለጡን በተመለከተም፣ መንግሥት የሚፈልጋቸውን ጉዳዮች ብቻ ኢምባሲው እንዲናገርለት ስለሚፈልግ ነው በማለት አማጺው ቡድን ተችቷል። Via:ዋዜማ @Addis_Reporter
إظهار الكل...
👍 10 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኮሪደር ልማት ሥራዎችን የክረምቱ ወቅት ከመግባቱ በፊት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ተባለ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን የክረምቱ ወቅት ከመግባቱ በፊት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ገለጹ። በአዲስ አበባ በአምስት አቅጣጫ የኮርደር ልማት ሥራ ከተጀመረ ከሁለት ወር በላይ ያስቆጠረ ሲሆን አራዳ፣ ልደታ፣ ቂርቆስ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶና ቦሌ ክፍለ ከተሞች ፕሮጀክቱ የሚሸፍናቸው አካባቢዎች ናቸው። የኮሪደር ልማቱ ከአራት ኪሎ ፒያሳና የአድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ፣ ከ4 ኪሎ አደባባይ በእንግሊዝ ኤምባሲ መገናኛ፣ ከሜክሲኮ ሳር ቤት በጎተራ ወሎ ሰፈር አደባባይ፣ ከ4 ኪሎ መስቀል አደባባይና ቦሌ ድልድይ እና በመገናኛ እስከ አዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን/ ኤግዚቢሽን ማዕከል/ ሥራው የሚከናወንባቸው ኮሪደሮች መሆናቸው ተጠቅሷል። የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ በኮሪደር ልማቱ የሚካሄዱት የፍሳሽ ማስወገጃ፣ የእግረኛና የተሽከርካሪ መንገድ፣ የታክሲና የአውቶቡስ መናኸሪያዎች ከተማዋን በሚመጥን መልኩ እየተገነቡ ነው። የኮሪደር ልማቱ በቀጣይ ለሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ትልቅ ልምድና ተሞክሮ የተገኘበት መሆኑንም አንስተዋል። @Addis_Reporter
إظهار الكل...
👍 9 1
Photo unavailableShow in Telegram
ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሏል! የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረችው ደራርቱ ለሜሳ ግድያ ወንጀል የተጠረጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ። የወረዳ አንድ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር በላቸው ፈረደ እንደገለጹት የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸው በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ልዩ ቦታው ሰላም ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ዕለቱ ረቡዕ ግንቦት 07/2016 ዓ/ም ከጧቱ በግምት 2:45 ላይ በሟች እና በተጠርጣሪው መካከል በተፈጠረው በሀሳብ ያለመግባባት ምክንያት በአሰቃቂ ሁኔታ ጀርባዋ ላይ በጩቤ በመውጋት የተማሪዋ ህይወት ሊያልፍ ችሏል ሲሉ ተናግረዋል። ምክትል ኮማንደሩ አክለውም ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ወንጀሉን የፈጸመውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ የሚገኝ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ የምርመራ ውጤቱን በአጭር ጊዜ ለህዝብ እንደሚገለጽም ተናግረዋል። በመጨረሻም የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ከዩኒቨርስቲው ግቢ ውጪ እና ተጠርጣሪው ከአዲስ አበባ ዱከም ከተማ አቋርጦ ወደ አሶሳ ከተማ ለስራ ጉዳይ በመምጣት የወንጀል ድርጊት የፈፀመ ሲሆን ነገር ግን በአንዳንድ ማህበራዊ ሚድያዎች ድርጊቱ የተፈጸመው በግቢ ውስጥ ነው በሚል የሚሰራጨው እና የብሔር ግጭት አስመስለው የሚወራው ፍጹም ከእውነት የራቀ እና ሁለቱም የአንድ ብሔር ተወላጅ እንዲሁም በጓደኝነት አብረው እየኖሩ የነበሩ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል። @Addis_Reporter
إظهار الكل...
👍 14🤯 1
ቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና ፐርፐዝ ብላክ አለመግባባታቸውን በስምምነት ፈቱ     ቢጂአይ-ኢትዮጵያ እና ፐርፐዝ ብላክ በፍርድ ቤት መር አስማሚ በኩል አለመግባባታቸውን በስምምነት ፈተዋል።   የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሁለቱ ወገኖች መካከል የተፈፀመውን ስምምነት አፅድቆ ክሱን በመዝጋት እግዱም እንዲነሳ አዟል፡፡   በስምምነቱ መሰረት ቢጂአይ-ኢትዮጵያ የተከፈለውን የቀብድ ክፍያ ለፐርፐዝ ብላክ የመለሰ ሲሆን ፐርፐዝ ብላክ በፍርድ ቤት የጀመረው ክስም ተቋረጦ እግዱ ተነስቷል። @Addis_Reporter
إظهار الكل...
👍 4

👍 6🤔 4 2