EECSF
الذهاب إلى القناة على Telegram
ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::
إظهار المزيد508
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
508
#Chain_prayer(Chain48)_update
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
📌 3ኛ ሳምንት
ርዕስ - መልካሙን ህይወት መኖር
ቀን 2፦ 1ኛ ጴጥሮስ 3:15- 22
📌 እግዚያብሔር በህይወታችን የመጀመሪያ እንድናደርገው ፣ ጌታ አድርገን እንድንሾመው
ሌላ ከዛ ውጭ በልባችን የከበረ፣ ጊዜችንን፣ አእምሮአችንን የያዘ ነገር
ካለ ንስሀ እየገባን
አግዚያብሔር በህይወታችን እዲከብር እንፀልይ
📌 የፈሰሰው የክርስቶስ ደም ከአብ ጋር ስላስታረቀን በእግዚያብሄር ፊት መቅረብ ስለቻልን
ደሙ ዛሬም ከሀጢያታችን ሊያነፃን ሀይል ስላለው
እግዚያብሔርን እያመሰገንን እንፀልይ
📌 መልካም በማድረጋችን መከራ ቢገጥመን ታጋሾች ሆነን አሁንም መልካም ማድረጋችንን እንድንቀጥል እግዚያብሔር እንዲረዳን እንፀልይ
📖 በቃል የሚጠና ጥቅስ፦
❝" ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥"
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3: 18)
**
የሕንፃ ኮሌጅ(EiABC) ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት
2012 ዓ. ም.
508
እንዲህ ፕሮግራማችንን ጨርሰናል አብራችሁን ስለነበራችሁ ጌታ ይባርካችሁ😊
❝እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።❞
ዕብራውያን 12: 1-2
508
ማስታወቂያ
📌 በጌታ ፊት እየተጋችሁ እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን አሁንም ለእኛ ደስታችን እርሱ ነውና ሳንታክት ወደ ፀጋው ዙፋን በዕምነት እንቅረብ
📌 እባካችሁ ማገልገል የምትፈልጉ በጌታ እንለምናችኃለን አሳውቁን!!!!!!!!!!
ተባረኩ
508
ስለ ቃሉ ጊዜ ጌታችን የተመሰገነ ይሁን!!
በሕያው ቃሉ መሰረት የምንኖር እና የምናድግ እንድንሆን ጌታ ይርዳን፤ አሜን። መልዕክቱን ያካፈለንን ወንድም አበባየሁ እግዚአብሔር ይባርክልን፣ያሳድግልን!!
508
አሜን! ስለ ፀሎት ጊዜው አምላካችን ይመስገን
አሁን ወደ ዝማሬ እናልፋለን😊
ዛሬ በዝማሬ የሚያገለግለን ተጋባዥ ወንድማችን ዮሴፍ ነው። ጌታን አብረን እናመልካለን። በዝማሬው ተባረኩበት አብረን እናምልክ።
508
አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ ስለ ሁሉ እጅግ አድርገን እናመሰግንሀለን ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን። በምሕረትህ ብዛት ዛሬም በሕይወት አለንና አንተ ብቻ ተመስገን። ሁላችንን ከክፉ ጠብቀሀልና እናመሰግንሀለን። ዛሬም ደግሞ እንድታስተምረን እንድትገስፀን አለንና አስተምረን ገስፀን። የሳተውን የምትመልስ የወደቀን የምታነሳ አንተው ነህና እንድትጎበኘን እፀልያለሁ። ሁሉ ለአንተ ክብር ይሁን። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፤ አሜን።
508
ሰላም🤗🤗 የክርስቶስ ኢየሱስ ለሆናችሁ ለእናንተ ይሁን!! ፕሮግራማችንን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጀምራለን፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር አምላክ በምህረቱ ጠብቆን ለዛሬ ደርሰናልና ክብር ሁሉ ለእርሱ ይሁን፡፡ ዛሬም የምንተናነፅበትን እና የምናድግበትን መልካም ፍሬ አብረን እንካፈላለን
አብራችሁን ቆዩ።😊
508
#Chain_prayer(Chain48)_update
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
📌 3ኛ ሳምንት
ርዕስ - መልካሙን ህይወት መኖር
ቀን 1፦ 1ኛ ጴጥሮስ 3:8- 15
📌 ሰዎችን እንደራሳችን አድርገን መውደድ እንድንችል ፤ ሁልጊዜ ቅንነት፣ ትህትና፣ ርህራሄ፣ ይቅር ባይነትን ለሰዎች ማሳየት እንድንችል
እግዚአብሔር እንዲረዳን እንፀልይ
📌 እንደመጣልን ወይም በዛ ሰአት በተሰማን ስሜት እንዳንናገር ፤ የሚሰድቡንን መባረክ ፣ የሚረግሙንን መመረቅ፣ ለሰዎች መፀለይ እንድንችል እግዚአብሔር ማስተዋል ፣ ሀይልን እንዲሰጠን እንፀልይ
⭕️ ስለ ክርስቶስ ስንጠየቅ ለመመለስ ሁሌ ዝግጁ እንድንሆን እግዚአብሔር እንዲረዳን
እንፀልይ
📖 በቃል የሚጠና ጥቅስ፦
❝ " ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤"
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3: 10)❞
**
የሕንፃ ኮሌጅ(EiABC) ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት
2012 ዓ. ም.
508
✨ጊዜ እና ለውጥ ✨
ዛሬ ባለንበት ዘመን በምድራችን የቆዳ ስፋት ልክ ብዙ ለውጥን የሚያመጡ ፈተናዎች ተከናውነዋል። ደግሞም ከሆነው በላይ የፈተና ንፋስ በዚህች ምድር ይዘረጋል።
በነዚህ ዘመናት ውስጥ እንደየግለሰቡ የልብ መሞላት ልክ ለውጥ ይመጣል።
በመጣውና በሚመጣው የለውጥ ንፋስ ሰነፎችን ልባቸውን አውርዶ መሸበርን በልባቸው ያስቀምጣል።
ይን ንፋስ የሰነፍ ልብን ከደመና በታች አውርዶ ጉልበታቸወን እንደሰለለች የአዛውንት ጉልበት ያብረከርከዋል። እነዚያም የተሸነፉ እግሮች መሬትን ረግጠው መቆም የተሳናቸው ለንፋሱ ጉልበት የተረቱ ናቸው።
ነገር ግን ብልህ ልቡ ከደመና በላይ በከፍታ ጥግ ይራመዳል። የሚመጣው ንፋስ ለእርሱ የፍርሃት ምንጭ ሳይሆን የከፍታው ምክንያት ነው። ንፋሱ እንደ እንጀራ ይሆንለታል። እናም በዘመን ዝቅታ ውስጥ ከፍ ብሎ ይበራል። ለብልህ የዘመን ፈተና ከፍታው ለሰነፍ ውድቀቱ ነው።
የአባቴ ልጆች ብልሆች ሁኑልኝ!
ልባችንን ከደመናው በላይ ባለው የከፍታ ጥግ ስር በመታመን ይሸሸግ።
አንድ ነገር ግን በሙሉ ልብ እርግጠኛ ሆኜ እነግራችኋለሁ በጌታ የእውነት ቃል ላይ ልቡን የሸሸገ እርሱ ያገኛታል በመከራም ጊዜ ከፍታ የእርሱ ነው።
አበባየሁ አናቶ
