cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ጉዞ ወደ መልካምነት🙏🙏

╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗ ║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣ ╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩╩═╝ ✨#STAY_AT_HOME⚡ 🙏 @masre12🙏 እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉና ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን ማንኛውም አይነት ፅሁፎች ከየትም እያሰባሰብን እናቀርባለን። አስታየቶን ይስጡን @Masre12 @Masre12

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
196
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ናችሁ🙏 ✍ይቺን ለቅምሻ! ከ"መግባት እና መውጣት " የተቀነጨቡ አንቀፆች (በእውቀቱ ስዩም) ምኡዝ እንዲህ አለ 1 “ የሰው ልጅ ተገንጣይ እንስሳ ነው፤ ባለፈው አንዱ “ የአዲሳባ ልጅ” የሚል ፅሁፍ ያለበት ቲሸርት ለበሰ፤ ወድያው ብዙ ሰዎች እንደሱ መልበስ ሲጀምሩ ተገንጥሎ “ የሽሮ ሜዳ ልጅ “ የሚል ፅሁፍ ያለበት ቲሸርት ለበሰ፤ ብዙ የሰፈር ልጆች እንደሱ መልበስ ሲጀምሩ፤ ተገነጠለና “ የእኛ ቤት ልጅ “ የሚል ቲሸርት ለበስ ፤ በመጨረሻ ወንድሞቹ እንደሱ መልበስ ሲጅምሩ “ ታላቁ ልጅ “ የሚል ቲሸርት ለበሰ፤” 2 “ ከእማማ የወረስኩት አሪፍ ቤት ውስጥ እኖራለሁ፤ ግን ምን ዋጋ አለው? ለእኔ አይነት አኑዋኑዋር አይሆንም! በየቀኑ ሴት ይዠ ስመጣ ጎረቤቶቼ በየመስኮታቸው አንገታቸውን አሾልከው ያፈጡብኛል፤ ባለፈው አንድ ሰውየ ከሁለተኛ ፎቅ ላይ ሆኖ ሲያፈጥ ወድቆ ወገቡ ተሰበረ:: በማግስቱ በዊልቼር ላይ ተቀምጦ እንደገና ማፍጠጡን ቀጠለ፤ ..አንዳንዴ ሳስበው አብርሃም በድንኩዋን ለመኖር የመረጠው ወዶ አይደለም፤ ጎረቤቶቹ ሲደብሩት ቤቱን በቦርሳው አጣጥፎ ከትቶ ወደ ሌላ ቦታ መሄድ ይችላል፤ እንዲህ አይነት ልዩ ነፃነት ስላገኘ ጤናው ተጠብቆ አምስት መቶ አመታት ኖረ፤ እኔ ግን የገዛ መንደሬ እስረኛ ነኝ፤ ትናንት ማታ እስኪጨላልም ድረስ ጠብቄ አንዱዋን ይዤ ወደ ቤት እየመጣሁ ነው፤ እና ድንገት በጨለማው መሀል አንድ ድንጋይ እንደ ሌሊት ወፍ ውልብ ብሎ ጀርባየ ላይ አረፈ፤ ማን የመታኝ ይመስልሃል? ሚስቱን ያባለግሁበት አባዋራ እንዳይመስልህ፤ ከጎረቤታችን ከሚኖሩ ጎረምሶች አንዱ ነው፤ ይህ ሰው በሴት ተዎዶ አያውቅም፤ የሴት ደስታን አያውቅም፤ የሴት ብልት እንኩዋ ያየው ፥የጎጂ ልማድ አስወጋጅ ኮሚቴ በሚያሳየው የግርዛት ቪድዮ ላይ ነው፤ ታድያ ቢወግረኝ ይገርማሀል’? 3 “…እግርዎትን ምን ሆነው ነው?” ሽማግሌ፡- በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት አደጋ ደርሶብኝ ነው” “ዘምተው ነበር? “ ሽማግሌ፡- አይ! አልዘመትኩም፤ ብቻ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት የቤቴን ጣራ በመጠገን እያለሁ ተንሸራትቼ ወደቅሁ”😂 🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያውለን፤ ቸር ያሰማን🙌
إظهار الكل...
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏 • በህይወቴ ዘመን ሁሉ ቤተሰቦቼ እንደ ልጅ ቆጥረዉኝ አያዉቁም፡፡ ጠንቋይ ቤት ሄደዉ ያላቸዉን ሀብት 'እኔ ላይ ካፈሰሱ ዉድቀትና ድህነት ቤታችን ዉስጥ እንደሚገባ ነገር ግን ወንድሜ ላይ ካፈሰሱ ቤታችን በበረከት እንደሚሞላ' ዘባረቀላቸዉ፡፡ ይህን ካዘዛቸዉ ቀን ጀምሮ እኔን እንደለማኝ ወንድሜን ደግሞ እንደንጉስ አሳደጉን፡፡ ወንድሜ 'አለ የተባለ ትምህርት ቤት' ሲያስገቡት እኔን ግን የመጨረሻ የድሃ ትምህርት ቤት ወረወሩኝ፡፡ ግን ምን እንደሆነ ልንገርህ ተከተለኝ... • አስተማሪዎቼ ቤተሰቦቼን ጠርተዉ 'ደደብ ተማሪና ተደብዳቢ እንደሆንኩና ለዚህም እንደመቀጫ የትምህርት ቤቱን ሽንት ቤት ማፅዳት እንዳለብኝ' መወሰናቸዉን ነገሯቸዉ፡፡ ቤተሰቦቼ ደስ አላቸዉ...አዎ የወለዱኝ ቤተሰቦች!! ስራ ስጀምር ከሽንት ቤት ማፅዳት መሆኑ ለኔ የኋላ ኋላ ለመልካም ሆነልኝ፡፡ ይኸዉ አሁን ከ 20 አመት በኋላ የትልቅ ካምፓኒ ባለቤት ነኝ፡ ይብላኝ ለነሱ! አሁንም ተከተለኝ... • ከልቤ የማፈቅራት ሴት ‘አንተ እንኳን ለፍቅር ለጉርብትናም ትደብረኛለህ!’ ብላኝ ትታኝ ሄደች፡፡ ግን ከ 10 አመት በኋላ እሷ ካለችበት ኢኮኖሚ 10 እጥፍ 'ሀብታምና የተሳካለት ሰዉ' ሆኜ ከች አልኩ! እሷ ግን እንደማንም ተራ ሆና አሁንም አለች! እኔን ጥላ በሄደችበት ጊዜ የዛኔዉ 'የልቧ ትርታ' አሁን ከሷ ጋር የለም...አዉላላ ሜዳ ላይ ‘አንቺን ብሎ ፍቅረኛ !’ ብሏት ላጥ! ገና አልጨረስኩም... • የሆነ የህይወቴ አስቸጋሪ ሰአት ሁሉን ከስሬና ባዶ ሆኜ ስመጣ የተማመንኩባቸዉ ሰዎች በሙሉ ካዱኝ፡፡ ‘አቅሙን የማያቅ!’ ብለዉ ተዘባበቱብኝ! ቀን ተገለበጠና እኔ ‘አንቱ’ የተባልኩ ሀብታም እነዛ ደግሞ 'ደፋ ቀና የሚሉ' የተለመደዉ አይነት ሆነዉ አሉ፡፡ ይኸዉ ነዉ የኔ ታሪክ! ሰዎች ሲጎዱኝ፣ ሲጫወቱብኝና እጃቸዉን መቀሰር ሲጀምሩ ያንኑ የተሰበረ ስሜት ተጠቅሜ ወደ ስኬት እለዉጠዋለሁ፡፡ ዉስጤ በቁጭትና በታታሪነት ይሞላል፡፡ ከዛም በህይወቴ የሚገርም ለዉጥ አያለሁ! አንተስ እንዴት እየኖርክ ነዉ?? 🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያውለን፤ ቸር ያሰማን🙌
إظهار الكل...
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏 • አሪፍ ፀባይ አለዉ የምትለዉ ሰዉ ለብቻዉ ሲሆን ትክክለኛ ነገር ይሰራል? • የካፌ አስተናጋጅ፣ ፅዳት የሚሰሩ ሰዎችን፣ ነዳጅ የሚቀዱ ሰዎችን እንዴት ነዉ የሚያነጋግራቸዉ? • ሰዉ ገንዘቡንና ሰአቱን የሚጠቀምበት መንገድ የሰዉየዉን ስብእና በትክክል ይናገራል፡፡ አባቴ ሳምንቱን ሙሉ በስራ ተወጥሮ ነዉ የሚያሳልፈዉ፡፡ እቤት ሲመጣ እንኳን አመሻሽቶ፣ ከስራ ደክሞት ነበር፡፡ ማታ የቀረዉን ትንሽ ሰአት ለኛ 'እንደአባት' ለእናታችን ደግሞ 'እንደባል' የሚገባዉን ሁሉ ይረዳን፣ ያግዘን ነበር፡፡ በሱ እድሜ ያሉ ብዙ ሰዎች ልክ እቤት ሲገቡ ቲቪ ላይ ተጥደዉ እንደሚያመሹት ሳይሆን እኛን የቤት ስራ በማገዝ፣ እናቴን ደግሞ ከጎኗ ሆኖ ጅርባዋን ሲያሽ፣ እግሬን ቆረጠመኝ ስትለዉ እግሯን ቁጭ ብሎ በቫዝሊን ሲያስታምም ነበር ልጅነቴን የማስታዉሰዉ፡፡ እንደአባቴ አይነት 'የገባበትን ሃላፊነት በትክክል አዉቆ' ቤተሰቡን ብር ከመወርወር ባለፈ ተንከባክቦና ደግፎ አሳድጎናል፡፡ ለዚህ ነዉ መልካም የሆኑትን እንቁላሎች ከተበላሹት ለመለየት ዉሃ ዉስጥ የሚከተተዉ፡፡ የችግርና የመከራ ወቅት ሲጀመር የምትወደዉ ሰዉ ማንነት በትክክል እየጠራ፣ እየታየና እየተገለጠ ይመጣል፡፡ 🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያውለን፤ ቸር ያሰማን🙌
إظهار الكل...
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏 • በህይወቴ ዘመን ሁሉ ቤተሰቦቼ እንደ ልጅ ቆጥረዉኝ አያዉቁም፡፡ ጠንቋይ ቤት ሄደዉ ያላቸዉን ሀብት 'እኔ ላይ ካፈሰሱ ዉድቀትና ድህነት ቤታችን ዉስጥ እንደሚገባ ነገር ግን ወንድሜ ላይ ካፈሰሱ ቤታችን በበረከት እንደሚሞላ' ዘባረቀላቸዉ፡፡ ይህን ካዘዛቸዉ ቀን ጀምሮ እኔን እንደለማኝ ወንድሜን ደግሞ እንደንጉስ አሳደጉን፡፡ ወንድሜ 'አለ የተባለ ትምህርት ቤት' ሲያስገቡት እኔን ግን የመጨረሻ የድሃ ትምህርት ቤት ወረወሩኝ፡፡ ግን ምን እንደሆነ ልንገርህ ተከተለኝ... • አስተማሪዎቼ ቤተሰቦቼን ጠርተዉ 'ደደብ ተማሪና ተደብዳቢ እንደሆንኩና ለዚህም እንደመቀጫ የትምህርት ቤቱን ሽንት ቤት ማፅዳት እንዳለብኝ' መወሰናቸዉን ነገሯቸዉ፡፡ ቤተሰቦቼ ደስ አላቸዉ...አዎ የወለዱኝ ቤተሰቦች!! ስራ ስጀምር ከሽንት ቤት ማፅዳት መሆኑ ለኔ የኋላ ኋላ ለመልካም ሆነልኝ፡፡ ይኸዉ አሁን ከ 20 አመት በኋላ የትልቅ ካምፓኒ ባለቤት ነኝ፡ ይብላኝ ለነሱ! አሁንም ተከተለኝ... • ከልቤ የማፈቅራት ሴት ‘አንተ እንኳን ለፍቅር ለጉርብትናም ትደብረኛለህ!’ ብላኝ ትታኝ ሄደች፡፡ ግን ከ 10 አመት በኋላ እሷ ካለችበት ኢኮኖሚ 10 እጥፍ 'ሀብታምና የተሳካለት ሰዉ' ሆኜ ከች አልኩ! እሷ ግን እንደማንም ተራ ሆና አሁንም አለች! እኔን ጥላ በሄደችበት ጊዜ የዛኔዉ 'የልቧ ትርታ' አሁን ከሷ ጋር የለም...አዉላላ ሜዳ ላይ ‘አንቺን ብሎ ፍቅረኛ !’ ብሏት ላጥ! ገና አልጨረስኩም... • የሆነ የህይወቴ አስቸጋሪ ሰአት ሁሉን ከስሬና ባዶ ሆኜ ስመጣ የተማመንኩባቸዉ ሰዎች በሙሉ ካዱኝ፡፡ ‘አቅሙን የማያቅ!’ ብለዉ ተዘባበቱብኝ! ቀን ተገለበጠና እኔ ‘አንቱ’ የተባልኩ ሀብታም እነዛ ደግሞ 'ደፋ ቀና የሚሉ' የተለመደዉ አይነት ሆነዉ አሉ፡፡ ይኸዉ ነዉ የኔ ታሪክ! ሰዎች ሲጎዱኝ፣ ሲጫወቱብኝና እጃቸዉን መቀሰር ሲጀምሩ ያንኑ የተሰበረ ስሜት ተጠቅሜ ወደ ስኬት እለዉጠዋለሁ፡፡ ዉስጤ በቁጭትና በታታሪነት ይሞላል፡፡ ከዛም በህይወቴ የሚገርም ለዉጥ አያለሁ! አንተስ እንዴት እየኖርክ ነዉ?? 🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያውለን፤ ቸር ያሰማን🙌
إظهار الكل...
"ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ እህት ወንድሞቻችን በሙሉ ኢድ-ሙባረክ፤ መልካም ረመዳን ይሁንላችሁ"
إظهار الكل...
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏 አንቺ • ከምታስቢዉ በላይ ቆንጆ ነሽ! • ከምትረጂዉ በላይ ምርጥ አእምሮ አለሽ! • ከሞከርሽዉ ከባድ ነገር በላይ ጠንካራ ነሽ! • ከገመትሽዉ በላይ በራስሽ መቆምና ህይወትን መምራት ትችያለሽ!! • ምንም ይሁን ምን ከምታምኝዉ በላይ ለቤተሰቦችሽና ለራስሽ ጠቃሚ ነሽ። አንተም እንደዛው። 🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያውለን፤ ቸር ያሰማን🙌
إظهار الكل...
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ🙏 ግራ ግብት ያለኝ ነገር¡ በዚህ ሰአት ግራ የገባኝ ነገር ለሰዉ ትሁት መሆን እንዴት ብሎ ከ “ጠበሳ” ጋር እንደሚገናኝ ነዉ፡፡ ለምሳሌ የሆነች ልጅ እየሄደች ወደቀችና መፃህፏ ተዘረገፈ...እየሮጥኩ ሄጄ አይዞሽ ብዬ መፃህፏን ሁሉ ሰብስቤ በመስጠቴ እንዴት 'ለመጥበስ ፈልጎ ነዉ' ይባላል? ቀኑን ሙሉ ደክሟት ወገቧ እየተንቀጠቀጠ አይቼ “እባክሽ እዛ ጋ አረፍ በይ ደክሞሻል” ብል ትህትና ማሳየቴ ግዴታ ወደጠበሳ ተጠምዝዞ መነበብ አለበት?? “ትህትናና” “ጠበሳ” ለየቅል ነዉ...ትህትና የሰዉን ማንነት ሳያዩ ወጣትም ይሁን ጎልማሳ ለመርዳትና የተቻለንን ጥረት ለማድረግ የምናደርገዉ ነገር ሲሆን ጠበሳ ደግሞ ያዉ ጠበሳ ነዉ! ስለዚህ ነገሮች ባይደበላለቁ ደስ ይለኛል ባይ ነኝ፡፡ እናንተስ? 🙌መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን🙌
إظهار الكل...
🐓🐓እንኳን ለጌታችን ለመዳኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳቹ። በአሉ የደስታ:የጤና:እና መልካም ነገሮች ሁሉ ወደኛ የሚመጣበት ይሁንልን።መልካም በአል እንዲሆንላቹ እንመኛለን እኖዳቹሀለን️❤️ፍቅር❣ ❣ ❣ ❣ ❣ ❣ ❣ ❣ ይህ የፋሲካ በአል የይቅርታ እና የምስጋና ቀን ነው ስለሆነም ❣ሳላዉቅ በስህት❣ 💙አውቄ በድፍረት💔 አስቀይሜ አሳዝኜ አስከፍቼ 💜ከሆነ ከጉልበቴ በርከክ ብዬ💗 ትልቅ 💞ይ 💞ቅ 💞ር 💞ታ ጠይቃለው💕 🖤 ይህ በአል 💚 👉 ክርስቶስ ስለእኛ በመስቀል ላይ ወጥቶ የሚያደርጉት አያውቁምና ይቅር በላቸው እንዳለ እኛም ❤️ ከልባችን ይቅር ❤️ የምንባባልበት......እንዲሁም ክርስቶስ በሶስተኛው ቀን መቃብር ፈንቅሎ ሞትን ድል እዳደረገ እኛም 🙏 በይቅርታ🙏 ሰይጣንን ድል የምናደርግበት ይሁን። 💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕 እኔንም ይቅር ስለምትይኝ/ለኝ 💝አ 💝ና 💝ሰ 💝 ግ 💝ና 💝ለ 💝ው ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ❤️❤️መልካም በአል ❤️❤️ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ እስኪ ለምትወደው/ጂው ሰው ይህን መልእክት ላኪለት/ላክለት ❣💝💞💞💞💞💓💓 💘 for best friend💘 💛💚💙💜🖤💔 ሼር በማድረግ ወዳጆ ያካፍሉ 〽️ለበለጠ ቤተሰብ ይሁኑ〽️ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️ join us 👇👇👇 @Ahmaric_quo 🤜Share🤛
إظهار الكل...
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ🙏 "1. ብዙዎቻችን በህይወታችን በጣም አስፈላጊ የምንለዉን ነገር ማግኘት ሳንችል እንቀራለን፡ግን አሳዛኙ ነገር አስፈላጊ ነዉ ያልነዉን ነገር በትክክል ሳናጣጥመዉ እያሳደድን እንኖራለን፡፡ 2. ብዙዎቻችን ጠቃሚ የሆነዉን ነገር ትተን ጠቃሚ ይሆናል ብለን ባሰብነዉ ነገር ላይ እንዳክራለን፡፡ሳምንቱን ሙሉ ፈግተን ህልም ያልነዉን ነገር ስንጨብጠዉ የምንወዳቸዉን ሰዎችና ማንነቶች ወይ ሞተዉ አለበለዚያ ጥለዉን ሄደዉ እንደርሳለን፡፡ ሠአታችንን በራስ ወዳድነት‹ህልም› ዉስጥ ቀብረን ስናበቃ ያ ህልማችን ካጣናቸዉ ሰዎች ጋር ሲነፃፀር ተራ እንደነበር እንገነዘባለን፡፡ 3. ብዙዉ የህይወታችን ጊዜ ትርጉም አልባ ይሆንብናል፤ሌላ ቀን ደግሞ ህይወት ትርጉም ሰጥታን እንዉላለን፡፡አምላካችንን ስናማርርና ‹ምነዉ በገደልከኝ!› እያልን እንከርምና ትንሽ ፀሃይ ሲወጣልን ደግሞ ለአምላክ የምናሸበሽብ መላእክት እንደሆንን አይነት ይሰማናል፡፡ 4. ማንም ለማንም የማይጨነቅበት ሰአት ላይ ደርሰናል፡፡ሁላችንም ስለራሳችን በማሰብ ዘመናችንን እንጨርሳለን፡፡ምን እበላ ይሆን ምን እሰራ ይሆን እያልን ከራስ ያልዘለለ ማንነት ዉስጥ ተጠልለን እንሞታለን፡፡ 5. አለምን የምናየዉ በነበረበት ሁኔታ ሳይሆን በራሳችን ሁኔታ ነዉ፡፡ ስራ ያጣ ሰዉ አለምን የሚያየዉ ስራ ለሚፈልግ ሰዉ ቦታ የሌላት የዘመድ አዝማድ ጥርቃሚ የተሞላባት የመስሪያ ቤቶች ጋጋታ ሊሆን ይችላል፡፡ ፍቅር የያዘዉ ሰዉ አለምን የሚያየዉ ፍቅር እንዴት ታላላቅ መሪዎችን እንደማረከና አገሩ በሙሉ በጥንዶች እንደተሞላ እንዲሁም ምን ያህል እድለኛ እንደሆነ ነዉ፡፡ ከራሳችን ስሜት በላይ ሆነን አለምን የምናይ ሰዎች እጅግ ጥቂቶች ነን፡፡ ", 🙌መልካም አዳር፤ የነገ ሰው ይበለን🙌
إظهار الكل...
( ተነሳ ተራመድ !! ) : : ወዳጄ… በሄዱበት መምጣት እንዳገኙ ማጣት በቀጡበት አንቀፅ : እንዳለ መቀጣት : : : ማገናዘብ ስተው ማስተዋል ዘንግተው : ማስታወስ የረሱ ልዩ መሆን ሽተው የአብሮነት ምህላ : ኪዳን ያፈረሱ : : : በአውቃለሁ እብሪት ከትርክት አብረው : ታሪክ የከሰሱ በሆይ ሆይታ ደቦ ዲቤ ተደልቆ በታረሰ ቦይ ላይ : በአድማ የፈሰሱ : : : ሚዳ አጣን ብለው ከፍ ያለውን ጋራ : ተራራ የናዱ እኩይ ዘር በትነው ሀሰት አስረግዘው : በሬን ያስወለዱ : : : ከመግዘፍ ተፋተው ከማነስ ተዳርተው : በጥበት ሚጦዙ አንተ ባለህበት በአጥቢያህ ቢሰፉ : በዙርያ ቢበዙ : : : አንተ ግን በምስጠትህ ጀግን : ሄ…ድ… ወደ ተንቀልቃዩ ወደ ውብ ስቃዩ ወደ ሀሩሩ ፍመት ወደ ውስጥህ ዝመት……!! : : : ተነስ ተነስ ተነሳ ተራመድ በሀቂቃው መንገድ : ፍጠን ተነስ : ጋልብ ሽምጥ ወደ ነፍስህ ጥሪ : ወደአንተነት አምልጥ : : በል ግ…ባ ! በምስጠትህ ግዝፈት : ከፍታህን ገንባ : : በል አዜም በውስጥ ውብ ዜማ : ለውስጠት አዜም ፃፍ ዓትም በአዲስ ቀን ብራና : አዲስ ታሪክ አትም : : ፍጠን አብራ ኑረትህን አጥራ : ሽፍንፍኑን ግለጥ ናርዶሰ ቅጥፈትን ቅርሻታም ውበትን : በፀዳል ብለጥ : : ስማ አድምጥ ……ወደ ውስጥ አምልጥ ግዘፍ ብለጥ ጭጋጋም ውጪህን : በውስጠትህ ብለጥ…! : : : : ግን ደግሞ ይህንን ስል ምክር በቃል ስስል ይብሩልኝ ይዩልኝ ዓይኖችህ : ብሌንህ ይገለጥ ሔራን አለ ብለህ ሀቂቃህን ጥለህ ስንት ያወክበትን : ውጪህን እትርገጥ…!! : : : ብቻ ……’ሩጥ ሄ……ድ አምልጥ : አዳፋህን ብለጥ ያረጀው ምልከታህ ትላንታዊ ዕይታህ : በአሁን ይበለጥ…!! ===========^============
إظهار الكل...