cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ልዩ ምልከታ

አንድ ዐይኑን ወደላይ አንድ ዐይኑን ወደታች አድርጎ መመልከት የሚቻለው ማነው ? 🤷‍ 🤷‍ ልዩ ምልከታዎች ⚡ታሪካዊና አስገራሚ ፎቶዎች ⚡ ሀሳቦች💭💭💭 ⚡ Myth and reality ⚡ Weird history ⚡ ከስእል ጀርባ

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
253
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-17 أيام
-230 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን ... ሰው መጀመሪያ በበሽታ ሲያዝ ምኑን ሚያጣ ይመስላችኋል ? ልክ ናችሁ "ስሙን ነው" መጣ ደሞ' መጣ ስኳር በሽተኛው ....,ረሳኸው እንዴ ደምግፊት ያለበት ሰወዬ.. @leyumelketa
إظهار الكل...
እንዴት ትላንት ተስፍ ይሆናል፣ ነገንስ መፍራት ልክ ነው ? ወይንስ ይሄ ሁሉ ከቀንዳውጣ ወደ ቢራቢሮ መስፈንጠሪያ ነው ? አሜን ይርግልን
إظهار الكل...
ለብዙ አመታት የሰናፍንጭ ቅንጣት ያህል እምነት እንዳለኝ አስብ ነበር ተመፃድቂ ለመሆን ሳይሆን የእውነት ፈጣሪ እንዳለ እና እንደማምነው ይሰማኝ ነበር ነገር ግን ይህ ከቶ እንዳልነበር የገባኝ ጊዜ ሲያልፍ ነው በእርግጥም እስካሁን በውል አልገባኝም። ብዙዎቻችን ለሀጥያቶችን ምንጭ ደጋማስ ስጋችን ወይም  ሰይጣን ላይ እናሳብባለን ነገር የ በደላችን ሁሉ መጀመሪያው ፈጣሪ እንዳለ አለማመናችን ነዉ ከልብ ሆነን እራሳችንን ብንጠይቅ ፈጣሪ እንዳለን አናምንም።
إظهار الكل...
ያለይሉኝታ የሚገስፅህ ሰው ከሌለህ በጣም ምስኪን ነህ ። ያለይሉኝታ የሚገስፅህ መምህር ብታጣ ያለ ይሉኝታ የሚገስፅህ እብድ እንኳን እንዲሰጥህ ለምን ። የምትሰራውን ሁሉ አንተ ብቻህን መመዘን አትችልም ። በህይወትህ በጥቂቱ የተለወጥክበትን ነገር ስታየው ያለ ይሉኝታ የተገሰፅክበት ስህተት ሆኖ ታገኘዋለህ ። #share #share #share @leyumelketa @leyumelketa
إظهار الكل...
...ምሽት ላይ በኩራት ቆሞ " እንግዲ ምድር ደህና ሰንብቺ " በማለት ምድርን ተሰናብቶ አልጋው ላይ ወጣ ። አልጋው ግን እንደ ነገሩ ነበርና ብዙም ሳይቆይ መሬት ላይ ጣለው ። ደህና ሰንብቺ ያለው ሰውዬ በራሱ አፍሮ " እንዴት ዋልሽ ምድር?  ሳልውል ሳላድር " አለ ይባላል ። @leyumelketa @leyumelketa
إظهار الكل...
አንድ መምህር ያለ ጭንቀት መኖር ጥበብ ሲናገ ሩ እንዲህ ነበር ያሉት ፣ መኪና ይዛችሁ ልክ ዝናብ ሲመጣ (wind cleaner)ON ማድረጋችሁ አይቀርም ነገር ግን wind cleaner ጋር ብቻ ትኩረታችሁን ካደረጋችሁ አንዴ ወደ ቀኝ አንዴ ወደ ግራ ስትሉ መኪናውን ይዛችሁ ገደል መግባታችሁ ነው ፣ ትኩሩታችሁ ግን መሆን ያለበት መንገዱ ላይ ነው ዝናብ ሊጨምር ይችላል ፣ wind cleaner ፍጥነትም በዛው ልክ ይጨምራል ግን አትረበሹም ምክንያቱም ሀሳብችሁ ሁላ መንገዱ ላይ ብቻ ስለሚሆን ነው። ትኩረታችሁን(wind cleaner) ላይ እንዳደረጋችሁ ፣ ህይወትም እንዲ ናት ልክ አንድ ሀሳብ ሲመጣ #focus ብቻ ስታደርጉ ደሞ ሌላ ሀሳብ ሲመጣ ወደ እዛው ሲትባዝኑ የኑሮአችሁን መሪ ታጣላችሁ። "ብዙዋች ይመጡ እና  መምህር በጣም ብዙ ሀሳብ አለብኝ መቆጣጠር አልቻልኩም አልቻልንም ይሉኛል እነሱ ያልተረዱት ግን የመጣው ምንም ሀሳብ ይሁን ሀሳቡ ትልቅ ነው ብሎ ማሰብ እራሱ ሌላ ታላቅ ጭንቀት ነው በቃ መንገዱ ላይ ብቻ ትኩረት አድርጉ  ልክ መኪና ስታሽከረክሩ እንደ ምታደርጉት"። @leyumelketa @leyumelketa @leyumelketa
إظهار الكل...
እማን ዘንድ ይደር ..... አለም አንዳንዴ( ) በተሰበረ መነፅር ነገን እንድናይ እንገደዳለን ፣  ምናየው ሁላ ሰባራ ሆኖ  ጎዳሎችንን ማይሞላ ሆኖ ይሰማናል። አይናችን ብሌን መሀል የተነቀሰው የትላንት ትዝታ ነገን መስሎ ዛሬን ያስከዳናል። ካቻምና በዘነበው ዝናብ ዘንድሮ ያረጥበናል አምና የወጣችው ጠሀይ ዛሬ ላይ ሆና ትወብቀናለች።  ያልቀጠርነውን ሰው ዛንጥላ ይዞ  መጠበቅ  ይታክታል አይደልም ግን እና ተልይተን አደለም ፣ትላንት ከእኛ ስላልተለየን ነው። ልባችን እማን ዘንድ ይደር.... @leyumelketa @leyumelketa @leyumelketa
إظهار الكل...
ድንጋይ ህልውና አለው ነገር ግን አይተነፍስም አይንቀሳቀስም፣ ዛፍ ህልውና አለው ነገርግን ከድንጋይ በተሻለ ህልውና ይተነፍሳል ። ውሻ ህልውና አለው ነገርግን ከድንጋይ እና ዛፍ በተሻለ ህልውና ይንቀሳቀሳል ይተነፍሳል ይቀምሳል ያሸታል ። ሰው ህልውና አለው ነገርግን ከድንጋይም ከዛፍም ከውሻም በተሻለ ህልውና ይተነፍሳል ይንቀሳቀሳል ከእነዚህም በተለየ እውቀት ማስተዋል ና ማሰብ አለው ። እንግዲ ስለፈጣሪ ህልውና ስናስብ ከነዚ ህልውናዎች ሁሉ የላቀ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል ። @leyumelketa
إظهار الكل...