cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Venue

መድረሻ ባይኖር ፣ መጓዝ ብርቅ ነበር! : መራመድ ባልከፋ ፣ መድረሻም ባልጠፋ ነገ ላይ ለመድረስ ፣ ሰው ባያጣ ተስፋ ።

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
2 180
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
+3030 أيام
توزيع وقت النشر

جاري تحميل البيانات...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
تحليل النشر
المشاركاتالمشاهدات
الأسهم
ديناميات المشاهدات
01
« የኔም እንዳንቺ ነበር አውቀዋለሁ… ፈገግታሽ ሙናፊቅ ነው አያታልለኝም! ግዴለሽም አርፈሽ ወዳ’ምላክሽ ሄደሽ ሳቂ! » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
720Loading...
02
ነገ ምሽት ላይ የአላህ ፍቃድ ከሆነ ይኖረናል። ጥያቄውን ለሚመልሱ ሶስት የቬኑ ቤተሰቦች የ #ሊቀ_ቀንበር_የወግና_የመዝናኛ_ድግስ የመግቢያ ትኬቶች ተሸላሚ ይሆናሉ! ተዘጋጁ😊😊
2570Loading...
03
የቲኬት ሽያጭ ተጀምሯል! 🎫 . በጉጉት የሚጠበቀው የሊቀ-ቀንበር የወግና የመዝናኛ ድግስ የመግቢያ ቲኬቶች ለገበያ ቀርበዋል። ቲኬቶቹ የት ይገኛሉ? 1. ቤተል ሚስተር ኮፊ፣ ፋሚሊ ታወር 4ኛ ፎቅ 2. ዋልያ ቡክስ (4 ኪሎ ኢክላስ ህንጻ) 3. the hungout cafe (አዶት ሲኒማ ህንጻ ground ላይ) . ባሉበት ኾነው ቲኬቱን በሞባይል ባንኪንግ ለመቁረጥ :- 1000413125654 Feysel በዚህ አካውንት በመቁረጥ ስክሪንሾቱን የዝግጅቱ ዕለት መግቢያ ላይ እያረጋገጡ መታደም ይችላሉ። . የቲኬቱ ዋጋ:- መደበኛ :- 200 ብር ቪ.አይ.ፒ:- 300 ብር . መሠናዶው የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 24 ብስራተ-ገብርኤል አካባቢ በሚገኘው አዶት ሲኒማ ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ይካሔዳል። . @huluezih @huluezih
2090Loading...
04
« የህይወት ትርጉም ጠፍቷችኋል? ልባችሁን የሚያስደስት ነገር አጥታችሁ ሁሉም ነገር ትርጉም አልሰጥ ብሏችኋል? እንኳን ስለ ነገ ለማለም ቀርቶ ዛሬን እንዴት መኖር እንዳለባችሁ ግራ ገብቷችኋል? የምትወዷቸውን፣ ከማንም ከምንም በላይ ለልታጧቸው የማተፈልጉ ሰዎችን ተለይታችሁ ልባችሁ አዝኗል? መከዳት፣ መውዋሸት፣ ስም መጥፋት፣ ፍቅር ማጣት ልባችሁን አቁስሎታል? ከእናንተ የበለጠ የተፈተነ እየመሰላችሁ ፈተናዎቻችሁ ከብዷችኋል? ከሰዎች ጋር መግባባት፣ መኗኗር አቅቷችኋል? ደስታን መፍራት፣ መላመድን መጠየፍ፣ በብቸኝነት ውስጥ ሽጉጥ ማለት ጀምራችኋል? ሙከራዎቻችሁ ሁሉ እየከሸፉ ዝላችኋል? ትላንታችሁ እንደ ገመድ አንገታችሁን አንቆ ዛሬን አላፈነናፍን ብሏችኋል? ልትርቋቸው፣ ልትጠሏቸው፣ በማይቻላችሁ ሰዎች ደምታችኋል? ሞት የሁሉም ነገር መፍትሄ መስሏችኋል? ተስፋ መቁረጥ ጎብኝቷችኋል? ብዙ… ብዙ ሊገለፁና ሊነገሩ የማይችሉ ህመም ስቃዮች ገጥሟችኋል? እንግዲያውስ መፍትሄው አንድ እና አንድ ብቻ ነው። ይህም አላህን ማወቅ ነው። በአላህ እምላለሁ አላህን ያወቃችሁበት መንገድ የተሳሳተ ከሆነ የትኛውም ቅንጣት ችግር እናንተ ዘንድ ከፍጥረተ ዓለሙ የገዘፈ ይሆናል። የትኛውም ስብራት፣ የትኛውም ህመም በልብ ውስጥ ፀንቶ የሚቆየው አላህን የሚያውቁትን፣ የሚያምኑትን ያህል ነው። እምነት ሲጓደል ህመም ይገዝፋል። በአላህ እምላለሁ የትኛውም ሰባኪ ስለ አላህ እዝነት ከነገራችሁ በላይ አላህ እጅጉን ሩህሩህና አዛኝ ነው። የትኛውም እውቀት አለው ብላችሁ የምትሉት ሰው ስለ አላህ መሀሪነትና አዛኝነት ከነገራችሁ በላይ አላህ አዛኝ እና መሀሪ ነው። አላህን ለማወቅና በትክክል በእርሱ ላይ ፍፁም ተወኩል ለማድረግ በምትተጉበት ጊዜ ህመማችሁ፣ ስቃይ መከራችሁ፣ ልባችሁን የሚያስጨንቀው ነገር ካልተስተካከለ ወይም መፍትሄ ካላገኘ በእርግጥ ይህን የተናገርኩትን ነገ በአላህ ፊት ጌታዬ ይህ ሰው ዋሽቶኛል ማለት ለእናንተ የተገባ ነው። እኔም ጌታዬ ስላንተ እንዲያውቁና ልባቸውን እንዲያረጋጉ ላስታውሳቸው ብቻ ሞከርኩ፣ በሙከራቸው ተሰላቹና ዋሽተሀል አሉኝ፣ ጌታዬ አንተ አዛኝ እና መሀሪ ነህ ለእኔም ለእነሱም እዘንላቸው እለዋለሁ። ይህን ስላችሁ መታበይ ወይም መኩራራት አይደለም፣ አላህን በፍፁም ልባችሁ እንደሚያሽራችሁ እንድታምኑ እና እርግጠኛ እንድትሆኑ እንጂ! የሚገለፁም፣ የማይገለፁ፣ የሚድኑም፣ ፈፅሞ የማይሽሩ የሚመስሉ ህመሞች ሁሉ መፍትሄያቸው አላህ ዘንድ ብቻና ብቻ ነው። አንዳንድ ህመሞች ከፈዋሹ ርቀው ፈውስ ሲፈልጉ ነው የማይድኑ፣ የማይሽሩ፣ የማይቻሉ የሚመስሉት። ከመፍትሄያችን ርቀን መፍትሄ እናገኛለን ብለን ባንታገል መልካም ነው። ብቻ ልቤ እንዲህ ይለኛል። » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
2520Loading...
05
« ተሰብራ ትቀራለች ብለው ለደመደሙት ልክ እንዳትሆኚላቸው፣ ደህና ሆነሽ አሳፍርያቸው። አበቃለት ብለው ላሉት እንዳሉት እንዳትገኝላቸው፣ እራስህን ከጣልከው ካንተ በቀር ችሎ የሚያነሳው ሰው የለምና ጌታህን ይዘህ እየታገልክ አሳፍራቸው። ማህፀንሽን ያደረቁት ይመስል መሀን ለሚሉሽ አትሰበሪላቸው፣ ወደ ጌታሽ ሰርክ በዱዓ እየማለድሽ በልጅሽ ፈገግታ እንደምታሳፍርያቸው በጌታሽ ላይ ፍፁም ተወኩል ይኑርሽ! ከአወዳደቅ ሁሉ መነሳት የሌለው ከአላህ አስበልጦ ወደ ፍጡራን መዘንበል ነውና ጀሊሉን ሙጥኝ ብለን እንያዝ። ልባችሁ የምር ፈገግ የሚልበት ጊዜ አይራቅ። የምወድሽዋ አብሽሪ! የምወድህዋ አብሽሩ! ሰላም ለልባችሁ! » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
3900Loading...
06
« አንዳንድ ምስጋናዎችህ እርባና ቢስ የሚሆኑበት ጊዜ አለ። ልክ እንደዝያ ሰውዬ ዝሙትን ከፈፀመ በኋላ ስላረካኸኝ ተመስገን ጌታዬ እንዳለው። አንዳንድ ህልሞችህ መሳካታቸው ፋይዳ ቢስ የሚሆኑበት ጊዜ አለ። ልክ እንደዚያች ሴትዮ የልጇን ሚስት ካስገደለች በኋላ ከልጇ ጋር ለቅሶ እንደተቀመጠችው። ስጋት የመሰለህን ሁሉ ለማስወገድ ያደረግከው ሁሉም ሙከራ የሚያጠፋህ ጊዜ አለ። ልክ እንደ ፊርዓውን። በህይወት ውስጥ አንዳንድ ሙከራዎችህ፣ ምስጋናዎችህ፣ ህልሞችህ እርባና ቢስ እንዳይሆኑብህ የጌታህ አይነስህ፣ የቀደርህ አይቅለልብህ! » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
3700Loading...
07
« የስቃይና የመከራ ከፈን ተከፍነው አሁንም ድረስ ከከፈናቸው እያጮለቁ በሰዎች ላይ መልካሙን ለማንፀበረቅ በሚተጉት ላይ የአላህ ሰላም ይስፈን። አይታይም እንጂ የልብ መመሰቃቀል ከመጠጥ ስካር ይበልጥ ያንገዳግዳል። ሰላም ለዝምተኛ ታጋሾች፣ ሰላም ስለ ህመማቸው ሳይጮህ የህመማቸውን ሲቃ ተረድቶ የሚያዳምጣቸው ለናፈቁ። ልባቸው ታፍኖ ለመኖር በሚጣጣሩት ሁሉ ሰላም ይስፈን። » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
4300Loading...
08
« ሰላም ለእነዝያ ሰንሄድ ለሚያፈላልጉን፣ ስንጠፋ ለሚያጠያይቁን! ሰላም ለእነዝያ ልባቸው እንዳይከፋው መሻታችንን ለተቆጣጠርንላቸው፣ ሽሽታችንን ለገታንላቸው። ሰላም ለእነዝያ የፈለግነውን በቀላሉ ተረድተው ቃላት እንድናባክን ለማያደርጉን። ሰላም ለመንገዱ ሰበብ ሆኖ ለተገናኘንበት፣ የማንፍቀው ትዝታ በልባችን ላተምንበት። ሰላም ለጊዜው በትውስታ መዝገባችን የሚቀመጥ ቅርስ ላኖርንበት። ያኔ ብለን የምናወሳውን ላገኘንበት። ሰላም ለእናንተ! ሰላም ለልባችሁ! » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
4330Loading...
09
« ሰላም ላንተ " ያልፋል" ማለት በቁስልህ መቀለድ ለሚመስለኝ። ላፅናናህ አቅም ለሚያንሰኝ፣ ለብርታትህ ሰበብ ለመሆን ብሞክር የምሰብርህ ለሚመስለኝ አንተ ሰላም ለልብህ! ልብህ እንደ የቲም ልጅ እንክብካቤ ለሚፈልገው ሰላም ለልብህ! » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
4150Loading...
10
« ሰላም ላንቺ ትዕግስትሽ በእንባ ሊገለፅ ለማይቻለው። አድገሽም እንደ ህፃን ልጅ ገላ ለስልሰሽ ለምትኖሪው ሰላም አንቺዬ! ሀዘን መከራዬን ከቻልሽው ፊት ሳቀርበው ምንም እንደሆነ ለምታሳውቂኝ አንቺ ሰላም ለውስጥሽ! ውስጥሽ ከጦርነት አውድማ በላይ ተመሰቃቅሎ ፊትሽ ፈገግ ለሚለው ሰላም ለልብሽ። » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
3920Loading...
11
« አንቱ ሰው እስቲ ስለ ሰዎች ይንገሩኝ! » « የኔ ልጅ አንዳንዴ ሰዎች ልክ እንደ ሸዋል ወር ናቸው። » « እንዴት? » « የሸዋል የመጀመርያ ቀን ኢድ ነው መፆም ይከለከላል። ከሸዋል አንድ ቀን በፊት ደግሞ መፆም ግዴታ ነበር። የሸዋል ሁለተኛ ቀን ደግሞ መፆም የተወደደ እና የተፈቀደ ነው። ሰዎችም በህይወታችን ውስጥ እንዲያ ናቸው። ትላንት መውደድ፣ ማፍቀር ግዴታችን የሆኑብን የነበሩ ሰዎች ዛሬ ላይ እነሱን መውደድ እና ማፍቀር የተከለከለ ይሆናል። ነገ ደግሞ እነዚህን ሰዎች ልናፈቅር እና ልንወዳቸው ሊፈቀድልን አልያም ሊወደድልን ይችላል። » « ይገርማል አስቤው ግን አላቅም! » « የኔ ልጅ የወደድካቸውን ሰዎች ላለመጥላትህ ዋስትና የለህም፣ የጠላሀቸወንም ሰዎች ላለመውደድህ ማረጋገጫ የለህም። የኔ ልጅ በተቻለህ መጠን ከሰዎች ጋር በመልካሙ ተኗኗር። ስምህ በተጠራ ቁጥር ልብን የሚያውድ መልካም መዓዛ ይኖርህ ዘንድ ለጌታህ ፅድት በል። » « አንቱ ሰው እወዶታለሁ! » « ጌታዬ ያስወድድህ! » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
4320Loading...
12
« ነጅዋ እንግዲህ ከራሷ ጋር ለመማከርም፣ ለልቧም አሁን ፅሁፍ መፃፍ ለጊዜው አቁማለች(ቬኑ ላይ)። ትችት የመፍራት ወይም የመሸሽ አይደለም። ልብ ነፃነትን ይሻል፣ የልብ ጉዳይ ነው። መመለሷን እኔም እናፍቀዋለሁ። ውሳኔዋን ግን አከብራለሁ። ያው አንዳንዴ የሆነ የራሳችን ጊዜ እንፈልጋለን አይደል። እንደዚያ ነው። ቬኑ ላይ አትፃፍ እንጂ አለች። እንዲህ ስትወስን ደስ ባይለኝም እርሷ መመለስ የፈለገች ጊዜ እርሷው ታውቃለችና ቃሏን እናከብራለን። ባይሆን ጨቅጭቁልኝ ጭራሽ መፃፍ እንዳታቆም! » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
4160Loading...
13
ማሳሰቢያ(አይደለም ኮ ግን ርዕሱ ምን ይሁን?) (ነጃት ሐሰን) : ኑ እስቲ እንነጋገር እዚህ ጋር.... ብዙ ማለት ፈልጊያለሁ ግን ስሜታዊ መሆንና ነገሮችን ማበላሸት አግባብ ስላልሆነ ምንም አለማለትም ፈልጊያለሁ። ይህ ቤት ማለትም Venue ከዚህ በፊት እንዳልኳችሁ ፡ ምንም መፃፍ ካለመቻል ትንሽ ወደመሞከር ብሎም ለሰው ወደማስነበብ ያሸጋገረኝ ነው። በጣም ትልቁ ውለታው ደግሞ ብዙውኑ በቀጥታ አሊያም በተዘዋዋሪ ወዳጅ የምላቸውን ሁላ ያገኘሁበት ቤት ነው... አብዛኞቹ ጓደኞቼ ቀድመው እሚያውቁኝ እዚህ ነውና እንደቤቴ ነው። ሰው የማያስከፋ እና የአላህን ድንበር እስካላስጣሰኝ ድረስ እንደመሻቴ የምሆንበት ቤት ነው። እንደኔ የምሆንበት። ቀደም ያላችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች እንደምትታዘቡት ይህንና የቀደመውን አመት መፃፍ እጅግ የቀነስኩበት ነው። ከራሴ ስንፍና ጀምሮ ብዙ ምክንያቶች አሉ። ከዚህ ኋላ የምላችሁን የምለው ብዙ ጊዜ አስብበት የነበር ጉዳይ ስለሆነ ነው። 1ኛ ከተፈጥሮ የተቃረነ ነገር እስካልሆነ ድረስ «ኢስላማዊ» እና «ዓለማዊ» ብለን ነገር ለምን እንከፋፍላለን? ዱኒያዊ ስራዎቻችንም ቢሆኑ መልካም ኒያ እስከታከለባቸው ያው አላህን መገዛት አይደሉምን? የሚፃፉ ፅሁፎች ሁሉም ለምን አረብኛ ቃል ካልተጨመረባቸው ሐራም ናቸው ይባላል?(መልሱን ለራሳችሁ) 2ኛ እናንተ ትክክል ነው ብላችሁ የያዛችሁት ዓቂዳ ለሌላው እጅግ የጥፋት መንገድ መስሎ እንደሚታይ አታውቁም? እዚህ ላይ ወጉ ብዙ ነው.... «መንገዴ» የምትሉትን አጥብቃችሁ ያዙ እንጂ ስለሌላው ምን የማለት የእውቀት አክሊል ደፍታችሁ ነው? ደፍተን ነው? የድሮ ሼይኾቻችን በጣም ዓሊሞች ከመሆናቸው ጋር አንድ ሰውን ለመፈረጅ አይቸኩሉም ነበር... ያልደረሱበት የዒልም ገፅ ይኖር እንደሆነ ይፈትሻሉ እንጂ!! ይህ የፈትዋ ቤት አይደለም... ልክ ያልመሰላችሁ ካለም የእውቀት ባለቤቶችን ጠይቁ። በአጠቃላይ ለፍረጃ ለምን በዚህ ያኽል ፈጣኖች እንደሆንን እየገባኝ አይደለም። እራሳችንን የጀነት አለቆች አድርገን ሹመንና ምዕመኑ እንዳለ የጀሐነም ማቀጣጣያ እንደሆነ እንምናስብ አልገባኝም። እዚህ ቤትም በተለያዩ ጊዜያት የሚሰጡ አስተያየቶች በጣም በትኩረት አያለሁ(በተለይ የእኔዎቹ ላይ ነው ምላችሁ).... jugmental የሆኑት ይበዛሉ አንዳንዴም... ቤቱ ላይ ክርክርና ደስ የማይል ድባብ ላለመፍጠር በሚል እንደተኮመቱ ያጠፋኋቸው አስተያየቶችም አሉ። ደስ አይደልም አይደል? ብዙ አላወራም ካሉ ኋላ ይህንን ሁላ ማውራት ራሱ😴 እናም... እኔ ነጃት ሐሰን የተባልኩ ግለሰብ(😂) እኔም ነፃነቴን ሲነፍጉኝ የማልወድ ስለሆንኩ... እያሰብኩ ደግሞ ከእኔነቴ የራቀን ነገር መፃፍም ስለማልፈልግ... እናንተም የማይመቻችሁን እንድታነቡ ከምትገደዱ በሚል እዚህ ቤት መፃፍ ብተው ጥሩ ይሆናል የሚል ነው የዚህ ፅሀፍ ማጠቃለያው። ህይዎት መንገዷ ብዙ ነው... በሆነኛውና በመልካሙ እንደምንገናኝ ተስፋ አደርጋለሁ🌼 ሑላችሁንም እወዳችኋለሁ የሐቅ አላህ የልቤን ያውቃል። ያልጠና ብዕሬን ከፅሁፍ ቆጥራችሁ ስላነበባችሁኝ በጣም አመሰግናለሁ። አላህ ይጠብቃችሁ🌼! ወሰላሙዓለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ። : @Venuee13 @Venuee13
5892Loading...
14
በእድሜ ዘመኔ እጄ ላይ ያለን መጠነኛ መፅሀፍ ለመጨረስ ይህን ያህል ጊዜ ወስዶብኝ ማወቁን አላስታውስም። መፅሀፍ እውቀት ለመቃረም ብቻ ነው የሚነበብ? ወይ የፅሁፍ ችሎታን ለማሳደግ? ወይ በሆነ ነገር ከፍ ለማለት? እንደኔ ከሆናችሁ አንዳንዴ ማለት ያቃታችሁን የልብ መቃተት የሚልላችሁን ፍለጋ.... ህመማችሁ የግላችሁ ብቻ እንዳልሆነ ከሆነ ሰው መስማት ስትሹ.... አብሮ ለማልቀስ... ስለጨለማ ቀናቶቻችን አብሮ ለመቆዘም ስትፈልጉም ይነበባል። ስከፍተው... ህምም እያልኩ ራሴን ሳባብል... ስዘጋው እንደገና... ሐገሬን ሳይ... ልቤን ሳይ... እኔ ፡ ትውልዴ መድከሙን ተከትቦ ሳይ... ሐቅነቱ ሲያስጨንቀኝ... አንጀቴን ሲያሳክከኝ... ብቻ እንደምንም አለቀ። ብታነቡት አንደበት ሁኖ ያላችሁበትን ይናገርላቹሃል። ÷ጸሀይ ከጨለማዬ ምን አለሽ? በእሱባለው አበራ ንጉሤ (ነጃት ሐሰን) : @Venuee13
7158Loading...
15
#ኡራዝ_ቪ በዚህ መልኩ ተጠናቋል። እንዴት ነው ከቁም ነገሩ ጋር ተገናኛችሁ ወይ? ፅሁፉስ እንዴት ነበር? ያላችሁን ማንኛውም ሀሳብ አስተያየት ከአሁን ጀምሮ ልታደርሱኝ ትችላላችሁ! ሀሳቦቻችሁን @Venuee13bot ላይ ማካፈል ወይም እዚሁ ማስፈር ትችላላችሁ። አመሰገንኩ። [አብዱልሀኪም ሰፋ]
7371Loading...
16
« ኡራዝ ቪ» [አብዱልሀኪም ሰፋ] (ሁለት ወደ ኋላ: አንድ ወደ ፊት!) : « ሀሊሜ የኔ ውድ አቅፈኸኝ ምን ሀሳብ ገባህ? » ሀሊም በእናቱ እቅፍ ውስጥ እንዳለ በትውስታው ሲርቅ እናቱ ቀሰቀሱት። « አለሁ እማዬ… » ከእናቱ እቅፍ እየተላቀቀ። « ሀሊሜ አባትህን እንዳትቀየመው በተወው ትላንት አሁን እንዳትወቅሰው! » « እማዬ ግን ምን አይነት ልብ ነው ያለሽ? » « የሰው ነዋ የኔ ልጅ… አባትህ እኮ መልካም ሰው ነው አንድም ቀን ሀቄን አጉድሎ አያውቅም። » « አውቃለሁ እማዬ እሱን እኔም መመስከር እችላለሁ! ግን እማ ፍፁም ያልጠበቅኩት ስለነበር ለመቀበል አቃተኝ እንጂ አባቴንማ ልጠላው አልችልም።» « እንግዲህ ጌትየው እንዴት አድርጎ እንደሚፈትን አይታወቅም። እርሱ ልባችንን ታጋሽ ያርግልን! » « አሚን… እማ… » ሀሊም ከእናቱ እቅፍ ውስጥ ተሸጎጠ። ልቡን ሰላም የሚያደርግለት የምድር ሰላማዊው እቅፍ ውስጥ ሽሽግ አለ። የሀሊም እናት ልጃቸውን በእቅፋቸው ውስጥ እንደሸሸጉ እንባቸውን አልሸሸጉም። የሀሊም አባት እናት እና ልጅ ተቃቅፈው ከባለቤታቸው አይን ላይ እንባቸውን ከርቀት ስብር ባለ እይታ ከውጭ ወደ ውስጥ ሲገቡ ተመለከቱ። መዓልት ትርጉም የያዘ ልብ የሚሰረስር እንባ ነበር። ★……………★……………★ « በህይወት ውስጥ አንዳንዴ ለመታገል አቅም ታጫለሽ። እውነት ነው ብለሽ የተቀበልሽው ነገር ድንገት ውሸት ሆኖ ታገኚዋለሽ። ያኔ ከስንቱ ጋር ትጋጫለሽ? ይደክምሻል! መታገልም ደስ የሚለው አቅም ሲኖር ነው። » « እንዴት ግን እውነቱን ካወቅክ በኋላ ከዋሸህ ሰው ጋር መኖር ቻልክበት? ምን አይነት ልብ ነው ያለህ? » « ከማይጠቅም ትግል ትርጉም ያለው ሽንፈት በላጭ ነው። እኔ በመሸሽ ነበር የምታገለው። ማረፍ እየፈለግኩ መሄድ፣ እቅፍ እየፈለግኩ ብቸኝነትን ሳሳድድ ነው የከረምኩት። ምናልባት ቀሽም ሆኜ ይሆናል። ምናልባት አቅም አጥቼ ይሆናል። ምናልባት ምናልባት መለያየት ከማውቀው ውሸት የበለጠ የሚያስፈራ መስሎኝ ፈርቼ ይሆናል። ምናልባት የትም መሄጃ ስለሌለኝ፣ የኔ የምለው ሰው ስለሌለ የኔ ብዬ ካልኳቸው ለመራቅ ድፍረት ስላጣሁ ይሆናል። ምናልባት ምንም አላውቅም ይሆናል። ምናልባት አንቺን ስለምወድሽና የኔ አይደለሽም ብዬ መካድ ኃጥያት መስሎኝ ይሆናል። ምናልባት…» የታፈነ እንባው ተረጋግቶ ወረደ። ያልተገለፀን ህመም የደበቀ የተለየ እንባ ፈሰሰው። ጊዝሊ ልቧ በፀፀት ይቃጠላል። እንባዋ ከቁጥጥሯ ውጪ ሆኗል። እርሱ በህይወቷ ፍፁም እንቢ ልትለው የማትችለው ሰው ሆኗል። እድሜ ዘመኗን ሁሉ ሀቅ ነው ብላ የተቀበለችው ነገር ፍፁም ተቃራኒ ሆኖባት ሀቀኛ ሆኖ ያገኘችው እርሱን ነው።። « ይቅር በያት! እውነቱን ከማወቅሽ የበለጠ ቅጣት የለም ለሷ! የኖረችው ሁሉ የስጋትና የቅጣት ነበር። እራሷን ከቀጣችው የበለጠ አትቀጫትም! ተያት፣ ይቅር በያት ምንም ብትሆን እናትሽ ነች። » « እንዴት አይን አይኔን እያየች በውሸት አኖረችኝ? ምን አይነት እናት ናት? እንዴት…? » እንባዋን ሳግ አጀበው። ቃላቶቿ በእርጋታ ከአንደበቷ ለመውጣት ተቸገሩ። እርሱ እንባውን ከጠረገ በኋላ ጊዝሊን ያፅናናል። እርሱ አሁን ክንፉን እንደዘረጋ መልዓክ ነው። « ይቅር ትለኛለህ ግን? አንድ ቀን እንኳ… » መናገር አቃታት። በእቅፉ ስር ተሸጎጠች። እድሜ ዘመን ሙሉ ሲከዱት የነበረውን ነብይ እውነተኝነት አውቀው ቀና ብለው ለማየት ሀፍረት እንደያዛቸው ሰዎች ሆነች። በእቅፉ ስር ተንሰቀሰቀች። አቅፏት በእንባው ተከተላት። እንባው ግን ፈገግታም ነበረው። ልክ ደስ እንደሚል ስቃይ፣ ስቃዩን እያነባ የናፈቀውን እቅፏን ናፍቆት በፈገግታ ይገልፃል። ስታቅፈው ወላድ ሆነ። ★……………★……………★ …………………………………… « ይህ ያንቺ ታሪክ ነው ማለት እንችላለን? » « የኔ ብቻ ማን አደረገው የብዙዎች ያልተነገረ ታሪክ ሊሆን ይችላል። ባለፉት ትላንቶቻችን ስህተት ዛሬ ላይ ዋጋ እየከፈሉ ያሉ መዓት ሰዎች ይኖራሉ። ፍቅር እኮ ትዝታ ብቻ ሆኖ አይቀርም። አንዳንዴ መርዝ፣ አንዳንዴ የማይደርቅ ቁስል ፣ አንዳንዴም ፈውስ ይሆናል። » « በመፅሀፍሽ ውስጥ ያልመለስሻቸው ወይም እንድትመልሺልን የምንጠብቃቸው ብዙ ነገሮች ነበሩ። ለምን በቀጥታ ለመመለስ አልፈለግሽም? » « ስኖር የገባኝ ነገር ሁሉም መልሶች የራሳቸው ጊዜ አላቸው። ምናልባት እኔ ሁሉንም በግልፅ ያልተናገርኩበት ምክንያት ከዚህ የመነጨ ሊሆን ይችላል። በህይወት ውስጥ ስለ ሁሉም ነገር መልስ እያገኘን ነው የኖርነው ማለት አልችልም። ምላሽ አለማግኘት በራሱ ምላሽ ይሆናል። » « ከዚህ ታሪክ በኋላ የገጠመሽ የተለየ ገጠመኝ አለ? » « እየኖርኩት ነው የገጠመኝን። ልቤ ትንሽ ፀፀት አለው። አውቃለሁ ሁሉንም ማስደሰት አትችልም። አንዳንዴ ብዙዎች ስህተት ላይ እንዳይወድቁ ስትል በህይወትህ ልክ የሆነውን ታጣለህ። ያው ይኖራል የለም ማለት አልችልም። » « የመጨረሻ ጥያቄዬ ላድርገውና መፅሀፉ የተለያዩ አጫጭር ታሪኮችን የያዘ ለየት ባለ አቀራረብ የተዘጋጀ ነው። ግን እንዴት ኡራዝ ቪ ልትዪው ቻልሽ? ትንሽ ስሙ ለየት ያለ እና አነጋጋሪ ነው። » « እውነቱን ለመናገር መፅሀፉ ውስጥ ያሉ ታሪኮች ተፅፈው ከተጠናቀቁ በኋላ ታሪኮቹን የሚገልፅልኝ ርዕስ ለመወሰን ተቸግሬ ነበር። እንደሚታወቀው ህይወት ወይም በኔ አገላለፅ ቪ ብዙ ስሜቶችን የያዘ ነው። እኔ ላሰፈርኳቸው ታሪኮች ደግሞ ተስማሚ የሚሆን ቃል ኡራዝ እንደሆነ አመንኩ። ምን መሰለህ ኡራዝ በአንድ በኩል እድል፣ እጣ ፈንታ፣ ክብር፣ ጥንካሬ የሚል ትርጉም አለው። በሌላ በኩል ስብራት፣ ህመም፣ የስነ ልቦና ቀውስ ወይም በእንግሊዘኛው Trauma የሚል ትርጓሜ አለው። ሙሉ መፅሀፌ ውስጥ የሚገኙ ታሪኮች በእነዚህ ዙርያ ያጠነጥናል። እናም ኡራዝ ቪ ያልኩት በመፅሀፉ ውስጥ ያሉትን ታሪኮች ለመግለፅ ተስማሚ ቃል ሆኖ ስላገኘሁት ነው። » « ክቡራን ተመልካቾቻችን ከወጣቷ ደራሲ ቪደን ሎክዋቼ ጋር ያደረግነው ቆይታ ይህን ይመስላል። ኡራዝ ቪ የተሰኘውን መፅሀፏን ገዝታችሁ አንብቡላት። በዚያውም በመፅሀፉ ውስጥ የተነሱ በማህበራዊ ኑረቶቻችን ውስጥ የምናስተናግዳቸውና መፍትሄ ሳናበጅላቸው ምስጢር አድርገን የምንሸሽገጋቸው ጉዳዮች ቤተሰብን ብሎም ሀገርን የማፈራረስ አቅም አላቸውና እንምከርባቸው። ሁላችሁም መፅሀፉን በማንበብ እንድትወያዩበት እንድትነጋገሩበት ከወዲሁ ግብዣዬ ነው። እንግዲህ ደራሲ ቪደን ሎክዋቼ ለነበረን ቆይታ፣ ላበረከትሽልንም ድንቅ መፅሀፍ እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ። በሌላ አዲስ ስራ እንደምንገናኝ ተስፋ አደርጋለሁ። » ሞቅ አድርጎ ጋዜጠኛው ተሰናበታት። ቪደን በአንድ መፅሀፏ ስሟ ናኘ። ጋዜጠኛው አመስግኗት ተሰነባብተው ስትወጣ ፈገግ ብትልም ፈገግታዋ ሙሉ አልነበረም። ህመም ነበረው ዳግም የማይጠገን ቁስል አይነት። በምስለ ህሊናዋ የጊዝሊ የማይረሳ ፈገግታ ብቅ አለባት። ልትፈግግ ስትል መልሶ ፈገግታዋ ቅጭም አለ። ያ ፈገግታ ላታገኘው አምልጧታልና። ★……………★……………★ ……………………………………
5782Loading...
17
« ምን አደረግኩሽ? ምስጢሬን ምንም ሳልደብቅ ስላካፈልኩሽ በአደባባይ ታዋርጂኛለሽ? » « ጊዙ ምንድን ነው የምትዪው? » « ዝም በይ… አንቺ አታላይ ነሽ እኔን ብቻ አይደለም ሁላችንንም ነው ያሞኘሽን! » « ኧረ በፈጠረሽ ጊዙ ምን አደረግኩሽ? » ቪደን በጊዝሊ ሁኔታ ተደናግጣለች። በምን ጉዳይ እንደምትወቅሳትም አታውቅም። ጊዝሊ እንባ እየተናነቃት ንዴት ብስጭቷን፣ ስብራቷን የገለጠችባትን ጓደኛዋን እየወቀሰች ነው። « ምን እንዳደረግሽ አታውቂም አይደል? እ… ምንም አታውቂም አይደል? » እያለቀሰች ቪደን ካሳተመችው መፅሀፍ ውስጥ የምታነበውን ገልጣ መፈለግ ጀመረች። « ምንም አታውቂም አይደል? » እንባ እየተናነቃት የመፅሀፍቱን ገፆች ትገልፃለች። ከመፅሀፉ ውስጥ ገፅ 30 ላይ ስትደርስ ማንበብ ጀመረች። «… ሰማይ ወድቆ ምድር ተሰንጥቆ ቢውጣት ተመኘች። እራሷን ረገመች። የእድለ ቢስነት ስሜት ጠልቆ ወጋት። ኢልሀም ተሰበረች። …» « ምንም አታውቂም አይደል? » በእንባዋ እየታጀበች ሳግ እየተናነቃት ቀጠለች። « … አሚር ወደ ኢልሀም ቤተሰቦች አባቱን አስከትሎ ሽምግልና ሲልክ የኢልሀም እናት ጋብቻው እንዳይፈፀም ተከላከለች። ኢልሀም ከአሚር አባት የተወለደች ናት። ስለ ኢልሀም አባት ከእናቷ በስተቀር ማንም አያውቅም ነበር። እናቷ በድብቅ ታፈቅረው ከነበረው ከድሮ ፍቅረኛዋ ጋር ስትለያይ እርጉዝ ነበረች። ቤተሰቦቿ ባል አምጥተው በግድ ሊድሯት ሲወስኑ እርግዝናዋን ከሁሉም ደበቀች። የቀድሞው ፍቅረኛዋ ማርገዟን እንኳ ሳያውቅ ተለያዩ። እንዳረገዘች ባለቤቷን አገባች። …» ጊዝሊ መፅሀፉን ገልጣ ማንበቧን ቀጠለች። ንባቧ በሚቆራረጥ የሀዘን ድምፅ የታጀበ ነበር። በየመሀሉ ብሶትዋ እየገነፈለ « ምንም አላደረግሽም አይደል? » እያለች በንዴት እያቋረጠች መልሳ ትቀጥላለች። «… ኢልሀም የምታፈቅረው አሚር ወንድሟ የማታውቀው አባቷ ልጅ ሆኖ ተገኘ። እናቷ ከሁሉም የደበቀችውን ምስጢር ልጇ ስታፈቅር እራሷ ምስጢር የነበረችው ልጇ ገለጠችባት!…» ጊዝሊ ማንበብ አቃታት። እንባዋ ገታት… « ጊዙ…» « ዝም በይ! ዝም በይ!… » ቪደን ለመናገር ስትሞክር ጊዝሊ በቁጣ አስቆመቻት! « የኛ ቬን ዝም በል! ዝም በይ… ኢልሀም ያንቺ የተነሳሽነት ምልክት እ? በጣም ተራቀሻል አይደል? ቆይ ግን ምን አገኘሽ? ውርደቴን፣ ስብራቴን፣ ህመሜን በራሴው ገንዘብ አሳትመሽ ለዓለም ስታስነብቢው ምን ተሰማሽ? ስሜን ቀይረሽ ታሪኬን ስለፃፍሽው፣ ምስጢሬን በሌላ ሰው መስለሽ ስለተናገርሽው አያመኝም? ምን አገኘሽ? ህመሜን ሽጠሽ ምን አተረፍሽ? » ድምፇ ውስጥ ስብራቷ፣ ህመሟ ይጮሀል። ድምፇ ተስለመለመ። ቪደን የምትናገረው ጠፍቷት ተለጉማለች። « ከእንግዲህ በህይወቴ ውስጥ እንዳላይሽ! ለነገሩ ምን ህይወት አለኝ… ሒጂልኝ አሁን በህመሜ እንደነገስሽው ኑሪ! በ…» ጊዝሊ የምትናገርበት ቃል አጥታ በእጇ ያለውን መፅሀፍ ቪደን ላይ ወርውራ ወጣች። ቪደን ከሄደችበት ጠዝጣዥ ትውስታዋ ተመልሳ ባዶ ሆና እየተጨበጨበላት ንግግሯን ለማድመጥ ለመጡ ታዳሚዎች ንግግር ለማድረግ ወደ መድረኩ ለመውጣት ከተቀመጠችበት ተነሳች። ጭብጨባው ግን ልቧን የሚያሞቅ አልነበረም። ጭብጨባው እያንዳንዱ የጊዝሊ እንባ የሚያስታውሳት ደውል ነው። ቪደን ደስታዋ በመፅሀፏ እንዳሰፈረችው ሁለት ወደ ኋላ: አንድ ወደፊት ሆኗል። ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። « ያመንከው ፍቅር ሊያቆስልህ፣ የምትሸሸው ጥላቻ ሊያሽርህ ይችላል። ማን እየፃፈህ፣ ማን ለዓለም ምስጢሮችህን ሊናገር እንዳሰፈሰፈ አታውቅም። የተውከው ትላንት አንተ ስለተውከው ብቻ አይተውህም። ተሸሽገህም ሆነ ሸሽገህ ሁሌም በሰላም አትኖርም። የነበርክበትን መንገድ ስለማትመለስበት መንገዱ አያበቃም። አንዳንድ መንገዶች አያልቁም። ህይወት አይደል ምንም ይሁን ምን ህይወትን ለሰጠህ ጌታህ ታመን። ተፈፀመ የሚባል ነገር የለም፣ ህይወት ይቀጥላል። እኔ ግን አበቃሁ! 🙏🙏🙏» [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
7353Loading...
18
እጅግ የምንፈልገው ነገር እንደሚፈልገን ያወቅኩት÷ ሸንኮራ አገዳ ማከፋፈያ በራፋችን ላይ ሲከፈት ነው። እኔ ነኝ(አብዱዋ አይሆንም መቼስ😂) : @Venuee13
6713Loading...
19
እም ወላጆቻችሁ ፡ ቀለም ደጃፍ የተመላለሳችሁ ስለሆናችሁ ሑሉንም የዓለም እውቀት የተባለን የምታውቁ ይመስላቸዋል... ትንሹንም ትልቁንም የዚህ ዘመን ወግና አዲስ ነገር ይጠይቋችኋል... አላውቅም መባልን አይፈልጉም... የዚህን ሑሉ ዓመት ልፋታቸውን መልስ በጥያቄዎቻቸው ያስሳሉ.... ይህ «እውቀት» ተብዬ ለሕይዎታችን እዚህ ግባ የሚባል ነገር እንዳላዋጣ መንገር አትችሉም... የሚሆነውንም የማይሆነውንም መልስ ትደነኩራላችሁ... ይደክማል አንዳንዴ...! (ነጃት ሐሰን) : @Venuee13
7966Loading...
20
« ለምንድን ነው ግን የምትጠዪኝ? » በጥያቄው ውስጥ ሀዘኑ ይደመጣል። ድምፁ እጅጉን የተረጋጋ እና ያዘነ ነበር። ኢልሀም አፍና የቆየችው ንዴቷ በሙሉ ተጠራቅሞ ከአንደበቷ ዋለ። አባትነቱን ረሳች። « እንዴት ብዬ ልውደድህ? የት ነበርክ ስፈልግህ? እኔ አባት እያለኝ አባት እንደሌለው ሰው ስኖር፣ ስናፍቅህ ምን እንደሚሰማኝ ታውቃለህ? ሲጀመር አንተ ራስ ወዳድ ነህ ለራስህ እና ለራስህ ብቻ ነው የምታስበው! ሁለታችንንም አትወደንም! ታውቃለህ አንተ ስትኖር ሁሉ ነገር ይጨንቀኛል። ሁሉም ነገር ያስጠላኛል። አንድም ቀን ስለኛ አስበህ አታውቅም! እራስ ወዳድ ነህ! ጨካኝ!… አትወደንም! አዎ አልወድህም! እናቴም አትወድህም! » ንዴቷ ሁለመናዋን ተቆጣጠራት። ጨከነች፣ ነደደች፣ የልቧን ተፋች። ኢልሀም ድምፇ ከፍ ብሎ ስትናገር የሰማችው እናቷ በድንጋጤ መጥታ ኢልሀም መናገሯን እንድታቆም ተቆጣቻት። « እማዬ አይወደንም… ተዪኝ… አንቺም አትወጂውም! እንደማንወደው ይወቅ…» የኢልሀም እናት በንዴት ልጇን በጥፊ አናጋቻት። ልጇን ከመታቻት በኋላ እጇ ተንቀጠቀጠ። ኢልሀም በንዴት ጦፋ ወደ አባቷ ተመለከተች። ዝም ብሎ ምንም ቃል ሳይተነፍስ እንባው በግራ አይኑ በኩል የአፍንጫውን ጠርዝ ታኮ እየወረደ ነበር። ወድያው እጁን ልኮ እንባውን ጠርጎ ምንም ሳይናገር ከተቀመጠበት ተነስቶ ወጣ። ኢልሀም ከነንዴቷ ወደ መኝታ ክፍሏ አመራች። የኢልሀም እናት ብቻዋን መመገብያ ክፍሉ ውስጥ ግራ ገብቷት፣ ድንጋጤው እያንቀጠቀጣት ታለቅሳለች። የኢልሀም ቤት የታፈኑ ስሜቶች ገንፍለውበት ድብልቅልቁን ወጣ። የእንባ መናኸርያ ሆነ። የተተፋው ሁሉ እንባ እየለኮሰ ሀዘን ያቀጣጥል ጀመር። የእናት፣ የልጅ እና የአባት እንባ በአንዴ ፈሰሰበት። …» እንባዋ ከአይኖቿ አፈተለከ። ሰውነቷ ይንቀጠቀጣል። ልቧን እያፈናት መጣ። ★……………★……………★ …………………………………… ድንገት ህልም እንደ ጉም ይተናል። በዘመናት የተገነባ አብሮነት በቅፅበት ይፈርሳል። እድሜ ዘመን ፍፁም እርግጠኛ የሆኑበት ሰው ምንም እንደማያውቁት የሚገለጥበት ቀን ይመጣል። የጠሉት፣ የናቁት ማንነት ስር በሀፍረት ለመሸጎጥ አቅም ይጠፋል። ልብ ሲያዝን አይን ያለቅሳል። ልብ ሀዘኑ ሲጠነክር ግን እንባ ይደርቃል። ሆድ በቀላሉ መባስ ያቆማል። ጥርስ ይስቃል ግና ለደስታ ምንም አያዋጣም። እንዲያ ይሆናል ድንገት… « ለምንድን ነው እማዬ ትዳር እንዳልይዝ የምትከላከዪኝ? አንደማንም ልጅ ታቅፌ ማስፈራራት ነበረብኝ? ምናደረግኩሽ? ምንድን ነው የምትፈልጊው? » ጊዝሊ እንባዋ ለአጀብ ይወርዳል። የምትወደውን ሰው እንዳታገባ ተከልክላለች። እናትዋ በድንጋጤ፣ በፍርሀት፣ የሆነ የቅዠት ዓለም ውስጥ ያለች ይመስላታል። ድንጋጤዋ እንባ ከለከላት። የጊዝሊ አባት ጊዝሊን እየተመለከተ ዝም ብሏል። አንደበቱ ከቃላት አልታረቀም። ሚስት እና ልጁን እያፈራረቀ ይመለከታል። ጊዝሊ መልስ ፍለጋ እናቷን መወትወቷን ቀጥላለች። እንዲያ ይሆናል የማይሆነው ይሆናል። አበቃ ያሉት ትላንት አንዳንዴ ዛሬ ይቀጥላል! : @Venuee13 @Venuee13
6711Loading...
21
« ኡራዝ ቪ» [አብዱልሀኪም ሰፋ] (አይቻልም እኔን አትባዪም!) : «… « ከሰማሁ በኋላ» ……ገፅ 12…… « ኢልሀም እና አሚር እኛን ፈነገሉን እኮ። » « ያው አንተ ስትፈዝ አመለጠችህ እንግዲህ ምን ታረገዋለህ? » « ቲሽ እኮ እኔ ሰው አጥቼ? » « አንተን አሁን ማን ይወድሀል? » « ኧረ ማንም አይውደደኝ እኔም አልፈልግም! ነፃ ሆነህ መኖር፣ ስለማንም ፍቅርና መውደድ ሳትጨነቅ መኖር እንዴት ደስ እንደሚል! ከዚያ ደግሞ አንዳንዴ እንደ አሚር አባት በራስ ዓለም ፏ ማለት ው… እንዴት ረሀ እንደሆነ እኮ… » « ማለት? » « እሺ ቬን ለወሬማ ሟች ነህ! ሀሀሀሀ… » ነቢል በቬን ላይ ተሳለቀ። « አትረባም እኮ አንተን ሰው ብዬ መምጣቴ… አርፌ ኢሉ ጋር ብውል ይሻለኝ ነበር። » « ኧረ ቀስ የሆነ ነገር እየጨሰ ነው…» ነቢል አብሻቂ ፈገግታው እያጀበው ነበር። « የምሬን እኮ ነው ኢሉ እየደበራት ነው የወጣሁት። ደግሞ ከአሚር ጋር ስላላቸው ግንኙነት ስጠይቃት የሆነ አቅማማችና ወሬ አስቀየሰችኝ! » « ያው ልቧ እየተንገዳገደ ይሆናላ። ያርግላት ጓደኛዬ ፀዴ ነው። » « ከጓደኛዬ ግን አይበልጥም።» « ኧረ እንደውም ረስቼው አሁን ትዝ አለኝ! አንተ እኔ ያንን ኃያሲ አስተዋውቄህ በጎን ለብቻህ ታገኘዋለሀ?። ኧረ ደስ አይልም ሙድህ ከባድ ነው። ደግሞ እኮ ባለፈው ተገናኝተን ስላንተ እንደማላውቅህ አድርጎ እንዳዲስ አያወራልኝም መሰለህ? » « የምርህን ነው? ምን አለህ በናትህ? » « ኧረ ዝም በለው በናትህ ለካ ኃያሲዎችም ይቀባጥራሉ። » « ምንድን ነው ብትናገር ትሞታለህ እንዴ ሀይ! » « ባክህ ሲቀባጥር ጓደኛህ ጥሩ ፀሀፊ ነው ምናምን እያለ ተጃጃለብኝ። » « ቀንተህ ነዋ? ሀሀሀ » « ምን ፅፈህለት ነው ግን? » « ምንም የተለየ ነገር አላሳየሁትም። የሆነ ሀሳቡን ሳይሆን ሀሳቡን የነገርኩበት መንገድ ነው የተመቸው። ስለ ትላልቅ ሰዎች ስብዕና ምናምን ከህይወት ጋር እያቆራኘሁ የፃፍኩትን አሳይቼው ነው። » « ስለ ጋሼ ብትፅፊማ በቃ ወሬውን አልችለውማ በዚህ አይነት! » « ማናቸው ጋሼ! » « የአሚር አባት ናቸዋ። ገራሚ ሰውዬ ብታይ ደግሞ መች መች ይራቀቃሉ መሰለህ! » « እና እስካሁን እንዴት አልነገርከኝም። አቦ በናትህ እስቲ ንገረኝ! የምር ስለ አሚር እራሱ እኮ ብዙ አላውቅም ጓደኛዬ እንዳትበላ! » ቬን የአሚርን የቅርብ ጓደኛ ስለ አሚር እና ቤተሰቦቹ ለማወቅ በጉጉት ጠየቀ። ነቢል አውርቶ ስለማይጠግብለት ቤተሰብ ለቬን መተረኩን ቀጠለ። …» የምትድንበት መድሀኒት ሊነገርህ ነው እንደተባለ በሽተኛ ልቧ ተንጠለጠለ። ተቀምጣ መቀመጥ አማራት፣ ተንቆራጠጠች። ★……………★……………★ …………………………………… « ቃላቶቼ ከእንግዲህ አንተ ዘንድ ዋጋ ያላቸው አይመስለኝም። » የሀሊም አባት ናቸው። ሀሊም አንደበቱ ቃል ማውጣት አቃተው። ተለጎመ። ድንጋጤ ልሳኑን ዘጋው። ቤታቸው አዲስ የማይለመድ ሀዘን ገባ። ኢዝሀር የሰማውን ማመን አቅቶታል። ጓደኛውን ሀሊም በምን መልኩ ማናገር እንዳለበት ግራ ገብቶታል። ነገር ዓለሙ ሁሉ በአንዴ ተቀየረ። ሊሆን ይችላል ተብሎ የማይታሰበው ሆነ። 6 ነፍሶች በሁለት ነፍሶች ሰበብ ይሰቃዩ ጀመር። የማይገለፅ ጥልቅ ህመም ያዘለ ዘላለሙን በውስጥ የሚቀር ስብራት ተሰማ። ቢናገሩትም ዝም ቢሉም ሁሉ ነገርን የሚያውክ ጠዝጣዥ ቁስል። « ከዚህ በኋላ እንዴት ብዬ ነው የልጄን ፊት የምመለከተው? » የሀሊም አባት ጭንቀት ሀዘናቸውን ለባለቤታቸው እያማከሩ ነው። « ታውቅ ነበር ግን? » ከእንባቸው ጋር እየታገሉ ነው። « በፍፁም ጌታዬ ምስክሬ ነው ምንም አላውቅም ነበር። ካለፍኩበት ትላንት ተሽዬ ለመገኘት ትላንቴን ሁሉ ነግሬያት ያገባኋትን ሚስቴን ይህን ባውቅ የምደብቃት ይመስልሻል? » « አውቃለሁ አትዋሽም… » ትውስታቸው ወደ ኋላ ሰደዳቸው። ቤተሰቦቻቸው ተፈቃቅደው ለትዳር ከተታጩ በኋላ ከሀሊም አባት ጋር እንዲተያዩና እንዲያወሩ ለመጀመርያ ጊዘፀ አብረው ወደ ተቀመጡበት ጊዜ፣ ወደ ያኔ ለትዳር የታጩበት ጊዜ ላይ ሄደ ትውስታቸው። « አንድ ነገር እንድታውቂ እፈልጋለሁ። እኔ ትዳራችንን እውነተኛ ሆኜ መጀመር እፈልጋለሁ። በምነግርሽ ነገር ላይ ተመርኩዘሽ ትዳሩን አልፈልግም ማለት ትችያለሽ። » የሀሊም እናት በሀፍረት እጅና እጃቸውን እየፈተጉ ያዳምጣሉ። « ስላንቺ መልካምነት ነግረውኛል። የኔንም ነግረውሽ ይሆናል። ግና እነሱ ያልነገሩሽን እነግርሻለሁ። » የሚነገራቸውን ለማዳመጥ ቸኮሉ። « እነሱ እንደነገሩሽ መልካም ሰው አይደለሁም። ጌታዬ የደበቀልኝ ብዙ ነውሮች አሉኝ። ልቤ ንፁህ አይደለም። ካንቺ ቀደም ሰው ወድጄበታለሁ። የጌታዬን ክልከላ ተላልፌ ክብር አጉድፍያለሁ። አሁን ምስጋና ለጌታዬ ይሁንና በትላንትናው ማንነቴ ላይ አይደለሁም። ወደ ጌታዬ ፍፁም ከተመለስኩ ረጅም ጊዜ ያስቆጠርኩ አይደለሁም። የምነግርሽ ሁሉ ሊጠቅምሽም ላይጠቅምሽም ይችላል። እኔ ግን ስለራሴ ደብቄ እራሴን ልሰጥሽ አልሻም። ከነገሩሽ ማንነቴ ውጪ የነበረውን ማንነቴን ይቅር ብለሽ የምትቀበዪኝ ከሆነ ባንቺ ደስተኛ ነኝ። ካልተቀበልሺኝም አላዝንብሽም። » ከትውስታቸው እንደመባነን ብለው ያኔ እንደተመለከቷቸው ባለቤታቸውን በእንባ ታጅበው ተመለከቷቸው። በጊዜው ሀቀኝነታቸው ማርኳቸው፣ ስላለፈው ማንነታቸው ሳይሆን ከዚያ በኋላ የገነቡትን ማንነታቸውን ወደውና ፈቅደው መጋባታቸው ታወሳቸው። ባለቤታቸው እንደማይዋሹና ድብብቆሽ የማይጫወቱ መሆናቸውን ጠንቅቀው ያውቃሉ። ግራ ገባቸው። « አንቺም ዝም አትበዪኛ… » « ምን ላድርግ እንደው ጭንቅ ጥብብ ቢለኝ እኮ ነው። አይ… ዘገየሁ…አይ ልጄን » እንባቸው አጀባቸው። « እንዴት ያለ ፈተና ነው ይሄ? » ይገልፁበት፣ የነገሩን ውስጠ ምስጢር ይረዱበት መንገድ አጡ። ★……………★……………★ …………………………………… «… « ምሬቴን ስተፋ » ……ገፅ 20…… ኢልሀም ፈራ ተባ እያለች ከአባቷ ፊት ለፊት መመገብያ ክፍሉ ውስጥ ተቀምጣለች። ለጓደኛዋ ቬን ለመስጠት ያሰበችውን ገንዘብ ለመጠየቅ እያወረደች እያወጣች ነው። ምክንያቱን ስለምትጠይቃት እናቷን ለመጠየቅ አልፈለገችም። ብዙ የማይናገራት አባቷን ገንዘቡን ጠይቃ ለመቀበል ወሰነች። « ገንዘብ ያስፈልገኛል! » ቀና ብላ ሳትመለከተው ፍላጎቷን አስቀደመች። « ለምንድን ነው ገንዘብ ያስፈለገሽ? » ሲጠይቃት ተናደደች። « ለምንስ ብፈልገው ምን አገባው? ስለኔ ሳይገደው መኖሩ ሳያንስ አሁን ገንዘብ የመፈለጌ ምክንያት ምን ያረግለታል? » በውስጧ በብሽቀት ታጉተመትማለች። ለአባቷ ምንም ነገር ለማስረዳት አቅም ታጣለች። « ተወው በቃ እንደውም አልፈልገም! » ንዴቷ ገብቶታል። ለምን ተናደድሽ፣ ለምን እደዚህ ትሆኛለሽ አላላትም። በቀጥታ ፍላጎቷን ሊፈፅምላት ወሰነ። « ምን ያህል ገንዘብ ነው የሚያስፈልግሽ? » ኢልሀም ያሰበችውን፣ የመጣላትን ለጓደኛዋ ይበቃል ብላ ያሰበችውን ቁጥር ጠራች። ገንዘቡን ነገ አዘጋጅቶ እንደሚሰጣት አሳወቃት። ልቧ ተደሰተ። ለአባቷ ግን ምንም አላለችም። የኢልሀም አባት በቁዘማ በተቀመጠበት ድንገተኛ ጥያቄ ለልጁ ሰደደ።
6101Loading...
22
እራሴን በብዙ መንገድ ታዘብኩት-የማስበውን ያህል ጥሩ እንዳልሆነ። አሁን የመተኛ ሰዐቴ ነው... በቅርብ ርቀት ደግሞ የሞተ ሰው በመኖሩ በጣም ጩኸትና ለቅሶ አለ... መርረበሽ አለው በጣም ፡ የሴቷ ድምፅ በተለይ በተለይ.... እና አሁን እኔ እያዘንኩ ያለሁት ለሞተው ሰው ወይስ ለተሰዋው እንቅልፌ? ለሑለተኛው ይመስለኛል... ሞት ምነው ማስደንገጡን እየረሳ መምጣት ጀመረ?! (ነጃት ሐሰን) : @Venuee13
6272Loading...
23
#ኡራዝ_ቪ እንደ አላህ ፍቃድ ሰኞ ይቀጥላል። ሰላም ለልባችሁ!
7780Loading...
24
« ኢሉ ለወላጆቼ ምን ለማድረግ ሁሌም እንደምሞክር ታውቅያለሽ? » አንገቷን ወደ ግራ ወደ ቀኝ እያንቀሳቀሰች፣ በሁለት እጆቿ እንባዋን እየጠረገች፡ ፈገግታዋ ሳይለያት እንደማታውቅ ገለፀችለት። « ይኸውልሽ እኔ ሁሌም ወላጆቼ ልጄ ብለው ሲሉ የሚሰማቸውን ደስታ እና ለሰዎች ልጄ እንዲህ ነው ብለው በኩራት የሚናገሩበትን ድፍረት እንዳልነጥቃቸው ነው የምሞክረው። አንድ ወላጅ ስለ ልጁ በኩራት በሰዎች ፊት እንዳይናገር በራስ መተማመኑን እራሱ ልጁ ከነጠቀው ከዚያ ወዲህ ምንም ቢደረግለት ስለ ልጁ በማውራት ይሰማው ከነበረው ደስታ ጋር አይስተካከልም። በቃ እኔ አባቴ የኔ ልጅ እኮ ብሎ ሲል እንዳያፍር ክብሩን ለመጠበቅ እጣጣራለሁ። በዚህ ደግሞ ምን ያህል ደስተኛ እንደሆነ አውቃለሁ። ምንም ቢሆን ምን አባትሽ ስላንቺ የሚሰማቸውን ልጄ እኮ ብለው ለሰዎች በኩራት ለማውራት ሀፍረት እንዲሰማቸው እንድታደርጊ አላግዝሽም። ምናልባት አንቺ ይህን ክብር ስላልነጠቅሻቸው እድሜ ልካቸውን ያመሰግኑሻል። » ኢልሀም እንባዋ ከቁጥጥሯ ውጪ ሆነ። አባቷን የሚያከብር ሰው ስለወደዳት ይሁን አባትዋን እንደምትወደው ሰው መውደድ ስላልቻለች ይሁን የምታለቅሰው ለየትኛው እንደሆነ አይታወቅም። ግና እርግጥ ነው ልቧ አሚርን በክብር መዝገቡ ላይ በጉልህ አስፍሮታል። …» ልቧ ፍርሀቱ ይበልጥ እየጨመረ መጣ። ከልክ በላይ አለቅጥ ደረቷን ይደልቃት ጀመር። ★……………★……………★ ትላንት እንደ ዛሬ፣ ዛሬ እንደ ነገ ባለበት ሳይቀየር ይቀጥላል? : @Venuee13 @Venuee13
7732Loading...
25
« ኡራዝ ቪ» [አብዱልሀኪም ሰፋ] (ከኋላሽ ማን ነበር?) : «… « ማሰብ የጀመርኩት » ……ገፅ 6…… « የት ነው ግን የምትተዋወቁት? » « ከማ ከነቢል ጋር? » « ጭራሽ ስሙ ነቢል ነው? » « እ… በቃ ባንቺ ቤት አራዳ ሆንሻ ሳታስነቂ በሙድ ስሙን ጠየቅሽኝ ማለት ነው።» « ምን ታረገዋለህ ብለህ ነው። እንደው ሲፈጥረኝም ብልህ ነኝ። » « ቲሽ… ለማያውቅሽ። አንድ ግቢ ሆነን እንዴት አትተዋወቁም? ነቢሎ ምስኪን ልጅ ነው። » « ጥሩ ትተዛዘኑ የለ እንዴ? » « በነገራችን ለይ አስተዋውቁኝ ማለት ክፋት የለውም። » « እኮ እኔ? » « ኧረ እርሶን ነው። » « ባክህ ገርሞኝ ነው። » « ምኑ? » « ቅርበታችሁ ነዋ ጓደኛዬን እንዳይቀማኝ ሰጋሁ በዚህ አያያዝ። » « ባክሽ እንደ ድንገት ነው የተግባባነው። ታሪክ የሌለ ነው የሚወደው። ያው ታውቅያለሽ ታሪክ እና ስነ ፅሁፍ እኔም እንደምወድ። እንዴት እንደሆነ ባላውቅም የሆነ ቆንጆ ታሪክ ካገኘሁ የሚገርም አድርጌ ነው የምተርከው። » « እሰይ ጭራሽ? » « የምሬን ነው ኢሉ። » « በቃ እኔ ደግሞ ቆንጆ ያልከውን ታሪክ እንድትተርከው ብሩን እሰጥሀለው። » « ከየት ታመጫለሽ ቆይ? » « እሱን በኔ ጣለው። » ኢልሀም ለምትወደው ጓደኛዋ ሰማይ መቧጠጥ ካለባት አታመነታም። ከሚጮህባት የቤቷ የድባቴ ጩኸት ለአፍታም እረፍት የምታገኘው ከጓደኛዋ ቬን ጋር ስትሆን ነው። ኢልሀም ስትወድ ከምሯ፣ ዘንበል ያለች ጊዜ ደግሞ መመለሻዋ የራቀ፣ ወደ ውስጥም ወደ ውጭም የምታለቅስ ቅላትና ጥቁረትን አግባብታ የምትኖር ቀይ ጠይም ሴት ናት። …» “ አ… ማ… ማለት? " ስሜቷን የምትገልፅበት ቃል አጥታ ተንተባተበች። ★……………★……………★ …………………………………… « እማዬ አባ አንድ የማወራችሁ ነገር አለ። » ሀሊም ሀፍረት እየተሰማው ከራሱ ጋር እያመነታ የነበረበትን ጉዳይ አብሯቸው ተቀምጦ ለሚመለከታቸው ሊያፈርጠው ወሰነ። አንገቱን እንዳቀረቀረ የሞት ሞቱን ቃሉን ተነፈሰ። « አባዬ እማ ለማግባት ወስኛለሁ። » ሰውነቱ ይንቀጠቀጣል። « ክብሯን ነክተሀል? » « በፍፁም በክብር መረማመድን ካንተ አልተማርኩም። » « ቆንጆ ነች? » « እንግዲህ እማዬ ልቤ ወዷታል። ያፈቀረ ዘንድ የተፈቃሪው መልክ ፍቅሩ ነው። እንዲህ አይደል አባ የሚለው። » « ህልሞች አሏት? » « እኔንጃ አባዬ ጠልቄ አልጠየቅኳትም።» « መቼ ነው ታድያ ልትጋቡ የወሰናችሁት? » « ከሰሞኑ አባዬ ወደ አባቷ ዘንድ ሄዶ እጇን ይጠይቃል። » « ጎሽ ልጆችህን ባይኔ ሳላይ እንዳትገለኝ ብዬ የለመንኩት ጌታዬ ልመናዬን ሰምቶኛል መሰለኝ። » የሀሊም እናት ደስታቸው ፊታቸውን አበራው። « እማዬ የጠሪን ጥሪ ሰሚም አይደል፣ እንዴት አይሰማም ብለሽ ነወ። አባዬ ምን ትላለህ? » « ልብ አፍቅሮ ሲጎዳ ቀድሞ ከፈጣሪው ይጣላል። ከፈጣሪህ እንዳትጣላ የፍቅርህን ጤነኝነት እርግጠኛ ሁን። » « ይኸው አባትህ ጀመረው። አንዳንዴ እኮ የሚናገረው አይገባኝም። በሉ እንደፍጥርጥራችሁ እኔ መሰናዳቴን ከወዲሁ ጀምርያለሁ። » የሀሊም እናት በደስታ እየተውለበለቡ ያሉበትን ክፍል ለቀው ወጡ። ሀሊም የእናቱን ፈገግታ ሲመለከት ሀሴት ተሰማው። ተረጋግተው ዝም ወዳሉት አባቱ ጋር እያማተረ « አባ ለምንድን ነው እንደዚህ ያልከኝ? » ሲል ጥያቄውን ሰደደ። « ልብ እንደ ምድር ነው። የተሸከመዉን፣ የሚሸከመውን አይናገርም። ሰዎችም የሸክሙን ክብደትና ቅለት አያውቁም። ልብ እንደ ምድር ስለ ሸክሙ አያወራም። የሸክሙን ክብደትም ስለታወቀለት ክብደቱ አይቀንስለትም። ልብ እንደ ምድር ሌሎችን የምታኖርበት ቦታ ነው። መልካም ሰዎችን ስታስቀምጥበት እንደ ደጋጎች ህይወትና ቀብር ያማረ ይሆናል። ሲኖሩ ደስታ፣ ሲለዪ ትዝታቸው ጥሩ ሚስክ ይሆናል። አደራህን ልጄ ስለ ልብህ! » « አባዬ ያልነገርከኝ ልብህ ውስጥ የደበቅከው ሸክም አለ? » « ልብ ያለ ሸክም ይኖራል ብለህ ነው ሀሊም? ይህን ብቻ እንዳትረሳ። ለመጨረሻ ጊዜ ከጀሀነም ወደ ጀነት እንደገባው ሰው ነህ። » « እንዴት አባ አልገባኝም? » « የአባትነት አንዱ መንገድ ለልጁ ሁሉንም አያስረዳም። ልጁ ጠንካራ እንዲሆንለት ይሻልና ወደፊት የሚረዳውን ብቻ በማድረግ ይጠመዳል። » « አባዬ ወላጆቿ ለኔ ለመዳር ፍቃደኛ ባይሆኑስ ግን? » « ወደፊት ትቀጥላለህ። ከቀደር ጋር መሟገትህን ታቆማለህ! » « በፍቅሬ ተስፋ ልቆርጥ? » « ሁሉም ፍቅር ተስፋ አያስፈልገውም። ሁሉም ፍቅር ተስፋ የለውም። » « ያን ያህል ቀላል ነው እንዴ ወደፊት መቀጠል? » « ሁሉም መንገዶች ክብደት የላቸውም። አንተ ነህ ክብደቱን የምትሰጠታቸው። » « አባዬ እኔ ምንም ቢሆን ያንተን ያህል እንኳ ጥንካሬ የለኝም! » « እውነት እኔ ጠንካራ እመስልሀለው? » « እንዴታ ካንተ ውጪ ለጥንካሬ ተምሳሌት የሚሆን አልገጠመኝም። » « ልባችንን እንደ ምድር ላደረገው ጌታ ምስጋና ይገባው። በእርግጥም ሰዎች ስለ ልባችን አያውቁም። » ★……………★……………★ …………………………………… «… « ደስታዬ» ……ገፅ 15…… ተግባቡ። አንድ ላይ አለሙ። ጎጇቸውን ሳይደርሱ ቀለሱ። እርሱ ሀሳቡ ቀድሞ ፍቅሩን ልክ ማድረግ ነበር አላማው። ፍላጎቱን አሳወቃት። ደስታዋ ልኬት አጣ። ልቦቻችው እንጂ አካላቶች አላወሩም። ከሚደብታት ቤት የመላቀቅ መሻቷ ይበልጥ ሲፈጥን ደስታው አሰከራት። የደስታዋ ሰበብ ሊሆን ከፊት የተሰለፈው አሚርን ትገልፅበት ቃል አጣች። ስለወደደችው፣ ስለወደዳት በክብሯ ሊፀዳዳ አልሞከረም። ፍቅሩን በትዳር ሊያከብረው ቀድሞ ወሰነ። ትደነግጥበት አቅም አጣች። ፈገግታዋ እንባ ቀላቀለ። ፍቅሩን በትዳር የሚገልፅላትን አገኘችና የሀሴት ማማ ላይ ሆና እራሷን አገኘችው። ከቃላት ባለፈ ልዩ ሰላምታን አልተሰጣጡም። « መቼ ታድያ ሽማግሌ ልላክ? አባትሽን ጠይቅያቸው እስቲ። » ኢልሀም የህይወቷን አዲስ ምዕራፍ ልትጀምር ስታስብ የአባቷን ፍቃድ መጠየቁ አልተዋጠላትም። « ግዴታ ነው የአባቴ መፍቀድ? » « ቤተሰብ ስለመመስረት እያሰብን ወላጆቻችን መግፋት ነውር ነው። አባትሽ አንቺ ላይ መብት አላቸው። » « ማን ስለሆነ? ስለወለደኝ ብቻ መብት አለው እኔ ላይ? እናቴ ነው ስለኔ የሚያገባት! እሱ አይመለከተውም! » « ታድያ መጋባታችን ይቅር? » « እንዴ? ለምን? » « አብረን ስንኖር ባልሽ ብቻ ሆኜ የምኖር ነው እንዴ የሚመስልሽ ለልጆችሽም አባት እንደምሆን አታውቂም? » « ምን አገናኘው ታድያ? » « ይኸውልሽ ኢሉ ለአባትሽ ያለሽን ፍቅር አልዳኘሁም። እኔ የምወደው አባት አለኝ። ማንም እንዲንቀው እና ክብሩን እንዲነካ አልፈልግም። ነገ ባለቤቴ ስትሆኚ አባትሽን ልክ እንደ አባቴ ነው የምመለከታቸው። እንደአባቴ የምመለከታቸውን ሰው ደግሞ አዝነው እና ሳያውቁ ልጃቸው መሆንን አልሻም! ወላጆቼም ቢሆን ይህን በፍፁም አይፈቅዱም! » ኢልሀም እንባዋ ተፈተለከ። በሳግ አጀበችው። « ያው አቅፌ ስለማላባብልሽ በኋላ ቤታችን በደንብ ብታለቅሺ አይሻልም? » ሳቋ እንባዋን እየገፈተረ ብቅ አለ። ለሳቋ ክብር በእጆቿ እንባዋን በእጇ ጠረገች። አሚር በእርጋታ ፈገግ እያለ
7372Loading...
26
ስለ ሀዘን... ስለቁርፍድ ገፆች... ስለ ጭምድድ ልብሶች... ውስጣቸው ስላለቁ ብርጭቆዎች... ስለነሱ «ውበት» ማውራት እጅግ ለልሳኔ የቀለለው ከመች ጀምሮ ነው? የሚል ጥያቄ አለኝ ለራሴ። (ነጃት ሐሰን) : @Venuee13 @Venuee13
6873Loading...
27
« ኡራዝ ቪ» [አብዱልሀኪም ሰፋ] (ወደ ኋላ: ወደ ፊት!) : « ብዙ ነገር ሆና ስለነበር ቀብሯ እንዲያምር ብላ ተስተካክላ ለመሞት እየሞከረች ነበር። አትድከሚ እያሉ ደጋግመው በነገር ሲታገሏት ተስፋዋን ተወችላቸው። ሞቷን አገኙ መሰል ተደሰቱባት። ለዚያ ነው ጌታዋን በነሱ በኩለ ለማወቅ የማትጥረው። ለዚያ ነው የእነሱና የእሷ ጌታ ይለያያል የምትለው። ደጉ ጌታ ግን ስንቴ በክፉ አምላኪው ተወቀሰ? » ★……………★……………★ « እስከመች ትሸሻለሽ? » « አላውቅም። በቃ መሸሽ ነው የቻልኩት። ታውቃለህ… » እንባዋ ገታት። ለእንባ የከበደ ብሶቷን ልትተነፍስ እየዳዳች። « ይቅር በያት ምንም ቢሆን እኮ ቆርጠሽ አትጥያትም። » « እኔ እንዳንተ መሬት የሚያህል ይቅርታና ትዕግስት የለኝም። » « በይ ተነሽ አሁን የሆነ ቦታ ይዤሽ ልሂድ! » እምቢታዋን ልትሰጠው ትፈልጋለች ግና እርሱ እምቢ የሚባል አይነት ሰው ከሆነባት ቆየ። ያ ተጠዪ ሲፈቀር ፍቅሩ ድንበር አልባ ሆነ። እንደጌታው መልዐክ ተቀደሰ። እንዴት ፈጠረው ተባለ ጌታው። ጌታው ሰው አለው መቼስ አያልቅበት ነገር ሸሽጓቸው የሆኑ የሆኑ ዘመኖች ላይ ይገልጣቸዋል። ተገለጠ በጊዜው፣ ታፈረ በሀቁ። ተከበረ በሰብሩ። ጊዝሊ ከስብራቷ የተራረፋትን ልቧን ይዛ መኖሩን ትጠላው ከነበረው፣ መኖርን ለርሱ ልታደርግ ትታገላለች። ስቃይ ነው መቼስ አልቅሰውት የማይወጣ፣ ጠልተው የማይረሱትን ሰው በልብ መያዝ።  ★……………★……………★ …………………………………… « የትዳር መልኩ የአባቴና የእናቴ ይመስለኛል። እንደ አባዬ ቁጥብ፣ እንደ እናቴ ፈገግ የሚል። አባቴ ከተንቀለቀለበት ዘመን ወጥቶ በእናቴ ሰበብ ሰክኗል። እናቴ ባለፈ ነገር ጦር እየተማዘዘች መኖርን አትወድም። ሰው ከትላንቱ የተሻለ እንዲሆን ይቅር ማለት መልካም ነው ትላለች። ብቸኛ ነኝ በነሱ ዓለም ውስጥ፣ ብዙም ነኝ በነሱ አይን ውስጥ። የእናቴና የአባቴ ተፈጥሮ የተለያየ ነው። እናቴ ሁሉም ነገሯ ፊት ለፊት ነው። ንዴት ብስጭቷ አይደበቅም። አባቴ ዝምታ ይቀናዋል። ንግግሩ በብዙ ይተረጎማል። የተናገረው እያደር ብዙ ትርጉም ይኖረዋል። ጓደኛ የለውም። እናቴ ታጃቢ ነች። ሁሉም ጋር አለች። ስለ ሁሉም ደህንነት ያስጨንቃታል። « ምንም ቢሆን ከሰው አትለይ። ሰው እንዲሁ አይከፋም፣ እንዲሁም ጥሩ አይሆንም። ሰው ደግ ነው ካልከው ሰላም የምትሆንበት ፍጥረት ነው። » እናቴ ይህ የሁሌም ንግግሯ ነው። « ለራስህ ግድ ከሰጠህ የሰው ነገር አይከብድህም። ሆነም ቀረ በስተመጨረሻ ብቻህን ነህ። » ብቻውን ለመሆን ያደረገውን፣ የገጠመውን ባላውቅም አባቴ ግን እንዲህ ይለኛል። እኔ ከሁለቱም ወርሼ ለራሴ ያነፅኩት ምግባር አለኝ። ታጋሽ ሆኜ የተከበርኩ እሆን ዘንድ ሀሊም አሉኝ። « አባትህ ግን የሆነ መፈላሰፍ ይቀናቸዋላ? » ብቸኛው ጓደኛዬ ኢዝሀር የአባቴን ንግግሮች ሲሰማ ሁሌም በአዕምሮው ላይ ፍልስፍና ያቃጭልበታል። ይህን ንግግሩ ስሰማ ሳቅ ይቀድመኛል። « የሆነ ውስጣቸውማ የሰለመ አርስቶትል ይኖራል። » « አል ገዛሊ እያሉ አርስቶትል አባዬ ውስጥ ምን ሊያደርግ ይገባል ብለህ ነው? » « የአባቱ ልጅ ምነው አባቴን የምወደው ከማህሙድ ደርዊሽ የፍቅር ግጥሞች በላይ ነው አልክ! » « በል በል እኔ እውቀቱ የለኝም አባዬ ስለሚወዳቸው ነው የጠቀስኩልህ። » « በተለየ ሁኔታ ግን እንዴት ኢማም አልገዛሊን ወደዳቸው? » « እንደነገረኝ ከሆነ ኢማም አልገዛሊ ለደረሱበት እውቀት ሰበብ የሚሆናቸውን መንገድ ያመላከታቸው አንድ ሽፍታ እንደሆነ ይታሰባል። » « ማለት? » « አንድ ጊዜ ኢማም አልገዛሊ ለአምስት አመታት ያህል ለትምህርት ካመሩበት ከተማ ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን ወደ ትውልድ ቀያቸው እየተመለሱ ነበር። በመንገድ ላይ ሽፍታዎች አስቆሟቸውና ሁሉንም ንብረቶቻቸውን ነጠቋቸው። ኢማም አል ገዛሊ ለአምስት አመታት ሙሉ ሲማሩ የፃፏቸውን ትምህርቶች የያዘው ማስታወሻቸው ሲወሰድባቸው በእጅጉ ተጨነቁ። ወደ ሽፍታዎቹ መሪ ጋር በመሄድ ሁሉንም በማሰረዳት ማስታወሻውን እንዲመልስላቸው ጠየቁት። ሽፍታወም እንዲህ አላቸው " ተምርያለሁ ትላለህ ግና ማስታወሻህን ስወስድብህ እውቀትን ታጣለህ፣ በልቦናህ መማር ሲኖርብህ በማስታወሻ ደብተርህ ላይ ተውከው " አላቸውና ማስታወሻውን መለሰላቸው። አልገዛሊ የሽፍታውን ንግግር ከአላህ ዘንድ የደረሳቸው ማስጠንቀቅያ አድርገው ተቀበሉት። በሶስት አመት ውስጥም ሁሉንም በአዕምሯቸው ሸምድደው ተረድተው ያዙት። ከዚያ በኋላ በማስታወሻ ደብተር ጥገኛ ከመሆን ተላቀቁ። እንግዲህ አባዬ እንደሚለው የኢማሙ መረዳትና ማስተንተን ጥልቅ ስለነበር እንጂ ንግግሩን ማንኛውም ተራ ሰው ቢሆን ከቁብም አይቆጥረውም ይላል። ለዚህም ይመስለኛል በጣም የሚወዳቸው። » « እኮ ጋሼ እኮ ይፈላሰፉታል የምልህ ለዚህ ነው። » « በል ሰውዬ ከአባዬ ራስ ውረድ! » ከኢዝሀር ጋር ስንገናኝ እንደነዚህ አይነት ጉዳዮችን ሳናወራ አንለያይም። ኢዝሀር ፈጣን እና አዳዲስ ነገሮችን ለማወቅ የሚተጋ ሰው ነው። ብዙ አንባቢ ባይሆንም ከሚያነቡ ሰዎች ጋር ተግባብቶ መኖር ይችልበታል። የእኔና የኢዙ ግንኙነት ቤተሰቦቻችንም ያውቃሉ። በእድሜ እኩያሞች ብንሆንም እንደ ታናሽ ወንድሜ እመለከተዋለሁ። ምናልባት የትምህርት ዓለም ውስጥ ካገኘሁት አንዱ ስጦታ ጓደኛዬን ኢዝሀር ይሆናል። ★……………★……………★ «… « ትውውቃችን» ……ገፅ 5…… « የተነጀሰ ልብ ትፈልጋለህ? » « አለኝ! » « ከየት አገኘህ? » « እየኖርኩ። » « ፍቅርስ አለህ? » « እሱማ ንፁህ ልብ ይፈልጋል። » « ንፁህ ልብ ከመጠበቅ የተነጀሰውን ማፅዳት አይበልጥም? » « ምነው የተቀደደ ተስፋ ሰፍተሽ ታውቅያለሽ እንዴ? » « ታድለህ! » « ለምኑ? » « የተቀደደ ተስፋ አግኝተሀል! » « መታደል ነው? » « ተስፋ ከማጣት አይሻልም? » « አቅምሽ ከባድ ነው ማለት ነው። » « እንዴት? » « ተስፋ ለማጣት እኮ ትልቅ አቅም ነው የሚጠይቀው። » ፊቷ ፈገገ። በምላሹ ፈገግ አለች። አፀፋውን መለሰላት። « እውነት ለመናገር አሁን ስላወራሁት ነገር ምንም የማውቀው ነገር የለም። ጓደኞቼ ናቸው እንዲህ ብለሽ አናግሪው ያሉኝ። » እጇን ወደ ጓደኞቿ እየጠቆመች አመላከተችው። ዞር ብሎ ያመላከተችውን ተመለከተ። ጓደኛው ፈገግ አለለት። በአግራሞት ፈገግታውን አስከተለ። « ኢልሀም እባላለሁ መተዋወቅ እንችላለን? » « ተዋወቅን እኮ መቼስ የምታውቂውን ስሜን ደግሜልሽ አላስመስልም። » ሳታስበው ሳቋ አመለጣት። አንዴ በአይኑ በፈገግታ ቃኘት አደረጋት። አንዲት የምትስቅ ሴት ነች። « ምነው ውበቴ አፈዘዘህ? » « ፈገግታሽ መች እድል ሰጠኝ። » የማትቆጣጠረው ሳቋ አመለጣት። « ኧረ…» ድምፇን እንድትቀንስ እጆቹን በአፉ እየጫነ ምልክት ሰጣት። « ገና በተዋወቅሺኝ ቀን ከላይብረሪው ልታስባርሪኝ ነው እንዴ? » እጇን በአፏ ጭና ከነፈገግታዋ ከፊት ለፊቱ ወንበር ስባ ተቀመጠች። ኢልሀም ለመርዘም ያልሞከረች፣ ለእጥረት ያላጎበደደች መካከለኛ ሴት ናት። ፈገግታዋ መልኳን ይበልጠዋል። ፈገግታዋ አምባገነን ነው መልኳን የመመልከቻ ጊዜ አይሰጥም። …» " ምንድን ነው እየተካሄደ ያለው? " ግራ ገብቷታል መጠየቋን ትቀጥላለች። ልብ የያዘ ሁሉ ልብ አይልም። እነዝያ ልባሞች ግን በእርግጥ የማወቅ ጉጉታቸው ይቀጥላል! : @Venuee13 @Venuee13
6773Loading...
28
@Venuee13 @Venuee13
7251Loading...
29
ጁምዓም አይደል ሰደቃ ይወደዳል። አንድ ነገር ልጠቁማችሁ። ፉአድ ሙና የጎደሉ አሉ 2 በሚል ፕሮጀክት በየእስር ቤቱ የሚገኙ የዋስ ብር ከፍለው መውጣት ያልቻሉትን ክፍያቸው በመክፈል ነፃነታቸውን እንዲያገኙ ከወዳጆቹ ጋር እየተንቀሳቀሱ ነው። እናንተም አነሰ በዛ ሳትሉ አቅማችሁ በፈቀደው ልክ በገንዘባችሁ፣ በዱዓ በምትችሉት ሁሉ ኒያችሁን በማሳመር እንድትሳተፉ እጋብዛችኋለሁ። የአካውንት ቁጥር ለመውሰድ በዚህ @Ifadasales ላይ በመጠየቅ መውሰድ ትችላላችሁ። በተጨማሪማ እስካሁን በተሰበሰበው ገንዘብ በእስር ቤት የተፈፀሙ ክፍያዎችን በራሱ በፉአድ ሙና ቻናል @fuadmu ላይ ማየት ትችላላችሁ።
6042Loading...
30
የጎደሉ አሉ! ፕሮጀክት ሁለት! ባሳለፍነው ረመዳን የውሀ ጉድጓድ ለማውጣት ባካሄድነው ዘመቻ በአላህ ፈቃድ በጅማ ዞን ሳኮሩ ወረዳ 1 የውሀ ጉድጓድ እንዲሁም በሀረማያ 2 የውሀ ጉድጓድ ለማውጣት እና የበርካታዎችን ድካም ለማቅለል ችለናል፡፡ አሁን ደግሞ እስርቤት ውስጥ ሆነው የዋስ ብር መክፈል አቅቷቸው እየማቀቁ ያሉ ወንድም እህቶችን በማያውቁት እጅ ነፃ እናወጣቸው ዘንድ ፕሮጀክት 2 ጀምረን ስድሳ ሺህ ብር አልፈናል፡፡ ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገን ገንዘብ ብዙ ነውና ሁላችሁም የራሳችሁን አሻራ እንድታሳርፉ እጠይቃለሁ፡፡ አካውንት @ifadasales ላይ በመውሰድ የአቅማችሁን አበርክቱ! አላህ ሀጃችሁን ያውጣ! ስራችንን ይውደድ! ኢንሻአላህ አንድ ላይ እንችላለን! . @fuadmu
5933Loading...
31
«ኡራዝ ቪ» [አብዱልሀኪም ሰፋ] (ባትናገሪው በበጀ) : « መልኳን ጌታዋ አስውቦ ፈጥሮት ሳለ ባደነቃት ሰው ተደነቀች። ክፉ ነው አድናቂው ውብ አድርጎ ጌታሽ ሰርቶሻል አላላትም፣ ውበትሽ ቀልብ ያሸፍታል አላት እንጂ። ላወቁት ፍጥረት መሸፈት እንጂ ካላወቁት ጌታ መሸሽ እኮ ልብ አያስደነግጥም! ምናረገች ተዏት ቢያንስ ላወቀችው ልክ ለመሆን ሞክራለች። ይልቅ ጌታዋን ብታሳውቋት ደግ አይደል? ለነገሩ  ተዓምርም ሆነ ተልዕኮ የሌላቸው ጌታ አልባ ስመ ነብያት በበዙበት ጊዜ እንዴት ብላ ደጓን ትወቅ! እንዲያ ሆኗል ነገሩ ለጀሀነም የታጨውን ጀነት አስገባኝ ብሎ እንደመማፀን ነው። » ስትሄድ ርቃ፣ ስትመለስ ግን የምትረጋበት የለም። መነሁለል ይሉት ጀመር የሷን መራቅ። ★……………★……………★ « እንዴት ነበር የመጀመርያው ግንኙነታችሁ? » « ያገኘሽውን መንገደኛ ሁሉ አታስታውሺም አይደል? » « ምን የተወሰነ ነገር ብናወራበት ብዬ እኮ ነው። » « ባክሽ የሁለት ሰዎችን ምስጢር ገልጠሽ አታተርፊም። » « ቆይ የሚረብሽሽ ነገር ምንድን ነው? » « እኔ ምልሽ መርሳትን ግን ለምንድን ነው በሽታ የምንለው? » « ለምን ጠየቅሺኝ? » « ማስታወስ በሽታ መሆን የነበረበት አይመስልሽም? » « እንዴት? » « ቆይ ሰው በረሳው ነገር ነው ወይስ በሚያስታውሰው ነገር ነው ይበልጥ የሚሰቃየው? » « አስቤው አላውቅም። » « ግን ልክ አይደለም። መርሳት በሽታ ብቻ ሊባል አይገባም። ማስታወስም እንደ ጸጋ ብቻ መቆጠር የለበትም። ቆይ የመርሳት በሽታን ማከም እንጂ የመርሳት በሽታን ማስተላለፍ ትችላላችሁ? » « መርሳት ተላላፊ በሽታ አይደለም። » « ቲሽ… በሽታውን ማስተላለፍ ሳትችሉ ስለማከሙ አወቃችሁ? ሃሃሃሃ… ግዴለሽም እኔን የመርሳት በሽታን አሲዢኝ። » « አይ ጊዝሊ አንዳንዴ እኮ ሾጥ ነሽ። » « ምን አንቺ እንደዝያ እያነበብሽና እየፃፍሽ ይሄ ከብዶሽ ነው? ቪዱ የምር እንቺ እራሱ እኮ ነካ ያረግሻል አንዳንዴ ወሬሽ አይገባኝም! » « በይ በይ አሁን ቤት ቶሎ ልድረስ አትለፍልፊብኝ! » « ሰለቸሁሽ? » « አልጠግብሽም! » « እሺ መች ነው የምትመለሺው? » « እያወቅሽ! » « እሺ ይቅናሽ እወድሻለሁ። » በፈገግታ ተሰናበተቻት። ጊዝሊ ቪደንን ከሸኘቻት በኋላ ዞር ብላ በአይኗ ዙርያዋን ስትቃኝ ቀፈፋት። ★……………★……………★ «… « ቤታችን » ……ገፅ 3…… : «… ያረጀ እድሜ በልጅነት ላይ ተገኘና ማርጀት አላስደንቅ አለ። መሸምገል ትርጉም አጣ። መኖር አላጓጓ አለ። ሞት ትልቅ እረፍት መሰለ። ህይወት ደግሞ የሞትን ግርማ ሞገስ ተላበሰ። ከየትኛው ልጀምር? የትኛው ታሪኬ ያጓጓል? ዛሬን ለመረዳትና ነገን ለመተንበይ ትላንትን ማውቅ ስለሚያስፈልግ ወደ ትላንት እወስዳችኋለሁ። ይህ የኔ ታሪክ ነው። የእኔ የኢልሀም። …» " ኡፍ… ወደ ገደለው ግቢ! " የማወቅ ጉጉቷ ትዕግስቷን ተፈታተነው። ካቆመችበት ቀጠለች። «… ባሏን የምትንቅ የማታለቅስ እናት አለችኝ። ሚስቱን የሚያከብር የሚያለቅስ ባል ልጅ ነኝ። አንድ ቀን የእናቴ ባል ታመመ። በአልጋ ላይ ውሎ አይን አይኔን በስስት ያየኝ ነበር። የእናቴ ባል ብዙ የሚያወራ አይደለም። ሹፌር ሆኖ ብዙ የማያወራ እሱ ይመስለኛል። የከባድ መኪና ሹፌሮች አያወሩም እንዴ? አባታቸው ከአጠገባቸው ሆነው በሚያድጉ ልጆች ዘውትር እንደቀናሁ አደግኩ። መንገደኛ ነው አባቴ፣ ቀን በቀን ስለ ደህንነቴ አያውቅም። ይህን አጠፋሽ፣ ይህን አደረግሽ ብሎም አይቆጣኝም። አንድ ነገር ብቻ ይለኛል። " እራስሽን ጠብቂ! " ይህ ቃሉ ምክር ይሁን ቁጣ ምን ማለት እንደሆነ አይገባኝም። ቢጠብቀኝ ምን አለበት ቆይ እራስሽን ጠብቂ ከሚለኝ? አባት አይደል? ነገረ ስራው ሁሉ አይጥመኝም። ቆይቶ የመጣ ጊዜ ቤቱ ድባቴ ይጫነዋል። እናቴ እና እኔ እንደፈለግን የምናስካካበት ቤት ልክ እሱ ሲመጣ ቤታችን የሀዘን ቤት ይመስላል። አባትን መናቅ ነውር ነው አይደል? እናቴ ባሏን ከናቀችው ከሁሉም አብልጬ የምወዳትን እናቴን ፈለግ ብከተል ነውር አለው? …» “ እንዴ… ይ… " ቃል አጠራት። ተስተካክላ ጨርሳ በተቀመጠችበት ይበልጥ ለመስተካከል ብላ ተስተጓጎለች። በድጋሚ ወደ ነበረችበት በታላቅ ጉጉት ተመልሳ ተደላድላ ቀጠለች። ……………★…………… ……ገፅ 4…… «… « ንቀት ሁሉ ነገርን የሚበላ እጅግ መርዛማ በሽታ ነው። እናቴ ለኔ ያልነገረችኝ አልወጣልህ ያላት የሆነ በድሏታል መሰለኝ ስትንቀው አትሰስትም። ባሏን የምትንቀው እናቴን ከባሏ የበለጠ እወዳታለሁ። እኔ እንኳ ስሜ ከኋላው መጠርያ ስላስፈለገው እንጂ አባት የማያስፈልገኝ ነበርኩ። አባቴን አልወደውም እናም የእናቴ ባል ብዬ ስጠራው ይበልጥ ይሻለኛል። የት ነበር? ሲያስፈልገኝ፣ ስፈልገው የት ነበር? ከተማ ለከተማ ተዟዙሮ መስራትን ለምን መረጠ? እንዴት ሰው የታወቀ የንግድ ሱቁን ዘግቶ የከባድ መኪና ሹፌር ይሆናል? « የኔ ውድ እራት እንብላ ተነሽ! » የተራበ ልቤን የማያጠግብ የአካሌን መብል እንድመገብ እናቴ ነበር የጠራችኝ። « እሺ እማዬ መጣሁ። » ከመደበቅያዬ በፈገግታ ትወጣለች። ከሰው ልጅ አንድ የማደንቀው ስልጣኔ ቤትን በተለያየ ክፍል የመክፈልን ሀሳብ ነው። የተለያዩ ክፍሎች በአንድ ቤት ውስጥ የመስራት ሀሳብ የሰው ልጅ ባያፈልቅ ኖሮ እንዴት ብለን ከራሳችን ሰዎች መሸሽ እንችል ነበር? አብረን እየኖርን አብረናቸው ከማንሆን ሰዎች ጋር በምን መልኩ ገደብ ማበጀት እንችል ነበር? ምናልባት በአንድ ቤት ውስጥ የተለየያ ክፍል የመስራትን ሀሳብ በመጀመርያ ያሰበው ሰው በጣም ብቸኝነት አስፈልጎት የመጣለት ሀሳብ ይሆናል። » ቤቱ ውስጥ ፀጥታ ሰፍኗል። እንደ ጽልመት የገዘፈ ፀጥታ። ዝም… ጭጭ… አንዲት እናት… ከምትንቀው ባሏ ከልጇ ጋር ቁጭ ብለው እራታቸውን ይመገባሉ። « ደስ ሲል ገበታ ለያይቶ መብላት። ለመጀመርያ ጊዜ በተለያየ መመገብያ መብላትን የመረጠው ሰው አብሮነት ሰልችቶት መሆን አለበት። » ኢልሀም ከራሷ ጋር ታጉተመትማለች። ዝም… ጭጭ… የሚታኘክ ምግብና፣ የሚጠጣ ውሀ ብቻ ድምፅ ይሰማል። የኢልሀም ቤት አብሮነት የሚደብተው፣ የተናቀ ባል የሚኖርበት፣ ልጅ አባት የተቀየመበት፣ እናት ንቀት የማትሰስትበት ድባቴ የጠናበት ቤት። …» ★……………★……………★ « ልብሽ የሚሽረው ነውርሽ ባልሆን ነበር። ነውርሽ ነኝ አሁን ብትሸሽጊኝ አትጠገኚም። በኔ ሰበብ ለምታጎድፊው ሀቅ ትጠየቂ ይሆን? እነሱስ ከአምላካቸው ፊት ተኝተው በድብቅ እኛን አገኙ። እኛ ግን እነሱን አጣን! ደግ ነው ጌታሽ ልክ ልሆን ስል አንቺን አሳጣኝ፣ ምንም ይሁን ብቻ እንኳን ገላሽ ገላዬን አልነካኝ። » « ምን እያሰብክ ነው? » « ምንም አለ ይደል ዝም ብሎ…»  ከሰጠመበት የሀሳብ ውቅያኖስ በጥያቄዋ ቀዝፎ እየወጣ። « ልቀፍህ? » « ደስ ይለኛል። » በፈገግታው እየታገለ በእቅፏ ውስጥ ተሸጎጠ። በሰላማዊው የምድር እቅፍ ውስጥ ሳለ ተናነቀው። « ይቅርታ አድርግልኝ ዘገየሁ! » እንባዋ ያጅባታል። « አንቺ ምንም አላጠፋሽም እኔ ቸኩዬ ነው። » አጥብቃ አቀፈችው። የሆነ ቋንቋ አልባ እንባ የሚጮህበት ዝምታ ሰፈነ። ሀሊም በእቅፏ ውስጥ እንዳለ ትውስታው የኋሊት አንደረደረው። በእቅፏ ውስጥ እንዳለ ተሰደደ። የምታውቁትን ሁሉም አታውቁም፣ የምትጠብቁትን ሁሉም አታገኙም። የመንገዱን ቀደር መቀበል ደስታን ይቀጥላል! : @Venuee13 @Venuee13
7294Loading...
32
💚🌼!
7700Loading...
33
ላመኑበት ነገር እስከመጨረሻው እጃቸውን ከማይሰጡ ሰዎች መሀል አንዱ እንደሆነ መናገር እችላለሁ። ሲሰራ አድምቶ ይሰራል፣ በተቻለው አቅም የሚጠላውን ነገር ከማይሰጡት ነው። እንዲህ ሰራሁ እንዲህ አደረግኩ አይልም፣ ግን ሲሄድ ሰርቶ ባለፈበት ቦታ መመዘኛ ልኬት ሆኖ ይቀራል። ከሚድያው ውጪ በቅርበት ለማየት አጋጣሚውን ስላገኘሁት ስለ ፈይሰል አሚን ነው ያወራኋችሁ። እነሆ ድምፁን አጥፍቶ ሲተጋ ነበር፣ አሁን ደግሞ በአዲስ ነገር #ሊቀ_ቀንበር ብሎ ተከስቷል። ግንቦት 24 እለተ ቅዳሜ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ብስራተ ገብርኤል በሚገኘው አዶት ሲኒማ ዝግጅቱን ተጋብዛችኋል። ፕሮግራማችሁን እያስተካከላችሁ ወገን።
7685Loading...
34
« ኡራዝ ቪ» [አብዱልሀኪም ሰፋ] (ከረፈደ ድንገት) : « የተረኩን ሁሉ አልገባናቸውም። የተመሰጣጠርናቸው ሁሉም ምቾት አልሰጡንም። ይገባኛል ዓለም ሰዎች አሏትና ደስታም ስቃይ አላት። ይገባኛል በፍቅር የመጣ ኅጥዕ ሲቆርጥ ቀስ ብሎ ነው። እነዚህን ድሮ የሚያውቃቸው ሸይጧን አሁን የገጠማቸውን ተመለከተና ተፀፀተ መሰለኝ። ግን ምነው ትዕዛዙን ሳይጥሱ ፈፅመው አስደስተውት እንዳልነበር አሁን ለምን ከዳቸው? ድሮም ሸይጧን የሚበልጠውን አይወድም! » የማሰላሰል ነፃተነቷን ተጠቅማ ሩቅ ትሰደዳለች። ወደ ማንም፣ ወደ ምንም፣ ምንም ሆና ምንም ላታገኝ ልትመነምን። ★……………★……………★ «… መግቢያ በቅድሚያ ይህን ምንም ካለማወቅ ወደ ማወቅ ላሸጋገረኝ ጌታዬ ምስጋና ይገባው። ብዙ የማውቅ አልነበርኩም፣ አሳወቀኝ። ብዙ ወንጀሎችን የምሰራ ነበርኩ፣ እዝነቱን አጎናፀፈኝ። ብቸኛ ነበርኩ፣ እጅግ ውድ እና ደስ የምትል ጓደኛ ሰጠኝ። በእውነቱ ለዚህ ሁሉ ነገር እጅግ በጣም አመስጋኝ ነኝ። ከልጅነቴ ጀምሮ አንድ ማሳካት የምፈልገው፣ እራሴን ማየት የምፈልገው ቦታ ነበር። ይህ ህልሜ መና ሆኖ እንዳይቀር ጊዝሊ ወደ ሀይወቴ ገባች። ከዛ በኋላ የተቀረው እንግዲህ ታሪክ ነው። ጊዝሊ እወድሻለሁ ከማለት ውጪ አንቺን የምገልፅበት ምንም ቃል የለኝም። በብዙ ነገር ከጎኔ በመሆን ስታግዙኝ የነበራችሁ ሁሉ ውለታችሁን ለመክፈል ያብቃኝ። ሰዎች ሲቆነጁ ህይወት ቆንጆ ናት። እናንተ ውብ ቆንጆዎች እወዳችኋለሁ። ማንኛውም ሀሳብ አስተያየታችሁን ለመቀበል ሁሌም ዝግጁ ነኝ። አመሰግናለሁ። ©ቪደን ሎኩዋቼ « ስለ እኔ » ……ገፅ 1…… «ጊዜ በቀሉ ከባድ ነው። ጊዜ ምስጢር ጠባቂ አይደለም። የራሱ ጊዜ ላይ የደበቀውን ምስጢር መቼ እንደሚያወጣው አይታወቅም። ምናልባት እኔም ይገለጥብኝ ይሆናል። ስሜን አንዳንዴ እረሳዋለሁ። ስም አልባ፣ ውል አልባ መሆን ያምረኛል። ግን ልረሳው አልችልም አንዴ ኢልሀም ተብያለሁ። » እሷ ገና በማለዳው እስከ እርጅና ዘመኗ ድረስ የተኛች ነች። እሷ ሁለት ቋንቋ ያላት፣ አንዱን ቋንቋዋ እራሷ ብቻ የምትናገረው ለሰሚዋ ግር የሚል ነው። …» ኢልሀም ማነች? እቺ ጉደኛ ደግሞ ከየት አመጣችው ይህን ስም? «… « መሄድ ፈልገን መንገዱ ላይ የምናገኛቸው ሰዎች ሆኑ። ጉዟችን ከበደ። ወደ ኋላ መመለስ ፈለግን። እንባና ትዝታ አገኘን። ቢያንስ አዳዲስ ሰዎች የሉም። የምናውቀውን ህመም መቻል አይከብደንም! » « ታውቃለህ ስታለቅስ ብታማርርም ተስፋ ታደርጋለህ። ስትስቅ ግን ባታማርርም ተስፋ ማድረግን ትረሳለህ። » « ሰው ግን እንዴት ሞት ይርሳኝ ብሎ እራሱን ይረግማል? ይቺ ዓለም መለያየትና ሞት ባይኖር ኖሮ እኮ እጅጉን ታስጠላ ነበር።» « ለነፍሳቸው ነብይም ጌታም ሆኑ! አሁን እኛን ጀነት ነው ወይስ ጀሀነም የሚዶሉን? » …» " ምን? ማ… ማለት? " ንግግሩ በትውስታዋ አቃጨለ። ልቧ መንጎዳጎድ ጀመረ። ጋደም ካለችበት ይበልጥ ተስተካከለች። አቅሏ መላ ሰውነቷን በግርምት አነቃቃው። ሊገለጥላት ገለጠች። ……………★…………… ……ገፅ 2…… «… « ለምንድን ነው ግን የኔን ታሪክ ለሌላ ሰው ለመንገር የፈለግከው? » « ባንቺ ውስጥ እራሳቸውን የሚያገኙ ብዙ ሰዎች አሉ። » « ከኔ ምን ይገኛል ብለህ ነው? እኔኮ ሰው ሆኜ እንኳ ለሰው ባዳ ነኝ። አሁን በኔ ውስጥ ማንም እራሱን ቢያገኝ ባያገኝ እኔን ምን አገባኝ? አታድክመኝ ባክህ አንተ ብቻ ካወቅከው ይበቃኛል። » « ግን አይገርምም መቼም እኮ ጓደኛሞች እንሆናለን ብዬ በህልሜም በውኔም አስቤም አላውቅም ነበር። » « እንዴ እኔስ ብትል የሆነ ጢባራም ነበር የምትመስለኝ! » « የምር እንደዛ በተዓምር ከአደጋ ተርፌ ከነጋሼ ጋር ልትጠይቁን ስትመጡ አላመንኩም ነበር። አሳዘንኩሽ መሰለኝ ፊትሽ ቀልቶ ነበር። » « ባክህ እንዴት ትተርፋለህ ብዬ ተናድጄ ነው።» « ምን ታረጊዋለሽ መጥፎ ሰው እኮ ይቆያል። » « ማለት ቀድመሺኝ ነው የምትሞቺው እያለከኝ ነው? » « ኧረ ባክሽ እራስሽን በደግ አይበረክትም ሒሳብ ነው እንዴ የምታዪው? » ሳቅ እና ፈገግታቸው ያሸንፋል። ተፈቃቅደው ተሸካክመዋል። ሳይማማሉ ተመሳጥረዋል። ልባቸው በአንደበታቸው በኩል ሲያወጋ አይደነቃቀፍም። ፍርሀትም አይሰማውም። ልብ ፍርሀት ካልተሰማው አይጠነቀቅም። ልብ ስደተኛ ነው። በስደት ጉዞው ውስጥ ትንሽ ነፍስ የሚዘራበት ነገር የሚያገኝ በመሰለው ቦታ ያርፋል። …» ★……………★……………★ « ይህን ያህል እሱን መታገስ እንዴት ቻልክበት? » « ትንፋሽህ ከብዶህ ያውቃል? » « ገባኝ በቃ! » « የማይከብድህ ሰው አለህ? » « አሁን እንኳ መታገስን ለምጃለሁ። መርሳት አይደለም ግን መላመድ ነገር። » « የሆነማ የሚከነክንህ ነገር ይኖራል። እስከማጣ የማልረዳ የነበርኩ መሆኔ ያነደኛል። ይልቅ ምን እያሰብክ ነው። » « ትንሽ ሀሴት ስለማዋጣት ነው አሁን እሳቤዬ። » « ለልቧ የሚሆን ነው? » « ለልቤም! » « ሸክምህን ማቅለል ትፈልጋለህ? » « አትታመም የውስጥህ ይበቃሀል! » « ማወቅ በእርግጥ ክፍያ አለው። » « በጥልቀት ለተረዱት ነዋ። » « ቆይ ግን ስንት እድሜ ይበቃሀል? » « ማን ያውቃል ይሄ ሁሉ ውብ እድሜዬ ይሆናል። » « እንዳልክ እንግዲህ በል ልሂድ! » « እየተሰናበትከኝ ነው? » « በዱዓ(ፀሎት) ተከተለኝ። » « ከሱ ውጪ ምንም አልቀረኝ! » ተዋውቀው ተሸካክመዋል። ከአደብ ጋር ተመሰጣጥረዋል። እየተሞካከሩ ዘልቀዋል። ሀሊም እና ኢዝሀር። አቅላቸውን ይጠቀሙ ዘንድ የሚቀላቸው አይቀርብላቸውም። በእርግጥም የአዕምሮ ባቤቶች ናቸውና እስካልሰነፉ የማወቅ ጥረታቸው ይቀጥላል! : @Venuee13 @Venuee13
79514Loading...
35
ይህንን ቻሌንጅ ተቀላቀሉ‼ ================== ✍ ይህንን ባለ 15 ገፅ የመንግስትንና የኃይማኖቶችን ግንኙነት በተመለከተ በዝርዝር ያብራራል የተባለለትን አዲሱን ረቂቅ አዋጅ ሶፍት ኮፒ በስልካችሁ ላይ ላለ ሰው ሁሉ፣ በምታገኙት ግሩፕና ቻነል እንዲሁም በማንኛውም ገፅ ላይ በማሰራጨት መረጃው በእያንዳንዱ ሙስሊም እጅ ላይ ደርሶ እንዲያነበው እናድርግ። ለዚህ ረቂቅ አዋጅ ግብዓት ይሆን ዘንድ የቀረበውን ባለ 164 ገፅ ጥናት ማንበብ ለሚፈልግም ሶፍት ኮፒው በዚህ ሊንክ ይገኛል። https://t.me/MuradTadesse/35708 * ሰው ጽሑፉን ዝም ብሎ ቢያነበውም ከላይ ሲመለከታቸው አንቀፆቹ ጤነኛ ሊመስሉት ስለሚችሉ፤ ፍንጭ ይሰጠው ዘንድ ረቂቅ አዋጁ ከኛ ከሙስሊሞች ጋር የሚያጋጩትንና ጥያቄ የሚያጭሩ 15+ ነጥቦች የተጠቀሱበትን ይህንን ጽሑፍም ጨምሩለት። https://t.me/MuradTadesse/35742 ይህንን የአዲሱን ረቂቅ አዋጅ PDF ለሁሉም በማሰራጨት መረጃው እንዲደርሰው እናድርግ። የላ ቻሌንጃችን ይጀመር! አብዛሃኛው ሰው ከጀርባ ምን እየተካሄደ እንዳለ መረጃው የለውም። ጭራሽ አዲስ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ራሱ እንኳን ከመረጃው የራቀው ማኅበረሰብ ሚዲያ ላይ አለን የሚለው ራሱ በበቂ ሁኔታ የሰማ አይመስለኝም። ወሬውን ቢሰማም ዶክመንቱ በተጨባጭ ያልደረሰው ብዙ ነውና ይህንን በማድረግ ግንዛቤ እንፍጠር። የፌዴራሉ መጅሊስም በዚህ ጉዳይ ተቃውሞ ያወጣውን ባለ 4 ገፅ መግለጫ አያይዘን እናሰራጨው። መግለጫው በዚህ ሊንክ ይገኛል። https://t.me/MuradTadesse/35632?single ከተቋማችንም ጎን እንቁም። የላ! ከአሁኑ ይጀመርና ያሰራጨ ሰው ለማነቃቂያ ስክሪን ሹቱን ኮመንት ላይ አስቀምጡት!
56811Loading...
36
« ኡራዝ ቪ» [አብዱልሀኪም ሰፋ] : ሁለት ወደ ኋላ: አንድ ወደፊት! : በስተመጨረሻ ነገ 7/9/2016 ይጀመራል! መልካም ንባብ ይሁንላችሁ! : @Venuee13 @Venuee13
8531Loading...
37
Media files
9967Loading...
38
~ስለተሰረቁ መስከረሞቻችን እንማልዳለን (እምላችሁ ስለዚህ ስለውዴታዬ ጉራማይሌ መፅሀፍን የሚሰጠኝ የለም?እጀግ የሚወዱት ነገር እጅ ለመግባት ለምን ይህን ያህል ዘመን እንደሚያስጠብቅ አይገባኝም) ነጃት ነኝ። @Venuee13
1 0125Loading...
39
እናንተ ምነው ቀኑ እሁድ መሆኑን ደበቃችሁ?
9681Loading...
« የኔም እንዳንቺ ነበር አውቀዋለሁ… ፈገግታሽ ሙናፊቅ ነው አያታልለኝም! ግዴለሽም አርፈሽ ወዳ’ምላክሽ ሄደሽ ሳቂ! » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
إظهار الكل...
🥰 5 3
ነገ ምሽት ላይ የአላህ ፍቃድ ከሆነ ይኖረናል። ጥያቄውን ለሚመልሱ ሶስት የቬኑ ቤተሰቦች የ #ሊቀ_ቀንበር_የወግና_የመዝናኛ_ድግስ የመግቢያ ትኬቶች ተሸላሚ ይሆናሉ! ተዘጋጁ😊😊
إظهار الكل...
11👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
የቲኬት ሽያጭ ተጀምሯል! 🎫 . በጉጉት የሚጠበቀው የሊቀ-ቀንበር የወግና የመዝናኛ ድግስ የመግቢያ ቲኬቶች ለገበያ ቀርበዋል። ቲኬቶቹ የት ይገኛሉ? 1. ቤተል ሚስተር ኮፊ፣ ፋሚሊ ታወር 4ኛ ፎቅ 2. ዋልያ ቡክስ (4 ኪሎ ኢክላስ ህንጻ) 3. the hungout cafe (አዶት ሲኒማ ህንጻ ground ላይ) . ባሉበት ኾነው ቲኬቱን በሞባይል ባንኪንግ ለመቁረጥ :- 1000413125654 Feysel በዚህ አካውንት በመቁረጥ ስክሪንሾቱን የዝግጅቱ ዕለት መግቢያ ላይ እያረጋገጡ መታደም ይችላሉ። . የቲኬቱ ዋጋ:- መደበኛ :- 200 ብር ቪ.አይ.ፒ:- 300 ብር . መሠናዶው የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 24 ብስራተ-ገብርኤል አካባቢ በሚገኘው አዶት ሲኒማ ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ይካሔዳል። . @huluezih @huluezih
إظهار الكل...
« የህይወት ትርጉም ጠፍቷችኋል? ልባችሁን የሚያስደስት ነገር አጥታችሁ ሁሉም ነገር ትርጉም አልሰጥ ብሏችኋል? እንኳን ስለ ነገ ለማለም ቀርቶ ዛሬን እንዴት መኖር እንዳለባችሁ ግራ ገብቷችኋል? የምትወዷቸውን፣ ከማንም ከምንም በላይ ለልታጧቸው የማተፈልጉ ሰዎችን ተለይታችሁ ልባችሁ አዝኗል? መከዳት፣ መውዋሸት፣ ስም መጥፋት፣ ፍቅር ማጣት ልባችሁን አቁስሎታል? ከእናንተ የበለጠ የተፈተነ እየመሰላችሁ ፈተናዎቻችሁ ከብዷችኋል? ከሰዎች ጋር መግባባት፣ መኗኗር አቅቷችኋል? ደስታን መፍራት፣ መላመድን መጠየፍ፣ በብቸኝነት ውስጥ ሽጉጥ ማለት ጀምራችኋል? ሙከራዎቻችሁ ሁሉ እየከሸፉ ዝላችኋል? ትላንታችሁ እንደ ገመድ አንገታችሁን አንቆ ዛሬን አላፈነናፍን ብሏችኋል? ልትርቋቸው፣ ልትጠሏቸው፣ በማይቻላችሁ ሰዎች ደምታችኋል? ሞት የሁሉም ነገር መፍትሄ መስሏችኋል? ተስፋ መቁረጥ ጎብኝቷችኋል? ብዙ… ብዙ ሊገለፁና ሊነገሩ የማይችሉ ህመም ስቃዮች ገጥሟችኋል? እንግዲያውስ መፍትሄው አንድ እና አንድ ብቻ ነው። ይህም አላህን ማወቅ ነው። በአላህ እምላለሁ አላህን ያወቃችሁበት መንገድ የተሳሳተ ከሆነ የትኛውም ቅንጣት ችግር እናንተ ዘንድ ከፍጥረተ ዓለሙ የገዘፈ ይሆናል። የትኛውም ስብራት፣ የትኛውም ህመም በልብ ውስጥ ፀንቶ የሚቆየው አላህን የሚያውቁትን፣ የሚያምኑትን ያህል ነው። እምነት ሲጓደል ህመም ይገዝፋል። በአላህ እምላለሁ የትኛውም ሰባኪ ስለ አላህ እዝነት ከነገራችሁ በላይ አላህ እጅጉን ሩህሩህና አዛኝ ነው። የትኛውም እውቀት አለው ብላችሁ የምትሉት ሰው ስለ አላህ መሀሪነትና አዛኝነት ከነገራችሁ በላይ አላህ አዛኝ እና መሀሪ ነው። አላህን ለማወቅና በትክክል በእርሱ ላይ ፍፁም ተወኩል ለማድረግ በምትተጉበት ጊዜ ህመማችሁ፣ ስቃይ መከራችሁ፣ ልባችሁን የሚያስጨንቀው ነገር ካልተስተካከለ ወይም መፍትሄ ካላገኘ በእርግጥ ይህን የተናገርኩትን ነገ በአላህ ፊት ጌታዬ ይህ ሰው ዋሽቶኛል ማለት ለእናንተ የተገባ ነው። እኔም ጌታዬ ስላንተ እንዲያውቁና ልባቸውን እንዲያረጋጉ ላስታውሳቸው ብቻ ሞከርኩ፣ በሙከራቸው ተሰላቹና ዋሽተሀል አሉኝ፣ ጌታዬ አንተ አዛኝ እና መሀሪ ነህ ለእኔም ለእነሱም እዘንላቸው እለዋለሁ። ይህን ስላችሁ መታበይ ወይም መኩራራት አይደለም፣ አላህን በፍፁም ልባችሁ እንደሚያሽራችሁ እንድታምኑ እና እርግጠኛ እንድትሆኑ እንጂ! የሚገለፁም፣ የማይገለፁ፣ የሚድኑም፣ ፈፅሞ የማይሽሩ የሚመስሉ ህመሞች ሁሉ መፍትሄያቸው አላህ ዘንድ ብቻና ብቻ ነው። አንዳንድ ህመሞች ከፈዋሹ ርቀው ፈውስ ሲፈልጉ ነው የማይድኑ፣ የማይሽሩ፣ የማይቻሉ የሚመስሉት። ከመፍትሄያችን ርቀን መፍትሄ እናገኛለን ብለን ባንታገል መልካም ነው። ብቻ ልቤ እንዲህ ይለኛል። » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
إظهار الكل...
13👍 5🔥 1🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
« ተሰብራ ትቀራለች ብለው ለደመደሙት ልክ እንዳትሆኚላቸው፣ ደህና ሆነሽ አሳፍርያቸው። አበቃለት ብለው ላሉት እንዳሉት እንዳትገኝላቸው፣ እራስህን ከጣልከው ካንተ በቀር ችሎ የሚያነሳው ሰው የለምና ጌታህን ይዘህ እየታገልክ አሳፍራቸው። ማህፀንሽን ያደረቁት ይመስል መሀን ለሚሉሽ አትሰበሪላቸው፣ ወደ ጌታሽ ሰርክ በዱዓ እየማለድሽ በልጅሽ ፈገግታ እንደምታሳፍርያቸው በጌታሽ ላይ ፍፁም ተወኩል ይኑርሽ! ከአወዳደቅ ሁሉ መነሳት የሌለው ከአላህ አስበልጦ ወደ ፍጡራን መዘንበል ነውና ጀሊሉን ሙጥኝ ብለን እንያዝ። ልባችሁ የምር ፈገግ የሚልበት ጊዜ አይራቅ። የምወድሽዋ አብሽሪ! የምወድህዋ አብሽሩ! ሰላም ለልባችሁ! » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
إظهار الكل...
30👍 2
« አንዳንድ ምስጋናዎችህ እርባና ቢስ የሚሆኑበት ጊዜ አለ። ልክ እንደዝያ ሰውዬ ዝሙትን ከፈፀመ በኋላ ስላረካኸኝ ተመስገን ጌታዬ እንዳለው። አንዳንድ ህልሞችህ መሳካታቸው ፋይዳ ቢስ የሚሆኑበት ጊዜ አለ። ልክ እንደዚያች ሴትዮ የልጇን ሚስት ካስገደለች በኋላ ከልጇ ጋር ለቅሶ እንደተቀመጠችው። ስጋት የመሰለህን ሁሉ ለማስወገድ ያደረግከው ሁሉም ሙከራ የሚያጠፋህ ጊዜ አለ። ልክ እንደ ፊርዓውን። በህይወት ውስጥ አንዳንድ ሙከራዎችህ፣ ምስጋናዎችህ፣ ህልሞችህ እርባና ቢስ እንዳይሆኑብህ የጌታህ አይነስህ፣ የቀደርህ አይቅለልብህ! » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
إظهار الكل...
21👏 3👌 2
« የስቃይና የመከራ ከፈን ተከፍነው አሁንም ድረስ ከከፈናቸው እያጮለቁ በሰዎች ላይ መልካሙን ለማንፀበረቅ በሚተጉት ላይ የአላህ ሰላም ይስፈን። አይታይም እንጂ የልብ መመሰቃቀል ከመጠጥ ስካር ይበልጥ ያንገዳግዳል። ሰላም ለዝምተኛ ታጋሾች፣ ሰላም ስለ ህመማቸው ሳይጮህ የህመማቸውን ሲቃ ተረድቶ የሚያዳምጣቸው ለናፈቁ። ልባቸው ታፍኖ ለመኖር በሚጣጣሩት ሁሉ ሰላም ይስፈን። » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
إظهار الكل...
23👍 5🔥 2🥰 1
« ሰላም ለእነዝያ ሰንሄድ ለሚያፈላልጉን፣ ስንጠፋ ለሚያጠያይቁን! ሰላም ለእነዝያ ልባቸው እንዳይከፋው መሻታችንን ለተቆጣጠርንላቸው፣ ሽሽታችንን ለገታንላቸው። ሰላም ለእነዝያ የፈለግነውን በቀላሉ ተረድተው ቃላት እንድናባክን ለማያደርጉን። ሰላም ለመንገዱ ሰበብ ሆኖ ለተገናኘንበት፣ የማንፍቀው ትዝታ በልባችን ላተምንበት። ሰላም ለጊዜው በትውስታ መዝገባችን የሚቀመጥ ቅርስ ላኖርንበት። ያኔ ብለን የምናወሳውን ላገኘንበት። ሰላም ለእናንተ! ሰላም ለልባችሁ! » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
إظهار الكل...
23🥰 3👍 2
« ሰላም ላንተ " ያልፋል" ማለት በቁስልህ መቀለድ ለሚመስለኝ። ላፅናናህ አቅም ለሚያንሰኝ፣ ለብርታትህ ሰበብ ለመሆን ብሞክር የምሰብርህ ለሚመስለኝ አንተ ሰላም ለልብህ! ልብህ እንደ የቲም ልጅ እንክብካቤ ለሚፈልገው ሰላም ለልብህ! » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
إظهار الكل...
29
« ሰላም ላንቺ ትዕግስትሽ በእንባ ሊገለፅ ለማይቻለው። አድገሽም እንደ ህፃን ልጅ ገላ ለስልሰሽ ለምትኖሪው ሰላም አንቺዬ! ሀዘን መከራዬን ከቻልሽው ፊት ሳቀርበው ምንም እንደሆነ ለምታሳውቂኝ አንቺ ሰላም ለውስጥሽ! ውስጥሽ ከጦርነት አውድማ በላይ ተመሰቃቅሎ ፊትሽ ፈገግ ለሚለው ሰላም ለልብሽ። » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
إظهار الكل...
32🥰 4