Addis Ababa City Manager Office
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
የመንገድ መብራቶችን በመጠገን ለምሽት እንቅስቃሴ ምቹ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የህብረተሰቡን የምሽት እንቅስቃሴ ምቹ፣ ሰላማዊና ደህንነቱ የተጠበቀ ከማድረግ አኳያ በመንገድ መብራቶች ላይ ጥገና በማድረግ በይበልጥ በሁሉም አካባቢዎች ተዳረሽ ለመሆን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ ከመንገድ እስከ ደጃፍ ያለውን የመንገድ ዳር መብራት ሽፋን ለማሳደግ የሚያስችለውን የተለያዩ አሰራሮች በመዘርጋት በሁሉም አካባቢዎች በተለያዩ ምክንያቶች አገልግሎት መስጠት ያቆሙ፣ ድንገተኛ ብልሽት ያጋጠማቸውንና መሰረተ ልማቱ ባልተሟላባቸው መንገዶች ላይ ተገቢውን ጥናትና ዕቅድ በመያዝ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
በዚህም በላንቻ ወደ አጎና ሲኒማ እና ወደ አርባ ምንጭ አሳ ቤትና አካባቢው የሚያወጣውን የውስጥ ለውስጥ የመንገድ መብራት አጋጥሞ የነበሩ የተለያዩ ብልሽቶችንና የመስመር ችግሮችን በመጠገንና አምፖሎቹን ከሶዲየም ወደ ኤል.ኢ.ዲ በመቀየር ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲውል አድርጓል፡፡
ነሃሴ 14/2017
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ባለፈው በጀት አመት መዲናችን አዲስ አበባን ፅዱ፣ምቹ፣ ዉብ እና ከአደጋ ስጋት የተጠበቀች በማድረግ ሂደት የተጠናከረ የህብረተሰብ ተሳትፎ የጎለበተበት እና የህ…
See more
የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በ65 ቀን ዕቅድ አፈጻጸምና ለአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ዕቅድ ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡
ኤጀንሲው ከ90ቀን ዕቅድ የ65ቱን ቀን ዕቅድ አፈጻጸምን የኤጀንሲው አመራሮች፣ የክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊዎችና ደጋፊ ባለሙያዎች በተገኙበት ገምግሟል።
በዚህ ወቅት በቀረበው ሪፖርት በ65ቱ ቀናት በአማካይ ከ723ሺህ በላይ የተለያዩ የህ/ሰብ ክፍሎች በሳምንታዊ የጽዳት ንቅናቄ ተሳትፈው ከ4ሺህ በላይ የሚሆኑ ብሎኮች በተለይም የውሃ/የጎርፍ መውረጃ መስመሮች፣ ቱቦዎችና ማንሆሎች ላይ ትኩረት በማድረግ የጽዳት ስራ እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በዘርፉ የስራ ዕድል ፈጠራ ስራ አፈጻጸም፣ የደረቅ ቆሻሻ ማቆያና የመልሶ መጠቀም ቦታዎች አጥር የማጠርና የመሳሰሉ በ90 ቀኑ እንዲከናወኑ የታቀዱ ተግባራት አፈጻጸም በዝርዝር በመገምገም ቀሪ ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
በሌላ በኩል በከተማችን በቀጣይ ቀናት የሚከናወኑ ታላላቅ ዓለምአቀፍ ስበሰባዎች ጋር ተያይዞ የሚካሄዱ የጽዳት ተግባራት በተቀናጀ ሁኔታ ለመምራት የተዘጋጀው ዕቅድ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬከተር ከተማችን ትላልቅ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች የማሰተናገድ አቅም በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ የመጣና የኮንፈረንስ ማዕከል እየሆነ በመሆኑ ይህንን ታሳቢ ያረገና ከማዕከል እስከ ወረዳ ያለውን መዋቅርና ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ ጽዳት ክትትል በልዩ ትኩረት መደረግ እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ዕቅዱ እስከ ክፍለ ከተማና ወረዳ ድረስ በፍጥነት በማውረድ ወደ ትግበራ እንዲገባም መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
ነሐሴ 13/2017
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
አገሩን ወዳድ እንዲሁም በኢትዮዽያ የኪነጥበብ ታሪክ ዉስጥ ጉልህ ስፍራ የነበረዉ አርቲስት ደበበ እሸቱን የአስክሬን ሽኝትና የአበባ ጉንጉን የማኖር ስነ-ስርአት በብሔራዊ ቴአትር አከናዉነናል።
አርቲስት ደበበ እሸቱ በዘመን ተሻጋሪ ስራዎቹ እና መልካም ስብእናዉ ምንጊዜም ስናወሳዉ እንኖራለን።
ለቤተሰቦቹ ፣ለወዳጆቹ፣ ለሙያ አጋሮቹ እና ለመላዉ የጥበብ ወዳጆች ሁሉ መፅናናትን እንዲሰጥ እመኛለሁ!
ፈጣሪ አምላክ ነብሱን በአጸደ ገነት ያኑርልን!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ዛሬ የ90 ቀን የሁለት ወር ሥራ አፈፃፀም ገምግመናል::
የአገልግሎት አሰጣጥ ማዘመን እና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የሚቀርቡ ግብአቶች አቅርቦትን ፣ የገበያ ማረጋጋት ፣የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፣ የፕሮጀክቶች ግንባታ፣ የገቢ አፍፃፀም እና ለኮንፍረንስ የቱሪዝምን ምቹ ሁኔታ መፍጠር በትኩረት ገምግመናል።
በዚህም የሁለቱ ወር ስራ አፍፃፀም ውጤታማ እንደነበረም በርካታ ማሳያዎች ቀርበዋል ።በተለይ ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ ምርቶች በስፋት ወደ ከተማው መግባታቸው ፣ የገቢ አፈፃፀም፣ የክረምት በጐ ፍቃድ አገልግሎት፣ የስራ እድል ፈጠራ እና የፕሮጀክቶች አፈፃፀም የተሻሉ እንደነበራቸው አይተናል።
በሌላ በኩል ደግሞ መሻሻል የሚገባቸው እና በክፍታት የታዩትን በፍጥነት እንዲታረም አቅጣጫ አስቀምጠናል።ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ የሚከናወኑት 2ተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ እንዲሁም የካሪቢያን መሪዎች ታላላቅ ስብስባ እና ጉባኤን በፍጹም ፀጥታ፣ በትሁት ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ተቀብለን ለማስተናገድ ከወትሮው የተለያ ርብርብ እንድናደርግ ፤ ሁሉም የከተማው አመራር በትኩረት እንዲሰራ ተግባብተናል::
ማህበረሰባችንም ለእንግዶቻችን ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን በተግባር እንድናስይ ስል በአክብሮት እጠይቃለሁ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኮንፍረስ ቱሪዝም ያልተነካ እምቅ ሀብታችን ነዉ ።”
በመጪዎቹ የዻጉሜ እና የመስከረም ወራት በመዲናችን አዲስ አበባ ለሚካሄዱት የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ሳምንት, ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ , ሁለተኛው የካረቢያን እና አፍሪካ መሪዎች“ካሪኮም” ጉባኤን አስመልክቶ ከሆቴል ኢንዱስትሪ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ላይ ጠቃሚ ዉይይት አድረገናል ።
የአገራት መሪዎችን ፣ የአለም አቀፍ ተቋማት ፣ የአየር ንብረት ተመራማሪዎችን ፣ አለም አቀፍ የሚዲያ አካላትን ጨምሮ ከ 25 ሺህ በላይ ታዳሚዎች የሚሳተፉበት የአየር ንብረት ጉባኤ በመዲናችን መካሄዱ ባለፉት የለዉጥ አመታት ለዘርፉ ልማት የሰጠነዉን ከፍተኛ ትኩረት ተገቢነት የሚያረጋግጡ ማሳያዎች ናቸዉ ።
መዲናችን አዲስ አበባም ከዚህ ቀደም ከተለመዱ ዉስን ጉባኤዎች በእጥፍ የላቁ አለም አቀፍ ኩነቶችን በስኬት በማስተናገድ ላይ ትገኛለች ፣ ለአብነት በተጠናቀቀዉ የበጀት አመት 150 አለም አቀፍ ኩነቶችን በከፍተኛ ስኬት ያስተናገደች ሲሆን 1.3 ሚሊዮን ያህል ጎብኚዎችንም አስተናግዳለች በዚህም 143 ቢሊዮን ብር ያህል ሀብት ወደ ኢኮኖሚያችን ገቢ ሆኗል ።
ለዚህ ከፍተኛ ዉጤት መመዝገብ አዲስ የተገነቡ ፣ የታደሱ ነባር የቱሪዝም መሰረተ ልማቶች፣ የከተማችን ነዋሪዎች የእንግዳ ተቀባይነትና ተባባሪነት ፣ የግሉ ዘርፍ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና የመንግስት የተናበበ ቅንጅት ፣ ጉልህ ድርሻ አላቸዉ።
ጉባኤዎቹ የመዲናችንን አዲስ ገፅታ ፣አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስተዋወቅ ረገድ የሚኖራቸዉ አስተዋፆ ጉልህ በመሆኑ ይህንን ግብ ለማሳካት በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜትና የላቀ የአምባሳደርነት ሚና ይበልጥ ተቀናጅተን መስራታችን እንዲቀጥል ጥሪዬ አቀርባለሁ ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የሃዘን መግለጫ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በክቡር ዶ/ር አርቲስት ደበበ እሸቱ ህልፈት ህይወት የተሰማውን ሃዘን እየገለፀ ተቋማችን የስምንት አስርተ ዓመታት የታሪክ ጉዞውን በሚዘክርበት ወቅት የተቋሙን የስራ ጉዞ ታሪክ በማውሳት እንዲሁም ታርካዊ ማስረጃዎችን በመስጠት የዕድሜ ዘመን አምባሳደር ሆነው ላበረከቱት ታሪካዊ አስተዋፅዖ ምስጋናውን ያቀርባል።
ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንመኛለን::
Condolence Message
The Addis Ababa City Administration Civil Registration and Residency Service Agency expresses its deep sorrow on the passing of the esteemed Dr. Artist Debebe Eshetu.
As our institution marks its eighty-year journey, we are reminded of his remarkable contribution as an ambassador of generations. Through his support in sharing his professional journey and providing historical testimonies, he enriched the legacy of our institution.
We extend our heartfelt gratitude for his invaluable historical contribution and lasting impact.
የመንገድ መብራቶችን ጠግኖ ወደ አገልግሎት የማስገባቱ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል
የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አግልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የኦፕሬሽንና ጥገና ዘርፍ በከተማዋ ያሉ የመንገድ መብራቶቸን ለህብረተሰቡ የምሽት እንቅስቃሴ ምቹ፣ ሰላማዊና ደህንነቱ የተጠበቀ የማድረግ ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ባለስልጣኑ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የሚገኙ የመንገድ መብረቶችን በመጠገን አገልግሎት እንዲሰጡ የማድረግ ስራውን እያከናወነ ሲሆን ባጋጠመ የተለያዩ ብልሽቶች ምክንያት አገልግሎቱ ተቋርጦ የነበረውን ከሜክሲኮ- ልደታ ፍርድ ቤት እና ልደታ ፀበል ያለውን የመንገድ መብራት በመጠገን ወደ አገልግሎት አስገብቷል፡፡
እንዲሁም ከላንቻ ወደ አርባ ምንጭ አሳ ቤት የሚያደርሰውን የውስጥ ለውስጥ የመንገድ መብራትን በመጠገን በአካባቢው ላለው የእግረኛና ተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ምቹ አድርጓል፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ በከተማዋ ያለውን የመንገድ መብራት በመጠገን ከተማችን አዲስ አበባ የቀን ብቻ ሳትሆን በምሽትም በተሻለ ሁኔታ የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለማሳደግ በጥገና ስራው በይበልጥ ተደራሽ ለመሆን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
