Addis Ababa City Manager Office
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
የከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ ቤት አመራሮች የረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ እና የቆሻሻ ማስወገጃ ስፍራ አሁናዊ የስራ እንቅስቃሴ ላይ የመስክ ምልከታ አካሄዱ::
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን ከፅ/ቤቱ አመራሮች:- ከፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲና ከኮልፌ ክ/ ከተማ አመራሮች ጋር የረጲ የቆሻሻ ኃይል ማመንጫ ጣቢያና የቆሻሻ ማስወገጃ ስፍራ አሁናዊ የስራ እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ተመልክተዋል::
የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አመራሮች የአዲስ አበባ ከተማን ፅዱ ከማድረግ አንፃር የረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያና የቆሻሻ ማስወገጃው ስፍራ ከከተማው ቆሻሻ አወጋገድና አስተዳደር ጋር ተያይዞ እያበረከቱት ባለው ፋይዳ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል::
በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ በየቀኑ ከሚመረተው ቆሻሻ ወደ 2 ሺህ 600 ቶን የሚጠጋ ቆሻሻ በኃይል ማመንጫ ጣቢያና በማስወገጃ ስፍራው እንደሚወገድ ተመልክቷል::።
የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ በከተማዋ እያደገ ከመጣው የህዝብ ቁጥር ጋር ተያይዞ የሚመረተው ቆሻሻ በየጊዜው እየጨመረ በመምጣቱ ከተማዋን አሁን በተያዘው መልኩ ፅዱና ሳቢ አድርጎ ለመቀጠል ተጨማሪ የሃይል ማመንጫ ጣቢያ ግንባታ አሊያም ተለዋጭ የቆሻሻ ማስወገጃ ስፍራ በፍጥነት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል::
ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን በበኩላቸው ከተማዋ ያለችበትን የእድገት ደረጃን የሚመጥን ዘመናዊ የማዘጋጃ ቤታዊ ቆሻሻ አወጋገድ ስርአት መገንባት አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል::
አክለውም አለምአቀፍ እውቅና ያገኘንበትን የቆሻሻ መልሶ መጠቀምን ጨምሮ ሌሎች ቆሻሻን ወደ ሃብትነት መቀየር የሚያስችሉ ዘዴዎችን ተግባራዊ በማድረግ የከተማችንን ፅዳትና ውበት በዘላቂነት ማስጠበቅ በከተማ አስተዳደሩ ትልቅ ትኩረት እንደተሰጠው አስገንዝበዋል::
በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ዳይሬክተር ከሆኑት ኦስማን ዲዮን ጋር በከተማችን በዓለም ባንክ የሚደገፉ የልማት ፕሮጀክቶች በጥራትና በፍጥነት ስለሚጠናቀቁበት እንዲሁም ቴክኒካል ድጋፎችን በዘላቂነት ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተናል።
ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን የመላው ጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ያስጎበኘናቸው ሲሆን፣ እስከ አሁን ያከናወናቸዉ የልማት ስራዎችን በመደገፍ ከጎናችን ስለቆሙ እና ወደፊትም ይበልጥ ለመደገፍ ቃል በመግባታቸዉ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተሰሩ የልማት ስራዎች በከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ተጎበኙ።
ከፍተኛ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተሠሩ የልማት ስራዎች የመንገድ አካፋይ የአረንጓዴ ልማት ፣የከተማ ግብርና እንዲሁም በከንቲባ አዳነች አቤቤ ከፍተኛ አስተባባሪነት የተገነቡ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ያደረጉ ባለ አራት ፎቆች ስድስት ህንፃዎች ግንባታን በተጨማሪም የእንጀራ ማምረቻ ፋብሪካን ጎበኝተዋል።
በጉብኝቱ ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ የገቢዎች ሚኒስተር ሚስትር፣የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ቢቂላ ኡሪሳ እና ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ተገኝተዋል።
በጉብኝቱ ተግባራቱን አስመልክተው ማብራሪያ የሠጡት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር እንዳሉት ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በብልፅግና እሳቤ የተወለደች አዲስ ክፍለ ከተማ ብትሆንም በተግባር አፈፃፀሟ ከነባር ክፍለ ከተሞች የማይተናነስ ስራ መስራት ችላለች:: እነዚህ ተግባራት ለበርካታ ሴቶችና ወጣቶች የስራ እድል የፈጠሩ፣ምቹ የስራ አካባቢንና ንፁህ ነፋሻማ አየር እንዲኖር ያደረጉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደረጉ እጅግ ሠፋፊ ስራዎች ናቸው ሲሉ ለጎብኚዎች ገልፀዋል።
ብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል የህዝብ ውይይት በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው፤
---------
በ11ዱም ክ/ተሞች እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ የውይይት መድረክ ተሳታፊ የሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች አጠቃላይ ሀገራዊ፣ ከተማዊ እና ከባቢያዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እንዲሁም የሠላም ሁኔታዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት "ህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ከነዋሪዎች ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ::
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተደደር " ሀብት የመፍጠር ጉዟችን ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች" በሚሉ አጀንዳዎች ዙሪያ ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው
በዉይይት ላይ የኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ ፣ የብልጽግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባልና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ሂክማ ሀይረዲን፣ የኦሮምያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ዶ/ር ቢቂላ ሁሬሳ እና ሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
ውይይቱ በክፍለ ከተማዉ የሚገኙ የሃይማኖት አባቶች ፣የአካባቢዉ ሽማግሌዎች እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉበት ይገኛል።
በለዉጡ አመታት በብልጽግና ፓርቲ እሰካሁን የተሰሩ የልማት ስራዎች አንዲሁም ሃብትን ከመፈጠር ረገድ ከተማዋ ያለችበት ሁኔታ እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እየተነሱበት ነዉ።
የብለልጽግና ፓርቲ በተመሳሳይ ሁኔታ በመላዉ ሃገሪቱ ዉይይት ሲያደርግ መቆየቱንም ተገልጿል።
"ህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ ውይይት በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
---------
በከተማዋ 11ዱም ክፍለ ከተሞች "ህብረብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ ውይይት መካሄድ ጀምሯል።
ህዝባዊ ውይይቱን የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች እና የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች ከከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ እየመሩት ይገኛሉ፡፡
የውይይት መድረኩ ዋና ዓላማ ህዝቡ አጠቃላይ ሀገራዊ፣ ከተማዊ እና ከባቢያዊ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እንዲሁም የሠላም ሁኔታ ላይ በበቂ ሁኔታ ከመንግስት ጋር በመወያየት የጋራ ርብርብ ለማድረግ መሆኑ ታውቋል።
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
"ህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ ውይይት በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
---------
በከተማዋ 11ዱም ክፍለ ከተሞች "ህብረብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ ውይይት መካሄድ ጀምሯል።
ህዝባዊ ውይይቱን የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች እና የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች ከከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ እየመሩት ይገኛሉ፡፡
የውይይት መድረኩ ዋና ዓላማ ህዝቡ አጠቃላይ ሀገራዊ፣ ከተማዊ እና ከባቢያዊ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እንዲሁም የሠላም ሁኔታ ላይ በበቂ ሁኔታ ከመንግስት ጋር በመወያየት የጋራ ርብርብ ለማድረግ መሆኑ ታውቋል።
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
የአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጠናቀቀ፤
-----------------
ምክር ቤቱ በዛሬው የጉባኤ ውሎ የከተማ አስተዳደሩን የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በመገምገምና የዳኞችን ሹመት በማጽደቅ ተጠናቋል።
በዚሁ መሠረት በክብርት ከንቲባ የቀረበውን የግማሽ በጀት ዓመት አፈጻጸም በማዳመጥ፣ ከከተማው ነዋሪዎች ተሣትፎና ተጠቃሚነት አንጻር የታዩ ጠንካራ አፈጻጸሞች እንዲቀጥሉ፣ ውስንነቶች ደግሞ እንዲታረሙ አቅጣጫ አስቀምጧል።
በበጀት ዓመቱ ቀሪ 6 ወራትም በተለይ ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት፣ ከመሠረተ ልማት ግንባታ፣ ከፕሮጀክቶች አፈጻጸም፣ ከሀብት አሰባሰብና አጠቃቀም እንዲሁም ከአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር አንጻር ሊያተኩሩባቸው የሚገባቸውን ጉዳዮች ተለይተው እንዲፈጸሙ መክሯል።
በመጨረሻም ምክር ቤቱ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ በፍትህ ሚኒስቴር ጥያቄ የቀረበባቸውን የምክር ቤቱ አባል የሆኑት ዶ/ር ካሣ ተሻገርን በተመለከተ የሰላም ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርት እና የውሳኔ ሐሳብ አድምጦ የዶ/ር ካሣ ተሻገርን ያለመከሰስ መብት በማንሳት ጉባዔውን አጠናቋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ2016 በጀት ዓመት ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለምክር ቤቱ ማቅረባቸውን ተከትሎ ከምክር ቤቱ የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽና ማብራርያ ከተሰጠበት በኋላ የቀረበውን ሪፖርት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎትን ለማሻሻል 200ሺ576 ነዋሪዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለመመዝገብ ታቅዶ 311ሺ 41 መፈፀም የተቻለ ሲሆን ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር 24 % ብልጫ አሳይቷል።
በተመሳሳይ 428ሺ 500 የነዋሪነት መታወቂያ ለመስጠት ታቅዶ 393ሺ 303 መስጠት የተቻለ ሲሆን ከተሰጠው የነዋሪነት መታወቂያ ውስጥ ዲጂታል መታወቂያ 366ሺ174 ወይም 93% የሚሸፍን ሲሆን በበጀት ዓመቱ ተመሳሳይ ወቅት አምና ሲፈፀም ከነበረው ስንመለከት በ 57% ብልጫ አለው። "
ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በ3ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሪፓርት ካቀረቡት
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የምክር ቤት አባል የሆኑት የዶ/ር ካሣ ተሻገር ያለመከሰስ መብት አነሳ፤
------
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
የዶ/ር ካሣ ተሻገር ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ በፍትህ ሚኒስቴር የቀረበውን ጥያቄ በተመለከተ የሰላም ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ አቅርቧል፡፡
በዚሁ መሰረት ምክር ቤቱ በጉባኤው የምክር ቤት አባል የሆኑት የዶ/ር ካሣ ተሻገርን ያለመከሰስ መብት አንስቷል፡፡
በመዲናዋ የኃይል መቆራረጥ ችግርን ለመቅረፍ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል ፡፡
የምክር ቤት አባላት የኃይል መቆራረጥን በተመለከተ ላነሱት ጥያቄ የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ገበየሁ ሊካሳ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚው በሰጡት ማብራርያ በአዲስ አበባ ከተማ በዘርፉ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ በመሆናቸው የኃይል አቅርቦት እየተሻሻለ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ በ2009/2010 ጀምሮ በ4 ምዕራፎች የተከፋፈሉፕሮጀክቶች ተቀርፀው እየተተገበሩ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
ከነዚህ መካከል ሁለት ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውን እና ሁለቱ በሂደት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የተቀሩት ሁለቱ ፕሮጀክቶቹ በ2017 በጀት ዓመት መጨረሻ ድረስ እንደሚጠናቀቁ አስታውቀዋል፡፡
በተለይም የሶስተኛው ምዕራፍ ፕሮጀክት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ጠቁመዋል፡፡
የእነዚህ ፕሮጀክቶች ግንባታ ሂደት ለመብራት መቆራረጥ አንዱ ምክንያት መሆኑን አንስተዋል፡፡
ከዚህ በፊት በተሰሩ ስራዎች አዎንታዊ ለውጦች መመዝገባቸውን በመግለፅ የኃይል መቆራረጥ ችግር በጥናት እየተመለሰ ነውም ብለዋል፡፡
አገልግሎት አሰጣጡን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ በተሰራው ስራ የገንዘብ አሰባሰብ ሂደቱን ዲጂታል ማድረግ መቻሉንም ተናግረዋል፡፡
#Addis media network
በኮልፌ ክፍለ ከተማ የተቀናጀ የፅዳት ውበትና አረንጓዴ ልማት ስራዎችን አስመልክቶ ንቅናቄ ተካሄደ።
የክፍለ ከተማው የፅዳት አስተደዳደር ፅ/ቤት፣የከተማ ውበትና አረንጎዴ ልማት ፅ/ቤት፣የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት በጋራ በመቀናጀት በክፍለ ከተማው ወረዳ 03 ረጲ ኮንዶሚኒየም አካባቢ በመገኝት የተቀናጀ የፅዳት ፣ውበትና አረንጎዴ ስራዎች የንቅናቄ መርሀ ግብር ተካሂዷል።
በንቅናቄው ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፍት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ታደለ አለሙ እንዳሉት የአካባቢው ማህበረሰብ ዘወትር ቅዳሜ አካባቢውን እንዲያፀዳ እና የተተከሉ ችግኞችን እንዲንከባከብ ገልፀው ህብረተሰቡ አካባቢውን መንደሮችን ብሎኮችን በፅዳትና ውበት ስራ ሞዴል እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በንቅናቄው የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል።
Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ ኮሙኒኬሽን
ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
ከከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጋር በተያያዘ ከንቲባ አዳነች አቤ ካቀረቡት ሪፖርት፡-
-----------
👉 የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት በግማሽ ዓመቱ 50 ሄ/ር አዳዲስ የመንገድ ፓርክ እና ቦታዎችን ለማልማት ታቅዶ 75.9 ሄ/ር (ከ100% በላይ) ማልማት ተችሏል፣
👉 የከተማ አሰተዳደሩን ውበትና አረንጓዴ ልማት ለማሳደግ 17 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ከእቅድ በላይ 17,445,385 ችግኝ መተከሉን በሪፖርቱ አንስተዋል፣
👉 የወንዝ ዳርቻ ቦታዎችን ለማጽዳትና እንክብካቤ የማድረግ ስራ እየተሰራ ሲሆን 5 ሄ/ር የላይኛው እና የታችኛው ተፋሰስ ቦታዎችን ለማልማት የታቀደ ሲሆን 7.3 ሄ/ር ለማልማት ተችሏል ብለዋል፣
👉 9.8 ኪ.ሜ የቀበና እና ባንተይቀጡ ወንዝና የወንዝ ዳርቻ ቦታዎችን እንዲለማ ለማድረግ ታቅዶ 6.9 ኪ.ሜ ቦታ ማፅዳት የድጋፍ ግንብ ስራ ተሰርቷልም ተብሏል፣
👉 ከተማዋን ውበት ደረጃ የማስጠበቅ የማስዋብና ለመዝናኛ አገልግሎት ክፍት ለማድረግ በቀሪ ጊዜያቶች ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ተገልጻል፡፡
