Addis Ababa City Manager Office
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
በመዲናችን አዲስ አበባ ተጨማሪ ከደረቅ ቆሻሻ ወደ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያ (Waste to Energy) ግንባታ ለዘመናዊ የቆሻሻ አስተዳደር እና ጽዱና ጤናማ አካባቢን ከመፍጠር አንጻር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አስታወቁ።
ከአዲስ አበባ የሚመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ አሁን በስራ ላይ ካለው ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያ ግንባታን በማፋጠን ወደ ሃይል ምንጭነት ለመቀየር የሚያስችል ስምምነት በዛሬው እለት ተፈርሟል።
ስምምነቱ የተፈፀመው በቻይናዎቹ ሻንዥን ኢነርጂ ግሩፕ እንዲሁም በቻይና ብሔራዊ ኤሌክትሪክ ኢንጅነሪንግ ድርጅት እና በጀርመኑ ኮቬናንት ኢንጅነሪንግ ድርጅት መካከል ነዉ፡፡
ስምምነቱ የተፈፀመው በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሀይ እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ነው፡፡
ኢንጅነር ወንድሙ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ለመዲናችን ፅዳት እንደተግዳሮት የሚወሰደው ደረቅ ቆሻሻ ወደ ጠቃሚ የኤሌክትሪክ ሃይል የመቀየር ተግባርን በማጠናከር በአሁኑ ወቅት ለሁለተኛው ፕሮጀክት እውንነት እየተደረገው ያለው እንቅስቃሴ ምቹ ስነ ምህዳርን ከመፍጠርም ባሻገር ለበርካታ ዜጎች የስራ እድልን በመፍጠር ለኢኮኖሚያዊ እድገቱ የሚያበረክተው ሚና የጎላ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ትላንት ማምሻውን በካዛንቺስ ኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራ ላይ ሃገር የማበልፀግ ራእያችንን በመጋራት በርካታ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶችን ፣ እረፍት አልባ የስራ መርሃግር በማሳለፍ አብረዉን ለሰሩ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች ፣አመራሮች ፣ሰራተኞች እና ተቋማትን አመስግነናል::
ከነዚህም መካከል ማሽኖቻቸውም በነጻ ለዚህ ስራ ያዋሱ ባለሃብቶችን፣ ስራ ወስደው በፍጥነትና በጥራት ፕሮጀክቶችን በጊዜ በማጠናቀቅ ያስረከቡ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎችን፣ ይህን ስራ ከጅማሮ እስከ ፍጻሜ በፍጹም ታታርነት እና ቅንነት ያስተባበሩ የከተማችን አመራሮችን፣ የግል የመንግስትና የፌደራል ተቋማትን እንዲሁም የህንጻ ባለንብረቶችን ራዕያችንን በመጋራት ሃገር በመገንባት ስራችን ላበረከቱት ጉልህ አስተዋፅዖ ሁሉ በራሴ እና በነዋሪዎቻችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ዛሬ ሚያዚያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በጉለሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ ሰባት ጌሾ ወንዝ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ18 ሰዉ የጫነ ሚኒባስ ታክሲ ዋናዉን መንገድ ስቶ ወንዝ ዉስጥ በመግባቱ በተሽከርካሪ ዉስጥ የነበሩ 18 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ጉዳት የደረሰባቸዉ ተጎጂዎች በኮሚሽኑ አምቡላንስ እና በፖሊስ አምቡላንስ ወደ አቤት ሆስፒታልና አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ ተወስደዉ ህክምና እየተደረገላቸዉ ይገኛል ።
የአደጋ ጥሪዉ ለኮሚሽን መ/ቤቱ እንደደረሰ የአምቡላንስ አገልግሎት ቡድኑ በስፍራዉ ፈጥኖ በመድረስ በተሽከርካሪዉ ዉስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች የከፋ ጉዳት ሳይደርስባቸዉ በህይወት በማዉጣትና የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና በመስጠት ወደ ሆስፒታል እንዲወሰዱ አድርጓል።
ጉዳት ከደረሰባቸዉ ተግጂዎች መካከል አንድ ነፍሰ ጡር ሴትና ወደትምህርት ቤት እየሄዱ ያሉ ተማሪዎች ይገኙበታል።
የኮሚሽኑ አመራሮችም በአቤት ሆስፒታል በመገኘት ተጎጂዎችን ጎብኝተዋል።
የአደጋዉን መንስዔ እና ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን ፖሊስ እያጠራ ይገኛል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ከከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ የኮሪደር ልማት የመንገድ መብራትና ሌሎች የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዛሬው እለት ምሽት የመስክ ምልከታ ያካሄዱት በም/ከንቲባ ማእረግ የስራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ እና በም/ ከንቲባ ማእረግ የፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀምበር እንዲሁም የከተማው የመሠረተ ልማት ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ነው።
የመስክ ምልከታውም የሲኤምሲ- ጎሮ - ቦሌ ቪአይፒ ኮሪደር፣ የመገናኛ መስቀል አደባባይ ኮሪደር፣ የአራት ኪሎ- ሽሮ ሜዳ ኮሪደር፣ እና የአንበሳ ጋራዥ- ጎሮ ኮሪደር እየተከናወነ ያለውን የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ያካተተ ነው።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በምልከታው ወቅት በኮሪደር ልማቱ የመንገድ መብራትና ሌሎች የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ስራዎች የደረሰበትን ደረጃ ከተመለከቱና በአመራሮችና በባለሙያዎች የተሰጠውን ገለፃ ካዳመጡ በሁዋላ በ2ኛው ዙር የኮሪደር ልማት እየተከናወነ ያለው የመንገድ መሠረተ ልማትና የመብራት ዝርጋታ፣ የኤሌክትሪክ፣ የቴሌኮሙዩኒኬሽን መስመር፣ የትራንሰፓርት መሰረተ ልማት እና የውሃና ፍሳሽ መስመር ዝርጋታ እንዲሁም የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎችን ተናባቢ እና ቅንጅታዊ አሰራርን ባጠናከረ መልኩ ሊጠናቀቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።
አክለውም እየተከናወኑ ያሉ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ስራዎች ደረጃቸውን በጠበቀ እና በላቀ ጥራት እንዲፈፀም አሳስበው በተለይም በመንገድ ዳር መብራት ዝርጋታዎች ላይ መጠነኛ ያልተጠናቀቁ ስራዎች ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ እና በፍጥነት እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
እንኳን ደስ አላችሁ !
እነሆ አዲሷን ካዛንችስ !
ያከናወነልን ፈጣሪ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የመዲናችን አዲስ አበባ ሁለንተናዊ ለውጥ
በኢንስፔክተር አሰፋ መዝገቡ አንደበት ሲገለፅ
ቀጣዩን ቪዲዮ ይመልከቱ👉👉
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ከተሞቻችንን የማዘመን ሰፊ ጥረት አይነተኛ ማሳያ የሆነውን በካዛንቺስ ያለዉን የኮሪደር ልማት ክፍል በይፋ መርቀናል። የተጎሳቆሉ እና በእጅጉ የተጎዱ ቤቶች እና ከባቢ መገኛ የነበረው ካዛንቺስ ዛሬ የጋራ ጥረት እና ለውጥ ሽልማታችን ሆኖ ተገኝቷል። ከዚሁ አካባቢ ተነስተው ለማኅበረሰባችን የከበረ የኑሮ ሁኔታን ለመፍጠር ያለንን ፅኑ እምነት እና ተግባር በሚያሳይ አኳኋን ለኑሮ ወደ ተሻለ ከባቢ የተዛወሩትን ነዋሪዎች ከጥቂት ቀናት በፊት ጎብኝተን ነበር። የተዛወሩበት ከባቢ እጅግ ምቹ መሆኑን አይተናል። ዛሬ ደግሞ የተነሱበትን ሰፈር ድንቅ የኮሪደር ልማት ሥራ መርቀናል።
በአስደናቂ አጭር ጊዜ የተጠናቀቀው የካዛንቺስ ለውጥ ለዘመነ ከተማ ልማት ሥራችን ለአረንጓዴ፣ ንፁህ እና ዘመናዊ የከተማ ማዕከላት ያለንን ርዕይ ግዘፍ ነስቶ በማሳየት መሠረት የሚጥል ነው። በዚህ ግዝፈት የሚከወኑ ሥራዎች ሰፋ ያለ ጥረት ይሻሉ። ጊዜያዊ ምቾት የሚነሱ ፈተናዎችንም ሊያስከትሉ ይችላሉ። ነገር ግን ለታላቁ የሀገር ጥቅም የሚከፈሉ አስፈላጊ መስዋዕትነቶች ናቸው። ይኽ የእድገት መንገድ መቀጠል ያለበት ነው። የታደሰ ተስፋ ይሰጣልና። በተለይ ለልጆቻችን ነገ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
