ar
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
photo content
+7

ከብክለት ወደ ዉበት!! ግንባታዉ እየተፋጠነ ያለዉ ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ ፓርክ 21.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 650 ሄክታር የሚሸፍን የሸገር ወንዝ ዳርቻ ልማት ። የረዳን ፈጣሪ ይመስገን ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content

photo content
+4

ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የምናደርገውን ውይይት በመቀጠል ዛሬ ከጤና ባለሞያዎች ጋር ውይይት አድርገናል። እድሎችን እና በጎ ርምጃዎችን ብሎም ክፍተቶችን እና ተግዳሮቶችን ዳሰናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

photo content
+9

"ለ90 ቀናት እቅድ ስኬታማ ተፈፃሚነት የህብረተሰቡ ተሳትፎና የአመራር ቁርጠኝነት ወሳኝ ናቸው"- -በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ "ለ90 ቀናት እቅድ ስኬታማ ተፈፃሚነት የህብረተሰቡ ተሳትፎና የአመራር ቁርጠኝነት ወሳኝ ናቸው" ሲሉ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናገሩ። በዛሬው እለት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የ90 ቀናት እቅድ ላይ ውይይት አካሂደዋል:: ኢንጂነር ወንድሙ በውይይት ወቅት እንዳሉት የተለያዩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡና የከተማችን ገፅታ የቀየሩ ስራዎች እውን የሆኑት በህዝቡ ተሳትፎና በአመራሩ ቁርጠኝነት ነው አሁን የተጀመሩ ስራዎም በባህሪያቸው ከህዝብ ጋር ተቀራርበን የምንሰራቸው ናቸው ያሉት ኢንጂነሩ ስራዎቻችን ብሎክን መሰረት በማድረግና ህዝቡን በስፋት የሚያሳትፉ መሆን ይገባቸዋል ይህን ማረጋገጥና በ7/24 ቆራጥ የስራ ባህል መምራትና በአጭር ጊዜ ውጤት ማምጣት ደግሞ ከአመራሩ ይጠበቃል ብለዋል ከዚህም ባለፈ በቅንጅት መስራትና ለየት ያለ የሰዓት አጠቃቀም ዝይቤን ልንከተል ይገባል ብለዋል የክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ በበኩላቸው እቅዱን ተግባራዊ ማድረግ ቀድሞ መጀመሩንና በተያዘው ግለት ልቀጥል ይገባል ብለዋል:: በተገቢው ስራ ክፍፍልና በጥብቅ ድጋፍና ክትትል እንደሚመራም አረጋግጠዋል:: በመድረኩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱን ጨምሮ የ13 ወረዳ የ6ቱ ግብረሀይል ተሳትፈዋል። Lafto Communication- ላፍቶ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+4

በውስጥ አቅም የተሸከርካሪ ስምሪት እና ደህንነት መቆጣጠሪያ ሲስተም ማልማት መቻሉ ተገለፀ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አዲስ የመኪና ስምሪት እና የተሸከርካሪ መቆጣጠሪያ ሲስተም (Vehicle Management System) ማልማት መቻሉ አስታወቀ፡፡ ሶፍትዌሩን በራስ አቅም የኤጀንሲው የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት የሶፍት ዌር ጥገና ባለሙያ በሆኑት አቶ ጥላሁን አናጋው የለማ ሲሆን ሲስተሙ የሰራተኛ መለያ ቁጥር እና ኢሜል እና ሌሎች መረጃዎችን የያዘ መሆኑን በማንሳት የሚወጡ እና የሚገቡ መኪናዎች መቆጣጠሪያ ያለው እንዲሁም ለአገልግሎት አሰጣጥ ፈጣን፣ጊዜ እና ጉልበት ቆጣቢ ወደ ሆነ የሲስተም ስርዓት የተቀየረ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አቶ ጥላሁን የለማው ቴክኖሎጂ የወረቀት ስራን በማስቀረት፣በየትኛውም ቦታ በመሆን ተሸከርካሪ ለመጠየቅ፣በቀላሉ ሪፖርት ለማውጣት፣የተሽከርካሪ አሁናዊ መረጃ ለማወቅ እንዲሁም ጊዜን ለመቆጠብ የሚያግዝ መሆኑን ባለሙያው ተናግረዋል፡፡ ባለሙያው አክለውም ዲጂታል ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት ለመስጠት በባለቤትነት መስራት እና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ሀገራችንን ከፍ ልናደርጋ ይገባል ብለዋል፡። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+3

photo content
+9

መዲናችን አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ጽዱ እና ውብ ለማድረግ በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች በቀጣይ 90 ቀናት በልዩ ትኩረት ተጠናክረው ይቀጥላሉ- በም/ ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር " የፍሳሽ መውረጃ መስመሮች የውሃ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም!" በሚል መሪ ቃል 7ኛ ሳምንት ከተማ አቀፍ የክረምት ጽዳት ንቅናቄ ተካሄዷል። "የፍሳሽ መውረጃ መስመሮች የውሃ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም" በሚል መሪ ሀሳብ ከተማ አቀፍ የክረምት የፅዳት ንቅናቄ የተካሄደው በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ነው። በጽዳት ንቅናቄ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ባስተላለፉት መልዕክት ከተማችን አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ ምቹ ጽዱ ውብ እንድትሆን የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት ይዞ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው በመሆኑም ነዋሪው ጽዳትን ባህል እንዲያደርግ በስፋት ግንዛቤ እየተፈጠረ ሲሆን ከዚህም ጎን ለጎን የተለያዩ ደንቦችና መመሪያዎችን ተግባራዊ እየተደረገ ነው ብለዋል። አያይዘውም ይህንን ተላልፎ የሚገኝ አካል ህጉ ተፈፃሚ እንደሚሆን ጠቅሰዉ ቆሻሻ በአግባቡ ከተወገደ የገቢ ምንጭ እንደሚሆን ከዚህም ባሻገር ትልቅ ሀብት እንደሆነ መልዕክት አስተላልፈዋል። የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው ህብረተሰቡ ጽዳትን ባህል እንዲሆን የጽዳት ንቅናቄዎች እየተደረገ ይገኛል ያሉ ሲሆን ክረምት ወቅት የውሃ ፍሰት ከፍተኛ በመሆኑ የውሃ መውረጃ ቦዮች ፀድተው ለውሃ መውረጃ ክፍት መሆን ሲገባው በግዴለሽነት ቆሻሻ መጣል ተገቢ አለመሆኑን ጠቁመው፣ ቆሻሻ በዓይነት ተለይቶ በማስወገድ መልሶ መጠቀም እንደሚገባ ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ደስታ በበኩላቸው ከሰኔ እስከ መስከረም የሚዘልቅ "ቦዮች የውሃ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም" በሚል መሪ ሀሳብ የውሃ መውረጃ ቦይን በማፅዳትና ክፍት በማደረግ የከተማ አስተዳደሩ ፅዱ፤ ማራኪና ለነዋሪዎች ምቹ ማድረግ የሁሉም ነዋሪ ሚና ሊሆን እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል። በጽዳት ንቅናቄ ላይ በመልሶ መጠቀም የተሰሩ ስራዎች አውደ ርዕይ የቀረበ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ የፀጥታ አካላት ፣ የአካባቢዉ ነዋሪዎችና የፅዳት አምባሳደሮች ተሳትፈዋል። በተያያዘም ሞዴል መንደር በዕለቱ የክብር እንግዶች የተጎበኘ ሲሆን ህብረተሰቡ የክፍለ ከተማው ብሎም የከተማው የጽዳት አምባሳደር ለመሆን በጋራ ቃል ገብቷሎ።

photo content
+6

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት እና የፓርቲ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ በጋራ በመሆን ለማህበረሰብ አንቂዎችና ለወረዳና የክ/ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል። በመድረኩ ላይ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሪት ወይንሸት አስናቀ የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎችና የማህበረሰብ አንቂዎች ወቅታዊ፣ ጥራት ያለውና ሚዛናዊ መረጃን በማስተላለፍ በህዝብና በመንግስት መካከል ድልድይ ሆነው በመስራት ከፍተኛ አስታዋጽኦ የሚያበረክቱ አካላት በመሆናቸው በዘርፉ ያላቸውን እውቀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጠናከሩ መሄድ አስፈላጊ በመሆኑ ስልጠናው መሰጠቱን ተናግረዋል። ስልጠናውን የሰጡት በአዲስ አበባ ስራ አስኪያጅ ቢሮ በም/ቢሮ ሃላፊ ደረጃ የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሃይማኖት ዘለቀ በበኩላቸው የዲጂታል ሚዲያው አሁን ላይ ሁሉንም መደበኛ ሚዲያዎች በሚያስንቅ መልኩ የተደራሽነት አድማሱን እያሰፋና ተጽዕኖ ፈጣሪነቱን እያሳደገ የመጣ ዘርፍ በመሆኑ በዘርፉ ያለውን እውቀት በአግባቡ ማስተዳደር እንደሚያስፈልግና ራስንም በዚያ ልክ ብቁ በማደረግ እውቀትን ለሀገር ግንባታ በሚጠቅም መልኩ ማዋል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በቀለች ጨርቆ ስለሚዲያ አጠቃቀም በሰጡት ሃሳብ የማህበራዊ ሚዲያ ከሌሎች ሚዲያዎች በተለዬ ሁኔታ ያለማንም ሰው ኤዲቶሪያል/ሳንሱር/ ግለሰቦች/ስልካቸውን ከኪሳቸው አውጥተው የመሰላቸውን ትክለኛም ሆነ የተዛባ መረጃ ወደ ህብረተረቡ በመንዛት ሀገርን መገንባት ወይም ማፍረስ የሚችሉበት መሳሪያ በመሆኑ በጥብቅ ዲሲፕሊን መመራት እንዳለበት ተናግረዋል። Lemi Kura Communication ለሚ ኩራ ሰኔ 13/2017 ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content

ከ1950ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ፈር ቀዳጅ በነበሩት አልቤርቶ ቫርኔሮ ህልፈት የተሰማኝን ሀዘን ለመግለጽ እፈልጋለሁ። ስራቸው የሀገራችንን የግንባታ ከባቢ እና ታሪካዊነት ያላቸው ምልክቶችን ላቅ ባለ ደረጃ የቀረፀ ነው። ከታሪካዊ ስራዎቻቸው መካከል የአፍሪካ አዳራሽ (የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን)፣ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ሂልተን ሆቴል፣ ሚሊኒየም አዳራሽ፣ የጅማ አባጅፋር አውሮፕላን ማረፊያ ማሻሻያ፣ የአብርሆት ቤተመጻሕፍት፣ የአንድነት ፓርክ እና የብሔራዊ ቤተመንግሥት እድሳት ሥራ ይገኙበታል። የሥራ ውርሳቸው በነዚህ ብሔራዊ ምልክቶች እና በሚወክሉት የእድገት ትእምርት ሲታወስ ይኖራል። ለነፍሳቸው ረፍትን፣ በረፍታቸው ላዘኑ ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

photo content
+4

ኤጀንሲው በቀጣይ 90 ቀናት በሚተገበሩ ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄደ:: ሰኔ 13/2017ዓ.ም *************** የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች፣ የኅብረተሰብ ተሳትፎ እና የበጎ ፍቃድ ሥራዎች በ90 ቀናት የማስፈፀሚያ ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ማሰፈፀሚያ ዕቅዱን ያቀረቡት የኤጀንሲው ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙላት ተገኝ እንደተናገሩት በቀጣይ 90 ቀናት በደረቅ ቆሻሻ መሠብሰብ ዘርፍ እና በመልሶ መጠቀም ዘርፍ ለ300 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር፣ 750,000 የሚሆኑ የከተማችንን ነዋሪዎች በማሳተፍ 4,350 የሚሆኑ ብሎኮችንና ተቋማትን፣ የግንባታ ተረፈ ምርቶችን፣ የወንዝ ዳርቻዎችን፣ ቦዮችን የጎርፍ ስጋትን ታሳቢ ያደረገ ልዩ የክረምት ፅዳት ንቅናቄ ማካሄድ፣ በሁሉም ክ/ከተሞች 100 ብሎኮችን በፅዳታቸው ሞዴል ማድረግ፣ 50 ሺህ የሚሆኑ ችግኞችን መትክል፣ የአቅመ ደካማ ቤቶችን ማደስ ፣ ስራዎችን በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሠረት መፈፀም፣ የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ምዕራፍ እና የ2018 በጀት ዓመት የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎችን ማከናወን ትኩረት የሚሰጣቸው ተግባራት መሆናቸውን በዝርዝር አቅርበዋል። ውይይቱን የመሩት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ደሲሳ የ90 ቀናት ዕቅዱ በሁሉም መስኮች ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ውጤታማ ተግባራትን ለማከናወን የታለመ መሆኑን ጠቁመው፣ ለዕቅዱ ተፈጻሚነት ባለድርሻ አካላትን አስተባብሮ መሥራት እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡ አክለውም ዋና ዳይሬክተሩ ዕቅዱን ስናቅድ ከመደበኛው ዕቅድ ጋር ተናባቢ መሆን እንደሚገባው ገልፀዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

photo content
+5

በአዲስ አበባ ከተማ የፋይዳ ምዝገባ ያላከናወኑ ነዋሪዎችን ተደራሽ ለማድረግ በብሎክ አደረጃጀት እንዲመራ አቅጣጫ ተሰጠ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት ጋር እያከናወነ ያለው የፋይዳ ምዝገባ ስራ ከክረምት የ90 ቀን ስራዎች ጋር በጋራ እንዲመራ በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አቅጣጫ የተሰጠ ሲሆን በዚሁ መሰረት በዛሬው ዕለት የተቋማት እቅድ ዝግጅትና አሁናዊ አፈፃፀም ገለፃ ቀርቦ ውይይት ተደርጓበታል። በውይይቱ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ክቡር ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እና የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ክብርት ወ/ሮ ዓለምፀሃይ ሽፈራው ተገኝተዋል። ለውይይት መነሻ የሚሆን ገለፃ በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ቀርቦም ውይይት የተደረገ ሲሆን በማጠቃለያ ላይ በተሰጠው አቅጣጫ እስከ ሰኔ 30 በዕቅድ የተለዩ ሴክተር ተቋማት ትኩረት ሰጥተው ለምዝገባው እንዲሰሩና በከተማው ቀሪ ያልተመዘገቡ እድሚያቸው 5 ዓመት የሞላቸው የከተማው ተማሪዎች እንዲሁም ነዋሪዎችን በመመዝገብ በግዜ ገደቡ ማጠናቀቀ እንደሚጠበቅ ክቡር እንጂነር ወንድሙ ሴታ ማሳሳቢያ ሰጥተዋል። የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ክብርት ወ/ሮ አለምፀሃይ በሰጡት መመርያ ስራው በዲሲፕሊን እንዲመራና ውጤቱ እንዲመጣ ርብርብ ማድረግ የሚጠበቅ መሆኑን አፅንዖት የሰጡ ሲሆን በፋይዳ ምዝገባ አዲስ አበባ ያሳየችውን ቀርጠኝነት ስራው እስኪጠናቀቅ የሚጠበቅ መሆኑን ተናግረዋል። በከተማው የክረምት ስራ በሁሉም ብሎኮች የፋይዳ ምዝገባ እንደ አንድ የሞዴል መስፈርትነት የተያዘ ሲሆን ቀሪ ያልተመዘገቡ ነዋሪዎች የፋይዳ ምዝገባ በብሎክ ደረጃ ተለይቶ እንደሚመራ ተነግሯል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager