Addis Ababa City Manager Office
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የቅንጅታዊ ፎረም የ1ኛ የሩብ አመት የስራ እቅድ አፈፃፀምን ግምገማ እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ፣የምክር ቤት የማዘጋጃ ቤታዊና የመሠረተ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ግዛቸዉ አይካ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ፣ የክፍለ ከተማ አመራሮች፣ ሌሎችም በቅንጅታዊ ፎረም የተካተቱ 30 የሚደርሱ የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ሃላፊዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋ/ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ መድረኩን በመክፈቻ ንግግር አስጀምረዋል።
በመድረኩ የቅንጅታዊ ፎረሙ የ2017 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት አፈፃፀም ቀርቦ በጋራ እየተገመገመ ይገኛል።
ህዳር 17/ 2017
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ከሳር ቤት አረቄ ፋብሪካ ፣ከካርል አቦ ማዞሪያ የሚሰራው ሁለተኛ ዙር የኮሪደር ልማት ስራ ያለበት ደረጃ ተገመገመ።
በመድረኩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ይመር ታደሰ፥ የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ፥የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ ስንታየሁ ደስታ እና የከተማና የልደታ ክፍለ ከተማ አመራሮች እንዱሁም የሚመለከታቸው አካላት ባሉበት ስራው እየተሰራ ያለበትን አግባብ በሰፊው ውይይት ተደርጓል።
መድረኩን የመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እንዳሉት በልደታ ክ/ከተማ እየተሰራ ያለው ስራ ጥሩ እንደሆነ ገልፀው በቀጣይ ትኩረት የሚሹ እና ወደ ተግባር ሲገባ ተግዳሮት እንዳይሆኑ በጥንቃቄና በጥራት መረጃዎችን መያዝ እና በቅድሚያ የሚሰሩትን ስራዎች አስቀድሞ መጨረስ እንደሚገባና በየጊዜው ስራው በክ/ከተማው ከፍተኛ አመራሮች ውጤት በሚያመጣ መልኩ እየተገመገመ መሄድ እንዳለበትም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
Lideta sub-city communication office
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ፒያሳ ደጃች ዉቤ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ
አራዳ ክፍለ ከተማ ደጃች ዉቤ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በቻይና ጃንጉዜ የኮንስትራክሽን ስራ ድርጅት ላይ የተከሰተው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
አደጋውን በቁጥጥር ስር ለማዋል የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች ፣ የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላትና ተሽከርካሪዎች እንዲሁም የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍ ያለ ርብርብ አድርገዋል።
የእሳት አደጋው ዛሬ ከቀኑ 9:00 አካባቢ የተነሳ መሆኑን የገለፀው የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፤ የእሳት ቃጠሎው ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቋል።
እሳቱ የተከሰተበት ቦታ አሽዋ ፣ ጠጠርና መሰል የኮንስትራክሽን ምርቶች ያሉበት ቦታ መሆኑ የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች በቀላሉ ወደ ቦታው እንዳይገቡ ምክንያት ሆኗል ተብሏል።
AMN-Addis Media Network
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የ"ህዳር ሲጸዳ" የጽዳት ንቅናቄ
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ እና የከተማችን ከፍተኛ አመራሮች በተሳተፉበት የልደታ ክ/ ከተማ የጽዳት ንቅናቄ ማእከል "ቆራሊዮ" በሚል ዜማው ኮሜዲያን ማርቆስ ለጽዳት ንቅናቄው ልዩ ድምቀት ሰጥቶት ነበር።
#ክብር # ለከተማችን የጽዳት ባለሙያዎቻችን!
ኤጀንሲው በቀጣይ 90 ቀናት ከ1800 በላይ በዘርፉ የስራ ዕድል ለመፍጠር አቅጃለሁ አለ።
የአዲሰ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በበጀት ዓመቱ ቀጣይ 90 ቀናት በመልሶ መጠቀም እና ደረቅ ቆሻሻን ቤት ለቤት በመሰብሰብ ዘርፍ ለስራ አጥ ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር አቅዶ እየሰራ እንደሆነ ተገልጿል።
ማሰፈፀሚያ ዕቅዱን ያቀረቡት በኤጀንሲው የደረቅ ቆሻሻ አገልገሎት አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግርማ ሀይሉ እንደተናገሩት በደረቅ ቆሻሻ መሠብሰብ ዘርፍ ለ1182 እና ደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ዑደት ማድረግ ዘርፍ ላይ ደግሞ ለ700 ዜጎች በቀጣይ ሶስት ወራት ወደ ስራ ለማስገባት በሂደት ላይ አንዳለ ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት ደረቅ ቆሻሻን ማዕከል አድርጎ እየሰራ የሚገኘው የስራ ዕድል ፈጠራ በከተማዋ እየተስተዋለ ያለውን የስራ ማጣት ችግር ያቃልላል ተብሏል፡፡
የስራ ዕድል ፈጠራው የደረቅ ቆሻሻ መሰብሰብ፣ የፕላስቲክ እና የወረቀት መልሶ መጠቀም እና ሌሎችን የስራ ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በአሁኑ ወቅት ደረቅ ቆሻሻን ማዕከል አድርጎ እየሰራ የሚገኘው የስራ ዕድል ፈጠራ በከተማዋ እየተስተዋለ ያለውን የስራ ማጣት ችግር ያቃልላል ተብሏል፡፡
የስራ ዕድል ፈጠራው የደረቅ ቆሻሻ መሰብሰብ፣ የፕላስቲክ እና የወረቀት መልሶ መጠቀም እና ሌሎችን የስራ ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በውይይቱ ላይም የመስሪያ ቦታ ችግር እና የስራ ቅጥር መዘግየት ጋር ተያይዞ የሚገጥሙ ዋና ዋና ችግሮች አነደሚሆኑ ተጠቁሟል።
ከስራ ዕድል ማስፈፀሚያ ዕቅዱ ጎን ለጎን ባለፈው ሳምንት ህደርን በፅዳት በሚል መሪ ቃል ለ7 ተከታታይ ቀናት የተካሄደውን ከተማ አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ አፈፃፀምን ገምግመዋል።
በርካታ የፅዳት ንቅናቄ ስራዎች እንደ ከተማ ተካሂዷል ህዳርን በፅዳት ሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው ግን በጣም ጥሩ አፈፃፀም እንደነበር ተገምግሟል።
ይህም ንቅናቄ በቀጣይ ግለቱን በጠበቀ መልኩ መቀጠል አንዳለበት ተመላክቷል።
በውይይቱ ላይም የኤጀንሲው አመራሮችን ጨምሮ የክ/ከተማ ፅዳት አሰተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው የኤጀንሲው ዳይሬክቶሬቶች መታደማቸውን ከኤጀንሲው ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በአራዳ ክፍለ ከተማ ደጃች ዉቤ ሰፈር በቻይና ጃንጉዜ የኮንስትራክሽን ስራ ድርጅት ላይ ያጋጠመውን የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ለማዋል የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ርብርብ እያደረጉ ነዉ።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት በአደጋ ጊዜ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚቻልባት ምቹና ዘመናዊ ከተማ እየፈጠረ ነው
የኮሪደር ልማቱ በአደጋ ጊዜ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚቻልባት ምቹና ዘመናዊ ከተማ እየፈጠረ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ።
የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማእከል የሆነችው አዲስ አበባ የቤቶቿ ግንባታና መሰረተ ልማቷ ዘመናዊ አሰራርን በተከተለ መልኩ ሳይሻሻል ቆይቷል።
በዚህም ምክንያት በብዙ አካባቢዎች በተለይም ለእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት አዳጋች ማድረጉ በተደጋጋሚ ሲነገር ቆይቷል።
ከመጋቢት 2016 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የኮሪደር ልማት ግን ከተማዋን ውብና ዘመናዊ ከማድረግም ባለፈ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው ሆኗል።
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፤ የኮሪደር ልማቱ የመዲናዋን ፕላን ዘመናዊነት በማላበስ የአደጋ ተጋላጭነትንም መቀነስ ያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል።
የኮሪደር ልማቱ የትራፊክ መጨናነቅን በመፍታት የተሳለጠ እንቅስቃሴ እንዲኖርና በአደጋ ጊዜ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ምቹና ዘመናዊ ከተማ እየፈጠረ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
በመዲናዋ የአሰራር ማሻሻያ ሪፈርም እየተካሄደባቸው ካሉ ተቋማት መካከል የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አንዱ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የተቋሙ ቅርንጫፎች አሁን ካለበት 11 ወደ 26 ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው በአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትም በስፋት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛው፤ ከተማዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ ከሚሰሩ ስራዎች መካከል የአደጋ ተጋላጭነትን መቀነስ አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።
ለዚህም የኮሪደር ልማቱ በተለይም የእሳት፣ የጎርፍና ሌሎችም ድንገተኛ አደጋዎችን ለመቀነስ፣ ለመከላከል እንዲሁም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ሁነኛ መፍትሄ መሆኑን ነው የተናገሩት።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለአደጋ መከላከልና ምላሽ የመስጠት ስራ ዘመናዊ የአሰራር ስርአት መዘርጋቱንም አንስተዋል።
Ethiopian News Agency
ህዳር 15/ 2017 አ.ም
እንኳን ለብልፅግና ፓርቲ ምስረታ 5 ኛ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን፡፡
ያለፉት የለዉጥ አመታት በርካታ ድሎችን ያስመዘገብንበትና ተቃራኒ ኹነቶችንም ያስተናገድንበት ጊዜ ነበር ።
ከመከፋፈል እና አግላይ የፖለቲካ እሳቤ ወጥተን አካታች፣ ሚዛናዊ እና ህብረ ብሄራዊ አንድነት የሚያፀና ሃገራዊ ፓርቲ በመመስረት ለኢትዮጵያ ብልጽግና ራዕይ ሰንቀን መትጋት የጀመርንበት አዲስ ምዕራፍ ነዉ፡፡
የለውጡ መንገድ አልጋ ባልጋ ሳይሆን ኢትዮጵያን ለዘመናት ቀስፈው ከያዟት ጐታች አስተሳሰቦች እና ተግባራት ለማላቀቅ ከፍተኛ ትግል እና ውጣ ውረድ በፅናት ማለፍን የሚጠይቅ ነበር፡፡
ለማልማት ስንተጋ ለማጥፋት ከሚታገሉ ጋር፣ ለመገንባት ስንሯሯጥ ለማፍረስ ከሚጥሩ አካላትጋር ተፋልመናል ፡፡ "እውነት ከውሸት ዘመን ጋር፣ ፅኑ እምነት ከጥርጣሬ እና ክህደት ጋር፣ መልካምነት ደግሞ ከክፋት ጋር የተፋለሙበት እና የታገሉበት ምእራፍን በማለፍ እውነት ይዘን፣ በጎነት እየተገበርን በፅናት እያሸነፍን የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀበትን አመታት አሳልፈናል፡፡
በአምስቱ አስቸጋሪ የጉዞ መንገድ የድል ፍሬዎች ውስጥ የሚጠቀሱ አንኳር ስኬቶች እያስመዘገብን ”ቃልን በተግባር” በመፈፀም የፓርቲችንን አላማ አሳይተናል። ለመጪው ትውልድ የምናወርሰው እዳን ሳይሆን የበለፀገች እና የለማች ሀገር እና ከተማን እንደሚሆን ፅኑ እምነት አለን፡፡
የኢትዮጰያን ብልፅግና መረጋገጥ አይቀሬነት በመገንዘብ በውጣ ዉረዱ ጉዞ አብራችሁን የቆማችሁ ፣ ስንተጋ ከእኛ ጋር የተጋችሁ፣ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ጥሪ ስናቀርብ በጐ ምላሽ የሰጣችሁን ነዋሪዎቻችንን በሙሉ በራሴ እና በፓርቲያችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ብልፅግና - የአሁኑም የመጪውም ትውልድ ፓርቲ !
ኢትዮጵያችን የበርካታ ብሄር ብሄረሰቦች ማንነት ፣ ቋንቋ ፣ እምነት ፣ ባህል ህብርም መገኛም ናት፤ እጅግ በጣም ሰፊ ብዝሃነት ያለባት ድንቅ ሀገር ናት።
የብዝሃነት ፀጋዋ ነገ ሁለንተናዊ ብልፅግና የተረጋገጠባት ሀገር ለመገንባት የሚያስጎመጅ ሰናይ ዕድል እንጂ፣ ስጋቷ ሊሆን በፍፁም አይገባም።
መሪ ፓርቲያችን ብልፅግናም ይህንን መልካም ዕድል በመጠቀም በአንድ በኩል ብዝሃነታችንን በአግባቡ የሚያስተናግድበትን ፣በሌላ በኩል ደግሞ ሀገራዊ አንድነታችንን የሚያረጋግጥበትን እውነተኛ ህብረ ብሄራዊ ፌደራላዊ ስርዓት ለመገንባት እየሰራ ይገኛል።
ይህ ደግሞ ዛሬን ለማለፍ ብቻ ሳይሆን ነገንም ሰላምና አንድነት፣ እኩልነትና ብልፅግና ሰምረውልን እንደ አገርና ህዝብ ለመኖር ያስችለናል፤ ለዚህም ነው ብልፅግና - የአሁኑም የመጪውም ትውልድ ፓርቲ ነው የምንለው።
