ar
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

الذهاب إلى القناة على Telegram

إظهار المزيد
1 474
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-2130 أيام
أرشيف المشاركات
photo content
+3

ከፍተኛ የኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመሮች በተዘረጉበት አካባቢ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ***************** ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች የተዘረጉባቸው አካባቢዎች ላይ በቅርበት የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳሰበ፡፡ የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ከኢቢሲ ዶትስትሪም ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመሮች ክረምቱን ተከትሎ አደጋ ሊያስከትሉ ስለሚችሉ በቅርበት የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡ በዓመት ሁለት ግዜ በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ፍተሻ እንደሚደረግ የገለጹት አቶ ሞገስ፤ የላሉ ወይም የተበጠሱ መስመሮች ካሉ ጥገና ይደረጋል ብለዋል፡፡ ከፍተኛ ኃይል አስተላላፊ የኤሌክትሪክ መስመሮች ባሉባቸው ስፍራዎች ዛፍ የሚተክሉ፣ የግብርና ስራ የሚያከናውኑ፣ እንስሳትን የሚያግዱ ሰዎች ስለመኖራቸው የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ ክረምቱን ተከትሎ መሬቱ እርጥበት አዘል ስለሚሆን ሊደርሱ ከሚችሉ አደጋዎች ራስን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡ ከፍተኛ የኃይል መስመሮች ያለባቸው አካባቢዎች በማታው ክፍለ ጊዜ ከፍተኛ ኃይል ስለሚተላለፍባቸው የሚረብሹ ድምጾች እንደሚኖሩም ነው ያነሱት፡፡ ነዋሪዎች ከፍተኛ የኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመሮች ከሚገኙባቸው ቦታዎች 10 ሜትር እና ከዚያ በላይ እንዲርቁ የሚደረገው በመስመሮቹ ላይ የሚተላለፈው የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጨው ከፍተኛ የራዲዮ ሞገድ በጤና ላይ የሚያስከትለው ጉዳት በመኖሩም ጭምር ነው ብለዋል አቶ ሞገስ ፡፡ በከፍተኛ ኃይል አስተላላፊ መስመሮች ስር ረዥም ዛፍ ወይም እጽዋት ተክለው የሚያሳድጉ ሰዎች መስመሩን እንዳይነካው ጥንቃቄ በማድረግ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ መቀነስ እንደሚችሉም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

photo content
+6

photo content
+1

photo content

በ2018 በጀት አመት የሚጠኑ ጥናቶች ላይ ከተጠሪ ተቋማት ጋር የዉይይት መድረክ ተካሄደ። የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን በውጤታማነት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግና የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የሚረዱ በቀጣይ በ2018 በጀት አመት የሚጠኑ ጥናቶች ላይ ከተጠሪ ተቋማት ማለትም ከሲቪል ምዝገባና ከነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ፣ከፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ከእሳትና ከአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን እንዲሁም ከአዲስ አበባ የመንገድ መብራት አስተዳደር ባለስልጣን አካላት ጋር በዛሬዉ እለት የዉይይት መድረክ አካሂዷል። በዚሁ መድረክ በቀጣይ በ2018 በጀት አመት በዉስጥና አቅም እንዲሁም በዉጭ አቅም የሚጠኑ ጥናቶችን የያዘ ሰነድ ቀርቦ የጋራ ዉይይት ተደርጎበታል። በመድረኩም በቢሮ ሃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ እና የጥናትና ትግበራ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደስ እንደገለፁት በጽ/ቤቱ በቀጣይ በ2018 በጀት አመት የሚጠኑ ጥናቶች የተቋሞቻችን የአገልግሎት አሰጣጥን ፈጣን፣ ቀልጣፋና የዘመነ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው መሆኑን ጠቅሰዉ በበጀት አመቱ 5 ጥናቶች እንደሚጠኑ እና 2 ጥናቶች በዉጭ አቅም የተቀሩት 3 ጥናቶች በዉስጥ አቅም ለማስጠናት መታቀዱን ገልፀዋል። አክለዉም በተጠሪ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማዘመንና የሚሰጡ አገልግሎቶችን የተገልጋዩን የእርካታ መጠን ከፍ ለማድረግ እንዲሁም በቀጣይ የሚጠኑ ጥናቶችን ውጤታማ ለማድረግ ጥናቶችን በምርምር ላይ ተመስርቶ ተግባራዊ ለማድረግ አቅምን እንዲያጎለብቱ እንዲሁም ዉጤታማ አሰራሮችን ለመዘርጋትና መፍትሄም አመላካች ጥናቶች ለማካሄድ በጋራ ተቀራርቦ መስራቱ ከፍተኛ አቅም እንደሆነም አስገንዝበዋል። የሚጠኑት ጥናቶች በተቋማቶቻችን ከህብረተሰቡ የሚኑሱ አንዳንድ የአሰራር ክፍተቶችን የሚሞሉ እና ከጥናትነት ባለፈ መፍትሄ ሰጪ እንዲሆኑ ወደ ተግባር መግባት አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀው የተነሱ ሀሳቦችን እንደግብአት በመዉሰድ በቀጣይ ሁሉም አካል በቅንጅትና በትኩረት በመስራት ወደ ተግባር መግባት ያስፈልጋል ሲሉም አመልክተዋል።

የደንብ ማስከበር ተግባራቸውን በመወጣት ላይ በነበሩ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አባላት ላይ የድብደባ ወንጀል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያጣራ መሆኑን የን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ/ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ጀሞ መስታወት ፋብሪካ አካባቢ ሲሆን ተከሳሾች ዮሀንስ ከበደ፣ ሠዒድ ሠይፉ፣ እስማኤል ሱልጣን፣ ሃይረዲን ሽፋ፣ ፈጅሩ ሱልጣን፣ ባህሩ ራህመቶ፣ ሚነወር ሀይሉ፣ ሀይልዬ ጀማልና አስማረ አለሙ የተባሉ ሲሆኑ ካልተያዙ ሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በመሆን በእግረኛ መንገድ ላይ ህገ ወጥ የጎዳና ላይ ንግድ በማከናወን ላይ ሳሉ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አባላት የሆኑት ማቱሳላ ማዶሬና አቡሽ ሽጉጤ ድርጊቱን ለመከላከል ሙከራ በሚያደርጉበት ወቅት ተጠርጣሪዎቹ አባሪ ተባባሪ በመሆን አባላቱን በድንጋይና በእርግጫ ተረባርበው የድብደባ ወንጀል መፈጸማቸውን ፖሊስ አስታውቋል። ተጠርጣሪዎቹ በወቅቱ ድርጊቱን ፈጽመው ቢሰወሩም በክ/ከተማው ፖሊስ በተደረገ ክትትል በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን ፖሊስ ገልጾ በፈጸሙት የወንጀል ድርጊትም ተገቢውን ምርመራ የማጣራትና ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረቱን መቀጠሉንም ገልጿል። በጎዳና ላይ የሚደረጉ ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች የእግረኛና የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ በማወክ ዜጎችን ለመንገድ ትራፊክ አደጋ ተጋላጭ ከማድረጉም ባሻገር ጤናማ የንግድ እንቅስቃሴን የሚጎዳ መሆኑ እየታወቀ ይህንንም ድርጊት ለመከላከል የተሠማሩ የጸጥታ አካላት ላይ ትንኮሳ መፈጸምና ለህግ ተገዢ ያለመሆን ተጠያቂነትን የሚያስከትል ድርጊት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ያሳስባል።

ዘመናዊ የከተማ ግንባታን ለማሳካት ከሚከናወኑ ትላልቅ የህንፃና የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎቻችን ጎን ለጎን ቅድሚያ የምንሰጠው የዜጎቻችንን ደህንነት የማስጠበ… See more

በነሀሴ ወር ከባድ ዝናብ እንደሚኖር ተገለፀ በነሀሴ ወር በረዶ የቀላቀለና ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢኒስቲትዩት አስታወቀ። ኢኒስቲትዩቱ እ.ኤ.አ ከኦገስት 1 እስከ 31/2025 የሚኖረውን የአየር ጠባይ ሁኔታ አስታውቋል። በነሃሴ ወር ከሚጠናከሩት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ጋር ተያይዞ በተለይም በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ ምዕራብና በምዕራብ የሃገሪቱ ቦታዎች ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ተጠቁሟል። በተጨማሪም በፀሐይ ሀይል ታግዘዉ ከሚፈጠሩ የደመና ክምችቶች በመነሳትም በረዶ የቀላቀለ እና ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል ተመላክቷል። በሌላ በኩል በአንዳንድ ቦታዎች ከሚኖረው ተደጋጋሚ የሆነ የእርጥበት መብዛት ጋር ተያይዞ በረባዳማ አካባቢዎች የውሃ በሰብል ላይ መተኛት፣ የመሬት አቀማመጡ ከፍታ ባላቸውና ተዳፋታማ በሆኑ አካባቢዎች ደግሞ የመሬት መንሸራተትና በጎርፍ መጠቃት ሊያጋጥም እንደሚችል ተገልጿል። እርጥበት በሚበዛባቸው አካባቢዎች የሰብል በሽታ እና የአረም መስፋፋት ሊከሰት ስለሚችል አርሶ አደሮችና የሚመለከታቸው አካላት ሰብሎች በጎርፍ እንዳይጠቁ እና በማሳ ላይ ውሃ እንዳይተኛ የጎርፍ መቀልበሻዎችንና ከማሳ ውሰጥ ውሃን ማስወገጃ ቦዮችን ማዘጋጀት እንደሚገባ ተጠቁሟል። የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ ተፋሰሶች ላይ ደግሞ አልፎ አልፎ በሚኖረው ተደጋጋሚ ከባድ ዝናብ ቅጽበታዊ ጎርፍ የማስከተል እድል ስለሚኖር አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ኢንስቲትዩቱ መግለፁን ኢፕድ ዘግቧል።

ከእንጦጦ እስከ አራት ኪሎ ፕላዛ የተሰራው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት

ዉብ አዲስ!! አራት ኪሎ - ሽሮ ሜዳ እስከ እንጦጦ በምሽት !

የእንጦጦ እስከ አራት ኪሎ ኮሪደር የምሽት ድባብ…

ከእንጦጦ እስከ 4 ኪሎ ፕላዛ የኮሪደር ልማት ስራ ላይ የህዝቡ፣ የመንግስት እና የግል ተቋማት ተሳትፎ እጅግ ከፍተኛ ነበር - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀንበሩ (ዶ/ር)